YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአፍሪካ ቀንድ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባባች እስከ ግንቦት ዝናብ ካልዘነበ ድርቁ እጅግ ከባድ ጉዳት እንደሚያደርስ ፋኦ ገለፀ!

ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የቤት እንስሳት መሞታቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።በድርቁ የተጎዱትን ለመደገፍ 130 ሚሊዮን ዶላር ይስፈልጋል ተብሏል።

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
አምነስቲ ህውሓት በአማራ ክልል ከተሞች በንፁሃን ዜጎች ላይ የግድያ ፣ የመድፈር እና የዘረፋ ጥቃችን ፈጽሟል አለ!

በሰሜን ኢትዮጵያ የአማራ ክልል ሁለት አካባቢዎች ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሀት) ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች ሆን ብለው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድለዋል፣ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሴቶችን እና ልጃገረዶችን በቡድን ደፍረዋል፡፡

ከተደፈሩት ሴቶች መካከል ዕድሜያቸው ገና 14 ዓመት የሆኑ ልጃገረዶች እንደሚገኙበት ተቋሙ ዛሬ ባወጣው አዲስ ሪፖርት ገልጿል፡፡ይህ ብቻ ሳይሆን የግል እና የህዝብ ንብረቶችን ዘርፈዋል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል በዘገባ ው አስታውቋል።

እ.አ.አ በ2021 በነሀሴ ወር መጨረሻ እና በመስከረም መጀመሪያ በጭና እና ቆቦ አካባቢዎች በንጹሀን ላይ ግፉ የተፈፀመው የትግራይ ሃይሎች በሐምሌ ወር አካባቢዎቹን በተቆጣጠሩ ሰሞን ነው ይላል ሪፖርቱ።

ጥቃቶቹ በጭካኔ ድርጊቶች የተሞሉ ሲሆን ፣ የግድያ ዛቻዎች እና የብሔር ተኮር ስድቦችን የጥቃቱ አካል ናቸው፡፡በቆቦ የአካባቢውሚሊሻዎች እና የታጠቁ ነዋሪዎች ያሳዩት የመከላከል ጥንካሬ ያበሳጫቸው የትግራይ ታጣቂዎች በሰላማዊው ህዝብ እልሃቸውን እየተወጡ ይመስላል።

"የትግራይ ሃይሎች ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ሊከተሏቸው የሚገቡትን መሰረታዊ የአለም አቀፍ የሰብአዊ ህግ ደንቦችን ጥሰዋል ሲሉ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ አፍሪካ፣ ቀንድ እና ታላላቅ ሀይቆች ምክትል ዳይሬክተር ሳራ ጃክሰን ተናግረዋል።

ከጁላይ 2021 ጀምሮ የትግራይ ሃይሎች በአማራ ክልል ስር በሚገኙ አካባቢዎች የጦር ወንጀል እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን የሚያሳዩ መረጃዎች እየጨመሩ መሆናቸውንም አንስተዋል ዳይሬክተሩ፡፡

‹‹አስገድዶ መድፈር ፣ ግድያ ፣ ዘረፋ እና ሆስፒታሎች ጨምሮ ተቋማትን ማቃጠል ይጨምራል” ሲሉ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ አፍሪካ፣ ቀንድ እና ታላላቅ ሀይቆች ምክትል ዳይሬክተር ሳራ ጃክሰን ጨምረው ተናግረዋል።"የህወሓት ባለስልጣናት እንዲህ አይነት ግፍ በአስቸኳይ ማስቆም እና በዚህ አይነት ወንጀል የተጠረጠረውን ሰውም ለፍርድ እንዲያቀርቡ ።" ጠይቀዋል

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ ድጋፍ የሚዉል ተጨማሪ 2 ቢሊየን ብር (39 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር) ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ድጋፉ ድርቅ በተከሰተባቸዉ የአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ እና ሶማሌ ክልሎች ጉዳት ለደረሰባቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች እርዳታ የሚውል ነዉም ተብሏል፡፡

በሶማሌ፣ ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች ሙሉ በሙሉና በከፊል በተደጋጋሚ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመዝነቡ እንደዚሁም በአማራ ክልል በነበረው ግጭት ምክንያት በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ለምግብ እህል እርዳታ መዳረጋቸው ይታወቃል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
እስረኞች እንዲለቀቁ ኢሰመኮ ጠየቀ!

የኢትዮጵያ መንግስት ካለፈዉ ጥቅምት እስከ ትናንት ፀንቶ በነበረዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት ያሰራቸዉን ተጠርጣሪዎች እንዲለቅ የሐገሪቱ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጠየቀ።የኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት የፈረጀዉ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ወደ አዲስ አበባ ተቃርቦ በነበረበት ባለፈዉ ጥቅምት 23 የተደነገገዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ትናንት ተነስቷል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጁ እንዲነሳ በድምፅ ከመወሰኑ በፊት በተደረገዉ ዉይይት የተወሰኑ የምክር ቤቱ አባላት አዋጁ እንዳይነሳ አጥብቀዉ ተከራክረዉ ነበር።መንግሥት የሚቆጣጠረዉ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በፌስ ቡክ ገፁ ባሰራጨዉ መልዕት እንዳለዉ ግን «አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን በበጎ ተመልክቶታል።»አዋጁ ባለፈዉ ከተደነገገ በኋላ ከሕወሓትና ከኦነግ ሸኔ ጋር ግንኙነት አላቸዉ ተብለዉ የተጠረጠሩ በርካታ ሰዎች ታስረዋል።ከእስረኞቹ የተወሰኑት ግን ተለቅቀዋል።

ኢሰመኮ ዛሬ ባሰራጨዉ መልዕክቱ በአዋጁ መሠረት ታስረዉ እስካሁን ያልተለቀቁ ሰዎች «በአፋጣኝ» እንዲለቀቁ አሳስቧል።ከዚሕ ቀደም የተለቀቁትም ታስረዉ ስለመቆየታቸዉ ማረጋገጪያ ሥላልተሰጣቸዉ ወደ ስራ መመለስ አልቻሉም፤ መስራት ባለመቻላቸዉም ለማሕበራዊና ኤኮኖሚያዊ ችግር መጋለጣቸዉን ኢሰመኮ «በክትትል ደርሼበታለሁ» ይላል።ለተለቀቁት ሰዎች በእስር የቆዩበትን ጊዜ የሚገልፅ ማስረጃና አስፈላጊ ሰነዶችን የመስጠቱ ሒደት እንዲፋጠን ጠይቋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ በማከናወንና አስፈላጊ የሰነድ ማሻሻያዎችን በማድረግ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያስገቡ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ!

ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ በማከናወንና አስፈላጊ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንዲያስገቡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ፡፡

ምርጫ ቦርዱ ህዳር 23 ቀን 2014 ከፓርቲዎች ጋር ባደረገው ምክክር በአዋጅ ቁጥር 1162/11 እና በመመሪያ ቁጥር 3/2011 መሠረት ከ6ኛው አገራዊ ምርጫ መጠናቀቅ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱና የሰነድ ማሻሻያ እንዲያደርጉ የተገለፀላቸው ፓርቲዎች የሚጠበቅባቸውን አጠናቀው ባለማቅረባቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተነሳ በአንድ ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያከናውኑ እና ለቦርዱ እንዲያስገቡ መወሰኑ በምክክሩ ወቅትም ለፓርቲዎች መገለጹን አስታውሷል።

በዚህም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን ተከትሎ ከስር ስማቸው የተዘረዘረ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ በማከናወን እንዲሁም አስፈላጊ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንዲያስገቡ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል።

አገራዊ ፓርቲዎችም ፥ የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ነፃነት ፓርቲ ፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ፣ ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ፣ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር፣ ብልፅግና ፓርቲ ፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ፣ ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ናቸው፡፡

በተጨማሪም ክልላዊ ፓርቲዎች ፥ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ፣ ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ፣ የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ፣ ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ኅዳሴ ፓርቲ፣ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የአፋር ሕዝቦች ፍትሐዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ፣ ቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ፣ ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲ ሉዓላዊነት፣ የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የአርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅትእና የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሆናቸውን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሀገራዊ ምክክሩ በፓርላማ በአሸባሪነት የተፈረጁ አካላትን እንደማያካትት ብልፅግና ፓርቲ ገለፀ!

በኮሚሽነሮች ምርጫ ሂደት ላይ የሚገኘው ሀገራዊ የምክክር መድረክ “በህዝብ እንደራሴዎች በኩል አሸባሪ ተብለው ከተፈረጁ አካላት ጋር መደራደር ማለት አይደለም” ሲል ዛሬ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ላይ ባሰፈረዉ ጽሁፍ አመለከተ።

በታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለአናዶሉ ኤጀንሲ እንደገለፁት “ጉዳዩ እኔ የምናገርበት ባይሆንም፤ ህወሓት ወታደራዊ ትጥቁን የሚፈታ እና በውስጡ የሚገኙ ወንጀለኞችን አሳልፎ የሚሰጥ ከሆነ በሀገርዊ ምክክሩ ሊሳተፍ ይችላል” ማለታቸው መዘገቡ የሚታወስ ነው።

የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ዓላማ እንደ ህገ መንግስት እና ሰንደቅ ዓላማ ባሉ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከፋፋይ ሀሳቦችን በሚያቀራርቡ ሀሳቦች መተካት ማስቻል ነው ሲል ፓርቲዉ በጽሁፉ ገልጿል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ 42 እጩ ኮሚሽነሮችን በህዝብ ድምፅ ሰብስቦ ይፋ ያደረገ ሲሆን የምክክር ኮሚሽኑ በ11 ኮሚሽነሮች እንደሚመራ መገልፁ ይታወሳል።

[@AddisZeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርልስ ሚሼል ጋር ተወያዩ።

"ከአፍሪካ ኅብረት እና ከአውሮፓ ኅብረት የጋራ ጉባኤ አስቀድሞ ከወዳጄ ፕሬዚደንት ቻርልስ ሚሼል ጋር ተገናኝተናል" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ።

የአውሮፓ ኅብረት እና የኢትዮጵያን ግንኙነት፣ ቀጣናዊ እንዲሁም አህጉራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውንም ገልፀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
#ሀብት_ያለው_አእምሮህ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የእለት ጉርስህን ለማግኘት እየተጣጣርክ ወይም ያለህ ሀብት እንዲበዛ የምታደርግበትን መንገድ እየፈለግክ ነው?

እንግዲያውስ ሀብት ያለው አእምሮህ የተሰኘው አዲሱ የዶ/ር ጆሴፍ መርፊ መጽሀፍ ይረዳሀል፡፡ መጽሐፉ “የሁሉም ሀብት መነሻ አእምሮ ነው” ይለናል፡፡

“የምትኖረው በአእምሮህ ውስጥ ነው፡፡ ሀብታም ወይም ደሀ፣ ለማኝ ወይም ሌባ የምትሆነው እዚያ ነው፡፡ በህይወት ውስጥ የምትፈልጋቸውን ነገሮች የመፍጠር ኃይል እንዳለህ ስትገነዘብ ታላቅ ዋጋ ያለው እንቁ እንዳለህ ታውቃለህ፡፡ በውስጥህ ያለው ሀብት እና ኃይል በጭራሽ የሚቀንስ ስላልሆነ አንተ ከምታስቀምጠው ገደብ በስተቀር የአእምሮህ ሀብት ገደብ አያውቅም፡፡”

ከዝቅታ ህይወት ወደ ከፍታ ህይወት ተሸጋግረህ አንገትህን ቀና ለማድረግም ሆነ፣ በሕይወትህ ውስጥ የሚገባህን ብልጽግና ለማግኘት ይህ መጽሐፍ እንዴት የድብቁን አእምሮህን ኃይል መጠቀም እንዳለብህ ያስተምርሀል፡፡

#ሀብት_ያለው_አእምሮህ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
አዲስ አበባ ከተማ ሊገባ የነበረ 2500 የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ!

ትናንት ከሱሉልታ ወደ አዲስ አበባ በኤፍኤስአር የጭነት መኪና ተጭኖ ሊገባ የነበረው 2500 የክላሽ ጥይት ኬላ ፍተሻ ላይ መያዙን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ ገልፀዋል።

አቶ ጌታሁን አክለውም በፍተሻው ወቅት የጥይቱ አዘዋዋሪና ሹፌሩ ለጊዜው ሲሰወሩ መኪናው እና ጥይቶቹን ቁጥጥር ሥር በማዋል በኤግዚቢትነት ተይዘው በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነ መግለፃቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን የሚገኘው ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላንድ ሳምንት አቋርጦት የነበረውን የስኳር ምርት እንደገና ማምረት እንደጀመረ ለመንግሥት ዜና አውታሮች ተናግሯል። ፋብሪካው ምርቱን ላንድ ሳምንት ያቋረጠው ባካባቢው ባለው የጸጥታ ስጋት ሳቢያ የነዳጅ አቅርቦቱ በመስተጓጎሉ እንደነበር ገልጦ፣ አሁን ግን የነዳጅ አቅርቦት ችግሩ ስለተፈታለት ምርት መጀመሩን ነው ያስታወቀው። የፋብሪካው ምርት ካለፈው የካቲት 2 ጀምሮ የተቋረጠው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሳቢያ እንደሆነ ተደርጎ የተሠራጨውን ዘገባ ፋብሪካው አስተባብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
Forwarded from YeneTube
#የኢትዮጵያ_ታሪክ_ከንግስተ_ሳባ_እስከ_አዲስ_አበባ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የኢትዮጵያን ታሪክ ከንግስተ ሳባ እስከ አዲስ አበባ የሚቃኘውና በአማዞን የምንጊዜም የኢትዮጵያ ታሪክ መጻህፍት ሽያጭ ከፍተኛ ደረጃን የተቆናጠጠው መጽሐፍ በአማርኛ ተተርጉሞ ቀረበ፡፡

ይህ አለም በጣም ያደነቀው መጽሐፍ ኢትዮጵያን በትናንት፣ በዛሬና በነገ መነጽር የሚያሳይ የ30 ዓመታት ምርምር ውጤት የሆነ በቅጡ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው፡፡

የአጼ ኃይለስላሴ የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት ልዑል አስፋ ወሰን አስራቴ ስለመጽሐፉ እንዲህ ነው ያሉት፡-

“አንብቤ ለመጨረስ ሶስት ሌሊቶች ብቻ ነው የወሰደብኝ፡፡ ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊ፣ ኃይማኖታዊ ልምምድ ላይ ባልተለመደና ቀልብን በሚያነሆልል ሁኔታ የተጻፈ ነው፡፡ መጽሐፉ በአፍሪካ ምድር ከሚገኙ መሳጭ ስልጣኔዎች መካከል አንዱ ስለሆነው የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለንን ግንዛቤ የሚያፋፋ እጽ ነው፡፡”

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
Forwarded from YeneTube
🇭🇺የስራ ጉዞ ወደ #Hungary 🇭🇺
#Schengen_visa

👉 የሚሰራበት አገር - Budapest, Hungary
👉 የስራው አይነት - Construction work
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - 8 - 10 hr/day
👉 የወር ደሞዝ - €1500 and more
👉 ፆታ - ወንድ
👉 ዕድሜ - 18 እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው

#30_persons

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo


Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com
http://Sabinaadvisor.com
https://tttttt.me/sabinavisaa
Forwarded from YeneTube
🎁 #ArtLand_gifts 🎁

✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው" 🎁

✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን 👌

✔️እንዲሁም MUG, PUZZLE, ሀብል እና ፕላስቲክ MDF ላይ የወደዱትን ፎቶ ወይም ፅሁፍ ያሰሩ 🎁


🔘☎️contact us: 0931465618
🔘For Order @Artlandgifts

Join our telegram channel👇
@artlandengraving
ከአዲስ አበባ ወደ ወልቂጤ ከተማ ሽጉጥና የክላሽንኮቭ ጥይቶችን ይዞ ሊሄድ ሲል በቁጥጥር ሥር የዋለው ተከሳሽ የ9 ዓመት ፅኑ እስራትና የ80 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተወሰነበት!

ከአዲስ አበባ ወደ ወልቂጤ ከተማ ሽጉጥና የክላሽንኮቭ ጥይቶችን ይዞ ሊሄድ ሲል እጅ ከፍንጅ የተያዘው ተከሳሽ በ9 ዓመት ፅኑ እስራትና በ80 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት አንዲቀጣ ተወስኖበታል።

የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው አበበ ቦጋለ የተባለው ተከሳሽ የጦር መሳርያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀፅ 4/1 እና 22/3 ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ መጋቢት 22/2013 ከቀኑ 4:00 ሰዓት ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው አውቶብስ ተራ ውስጥ ወደ ወልቂጤ ከተማ ለመጓዝ ቅጥቅጥ አውቶብስ ላይ ተሳፍሮ እያለ፤ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ተጠራጥረው ድንገት ሲፈትሹት ይዞት በነበረው ሻንጣ ውስጥ “ሪታይ ፍልከን” የተባለ ሽጉጥ ከመሰል 4 ጥይቶች እና ብዛታቸው 300 (ሶስት መቶ ) የሆኑ የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይቶች ይዞ እጅ ከፍንጅ በመገኘቱ በፈፀመው የፀና ፍቃድ ሳይኖረው የጦር መሳርያ መያዝና ማዘዋወር ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ቀርቧል።

ተከሳሹ በተመሰረተበት ክስ ላይ የእምነት ክህደት ቃሉን ተጠይቆ ወንጀሉን መፈፀሙን ሙሉ በሙሉ ባለማመን ክዶ የተከራከረ ሲሆን፤ ዐቃቤ ህግ በበኩሉ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ለፍርድ ቤቱ ያስረዳሉ ያላቸውን ዝርዝር የሰው፣ የሰነድና በክሱ ላይ የተጠቀሰው የጦር መሳርያ በኢግዚቪት ማስረጃነት አቅርቦ አሰምቷል።

ይህንንም ተከትሎ ፍርድ ቤት ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም ተከሳሹ ማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን ጥፋተኛ ነህ ሲል ፍርድ በመስጠት ተከሳሽን ያርማል መሰል አጥፊዎችን ያስተምራል ያለውን በ9 ዓመት ፅኑ እስራትና በ80 ሺህ ብር የገንዘብ እንዲቀጣ እንደወሰነበት ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ በኢትዮጵያ ታውጆ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱን በበጎ እንደምትመለከተው አስታወቀች!

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ የአዋጁ መነሳት ብሔራዊ ምክክርን ለማፋጠን ያግዛል ብሏል።መንግስት አዋጁ እንዲነሳ ማድረጉ እየተካሄደ ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ተጨማሪ ጠቃሚ እርምጃ እንደሚሆንም ዋሸንግተን አስታውቃለች።ይህ እርምጃም በአዋጁ የታሰሩ ሰዎችን በአስቸኳይ በመፍታት ሊቀጥል እንደሚገባም ነው የአሜሪካ መንግስት የጠየቀው።

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
በእንግዳ ማረፍያ (ፔኒስዮን) የተነሳው እሳት እስካሁን ማንነታቸው ያልታወቀ የጥንዶችን ህይወት ቀጥፏል፡፡

በአቃቂ ክ/ከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ ዛምባባ ጠጅ ቤት አካባቢ በሚገኙ የንግድ ቤቶች ላይ የካቲት 9/2014 ሌሊት 8፡42 ገደማ የተነሳው የእሳት አደጋ በአንድ የመኝታ ክፍል ውስጥ ተኝተው የነበሩ ሁለት ሰዎችን ህይወት አሳጥቷል፡፡የእሳትና ድንገተኛ አደጋ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ ንጋቱ ማሞ በአደጋው ህይወታቸው ያለፈውን የሁለቱን ግለሰቦች ማንነት እንዲሁም የአደጋውን መነሻ ምክንያት ፖሊስ እያጣራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ግለሰቦች ህይወታቸው ያለፈበት “ፔኒሲዮን” ወይንም የእንግዳ ማረፊያ ክፍል ላይ ድንገተኛ እሳቱ በመነሳት ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡

በተጨማሪም፤ በአካባቢው ተያይዘው በሚገኙት አራት የንግድ ሱቆች፣ የሸቀጣሸቀጥ መደብር፣ ምግብ ቤት፣ ፀጉር ቤት እንዲሁም ግሮሰሪ ላይ ድንገተኛ እሳቱ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡

በአደጋው ምክንያት በአንድ መኝታ ክፍል ውስጥ ተኝተው የነበሩ ሁለት ጥንዶች ህይወት ከማለፉ በተጨማሪ በአደጋው የሶስት ሰዎች ህይወትን ማትረፍ የተቻለ ሲሆን ሰባት መቶ ሺ ብር የሚገመት ንብረት ሊወድም እንደቻለ ኢትዮ ኤፍኤም ሰምቻለሁ ብሏል፡፡

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ሶስት የእሳት አደጋ ተሸከርካሪዎች የተሰማሩ ሲሆን ሰላሳ በሚሆኑ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ባለሙያዎች በአንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ እሳቱን ለመቆጣጠር መቻሉንም አቶ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የካቲት 9 /2014 ዓ/ም ምሽት 11፡50 በኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አየር ጤና አካባቢ በመኖሪያ ቤት ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ ከ አንድ መቶ ሺ በላይ የሚገመት ንብረት ሲወድም ከ ሁለት መቶ ሺ በላይ ንብረት ደግሞ ማትረፍ መቻሉንም አቶ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡

በዚህኛው አደጋ የሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የነገሩን አቶ ንጋቱ ህብረተሰቡ እንዲሁም የንግድ ድርጅቶች ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት የሚሆኑ ነገሮች ላይ የተለየ ጥንቃቄን በማድረግ እራሳቸውንና ንብረታቸውን እንዲጠብቁ ጠይቀዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ነፃነታቸውን የተነፈጉ ሰዎችን መብት በሚመለከት ብሔራዊ ምርመራ ሊያደርግ ነው!

ኢሰመኮ የብሔራዊ ምርመራውን መጀመር አሰመልክቶ ዛሬ ሐሙስ የካቲት 10/2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከባለድርሻዎች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።

ኢሰመኮ ነፃነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች መብቶች ዙርያ የሚደረገው ብሔራዊ ምርመራ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የሚቆይ ነው ብሏል።

ምርመራው በአስፈጻሚ አካላትና በሌሎችም፣ ስልታዊና ውስብስብ በሆኑ መንገዶች ነፃነታቸውን የተነፈጉ፣ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎችን ጉዳይ የሚመለከት ነው ብሏል።

ለዚህ ብሔራዊ ምርመራ መነሻ የሆነው ኢሰመኮ በስፋት የተቀበላቸው ጥቆማዎችና ያደረጋቸው ምርመራዊ ጥናቶች መሆናቸውን የኢሰመኮ የሲቪል፣ የፖለቲካዊ፣ የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ኮሚሽነር አብዲ ጅብሪል (ዶ/ር) ለአሻም ነግረዋታል።

ብሔራዊ ምርመራው የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት ነፃነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች፣ ባለ ግዴታውችን እና የመብት ተሟጋቾችን በማሳተፍ በውይይት ላይ የተመሠረተ ፍትሕን ለማስፈን ይረዳል ተብሏል።

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
ህወኃትን ከአሸባሪ ዝርዝር ውስጥ ይውጣ ለሚለው ጥያቄ መንግስት ምንም ምላሽ የለውም ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ!

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀውን ህወኃት ከአሸባሪ ዝርዝር ውስጥ ይውጣ ለሚሉ ጥያቄዎች መንግስት ምንም አይነት ምላሽ የለውም ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።አምባሳደር ዲና በዛሬው እለት ሳምንታዊ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የስራ ማብራሪያ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ የደህንነት ጉዳይ ያገባናል የሚሉ አካላት ተደራደሩ እያሉ ነው፤ ለምን አላችሁ የምንለው ነገረ የለም መንግስት ግን የራሱን አቋም ያራምዳል ለጥያቄው ምንም ምላሽ  የለውም ሲሉ አስረድተዋል።ከተለያዩ አካላት ህወሃትን ከአሸባሪ ዝርዝር ውስር ይወጣ እያሉ ጥያቄ ቢያቀርቡሙ በመንግስት በኩል ምንም ምላሸ የለም ማለታቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው ስለ አፍሪካ ህብረት ጉባኤ በሰላም ስለመጠናቀቅ ያነሱ ሲሆን በጉባኤው የ23 ሀገራት ፕሬዝዳንቶች ፣ ሶስት ጠቅላይ ሚኒስትሮችና ሶስት ምክትል ፕሬዝዳንቶች መገኘታቸውን ገልጣልቃ ።ጉባኤው ካተኮረባቸው  ጉዳዮች መካከል ኮቪድ እና መፍትሄው ፥ ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚዊ እና የልማት  አጀንዳ መሆናቸውን አስታውሰዋል።

በጉባኤው የሰላም እና ጸጥታ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የጠመንጃ ድምጽ በአፍሪካ አህጉር እንዳይሰማ የተያዘው እቅድ  ሊሳካ አለመቻሉ አሳዛኝ ሲሉ አምባሳደር ዲና ገልፀውታል።እንዲሁም በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት መፈንቅለ መንግስት መብዛቱ አሳሳቢ መሆኑ የተነሳ ሲሆን እንዲሁም በአፍሪካ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ላይ ስለሚኖር ጣልቃ ገብነት የጉባኤው ተሳታፊዎች ነቅፈውታል።

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከስሎቪኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቻቸው ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገለፁ!

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አህመድ ከስሎቪኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጃኔዝ ጃንሳ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት "ከጠቅላይ ሚኒስትር ጃኔዝ ጃንሳ ጋር ለረዥም ጊዜ የዘለቀውን የኢትዮጵያና የስሎቪኒያ ወዳጅነት ስለማጠናከር እንዲሁም ስለቴክኒክ እና ኢኮኖሚ ትብብር ተወያይተናል።" ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa