ሴኔጋል የአፍሪካን ዋንጫ ድል ለማክበር ሰኞን ብሄራዊ በዓል ስትል አወጀች።
የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድናቸው በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ ማሸነፉን ተከትሎ ሰኞ የህዝብ በዓል እንዲሆን ሲሉ ማወጃቸውን የሀገሪቱ ቴሌቪዥን አስታወቀ።
ፕሬዝዳንቱ በግብፅ እና በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉዞ ሲያጠናቅቁ ኮሞሮስን ለመጎብኘት አቅደው የነበር ቢሆንም በድል አድራጊዎቹ አናብስት ምክንያት ወደ ዳካር ተመልሰዋል ሲል RTS ዘግቧል።
በእሁዱ የካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ሴኔጋል በሊቨርፑሉ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ መሪነት የመሀመድ ሳላህ ግብፅን 4-2 አሸንፋለች።
ጨዋታው ከተጨማሪ ሰዓት በኋላ ጎል ሳይቆጠርበት ተጠናቋል።
በ2002 እና 2019 ሴኔጋል ካለፉት ሁለት የፍጻሜ ሽንፈቶች በኋላ የመጀመሪያዋን የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ሆናለች።
አናብስቱ ማክሰኞ ዳካር በሚገኘው ፕሬዝዳንታዊ ቤተ መንግስት ትልቅ ድግስ ይጠብቃቸዋል ሲል RTS ቴሌቪዥን ተናግሯል።
Viab:- ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa

በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ እየተፈጸመ ስላለዉ መፈንቅለ መንግስት መሪዎች ቅሬታ አሰሙ
ባለፈው አንድ አመት አምስት ወታደራዊ የመንግስት ግልበጣ በአፍሪካ መፈጸሙን ተከትሎ የመፈንቅለ መንግስት ማዕበል ሲሉ በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የተገኙ መሪዎች ቅሬታቸዉን አሰምተዋል፡፡የምርጫ መስፋፋት እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር መኖር በአፍሪካ የመፈንቅለ መንግስት ቁጥር እንዲቀንስ አድርጎ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
የጦር ሰራዊት ሀይል በቅርቡ ስልጣን ከተቆጣጠረባቸው ሀገራት መካከል ሁለቱ ቡርኪናፋሶ እና ማሊ አማፂያንን ለመቆጣጠር ሲታገሉ ቆይተዋል።ባለፈው ሳምንት በጊኒ ቢሳው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተካሂዶ የነበረ ሲሆን የጊኒ ቢሳዉ ፕሬዚዳንት የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ቡድኖች ለመንግስት ግልበጣዉ ሙከራ ተጠያቂ አድርገዋል።
በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት በበርካታ ሰዎች ተቀባይነት ቢያገኝም፣ በጥቅምት አጋማሽ በሱዳን የተካሄደው ወታደራዊ የመንግስት ግልበጣ ግን የሲቪል አገዛዝ ይመለስ በሚሉ በርካታ የጎዳና ላይ ተቃውሞዎችን አስከትሏል። በዚህም የተነሳ ርህራሄ በሌለው ሃይል ከ70 በላይ ሰልፈኞች ተገድለዋል፡፡
በ አዲስ አበባ በተካሄደዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተገኙት እያንዳንዱ መሪ “በማያሻማ መልኩ የታየውን የመንግስት ለውጥ ኢ-ህገ መንግስታዊ በማለት ማውገዛቸውን” የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት መሪ ባንኮሌ አዴዮ ተናግረዋል፡፡ ወታደራዊ መንግስታትን አንታገስም ሲሉ አክለዋል፡፡
ወታደራዊዉን የመንግስት ግልበጣ ተከትሎ ቡርኪናፋሶ፣ጊኒ፣ማሊ እና ሱዳን ከአፍሪካ ህብረት አባልነት መታገዳቸዉ ይታወሳል፡፡
Via :- #ዳጉ_ጆርናል

አሸባሪው ሸኔ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ 168 ንጹሐን ሰዎችን መግደሉ ተገለጸ
👉87 ንጹሐን በጅምላ በአንድ ቦታ ተገድለው ተገኝተዋል❗️
አሸባሪው ሸኔ በጊዳሚ ወረዳ 168 ንጹሐንን መግደሉን በኦሮሚያ ክልል የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር አስታወቀ። መንግሥት በወሰደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ወረዳው ሙሉ በሙሉ ከአሸባሪው ሸኔ ነጻ መውጣቱ ተገልጿል።
የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር ተወካይና የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብሣ በሻ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በጊዳሚ ወረዳ አሸባሪው ሸኔ ዘግናኝ ግድያዎችንና የንብረት ውድመት ፈጽሟል።
በወረዳው በተለያዩ ቦታዎች 81 ሰዎችን እንዲሁም በጅምላ ተገድለው አስከሬናቸው አንድ ቦታ የተገኙ 87 ሰዎችን በድምሩ168 ንጹሐን መገደላቸውን ገልጸዋል። አሸባሪው ሸኔ በወረዳው በቆየበት ጊዜ 30 የመንግሥት ተቋማትን ንብረቶችን ማውደሙንና ዝርፊያ መፈጸሙን አስታውቀዋል።
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች፣ ተሽከርካሪዎች ፣ኮምፒውተሮችና ሰነዶች ዝርፊያና ውድመት ደርሶባቸዋል። የወረዳው አስተዳደር ጽህፈት ቤት፣ ከተማ ማዘጋጃ ቤትና ፖሊስ ጣቢያንም ማቃጠሉን ገልጸዋል። የሽብር ቡድኑ በትምህርት ዘርፉና በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
Via :-ኢፕድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህርስቶር ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥልቅ ግንኙነት ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ኢትዮጵያ ከኖርዌይ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ አጋርነት ትገነዘባለች ብለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው ወደ አገር ቤት ከገቡት ዲያስፖራዎች 22 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የሚገመት የጥሬ ገንዘብና የዓይነት ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እንድሪስ (ዶ/ር) ዲያስፖራዎቹ ለአገር ከፍተኛ ገቢ ከማስገኘታቸው ባለፈ ለሰላምና ገፅታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ጠቁመዋል፡፡
የአገር ገፅታ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲገነባ አንዲሁም የአገርን ሃብት በአግባቡ ለመጠቀም እና መዋዕለንዋይ ፈሰስ ለማድረግ ከ400 በላይ ዲያስፖራዎች መመዝገባቸውንም ገልፀዋል፡፡
አገር በአሸባሪው የትሕነግ ቡድን የተከፈተባትን ጦርነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የሀሰት መረጃዎችን ሲያሰራጩ የነበሩ የውጭ አገራት መገናኛ ብዙኃንን ለመመከት ዲያስፖራው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱም ተነስቷል፡፡
Via Walta

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተለያዩ ውሳኔዎቹን ማሳለፉን የመዲናዋ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃለፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ ለቻይና የባሕል ማዕከል ግንባታ የቀረበውን ጥያቄ የከተማዋ ካቢኔ መፅደቁን ገልጸው÷ ለዚህም 6 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ እንዲሰጥ ተወስኗል ብለዋል፡፡ይህም በሁለቱ ሃገራት መካከል የሚኖረውን የባህል፣ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚጠናክረው ነው ተናገሩት፡፡
በተያያዘ በቻይና መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የሚገነባውም የአፍሪካ የቀርከሃ ሰርቶ ማሳያ ማዕከል ግንባታም ጥያቄም ተመልሷል ብለዋል ሃላፊው።
ካቢኔው ከወሰናቸው ጉዳዮች መካከል የ13 የአፍሪካ ሀገራት የሊዝ ውል መሰረዙንም ነው አቶ ዮናስ በመግለጫቸው የጠቀሱት።በሌላ በኩል 35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በሰላም እንዲጠናቀቅ ጉልህ ድርሻውን ለተወጣው ሰላም- ወዳዱ ህዝብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምስጋና ያቀርባል ብለዋል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃለፊው፡፡
(ኤፍ ቢ ሲ)

የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ኡመር የተመድ ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በሱማሌዋ ዶሎ ከተማ የስደተኞች መጠለያ እንዲያቋቁም መጠየቃቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል። ሙስጠፌ ጥያቄውን ያቀረቡት፣ በጉረቤት ሱማሊያ በተከሰተው ከባድ ድርቅ ሳቢያ ወደ ሱማሌ ክልል የሚሱደዱ ሱማሊያዊያን ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ በድርቅ ለተጎዳው ሱማሌ ክልል የመሠረተ ልማት እና ዕርዳታ አቅርቦት አቅም ላይ ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል በሚል ስጋት እንደሆነ ጠቁመዋል። ስደተኞች ከአገራቸው ሳይሰደዱ ቢያንስ ድንበር ላይ ዕርዳታ ቢያገኙ እንደሚሻል የጠቆሙት ሙስጠፌ፣ ወደ ክልሉ ሊበን ዞን ዶሎ አዶ ወረዳ የገቡ 740 ሱማሊያዊያን ስደተኛ አባውራዎችን የክልሉ መንግሥት እየተንከባከበ እንደሆነ ገልጸዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከዚህ (shein.com) website ላይ ያሉ ለሴት እና ለወንድ በተጨማሪም ለህጻናት የሚሆኑ እቃዎችን ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል ይዘዙን
Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
Forwarded from YeneTube
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ
አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
Forwarded from YeneTube
Kdamie.com ንግድ እና አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ፡፡
#ጅምላና ችርቻሮ ንግዶችን አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ከጨረታና ፐርፎርማ እንዲሁም የስራ ማስታወቂያዎች እና መረጃዎች ጋር፣
#በጉዞዎ መዳረሻዎችን ከነ አስጎብኚዎች እና የጉዞ ወኪሎች ጋር
#የእንግዳ ማረፊያ ሆቴልና ሪዞርቶችን ፈርኒሽድ አፓርታማዎችን ገሰት ሀውሶችን እና ፔንሲዮኖችን
ለመኖሪያ የሚሆኑ ቪላ እና ኮንዲሚኒየሞችን
#በሁሉም የገበያ ማዕከላት ለሱቅ እና ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎችን ሳይዞሩ ሳይደክሙ የሚያገኙበት Kdamie.com
#በንግድ በቱሪዝም እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ለሆኑ ድጅቶችም ኑ አብረን እንስራ ይሎታል Kdamie.com
ከኛ ጋር መስራት ንግድና አገልግሎቶን ማዘመን፣ደንበኞችዎን ባሉበት ማግኘት ነው!! Kdamie.com
#በሁሉም የማህበራዊ ገፆች
Telegrame እና whatsup - +251-911705126
Kdamie.com - https://tttttt.me/+K7sPcHhHYy44NDI0
facebook - https://www.facebook.com/Kdamie-107188781818909
Instagram - https://www.instagram.com/p/CZkVH-FAd11/?utm_source=ig_web_copy_link
Email - kdamiesells@gmail.com
phone:- +251911705126/+251916821091 ያገኙናል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና ተጀመረ
የብልጽግና ፓርቲ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ መድረክ ሥልጠና ዛሬ ተጀምሯል፡፡
የአቅም ግንባታ መድረኩ ዓላማ አመራሩ ወቅቱ የሚጠይቀውን የአመራር ብቃትና አስተሳሰብ እንዲያጎለብትና የመረጠውን ህዝብ በትጋትና በቅንነት እንዲያገለግል ለማስቻል ነው ተብሏል።
@Yenetube @Fikerassefa
የብልጽግና ፓርቲ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ መድረክ ሥልጠና ዛሬ ተጀምሯል፡፡
የአቅም ግንባታ መድረኩ ዓላማ አመራሩ ወቅቱ የሚጠይቀውን የአመራር ብቃትና አስተሳሰብ እንዲያጎለብትና የመረጠውን ህዝብ በትጋትና በቅንነት እንዲያገለግል ለማስቻል ነው ተብሏል።
@Yenetube @Fikerassefa
የአማራ ክልል በግብርና ዘርፍ ላይ ከ340 ቢሊዮን ብር በላይ ውድመት እንደደረሰበት አስታወቀ
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ጦርነት በተደረገባቸው ዘጠኝ ዞኖች ላይ ሦስት ወራት የፈጀ ጥናት አድርጎ፣ በግብር ዘርፉ ላይ የ340.6 ቢሊዮን ብር ውድመት እንደደረሰ ማረጋገጡን አስታወቀ፡፡
አማራ ክልል ውስጥ ካሉት 11 ዞኖች ውስጥ በዘጠኙ ጦርነት የተካሄደ መሆኑን፣ በእነዚህ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ 76 ወረዳዎች ላይ በግብርናው ዘርፍ ጉዳት መድረሱ በጥናቱ ላይ ተመላክቷል፡፡ ጦርነት በተደረገባቸው እነዚህ ዞኖች ውስጥም 9.8 ሚሊዮን ሕዝብ እንዳለ ታውቋል፡፡

ከኢትዮጵያ ተነስቶ አፍሪካን የሚወክል ሚዲያ በምስረታ ላይ መሆኑ ተገለፀ::
“ግሎባል ቴሌቭዥን ኔትዎርክ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ” የመጀመሪያውን ምዕራፍ አጠናቆ በሁለተኛ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የሚዲያው መስራችና ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ግሩም ጫላ አስታውቋል።ሚዲያው በአፍሪካ ከመረጃ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ዘመኑን በሚመጥን የሚዲያ ግብዓት ተደራጅቶ የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል።ኢትዮጵያ አፍሪካን አንድ በማድረግ ሂደት ያላትን ፋይዳ መነሻ በማድረግ ሚዲያው ከኢትዮጵያ በመነሳት በመላው አፍሪካ የሚሰራ እንደሆነም ግሩም ጫላ ተናግሯል።
ሚዲያው መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገና ለዚህም 5 ሺህ ካሬ የሚገመት መሬት 30 ሚሊዮን ብር የሊዝ ገቢ በማድረግ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መረከባቸውን ጋዜጠኛ ግሩም ገልጿል። ሚዲያው በመላው አፍሪካ ዘጋቢዎች ይኖሩታል የተባለ ሲሆን፣ በሌሎች የአለም አገራት ኒዮርክ፣ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ቤጂንግ እና ለንደን መቀመጫ እንደሚኖረውም መመላከቱን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል።ሚዲያው ነጻና ገለልተኛ በመሆን የአፍሪካን ገጽታ ለመቀየር በትኩረት ይሰራልም ተብሏል።

ፈተና መሰረቅ ከግለሰብ ይልቅ ተቋማዊ እየሆነ መምጣቱ የትምህርት ሚኒስቴሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ
የፈተና መሰረቅ ከግለሰብ ይልቅ ተቋማዊ እየሆነ መምጣቱ እና በአጠቃላይ የደረሰብን የሞራል ክስረት ከፍተኛ እንደሆነ ሚንስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡
የእኔ ክልል ተማሪዎች ማለፍ አለባቸው በሚል በተቋም ደረጃ የፈተና ወረቀቶችን በመስረቅና መልስ በመስጠት ጭምር ተባባሪ የሆኑ አመራሮች መኖራቸው ፣ የትምህርት ሲስተሙ ጥራት ተዓማኒነት ከፍተኛ ጥያቄ ዉስጥ መግባቱን አንስተዋል፡፡
አንድ ሰዉ በዚህ የትምህርት ስርዓት ዉስጥ አልፎ ድግሪ ሲያገኝ ድግሪዉ ለማህበረሰብ መስጠት ያለበትን መልዕክት ይሰጣል ወይ፣ ትርጉም ያለዉ መመዘኛስ ይኖረዉ ይሆን መባል አለበት ይህንን ማድረግ የሚቻለዉ ግን ሲስተሙ ተዓማኒነቱ የተጠበቀ ከሆነ ብቻ ነዉ ብለዋል፡፡
‘’ግማሹ ለፍቶ ጥሮ ዉጤት እየያዘ ፣ ሌላዉ ደግሞ ከድግሪ ፋብሪካዎች ድግሪ እየተቀበለ የሚያልፍበት ሁኔታ ካለ ችግሩ የተወሰኑ ሰዎች ማለፍ ሳይሆን ፣ ችግሩ የትምህርት ጥራቱ ላይ ነዉ’’ ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ፈተና የሰዎችን ክህሎት እና ታታሪነት መለኪያ መሆኑ ቀርቶ ተሰርቆ ና መልስ ተሰጥቶ የሚመጣ ዉጤት ምዘና አያሟላም፣ ተዓማኒነትም አይኖረዉም ብለዋል፡፡
“የትምህርት ተቋማት ምዘና ተደርጎባቸዉ ሰርተፊኬት ይስጡ በሚባልበት ሁኔታ በተለይ ለግል ትምህርት ቤቶች የስራ ሰርተፊኬት የሚሰጠዉ በችሎታቸዉ ሳይሆን በጉቦ ከሆነ ሲስተሙ ፈርሷል ይህንንም ሁላችንም ነው የምናዉቀዉ ነገርግን ፊትለፊት ስለማንነጋገርበትም ስር የሰደደ መፍትሄ ልንፈልግለት ያልቻልነዉ ጉዳይ ነዉ“ ብለዋል፡፡
የትምህርት ስርዓቱን ተዓማኒነት ጥያቄ ዉስጥ የሚከት አካሄድ በጣም ተንሰራፍቷል ያሉት ሚንስትሩ የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል እንደዚህ ያሉ አሰራሮችን ማስቆም ና የሲስተሙን ተዓማኒነት ችግር ዉስጥ የሚከቱ ጉዳዮችን ከስር መሰረታቸዉ መፍታት አለብን ሲሉ ለሰው ሃብት ልማት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተናግረዋል፡፡
Via :- Ethio FM

አሜሪካ በአፍጋኒስታን የአይኤስኤስ መሪ ሳኑአላህ ጋፋሪ ያለበትን ለጠቆመ 10 ሚሊየን ዶላር እሰጣለሁ አለች
ሳኑአላህ ጋፋሪ ባሳለፍነው ነሀሴ ወር ላይ በካቡል ኤርፖርት የደረሰውን የሽብር አደጋ እንዳቀነባበረ ይጠረጠራል። አሜሪካ በዚህ የሽብር አደጋ 13 ወታደሮቿን በሞት ያጣች ሲሆን፤ ሌሎች ንጹሃንም በዚሁ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል።
ሳኑአላህ ጋፋሪ ያለበትን የጠቆመ ለእያንዳንዱ መረጃ 10 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥም ነው አሜሪያ ያሳወቀችው።
ሳኑአላህ ጋፋሪ ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ በአፍጋኒስታን የአይኤስኤስ መሪ እንደሆነ ይነገራል።
Via:- Al Ain

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ከ14 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ
የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ለተጎዱ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ከ14 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ፡፡ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በአማራ ክልል ውድመት ለደረሰባቸው መቅደላ አምባ፣ ወሎ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን የቤተ-ሙከራ ዕቃዎችና ኮምፒውተሮችን አበርክቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በኢትዮጵያ በቅርቡ የቴሌኮም አገልግሎቱን በይፋ እንደሚጀምር የሚጠበቀው የኬንያው ሳፋሪኮም ኩባንያ የሞባይል ገንዘብ ግብይት አገልግሎትን ፍቃድ ጭምር እንዲያገኝ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን የገንዘብ ሚንስትር ደዔታ እዮብ ተካልኝ ለኬንያው ቢዝነስ ደይሊ ጋዜጣ ተናግረዋል።
መንግሥት በቅርቡ ላልተወሰነ ጊዜ ካራዘመው ሁለተኛው የቴሌኮም አገልግሎት ጨረታ ውስጥ የሞባይል ገንዘብ ዝውውርና ግብይት አገልግሎትን እንዳስወጣው እዮብ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለሳፋሪኮም ኩባንያ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር እና ግብይት ፍቃድ እንዲሰጥ የሚያስችለው የሕግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ እንደሆነ እና እስከ ቀጣዩ ግንቦት ወር ሳፋሪኮም ፍቃዱን ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ እዮብ አክለው ጠቁመዋል።
መንግሥት ቀደም ሲል የሞባይል ገንዘብ ግብይትን ለውጭ ኩባንያዎች ክፍት እንደማያደርግ በማሳወቁ፣ ሳፋሪኮም ኩባንያ አምና ተወዳድሮ ባሸነፈበት የመጀመሪያው የቴሌኮም አገልግሎት ጨረታ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር እና ግብይት አገልግሎት ፍቃድ አልተካተተም ነበር። ሆኖም መንግሥት አምና በግንቦት ወር ላይ እንደገና አቋሙን ቀይሮ የኬንያውን ሳፋሪኮም ጨምሮ የውጭ ኩባንያዎች በሞባይል ገንዘብ ግብይት አገልግሎት ጭምር እንዲሳተፉ መፍቀዱ ይታወሳል።
መንግሥት ሁለተኛውን የቴሌኮም አገልግሎት ጨረታ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን ባለፈው ታኅሳስ ያስታወቀው፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሀገሪቱ በነበረው ተጨባጭ ሁኔታ ሳቢያ ብቃት ያላቸው የውጭ ኩባንያዎች በጨረታው ላይሳተፉ ይችላሉ ብሎ በመስጋቱ እና በጨረታው የመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው የውጭ ኩባንያዎችም ጊዜው እንዲራዘምላቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት እንደሆነ ቀደም ሲል አስታውቋል። ሚንስትር ደዔታ እዮብ ግን ሁለተኛው የቴሌኮም አገልግሎት ጨረታ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ፣ ሳፋሪኮም ኩባንያን የሞባይል ገንዘብ ግብይት ፍቃድ ከማግኘት እንደማያግደው፣ መንግሥት ለኩባንያው የገባውን ቃል እንደማያጥፍ እና ኩባንያው በአፍሪካ በቀዳሚነት የሚታወቅበትን በሞባይል ገንዘብ የመገበያየት እና የማዘዋወር አገልግሎት ፍቃድ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ እንደሚያገኝ ቃል ገብተዋል።
ሳፋሪኮም ኩባንያ አምና በኢትዮጵያ ጨረታ ያሸነፈበትን የቴሌኮም አገልግሎት እስከ መጭው ሚያዚያ ድረስ እንደሚጀምር ቀደም ሲል ማስታወቁ ይታወሳል።
ሳፋሪኮም ኩባንያ በኬንያ ከ15 ዓመታት በፊት በጀመረው "ኤምፔሳ" (M-pesa) በተባለው የሞባይል ገንዘብ ዝውውር እና ግብይት አገልግሎቱ በሀገሪቱ ከ50 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ያሉት ሲሆን፣ በአፍሪካም ግዙፉ በሞባይል የገንዘብ መገበያያ እና ማዘዋወሪያ አገልግሎት ነው።
የሳፋሪኮም እህት ኩባንያ የሆነው የደቡብ አፍሪካው ቮዳኮም ደሞ በታንዛኒያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሌሶቶ፣ ጋና፣ ዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ እና ግብጽ ተመሳሳይ አገልግሎት ይሰጣል።
Via Wazema

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቀላይ ሀብት 1.1 ትሪሊዮን ብር መድረሱን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገለፀዋል።
[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የጀመረውን ሰላም የማስከበር ሂደት አጠናክሮ እንዲቀጥል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አንዳንድ ነዋሪዎች ጠየቁ።
መንግስት በበኩሉ በብሔረሰብ አስተዳደሩ ኦነግ/ሸኔ ሲገለገልባቸው የነበሩ ናቸው ያላቸውን ማሰልጠኛ ጣቢያዎችን ሰሞኑን መደምሰሱን ገልጧል።100 የሚደርሱ ታጣቂዎችንም መግደሉን አመለክቷል።መንግስት በአሸባሪነት የፈረጀው ኦነግ ሸኔ የተባለው ታጣቂ ቡድን በከሚሴ ከተማ በተደጋጋሚ ንብረታቸውን እንዳወደመባቸውና በሠራተኞቻቸው ላይም ድብደባ መፈፀሙን አንድ ባለሀብት ተናግረዋል።
ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ ታጣቂዎች መሸሸጊያ ሆናለች ያሉት እኝሁ ነዋሪ መንግስት የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።ሌላው የከሚሴ ከተማ ነዋሪም መንግስት እየወሰደ ያለውን ተግባር አድንቀው በአንድ ወረዳ የቡድኑ ማሰልጠኛ ጣቢያ መውደሙን እንደሚያውቁም አብራርተዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዪኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀማል ሁሴን ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ (DW) እንደተናገሩት ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት በተወሰዱ የተቀናጁ ርምጃዎች ኦነግ ሸኔ በብሔረሰብ አስተዳደሩ ሁለት ወረዳዎች ይገለገልባቸው የነበሩ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት ተደምስሰዋል።የታጣቂው 100 አባላትም ተገድለዋል፣ 600ዎቹ ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የደዋ ጨፋ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የወረዳው ሰላምና ሕዝብ ደኅንነት ኃላፊ አቶ ሰኢድ አደም በበኩላቸው በወረዳው የነበረ የታጣቂ ቡድኑ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ ወድሟል፣ ታጣቂዎቹና የጦር መሣሪያዎችም ተማርከዋል ብለዋል።ርምጃው የተወሰደው ባለፉት ሳምንታት በተከታታይ በተደረገ ጥናትና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንደሆነ የዞኑ የኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀማል ሁሴን ተናግረዋል።
(DW)