የአፍሪካ ህብረት 35ተኛው የመሪዎች ጉባኤ የመክፈቻ ስነስርአት እየተካሄደ ይገኛል ፡፡
በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የህብረቱ ኮሚሽነር ሙሳፋኪ ማሃማት ዋና ዋና ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተው ሰፊ ውይይት እንዲደረግ የጠየቁ ሲሆን በተለይም በአህጉሪቱ እየተደጋገመ የመጣው የመፈንቅለመንግስት የደህንነት ስጋት የምግብ ዋስትና አለመረጋገጥ እንዲሁም በህብረቱ የታዛቢነት ቦታ ጠይቃ የነበረችውን የእስራኤልን ጉዳይ በተመለከተ ግልጽ ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪም የእርስ በእርስ ግንኙነታችን በድጋሚ ሊጤን ይገባል ያሉት ኮሚሽነሩ በየቀጠናው ያለው የየሃገራት ግንኙነት እየሻከረ መምጣት አስጊ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ባደረጉት ንግግር ከ2 አመታት በላይ ህብረቱ ሳይሰበሰብ መቅረቱን አስታውሰው የኮሮና ቫይረስ ከነጠቀው የሰው ህይወት በተጨማሪም ያልተገባ የቫይረሱ መከላከያ ክትባት ስርጭት እና ሌሎች ፈተናዎችን ደቅኖብን ነበር ሲሉ አስታውሰዋል፡፡
በግብርናው ዘርፍ አህጉራችን በትኩረት መስራት ይገባታል ያሉትጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃገራችን የተከናወነውን የመስኖ ስራዎች ስኬትን እንደአብነት አንስተዋል የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የአየር ንብረት ለውጥን ያነሱት ዶ/ር አብይ ተፅዕኗቸው ከፍተኛ እንደበርም አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም አህጉሪቱ ተመድ እራሱን እንዲያድስ መጠየቅ እንዳለባት ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ70 አመት የተሻገረ እድሜ ያለው ድርጅቱ በሚያደርገው ሪፎርም ለአፍሪካ ቢያንስ 2 ቋሚ እና 5 የተለዋጭ አባልነት ቦታ እንደሚያስፈልጋትም በቀጥታ ስርጭት በተላለፈው የመሪዎቹ ጉባኤ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የአፍሪካ የሆነ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ያስፈልጋታል ያሉ ዶ/ር አብይ አህመድ የራሳችንን ጉዳይ እራሳችን ልንናገር ይገባናል ብለዋል፡፡
በጉባኤው ላይ የተመድ ዋና ፃሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝም ንግግር አድርገዋል፡፡
Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አፍሪካውያ ወንድምና እህቶች በአስቸጋሪው ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆማቸው ምስጋና አቀረቡ
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አፍሪካውያን ወንድምና እህቶች በአስቸጋሪው ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆማቸው ምስጋና አቀረቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በዛሬው እለት በተጀመረው 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት፤ ባለፈው አመት ለአፍሪካ በተለይ ለኢትዮጵያ ፈታኝ ወቅት ነበር፡፡
ኢትዮጵያ ባለፈው አመት የገጠማት ሌላው ችግር በዋናነት የውስጥ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህም በውስጥ የተነሳው ችግር መሰረት በማድረግ የህግ ማስከበር ስራው ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን የውጭ ሃይሎች ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር ከፍተኛ ርብርብ ማድጋቸውን ጠቁመዋል፡፡
በዚህ ሂደትም የውጭ ሚዲያዎች በዚህ ውስጥ የነበራቸው ሚና ከፍተኛ እንደነበር ጠቁመው አፍሪካ የራሷ ድምጽ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማሳደግ አለባት ብለዋል፡፡
በተለይ ከአህጉሩ ውጭ ያሉ ሚዲዎች አፍሪካን ለማጨለም ከመስራት ሊቆጠቡ እንምደሚገባም አሳስበዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ አፍሪካውያ በጋራ መቆም እዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ በተለይ በፀጥታው ምክር ቤት ሁለት ቋሚና አምስት ተለዋጭ አባላት ሊኖራት እንደሚገባ በዚሁ አጋጣሚ ጠቁመዋል፡፡
በኢትዮያ ላይ የሚደረገው ጫና አንዱ የሆነው ወደኢትዮጵያ አትሂዱ የሚለው ዘመቻ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ዘመቻ ግን በዲያስፖራ አባላት አሁን ደግሞ በአፍሪካውያ ወንድሞችና እህቶች በመክሸፉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
Via :- EPA

በኅብረቱ ጉባኤ ላይ መሪዎች የአፍሪካን አንድነት የሚያጠናክሩ ሃሳቦችን አንስተዋል- አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኅብረቱ ጉባዔ ላይ መሪዎች የአፍሪካን አንድነት የሚያጠናክሩና በአህጉሪቱ ላይ የሚታዩ የተዛቡ ትርክቶችን ለመቀየር የሚያስችሉ ሃሳቦችን ማንሳታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ። በኅብረቱ ጉባኤ ላይ በመሪዎች የተነሱ አንኳር ጉዳዮችን በሚመለከት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
ሙሉ መግለጫን ሊንኩን ለማግኛት 👇
https://www.fanabc.com/በኅብረቱ-ጉባኤ-ላይ-መሪዎች-የአፍሪካን-አ/

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአፍሪካ ህብረት ሰብሳቢዎች መልካም ምኞታቸውን ገለጹ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለተሰናባቹ እና ለአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሰብሳቢ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለተሰናባቹ የአፍሪካ ህብረት ሰብሳቢ ፕሬዚዳንት ፍሊክስ ሺሰኬዲ ባለፋት አመታት በስራቸው ላሳዩት ቁርጠኝነት የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክት ሲያስተላልፉ በምትካቸው ለተመረጡት አዲሱ የህብረቱ ሰብሳቢ ማኪ ሳል ደግሞ መልክሙን ሁሉ በስራቸው ተመኝተውላቸዋል፡፡
ምንጭ- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ህወሓት አንድ የአፋር ዞን ተቆጣጥሮ የኢትዮ-ጅቡቲ መስመርን ለመቁረጥ ውጊያ ከፍቷል- አፋር ክልል
የአፋር ክልል መንግስት ዛሬ ባውጣው መግለጫ የህወሓት ኃይሎች ከታህሳስ 10፣2014 ዓ.ም ጀምሮ በድጋሚ ወደ ክልሉ በመግባት ጥቃት በመክፈት በርካታ ቦታዎችን መቆጣጠራቸውን አስታውቋል፡፡
የህወሓት ኃይሎች የክልሉን ሰሜና ዞን ኪልበቲ ረሱ ዞን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረው “ሰርዶ ድረስ ዘልቆ በመግባት የኢትዮ-ጂቡቲ መተላለፊያ ኮሪደር ዋና መስመርን ለመቁረጥ” ውጊያ ከፍተዋል ብሏል ክልሉ፡፡
ህወሓት በሌሎች አካላት በኩል ከመንግስት ጋር ስወያይ ነበር አለ
መግለጫው በፌደራል መንግስት በሽብር የተፈረጀው ህወሓት ኃይሎች በአፍር ክልል በተቆጣጠሯቸው እና ጦርነት እያካሄዱ ባሉባቸው ወረዳዎች ውስጥ ንጹሃን ሰዎች በጅምላ መጨፍጨፋቸውን ጠቅሷል፡፡
የክልሉ መንግስት የህወሓት ኃይሎች በከፈቱት ጦርነት ምክንያት እስካሁን 300ሺ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ብሏል፡፡
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተቀሰቀሰው የህወሓት ኃይሎች በሰሜን እዝ ላይ ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ ነበር፡፡
ጦርነቱ ከተጀመረ ከ8 ወር በኋላ የፌደራል መንግስት ጦሩን ከትግራይ ሲያስወጣ የትግራይ ኃይሎች ወደ አፋር እና አማራ ክልል በመግባት በሰው ህይወትና በንብረት ላይ መጠነ ሰፊ ውድመት ማድረሳቸውን የአፋር እና የአማራ ክልል መንግስታት ገልጸዋል፡፡
መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ግንባር ከዘመቱ በኋላ የህወሓት ኃይሎች ተሸንፈው ከሁለቱ ክልሎች መውጣታቸውን መንግስት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ነገርግን ህወሓት ከምስራቅ አማራ ከአፋር የወጡት ለሰላም እድል ለመስጠት ነው ሲል መግለጹ ይታወሳል፡፡
የፌደራል መንግስት ህወሓት በድጋሚ በተለይ በአፋር በኩል ትንሶሳ እያደረገ መሆኑን እርምጃም እንደሚወስድ በቅርቡ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
በ2013 ዓ.ም ጥቅምት ወር በትግራይ ክልል የተጀመረው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲገደሉ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ እንዲፈናቀሉ ኑሯቸው እንዲመሰቃቀል ምክንያት ሆኗል፡፡
ህወሓት ግጭቱን ለመፍታት በሌላ አካል በኩል ከመንግስት ጋር ንግግር መጀመሩንና ጥሩ ነገር መኖሩን ቢገልጽም መንግስት ንግግርም ሆነ ድርድርም አለመጀመሩን ገልጿል፡፡
Via :- al ain

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያዘጋጁት የእራት ግብዣ በወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ ነው።
በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ለተገኙ ልኡካኖች የእራት ግብዣ መርሀ ግብር በወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባዘጋጁት በዚህ መርሀ ግብር የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና የልዑካን ቡድን አባላት እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈውበታል፡፡
Via :- Fidel Post

በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይና በስፍራው በተሰማሩ የፀጥታ አባላት ላይ ስለተፈፀመው ግድያ ፍትህ እንጠይቃለን!
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይና በስፍራው በተሰማሩ የፖሊስ አባላት ላይ ስለተፈፀመው የጅምላ ግድያ ያቀረበው ሪፖርት ከፍተኛ ሀዘን እና ድንጋጤን ፈጥሮብናል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (#ኢዜማ) በተጎጂዎችና በተጎጂ ቤተሰቦች፤ በአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲሁም እንዲህ ያለ አስነዋሪ ድርጊት በአገራቸው ቦታ እንዳይኖረው በሚታገሉ ኢትዮጵያውያን ስም ኮሚሽኑን ማመስገን ይፈልጋል፡፡ ሕዝብና አገር የሚጠቀሙት የገዢዎችን ፊት እያዩ ሳይሆን በመረጃ ላይ በተመሰረተ እውነት በሀቀኝነት በሚሰሩ ተቋማት በመሆኑ የሚዲያ፣ የፀጥታና የፍትህ ተቋማት የኢሰመኮን አርዓያነት እንዲከተሉ እንጠይቃለን፡፡
በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይ የተፈፀመው ያለ ፍርድ ግድያ (Execution without trial) ኢዜማ በአገራችን እንዲሰፍን የሚታገልለት የሕግ የበላይነት ከፍተኛ አደጋ ውስጥ መወድቁን ያሳያል፡፡ ዜጎች በእዚህ መልኩ ክቡር የሆነ ሕይወታቸውን እንዲያጡ ምንም ዓይነት ምክንያት ሊቀርብ አይችልም፡፡ ግድያውን ኢትዮጵያውያን ያለ ልዩነት በጋራ እንዲያወግዙት እየጠየቅን መንግስት ከጅምላ ግድያው ጋር በተያያዘ እጃቸው ያለበትን የፀጥታ እና የአስተዳደር አካላት ሁሉ በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲያቀርብ እንጠይቃለን፡፡ የዜጎች ደኅንነትን መጠበቅ የመንግስት ተቀዳሚ ተግባሩ ሲሆን በአካባቢው የፀጥታ አካላት ላይ ጥቃት የፈፀመውንም “ታጣቂ ቡድን” ተከታትሎ ለፀጥታ ሀይሉም ሆነ ለማኅበረሰቡ ስጋት እንዳይሆን በስልት መስራት ግዴታው እንደሆነ መንግስትን ልናስታውስ እንወዳለን፡፡
በግብር ከፋዩ ሕዝብ ሀብት የሚተዳደሩ የመንግስት የመገናኛ ተቋማት ግድያው በተፈፀመበት ወቅት አውቀውም ይሁን በስህተት በጉዳዩ ላይ ለሕዝብ የሰጡት በሀሰት የተቀናበረ መረጃ የተቋማቱን አደገኛ አካሄድ ዛሬም በግልፅ አሳይቷል፡፡ ሰፊ ተደራሽነት ያላቸውና የሕዝብ ሀብት የሆኑ የመንግስት ሚዲያዎች በጓዳቸው ካለ የትላንት ታሪካቸው ተምረው ለተቋቋሙበት ዓላማ፣ ለሕግና ለእውነት ብቻ እንዲሰሩ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ይህን እኩይ ተግባር በተሳሰተ መንገድ የዘገቡ ሚዲያዎች ሁሉ ሕዝብን ይቅርታ ጠይቀው የኮሚሽኑን ሪፖርት አልያም በራሳቸው መንገድ የተፈጠረውን ትክክለኛ ኩነት በድጋሜ ለሕዝብ እንዲያደርሱ እንጠይቃለን፡፡
ፍትህን በፅኑ እንጠይቃለን፡፡
ኢዜማ
ኢትዮጵያ

የፍልስጤም አስተዳደር ጠቅላይ ሚንስትር የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ለእስራኤል የሰጡትን የታዛቢነት መቀመጫ እና የዲፕሎማቲክ ውክልና የኅብረቱ መሪዎች ጉባዔ እንዲያነሳው ዛሬ በኅብረቱ ጉባዔ ላይ እንደጠየቁ የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ዘግቧል። ፍልስጤም የኮሚሽነሩ ውሳኔ እንዲሰረዝ የጠየቀችው፣ እስራዔል ባሁኑ ወቅት በፍልስጤማዊያን ላይ የአፓርታይድ ሥርዓት እንደዘረጋች በመግለጽ ነው። ኮሚሽነር ፋኪ የእስራኤልን በአፍሪካ ኅብረት የታዛቢነት እና የዲፕሎማቲክ ውክልና የማግኘት ጥያቄ የተቀበሉት ባለፈው ሐምሌ ሲሆን፣ የመሪዎቹ ጉባዔ ዛሬ ወይም ነገ በኮሚሽነሩ ውሳኔ ላይ ድምጽ ሳይሰጥ እንደማይቀር ዘገባው ጠቁሟል። ኮሚሽነሩ እስራዔልን በታዛቢነት በተቀበሉበት ወቅት በተለይ ደቡብ አፍሪካ እና አልጀሪያ ውሳኔውን በጽኑ በማውገዝ፣ በጉዳዩ ላይ የኅብረቱ መሪዎች ውሳኔ እንዲሰጥ መጠየቃቸው ይታወሳል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ሞሮኳዊውን ታዳጊ በህይወት ለመታደግ ሳይቻል ቀረ!
ካሳለፍነው ማክሰኞ ጥር 24 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ በድንገት በገባበት ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ያሳለፈው ሞሮኳዊው ታዳጊ ራያን በህይወት ሳይተርፍ ቀረ።አምስት ያህል ቀናትን 32 ሜትር ጥልቀት ባለው ጉድጓድ ውስጥ በህይወትና በሞት መካከል ውስጥ ሆኖ ያሳለፈውን የ5 ዓመቱን ታዳጊ በህይወት ለመታደግ የተደረጉ ጥረቶች ፍሬ ሳያፈሩ ቀርተዋል።
በከፍተኛ የአፈር ቆረጣና ቁፋሮ ርያንን ከቀናት በኋላ ከገባበት ጉድጓድ ለማውጣት ቢቻልም በህይወት ለማትረፍ ግን አልቻለም።ይህ ወላጆቹን ጨምሮ ሁኔታውን በቅርበት ሲከታተል የነበረውን የዓለም ህዝብ ያሳዘነ ነው።የሃገሪቱ ንጉሳዊ ቤተሰብ ርያን ማለፉን በይፋ አስታውቆ ሃዘኑን ገልጿል።ንጉስ መሐመድ ሳድሳዊ (6ኛ)ም ለርያን ወላጆች ደውለው አፅናንተዋል።
✍Alain

በጎንደር እና በባሕር ዳር ከተሞች በተፈጠረ አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ለውጥ ምክንያት የበረራ መስተጓጎል ማጋጠሙን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡
ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ የጠየቀው አየር መንገዱ ኹኔታውን በተመለከተ ለደንበኞቹ ወቅታዊ መረጃዎችን የሚያደርስ መሆኑን እንደገለጸ ኢዜአ ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ የጠየቀው አየር መንገዱ ኹኔታውን በተመለከተ ለደንበኞቹ ወቅታዊ መረጃዎችን የሚያደርስ መሆኑን እንደገለጸ ኢዜአ ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ትናንት እና ዛሬ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ጉባዔ እስራዔል በኅብረቱ ባላት የታዛቢነት መቀመጫ እና የዲፕሎማሲ ውክልና ላይ የመወያየቱን እና ድምጽ የመስጠቱን ሃሳብ ወደ ቀጣዩ ዓመት እንዳስተላለፈው ዓለማቀፍ ዜና ወኪሎች ዘግበዋል።
የመሪዎቹ ጉባዔ ድምጽ በመስጠት ፋንታ ጉዳዩን እንደገና አጥንቶ ለቀጣዩ ዓመት የኅብረቱ መሪዎች ጉባዔ የውሳኔ ሃሳብ የሚያቀርብ ኮሚቴ አቋቁሟል።
የኅብረቱ ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ እስራዔል በኅብረቱ የታዛቢነት መቀመጫ እና የዲፕሎማሲ ውክልና እንዲሰጣት ያቀረበችውን ጥያቄ፣ ለሰላም ጠቃሚ ርምጃ መሆኑን በመጥቀስ የተቀበሉት ባለፈው ሐምሌ ነበር። ፋኪ ለእስራኤል የታዛቢነት መቀመጫ መፍቀዳቸውን ተከትሎ፣ በተለይ ደቡብ አፍሪካ እና አልጀሪያ ውሳኔውን ክፉኛ በማውገዝ የኅብረቱ መሪዎች ጉባዔ የእስራዔልን የታዛቢነት መቀመጫ እንዲሰርዝ ሲወተውቱ ቆይተዋል።
በተመሳሳይ በኅብረቱ የታዛቢነት መቀመጫ ያላት ፍልስጤም እስራዔል ባሁኑ ወቅት በፍልስጤማዊያን ላይ የአፓርታይድ ሥርዓት እንደዘረጋች እና በፍልስጤማዊያን መከራ እና ግፍ እየፈጸመች መሆኗን በመጥቀስ የኅብረቱ መሪዎች የእስራዔልን የታዛቢነት መቀመጫ እንዲሰርዝ ትናንት በጠቅላይ ሚንስትሯ በኩል ጉባዔውን ጠይቃ ነበር። እስራዔልም በፊናዋ የኅብረቱ ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ያጸደቁላትን የታዛቢነት መቀመጫ ጥያቄ የመሪዎቹ ጉባዔ ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያጸድቀው ያደረገችው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
የመሪዎቹ ጉባዔ ጉዳዩን እንደገና አጥንቶ ለቀጣዩ ዓመት የውሳኔ ሃሳብ እንዲያቀርብ ያቋቋመው ኮሚቴ ደቡብ አፍሪካን፣ አልጀሪያን፣ ሩዋንዳን፣ ናይጀሪያም፣ ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክን እና ካሚሮንን ያቀፈ ነው። ዲፕሎማቶች እና ታዛቢዎች የመሪዎቹ ጉባዔ በጉዳዩ ላይ ድምጽ ከሰጠ፣ የኅብረቱ አባል ሀገራት ከሁለት ተቃራኒ ጎራ ሊከፈሉ ይችላሉ የሚል ስጋት ነበራቸው። የመሪዎቹ ጉባዔ የኮሚሽነር ፋኪን ውሳኔ መቀልበስ የሚችለው በ2/3ኛ ድምጽ ብቻ ነው።
[ዋዜማ ራዲዮ]

"ዛሬ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘ አክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጋር የተሳካ ውይይት አድርገናል።
ከቅድስት ቤተክርስቲያን በኩል የሚነሱትን ጉዳዮችን ህጋዊ ሰላማዊ መንገድ በውይይት መፍታት እንደሚቻል ተግባብተናል።ስለነበረን መልካምና ገንቢ ቆይታም ብፁዕነታቸውን ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።"
-ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
@YeneTube @FikerAssefa
ከቅድስት ቤተክርስቲያን በኩል የሚነሱትን ጉዳዮችን ህጋዊ ሰላማዊ መንገድ በውይይት መፍታት እንደሚቻል ተግባብተናል።ስለነበረን መልካምና ገንቢ ቆይታም ብፁዕነታቸውን ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።"
-ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
@YeneTube @FikerAssefa
ሴኔጋል በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆናለች።
120ደቂቃ ግብ ሳይቆጠር ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ባመራው ጨዋታ አንበሶቹ በሊቨርፑል አጥቂ ሳዲዮ ማኔ እየተመሩ ተጋጣሚያቸውን 4ለ2 በማሸነፍ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዋንጫው ባለቤት መሆን ችለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
120ደቂቃ ግብ ሳይቆጠር ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ባመራው ጨዋታ አንበሶቹ በሊቨርፑል አጥቂ ሳዲዮ ማኔ እየተመሩ ተጋጣሚያቸውን 4ለ2 በማሸነፍ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዋንጫው ባለቤት መሆን ችለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከዚህ (shein.com) website ላይ ያሉ ለሴት እና ለወንድ በተጨማሪም ለህጻናት የሚሆኑ እቃዎችን ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል ይዘዙን
Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
Forwarded from YeneTube
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ
አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
Forwarded from YeneTube
ሁሌም ወደተሻለ ሰው የመለወጥ ምርጫ በእጃችን ላይ ነው📈
.
.
.
The choice to be a better person is always in our hands 📈
JOIN our channel Telegram
https://tttttt.me/+qtDDnplBq9UzZGRk

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከሩሲያ ጋር ወደ ጦርነት ላለመግባት ስምምነት መድረስ የማይቻልና ሩቅ ነገር እንዳልሆነ ተናገሩ።
ማክሮን ጨምረው ሩሲያ የደኅንነት ስጋት እንዳለባት ማሳሰቧ ተገቢ ነው ብለዋል።ማክሮን ይህን ያሉት ዛሬ ሰኞ ቀጠሮ ከተያዘላቸውና ከቭላድሚር ፑቲን ጋር ከመነጋገራቸው ቀደም ብሎ በሰጡት ቃለ ምልልስ ነው።ማክሮን በምዕራቡና በሩሲያ መካከል አዲስ ሚዛን መፍጠር ያስፈልጋል፤ የአውሮጳ አገራትን ፍላጎትና የሩሲያን ፍላጎትም ማጣጣም ይቻላል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
ኾኖም ኢማኑኤል ማክሮን በሁለቱ ወገኖች ዘንድ ሚዛን ለማስጠበቅ ሲባል የዩክሬን ሉዓላዊነት ጉዳይ ለጥያቄ ይቀርባል ማለት እንዳልሆነ አስምረውበታል።ሩሲያ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ድንበር ማስጠጋቷ ከተገለጸ ወዲህ በአካባቢው የጦርነት ስጋት እንዳንዣበበ አለ።ሞስኮ አደጋው እንዲቀለበስ በርከት ያሉ ቅድመ ኹኔታዎችን ያቀረበች ሲሆን ከእነዚህ ዋናው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ወይም በምህጻሩ ኔቶ፣ ዩክሬንን አባል እንዳያደርግ የሚጠይቅ ነው።
Via BBC

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕወሓት አመራሮች ክስ ለምን እንደተቋረጠ ለፓርላማ ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተገለጸ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የሕወሓት አመራሮችን ክስ መንግሥት ለምን እንዳቋረጠ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በቅርቡ ማብራሪያ እንደሚሰጡ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ አስታወቁ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መንግሥት በታኅሳስ 2014 ዓ.ም. መጨረሻ በሦስት ክስ መዝገብ ጉዳያቸው ሲታይ ከነበሩ ተከሳሾች ውስጥ፣ ለሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች ያደረገው የክስ ማንሳት ውሳኔ፣ ‹‹ተጎጂዎችን ያላገነዘበ ውሳኔ ነው›› በማለታቸውና ከፍተኛ ክርክር በማስነሳቱ ነው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ እንደሚሰጡ የተገለጸው፡፡
Via Reporter

Kdamie.com ንግድ እና አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ፡፡
#ጅምላና ችርቻሮ ንግዶችን አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ከጨረታና ፐርፎርማ እንዲሁም የስራ ማስታወቂያዎች እና መረጃዎች ጋር፣
#በጉዞዎ መዳረሻዎችን ከነ አስጎብኚዎች እና የጉዞ ወኪሎች ጋር
#የእንግዳ ማረፊያ ሆቴልና ሪዞርቶችን ፈርኒሽድ አፓርታማዎችን ገሰት ሀውሶችን እና ፔንሲዮኖችን
ለመኖሪያ የሚሆኑ ቪላ እና ኮንዲሚኒየሞችን
#በሁሉም የገበያ ማዕከላት ለሱቅ እና ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎችን ሳይዞሩ ሳይደክሙ የሚያገኙበት Kdamie.com
#በንግድ በቱሪዝም እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ለሆኑ ድጅቶችም ኑ አብረን እንስራ ይሎታል Kdamie.com
ከኛ ጋር መስራት ንግድና አገልግሎቶን ማዘመን፣ደንበኞችዎን ባሉበት ማግኘት ነው!! Kdamie.com
#በሁሉም የማህበራዊ ገፆች
Telegrame እና whatsup - +251-911705126
Kdamie.com - https://tttttt.me/+K7sPcHhHYy44NDI0
facebook - https://www.facebook.com/Kdamie-107188781818909
Instagram - https://www.instagram.com/p/CZkVH-FAd11/?utm_source=ig_web_copy_link
Email - kdamiesells@gmail.com
phone:- +251911705126/+251916821091 ያገኙናል፡፡