የወሎ፣ የመቅደላ አምባና የወልደያ ዩኒቨርሲቲዎች በየካቲት ወር መጀመሪያ ላይ ተማሪዎችን ማስተማር እንደሚጀምሩ ሰምተናል
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ለኢዜአ እንደገለጹት በአማራ ክልል አሸባሪው ህውሓት በከፈተው ጦርነት ሳቢያ የወሎ፣ የመቅደላ አምባና የወልደያ ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማር ስራ አቋርጠዋል።
አሸባሪ ቡድኑ በወረራ በቆየባቸው ወራት ዩኒቨርሲቲዎቹን ዘርፎና አውድሞ መሄዱን አስታውሰው በዳግም ጥገና ስራ እንዲጀምሩ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል።
በመንግስት ድጋፍና ባላቸው አቅም አስፈላጊ ግዥዎችንና ጥገናዎችን እንዲያካሔዱ ከማድረግ ባለፈ አማራጭ የትምህርት ማስኬጃ መንገዶችንም እንዲያስቡና ወደ ስራ እንዲገቡ አሁንም ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በመሆኑም የወሎ፣ የመቅደላ አምባና የወልደያ ዩኒቨርሲቲዎች በየካቲት ወር መጀመሪያ ላይ ተማሪዎችን በመቀበል ዳግም ስራ የሚጀምሩ መሆኑን ዶክተር ሳሙኤል ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲዎቹ የመጨረሻ ዓመት ተመራቂ ተማሪዎችን ቀድመው በመቀበል ሌሎችንም በሚያወጡት መርሃ ግብር መሰረት የሚቀበሉ ይሆናል።
Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa

ሊጣሉ የሚችሉ ማእቀቦችን ያገናዘበ ዝግጅቶችን እያደረግን እንገኛለን - የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ
ዋሽንግተን በሩስያ በተለይም በፕሬዝደንት ፑቲን ላይ ማእቀብ እንደምትጥል በተደጋጋሚ ማሳወቋን ተከትሎ ሞስኮ ማእቀቡ ቢጣል እንኳን አስፈላጊ ናቸው ያለቻቸውን ዝግጅቶች ማጠናቀቋን አስታውቃች፡፡
ማእቀቦቹ የሃገሪቱ ባንኮች ላይም በዶላር እጥረት ሳቢያ ጉዳት እንዳያስከትል ዝግጅት መደረጉን ያስታወቁት ቃልአቀባዩ የአሜሪካ አካሄድ ተገማች ባለመሆኑ ጥንቃቄ የተሞላበትን ኢኮኖሚያዊ አካሄድ እየተከተልን እንገኛለን ብለዋል፡፡
ሩስያ በሚጣለው ማዕቀብ ሳቢያ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመወጣት ዝግጅት አድርጋለች ያሉት ዲሚትሪ ፔስኮቭ የማእቀቡ አይነት እና ጥንካሬው ባለመታወቁም በከፍተኛ ደረጃ ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል፡፡
ቃልአቀባዩ አክለውም ‹‹በድጋሚ መናገር እፈልጋለው! ዛሬም ቀውሱ እንዲባባስ አንፈልግም፡፡ አሜሪካም በአውሮፓ አህጉር የምትፈጥረውን ውጥረት እንድታቆም እንጠይቃለን›› ብለዋል፡፡
ብሉምበርግ እንደዘገበው ከሆነ ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች አሜሪካ እና አውሮፓ የሃገሪቱን ትልልቅ ባንኮችን ኢላማ ያደረገ ማእቀቦችን ለመጣል ማቀዳቸው እና ማእቀቦቹም ለባንኮቹ ዶላርን እንዳይሸጥ እስከማድረግ እና ምንም አይነት የውጭ ምንዛሬ እንዳይሸጥላት እስከማድረግ እንደሚደርስ ዘግቦ ነበር፡፡

በሞሮኮ 32 ሜትር ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የገባውን የአምስት አመት ህፃን ለማዳን ዛሬ ለሶስተኛ ቀን ቁፋሮ እየተከናወነ ነው
ባለፈው ማክሰኞ በሞሮኮ ገጠራማ ስፍራ ባለችው ባብ ቤርድ የአምስት አመቱ ራያን 32 ሜትር ጥልቀት ባለው ጉድጓድ በድንገት የገባ ሲሆን የነፍስ አድን ሰራተኞች በቁፋሮ ማሽን ልጁ ከገባበት አጠገብ ሌላ ጉድጓድ በመቆፈር ላይ ናቸው።ልጁ በደረሰበት ቦታ ትይዩ ቦታ ሲደርሱ አግድሞሽ ወደ ልጁ በመቆፈር ልጁን እናወጣዋለን ብለዋል።
ልጁ ሲንቀሳቀስ ታይቷል ሲሉ የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
እስከ አሁን 27 ሜትር ወደ ታች የቆፈሩ ሲሆን ከሰአታት በኋላ የቁፋሮ ስራቸውን ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለልጁ ኦክስጅን እና ምግብ በትቦ የተላከለት ሲሆን ከወጣ በኋላም ወደ ሆስፒታል ለመውሰድ ሂሊኮፕተር እና ዶክተሮች በስፍራው እየተጠባበቁ ይገኛል።
ነፍስ የማዳኑን ስራ በሞሮኮ የሚገኙ ቴሌቭዥኖች እንዲሁም ስካይ ኒውስ አረቢያ በቀጥታ ስርጭት እያሳዩት ይገኛሉ።
Via Fidel Post

ፋኖ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት አይደለም፣ ሕዝብን ያላማከለ ድርድርም አገርን አይጠቅምም ሲል ባልደራስ አስታወቀ!
ፋኖ በጭንቅ ጊዜ አገርን ከወረራ እና ከብተና የሚታደግ፣ በሠላም ጊዜ በየሙያ ዘርፉ ተሰማርቶ ሠላማዊ ኑሮውን የሚኖር ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ በዚህም መሠረት፣ ፋኖ፣ በጊዜያዊነት ተሰባስቦ በአገር ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ሙሉ በሙሉ እስከሚወገድ በዱር በገደሉ እየተሰማራ፣ አካባቢውንና አገሩን ከጥቃት የሚከላከል ህዝባዊ ኃይል እንጂ፣ቋሚ የሆነ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት አይደለም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ታሪካችን ብንጠቅስ እንኳን፣ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ወርሮ በነበረበት ጊዜ ይህ እውነታ በውል ታይቷል፡፡
ሐቁ ይህ ሆኖ እያለ፣ ለሀገሩ ሉአላዊነት የደም መስዋዕትነት ለመክፈል በከፍተኛ ወኔ ዝግጁ መሆኑን በተግባር ያስመሰከረውን የዘመናችንን ፋኖ፣ “ኢ-መደበኛ አደረጃጀት” በሚል ፍረጃ ወከባና ትንኮሳ እየተፈፀመበት ይገኛል፡፡
ይህ ድርጊት ባልተቋጨው ጦርነት በየምሽጉ በተጠንቀቅ የሚገኙትን ፋኖዎች የሚነካ ብቻ ሳይሆን፣ የመከላከያ፣ የልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላትን አንድነት፣ ሞራልና ቅስም የሚሰብር ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፣ ጫናውና ትንኮሳው ህወሓትን፣ ኦነግ/ሸኔን እና ሌሎች ፀረ-ኢትዮጵያ የሆኑ ቡድኖች እና ኃይሎችን ተጠቃሚ እና ደስተኛ፣ እንዲሁም ሞራላቸውን የሚያነቃቃ ነው፡፡
ከፌደራል መንግሥቱ የመከላከያ ኃይል ውጭ ያሉትን ታጣቂዎች ዕጣ ፈንታ በሚመለከት፣ ከጦርነቱ በኋላ በአገር አቀፍ ደረጃ በሚቀረጽ ፖሊሲ መወሰን ይገባል፡፡ እስከዚያው ድረስ፣ በፋኖ ላይ በተጠናጠል የሚፈፀሙ ትንኮሳዎች እንዲቆሙ በጥብቅ እንጠይቃለን፡፡ ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ መስዕዋትነት ከፍለው የአገርን ህልውና ለማስጠበቅ በተጠንቀቅ የቆሙ ልጆቹን ማንም እንዲነካበት አይፈልግም፡፡
በተጨማሪም፣ በመንግሥት እና በህወሓት መካከል በጎረቤት አገር ድርድር እየተካሄደ መሆኑ በተለያዩ ሚዲያዎች እየተገለፀ ይገኛል፡፡ ድርድሩን ከጥርጣሬ ነፃ ለማድረግ የሚከተሉትን ሰባት ምክረ-ሃሳቦች እናቀርባለን፡-
1/ ድርድሩ ለሕዝብ ግልጽ እንዲሆን፣ ሂደቱንም ሊከታተል በሚችልበት አውድ እንዲደረግ፣
2/ የአፋር እና የአማራ ክልላዊ መስተዳድሮች በድርድሩ ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው የሚያስችል አካሄድ እንዲኖር፣
3/ በሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ በፖለቲካ ድርጅቶች የጋራ መድረክ በኩል በቂ መረጃ የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች፣
4/ የአገር ሽማግሌዎች ሂደቱን በታዛቢነት እንዲከታተሉ፣
5/ የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን በማህበሮቻቸው በኩል ሂደቱን በታዛቢነት እንዲከታተሉ፣
6/ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሂደቱን በታዛቢነት እንዲከታተል፣
7/ ለመገናኛ ብዙሃን በቂ መረጃ የሚደርስበት ሁኔታ እንዲመቻች የሚሉት ናቸው፡፡
የአገራችን ህልውና አደጋ ላይ ወድቆ በነበረበት ጊዜ፣ መንግሥት በተደጋጋሚ የድረሱልኝ ጥሪ አቅርቦ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ምላሽ እንደሰጠው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ አደጋው በተወሰነ ደረጃ ከተቀለበሰ በኋላ፣ መንግሥት ሕዝቡን በአገለለ መልኩ ለመጓዝ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ መጨረሻው መንግሥትንም ሆነ አገርን የሚጠቅም ባለመሆኑ፣ አስቸኳይ እርምት እንዲረግበት በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ድል ለኢትዮጵያ!!!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ
@YeneTube @FikerAssefa

በአማራ ክልል ጦርነቱ ባስከተለው ጉዳት ከ11 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ዜጎች እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል ሲል የክልሉ መንግስት አስታወቀ።
የሕወሓት የሽብር ቡድን በፈፀመው ወረራ ሳቢያ የተፈናቀሉ ዜጎችን ነጻ በወጡ ስፍራዎች ወደ ቀያቸው መመለስ ቢቻልም ቡድኑ ዜጎችን ጥሪት አልባ በማድረጉ ከእርዳታ ጠባቂነት ማላቀቅ አልቻልኩም ብሏል።
በአሁኑ ስዓት እነዚሁ ዜጎችን ለመመገብም በየወሩ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል እህል በላይ እንደሚያስፈልግ የክልሉ አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኢያሱ መስፍን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
የክልሉ መንግስት የተለያዩ አካላትን በማስተባበር የጉዳቱ ሰለባ የሆኑ ዜጎች አምርተው ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥልም አሳውቀዋል፡፡
ምንም እንኳን በዚህ ሂደት የመንግስት ድርሻ ከፍተኛ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አኳያ ግን የሌሎች ረጅ ተቋማት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ገልፀው ለዚህም የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
ችግሩ የክልሉ ብቻ እንደሆነ ማሰብ ተገቢነት የለውም መላው ኢትዮጰያዊያን በጦርነቱ ያሳዩትን መተባበርም በመልሶ ማቋቋሙ ሂደት እንዲደግሙት ጥሪ አቅርበዋል።የተገለጸው አሃዝ በክልሉ ነጻ በወጡ ስፍራዎች ብቻ መሆኑን አሳውቀው አሁንም ድረስ በጠላት እጅ በሚገኙ ስፍራዎች ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ዜጎች በችግር ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡
[አሐዱ]

በበሻሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምን ተከሰተ ?
በዛሬው እለት በበሻሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከቀኑ 6ሰአት አካባቢ አንዲት ተማሪ ከአራተኛ ፎቅ ላይ እራሷን ጥላለች፡፡
እራሷን ከፎቅ ላይ የጣለችው ተማሪ ወዲያወኑ ወደ ሆስፒታል የተወሰደች ሲሆን በጊዜው ሂይወቷ አለማለፉን ተመልክተናል፡፡የተማሪዋ መውደቅ ተከትሎ በስፍራው የነበሩ በርካታ ተማሪዎች እራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡
የአስረኛ ክፍል ተማሪ እንደሆነች የተነገረው ተማሪዋ ከቤተሰቦቿ ተጣልታ ወደ ትምህርት ቤት መምጣቷን ነው የተነገረው፡፡ኢትዮ ኤፍ ኤም የትምህርት ቤቱን መምህራን አግኝቶ ስለተፈጠረው ክስተት የጠየቀ ሲሆን ተማሪዋ እንደተባለው ከቤተሰብ ጋር ተጣልታ ነው ለዚህ ውሳኔ የደረሰችው ብለውናል፡፡
ቁጥራቸው ከ100 በላይ የሚደርሱ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በተለይም የልብ ድካም እና ድንጋጤ የተሰማቸው ተማሪዎች አቅራቢያ ወደ ሚገኙ ሆስፒታሎች እየተወሰዱ ኢትዮ ኤፍ ኤም በስፍራው ሆኖ ተመልክቷል፡፡የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትም በትምህርት ቤቱ የተፈጠረውን ክስተት ለማጣራት ቦታው ደርሰው ጉዳዩን እያጣሩ ነበር፡፡
Via Ethio FM

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ህብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ምክር ቤቱ ዝርዝራቸውን ይፋ አድርጓል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለወጋገን ባንክ የአዲስ ፕሬዝደንት ሹመት ይሁንታ ሰጠ!
በዚህም መሰረት ባንኩን ለ6 ወራት በተጠባባቂ ፕሬዝደንትነት ሲመሩ የነበሩት አቶ አክሊሉ ውበት ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አነስቶ በፕሬዝደንትነት ወጋገንን መምራት ጀምረዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
በዚህም መሰረት ባንኩን ለ6 ወራት በተጠባባቂ ፕሬዝደንትነት ሲመሩ የነበሩት አቶ አክሊሉ ውበት ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አነስቶ በፕሬዝደንትነት ወጋገንን መምራት ጀምረዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
በፀጥታ ችግር ምክንያት የ2013 ዓ.ም አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ላልወሰዱ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው ፈተና በሰላም ተጠናቅቋል።
የህወሃት የሽብር ቡድን እና ተባባሪዎቹ በፈጠሩት የፀጥታ ችግር ምክንያት በ2013 ዓም ፈተናውን መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች በሁለተኛ ዙር ከጥር 24/2014 ጀምሮ ፈተናውን ሲወስዱ ቆይተዋል።
ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በአፋርና በቤንሻንጉል ክልል በ189 የፈተና መስጫ ጣቢያዎች የተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና ካለምንም እንከን በሰላም መጠናቀቁን ተናግረዋል።
ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ላበረከቱ የፀጥታ አካላት፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች እና የክልል ትምህርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ እየጨመረ በመጣው ድርቅ ሳቢያ ከ6.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ይሻሉ ተባለ።
የጀርመኑ የዜና ወኪል/ dpa) የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍን ጠቅሶ ከናይሮቢ እንደዘገበው ድርቁ በሀገሪቱ ስድስት አካባቢዎችን ያጠቃው ድርቅ ለሶስት ዝናባማ ወቅቶች የዘለቀ በመሆኑ የ የውሃ ጉድጓዶች መድረቃቸውን ፣እንስሳት መሞታቸውንና እና የሰብል ምርት መውደሙን አስታውቋል።እንደ ድርጅቱ በድርቁ ከፍተኛ ጉዳት በደረሰባቸው የኦሮሚያ ፤ሶማሌ ክልሎች ወደ 225,000 የሚጠጉ ህፃናት እንዲሁም ከ100,000 በላይ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ለተመጣጠነ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል። በመሆኑም ተጎጅዎቹ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ድርጅቱ አመልክቷል።ይህ ቀውስ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በተፈጠረው ግጭት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አደጋ ላይ በሚወድቁባት እና የ115 ሚሊዮን ሀገር በሆነችው ኢትዮጵያ ችግሩን ሊያባብሰው ይችላል ሲል ዩኒሴፍ ስጋቱን ገልጿል።
Via DW

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ በኅዳር ወር በምዕራብ ሸዋ ዞን የተገደሉ 14 የከረዩ ኦሮሞ አባገዳ አባላትን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣውን ሪፖርት በበጎ መልኩ እንደሚቀበለው ለመገናኛ ብዙኀን አስታውቋል። ግለሰቦቹ በተገደሉበት ወቅት የክልሉ ፖሊስ ገዳዮቹ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው የሚል መግለጫ እንዳልሰጠ እና ከፖሊስ ኮሚሽኑ መግለጫውን የሰጠ አካል ከነበረ ስህተት እንደሆነ የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን ተናግረዋል። በግድያው እስካሁን 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ተገልጧል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን 14ቱን ሰዎች ያለ ፍርድ የገደሏቸው የክልሉ ፖሊሶች እንደሆኑ አረጋግጫለሁ ማለቱ ይታወሳል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከዚህ (shein.com) website ላይ ያሉ ለሴት እና ለወንድ በተጨማሪም ለህጻናት የሚሆኑ እቃዎችን ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል ይዘዙን
Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ
አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga

ሁሌም ወደተሻለ ሰው የመለወጥ ምርጫ በእጃችን ላይ ነው📈
.
.
.
The choice to be a better person is always in our hands 📈
JOIN our channel Telegram
https://tttttt.me/+qtDDnplBq9UzZGRk

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ
የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ሳሚ ሹክሪ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ሹም አምባሳደር ፈይሰል አሊይ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
Via:- EBC

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል
35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ቅዳሜ ጥር 28 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይጀመራል፡፡
በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ያለፉትን ሁለት ዓመታት ተቋርጦ የቆየውን ጉባዔ የህብረቱ አባል ሃገራት መሪዎች በአካል ተገኝተው ነው የሚያካሂዱት፡፡
ጉባዔው የህብረቱ ስራ አስፈጻሚ የተወያየባቸውን ረቂቅ አጀንዳዎች ጨምሮ በሌሎችም ጉዳዮች ላይ መክሮ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡
የህብረቱ አዲሱ የዓመቱ (2022) ሊቀመንበር በይፋ ኃላፊነት የሚረከበውም በዚሁ ጉባዔ ነው፡፡
እስራኤል በህብረቱ የታዛቢነት ሚና እንዲኖራት ያቀረበችው ጥያቄም ምላሽ ያገኛል፡፡
Via:- Al Ain
@Yenetube @Fikerassef

በፓኪስታን አየር መንገድ የእረፍት ሰዓቴ ነዉ በሚል በረራ ያቋረጠዉ ፓይለት መነጋገሪያ ሆኗል
የፓኪስታን ኢንተርናሽናል አየር መንገድ (ፒአይኤ) አብራሪ በድንገተኛ አደጋ አዉሮፕላኑ ካረፈ በኋላ በረራው አብቅቷል በማለት ከዚህ በላይ ለመብረር ፈቃደኛ እንዳልሆነ አስታዉቋል። ዘ ኤክስፕረስ ትሪቡን እንደዘገበው በበረራ ቁጥሩ ፒኬ -9754 የሚታወቀዉ አዉሮፕላን መነሻዉ ከሳዑዲ ሪያድ ከተማ ሲሆን መዳረሻዉ በፓኪስታን መዲና እስላማባድ ነበረ።
ይሁን እንጂ የነበረዉ መጥፎ የአየር ሁኔታ አብራሪው በሳውዲ አረቢያ ዳማም ከተና እንዲያርፍ አስገድዶታል.፡፡አብራሪው በድንገተኛ አደጋ አዉሮፕላኑን ካሳረፈ በኋላ ለመብረር ፈቃደኛ ባለመሆኑ ችግሮች ይፈጠራሉ፡፡ፓይለቱ የስራ ሰዓቴ አብቅቷል በማለት በረራውን ለመቀጠል ፈቃደኛ አለመሆኑን ይገልጻል፡፡
በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ለመውረድ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የጉዞ መዘግየትን ቢቃወሙም ፓይለቱ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ወደ ፓኪስታን ኢስላማባድ የሚያደርጉትን ጉዞ እስኪቀጥሉ ድረስ መንገደኞች በሆቴል ውስጥ እንዲያርፉ ተደርጓል፡፡
የፓኪስታን አለም አቀፍ አየር መንገድ ቃል አቀባይ ለ ገልፍ ኒውስ እንደተናገሩት አንድ አብራሪ ማረፍ አለበት ምክንያቱም ለበረራ ደህንነት አስፈላጊ ስለሆነ ከማለት ዉጪ ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
ዳጉ ጆርናል