YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የወንጌላውያን ህብረት ለተፈናቀሉ ወገኖች ያሰባሰበውን 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረከበ::

ህብረቱ በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ከአማኞች የተሰበሰበውን 10 ሚሊየን ብር ነው በዛሬው እለት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስረከበው፡፡ድጋፉን ያስረከቡት የዘፀዓት ቤተክርስቲያን መሪ ፓስተር ዩሃንስ ግርማ ÷ የከተማ አስተዳደሩ ባደረገው ስለኢትዮጵያ ጥሪ የበኩላችንን ምላሽ ለመስጠት በርካታ ምእመናን በነቂስ በመሳተፍ ለወገኖቻቸው ያላቸውን አጋርነት ያላቸውን በማዋጣት አሳይተዋል ብለዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ፥ የተጎዱ ወገኖቻችንን በአንድነት ማቋቋም ይገባል በማለት የከተማ አስተዳደሩ ይህን ተግባር የሚመራ አንድ ግብረሃይል አቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱን አስታውሰው ይህንን ጥሪ ሰምተው ምላሽ የሰጡትን የወንጌላውያን ህብረት አመስግነዋል፡፡
የከተማው አስተዳደርም የጀመረውን ተጎጂዎችና ተፈናቃዮችን የማቋቋም ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውንም ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በሶማሊያ ዓለም አቅፍ አየር ማረፊያ አቅራቢያ የቦምብ ፍንዳታ ጥቃት ተፈጸመ!

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ በትንሹ ስምንት ሰዎች መሞታቸውን የነፍስ አድን ሰራተኞች ገለጽዋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው በአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ነው ተብሏል።

ፍንዳታው የተፈፀመው ለዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቅርብ በሆነው የሶማሊያ አየር ሀይል ካምፕ መግቢያ በር ላይ ባለው መንገድ ላይ ነው።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ ፍንዳታው በጣም ግዙፍ ከመሆኑ የተነሳ በመንገዱ አቅራቢያ የሚገኙትን ሕንፃዎች እና በአካባቢው የሚያልፉ ተሽከርካሪዎችን መውደማቸውን አመላክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከእስር የተለቀቁት የኦፌኮ አመራር አቶ ደጀኔ ጣፋ የተፈቱበት ክስተት ያልጠበቀና የማይታመን እንደነበር ተናግረዋል።

ፖለቲከኛው በመንግሥት ዓርብ ዕለት ምሽት ድንገት ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር የተለቀቁት ፖለቲከኞች ክስተቱ ያልጠበቀና የማይታመን እንደነበር ተናግረዋል፡፡የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ደጄኔ ጣፋ ውሳኔው የሚበረታታ እንደሆነ ገልጸው ፍሬ እንዲያመጣ የዓላማው ቀጣይ ሂደት ላይ እንድያተኮር ጠይቀዋል፡፡ፖለቲከኛው የእስሩ ገጠመኞቻቸውን በገለጹበት ቃለ ምልልሳቸው በይቅርታ መንገድ መወያየት እና መደራደር በኢትዮጵያ ለራቀው ሰላምና መረጋጋት እልባት ያመጣል ብለው እንደሚያምኑም ገልጸዋል፡፡

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
55 ሺህ 3 መቶ 42 ልጃገረዶች ሊከተቡ ነው፡፡

የማሕፀን ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት የሚሰጣቸው 14 አመት ለሞላቸው ልጃገረዶች ነው፡፡የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ እንደገለፁት ከሆነ ባለፉት ሦስት አመታት ክትባቱ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡በአገር አቀፍ ደረጃ 3 ነጥብ 6 ሚሊየን እንደ ከተማ ደግሞ 1 መቶ 50 ሺህ ለሚሆኑ ልጃገረዶች ክትባቱ እንደተሰጠ ቢሮው አስታውቋል፡፡ክትባቱ 14 ዓመት ለሞላቸው ልጃገረዶች በስድስት ወር ልዩነት ውስጥ ሁለት ጊዜ ይሰጣል፡፡

[አሐዱ]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ውሳኔ የመሳለፍ መብት የለውም" - አቶ እስክንድር ነጋ!

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ ይህን ያሉት በፅ/ቤታቸው ዛሬ ጥር 5 ቀን 2014 ዓ.ም በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

መግለጫው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠው መግለጫ የፌደራሉ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ያሳለፈውን ውሳኔ ኮንኗል።

"እስከ 200ሺህ የሚጠጋ የህወሓት ታጣቂዎች ከባድ የጦር መሣሪያዎች ጭምር አንግበው፣ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ወቅት ያሳለፈው ውሳኔ ተቀባይነት የለውም" ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ "የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ውሳኔ የማሳለፍ መብት የለውም" ሲሉ ወቅሰዋል።

"የኢትዮጵያ ህዝብ ኢትዮጵያ አትፈርስም ብሎ ወደ ግንባር ዘምቶና ተመን የለሽ መስዋዕትነት ከፍሎ እያለ ያሳለፈው ውሳኔ ተቀባይነት የለውም" ብለዋል።

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች በመጪዎቹ ቀናት ወደ አፋርና አማራ ክልሎች እንደሚሄዱ አሻም ለማወቅ ችላለች።

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
የማዕድን ሚኒስቴር ከተለያዩ ኩባንያዎች ጋር 8 የድንጋይ ከሰል ምርት ስምምነቶችን ተፈራረመ!

የማዕድን ሚኒስቴር በዛሬው እለት 6 ቢሊዮን ብር ካፒታል ካስመዘገቡ የተለያዩ ኩባንያዎች ጋር 8 የድንጋይ ከሰል ምርት ስምምነቶችን ተፈራርሟል። ፕሮጀክቶቹ ሀገራዊ ናቸው ያሉት የማዕድን ሚኒስትሩ ኢ/ር ታከለ ኡማ ኩባንያዎቹም ይህንኑ ተገንዝበው ፕሮጀክቶቹን በተቀመጠላቸው ጊዜ እንደሚያጠናቅቁ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።ለስምምነቶቹ ውጤታማነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ኢ/ር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አረጋግጠዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ከቀረጥ ነጻ መገበያት የሚቻሉ ሸቀጦችን እና አገልግሎቶችን የመለየት ስራ ከግል ዘርፉ ጋር ተሰርቶ ተጠናቀቀ!

ከአመት በፊት ወደ ትግበራ የገባውን አህጉራዊ የንግድ ቀጠና ለመተግበር የሚረዳ የሸቀጦች እና አገልግሎቶች ልየታ ስራ ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡መንግስት በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መሪነት የትኞቹ ምርቶችን እና አገልግሎቶች ክፍት ለገበያ ክፍት ይሁኑ ሲል ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ እና ማጠናቀቁን መግለፁ ይታወሳል፡፡

በቀጣይ የግሉ ዘርፍ የትኛው ዘርፍ በአጭር ጊዜ የትኛው በሂደት ይከፈት ወይም የትኛው ዘርፍ ጨርሶ አይከፈት የሚለውን ግብአት ሲሰጥ ቆይቶ መጠናቀቁን በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ድርድር ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሙሴ ምንዳዬ ተናግረዋል፡፡አቶ ሙሴ ለካፒታል እንደተናገሩት ከግሎ ዘርፍ የተገኘው አስተያየት ከተወሰኑ የተለዩ ሃሳቦች በስተቀር ሙሉ ለሙሉ ከመንግስትን ልየታ ጋር የተናበበ ነበር፡፡

የተሰጡ ለየት ያሉ ሃሳቦችን በሰነዳችን አካተን እንዲጸድቅ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ በዚህ ሳምንት እናስገባለን፣ ሲሉ አቶ ሙሴ ተናግረው ሰነዱ በጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ከፍተኛ አማካሪ እና የንግድ ጉዳዬች ዋና ተደራዳሪ ሆኑት አቶ ማሞ ምህረቱ አማካኝነት ለብሄራዊ ማክሮኢኮኖሚ ኮሚቴ ቀርቦ በቅርቡ እንደሚጸድቅ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና 90 በመቶ ሸቀጦች እና አገልግሎቶች የጋራ ነጻ ቀጠናው ወደ ትግበራ እንደገባ ክፍት እንዲሆኑ የሚያስገድድ ሲሆን ከቀሪው 10 በመቶ 7 በመቶ የሚሆነው በሂደት የሚገባ ይሆናል፡፡ቀሪው 3 በመቶ የሚሆነው ግን ለአአገራቱ ዝግ እንዲያደርጉ የተፈቀደ ነው፡፡እስካሁን 27 አገራት ልየታቸውን የጨረሱ ቢሆንም የንግድ እንቅስቃሴያቸው እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገው፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አኒከን ሁይትፌልድት ጋር በስልክ ተወያዩ።

አቶ ደመቀ ለኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ እየታዩ ስላሉ ለውጦች ገለጻ አድርገዋል።ኖርዌይ በጥር ወር በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሆና መመረጧን ተከትሎም የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፥ ኖርዌይ የምክር ቤቱ ፕሬዚደንትነቷን በመጠቀም የኢትዮጵያ መንግስት እያከናወነ ያለውን ተግባር ሚዛናዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ እንደምትመለከተው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።አቶ ደመቀ አክለውም፥ አገሪቱ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንትነቷ በጎ ሚና እንደምትጫወት ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልፀውላቸዋል።

የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አኒከን ሁይትፌልድት ፥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ለሰጡት መግለጫ አመስግነው ፥ የኢትዮጵያ መንግስት ጥረትን አድንቀዋል።አኒከን ሁይትፌልድት ፥ በቀጣይም ኖርዌይ ኢትዮጵያን በተመድ አጀንዳ የማድረግ እቅድ እንደሌላትም ማስታወቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ማረሚያ ቤቱ ኬሪያ ኢብራሂም ባቀረቡት አቤቱታ ላይ መልስ ሰጠ!

በስልክ በትግረኛ ቋንቋ ለማውራት እና ማስታወሻ ደብተር እንድንይዝ ይፈቀድልን ሲሉ ኬሪያ ኢብራሂም ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ማረሚያ ቤቱ መልስ ሰጠ።በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ለዛሬ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር በ6 ተከሳሾች በተነሱ አቤቱታዎች ላይ መልስ እንዲሰጥ በያዘው ቀጠሮ ችሎቱ የተሰየመ ሲሆን፤ አቤቱታ አቅርበው ከነበሩ ስድስት ተከሳሾች ውስጥ 11 ኛ ተከሳሽ ሙሉ ገ/እግዛብሔር ክሳቸው በመቋረጡ አቤቱታቸው ታልፏል።

በዛሬው ቀጠሮ 8ኛ ተከሳሽ ኬሪያ ኢብራሂም እና 19 ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በህመም ምክንያት በችሎት ያልቀረቡ ሲሆን 20ኛ ተከሳሽ አሰፉ ሊላይ 43 ኛ ተከሳሽ ተክላይ አብርሐ እና 44 ኛ ተከሳሽ ዘሚካኤል አንባዬ ግን ቀርበዋል።የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር የቀድሞ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዬ የነበሩት ኬሪያ ኢብራሂም በትግረኛ ቋንቋ ስልክ ለማውራት ስለተከለከልን እንዲፈቀድልት ይታዘዝልን ስሉ ያቀረቡትን አቤቱታን በተመለከተ ማረሚያ ቤቱ በስልክ ማውራትም የተከለከለው ለአገሪቷ ደህንነት ክትትል ስለሚደረግ መሆኑን በጽሁፍ ምላሽ ሰቷል።

በተጨማሪም በማስታወሻ ደብተር ተከልክለናል ሲሉ ባቀረቡት አቤቱታ ላይም ማረሚያ ቤቱ ከፍርድ ቤት ማህተም ካለበት ሰነድ ውጪ መያዝ የተከለከለው በደህንንነት መከታተያ ስርዓት መሰረት መሆኑን ምላሽ ሰቷል።መንጃ ፍቃዴንና ፖስፖርቴን አ/አ የሚኖር ለአንድ የዩንቨርስቲ ተማሪ ዘመዴ እንዲያሳድስልኝ በማረሚያ ቤት ስለተከለከልኩ እንዲፈቀድልኝ ሲል 43 ኛ ተከሳሽ ተክላይ አብርሐን ባቀረበው አቤቱታን በተመለከተ ማረሚያ ቤቱ የሚፈቀደው በኗሪነት መታወቂያ ብቻ በመሆኑን በጽሁፍ ምላሽ ሰቷል።

20ኛ ተከሳሽ የቀድሞ የትግራይ ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አሰፉ ሊላይ በባለፈው ቀጠሮ ለሶስት ወር በፖሊስ እጅ መቆየታቸውን ጠቅሰው ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀው ነበር።በዕለቱ በፍርድ ቤቱ ምላሽ እንዲሰጥ የታዘዘው ዓቃቢህግ በበኩሉ ተከሳሿ በነሀሴ 11 ቀን 2013 በህገወጥ መንገድ ወደ ውጪ አገር ሊወጡ ሲሉ በፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ጠቅሶ በነሀሴ 12 ቀን ደግሞ ጉዳያቸው ተሰብሮ በተከሰሱበት የክስ መዝገብ ወደ ክርክር እንዲገቡ ለፍርድ ቤቱ ማሳወቁን በማስረጃ አስደግፎ ምላሽ ሰቷል።

በሌላ በኩል ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በዚሁ መዝገብ ከተከሰሱ ሌሎች ተከሳሾች ጋር በአንድ ማረሚያ ቤት ነገር ግን በተለያዩ ቦታዎች መታሰራቸውን ተከትሎ ተገናኝተው ለመወያየት አለመቻላቸውን ጠቅሰው ተገናኝተው ለመወያየት እንዲፈቀድላቸው ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ማረሚያ ቤቱ መልስ ሳይሰጥ ማለፉ ተገልጿል።ይሁንና ማረሚያ ቤቱ በቀጣይ ከቀጠሮ ስስት ቀን በፊት በዶ/ር ሰለሞን የቀረበው ተከሳሾች ተገናኝተን ለመወያየት ይፈቀድልን የሚለው አቤቱታ ላይ ምላሹን አካቶ እንዲቀርብ ታዟል።

ዛሬ በችሎት የተገኘው የተከሳሾች ጠበቃ ወንደሰን በቀለ ኬሪያ ኢብራሂም በስልክ በትግረኛ ቋንቋ ማውራት ህገመንግስታዊ መብታቸው መሆኑን በማብራራት ክልከላው ሰብዓዊ መብታቸውን የሚጋፋ እና ህግን የተከተለ አደለም ሲል መቃወሚያ አሰምቷል።

ጠበቃ ወንደሰን የግል ማስታወሻ ደብተራቸው ላይ ጽፈው አዘጋጅተው ፍርድ ቤት ይዞ የመምጣት መብት እንዳላቸው በመግለጽ እየተፈተሽ መከልከሉ የግል ነጻነታቸውን የሚጋፋ ጫና የሚፈጥር አሰራር ነው ሲል ጠበቃቸው ለማረሚያ ቤቱ ጥብቅ ትዛዝ እንዲሰጥለት ፍርድ ቤቱን መጠየቁን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛው በማህበራዊ የትስስር ገጿ ላይ አስፍራለች።ፍርድ ቤቱም አቤቱታ በቀረበባቸው ጉዳዮች ብቻ መርምሮ ትዛዝ ለመስጠት ለጥር 17 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱም ታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አዲስ አመራር ሾሙ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቶ ጌታቸው መንግስቴን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሹመዋል።

እንዲሁም አቶ መንግስቱ ንጉሴን የኤር ናቪጌሽን የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ እስከ ጥር 13 ቀን 2014ዓ.ም ድረስ መራዘሙን የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አስታወቀ፡፡

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ማጽደቁ የሚታወስ ሲሆን÷ በዚሁ መሠረት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ከታህሳስ 26 እስከ ጥር 6 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡እስካሁን ዕጩ ኮሚሽነሮችን ለመጠቆም ዜጎች ያሳዩት ተነሳሽነትና እያደረጉ ያሉት ተሳትፎ የሚያበረታታ ነው ብሏል ምክር ቤቱ፡፡

ይሁንና ኮሚሽኑ ከሚኖረው ከፍተኛ ሀገራዊ ኃላፊነት አንፃር ተጨማሪ ዕጩዎችን ህዝቡ እንዲጠቁም እንዲሁም የአገሪቱን ብዝሃነት ታሳቢ በማድረግና በተለያዩ ምክንያቶች መጠቆም ላልቻሉ ዜጎች ዕድሉን ለመስጠት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ እስከ ጥር 13 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን ገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ዋስትና ከባንክ ብድር የመውሰድ አገልግሎት ተጀመረ፡፡

ምቹ የሚል ስያሜ የተሰጠውን ዲጂታል የብድር አገልግሎትን በጋራ መስጠት መጀመራቸውን የተናገሩት የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ እና ክፍያ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ናቸው፡፡ምቹ የብድር መጠየቂያ እና ማግኛ መተግበሪያ ሲሆን አጠቃቀሙም በሞባይል ስልክ ላይ በመጫን ነው፡፡

ብድር ጠያቂው በመተግበሪያው ላይ ጥያቄው ያቀርባል፣ ብድሩን ለማግኘት የሚጠየቁ መስፈርቶች ይሞላል መተግበሪያው በደቂቃዎች ውስጥ ውጤቱን ያሳውቃል ተብሏል፡፡ጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ የሥራ መስኮች ያለ ዋስትና ብድሩ የቀረበላቸው ሲሆን እንደ ስራው ዓይነትና የመመለሻ ጊዜ የብድር መጠኑ ከ30,000 ብር እስከ 150000 ብር እንደሚደርስ ሰምተናል፡፡ጉዳዩን በተመለከተ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክና ፕሬዝዳንትና ክፍያ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ስራ አስፈፃሚ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን እንደ መሳሪያ በመጠቀም ያለ አግባብ የታሰሩ ዜጎች መኖራቸውን አረጋግጫለሁ ሲል ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ አዋጁን ተገን በማድርግ የተለያዩ ጫናዎች የሚፍጥሩ አካላት መኖራቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ወቀሳ እንዳቀረቡለት ገልጿል፡፡በተለይም በደቡብ ክልል ኢዜማን ጨምሮ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ ማቅረባቸውን አስታውሶ ለቅሬታው ምላሽ የሚሰጥ አጣሪ ቡድን አቋቁሜ ችግሮችን ለማየት ሞክሪያለሁ ብሏል፡፡

ባደረገው ጥናትም የታሰሩ ዜጎችን መኖራቸውን ማረጋገጥ መቻሉን ጠቁሟል፡፡በደቡብ ክልል የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት እና መሪዎች መታሰራቸውንም ባቀረበው ሪፖርት ላይ ምርጫ ቦርድ አመላክቷል፡፡በሌላ በኩል አንዱ ሲፈታ ሌላው የማሰር አዝማሚያም አስተውያለሁ ብሏል።አንዳንዶቹ ታሳሪዎች የት እንዳሉ ጭምር ለማወቅ አለመቻሉም በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

[አሐዱ]
@YeneTube @FikerAssefa
በነፃ በመመዝገብ የሁሉታክሲ ቤተሰብ ይሁኑ!!

የሜትር ታክሲ አገልግሎት እየሰጣችሁ ያላችሁ ኮድ 1 እና ኮድ 3 ባለንብረቶች ቀድማችሁ በመመዝገብ የሁሉታክሲ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

በነፃ ለመመዝገብ:
0901339955 ፤ 0902339955
ወይም @Hulutaxiregistration ላይ በቀላሉ በቴሌግራም በመላክ መመዝገብ ይችላሉ።

ሁሉም በሁሉግራም ይቻላል።
Download Hulugram SuperApp
👇

https://play.google.com/store/apps/details?id=plus.ride.huluchat
ተቃዋሚው የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለአፋር ክልል የጦርነት ተጎጅዎች ባግባቡ እየደረሰ አይደለም ሲል ትናንት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መግለጫ ከሷል። የምግብ ዕርዳታ ለተረጅዎች ሳይከፋፈል መጋዘን ውስጥ ታሽጓል ያለው ፓርቲው፣ የዕርዳታ ክፍፍሉ ለፓለቲካ ትርፍ እና ለፖለቲካ ምስለ ግንባታ ሲባል ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ወድቋል በማለት ወቅሷል። የሰሜኑ ጦርነት በአፋር ክልል ላይ ያደረሰው መጠነ ሰፊ ውድመት የክልሉ መንግሥት ከገለጸው በላይ እንደሆነ እና የመልሶ ግንባታ እና ማቋቋም ሥራዎችን ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ ያለ ሌላ ገለልተኛ አካል እንዲያከናውናቸው ፓርቲው አክሎ ጠይቋል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
ስፖርት!

በመካሄድ ላይ በሚገኘው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 1 ሁለተኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በዳዋ ሁቴሳ ጎል መሪነቱን ቢወስድም ብዙም ሳይቆይ በአዘጋጇ ካሜሩን የአቻነት ግብ ተቆጥሮበታል።

በአሁኑ ሰአት ጨዋታው በአቻ ውጤት ቀጥሏል።

@YeneTube @FikerAss
የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ሥልጣን እንዲለቁ ግፊቱ በርቶባቸዋል ተባለ፡፡

ቦሪስ ጆንሰን ስልጣን እንዲለቁ ግፊቱ የበረታባቸው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክልከላ እና ገደቡን ተላልፈው ሰዎች በዙበት የፈንጠዝያ ዝግጅት ላይ ተገኝተዋል ተብለው ነው፡፡አጋጣሚው ካቻምና የተፈጠረ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡

የራሳቸው የወግ አጥባቂዎቹ የፖለቲካ ማህበር ሹሞች ሳይቀሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን እንዲለቁ እየጎተጎቱ መሆኑን ስፑትኒክ ፅፏል፡፡

ቦሪስ ጆንሰን ስለ ሆነው ሁሉ በፓርላማው ፊት ቀርበው ይቅር በሉኝ እንዳሉ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡እሳቸው የመንግስቱ ዋና መሪ ሆነው ሳለ በእንዲህ ዓይነቱ ደንብ ተላላፊነት መገኘታቸው በጭራሽ ተቀባይነት የለውም መባሉ እየጎላ ነው፡፡በፓርላማው የመተማመኛ ድምፅ እንዲነፈጋቸውም ጥያቄ መቅረቡ ታውቋል፡፡

Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን የጋዝ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ፈቀደች!

የኢትዮጵያ ተሽከርካሪዎች ጋዝ ወደ ኢትዮጵያ እንዲያስገቡ መፍቀዷን ካርቱም አስታውቀለች።የሱዳን ጦር አዛዥ ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋዝ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መፍቀዳቸውን የአገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡እንደዘገባዎቹ ከሆነ ካርቱም ተሽከርካሪዎች ከኢትዮጵያ በምትዋሰንበት በገላባት በኩል እንዲገቡና ጭነው እንዲወጡ ፈቅዳለች፡፡የሱዳን መንግስት ንብረት የሆነው ናይል ፔትሮሊየም ነው የጋዝ ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲያስገባ የተፈቀደለት፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ስፖርት! በመካሄድ ላይ በሚገኘው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 1 ሁለተኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በዳዋ ሁቴሳ ጎል መሪነቱን ቢወስድም ብዙም ሳይቆይ በአዘጋጇ ካሜሩን የአቻነት ግብ ተቆጥሮበታል። በአሁኑ ሰአት ጨዋታው በአቻ ውጤት ቀጥሏል። @YeneTube @FikerAss
ዛሬ በተካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ A ካሜሩን ኢትዮጵያን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት መርታት ችላለች።

ለካሜሩን ቪንሴንት አቡበክር ሁለት ግቦች በ53ኛው እና በ55ኛው ደቂቃ እንዲሁም ካርል ቶኮ ኢካምቢ በ8ኛው ደቂቃ እና በ67ኛው ደቂቃ ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል።ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዳዋ ሆቴሳ በ5ኛው ደቂቃ ማስተዛዘኛዋን ግብ አስቆጥሯል።33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ምሽቱን የሚቀጥል ሲሆን በዚሁ ምድብ ኬፕቨርድ ከቡርኪናፋሶ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የድርጅቱን የስነምግባር ደንብ በመጣስ እየፈፀሙት ያለውን አድሎ እንዲመረምርላት የድርጅቱን ስራ አስፈፃሚ ቦርድ ጠየቀች!

ኢትዮጵያ የአሸባሪው ህወሓት አባልና የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም የድርጅቱን የአሰራር መርህ እና የስነምግባር ደንብ በመጣስ እየፈፀሙት ያለውን አድሎ እንዲመረምርላት የድርጅቱን ስራ አስፈፃሚ ቦርድ ጠየቀች።ኢትዮጵያ ለድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ቦርድ በላከችው ደብዳቤ እንዳለችው፥ ኢትዮጵያ ዳይሬክተሩን ለቦታው በማጨቷ ደስተኛ ብትሆንም ሌሎች ሃገራትና የድርጅቱ ሰራተኞች ድጋፋቸውን በመግለፃቸው ምስጋና ያቀረበች ቢሆንም ዳይሬክትሩ ግን የሚጠበቅባቸውን ሙያዊ ግዴታ እየተወጡ አይደለም ብላለች።

ዶክተር ቴዎድሮስ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነትን ጨምሮ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እየገቡ መሆኑ በደብዳቤው ተገልጿል፡፡እንዲሁም ሽብርተኛ ተብሎ በኢትዮጵያ ፓርላማ ለተፈረጀው የሽብር ቡድኑ ህወሃት አባል እና ደጋፊ መሆናቸውን ቀጥለውበታል ብሏል፡፡የአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነታቸውንም ለግል ፖለቲካ መጠቀሚያነት አውለውታልም ነው ያለው ደብዳቤው፡፡

የሽብር ቡድኑ ህወሃት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ሽብር በግልፅ እንሚደግፉም በማህበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ካወጧቸው ፅሁፎች መረዳት ይቻላል ነው ያለው ደብዳቤው።ዋና ዳይሬክተሩ ጥፋታቸውን ያቆማሉ ተብሎ ተስፋ ቢደረግም ከድርጊታቸው እንዳልተቆጠቡ ገልጿል።የድርጅቱ ዳይሬክተርነትን በመጠቀምም የተመድ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ላይ በጠላትነት እንዲንቀሳቀሱም መሥራታቸውን አስረድቷል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ ጉዳይ በተመለከተ ሲያነሡም አድሎ በማድረግ የፈለጉትን ብቻ እንደሚመርጡም ነው የተመለከተው።የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዓለም ጤና ድርጅት የዳይሬክተሮች ቦርድ በላከው በዚህ ደብዳቤ ግለሰቡ ለዚህ ወንጀላቸው ተጠያቂ እንዲሆኑ ህጋዊ ሂደት መጀመሩን አስታውቋል።በመሆኑም ዋና ዳይሬክተሩ የሙያ ስነምግባር እና ከዓለም ጤና ድርጅት የአሰራር እና ስነምግባር መመሪያን የጣሰውን ተግባራቸውን እንዲመረምር እና የሚወስደውን እርምጃ እንዲያሳውቅ ጠይቋል ደብዳቤው።

@YeneTube @FikerAssefa