የአጎዋ ገበያ “ሳንጠቀምባቸው” በቆዩ የገበያ ዕድሎች ይተካል ተባለ!
ኢትዮጵያ ምርቷን ወደ አሜሪካ ገበያ ትልክ የነበረበትን እና በቅርቡ የታገደውን የአጎዋ ገበያን፣ ከዚህ በፊት ከቀረጥ ነጻ በሌሎች አገራት ለኢትዮጵያ ተሠጡ የገበያ አማራጮች እንደሚተኩት የንግድና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።ሠፊ ከሆነው የአፍሪካ ገበያ በላይ በርካታ ያልተጠቅምንባቸው የገበያ አማራጮች አሉ የሚለው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ የአሜሪካን ገበያ በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫችን አድርገን የቆየን ቢሆንም፣ አሁን ላይ የአጎዋ ገበያን ለመተካት ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ ተሰጥተው ነገር ግን ያልተጠቀምንባቸው ገበያዎችን ለመጠቀም ጥናት ተካሂዷል ሲል ነው ያስታወቀው።
የንግድና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር የንግድ ግንኙነትና ድርድር ዳይሬክተር ጀነራል ሙሴ ምንዳኤ ለአዲስ ማለዳ በሰጡት ማብራሪያ፣ ከ2001 ጀምሮ ከቀረጥ እና ከኮታ ነጻ ከጦር መሣሪያ ውጭ ማንኛውንም ምርት ወደ አውሮፓ እንድንልክ የገበያ አማራጭ ተሠጥቶናል ነው ያሉት።ይህም ትልቅ የገበያ አማራጭ መሆኑን ጠቅሰው፣ በአጎዋ በኩል ወደ አሜሪካ ይላኩ ለነበሩት የጨርቃ ጨርቅ እና የአበባ ምርቶች ሠፊ የገበያ መዳረሻ መሆኑን አንስተዋል።
እንዲሁም፣ በተመረጡ ምርቶች ላይ ከጃፓን፣ ካናዳ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬት እና ቱርክ ተመሳሳይ የገበያ ዕድሎች መኖራቸውን ካነሱ በኋላ፣ ከኢትየጵያ ወደ ጃፓን ከሚላኩ ምርቶች ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት ከቀረጥ ነጻ ናቸው ብለዋል።ቱርክም ወደ 4000 የሚጠጉ የተመረጡ የምርት ዓይነቶችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ከ20006 ጀምሮ የፈቀደች በመሆኑ፣ በቀጣይ ገበያውን በሥፋት ለመጠቀም መታሰቡን አመላክተዋል።
ተጨማሪ: https://bit.ly/3f8Hqmo
@YeneTube @FikerAssefa

የፌዴራል ፖሊስ የጤና ጉዳተኞች ማገገሚያ ማዕከል ለማስገንባት የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ!
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የሠራዊቱ የጤና ጉዳተኞች ማገገሚያ እና ማስተናበሪያ ማዕከል ለማስገንባት ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
ማዕከሉ ኮልፌ ቀራኒዮ በሚገኘው የቀድሞ ፈጥኖ ደራሽ ማሰልጠኛ ግቢ በ64 ካሬ ሜትር ላይ እንደሚገነባ መገለጹን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር ተወያዩ።
በስልክ የተደረገው ውይይት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ማትኮሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቲውተር ገጻቸው ጽፈዋል።በጋራ መግባባትና መከባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነትን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ተግባብተናልም ነው ያሉት።
@YeneTube @FikerAssefa
በስልክ የተደረገው ውይይት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ማትኮሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቲውተር ገጻቸው ጽፈዋል።በጋራ መግባባትና መከባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነትን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ተግባብተናልም ነው ያሉት።
@YeneTube @FikerAssefa
በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ የተከሠተ የእሳት ቃጠሎ እየተባባሰ መሆኑ ተገለጸ!
በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንገር ጉትን፣ ለሊ ማርያም በተሰኘ ቦታ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱን እና አሁን ላይ ቃጠሎው ይበልጥ እየተባባሰ መምጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ።ከታኅሣሥ ወር ሦስተኛ ሳምንት ጀምሮ በአንገር ጉትን ከተማ ውስጥ በሚገኘው ለሊ ማርያም ተብሎ በሚጠራው ቦታ የእሳት ቃጠሎ በመነሳቱ፣ በርካታ ቤቶችና ንብረቶች መቃጠላቸውን ነው አዲስ ማለዳ ከነዋሪዎቹ መረዳት የቻለችው።
በጊዳ አያና ወረዳ ያለው ሠላም የተረጋጋ ባለመሆኑ በቃጠሎው ምክንያት ምን ያህል ቤትና ንብረት እንደወደመ ትክክለኛውን ቁጥር ቀርቦ ማወቅ ባይቻልም፣ በርካታ ቤቶች፣ ንብረቶች የምግብ እህሎች እንደወደሙ ነዋሪዎቹ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።አዲስ ማለዳ የቃጠሎው መነሻ ምክንያት ምን እንደሆነ የጠየቀች ሲሆን፣ የአካባቢው ሰዎችም መንስኤውን በሚከተለው መልኩ አብራርተዋል።
https://bit.ly/3f4S7X0
Via Addis Maleda

በሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን እስካሁን በተካሄደ ኦፕሬሽን 433 የአሸባሪው ሸኔ ቡድን አባላት ሲደመሰሱ 115 አባላቱ ደግሞ መማረካቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።
የዞኑን ሰላም ወደ ቦታው ለመመለስ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በቅንጅት በመስራት አስተማማኝና ውጤታማ ኦፕሬሽን በዞኑ እየተካሄደ መሆኑን የሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ በቀለ ደቻሳ አስረድተዋል።በዚህም ወደ 433 የሸኔ ቡድን አባላት ሲደመሰሱ 115ቱ ተማርከዋል፤ የቡድኑ የመረጃ እና የሎጅስቲክስ ክንፍ የሆኑ ወደ 623 የሚደርሱ አባላትን በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል ሲሉም ገልፀዋል።
እንዲሁም ጠላት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ዘመናዊና ኋላ ቀር የጦር መሳሪያዎችም ገቢ የተደረጉ ሲሆን የሽብር ቡድኑን እንቅስቃሴ በማጤን አስፈላጊውን ምላሽ እየሰጠን ነው ብለዋል።
ሕዝቡን በማሳተፍና በማደራጀት ሰላምን የማረጋገጥ ሥራ በጋራ እየተሰራ ነው ያሉት አስተዳዳሪው በቀለ ደቻሳ አመራሩም ቡድኑ ከዞኑ ለማጥፋት በእቅድ እየተመራ አመርቂ ሚና እየተጫወተ ነው ሲሉም መግለፃቸውን ዋልታ ዘግቧል።አሁን ላይ ቡድኑ በዞኑ የሚያካሂደው መስፋፋት ሙሉ በሙሉ እየደረቀ ሲሆን፤ በአጭር ጊዜም ዞናችንን ከአሸባሪው ሸኔ ነፃ በማድረግ ለሕዝባችን የተሟላ ሰላም እናረጋግጣለን ሲሉም በቀለ ተናግረዋል።
Via Walta

ወደ ሀገር የመጡ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራዎች የሚሳተፉበት የኢንቨስትመንት ፎረም ተጀመረ።
የኢንቨስትመንት መድረኩ ከጥር 3 እስከ 6/2014 ዓ.ም በስካይላት ሆቴል የሚካሄድ ሲሆን ዲያስፖራዎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ ጋባዥ ሁኔታዎች ላይ ገለጻ እና ውይይት የሚካሄድበት መድረክ ነው።በመክፈቻ ስነ ስርአቱ ላይ ሚኒስትሮች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የክልሎች ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል ።
Via Capital

ተጠርጣሪዎች ክሳቸው የተቋረጠው ዐቃቢ ሕግ በተለያዩ ምክንያቶች ክሱን መቀጠል እንደማይፈልግ በማስታወቁ ነው፡- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
በቅርቡ በሶስት የተለያዩ መዝገቦች ክሳቸው የተቋረጠ ተጠርጣሪዎች ዐቃቢ ሕግ በተለያዩ ምክንያቶች ክሱን መቀጠል እንደማይፈልግ በማስታወቁ መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ገለፀ።ታህሳስ 28፣2014 ዓ.ም በሙሉ ወይንም በከፊል በተከሳሾች ላይ በሶስት መዝገቦች የቀረቡ ክሶችን እንዲቋረጡ የፍትህ ሚኒስትሩ ለሚመለከተው ችሎት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ሕጋዊ ስርዓቱን ተከትለው መስተናገዳቸውን ጠቅላይ ፍር ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በመሆኑም የክስ ሂደታቸው እንዲቋረጥ ከቀረቡት በከሳሽ ዐቃቤ ሕግ እና በተከሳሾች እነ ጀዋር ሲራጅ መሀመድ (በድምሩ 20 ተከሳሾች)፣ በከሳሽ ዐቃቤ ሕግ እና በተከሳሾች እነ እስክንድር ነጋ (በድምሩ 7 ተከሳሾች) እንዲሁም በከሳሽ ዐቃቤ ሕግ እና በተከሳሾች እነ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (በድምሩ ስድስት ተከሳሾች ላይ የቀረበው ክስ) የሚመለከቱ እንደሚገኝበት ፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሕገ-መንግስት እና ሽብር ጉዳዮች አንደኛ ወንጀል ችሎት የፍትህ ሚኒስትሩን ማመልከቻ በመመርመር በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6(3)ሠ መሰረት ክሱን ያነሱ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ተከሳሾቹ እንዲለቀቁ “ተከሳሾች በሌላ ወንጀል የማይፈለጉ ከሆነ” ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ለማረሚያ ቤት አስተላልፎ ተፈጻሚ መሆኑንም አመልክቷል፡፡

በአማራ ክልል የደረሰውን ውድመት ለታሪክ ለማስቀመጥ የሚረዳ ጥናት እየተካሄደ ነው!
በአማራ ክልል በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን የደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ለታሪክ ለማስቀመጥና ለመልሶ ግንባታ ግብዓት ሊሆን በሚችል መልኩ የሚያጠና ግብረኃይል ተዋቅሮ እየተጠና መሆኑን በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ተስፋዬ ሽፈራው (ዶክተር) ገለጹ።
ተስፋዬ ሽፈራው (ዶክተር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ አሸባሪው ቡድን ወረራ በፈጸመበት ወቅት ያደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት በጥናት በማስደገፍ ቀድሞ ከነበሩበት በተሻለ ቁመና መልሶ ለመገንባት የሚያስችል ጥናት አራት ቡድን ተዋቅሮ እየተጠና ነው።እንደ ተስፋዬ (ዶክተር) ገለጻ፤ ጥናቱ ውጤታማ እንዲሆን በክልሉ የሚገኙት አሥሩም ዩኒቨርሲቲዎች በተናጥል ከሚያደርጉት ጥናት ይልቅ በጋራ በመሆን የሚያጠኑት ውጤታማ የሆነ፣ የተደራጀ የጥናት ሰነድ እንዲኖር ያስችላል።
Via EPA

ዓለም ዐቀፍ የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች ጥምረት ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሆስፒታል የመድኃኒት እና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ!
መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው "ዓለም ዐቀፍ የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች ጥምረት" ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል ግምታቸው ከ500 ሺሕ ብር በላይ የሆኑ መድኃኒቶች እና የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉን ያስረከቡት የጥምረቱ ተወካይ መምህር ኮከብ ገዳሙ መንግሥት ዲያስፖራው ወደ አገሩ በመምጣት ከሕዝቡ ጎን እንዲቆም ጥሪ ባቀረበው መሰረት መገኘታቸውን ገልፀዋል፡፡
የጥምረቱ ተወካዮች በተለያዩ የሰሜኑ የአገሪቱ ክፍሎች በመዘዋወር በጦርነቱ የተጎዱ ቦታዎችን በመጎብኘት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎች ለኅብረተሰቡ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰው በዛሬው ዕለት ለዕዙ ሆስፒታል የተደረገው ድጋፍም ለ2ኛ ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል።
የዲያስፖራዎች ተግባር ምክር ቤት ጊዜያዊ ሥራ አስፈፃሚ ሊቀመንበር አለማየሁ አበበ በበኩላቸው ያለ ዲያስፖራው ተሳትፎ ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎች ተፈላጊውን ግብ እንደማይመቱ ገልፀው ይህንኑ ለማጠናከር ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር ውጤታማ ተግባር እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የሆስፒታሉ ጠቅላላ አገልግሎት ሎጀስቲክስ ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ሰብለ ሙሉጌታ የጥምረቱ አባላት ከዚህ በፊት "እንቁጣጣሽን ከሠራዊት ጋር" በሚል መርህ ከ200 ሺሕ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውሰው ይህንኑ በጎ ተግባር በማጠናከር ላደረጉት ድጋፍ በሆስፒታሉና በታካሚው ስም ምስጋና ማቅረባቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ አመልክቷል።

ኢዜማ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች የጥቆማ ጊዜ እንዲራዘም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ አቀረበ!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች የጥቆማ ጊዜ እንዲራዘም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ አቅርቧል፡፡ኢዜማ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በላከው ደብዳቤ ነው ጥያቄውን ያቀረበው፡፡
የአገራዊ ምክክር አዋጁ ረቂቅ ላይ ማኅበረሰቡም ሆነ ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ውይይት እና ክርክር ሳያደርጉበትና በበቂ ሁኔታ ግብዓት ሳይታከልበት በፍጥነት ለፓርላማ ቀርቦ እንዲጸድቅ መደረጉ የሂደቱን ፍትሐዊነት ጥያቄ ውስጥ እንዳያስገባው ስጋት እንዳለው የገለፀው ኢዜማ፣ አገራዊ ምክክሩ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ጠቁሟል፡፡አገራዊ ምክክሩ በቂ ትኩረት እንዲያገኝ መደረግ ያለባቸውን ምክረ ሐሳቦችም በደብዳቤው አስቀምጧል፡፡
«ማኅበረሰቡ በሌሎች በርካታ አጀንዳዎች ላይ ተጠምዶ በመክረሙ በአገራዊ ምክክሩ አጠቃላይ ፋይዳና ሂደቱ ላይ በቂ የሆነ ግንዛቤን የማስጨበጥ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል።» በማለት ስለ አገራዊ ምክክር ሂደት ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መሥራት እንደሚገባም አሳስቧል፡፡
የብዙኀን መገናኛዎች በአገራዊ ምክክሩ ላይ የሕዝብን ተሳትፎ ከማጎልበትና ከማንቃት አንጻር ተገቢውን ሚና እየተጫወቱ እንዳልሆነ የገለጸው ኢዜማ፣ ብዙኀን መገናኛዎች ለምክክሩ ሂደት ትኩረት በመስጠት ለአገርና ለሕዝብ ያላቸውን ወገናዊነት እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የኮሚሽነሮች ጥቆማ ሂደት ውስብስብነት የሚታይበት መሆኑን ያነሳው ኢዜማ፣ በማያሻማ ሁኔታ ጥቆማ እንዴት ማቅረብ እንደሚቻል ለሕዝቡ ግልፅ ማድረግ እንደሚገባ ጥያቄውን አቅርቧል፡፡
ከፖለቲካው ገለልተኛ የሆኑና ብቃት ያላቸውን ዜጎች ለመምረጥ እንዲያስችል ከታኅሣሥ 26/2014 እስከ ጥር 06/2014 ለኮሚሽነሮች ጥቆማ የተሰጠው የጊዜ ገደብ በቂ አለመሆኑን በደብዳቤው ላይ የገለጸው ፓርቲው፣ «የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የጥቆማውን ጊዜ እንዲያራዝመው» በማለት የጥቆማው ጊዜ እንዲራዘም ምክረ ሐሳቡን ማቅረቡን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ብሔራዊ ባንክ በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ ማንሳቱን አስታወቀ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ መነሳቱን ይፋ አድርጓል።
ብሔራዊ ባንክ ካለፈው ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ የባንኮች ደንበኞች በሳምንት ከአምስት በላይ የባንክ ዝውውሮችን እንዳያደርጉ የሚያዝ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል።
ይህም መመሪያ መደበኛ ባልሆነው የልውውጥ ገበያ ውስጥ ያሉ ተጫዋቾችን ተስፋ ለማስቆረጥ ያወጣው ደንብ መሆኑን አስታውቆ ነበር።
ይሁን እንጂ ካሳለፍነው ሳምንት ታህሳስ 27 ቀን 2014 ጀምሮ ይህ መመሪያ መነሳቱን በብሔራዊ ባንክ የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው፣ መግለፃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።
“የዝውውር ገደቡ አሁን ሙሉ በሙሉ በመመርያ ተነስቷል” ያሉት ፍሬዘር፣ ነገር ግን ባሳለፍነው ዓመት የወጣው የገንዘብ ወጪ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ገደቦችም አሁንም ድረስ ተፈፃሚ ሆነው ይቀጥላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ኦፌኮ የድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በገለልተኛ አጣሪ አካል እንዲጣራ ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መግለጫ ጠይቋል። ከድምጻዊው ግድያ ጋር በተያያዘ በአመራሮቹ ላይ የተፈጸመው እስር ፖለቲካዊ እንደነበር የገለጠው ኦፌኮ፣ የድምጻዊው ግድያ ምርመራ ፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንደነበረበት ጠቅሷል። ኦፌኮ ጨምሮም፣ በትግራይ፣ ኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ያሉ ግጭቶች በድርድር ላይ የተመሠረተ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ያሳሰበ ሲሆን፣ የውጭ ኃይሎች በተለይም በቀይ ባሕር አቅራቢያ ያሉ ሀገራት ሁሉም ወገኖች ግጭትን እንዲያቆሙ ግፊት እንዲያደርጉ እና መንግሥት የኦፌኮ እና ኦነግ አባላትን ጨምሮ ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች፣ ማኅበራዊ አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች እና ከአስቸካይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ግለሰቦችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ እንዲፈታም ጠይቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በሶማሌ ክልል በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር የተመራውን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎችን በጽ/ቤታቸው የተቀብሉ ሲሆን ፥ አስተዳደሩ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት ላደረገው የገንዘብ ድጋፍ በአሁኑ ወቅት ለህብረተሰባችን አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ልዑክ የ10 ሚሊየን ብር ድጋፉን ለሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ኡስማንና ሌሎች የክልሉ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት አስረክበዋል።

#ታደሰ ስዩም የተፈቀደለት የሂሳብ አዋቂ
ጊዜዎን ቆጥበው ሰራተኛ ወጣብኝ ሳይሉ በስራው ብዙ አመት ልምድ ባላቸው ሙያተኞች ጊዜው ባፈራቸው እውቅ ሳፍትዌሮች እና በተመጣጣኝ ዋጋ አጠቃላይ የድርጅቶን ሒሳብ መያዝ ይፈልጋለሁ?
እንግድያውስ ድርጅታችን እርስዎን ለማገልገል በሩን ክፍት አድርጎ ይጠብቃል::
እኛ ስለ ሒሳብዎ, እርስዎ ስለ ድርጅትዎ ብቻ ይጨነቁ
አድራሻ መገናኛ 22 ከጎላጎል በስተቀኝ የሚገኘው ሕንጻ 4ኛ ፎቅ የቤት ቁጥር 279/4/8 እንዲሁም በስልክ ቁጥር +251904591215/ +251900310388 +251902475483 ያገኙናል::

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአገሪቱ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም የተሰጠው 'የፊልድ ማርሻል' ማዕረግ አገርን ከከባድ አደጋ ለታደጉ የጦር መኮንን መበርከቱ አግባብ ነው ሲሉ ጄነራል ባጫ ደበሌ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ከቀናት በፊት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ለጄነራል ብርሃኑ ጁላ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ መስጠታቸው ይታወሳል።በዕለቱ የተሰጠው የፊልድ ማርሻልነት ማዕረግ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ከፍተኛው ወታደራዊ ሹመት ሲሆን በዕለቱ ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በተጨማሪ ለ100 የሠራዊቱ አባላት የተለያዩ ወታደራዊ ማዕረጎች ተሰጥቷዋል።
በዕለቱ ለጀነራል ብርሃኑ ጁላ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ የተሰጠው፤ በጄነራሉ አመራር ሰጪነት የህወሓት ኃይሎችን መመከት በመቻሉ እና የተመዘገበው ስኬት አገርን ከውድቀት የታደገ መሆኑን ብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ የአገር መከላከያ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር።
ይሁን እንጂ በርካቶች የጦር መኮንኑ የመሩት በአገር ውስጥ የተደረገ የእርስ በእርስ ጦርነት መሆኑን በማውሳት የተሰጠው የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ላይ ጥያቄዎችን ሲያነሱ ነበሩ።
በሥነ ሥርኣቱ ላይ ከሌተናል ጄነራልነት ማዕረግ ወደ ጄነራልነት ከፍ ያሉት ባጫ ደበሌ ግን ለኤታማዦር ሹሙ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ መሰጠቱ ትክክል ነው ይላሉ።
ጄነራል ባጫ፤ የፊልድ ማርሻል ማዕረጉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር መሰጠቱን በማስታወስ የሹመቱን ሕጋዊ አካሄደ ትክክለኛነትን አጽንኦት ሰጥተው አስረድተዋል።በዚህ መሠረት ኢትዮጵያ "የአገር ውስጥ እና የውጭ ኃይሎች" አገሪቱን ለማፈራረስ በተነሱ ወቅት የተደቀነባትን ከባድ አደጋ መቀልበስ ለቻሉት ይህ ማዕረግ መሰጠቱ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብለዋል።
Via BBC

የኦሮሚያ ክልል መንግስት በሁለት ሳምንት ውስጥ ብቻ 876 በሚሆኑ የሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ወስጃለሁ አለ!
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ በክልሉ የልማትና የፀጥታ ስራዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።የአሸባሪውን ሸኔ አጥፊ ቡድን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተቀላቀሉ ወጣቶች ከአባገዳዎች ጋር በመነጋገር 312 ወጣቶች እጅ እንዲሰጡ መደረጉ ተነግሯል።የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ባለው ስራም በሁለት ሳምንት ብቻ 876 የሚሆኑ የቡድኑ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱም በመግለጫው ተነስቷል ።
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወዲህም ከ2 ሺህ 400 በላይ የቡድኑ አባላት ሲደመሰሱ፥ በህብረተሰቡ ጥቆማ 540 የሚሆኑት በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው የተባለው።የአካባቢ ጥበቃ ስራን በተመለከተም፥ ለምርትና ምርታማነት ወሳኝ ሚና የሚጫወተው የአካባቢ ጥበቃ ስራ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በነገው እለት በይፋ እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡በክልሉ የመኸር ምርትን የመሰብሰብ ስራው ጋር ተያይዞ በአመርቂ ሁኔታ መከናወኑን ነው ሃላፊው ያነሱት።
በዚህም 6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር ላይ ከተዘራው ሰብል እስካሁን 5 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር ሰብል ተሰብስቧል ብለዋል።በመስኖ ስንዴ ልማት ዘርፉም 350 ሺህ ሄክታር ለማልማት ታቀዶ እስካሁን 302 ሺህ ሄክታር ማልማት መቻሉን አንስተዋል።ለተፋሰስ ልማቱም ቦታዎች መለየታቸውን ገልጸው ፥ነገ የልማት ስራው በይፋ ይጀመራልም ነው ያሉት።በዝናብ እጥረት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ሰብአዊ ድጋፍ የማድረስ ስራም ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።
Via FBC

በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ባለፉት ስድስት ወራት በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የ62 ሰዎች ህይወት አልፏል!
በአዲስ አበባ ከተማ እና ዙሪያዋ ባለፉት ስድስት ወራት በድንገተኛ አደጋዎች የ62 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 112 ሰዎች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ከብስራ ሬድዮ ጋር በነበራው የስልክ ቆይታ እንደተናገሩት በስድስት ወራት ውስጥ 236 ድንገተኛ አደጋዎች ደርሰዋል ብለዋል።
ከአደጋዎቹ መካከል 136 የእሳት ቃጠሎ ሲሆኑ 100 አደጋዎች ደግሞ ከእሳት ውጪ የደረሱ ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡በ2014 ዓ.ም በግማሽ ዓመት ከደረሰው አደጋ በእሳት ቃጠሎ የ5 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች 57 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
በአካል ላይ በደረሰ አደጋ በእሳት 54 ሰዎች ላይ በድንገተኛ አደጋዎች ደግሞ 58 ሰዎች ቆስለዋል። በደረሱት አደጋዎች ከ62 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረትም መውደሙ ተነግሯል፡፡እንደ አቶ ንጋቱ ማብራሪያ በተያዘው የበጀት ዓመት በስድስት ወራት የደረሱት አደጋዎች ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በሞት ሆነ በንብረት ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት በስድስት ወራት 46 ሰዎች ህይወት ሲልፍ በዘንድሮው አስራ ስድስት በመጨመር ስልሳ ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።የአደጋዎች መንስኤ በተመልከተ ከ236 አደጋዎች የ101 አደጋዎች መንስኤ የታወቀ ሲሆን የ135 አደጋዎች መንስኤ አለመታወቁን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ በከተማ ከእሳት አደጋ ውጪ የደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የሚባሉት የኤሌክትሪክ ፣ኩሬ ውስጥ እና ክፍቱን በተተዉ ቦታዎች ላይ መግባት እና የጎርፍ አደጋዎች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
[ዳጉ ጆርናል/ብስራት ሬድዮ]

በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ ከተማ ለሚገነቡ 10 ሺህ ተገጣጣሚ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።
በምዕራፍ 1 ፕሮጀክት የሚገነቡ የ5 ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳናች አቤቤ አስጀምረዋል።
ዛሬ ግንባታ ለማካሄድ የተጀመረው መሬት በህገ ወጥነት ተይዞ የነበረ ወደ መሬት ባንክ በማስገባት መሆኑም የተገለጸ ሲሆን ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሚገነባቸው የተጋጋጠሚ ቤቶቹ በአንድ ዓመት ተገንብተዉ ለማጠናቀቅ እንደሚሠራ ተነግሯል፡፡
የሚገነቡት ቤቶች ባለ 4 እና ባለ 10 ወለል ሕንጻዎች ሲሆኑ ቤቶቹ ተገንብተው ሲጠራቀቁ በከተማ ደረጃ የተያዘውን ቤቶችን ለዜጎች ተደራሽ የማድረግ ዕቅድ በከፊል የሚያሳካ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከከተማ አስተዳደሩ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል።

መንግሥት ክስ ስላቋረጠበት ምክንያት ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥ ተጠየቀ!
ከድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ከተፈጠረው ሁከትና ግድያ፣ እንዲሁም በሰሜን ኢትዮጵያ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ ተመሥርቶባቸው፣ በሕግ ጥላሰ ሥር የነበሩ ግለሰቦች ከሰሞኑ በመንግሥት ክሳቸው ተቋርጦ በመፈታታቸው፣ አገር ቤት የገቡ የዳያስፖራ አባላት ውሳኔው እንዳስቆጣቸው ገልጸው መንግሥት ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥበት ጠየቁ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መንግሥት ጥሪ አድርጎላቸው ወደ አገር ቤት ከገቡ የዳያስፖራ አባላት ጋር ‹‹የዳያስፖራው ሚና ለፓን አፍሪካን ንቅናቄ›› በሚል ርዕስ ጥር 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡
በሲምፖዚየሙ ተሳታፊ የነበሩ ከአሜሪካና ከአውሮፓ የመጡ የዳያስፖራ አባላት፣ ጉዳያቸው በሕግ እየታየ የነበረ ነገር ግን ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር እንዲፈቱ በመንግሥት የተላለፈውን ውሳኔ በተመለከተ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ዘገባውን ለማንበብ: https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/24366

በማይካድራ ከተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ ጋር ተያይዞ ክስ የተመሰረተባቸው በቁጥጥር ስር ያልዋሉ 179 ተከሳሾች በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው ፍርድቤት ትዛዝ ሰጠ ።
በተጨማሪም ፍርድቤቱ በማይካድራ ታድሶ ወስዶ ማህበረሰቡን ተቀላቅለው እየኖረ ነው የተባለው 6ኛ ተከሳሽ በተመለከተ ግን የፌደራል ፖሊስ አፈላልጎ በቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርበው አዟል፡፡
ትዛዙን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረ ሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው፡፡
አጠቃላይ ክስ የቀረበባቸው ተከሳሾች 202 ሲሆኑ በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸውን የሚከታተሉት ግን 22 ተከሳሾች ብቻ ናቸው።
ባሳለፍነው ህዳር 15 ቀን በነበረ ቀጠሮ በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ተከሳሾች ማለትም ከ1 ኛ እስከ 14 ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሰሱ እና ከ36ኛ እስከ 202 ኛ ተራ ቁጥር ክስ የቀረበባቸው 180 ተከሳሾችን በአድራሻቸው ተፈልገው እንዲቀርቡ ፍርድቤቱ በሰጠው ትዛዝ ከማይካድራ አስተዳደር
ከ6 ኛ ተከሳሽ ውጪ ያሉ ተከሳሾች በአድራሻቸው ተፈልገው አለመገኘታቸውን ማስረጃ መላኩን የተገለጸ ሲሆን
6ኛ ተከሳሽ በተመለከተ ግን ታድሶ ወስደው ማህበረሰቡን ተቀላቅለው እየኖረ መሆኑ ተጠቅሶ ነበር፡፡
ይሁንና ፍርድቤቱ በዛሬው ቀጠሮ 179 ተከሳሾች በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው ትዛዝ የሰጠ ሲሆን ታድሶ ወስዶ ማህበረሰቡን ተቀላቅለው እየኖረ ነው የተባለው 6ኛ ተከሳሽ በተመለከተ ግን የፌደራል ፖሊስ አፈላልጎ በቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርበው ታዟል፡፡
ከነዚህ በማረሚያ ቤት ከሚገኙት ተከሳሾች መካከል መምህር ጃንቦ ብርሀን: ኪሮስ ሲሳይ: አንድ የአራት አመት ታዳጊ ልጇን ይዛ በችሎት የምትቀርበው ወ/ሮ ህይወት አብርሐ : እንዲሁም ሶስት ህጻናት ልጆቿን ይዛ ፍርድ ቤት የቀረበችው ወ/ሮ አለምጸሃይ አሰፋ ይገኙበታል።
ዛሬ የተከሳሽ ጠበቃ ለመቅረባቸውን ተከትሎ ጠበቃቸው የማይሰየሙላቸው ከሆነ በቀጣይ የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲቆምላቸው መጠየቅ እንደሚችሉ በፍርድቤቱ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
ተከሳሾቹ ያልተያዙ ግለሰቦች እስኪያዙ ተብሎ መጠበቅ እንደሌለባቸው ጠቁመው የነሱ ጉዳይ ብቻ ተነጥሎ እንዲታይላቸው ጠይቀው የነበረ ሲሆን ፍርድቤቱ በጋዜጣ ጥሪ ከተደረገ በኋላ ውጤቱን ተመልክቶ ትዛዝ እንደሚሰጥበት አመላክቷል፡፡
ከሳሽ ዓቃቢህግ በማይካድራ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች የአማራ ተወላጆችን መግደል አለብን በማለት በመደራጀት ከ229 በላይ ንጹሀን ሰዎች ላይ አሰቃቂ የዘር ጭፍጨፋ መፈጸሙን ከ217 በላይ ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን እና በ10 ሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈጸሙን ጠቅሶ በ1996 ዓ/ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 240/ ንዑስ ቁ 2 እና 3 በመተላለፍ ወንጀል በየደረጃው ክስ መመስረቱ ይታወሳል።
Via Tarik Adugna