በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከእናቶች ወሊድ ጋር ተያይዞ ተፈጠረ በተባለው የእናቶች እና ጽንስ ሞት ዙሪያ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ከኦቶና ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንዲሁም ከሆስፒታሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ሆስፒታሉ የእናቶችና የጨቅላ ሕጻናት ሕክምናን በተመለከተ፤ በተለይም በወሊድ አገልግሎት መስክ ልዩ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊውን የሰው ኃይል እና ግብዓት ጭምር በማሟላት መጠነ ሰፊ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱንና በዚህም በሆስፒታሉ አንዲትም እናት በወሊድ ምክንያት ሕይወቷ እንዳያልፍ የዘርፉ ባለሙያዎች ሙያዊ ሀላፊነታቸውን በሚገባ በመወጣት ውጤታማ ስራ ሲያከናውኑ መቆየታቸውን የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ባካሄደው ውይይት አሳውቋል፡፡
ይሁን እንጂ ከሰሞኑ ተፈጠረ በተባለው የእናቶች እና ጽንስ ሞት ዙሪያ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ከኦቶና ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና ከሆስታሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ጥልቅ ውይይት በማካሄድ በጉዳዩ ዙሪያ የመከረ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም በተቋም ደረጃ ይህን መሰል ችግር ተከስቶ እንደማያውቅ፤ አሁን ከእናቶች ወሊድ ጋር ተያይዞ ተፈጠረ በተባለው የእናቶች እና ጽንስ ሞት ክስተትን በተመለከተ ሠፊ የማጣራት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እስከ ባለሙያ ያለውን አደረጃጀት በጥልቀት በመፈተሸ እውነታውን አስመልክቶ ለሚዲያ ተቋማት አግባብነት ያለውን ምልሽ ለመስጠት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
በወሊድ ምክንያት እናትም ሆነች ልጅ መሞት የለባቸውም የሚል መርህን በማንገብ ሆስፒታሉ ነጻ የወሊድ አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየ እና አሁንም አገልግሎቱን በስፋት እየሰጠ እንደሚገኝ፤ ምንም እንኳ በሆስፒታሉ የወሊድ አገልግሎት በነጻ ቢሰጥም የመድኃኒት እጥረት በሚያጋጥምበት ጊዜ በራሳቸው ገዝተው መታከም ለማይችሉ ሰዎች ተጠባባቂ በጀት እንዲመደብላቸው፤ ለህክምና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በፍጥነት ማሟልት ተገቢ እንደሆነ፤ በባለሙያዎች የሕክምና ስህተት ችግር እንዳይፈጠር የሙያ ስነ-ምግባርን ጠብቆ ሐላፊነትን በብቃት መወጣት እንደሚገባ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር በተጨማሪም አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
የሚዲያ ተቋማትም ማንኛውንም ክስተት ከስረ መሰረቱ በማጣራትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት አግባብነት ያለውን መረጃ በማሰባሰብ ሚዛናዊ ዘገባ በመስራት ሙያዊ ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው፤ ተፈጥሯል የተባለውን ክስተት ከጉዳዩ ጋር ፈጽሞ ከማይገናኙ ነገሮች ጋር ከማያያዝ ተቆጥበው የተቋሙን የሥራ ሐላፊዎች እና የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት መረጃ በመጠየቅ የዘገባ ሥራ ቢሰሩ መልካም እንደሆነ በውይይቱ በስፋት ተዳሷል፡፡
ምንጭ: ወላይታ ዩንቨርሲቲ
@YeneTube @FikerAssefa

በጎንደር ከተማ የሚከበረው የጥምቀት በዓል ፍፁም ሰላሙና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ህብረተሰቡን ያሳተፈ የፀጥታ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
የጥምቀት በዓል በዮኒስኮ ከማይዳሰሱ ቅርሶቹ መካከል አንዱ ሲሆን ይህ በዓል በጎንደር ከተማ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር በየአካባቢው የጥበቃ ሁኔታና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በጎንደር ከተማ የሚካሄደውን የጥምቀት በዓል ፍፁም ሰላሙና ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኖ እዲከበር ህብረተሰቡን ያሳተፈ አደረጃጀቶችን ፈጥሮ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
የጎንደር ከተማ መደበኛ ፖሊስ፣ የአድማ መከላከል ፖሊስ፣ ሚሊሻና የግል ታጣቂዎች የብሎክ አደረጃጀቶችን በመጠቀም አካባቢውን የመጠበቅ ተግባር ሲሰራ ቆይቷል አሁንም እየሰራ ይገኛል።
የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ከመቸውም ጌዜ በላይ አካባቢያቸውን እንዲጠብቁና ሁሉም ህብረተሰብ የከተማዋ ሰላም የኔ ሰላም ነው ብሎ በዓሉ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን እንዲወጣ የጎንደር ከተማ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚስተዋለው የድርቅ አደጋ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ፈጣን የድጋፍ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎች በትኩረት መሰራት እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ፡፡
የብሄራዊ አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚቴ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በአስቸኳይ ጊዜ የድጋፍ አሰጣጥ ሂደት አስፈፃሚ አካላት ያሳዩት ፈጣን ምላሽ እና ቅንጅታዊ አመራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
የብሄራዊ አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በስብሰባው ላይ እንደተናገሩት፤ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚስተዋለው የድርቅ አደጋ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ፈጣን የድጋፍ ምላሽ ያስፈልጋቸዋል፡፡
ቀደም ባሉት ጊዜያት በአስቸኳይ ጊዜ የድጋፍ አሰጣጥ ሂደት አስፈፃሚ አካላት ካሳዩት የተቀናጀ ርብርብ በተሻለ ትኩረት የድርቅ አደጋ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ፈጣን የድጋፍ ምላሽ ሊያገኙ እንደሚገባ አቶ ደመቀ አሳስበዋል፡፡
ብሄራዊ ኮሚቴው ባስቀመጠው አቅጣጫ በአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አቅርቦት እና ስርጭት ሂደት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ዘላቂ በሆነ መልኩ በመፍታት የድጋፍ ምላሹ የመጨረሻ ተጠቃሚዎችን ማዕከል ማድረግ እንደሚገባው አቶ ደመቀ አስምረውበታል፡፡
ሃገሪቱ የገጠማትን የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ተቋቁማ እንድትሻገር የዲያስፖራው ማህበረሰብ ላደረገው ድጋፍ አቶ ደመቀ ምስጋናቸውን የገለፁ ሲሆን፤ በቀጣይም በሁሉም አቅጣጫ የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የብሄራዊ አደጋ መከላከል ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በበኩላቸው፤ በብሄራዊ ኮሚቴ በሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች እና በሚያስቀምጣቸው አቅጣጫዎች መሰረት የተጀመሩት የድጋፍ እና ምላሽ አሰጣጥ ስራዎች በሚታይ መልኩ ወደ መሬት መውረድ ጀምረዋል፡፡
ይሁንና ሃገሪቱ ከገጠማት ውስብስብ ችግሮች አኳያ ከአጋር አካላት የሚደረገው ድጋፍ በቂ በሚባል ደረጃ ባለመሆኑ ምክንያት ጅምር የድጋፍ እና ምላሽ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ አሉታዊ ጫና እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም የብሄራዊ አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚቴ በአስቸኳይ ጊዜ የድጋፍ አሰጣጥ ሂደት አስፈፃሚ አካላት ያሳዩት ፈጣን ምላሽ እና ቅንጅታዊ አመራር ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
Via Deputy PMO

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሶማሌ ብሄራዊ ክልል በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የአንድ መቶ ሚሊዮን ብር የአይነት ድጋፍ አደረገ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወደ 2.4 ሚሊዮን የሚገመቱ ወገኖች የሚሆን የአንድ መቶ ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው የምግብ ቁሳቁስ እና የእለት ደራሽ ድጋፍ በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አማካኝነት ለክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ኡመር አስረክበዋል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በህልውና ዘመቻው ለተሳተፉ አትሌቶች እውቅና ሰጠ፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 25ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።በጉባኤ መክፈቻ ላይ የኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ባደረጉት ንግግር ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ስፖርቱን ለማሳደግ እንደሚሰራ አረጋግጠው ጉባኤው በይፋ መከፈቱን አብስረዋል።የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም በጉባኤው በህልውና ዘመቻ እስከ ግንባር ድረስ በመጓዝ ለተሳተፋ አትሌቶች ሻ/ቃ ሀይሌ ገ/ስላሴ፣ ገዛኸኝ አበራ፣ ማርቆስ ገነቲ፣ ፈይሳ ሌሊሳና ፋንቱ ማጊሶ እውቅና መስጠቱን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ቅዱስ ሲኖዶሱ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ላይ ሊያደርገው የነበረው ስብሰባ ተራዘመ!
ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 6 በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ሊያደርግ ያሰበው ስብሰባ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ባጋጠመቸው የጤና እክል ምክንያት ስብሰባው ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉ ተገለጸ።
ቅዱስነታቸው፣ በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ሆስፒታል ስለገቡና ቅዱስነታቸው በመንበራቸው ላይ በሌሉበት ሁኔታ ጉባኤውን ማካሔድ ስለማይቻል የቅዱስ ፓትርያርኩ ጤና እስከሚመለስ ድረስ ጉባኤው ላልተወሰነ ጊዜ የተላለፈ መሆኑን የቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ገልጿል።
[Addis Maleda]

ኢትዮ ቴሌኮም በብሔራዊ መታወቂያ ዋስትና የሞባይል ስልኮችን በዱቤ ሊሸጥ መሆኑን አስታወቀ!
ኢትዮ ቴሌኮም ስማርት ሞባይል ስልኮችን ለግለሰቦች በዱቤ ለመሸጥ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን፣ ሽያጩንም ብሔራዊ መታወቂያ ሲሰጥ እንደሚጀምር አስታወቀ።ስማርት የሞባይል ስልኮችን ድርጅቶች ዋስትና ለሚገቡላቸው ሠራተኞች በድርጅታቸው አማካይነት ላለፈው አንድ ዓመት በመሸጥ ላይ መሆኑን፣ እስካሁንም ከአሥር ሺሕ በላይ ስልኮችን መሸጡን ገልጿል።
ግለሰቦች ዋስትና ሊሆናቸው የሚችል ማስያዣ ማቅረብ ስለማይችሉና በሥራ ላይ ያለው መታወቂያ በቂ መተማመኛ ስለማይሆን፣ አገልግሎቱን ለማቅረብ አስቸጋሪ እንዳደረገውና በድርጅቶች አማካይነት ብቻ ሲሠራ እንደነበር የገለጹት የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ክፍል ኃላፊ አቶ መሐመድ ሃጂ ናቸው፡፡ በሚቀጥሉት ዓመታት ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ብሔራዊ መታወቂያ ይህንን ችግር ይፈታል ብለዋል፡፡
በዚህም መሠረት የዱቤ ሽያጩ ማንኛውም ግለሰብ የብሔራዊ መታወቂያ ከመያዝ በተጨማሪ፣ ብድሩን የመክፈል አቅሙ ተገምግሞ የዱቤ አገልግሎቱን የሚያገኝ መሆኑን ሌላ ተጨማሪ ዋስትና እንደማያስፈልገውም አብራርተዋል።
Via Reporter

ፌስቡክ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቃቶች እንዲባባሱ ማድረጉን እንዲመረምር ተጠየቀ!
የፌስቡክ ባለቤት የሆነው ሜታ ፌስቡክና ኢንስታግራም በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቃቶች እንዲባባሱ የነበራቸዉን ሚና ላይ ግምገማ እንዲያካሂድ በቁጥጥር ቦርዱ ተመክሯል።
ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ ዉስጥ ገልተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ግምገማ የሚያደርግ ኮሚሽን መመስረት የሚያስችለውን ሁኔታዎችን እያጠና መሆኑን በትላንትናው ዕለት ገልጿል።
ከወራቶች በፊት የፌስቡክ የቀድሞ ሰራተኛ የሆነችው ፍራንሲስ ሆገን ፌስቡክ በኢትዮጵያ እና ሚያንማር የጥላቻ ንግግሮች እንዲሰራጩና ጥቃቶችም የሚስፋፉበት መድረክ መሆኑን በማሳውቋ በተለያዩ አካላት ነቀፋ ሲቀርብበት ነበር።
Via Addis Zeybe

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኋላሸት ጀመረን የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን አሳውቀዋል፡፡
የኋላሸት ጀመረ የተሾሙት ባለስልጣን መ/ቤቱን ከመሰረቱትና ለረጅም ጊዜ በዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የነበሩት መኮንን አበራን በመተካት ነው።
[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
የኋላሸት ጀመረ የተሾሙት ባለስልጣን መ/ቤቱን ከመሰረቱትና ለረጅም ጊዜ በዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የነበሩት መኮንን አበራን በመተካት ነው።
[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ከደሴ እስከ ወልዲያ ሲከናወን የቆየው ጉዳት የደረሰባቸውን የኤሌክትሪክ መስመሮች የመጠገን ሥራ እየተገባደደ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመር ጥገና የቴክኒክ ድጋፍ ኃላፊ ገልፀዋል፡፡
ኃላፊው አቶ ተስፋዬ መንግስቱ እንዳስታወቁት እስከዛሬ ድረስ በተከናወነው ጥገና ጉዳት የደረሰበት መስመርና ምሰሶ ከ97 በመቶ በላይ ተጠናቋል፡፡
ቀሪ ሥራዎችን በርብርብ በማጠናቀቅ እስከ ወልዲያ ድረስ ያሉት ከተሞች ማምሻውን አልያም እስከ ነገ እኩለ ቀን ድረስ መብራት እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ከእስር የተፈቱት የባልደራስ አመራሮች በአፋር የጦር ቁሰለኞችን ጎበኙ!
በባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ የተመራው ልዑክ ዛሬ ጧት አፋር ገብቷል።የፓርቲው ልዑክ ቡድን በዛሬው ቆይታው ከሰመራ 10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ዱቢቲ ሪፈራል ሆስፒታል በማቅናት በግንባር የተጎዱ የጦር አባላትን ጠይቋል።
በአፋር ዱቢቲ ሪፈራል ሆስፒታል በጦርነቱ ሳቢያ የተጎዱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የአፋር ልዩ ኃይል፣ የአፋር ሕዝባዊ ሰራዊት እና ሚሊሻ እንዲሁም ቁስለኛ የህወሓት ሰራዊት አባላት ይገኛሉ።
በጉብኝቱ ወቅት የባልደራስ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ የጦር አባላቱ በግንባር ለከፈሉት የህይዎት እና የአካል መስዕዋትነት የተሰማቸውን ታላቅ ክብር በራሳቸውና በድርጅቱ ስም ገልፀው እውቅናም እንደሚሰጡት ተናግረዋል።
[Asham]

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት የተነሳ ነዳጅ እና ምግብ ከቦታ ወደ ቦታ ማዘዋወር ስላልቻልኩ የነፍስ አድን ሥራዎችን ከማቋርጥበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስጠንቅቋል።
ከታኅሳስ አጋማሽ ወዲህ ዕርዳታ ጫኝ ካሚዮኖቹ ወደ ትግራይ መግባት እንዳልቻሉ የገለጸው ድርጅቱ፣ ለዕርዳታ ሥርጭት ሥራው የነዳጅ እና ጥሬ ገንዘብ ዕጥረት እንደገጠመው፣ የሕጻናት እና ጡት አጥቢ እናቶች አልሚ ምግብ እንደተመናመነበት እና የመጨረሻውን የእህል፣ ጥራጥሬ እና ዘይት ክምችቱን በቀጣዩ ስምንት አከፋፍሎ እንደሚጨርስ ገልጧል። ድርጅቱ አያይዞም፣ ሁሉም የግጭቱ ተፋላሚ ወገኖች ለሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያስፈልጉ መንገዶችን ደኅንነት እንዲያስጠብቁ ጠይቋል።
[Wazema]

መንግሥት ፋኖን ትጥቅ ሊያስፈታ ነው የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት አስታውቋል።
የክልሉ መንግሥት ከፋኖ አደረጃጀት አባላት ጋር ተወያይቷል።ፋኖ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሀገርና ሕዝብን እየታደገ ያለ መከታ ኃይል ነው። ስለሆነም የፌደራልም ኾነ የክልል መንግሥት ፋኖን ትጥቅ የማስፈታት ሐሳብ የለውም፤ ሊኖረውም አይችልም ተብሏል በመድረኩ።
በቀጣይ የክልሉ መንግሥት የመሳሪያ አስተዳደር ሥርዓቱን ሊያሻሽል እንደሚችልም ተገልጿል።ፋኖ በስምም ሆነ በግብሩ የአማራ ሕዝብ ክብር መገለጫ በመሆኑ በፋኖ ስም የሚነግዱ አካላትን ፋኖና መንግሥት በጋራ ይታገላሉ ተብሏል።ፋኖን ማደራጀትና ማጠናከር የክልሉ መንግሥት አቅጣጫና ተግባር ኾኖ ሳለ ትጥቅ ማስፈታት የሚለው አሉባልታ አማራን የመከፋፈል እርስ በርስ የማጋጨት የማዳከም ሴራ አካል መሆኑም ተገልጿል።
[AMC]

PIXEL GRAPHIX + PRINTS
የተለያዩ ጥራታቸውን የጠበቁ የሕትመት ውጤቶችን እዚህ ያገኛሉ::
https://tttttt.me/+Vd_UT2L115fJyYK1
🔹የጥምቀት ቲሸርቶች በልዩ ዲዛይን
🔹የወረቀት ላይ ሕትመቶች
🔹የጥሪ ካርዶች
🔹ልዩ ልዩ ዲዛይኖች /Graphic Designs/logo designs/ branding
Branding . Advertising . Printing
Contact us for more @Hizk_X
+251921336809
ብዙ አማራጮች ስላሉን ይቀላቀሉ 👉

አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ በመጪው ሳምንት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ!
አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሱዳን እና ሳዑዲ አረቢያን ሊጎበኙ ነው ተባለ፡፡ሳተርፊልድ ከፈረንጆቹ ጥር 17-20 ባሉት ቀናት ነው ሃገራቱን የሚጎበኙት፡፡ በቅድሚያ ወደ ሪያድ እንደሚጓዙ የሚጠበቁት ልዩ መልዕክተኛው ቀጥሎ ካርቱምንና አዲስ አበባን ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ረዳት ጸሃፊ ሞሊ ፊ አብረዋቸው ወደ ሃገራቱ እንደሚጓዙም ነው ከመስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ የሚያመለክተው።በሱዳን ያለው ወታደራዊ አገዛዝ እንዲያበቃ የሚጠይቁ የለውጥ ኃይሎችን እንደሚያገኙና በመንግስታቱ ድርጅት አመቻችነት ለማካሄድ ስለታሰበው ሃገራዊ ውይይት እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል፡፡
ወደ ካርቱም ተጉዘውም ከተለያዩ የለውጥና የዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር እንዲሁም ከወጣት አደረጃጀቶች ጋር ይወያያሉ፡፡በኢትዮጵያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል፡፡መንግስት የተገኘውን የሰላም ጭላንጭል እንዲያጠናክር፣ የአየር ጥቃቶችን እንዲያቆምና ሌሎች መቃቃሮች እንዲያበቁ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገሩም ነው የተገለጸው፡፡ተኩስ እንዲቆም፣ እስረኞች አሁንም እንዲለቀቁና ሰብዓዊ እርዳታዎች ሳይስተጓጎሉ እንዲቀርቡ ይጠይቃሉም ተብሏል፡፡
[Alain]

የቦሌ ክፍለ ከተማ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ አገረ ስብከት የቦሌ ክፍለ ከተማ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ያሰባሰቡትን የ15 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው ድጋፍ ለክፍለ ከተማው አስተዳደር አስረክበዋል፡፡
በክፍለ ከተማው የሚገኙ ሰባት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናት ከምዕመናን ያሰባሰቡትን የ15 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው የተለያዩ ቁሳቁስን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ እና ጉራጌ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ መልከጸዴቅ ለቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዓለምጸሐይ ሽፈራው አስረክበዋል።
ብጹዕ አቡነ መልከጸዴቅ በርክክቡ ላይ ባደረጉት ንግግር የቦሌ ክፍለ ከተማ አብያተ ክርስቲያናት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ ባደረጉት ከፍተኛ እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ አገረስብከት በሞዴልነት የሚወሰዱ መሆናቸውን አውስተው፣ ለወገን ደራሽ ለመሆን የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ምስጋና እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ግጭቶችን የመፍታት እና የማርገብ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገለፀ!
የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ባለፉት ሦስት ዓመታት ግጭት ለመፍታት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት፣ የሽግግር ፍትሕ ለመስጠት፣ የሕዝቡን አብሮነት ለማጠናከር እና ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራ ሲሰራ መቆቱን ገልጿል፡፡
ኮሚሽኑ የሦስት ዓመታት እንቅስቃሴውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጠ ሲሆን÷ ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በትብብር በመስራትና እስከ ክልል ድረስ ጽህፈት ቤቶችን በመክፈት በክልል፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ ግጭቶችን የመፍታት እና የማርገብ እንቅስቃሴዎች ጀምሬያለሁ ነው ያለው፡፡
ስራው ለሀገራችን አዲስ እንደመሆኑ መጠን ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችን እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር ስለ ሰላም እና ዕርቅ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ መስራቱን አስታውቋል፡፡
Via FBC

ከደሴ እስከ ወልዲያ ያሉት ከተሞች ኤሌክትሪክ አግኝተዋል!
ከደሴ እስከ ወልዲያ ሲከናወን የቆየው ጉዳት የደረሰባቸውን የኤሌክትሪክ መስመሮች የመጠገን ሥራ ትናንት ምሽት ተጠናቆ ከተሞቹ ዛሬ ከ 10:05 ጀምሮ ኃይል አግኝተዋል።ጥገናው ትናንት ምሽት ቢጠናቀቅም መስመሩ በሚያልፍበት አካባቢ በደሴ እና በሀይቅ መካከል እንዲሁም መርሳ አካባቢ የበቀለ ዛፍ ከመስመሩ ጋር ተገናኝቶ ባለመቆረጡ የተነሳ ኤሌክትሪክ ማገናኘት አልተቻለም ነበር።
ይሁንና ዛሬ ዛፎቹ በመቆረጣቸውና ኃይል ለመስጠት የሚያግድ ነገር ባለመኖሩ ከተሞቹ ኤሌክትሪክ ማግኘት ችለዋል።
በተያያዘ ዜና ለወልዲያ ከተማና አካባቢው አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ የተዘረፈው ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያ የሚሰጠውን አገልግሎት የሚተካ ዘላቂ ሥራ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጀምሯል።የተጀመረው ሥራ በቀጣዮቹ ከአራት እስከ አምስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ከፍተኛ ኃይል ለመስጠት የሚያስችል ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከካናዳው አቻቸው ጀስቲን ትሩዶ ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከካናዳው አቻቸው ጀስቲን ትሩዶ ጋር በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከካናዳው አቻቸው ጀስቲን ትሩዶ ጋር በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ይማሩ የነበሩ 1700 የሚሆኑ ተማሪዎች መንግሥት እስካሁን ድረስ ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ሊመድበን አልቻለም በማለት ቅሬታ አቀረቡ።
ተማሪዎቹ በተወካዮቻቸው በኩል እንዳሉት ትግራይ ውስጥ በሚገኙ ተቋማት ይማሩ የነበሩ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ወደተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው እየተማሩ ሲሆን ወደ ባህርዳር፣ ጎንደር እና ደብረብርሃን እንደተመደብን ተነግሮን የነበርን ተማሪዎችን ግን ዩኒቪርሲቲዎቹ እንደማይቀቡሉ በመግለፃቸው መጉላላት ገጥሞናል ብለዋል።ለስምንት ወራት ያለምንም መፍትሔ መቀመጣቸውን የሚገልፁት ተማሪዎቹ የጉዳዩ ዋና ባለቤት ትምህርት ሚኒስቴር ችግሩን ሊፈታልን አልቻለም ብለዋል።
[DW]