YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
መንግሥት በሳዑዲ ዐረቢያ ችግር ላይ ያሉ 34 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እንደተዘጋጀ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን መናገራቸውን መንግሥታዊው ቴሌቪዥን ማምሻውን ዘግቧል፡፡ መንግሥት በሳምንት 1 ሺህ ስደተኞችን ለመመለስ ዕቅድ መያዙን ደመቀ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ልደቱ አያሌው እና ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን ተቀላቀሉ።

ከአንድ ወር በፊት ፓርቲያቸው በምርጫ ቦርድ የታገደባቸው አቶ ልደቱ አያሌው እና ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን መቀላቀላቸው ተገልጿል።

ኢዴፓ፣ ኢሀንና ህብር ኢትዮጵያ ነገ በይፋ ሊዋሀዱ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ (ኢሀን) እና ህብር ኢትዮጵያ በይፋ ተዋህደው በአንድ ፓርቲ ስር ሊሰሩ ነው።

ኢሀንና ኢዴፓ በምርጫ ቦርድ ከምርጫው የተሰረዙ ሲሆን ህብር ኢትዮጵያ ግን በምርጫው ለመወዳደር ፍቃድ በማግኘቱ ተዋህደው በህብር ኢትዮጵያ ስም ሊሰሩ መሆኑን ሰምተናል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ (ኢሀን ) ሊቀ መንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ለኢትዮ ኤፍ ኤም ይሄንኑ ያረጋገጡ ሲሆን ነገ በዚሁ ውህደት ዙርያና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ እንሰጣለን ብለውናል።

ህብር ኢትዮጵያ፣ ኢሀንና ኢዴፓ ኢትዮጵያ ህልውናዋ አደጋ ስለተጋረጠበት ፓርቲዎቻችን በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል በሚል አብሮነት ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነትን መስርተው በጋራ ሲሰሩ ቆይተዋል።

አሁን ይሄ ስብስብ ከነገ ጀምሮ አንድ ፓርቲ ሆኖ እንደሚቀጥል ኢንጅነር ይልቃል ነገረውናል።

የኢዴፓው አቶ ልደቱ አያሌው እና የኢሀኑ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተከትሎ በተነሳው ረብሻ ተጠርጥረው ለወራት ከታሰሩ በኋላ በዋስ ከእስር መፈታታቸው የሚታወስ ነው።

Via Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚመራው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) እራሱን ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) በማግለል በቀጣዩ 6ኛው ብሔራዊ ምርጫ በተናጠል እንደሚወዳደር ዐስታወቀ፡፡

በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚመራው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) እራሱን ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) በማግለል በቀጣዩ 6ኛው ብሔራዊ ምርጫ በተናጠል እንደሚወዳደር ዐስታወቀ። የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለዶይቼ ቬለ እንዳረጋገጡት በተለይም ለፓርቲያቸው ከመድረክ ለመውጣት መወሰን ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ጋር እየተፈጠረ የመጣው ልዩነት ዋነኛው ምክኒያት ነው።

የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በበኩላቸው እንዳረጋገጡት ኢሶዴፓ በራሱ ፈቃድ ከመድረክ እየተገለለ መምጣቱ እውን ቢሆንም ፊቺው ግን ገና በይፋ በጠቅላላ ጉባኤ ያልተደመደመ ነው ብለዋል።

ኦፌኮ በመድረክ ስር በተለመደው ሁኔታ ይቀጥላል ያሉት አቶ ሙላቱ የተለያዩ ፓርቲዎች መድረክን በጥምረት ለመቀላቀል ጥያቄ እያቀረቡም ይገኛሉ ነው ያሉት።

Via DW
@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ

ከ3,200 በላይ ዕቃዎች

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com

📞 0953707070

Dedicated online shopping platform
ዋሽንግተን የሩስያና ቱርክ ጦር ሊቢያን ለቆ እንዲወጣ ጥሪ አቀረበች


የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት እንዳስታወቀው የአሜሪካ ጦር በፍጥነት ሊቢያን ለቆ በመውጣት የተደረሰበትን ስምምነት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል።

በወርሃ ጥቅምት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና ከተሰጠው የሊቢያ መንግስት ጋር በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በሶስት ወር ውስጥ የውጪ ሀገራት የጦር ሀይሎች ሊቢያን ለቀው እንዲወጡ መስማማታቸው አይዘነጋም።

ይህው ቀነ ገደብ ባሳለፍነው ቅዳሜ ቢጠናቀቅም የሩሲያና የቱርክ ጦር አሁንም ሊቢያን ለቀው ለመውጣት ምንም እንቅስቃሴ እያደረጉ አይደለም ስትል ዋሽንግተን ተናግራለች።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ላይ በሊቢያ ጉዳይ ንግግር ያደረጉት አምባሳደር ሪቻርድ ሚልስ ቱርክ፣ሩሲያና ኢምሬትስ የሊቢያን ሉዐላዊነት በማክበር ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በሊቢያ 20ሺ ያህል የውጪ ሀገራት ወታደሮች የሚገኙ ሲሆን ቱርክ የትሪፖሊን መንግስት ስትደግፍ ተቀናቃኙ የጄነራል ሀፍታር ሀይሎች ጠንካራ የፈረንሳይ ሩሲያ፣ግብፅና ኢምሬትስ ድጋፍ አላቸው።

በስምኦን ደረጄ/ብስራት ሬድዮ

@Yenetube @Fikerassefa
ኖቫቫክስ የተሰኘ አዲስ የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድሃኒት 89 በመቶ በሽታውን የመከላከል አቅም እንዳለው ተነገረ

ኖቫቫክስ እንዳስታወቀው ለክትባት መድሃኒቱ በተደረገው የሶስት ዙር የሙከራ ሂደት ቫይረሱን የመከላከል አቅሙ 89.3 በመቶ የመከላከል አቅም አለው።ከ15 ሺ በላይ ሰዎች ላይ የክትባት መድሃኒቱ ሙከራ ተደርጎበታል።

ኖቫቫክስ እንዳስታወቀው ሙከራ የተደረገባቸው ሰዎች የእድሜ ክልል ከ18 እስከ 84 ባሉ ሰዎች ላይ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 27 በመቶ ያህሉ እድሜያቸው ከ85 ዓመት በላይ ናቸው።

የእንግሊዝ የጤና ዋና ፀሀፊ ማት ሀንኩክ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት የክትባት መድሃኒቱን እውቅና ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

እንግሊዝ ለሶስት የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድሃኒቶች እውቅና የሰጠች ሲሆን በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲና በአስትራዜኔካ ለተሰራው፣በፋይዘርና በሞደርና ለተሰሩት ናቸው።

በሚኪያስ ፀጋዬ/ብስራት ሬድዮ
@Yenetube @Fikerassefa
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በከተማ አስተዳደሩ ፈቃድ እንዳላገኘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ!

የአዲስ አበባ ከተማ የከንቲባ ፅ/ቤት አስተዳደር ጉዳዩች ዘርፍ ጥር 18 ቀን 2013 ዓ/ም በቁጥር አ/አከፀ 18 /03/ 128 ለባልደረሳስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በፃፈው ደብዳቤ ሰልፉ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ተቀባይነት እንዳላገኘ ምላሽ የሰጠ ሲሆን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንም በግልባጭ አሳውቋል።

የተጠራው ሰልፍ ፍቃድ ባያገኝም ጥር 23 ቀን 2013 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች መልእክት እየተላለፈ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

ተቀባይነት ያላገኘ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውሶ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን የሚሉም ሆነ መረጃውን እያሰራጩ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ኮሚሽኑ አሳስቧል።

የፖሊስን መልዕክት ተላልፈው ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት ላይ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
282 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ!

282 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው በትላንትናው እለት ተመልሰዋል።የተመለሱት ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይረክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
‹‹ሱዳኖች ያለ ጦርነት በጦርነት እንዳሸነፉ እያሰቡ ነው››
- አብዱረህማን ጀማል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድንበርና የድንበር ተሻጋሪ ሀብቶች ዳይሬከተር ጄኔራል

ኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል ባጋጠማት ችግር ምክንያት የህግ ማስከበር ሂደት ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ሱዳኖች የተያዘብንን መሬት አስመለስን በማለት ያለ ጦርነት በጦርነት እንዳሸነፉ እያሰቡ መሆናቸውን በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድንበርና የድንበር ተሻጋሪ ሀብቶች ዳይሬከተር ጄኔራል አብዱረህማን ጀማል አስታወቁ።

ዳይሬከተር ጄኔራል አብዱረህማን የኢትዮ-ሱዳን ወቅታዊ ጉዳይን በተመለከተ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ በአሁን ወቅት ሱዳኖች እየፎከሩ ያሉት የተያዘብንን መሬት አስመለስን በማለት ነው።

መሬቱን የያዙት ኢትዮጵያ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የህግ ማስከበር ሂደት ውስጥ በገባችበት ጊዜ ነው ፣ በአካባቢው የነበረው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ወደትግራይ ክልል ማቅናቱን ተከትለው ነው። በዚህም ሱዳኖቹ ያለ ጦርነት ሠራዊቱ በሌለበት በጦርነት እንዳሸነፉ ነው እያሰቡ ያለው።

ሱዳኖቹ ጠባቂ በሌለበት ብዙ ጉዳት አድርሰዋል። ብዙ ዜጎቻችንንም አፈናቅለዋል። ለሞትም ዳርገዋል፤ ንብረታቸውን ዘርፈዋል። ሀብታቸውንም አቃጥለውባቸዋል ያሉት አቶ አብዱረህማን ጀማል፣ ሴቶችንም እስከመድፈር ደርሰዋል እዛ አካባቢ በሱዳን ወታደር እየተደረገ ያለው ሁኔታ ተገቢ እንዳልሆነም አመልክተዋል።

ሱዳን ይህን ያደረገችው ኢትዮጵያ ሽግግር ላይ ነች፤ የውስጥ ፖለቲካዋም ትክክል አይደለም በሚል ልክ ባልሆነ ስሌት መሆኑን ያስታወቁት አቶ አብዱረህማን ጀማል ፤ ይህን አጋጣሚ እንደ ዕድል ወስደን ነገሩን እናስተካክላለን ማለታቸው የተሳሳተ ስሌት ነው ብለዋል።

የሱዳን ወታደሮች ሁለት ስህተት ሠርተዋል ያሉት ዳይሬክተር ጄኔራሉ፣ የመጀመሪያው እኤአ የ1972 ስምምነትን ሙሉ በሙሉ ጥሰዋል። ይህንን ስምምነት በዓለም አቀፍ መድረክ ዓለም አቀፍ ሰነዴ ነው ብለው ያሳወቁት ሱዳኖች እራሳቸው ናቸው። ሁለተኛው ስህተት ደግሞ በዜጎቻችን ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ነው ብለዋል።

ዕርምጃው በሁለቱ ሀገሮች ህዝቦች መካከል የነበረውን ረጅም ዘመን ያስቆጠረውን የወንድማማችነት እና የጉርብትና መንፈስ ያልተከተለ፣ የነበረውን ግንኙነት ችግር ውስጥ የሚከትና፣ ነባራዊ ሁኔታውን እየቀየረ ያለ ክስተት መሆኑን አስታውቀዋል።

(ኢፕድ)
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ተቀስቅሶ በነበረው ሁከት ሳቢያ ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው ለነበሩና በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ቤት ውጪ ለሆኑ ሕፃናት የአስቸኳይ ጊዜ የተከታታይ ዓመት ትምህርት መርኃግብር ይፋ ሆነ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር፣ የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ)፣ ጄኔቫ ግሎባል እና ኢጁኬሽን ካንኖት ዌት ይፋ ያደረጉት ፕሮግራም፣ በምሥራቅ ሐረርጌ አራት ዞንና በምሥራቅ ወለጋ ዞን አንድ ወረዳ ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተሰምቷል፡፡

ኤጁኬሽን ካንኖት ዌይት የተባለው ተቋም ለመርኃግብሩ ማስጀመሪያ 82 ነጥብ 14 ሚሊዮን ብር፣ እንዲሁም ጄኔቫ ግሎቫል 6 ሚሊዮን ብር እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች 14 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በመመደብ በዓመት 8 ሺ 274 ሕፃናትን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ እየሠሩ መሆናቸውንም ተሰምቷል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በነበረው ሁከት ምክንያት ከትምህርት ገበታ የተፈናቀሉ ሕፃናትና ቀደም ሲል በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከትምህርት ቤት ውጪ የነበሩ እድሜቸው ከ9 እስከ 14 የሆናቸው ሕጻናት ያባከኑትን የትምህርት ጊዜ በተፋጠነ የትምህርት አሰጣጥ መርኃግብር በመደገፍ ከዕድሜ አቻዎቻቸው ጋር በክፍል እንዲስተካከሉ ማድረግ የመርኃግብሩ ዓላማ ነው ተብሏል፡፡

አካል ጉዳተኛ እና ሴት ሕጻናትን በበለጠ ይጠቅማል በተባለው የአስቸኳይ ጊዜ የትምህርት መርኃግብር በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከ30 ሺህ የሚበልጡ ሕፃናትን በትምህርት፣ እንዲሁም ከ30 ሺ የሚበልጡ እናቶቻቸውን ደግሞ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

በግጭቱ ምክንያት ከምሥራቅ ሐረርጌና ከኦሮሚያ ዞኖች ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው የነበሩና ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ ሕፃናት የአስቸኳይ ትምህርቱን ከጀኔቫ ግሎባልና ከኢጁኬሽን ካንኖት ዌት ጋር በመተባበር ተግባራዊ የሚያደርጉ አምስት ግብረሰናይ ድርጅቶች በውድድር መመረጣቸውንም የጄኔቫ ግሎባል ዓለምአቀፍ ተቋም የኢትዮጵያ ቢሮ ዳይሬክተር ሳሙኤል አስናቀ ሲናገሩ ተሰምቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ በ2018 ሰራሁ ባለው ጥናቱ መሠረት ዕድሜአቸው ለትምህርት የደረሱና ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሲገባቸው ከትምህርት ቤት ውጪ የሆኑ ሕፃናት ቁጥር በኢትዮጵያ ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ነው ብሏል፡፡

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ኑሮውን በጅማ ከተማ ያደረገውና የወርልድ ቴኳንዶ ስፖርትን ከተወዳዳሪነት ተነስቶ ወደ አሰልጣኝነት ደረጃ ደርሶ የነበረው ይታገሱ ኃ/ሚካኤል በድንገተኛ አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

@Yenetube @Fikerassefa
በእነ ስብሃት ነጋ የምርመራ መዝገብ የተካተቱ 9 ተጠርጣሪዎች ተጨማሪ 14 ቀናት ተፈቀደባቸው፡፡

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ለ2ኛ ጊዜ ቀርበው ጉዳያቸው መታየቱን በስፍራው የነበሩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ስብሃት ጨምሮ በመዝገቡ የተካተቱ 9ኙም ተጠርጣሪዎች ችሎት ፊት ቀርበዋል። በዚህም በመጀመሪያው ችሎት በህመም ምክንያት ያልቀረቡት አባይ ወልዱና ሰለሞን ኪዳኔ በአርብ ረፋዱ ችሎት ተገኝተዋል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ ቡድን ፍርድ ቤቱ ባለፈው በተሰጠው ቀጠሮ ያከናወነውን ለችሎቱ ያብራራ ሲሆን፤ የእያንዳንዳቸውን የወንጀል ተሳትፎ በምርመራ ማረጋገጡን ገልጿል።

ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል በማለት ተጨማሪ 14 ቀን መጠየቁን ተከትሎም ችሎቱ ቀኑን ፈቅዶለታል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
አብን፣ መኢአድ እና ባልደራስ ፓርቲዎች ጥምረት ሊፈጥሩ መሆኑን አስታወቁ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት( መኢአድ) እና ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በቀጣዩ 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ አዲስ አበባ ጥምረት ሊፈጥሩ መሆኑን አስታውቀዋል።

የአብን ምክትል ሊቀመንበር እና የምርጫ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ የሱፍ ኢብራሒም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ሶስቱ ፓርቲዎች በጥምረት ሊሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ጥምረቱ በሶስቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች መካከል ውይይት ተደርጎ ስምምነቱ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የተደረሰ ሲሆን በቀጣይ በፓርቲዎቹ የማዕከላዊ ኮሚቴ ይጸድቃል ብለዋል።

ጥምረቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤቶች የጋራ እጩዎችን ማቅረብ እና ሌሎች የፖለቲካ ስራዎችን እንደ አንድ ፓርቲ ለማከናወን ያስችላልም ብለዋል አቶ የሱፍ በቀጣይ ተመሳሳይ አላማ ካላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋርም ተመሳሳይ ጥምረት ለማካሄድ ድርድሮች በመካሄድ ላይ እንደሆኑም አቶ የሱፍ ነግረውናል።

አቶ ልደቱ አያሌው እና ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን መቀላቀላቸው ይታወሳል።

ከአንድ ወር በፊት ፓርቲያቸው በምርጫ ቦርድ የታገደባቸው አቶ ልደቱ አያሌው እና ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የፓርቲዎቻቸው አባላትን ይዘው ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን መቀላቀላቸው ተገልጿል።

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
በ4 ነጥብ5 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የዘይት ፋብሪካ በቅርቡ ይመረቃል ተባለ!

በኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ በላይነህ ክንዴ በአራት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የዘይት ፋብሪካ በቅርቡ እንደሚመረቅ ባለሀብቱ ገለጹ።የበላይነህ ክንዴ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ በላይነህ ክንዴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ ፕሮጀክት ላለፉት ስድስት ዓመታት ግንባታ ላይ መቆየቱንና አጠቃላይ ወጪውም 4ነጥብ5 ቢሊዮን ብር ደርሷል።ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት የሙከራ ምርት የጀመረ መሆኑንና የሚመለከተውን የመንግስት አካል ይሁንታ ሲያገኝ በቅርቡ ምርቱ ወደ ገበያ እንደሚቀርብም አቶ በላይነህ አስታውቀዋል።

በአገሪቱ 45 ከመቶ በላይ የሚሆነውን የዘይት ፍላጎት ከመሸፈን ባሻገር ለውጭ ገበያ ምርቶችን መላክን ያነገበው የዘይት ፋብሪካ በቅርቡ ይመረቃል ብለዋል፤ አቶ በላይነህ።እንደ አቶ በላይነህ ገለፃ፤ ፋብሪካው ዘይት ብቻ አያመርTም። ሰባት ፋብሪካዎችን በውስጡ ያቀፈ ሲሆን፤ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የሚዘልቁ ዘመናዊ ግንባታዎች የተካተቱበት ነው። በርካታ ማሽኖችም በትልቅ ኃላፊነት የተገዙ ሲሆን ጥራታቸውን የጠበቁ እና ለቀጣይ ትውልድ ጭምር ግልጋሎት የሚሰጡ ይሆናሉ ያሉት አቶ በላይነህ፤ የዚሁን ሥራ ለማፋጠን ሲባልም 160 ከባድ መኪናዎች ገላን በሚገኘው የድርጅቱ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካው ተገጣጥመው ለሥራ ዝግጁ ተደርገዋል ብለዋል።

ፋብሪካው በቀን 1ነጥጥብ5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ያመርታል ያሉት አቶ በላይነህ፤ ፋብሪካው በዓመት 20 ሚሊዮን ኩንታል የቅባት እህሎችን የሚፈልግ ቢሆንም የአገሪቱ ዓመታዊ የማምረት አቅም ከሦስት ሚሊዮን ኩንታል የሚበልጥ እንዳልሆነ ገልጸዋል።የግብአት ችግሩን ለመፍታት ከውጭ ድፍድፉን በማምጣት ምርት በማምረት ላይ እንደሆነ የገለጹት አቶ በላይነህ፤ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከአርሶ አደሮች እና መንግስት ጋር የተቀናጀ አሰራር በመዘርጋት ምርቱን በአገር ውስጥ መሸፈን እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብክ በግጭት ምክንያት ከ200ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተፈናቀሉ፡ተመድ
በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ከ200ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ከተፈናቀሉት መካከል ግማሽ ገደማ የሚሆኑት ወደ ጎረቤት ሀገራት መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) አስታወቀ፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
🖼 ለጓደኛ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለሙሽሮች እና ለተመራቂዎች ለየት ያለ ስጦታ መስጠት ይፈልጋሉ?
#join
👇👇👇👇
@giftsoflovee
@giftsoflovee
👆👆👆👆
📱+251914839754
📱+251936871620
#ኣድራሻችን፡ 4 ኪሎ: ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ
የሲዳማ ክልል የ8ኛ ክፍል ውጤት በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ይፋ ይደረጋል።

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የ2012 ዓ.ም የ8ተኛ ክፍል የፈተና ውጤት በቅርቡ እንደሚሰጥ የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ ዛሬ ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት ፈተናው ታርሞ የተጠናቀቀ ሲሆን እስከሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ለተማሪዎች እንደሚሰጥ በክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊና መማ/ማስ/ምዘና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታፈስ ገ/ማርያም አሳውቀዋል።

Via:- Affini
@Yenetube @Fikerassefa
ትናንት ሁለት ከፍተኛ የመንግስታቱ ድርጅት ባለስልጣናት ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል


ትናንት ሁለት ከፍተኛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ነበሩ፡፡

ባለስልጣናቱ ኢትዮጵያ የነበሩት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በተለይም ተጠናቋል በተባለው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና ዘመቻውን ተከትሎ እየተደረጉ ባሉ ሰብዓዊ ድጋፎች ዙሪያ ከከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ለመምከር ነው፡፡

ከሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚልም ጋር መክረዋል፡፡

ባለስልጣናቱ የድርጅቱ የደህንነት ዋና ጸሀፊ ጊልስ ሚካድ እና የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ናቸው፡፡

ወ/ሮ ሙፈሪያት ቀደም ሲል በተጠቀሱት በኢትዮጵያ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚ/ር ጊልስ ሚካድ ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበረሰብ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

በትግራይ ክልል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ እየተከናወኑ ስላሉ የሰብዓዊ ድጋፍ እና የመልሶ ማቋቋም ተግባራት ጥልቅ ውይይት ማድረጋቸውን የገለጹም ሲሆን በቀጣይ የድጋፍና ትብብር መስኮች ላይ ተመካክረናል ብለዋል።

ሚኒስትሯ ከስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነሩ ፊሊፖ ግራንዲ እና ልዑካቸው ጋር በሰብዓዊ ዕርዳታና ስደተኞች ጉዳይ ዙርያ ውይይት ማድረጋቸውንም ነው የገለጹት፡፡

በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ባሉ እና አፋጣኝ ምላሽ በሚሹ ጉዳዮች ላይ በቀጣይ ይበልጥ በትብብር መስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ እንደተወያዩም ጽፈዋል፡፡
በቀጣይ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናልም ብለዋል ወ/ሮ ሙፈሪያት፡፡

Via Alian
@Yenetube @Fikerassefa
የደወንሌ ድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሽከርካሪ ማቆያ ተርሚናል ዛሬ ይመረቃል።

በሲቲ ዞን አይሻአ ወረዳ የተገነባው የደወንሌ ድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሽከርካሪ ማቆያ ተርሚናል ዛሬ ይመረቃል።

በትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራው ከፍተኛ የፌዴራል መንግሥት የስራ ሀላፊዎችም ድሬደዋ ገብተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
በአዳማ ከተማ ለእንግድነት ከወላጅ እናቱ ጋር የሄደ የ18 ወር ህፃን በጅብ ተበላ!

በአዳማ ከተማ መስተዳድር ዳቤ ክፍለ ከተማ ዳቤ ሹሉቄ ቀበሌ ልዩ ቦታው ቀጠና 9 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ለእንግድነት ከወላጅ እናቱ ጋር የሄደ የ 18ወር ህፃን በጅብ ስለመበላቱ ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

በተጠቀሰው እለት ከምሽቱ 3ሰዓት ላይ አንዲት እናት የአንድ ዓመት ከስድስት ወር ህፃን ልጇን በመታቀፍ አቶ ሚኒሊክ ታዬ ከተባሉ ግለሰብ ቤት ታቀናለች።

ጫካ አፋፍ ላይ ከሚገኘው መኖሪያ ቤት ደርሳም ቡና ተፈልቶላት ከቤተሰቡ ጋር በመጫወት ላይ ሳለች ፤ ከጫካው የወጣ ጅብ ህፃኗን ከእናት እቅፍ ፈልቅቆ በመውሰድ ይሰወራል።

የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ በተለይ ለብስራት ራዲዮ ሪፓርተር ሚኪያስ ፀጋዬ እንደተናገሩት ፤ በሁኔታው የተደናገጠው ቤተሰብ ጅቡን ተከታትለው ወደ ጫካ ቢገቡም ሊያገኙት የቻሉት ብቸኛ ነገር የህፃን ጨርቅ ብቻ ሁኗል።

ጉዳዩ ለአዳማ ከተማ ፖሊስ ሪፖርት የተደረገ ሲሆን የምርመራ ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛል ያሉት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ፤ በቅርብ ግዜያት መሰል አደጋ በከተማዋ ሲፈጠር ይህ ለሶስተኛ ግዜ መሆኑንም አስታውሰዋል።

[ብስራት ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa