YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ባካሄደው ስብሰባ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ፤ ባለቤት አልባ ህንፃዎች፤ የኮንደሚኒየም ቤቶች፤ የቀበሌ መኖርያና ንግድ ቤቶችን አስመልክቶ በጥናት የተገኘው ግኝትቶች ላይ የውሳኔ ሃሳብ አስተላለፈ፡፡

የከተማው ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የከተማው አመራር በሪፎርሙ በገባው ቃል መሰረት ምንም እንኳ ቢዘገይም የነዋሪው ቅሬታ መነሻ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት እና በተጨባጭ ጥናት በመመርኮዝ ለማጣራት እና ለመለየት የተደረገውን ጥረት ያመሰገኑ ሲሆን ወደፊት መወሰድ አለበት ባሉት እርምጃ ላይ አፅንኦት ሰተው ተወያይተዋል፡፡በመሆኑም በጥናቱ የተገኙ 322 ባለቤት አልባ ህንጻዎች በግልፅ ጨረታ ተሸጠው ወደ መንግስት ካዝና ገቢ እንዲሆኑ፤ በጥናቱ የተገኘው ህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ፤ ባዶ ሆነው የተገኙ 21,695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በማስለቀቅ ለተጠቃሚዎች እንዲታደል፤ በዋናነት በ1997 ተመዝጋቢ የሆኑና በቋሚነት እየቆጠቡ ላሉ ነዋሪዎች በእጣ እንዲተላለፍ፤ የቀበሌ ቤቶችን አስመልክቶ በህገ-ወጦች የተያዙ የመኖርያ ቤቶች ግልፅ የሆነ መስፈርት ወቶላቸው ለደሆች፤ ለአቅመ ደካሞችና ለተለያየ ችግር ለተጋለጡ ነዋሪዎች እንዲሰጥ፤ የቀበሌ የንግድ ቤቶች በህገ-ወጥነት ከያዙት ሰዎች ተነጥቆ ለስራ አጥ ወጣቶች በእጣ እንሰጥ ሲሉ ወስነዋል፡፡ካቢኔው በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ በሰፊው የተወያየ ሲሆን ይህ ችግርና ስርዓት አልበኝነት 1997 ጀምሮ እየተንከባለለ የመጣ መሆኑን እና ወደፊት እንዳይደገም እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በትግራይ ክልል የሚገኙ የኤርትራ ስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎችን ጎበኙ፡፡

ኮሚሽነሩ በማይ ዐይኒ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ የኤርትራውያን ስደተኞችን ነው የጎበኙት፡፡

በጉብኝቱ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ተሳትፈዋል።

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ጎንደር ዞን ሰዴ ሙጃ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ!

መነሻውን ከባሕር ዳር ያደረገው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ሰዴ ሙጃ ወረዳ ሲደርስ 200 ሜትር ከሚረዝም ገደል በመግባቱ የ24 ሰዎች ህይወት ማለፉን የደቡብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ጋሻው አለኸኝ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች በደብረታቦርና በፈለገሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ኮማንደር ጋሻው ለአብመድ በስልክ ገልፀዋል፡፡የአደጋው መንስዔ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ኮማንደሩ አመላክተዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ለመምህራን ይከፈል የነበረውን የቤት አበል ከብር 850 ወደ ብር 3 ሺህ እንዲሻሻል ወሰነ!

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ለመምህራን ይከፈል የነበረውን የቤት አበል ከብር 850 ወደ ብር 3 ሺህ እንዲሻሻል መወሰኑ ተገለጸ፡፡

የከተማ መስተዳድሩ ካሁን በፊት በከተማው ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩ መምህራን 5 ሺህ የመኖርያ ቤት ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ሆኖም ለሁሉም መምህራን በፍጥነት ቤት ማዘጋጀት ባለመቻሉ፤ ለሁሉም መምህራን 3 ሺህ ብር የቤት አበል ክፍያ እንዲከፈላቸው የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ዛሬ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ካቢኔው በተጨማሪም የከተማ የቦታ ደረጃና የመሬት ሊዝ ዋጋን አስመልክቶ በጥናት የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ አፀደቀ፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያጠናው ይህ የመነሻ ሃሳብ ከአሁን በፊት የከተማ ቦታ ደረጃ 14 የነበረውን ወደ 18 ከፍ እንዲል፤ እንዲሁም የሊዝ መነሻ ዋጋ በ18ቱም የቦታ ደረጃዎች ተጠንቶ መቅረቡ ነው የተገለጸው፡፡

የጥናቱ ዋና አላማ በዝቅተኛ ሁኔታ ኑሯቸውን የሚመሩ ዜጎችን እንዳይጎዱ፤ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት፤ ባለሃብቶች ወደ ኢንቨስትመንቱ እንዲገቡ ለማድረግ፤ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን እና ልማትን ለማፋጠን የሚረዳ መሆኑን ተገልጿል፡፡

ጥናቱ አጠቃላይ የከተማ አስተዳደሩ በተለያየ አግባብ የሚያወጣቸውን ወጪ መነሻ በማድረግ በሳይንሳዊ መንገድ እንዲጠና በመደረጉ ባለፉት ሁለት አመታት መሬት በምደባ ብቻ ይሠጥ የነበረውን አሁን ግን በምደባም በጨረታም ለመስጠት ያስችላልም ተብሎአል፡፡

ነባር ይዞታዎችና ሰነድ አልባ ቦታዎች ቀድሞ ባለው መመሪያ 11/2004 የሚስተናገዱ ይሆናሉ በማለት ካቢኔው መወሰኑን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በሱዳን ወረራ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ከ226 ሚ.ብር በላይ ንብረት መዘረፋቸውን ተናገሩ!

የዛሬ 2 ወር ገደማ የሱዳን ጦር በሃይል ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ገብቶ የመሬት ወረራ ሲፈፅም ከ226 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት፤ መዘረፋቸውን የአካባቢው ባለሃብት አርሶ አደሮች ለአዲስ አድማስ የገለፁ ሲሆን መንግስት አስቸኳይ ድጋፍ አድርጎላቸው፣ ወደ ስራቸው መመለስ እንዲችሉ ጠይቀዋል፡፡
16 የሚደርሱ ባለሀብት አርሶ አደሮች በሱዳን ወታደሮች ወረራና ጥቃት እያንዳንዳቸው ከ2.5 ሚሊዮን እስከ 39 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት እንደተዘረፉ ተናግረዋል፡፡ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት ተኩል ላይ ባልጠበቅነው ሁኔታ ነው ጥቃት የተፈፀመብን የሚሉት ባለሃብት አርሶ አደሮቹ፤ ቋሚ ንብረታቸውን ጨምሮ በማሳ ላይ የነበረ የደረሱ የሰሊጥና የማሽላ ሰብልም መዘረፋቸውን ነው ለአዲስ አድማስ ያስረዱት፡፡

[Addis Admas]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ዕዳ ተረክቦ የሚያስተዳድር ኮርፖሬሽን ልታቋቁም ነው።

የኢትዮጵያ የምኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት "ከፍተኛ የዕዳ ጫና ያለባቸውን የመንግስት የልማት ድርጅቶች የዕዳ ጫና ለማቃለል የቀረበ የውሳኔ ሐሳብ እንዲሁም የዕዳ እና የሐብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን" ማቋቋሚያ የደንብ ረቂቅን አጽድቋል።የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጽህፈት ቤት ይፋ ባደረገው መግለጫ የመንግስት የልማት ድርጅቶች በነበሩባቸው እንከኖች "ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር በብድር የወሰዱትን ገንዘብ መክፈል አልቻሉም" ብሏል። "ተለይተው የሚሰጡትን የልማት ድርጅቶች ዕዳዎች የሚያስተዳድር እንዲሁም በጥናት በተለዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የሚሰማራ ብሎም ውጤታማ የዕዳ እና የሐብት አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት የሚያስችል ኮርፖሬሽን" እንዲቋቋም ውሳኔ መተላለፉንም የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።የኢትዮጵያ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ እንደሚያሳየው አገሪቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ 21 የልማት ድርጅቶች አሏት። ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና የስኳር ኮርፖሬሽን ከእነዚህ መካከል ይጠቀሳሉ።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የመቐለ ከተማን ነዋሪ ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያግዙ ከ400 በላይ ነባር የፖሊስ አባላት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውን የከተማዋ ጊዜያዊ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በጽህፈት ቤቱ የወንጀል መከላከል ሃላፊ ኢንስፔክተር ሠለሞን ገብረመድህን ለኢዜአ እንደገለጹት ወደ ስራቸው የተመለሱት በተደረላቸው ጥሪ መሰረት ቀደም ሲል በከተማው ከነበሩት ከ800 በላይ የፖሊስ አባላት መካከል ነው።

ወንጀልን በመከላከል የከተማዋን ነዋሪ ህዝብ ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የፖሊስ አባላቱ መደበኛ ስራቸው መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅት በክፍለ ከተማ ደረጃም የፖሊስ አባላትን የማደራጀት እየተከናወነ መሆኑን ኢንስፔክተር ሠለሞን አስረድተዋል።

ህብረተሰቡ ሠላምና ፀጥታውን በማስጠበቅ ተሳታፊ መሆን እንዳለበት ያመለከቱት ኢንስፔክተር ሠለሞን በቀጣይም በቀበሌ ደረጃ የኮሚኒቲ ፖሊስ የማደራጀት ስራ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

በከተማ ደረጃ ወንጀሎችን የመከላከል ስራ መቀጠሉን ገልጸው በእስካሁኑ ሂደትም ልዩ ልዩ ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠሩ45 ግለሰቦች መያዛቸውንና ጉዳያቸው ተጠርቶ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የህዳሴው ግድብ ግንባታ በታቀደለት ጊዜና በሚፈለገው መንገድ እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ!

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ እና የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ ቦርድ አባላት በትናንትናው ዕለት በስፍራው በመገኘት ግምገማ አድርገዋል። ከጉብኝቱ በኋላ ፣ የግድቡ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ እየተከናወነ እንደሆነና የግንባታ ሂደቱም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡ሚንስትሩና የቦርድ አባላቱ የግንባታ ስራውን ከሚያከናውኑ ኮንትራክተሮች ፣ ከባለሙያዎችና አማካሪዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡ ለግድቡ መጠናቀቅ መላው ኢትዮጵያውያን ከሃገር ውስጥና ውጪ እያደረጉት ያለው ድጋፍ ከምን ግዜውም በላይ ተጠናክሮ ቀጥሏልም ነው ያሉት።

@YeneTube @FikerAssefa
የህዳሴው ግድብ ግንባታ በታቀደለት ጊዜና በሚፈለገው መንገድ እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ!

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ እና የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ ቦርድ አባላት በትናንትናው ዕለት በስፍራው በመገኘት ግምገማ አድርገዋል። ከጉብኝቱ በኋላ ፣ የግድቡ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ እየተከናወነ እንደሆነና የግንባታ ሂደቱም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡ሚንስትሩና የቦርድ አባላቱ የግንባታ ስራውን ከሚያከናውኑ ኮንትራክተሮች ፣ ከባለሙያዎችና አማካሪዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡ ለግድቡ መጠናቀቅ መላው ኢትዮጵያውያን ከሃገር ውስጥና ውጪ እያደረጉት ያለው ድጋፍ ከምን ግዜውም በላይ ተጠናክሮ ቀጥሏልም ነው ያሉት።

@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ክትባት በመጪው ሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ ተገለጸ!

ክትባቱ 20 ከመቶ ለሚሆኑ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ይዳረሳል ተብሏል፡፡ የክትባት ስራውን የሚያስተባብር ግብረሃይል በብሄራዊ ደረጃ መቋቋሙንም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የህወሃት ሊቀመንበር የሆኑት ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ከሁለት ወራት ዝምታ በኋላ በትናትናው ዕለት፣ ጥር 22፣ 2013 ዓ.ም በድምፂ ወያነ ትግራይ ፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ለትግራይ ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) በትግራይ ላይ የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ በተቋረጠው ድምፂ ወያነ ትግራይ የፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ለ13 ደቂቃዎች በድምፅ ባስተላለፉት መልዕከት ክልሉ ላይ ደርሷል ስለተባሉ ውድመቶች፣ ቀጥሏል ስላሉት ትግል ሁኔታ እንዲሁም ለትግራይ ህዝብና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥሪ አቅርበዋል።"የትግራይ ሴቶች በተናጠልና በደቦ ይደፈራሉ። የትግራይ ሰዎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ነጻነቶች በከፋ መገለጫና አኳሃን ይጣሳሉ፣ ይገፈፋሉ። የትግራይ መንደሮችና ዓብያተ እምነቶች፣ የትግራይ ሰራዊት ይኑርበት አይኑርበት ሳይገዳቸው የቦምቦችና የመድፎ ዒላማ ይደረጋሉ። ውድና መተኪያ የሌላቸው ቅርሶችም ይወድማሉ፣ ይዘረፋሉ። በሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ እንዳለ ከቀየው ወጥቶና ተፈናቅሎ የመከራ ኑሮ ይኖራል።" ብለዋል።

በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። ከነዚህም አመራሮች አንዱ የህወሃት ሊቀ መንበር ደብረ ፅዮን ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት ያሉበት አይታወቅም።ለእስር ማዘዣው ዋነኛ ምክንያቶቹ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል በመፈፀም፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ነው።

(BBC)
@YeneTube @FikerAssefa
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ጉለሌ እጽዋት ማዕከል ውስጥ የተነሣው የእሳት ቃጠሎ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል እና ወደ ሌላ ቦታ ሳይስፋፋ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ዛሬ ከቀኑ 7:00 ሰዓት አካባቢ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በጉለሌ እጽዋት ማዕከል ውስጥ ተነስቶ የነበረው እሣት በተደረገው ርብርብ እሳቱ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እና ወደ ሌላ ቦታ ሳይስፋፋ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል ።
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የእሣት አደጋው በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።የተነሣውን እሳት ማጥፋት በርካታ የአዲስ አበባና የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች እና አባላት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት እና የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ባለሙያዎች ፣ የመንገዶች ባለስልጣን፣ የአካባቢው አስተዳደር እና ህብረተሰቡ እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸውን ወ/ሮ አዳነች ገልጸዋል።እሳት ውስጥ ገብታችሁ እሳት ላጠፋችሁ ሁሉም አካላት በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ ብለዋል።ለእሳቱ ምክንያት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ያሉት ወ/ሮ አዳነች ቀሪ ስራዎችን በልዩ ትኩረት የምናከውን ሲሆን መረጃዎችን በየወቅቱ ለህብረተሰቡ እናደርሳለን ብለዋል ።

Via Addis Ababa City PS
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 629 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 7,109 የላብራቶሪ ምርመራ 629 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

ባለፋት 24 ሰዓታት የ2ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 2,093 አድርሶታል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 274 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 122,862 አድርሶታል፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 137,650 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
#CoupAlert

በማይናማሯ መሪ አንግ ሳን ሱ ኪ ላይ መፈንቅለ መንግሥት ተፈፀመ!

በቀድሞዋ በርማ በአሁኑ መጠሪያዋ ማይናማር የምትባለው ሀገር መሪ ዳው አንግ ሳን ሱ ኪ ላይ በመከላከያ ሰራዊቱ መፈንቅለ መንግስት እንደተፈፀመባቸው እየወጡ የሚገኙ ዘገባዎች ያሳያሉ። የሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን የተቋረጠ ሲሆን የኢንተርኔት እና የስልክ ግኑኝነት በተመሳሳይ ተቋርጠዋል። መከላከያ ሰራዊቱ በራሱ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንዳስታወቀው ከሆነ በሀገሪቱ ለአንድ አመት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል። ይህንንም ተከትሎ ሁሉም ስልጣኖች በመከላከያ ሰራዊቱ እጅ እንደሚሆኑም ተገልጿል። በዚህ መግለጫ መሪዋና የሷ ሰዎች ከሁለት ወር በፊት የተደረገውን የምርጫ ውጤት በማጭበርበራቸው ከስልጣን እንዲነሱና እንዲታሰሩ ተደርገዋል በሚል ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ

ከ3,200 በላይ ዕቃዎች

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com

📞 0953707070

Dedicated online shopping platform
Forwarded from YeneTube
🖼 ለጓደኛ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለሙሽሮች እና ለተመራቂዎች ለየት ያለ ስጦታ መስጠት ይፈልጋሉ?
#join
👇👇👇👇
@giftsoflovee
@giftsoflovee
👆👆👆👆
📱+251914839754
📱+251936871620
#ኣድራሻችን፡ 4 ኪሎ: ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ
በአዲስ አበባ እፎይታ የገበያ ማዕከል ትላንት ምሽት የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ!

ትላንት ከምሽቱ 2:20 አካባቢ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ የገበያ ማዕከል ሱቆች ላይ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።የእሳቱን ለማጥፋት የእሳት አደጋ መከላከያ፣ ፖሊሶች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ባደረጉትርብርብ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ነው ምክትል ከንቲባዋ በማህበራዊ ገፃቸው የገለፁት።
ጠቅላላ የተቃጠሉ የሱቆች ቁጥርና የደረሰው የጉዳት መጠን እየተጣራ ሲሆን፤ ሙሉ መረጃውን እንደደረሰ ይፋ እንደሚፈረግም ተገልጿል።

አደጋው በቁጥጥር ስር ቢውልም፤ የእሳት ቃጠሎ ትላንት ከሰዓት በኋላ ብቻ በአዲስ አበባ የደረሰ ሁለተኛ አደጋ በመሆኑ እና እሳቱ በተነሳ ጊዜ ዘረፋም ስለነበረ ጠንከር ያለ የምርምራ ስራ ተጀምሯል ብለዋል ም/ከንቲባዋ። ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ለጋራ ሰላም ሲባል ምንም አይነት መረጃ ያለው ግለሰብ ለህግ አስከባሪ እና ለፖሊስ መረጃውን እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
ሁሉም የከተማዋ አመራር እና ነዋሪዎች መሰል አደጋዎች ዳግም እንዳይከሰቱ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አሳስበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት ስድስት ወራት 125 አዳዲስ ከተሞች የኤሌክትሪክ ሐይል ማግኘታቸው ተገለጸ!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ባልተዳረሰባቸው የሃገሪቱ አካባቢዎች ፍትሃዊ ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል።በዚህም ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት 161 አዳዲስ ከተሞች ኤሌክትሪክ እንዲያኙ ለማድረግ ታቅዶ 125ቱ  የኤሌክትሪክ ሃይል አግኝተዋል።በመልሶ ግንባታ ሥራ ደግሞ 10 አቅዶ 10 ከተሞችን ማገናኘት ችሏል፡፡በአዲስና በመልሶ ግንባታ ሥራዎች 171 የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ አቅዶ 135ቱን ማሳካቱንም ነው ተቋሙ የገለጸው

ከዚህ ባለፈም ባለፉት ስድስት ወራት የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ 1 ሺህ 35 ነጥብ 15 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ ለማከናወን ተቋሙ አቅዶ 1 ሺህ 439 ነጥብ 67 ኪሎ ሜትር  በመዝርጋት ከዕቅድ በላይ አፈፃፀም አሳይቷል።በተጨማሪም 749 ነጥብ 93 ኪሎ ሜትር  የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ለማከናወን አቅዶ 1 ሺህ 439 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር መዘርጋት መቻሉን ገልጿል፡፡

እንዲሁም በተለያዩ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን 427 የትራንስፎርመር ተከላ ለማከናወን ታቅዶ 314 ያህሉ ተከናውኗልም ነው ያለው፡፡ተጠቃሚነትን ከማሳደግ አኳያ በ2013 የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት 142 ሺህ 11 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙም መደረጉንም ነው ተቋሙ ያስታወቀው።በቀጣይም ከዋናው የኃይል ቋት የሚርቁ 25 የገጠር ከተሞችና መንደሮች በሚኒ ግሪድ የሶላር ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራም እንደሚገኝ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትን ጠቅሶ የዘገበው ፋብኮ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለስልጣን አሁን ካለው ተጨማሪ የባለ ሁለት እግር ሞተር ፈቃድ የመስጠት ፍላጎት እንደሌለው ተናገረ፡፡

በ2011 አዲስ መመሪያ መዘጋጀቱን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት 3600 የሚደርሱ ሞተሮች ፈቃድ ተሰጥቷቸው እየሰሩ ሲሆን ይህ ቁጥር ለከተማው ለጊዜው በቂ ነው ብሏል፡፡

የትራንስፖርት ባለስልጣን በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት ዙሪያ በመከረበት መድረክ ላይ ተገኝተን እንደሰማነው አሁንም አልፎ አልፎ በሞተር ሳይክሎች በከተማዋ ዝርፊያ እየተፈፀመ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ለቁጥጥር ያስቸገረና የተደራጀ ዝርፊያና ስርቆት በሞተር ሳይክሎች መፈፀም መብዛቱን ተከትሎ ሞተር ሳይክሎች ሙሉ በሙሉ ከከተማው እንዲወጡ ተደርጎ ነበር፡፡

ቆይቶ ሞተር ሳይክሎቹ በማህበር ሆነው ቀለም አስቀብተው የጂ.ፒ.ኤስ መቆጣጠሪያ ተገጥሞላቸውና ዩኒፎርም መልበስ ግዴታ እንዲሆን ተደርጎ ለ3600ዎቹ ዳግም ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡

በፊት ከነበሩት 15,000 ገደማ የሞተር ሳይክሎች ውስጥ ከ11,000 በላይ የሚሆኑት ፈቃድ ቢጠይቁም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሁን በስራ ላይ ያሉትን በወጉ ሥርዓት የማስያዝና የመቆጣጠር እንጂ አዲስ ፈቃድ የመስጠት ፍላጎት እንደሌለኝ እወቁት ብሏል፡፡

Via:- Sheger FM
@Yenetube @Fikerassefa
አንቶኒዮ ጉተሬዝ የምያንማርን መሪ ኦንግ ሳንሱካይ መታሰርን አወገዙ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የምያንማር መሪ ኦንግ ሳን ሱ ካይንና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎች በምያንማር የፓርላማ መክፈቻ ዋዜማ ላይ መታሰራቸውን አወገዘ፡፡

ጉተሬዝ የሀገሪቱ ህግ አውጭ፣ አስፈጻሚና የፍርድቤት ስልጣን ወደ ወታደር መተላለፉ እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል፡፡ የምያንማር ወታደር መፈንቅለ መንግስት በማካሄድ ኦንግ ሳን ሱ ካይን አስሯል፤ለአንድ አመት የሚቆይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል፡፡

Via:- Alian
@YeneTube @Fikerassefa