YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ በተከሰተ የእሳት አደጋ የ ሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ።

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በትላንትናው እለት በደረሰ ድንገተኛ የእሳት አደጋ የሁለት ሰው ህይወት ማለፉን ገልጿል፡፡አደጋው የደረሰው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ቦኖ ውሃ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ በቀበሌ መኖሪያ ቤቶች ላይ ነው፡፡በተከሰተው ድንገትኛ የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ታውቋል፡፡

ህይወታቸው ያለፈው አንድ አረጋውያንና አንድ ወጣት ናቸው፡፡እንደዚሁም አንድ ወጣት ህክምና ተሰጥቶት ወደ ቤት መመለስ መቻሉንና በአደጋውም ሁለት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መቃጠላቸውንም ነው ያስታወቀው፡፡የአደጋው መንስኤ በፖሊስ በመጣራት ላይ የሚገኝ ሲሆን በአደጋው ምን ያህል ንብረት ለውድመት እንደተዳረገ እና ምን ያህል ንብረት ደግሞ ማዳን እንደተቻለ በመጣራት ላይ ነው፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የእነ አቶ ጃዋርን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ፍርድ ቤቱ በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ!

የእነ አቶ ጃዋር መሀመድን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ፍርድ ቤቱ በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስትና የጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ዛሬ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ተሰይሞ የነበረው የተጠርጣሪዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመመልክት ነበር።ይሁንና ተከሳሾቹ ቤተሰቦቻቸን ችሎት ስላልታደሙ የእምነት ክህደት ቃላቸንን መስጠት አንችልም ሲሉ አቤቱታ አሰምተዋል።

አቃቢ ህግም ጊዜው በተገፋ ቁጥር የተከሳሾችም ሆነ የኛንም ጊዜ እየተወሰደ ይሄዳል ስለዚህ ጊዜው ታሳቢ ቢደረግ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።አቶ ጃዋርም የፍርድ ቤቱን ጊዜ ለመውስድ አይደለም ቤተሰቦቻችን መግባት ስላለባቸው ነው ሲሉ በፍርድ ቤቱ ያላቸውን እምነት ጥሩ እንደሆነ ገልጸዋል።አቤቱታውን ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመመልከት ለጥር 27 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ኢቢሲ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል አንዳንድ ቦታዎች የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት በድጋሜ የተቋረጠበት ምክንያት ምንድን ነው?

Exclusive by @EthiopiaCheck

ትናንት ከሰአት በሗላ ጀምሮ በትግራይ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት እንደገና ስለመቋረጡ የሚገልጹ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተሰራጭተዋል።

መረጃው ትክክል መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚዋ እንደተናገሩት የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎቱ የተቋረጠው በመቀሌ እና በአዲሽሁ ከተማ መካከል የሚገኝ የፋይበር መስመር በመቆረጡ ምክንያት ሲሆን አገልግሎቱን እንደገና ለማስጀምረ ወደ ስፍራው የተላኩ ሶስት ቡድኖች ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ የጥገና ስራ በማከናወን ላይ ይገኛሉ።

በቶሎ የደህንነት ከለላ (security clearance) አለማግኘት፣ ከዚህ በፊት በክልሉ የቴሌኮም መሰረተ ልማት የደረሰው ከፍተኛ ጉዳት እንዲሁም የሀይል አቅርቦት ጥገናውን በፍጥነት ለማከናወን የገጠሙ ተግዳሮቶች እንደሆኑ ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ጨምረው ለኢትዮጵያ ቼክ ገልጸዋል። 

@YeneTube @FikerAssefa
በመቀሌ እና አዲሽ ከተማ መካከል የሚገኝ ፋይበር በመቆረጡ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የስልክ አገልግሎት ዳግም መመለሱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ለሸገር ነግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢዜማ የቀድሞው የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ በህግ ሊጠየቁ ይገባል አለ!

ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በነበሩት 2 ዓመታት ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባን በም/ከንቲባነት ያስተዳደሩት ኢ/ር ታከለ ኡማ በህግ መጠየቅ አለባቸው የሚል አቋም እንዳለው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢ.ዜ.ማ አስታውቋል፡፡

ፓርቲው፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አዳነች አበቤ፣በከተማይቱ ስለተፈፀመው የመሬት ወረራ፣የቤቶች ዕደላ እና በሌላም ህገ-ወጥ ተግባር ዙሪያ ትናንት መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ነው ይህን ያለው፡፡

የኢዜማ የኮሚዩኒኬሽን ሀላፊ አቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ሲናገሩ፣ከዚህ ቀደም ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በአዲስ አበባ ስለተፈፀሙ ተመሳሳይ ህገ-ወጥ ተግባራት ፓርቲያቸው በዝርዝር ሪፖርት አቅርቦ እንደነበር አስታውሰው፣ለዚህ ደግሞ የቀድሞው የከተማይቱ ም/ከንቲባ ታከለ ኡማን ጨምሮ በጊዜው በሀላፊነት ቦታ ላይ የነበሩ ሁሉ ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው ኢዜማ ፅኑ አቋም ይዟል ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለም፣ትናንት ም/ከንቲባ አዳነች አበቤ ያቀረቡት ሪፖርት፣ከለውጡ ወዲህ በተፈፀሙት ህገ-ወጥ ተግባራት ላይ ከማተኮር ይልቅ፣ችግሩን ከዛሬ 15 ዓመታት በፊት ከነበረው ሂደት ጋር ይበልጥ ለማያያዝ መሞከሩ አግባብነት የለውም ነው ያሉት የኢ.ዜ.ማ የኮሚዩኒኬሽን ሀላፊ አቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እራሱ ባደራጀው ቡድን አካሄድኩት ባለው ጥናት፣322 ባለቤት አልባ ህንጻዎች፣ከ13 ሚልየን ካሬ ሜትር በላይ በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ ቦታዎች እና ከ21ሺ በላይ ባልተገባ ወገን ባለቤትነት ስር የሚገኙ የጋራ-መኖሪያ ቤቶች መገኘታቸውን፣የከተማወ ም/ከንቲባ አዳነች አበቤ ትናንት በሰጡት መግለጫ ተናግረው ነበር፡፡

[ብስራት ሬዲዮ]
@YeneTube
መንግሥት ላለፉት ሁለት ዓመታት ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ሲሸፍን መቆየቱን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ!

መንግሥት ከ2011 ዓ.ም ሚያዝያ ወር ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ቢያሳይም ጭማሪውን በመሸፈን ላለፉት 2 ዓመታት 24.05 ቢሊዮን ብር የዋጋ ጭማሪውን እየደጎመ መቆየቱን የኢፌዴሪ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል። የኢፌዴሪ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2013 በጀት ዓመት የጥር ወር የነዳጅ ዋጋ ላይ መጠነኛ ክለሳ ማድረጉንም አስታውቋል።የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በጥር ወር የነዳጅ ምርት አቅርቦት ላይ መጠነኛ የዋጋ ክለሳ መደረጉን የገለጹት በሚኒስቴር መሥሪያቤቱ የንግድ ዕቃዎች ዋጋ ጥናት ክትትል እና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት ናቸው።

በተጠናቀቀው የታኅሣሥ ወርም ምርቱ 1.5 ቢሊዮን ብር የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል ያሉት ዳይሬክተሩ፣ መንግሥት ሁሉንም የዋጋ ጭማሪውን ሸፍኖ ከሄደ በኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ ተጸእኖ የሚያሳድር በመሆኑ መንግሥት 75 በመቶውን እንዲሸፍን እና ቀሪው 25 በመቶ በኅብረተሱ እንዲሸፈን ተደርጎ መጠነኛ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉን አብራርተዋል።ሌሎች መሠረታዊ ሸቀጦች የአቅርቦት እና ሥርጭትን በተመለከተ የጊዜ ሰሌዳቸውን ጠብቀው ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ለኅብረተሰቡ እየተሰራጩ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ካሳሁን፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተከትሎ ገበያውን ለማረጋጋት በተደረገው ጥረት ላለፉት ስድስት ወራት ከ392 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት እና 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስኳር እና ከ8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሩዝ ምርት ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ መደረጉን ተናግረዋል። አሁን ላይ የ5 በመቶ ቀረጥ እየከፈሉ ምርቶቹን እንዲያስገቡ መደረጉንም ነው የገለጹት።

በቀጣይም የቀረጥ እና የታክስ ሁኔታዎችን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንደ አስፈላጊነቱ የሚታይበት ሁኔታም እንዳለ ተገልጿል።አገሪቱ ከወጪ ንግዱ የምታገኘው የገቢ መጠን እና ከውጭ ወደ አገር ውስጥ ለሚገቡ ምርቶች የምታወጣው የንግድ ሚዛን መጠን ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ሸቀጦችን በአገር ውስጥ ምርት መተካት አስፈላጊ በመሆኑ ስትራቴጂ ተቀርጾ ወደ ሥራ መገባቱን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።በዚህም የዘይት ምርት በአገር ውስጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን እና 2 ፋብሪካዎች ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው ወደ ሥራ የገቡ መሆኑን፣ ሌሎችም በቀጣይ እንደሚገቡ ተናግረዋል።ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚደረገው ጥረት በሌሎች የመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
500 ትምህርት ቤቶችን ያቀፈ የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮጀክት ይፉ ሆነ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከህፃናት አድን ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ሰፉ ያለ አካታች ሀገር በቀል የትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።በምገባ ፕሮግራሙም ወደ 500 ትምህርት ቤቶች የሚታቀፉ ሲሆን በዚህም ከ 163ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባው አካል እንደሚሆኑ ተነግሯል።ፕሮግራሙ በ 5 ክልሎች ውስጥ ባሉ 13 ወረዳዎች ተግባራዊ እንደሚደረግም ነው የተገለፀው።

በፕርግራሙም ቅድመ መደበኛ እና አንደኛደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚካተቱ ሲሆን ለ አንድ አመት እንደሚቆይም ተነግሯል።የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚለዬን ማቲዎስ ፕሮጀክቱ የነገ ተስፋ የሆኑ ህፃናት ከትምህርት ቤት እንዳይቀሩ እና በትምህርት ቤት ትምህርታቸውን በትኩረት እንዲከታተሉ ትልቅ አስተዋጾ አለው ብለዋል።

የህፃናት አድን ድርጅት በኢትዬጵያ ዋና ዳይሬክተር ኢኪን ኦጉቶጉላሪ በበኩላቸው ይህ ፕሮጀክት ድርጅቱ ትኩረት አድርጎ ከሚሰራባቸው መስኮች መካከል አንዱ በመሆን በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።የምገባ ፕሮግራሙ በተፈጥሮ እና በአንዳንድ ምክንያቶች የተጎዱ እና ከዚህ በፊት ድጋፍ ያልተደረገላቸው አካባቢዎችን የሚያካትት መሆኑም ተገልጿል።ፕሮጀክቱ ይፋ የሆነው Global partnership for education በተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት ድጋፍ አማካኝነት ነው።ከዚህ ቀደም ሀገር በቀል የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳል።

[MoE]
@YeneTube @FikerAssefa
የወጋገን ባንክ የቀድሞፕሬዘዳንት አቶ አባይ መሀሪ መታሰራቸው ተሰማ።

የወጋገን ባንክ የቀድሞ ፕሬዘዳንት እና ምክትል ፕሬዘዳንት ጨምሮ 8 የባንኩ የስራ ሃላፊዎች የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው ነበር፡፡

የቀድሞ ወጋገን ባንክ ፕሬዘዳንት ግንባታ ባልተካሄደበት ይዞታ ከ 88 ሚሊየን ብር በላይ በማበደር ተጠርጥረው ነበር።

እሳቸውን ጨምሮ ሌሎች የባንኩ የስራ ሃላፊዎች ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክስ መስርቷል።

ዛሬ ጥር 19፣2013 ዓ/ም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ፀረ ሙስና ችሎት የተከሳሾችን ጉዳይ ለማየት የተሰየመ ሲሆን የወጋገን ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ አባይ መሃሪም በችሎቱን ተገኝተዋል።

1ኛ ተከሳሽ አቶ አባይ መሃሪ ቋሚ አደራሻ እያለን ፌደራል ፖሊስ ሳንጠራ እንደ ማንኛውም ሰው በመገናኛ ብዙሃን ሰምተን በፍቃደኝነት መጥተናል ሲሉ በጠበቃቸው በኩል ለችሎቱ ተናግረዋል፡፡

በጡረታ ነው የምተዳደረው ያሉት አቶ አባይ መሀሪ ጡረታዬም ታግዶብኛ ሲሉ ለችሎቱ ተናግረዋል። ዋስትናም ሊጠበቅልኝ ይገባል ሲሉ ተከርክረዋል።

ፍርድ ቤቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለጥር 25፣2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

የቀድሞ የወጋገን ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ አባይ መሃሪ ግን እስከዛው ባሉበት እንዲቆዩ ሲል አዟል፡፡

via Sheger
@Yenetube @Fikerassefa
ከህወሓት ታጣቂ ሃይል ጋር በመሰለፍ ሲዋጉና ሲያዋጉ የነበሩ 18 ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከህወሓት ታጣቂ ሃይል ጋር በመሰለፍ ከመቀሌ እስከ ቆላ ተንቤን ሲዋጉና ሲያዋጉ የነበሩ 18 ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መከላከያ አስታወቀ።
መኮንንኖቹ በመከላከያ ሠራዊት እና በፌዴራል ጸጥታ ሃይሎች የጋራ አሰሳና ፍተሻ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡

እንደ ኢንዶክትርኔሽን ዋና ዳይሬክተሩ ሜጀር ጀኔራል መሀመድ ተሰማ ገለጻ ከ18ቱ መኮንኖች መካከል 9ኙ የሙሉ ኮሎኔል ማዕረግ፣ 7ቱ የሌተናል ኮሎኔል ማዕረግ ያላቸው እና 2ቱ ደግሞ የፖሊስ ኮማንደሮች ናቸው።

ወንጀለኞችን የማደኑ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ ለኢዜአ የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ከቡድኑ ጋር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተሰለፉ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።
ከቡድኑ ጋር ተሰልፈው የነበሩት ሜጀር ጄኔራል መሀመድ እሻን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በቅርቡ እጃቸውን መስጠታቸው የሚታወስ ነው።

Via:- Alian
@Yenetube @Fikerassefa
አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የዶ/ር ዐቢይን መልዕክት ለኬንያው ፕሬዝዳንት አደረሱ!

የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከኢፌዴሪ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተላከ መልዕክት ዛሬ(ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም) በቤተመንግስታቸው ተቀበሉ።መልዕክቱን ለፕሬዝዳንት ኡሁሩ ያደረሱት የኢፌዴሪ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር እና የዶክተር አብይ ልዩ መልዕክተኛ ክቡር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ናቸው።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሚገኙበት ልዑክ ከኬንያ መንግስት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል።አቶ ኃ/ማርያም እና ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ያደረጉት ውይይት በሁለትዮሽ በአካባቢያዊ የሰላምና ፀጥታ ሁኔታዎች ያተኮረ እንደሆነ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ሁለቱ አገሮች ለአካባቢው ሰላም ቁልፍ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።የኢትዮ-ኬንያ ወዳጅነት በትውልዶች ሽግግር እየጎለበተ የመጣ በመሆኑ የበለጠ ልናጠናክረው ይገባል ብለዋል።

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አሳሰበ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በላኩት መግለጫ፤ ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ዘረፋ፣ መደፈር፣ እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈፀሙ ታማኝ ከሆኑ ሪፖርቶች ተሰምቷል ብለዋል። ቃል አቀባዩ አያይዘውም “በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞችን የኤርትራ ወታደሮች በሃይል ወደ ኤርትራ እየመለሷቸው ስለመሆኑ ማስረጃ አለ” ብለዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተጽፎ የወጣው መግለጫ፤ ከአፍሪካ በ140 ሚሊዮን የሕዝብ ብዛቷ ከፍተኛነት ሁለተኛ የሆነችውን ኢትዮጵያን እያስተዳደረ በሚገኘው የኢትዮጵያ መንግሥትን እና ሦስት ወራት ባስቆጠረው የትግራይ ክልል ጦርነት ተዋናይ በሆኑ አካላት ላይ አዲሱ የአዲሱ የፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደር የሚያደርገውን ግፊት የሚያሳይ ነው ሲል አሶሼትድ ፕሬስ በዘገባው ላይ አስፍሯል።

ከትግራይ ክልል የወጡ የዐይን እማኞችን ጠቅሶ የዜና ተቋሙ ባጠናቀረው ዘገባ፤ የኤርትራ ወታደሮች ዘረፋ እንደሚፈፅሙ፣ ቤት ለቤት እየተዟዟሩ ሰዎችን እንደሚገድሉ እና ልክ እንደ አካባቢው አስተዳዳሪ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ መንግሥት ሃገር ከድተዋል ተብለው የሚታመኑትን የትግራይ አመራሮች ለመያዝ በሚያደርገው ውጊያ ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች ተሳትፈዋል ያለው ዘገባው፤ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራ ወታደሮች መሳተፋቸውን ሙሉ ለሙሉ አስተባብሏል ብሏል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ

ከ3,200 በላይ ዕቃዎች

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com

📞 0953707070

Dedicated online shopping platform
የትግራይ ሰብኣዊ ድጋፍ ጉዳይ

በሰሜናዊ የአገራችን ክፍል የሕግ ማስከበሩ ሂደት ከተጠናቀቀ ወዲህ ምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች እና የሕክምና አቅርቦቶችን የያዘ የሰብዓዊ ድጋፍ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 1.8 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ደርሷል በማለት መንግሥት ተናግሯል።

በአጠቃላይ በክልሉ 2.5 ሚሊዮን እርዳታ ፈላጊዎች አሉ ቢልም ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ቁጥሩን 4.5 ያደርሱታል። ዓለም ዓቀፍ ተቋማት በመንግሥት እርዳታ እንዳናደርስ መንገዶችን ተዘግቶብናል በማለት ለጊዜውም ቢሆን እርዳታ እነዳይሰጥ ጭምር ከልክለዋል።

አዲስ ማለዳ የትግራይ ሰብኣዊ እርዳታ አቅርቦት ጋር ያሉ ጉዳዮችን በ ሐተታ ዘ ማለዳ አቅርቦታል።
https://buff.ly/2KQ303B

[Addis Maleda]
@Yenetube @Fikerassefa
ለሁለተኛው ዙር የ40/60 ንግድ ቤቶች ጨረታ በካሬ 151 ሺሕ ብር ከፍተኛና 23 ሺሕ ብር ዝቅተኛ ዋጋ ቀረበ

ኮርፖሬሽኑ በቦሌ እህል ንግድ፣ በቦሌ አያት፣ በቦሌ ቡልቡላ፣ በቦሌ ሎቄ፣ በቦሌ ሕንፃ አቅራቢ፣ በልደታ ሰንጋ ተራ፣ አቃቂ ቃሊቲ ክራውንና በኮልፌ ቀራኒዮ ሳይቶች በተገነቡ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር የተገነቡ 149 የንግድ ቤቶችን ለጨረታ አቅርቦ ነበር፡፡

ከፍተኛ ዋጋ 151,000 ብር በማቅረብ በቦሌ እህል ንግድ ሳይት የ40/60 ንግድ ቤትን ያሸነፈው ደቡብ ግሎባል ባንክ አክሲዮን ማኅበር ሲሆን፣ ተፎካካሪው ብርሃን ባንክ አክሲዮን ማኅበር ካቀረበው 83,460 ብርን በ67,540 ብር በልጦ አሸንፏል፡፡

ዘገባው የሪፖርተር ነው ተጨማሪ ለማንበብ: https://bit.ly/3sWQ39c

@YeneTube @FikerAssefa
የአለም ጤና ድርጅት አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ወደ 70 ሀገራት መስፋፋቱን ገለጸ!

የዓለም ጤና ድርጅት ቫይረሱ በጣም እንዲስፋፋና ክትባቱ እንዲዳከም እንዲሁም የጸረ-እንግዳ አካል የመከላከል አቅምን ደካማ የሚያደርገው አዲሱ ቫይረስ በአንድ ሳምንት ከ10 በላይ በሆኑ ሀገራት መከሰቱን አስታውቋል፡፡እንደ ድርጅቱ ገለጻ በፈረንጆቹ ጥር በብሪቴን የተከሰተው አዲሱ ቫይረስ እስካሁን በሁሉም ቀጣናዎችና አህጉር በሚገኙ 70 ሀገራት ተሰራጭቷል፡፡ኮቪድ 202012/01 ወይም ቢ.1.1.7 በመባል የሚታወቀው አዲሱ ቫይረስ ከመጀመሪያው ቫይረስ በቀላሉ የሚተላለፍ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ብቻ ከ10 በላይ የሆኑ ሀገራትን አዳርሷል፡፡ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲሱ ቫይረስ ገዳይ ነው ያሉ ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅት ግን ይህን ለማረጋገጥ ተጨማሪ ጥናት ያስፈልጋል ብሏል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን ከአል-ፋሻጋን ክልል አንድ ሴንቲ ሜተር አሳልፌ አልሰጥም ስትል አስታወቀች!

ሱዳን በቅርቡ በምስራቃዊ ግዛቴ ባለችዉና ከኢትዮጵያ ሚሊሻዎች በመዋጋት በኃል ከወሰደችው አከራካሪዉን የአል ፋሻግን ግዛት ለማንኛውም ሀይል አሳልፋ እንደማትሰጥ መናገሯን የሱዳን መንግስታዊ የዜና አገልግሎት ሱና ዘግቧል፡፡

የሱዳን የእግረኛ ጦር 2ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሃይደር አል ቲራይፊ የሱዳንን የአልፋሻጋን ግዛት አንድ ሴንቲ ሜትር መሬት አሳልፈን አንሰጥም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ለመከላከያ ሰራዊት ምልመላ መጀመሩንም ተናግረዋል፡፡

ጄኔራሉ ይህንን የተናገሩት በትላንትናዉ እለት በምስራቃዊው የአልቃዲሪፍ ግዛት ከሚገኘው ከፋላታ ጎሳ የልዑካን ቡድን አባላትን በተቀበሉበት ወቅት ነዉ፡፡

የሱዳንን ግዛት እንዲጠቀብ የክልሉ ነዋሪዎች ልጆቻችሁ ወደ ታጣቂ ኃይሎች እንዲቀላቀሉ ይሁን ሲሉም አሳስበዋል፡፡የኢትዮጲያ የዉጪ ጉዳይ ዋና ጸሀፊ ዲና ሙፍቲ ሱዳን የያዘችዉን የኢትዮጲያ ግዛቶች ለቃ እስካልወጣች ድርድር እንደማይኖር መናገራቸዉ አይዘነጋም፡፡

ዳጉ ጆርናል
@YeneTube @FikerAssefa
የዲላ ዩኒቨርሲቲ 3 ሺህ 725 ተማሪዎቹን ዛሬ እያመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ 3ሺህ 159 ተማሪዎችን እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ 580 ተማሪዎችን እያስመረቀ መሆኑ ታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከሰሞኑ ከህዝብ ዕይታ ርቀው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጎበኙ፡፡

በተለያዩ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች አካላቸው ለጎደለ ኢትዮጵያዊያን የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ በማምረት የሚያቀርበው ድርጅቱ በጤና ሚኒስቴር ሥር በቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኝ ነው እንደ ኢቢሲ ዘገባ፡፡የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ዕይታ መራቅ ከሰሞኑ ሲያነጋግር ነበረ፡፡የጤና እክል ገጥሟቸው ሊሆን እንደሚችል በመገመትም ብዙዎች ጭንቀታቸውን ሲገልጹ ተስተውለዋል፡፡በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ሲራገቡ የነበሩ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ለዚህ መንስዔ ናቸው፡፡የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ይሄንኑ ጉዳይ በማስተባበል ዶ/ር ዐቢይ በተሟላ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ማስታወቁም የሚታወስ ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና ከፌደራል መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ!

ስምምነቱ በዋናነት የኮርፖሬሽኑን መሰረተ-ልማት ወደ ዲጂታል ስርአት እንዲገባ የማድረግ እና የሳይበር ልማት ስትራቴጂክ ፍኖተ-ካርታ የማዘጋጀት እንዲሁም የመረጃዎቹን ደህንነት ማስጠበቅን የካተተ እንደሆነም ተገልጿል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው እና የፌደራል መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሌንሳ መኮንን ስምምነቱን ፈርመዋል፡፡

ከኤጀንሲው ጋር የተደረገው ስምምነት ኮርፖሬሽኑ በቴክኖሎጂ ራሱን ለማዘመን በሚያከውናቸው ስራዎች ላይ ማእከል ያደረገ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፤ በተለይ መረጃን ደህንነቱን ለማስጠበቅ ያለመ ነው ማለታቸውን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ ገለፀ፡፡

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፎች የተሰረዙበት ፓርቲው በእሁዱ ሰልፍ በ4 መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ መንግሥት ላይ ጫና ለመፍጠር አቅጃለሁ ነው ያለው፡፡የፓርቲውን አመራሮች እስር፣ በአገሪቷ የተከሰተውን ማንነትን መሰረት ያደረገ ግድያ፣ የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ እየፈፀመ ነው የሚለውን የመሬት ወረራ እንዲሁም የሱዳን ኃይል የድንበር ጥሰትን መቃወም ዋነኞቹ አጀንዳዎቼ ናቸው ብሏል፡፡የኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባን እየወረረ ነው በሚል ከቀናት በፊት ጥያቄ ቀርቦላቸው የነበረው የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባ ይህን ያህል የሰፋችው ተወራ ነወይ? በማለት ኦሮሚያ እና አዲስ አበባ ያልተፈታ የወሰን ጥያቄ እንዳላቸው ማብራራታቸው ይታወሳል፡፡

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa