YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የቦረና አባ ገዳ ኦነግ-ሸኔ የሕዝብ 'ጠላት ነው' ሲሉ አወጁ!

የቦረና አባ ገዳ የሆኑት ኩራ ጃርሶ በምዕራብና በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሽምቅ ጥቃት እየፈጸመ እንደሆነ የሚነገረውን ኦነግ-ሸኔን የሕዝብ ጠላት ነው ሲሉ ቡድኑን አወገዙ።አባ ገዳ ኩራ ለቢቢሲ እንደረናገሩት በታጣቂ ቡድኑ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ሠላማዊ ሰዎች በመገደላቸው በመሆኑ ነው። "እነዚህ ታጣቂዎች የቦረናን ሕዝብ እየገደሉ ነው። ለሕዝብ እታገላለሁ የሚል አካል መልሶ ሕዝብን መግደል የለበትም" ሲሉ ነው ቡድኑን ያወገዙት።ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተነጥሎ የወጣው ታጣቂው የኦነግ-ሸኔ ቡድን በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ጥቃት እንደፈጸመና መንግሥትም ቡድኑ ላይ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ መግለጹ አይዘነጋም።

የቦረና አባ ገዳው ኩራ ጃርሶ የኦነግ-ሸኔ አባላት እንዳሉት "ሴቶችን አስገድደው ይደፍራሉ። በቦረና ባህል ይህ እጅግ አጸያፊ ነው። ባል እያባረሩ ከሚስት ጋር ያድራሉ። የጦር መሣሪያ ይነጥቃሉ። ታዋቂ የሆኑ ሰዎችን ይገድላሉ። ከብት ዘርፈው አርደው ይበላሉ" ሲሉ ቡድኑ እየደረሰ ነው ያሉትን ድርጊት ገልጸዋል።ቡድኑ በምዕራብና በደቡብ የተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ እንዲሁም በመንግሥት ሠራተኞች ላይ ጥቃት እንደሚሰነዝር በተደጋጋሚ ሲዘገብ ነበር።አባ ገዳ ኩራ እንዳሉትም የቡድኑ አባላት በእድሜ የገፉ አዛውንቶችን እና ሕጻናትን ጨምር እየገደሉ መሆኑን በመግለጽ ለዚሁ መሳያ የሚሆን ምሳሌም ጠቅሰዋል።"ለምሳሌ አሬሮ ወረዳ የ12 ዓመት ልጅ ገድለዋል" ያሉት አባ ገዳው አያይዘውም "እዚህ ደረጃ ላይ ስለደረሱ ኦነግ-ሸኔ የቦረና ሕዝብ ጠላት ነው ብለን አውጀናል። ሕዝቡ ራሱን እንዲከላከል አውጀናል" ብለዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ያሉ ኤርትራዊያን ስደተኞች የምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል ተባለ!

ከሦሰት ሳምንታት በላይ ወታደራዊ ግጭት በተካሄደባት ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ የስደተኛ ማቆያዎች ውስጥ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ስደተኞች የምግብ እጥረት እያጋጠማቸው እንደሆነ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ዩኤንኤችሲአር አስታወቀ።ተቋሙ ለስደተኞቹ አስፈላጊውን አቅርቦት ለማድረስ የሚያስችለው የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አቅርቦት መንገድ እንዲከፈት ጠይቋል።

በትግራይ ክልል ኃይል እና በፌዴራል መንግሥት ሠራዊት መካከል ወታደራዊ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ በክልሉ የመገናኛ መስመሮችና እርዳታ የሚገባባቸው መንገዶች ተዘግተዋል።እንደ ድርጅቱ መረጃ በትግራይ ክልል ውስጥ 100 ሺህ የሚሆኑ ኤርትራውያን በአገራቸው ያለውን ፖለቲካዊ እስርና አስገዳጅ የግዳጅ የውትድርና ሥልጠና በመሸሽ ተሰደው ይገኛሉ።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተገኙበት የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እየተወያዩ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በተገኙበት የተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ውይይት እያካሄዱ ነው።ከውይይቱ አስቀድሞ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የምርጫ ተዋናዮች ሚና እና የተለያዩ አገሮች የምርጫ ስርዓቶችን የሚመለከት የውይይት መነሻ ጽሑፍ አቅርበዋል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ ማለዳ በፈነዳው ቦንብ ምንም የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ገለፀ፡፡

ዛሬ ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ጎርጎርዮስ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ አንድ የቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ተጥሎ የተገኘ ቦምብ ከአካባቢው ሰዎች በደረሰው ጥቆማ የፈንጅ አምካኝ ባለሙያዎች ወደ ቦታው በማቅናት ለማምከን ባደረገው ሙከራ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሊፈነዳ ችሏል፤ በዚህም አንድ ግለሰብ የቦንቡ ፍንጣሪ በቅርብ ርቀት ከሚሰራበት ጋራዥ ቅጥር ግቢ በስራ ላይ ሳለ በፍንጣሪው ቀላል ጉዳት የደረሰበት ሲሆን ተጎጂው የህክምና ርዳታ በማግኘት ወደ ቤቱ መመለሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል ።

ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ባላቸው ግለሰቦችና አጠቃላይ የምርመራውን ውጤት እንደደረሰው አሳውቃለው ያለ ሲሆን በተመሳሳይ በዚሁ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጉርድ ሾላ ቅዱስ ያሬድ ሆስፒታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለፖሊስ በደረሰ መረጃ መሰረት ባለሙያዎች ቦታው ድረስ በመገኘት ቦንቡን የማምከን ስራ ሰርተዋል፡፡በነብስ ውጪ ግቢ ጣር ላይ የሚገኘው የ'ጁንታው' ተላላኪዎች በከተማው አዲስ አበባ በንፁሃን ላይ ከባድ ጉዳት ለማድረስ የሚደርጉትን መንፈራገጥ ለማምከን የሚቻለው ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር የሚኖረውን የመረጃ ልውውጥ በማጠናከርና አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ መሆኑን ኮሚሽኑ አስገንዝቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ዛሬ ረፋድ ታጣቂዎች በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ባደረሱት ጥቃት በሰባት ሰዎች ላይ ቆሰሉ።

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ኤዲዳ በተባለ ቀበሌ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ላይ በከፈቱት ተኩስ በ7 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት መድረሱ ተገለፀ፡፡የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ምስጋና ኢንጂፈታ እንደገለፁት ዛሬ ጠዋት ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ማንዱራ ወረዳ ኤዲዳ የተባለ ቀበሌ እንደደረሰ በሽፍቶች ተኩስ ተከፍቶበታል፡በጥቃቱም 1 ከባድ ጉዳት እና 6 ቀላል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ዜናውን እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ የሞተ ሰው አለመኖሩን ገልፀዋል፡፡ በጥይት ተመተው ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በፓዊ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ኢንስፔክተር ምስጋና ተናግረዋል፡፡

ጥቃት አድራሾችን በቁጥጥር ስር ለማዋል መከላከያ ሰራዊት ፤ ፖሊስ እና የፀረ-ሽምቅ ሀይል በአካባቢው ደርሶ አሰሳ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ምስጋና እንደገለፁት ከትናንት በስቲያም በተመሳሳይ ቦታ ላይ በህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ላይ ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር ገልፀው በሰዎች ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ አረጋግጠዋል፡፡በክልሉ መተከል ዞን ላይ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ፀረ-ሰላም ሀይሎች አሁን ላይ በተበታተነ ሁኔታ የሚገኙ ሲሆን አልፎ አልፎ በተሽከርካሪ መኪኖች ላይ ጥቃት የመሰንዘር ሁኔታዎች እየተስተዋሉ ነው ብለዋል፡፡እነዚህ ሀይሎች ይህንን እንቅስቃሴያቸውን ከማቆምም ባለፈ የክልሉ መንግስት ባስቀመጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ እጅቸውን እንዲሰጡ አስጠንቅቀዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የፌደሬሽን ምክር ቤት ከኢስት አፍሪካ ኢንተርቴመንት እና አድቨርታይዚንግ ጋር በመሆን 15ተኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓልን ለማክበር በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በበዓሉ ሚስ ዩኒቲ (miss unity) የተሰኘ 10 ክልሎች እና ኹለቱ የከተማ አስተዳደሮች የሚሳተፉበት የቁንጅና ውድድር ይካሄዳል።

አሸናፊዎች እስከሚቀጥለው ዓመት ድረስ የየክልላቸው አምባሳደር ሆነው በአገሪቱ እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ ተብሏል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች በዳንሻ ከተማ በመሰባሰብ በአማራ ክልል የመስተዳደር ጥያቄያቸው አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኝ በህዝባዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
አክሱም ከተማ የገባው የፀረ-ሽብር ልዩ ኮማንዶ ሀይል ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም በአክሱም ከተማ የተከበረውን ዓመታዊ የፅዮን ማርያም ንግስ በዓልን ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲያከብር ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን በአካባቢው ፀጥታ የማስከበር ስራ መስራቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በዚህ ወቅት የ'ጁንታው' ህወሓት ቡድን ለእኩይ ተግባር ሊጠቀምበት የነበረ የተለያዩ የጦር መሳሪዎች መያዝ ተችሏልም ነው ያለው ኮሚሽኑ።ይህ መስዋዕትነት ተከፍሎበት እየተሰራ ያለው ህግን የማስከበር ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የእርዳታ ሰራተኞችን እንድትተባበር የአውሮፓ ህብረት አሳሰበ!

የአውሮፓ ህብረት የአደጋ ስራ አመራር እና ዝግጁነት ኮሚሽነር ያኔዝ ሊናርቺች ከሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ጋር መወያየታቸውን ገለጹ።ኮሚሽነሩ ወደ ሱዳን በማቅናት ላይ ነበርኩ ብለዋል፡፡በግጭቱ ወደ ተጎዱ አካባቢዎች በአፋጣኝ እና ያለ ችግር መድረስ የሚፈልጉ የእርዳታ ሰራተኞችን እንዲተባበሩ በህብረቱ ስም የኢትዮጵያን ባለስልጣናት አሳስቤያለሁ ያሉት ኮሚሽነሩ ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲበጅ ጥሪ ስለማቅረባቸውም በማህበራዊ ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡ማሳሰቢያውን በተመለከተ ሙፈሪያት ያሉት ነገር እንዳለ በኮሚሽነሩም ሆነ በሚኒስትሯ ይፋዊ የማህበረሰብ ገጽ አልያም በሚኒስቴር መስሪያ አድርሻ ጭምር የተገለጸ ነገር የለም፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ዛሬ ረፋድ ታጣቂዎች በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ባደረሱት ጥቃት በሰባት ሰዎች ላይ ቆሰሉ። በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ኤዲዳ በተባለ ቀበሌ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ላይ በከፈቱት ተኩስ በ7 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት መድረሱ ተገለፀ፡፡የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ምስጋና ኢንጂፈታ…
በመተከል ዞን 43 ፀረ-ሰላም ሀይሎች ለመንግስት እጃቸውን ሰጡ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ጦር መሳሪያ ይዘው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች እጅ እንዲሰጡ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ምስጋና ኢንጂፈታ እንደተናገሩት በመተከል ዞን የሚገኙ የጥፋት ቡድኖች ለክልሉ መንግስት እጅ እንዲሰጡ በቀረበው ጥሪ መሰረት እስከ ትናንት ድረስ ዳንጉር ወረዳ ላይ ይንቀሳቀሱ የነበሩ 43 ፀረ-ሰላም ሀይሎች እጅ የሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ቡድኖችን የሚመሩ ግለሰቦች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል የሚሉት ምክትል ኮሚሽነሩ በመሪዎቹና በተላላኪዎቹ መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ በተበታተነ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ለማወቅ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

እስከ አሁን ድረስ እጃቸውን ለመንግስት የሰጡት 43 ፀረ-ሰላም ሀይሎች በዚሁ የአሳብ ልዩነት እጅ ሊሰጡ እንደተገደዱ መረጃዎች አግኝተናል ብለዋል፡፡እነዚህ ሀይሎች በዳንጉር ወረዳ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ሲሆኑ በሌሎችም ወረዳዎች የሚገኙ የጥፋት ቡድኑ ርዝራዦች እጅ በመስጠት ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል፡፡ምክትል ኮሚሽነሩ እንደሚሉት ለጥፋት ቡድኑ ጥሪ የቀረበው የህዝብና የሀገር ድንነት ለማረጋገጥ እንደሆነ ጠቁመው የጥፋት ሀይሎች ጥሪውን ተቀብለው ለመንግስት እጅ እንዲሰጡ ጠይቀው እጅ በማይሰጡት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል በሚገኙ አካባቢዎች ማለትም በዳንሻ፣ በተርካን፣ በሁመራ፣ በሽራሮ፣ ማይፀብሪና እና በማይካድራ በከፊል፣ በአላማጣ ደግሞ ሙሉ በሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

በተቀሩት የትግራይ አካባቢዎች አገልግሎቱን ለማስጀመር የተጎዱ የቴሌኮም መሰረተልማቶችን በመጠገን መልሶ በማቋቋም እንዲሁም መደበኛ የኃይል አቅርቦቶችን በመጠቀም በሁሉም አካባቢዎች አገልግሎቱን ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
የተሳሳተ መረጃ ማስተካከያ!!

የኢፌዲሪ ፈዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሀገር ክህደት ወንጀል የፈፀሙ በርካታ የህወሓት ቡድን አባላት የሆኑ ጀኔራል መኮንኖች ፣ ከፍተኛና የመስመር መኮንኖች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ማውጣቱንና እነዚህን ህገወጦች በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል መጀመሩን ለህዝብ ይፋ ማደረጉ ይታወቃል።

ኮሚሽኑ የክትትል ስራውን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በኢትዮ FM የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ መግለፃቸውን ጠቅሰን 38 የህዋሀት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለን ያስተላለፍነው መረጃ ሐሰትና በም/ኮሚሽነር ጀነራሉ ያልተላለፈ መሆኑን የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት አስታውቋል።

ተያዙ በሚል ሃላፊው የገለፁት መከላከያ ውስጥ የግንኙነት መስመር ያቋረጡና ከዚህ ድርጊት ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፍቃዱን (ወዲ ነጮን) ጨምሮ 38 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ስለመቅረባቸው መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቁሞ ከ'ጁንታው' ቡድን አባላት እስከአሁን የተያዙ አለመኖራቸው ታውቆ ሌሎች ሚዲያዎች ይህንን የተዛባ መረጃ ለህበረተሰቡ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን ብሏል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን።

ይህንንም ተከትሎ ቀደም ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤምን ጠቅሰን የለቀቅነውን ዜና ከገፃችን ላይ አንስተነዋል!
@YeneTube @FikerAssefa
በኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን ጥቃት ደርሶብናል ያሉ የምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ወረዳ ነዋሪዎች አሁንም የደኅንነት ስጋት ውስጥ ነን ሲሉ መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠየቁ።

በተለይም የፀጥታ አካላት ወደ አካባቢው ደርሰው ሲመለሱ ታጣቂዎቹ ጥቃት እያደረሱብን ነው ብለዋል።የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በበኩሉ በየአካባቢው ከነዋሪዎች የተውጣጣ ሚሊሻ እና የፀጥታ አስከባሪ ኃይል እያደራጀሁ ነው፤ የኦነግ ሸኔ አባላትን በመደምሰስ ችግሩን ለመፍታት እየሰራሁ ነው ሲል ለአሐዱ ቴሌቪዥን ምላሽ ሰጥቷል።ከሰሞኑ ሰፊ ሕግ የማስከበር ዘመቻ ላይ ስለመሆኑ የሚገልፀው ክልሉ በርካታ የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን አባላትን እየገደለ፤ እየማረከና በቁጥጥር ስርም እያዋለ መሆኑን የሚያመለክቱ መረጃዎችን በመስጠት ላይ ነው።ቡድኑ ከሕወሓት ከፍተኛ የገንዘብና የትጥቅ ድጋፍ አለው በማለትም ከሕወሕት ታጣቂ ቡድን ጋር አብሮ እንደሚጠፋ የክልሉ ባለሥልጣናት ሲናገሩ ይደመጣል።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
የኩላሊት ልገሳ የሚፈቅደው ሕግ በአፋጣኝ እንዲፀድቅ የሕመምተኞች ማኅበር ጠየቀ!

በኢትዮጵያ የኩላሊት ልገሳን የሚፈቅደው የጤና ሕግ ባለመፅደቁ ምክንያት በኩላሊት ሕመም የሚሰቃዩ  ሰዎች እየበዙና የሟቾች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን፣ የኢትዮጵያ የኩላሊት ሕመምተኞች ማኅበር ገለጸ፡፡ማኅበሩ ከሦስት ዓመታት በላይ የዘገየው ሕግ በአፋጣኝ ፀድቆ ወደ ሥራ እንዲገባ ጠይቋል፡፡ከዚህ ጋር ተያይዞ ከሰሞኑ አንዳንድ የኩላሊት እጥበት የሚያደርጉ ሆስፒታሎች የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን፣ ያደረጉት የዋጋ ጭማሪም በሳምንት ሦስት ጊዜ እጥበት ለሚያደርጉ ሕመምተኞች በወር ከ9,000 ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ ሊዳርጋቸው እንደሚችል ማኅበሩ አስታውቋል፡፡

የማኅበሩ ፕሬዚንት አቶ ሰለሞን አሰፋ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ቢያንስ ከ40 ሺሕ በላይ ዜጎች የኩላሊት እጥበት እንደሚያስፈልጋቸው ቢታወቅም፣ ከአገልግሎቱ ውስንነት የተነሳ ከ1,800 የማይበልጡ ሕሙማን ብቻ ክትትል እየተደረገላቸው ነው፡፡በሦስት የመንግሥትና በ13 የግል ሆስፒታሎች አገልግሎቱ እየተሰጠ እንደሆነ የገለጹት አቶ ሰለሞን፣ ታማሚዎቹን በበቂ ሁኔታ ሊያስተናግድ የሚችል የሕክምና ተቋም ካለመኖሩ ጋር ተዳምሮ በጎ ፈቃደኞችና ለጋሽ ሰዎች ኩላሊት መለገስ ቢፈልጉ የሚፈቅድ አገራዊ ሕግ የለም ብለዋል፡፡ኩላሊት መለገስ የሚፈልጉ ሰዎች ሳይለግሱ፣ ልገሳ የሚፈልጉ ሰዎችም ሳያገኙ ሕይወታቸው ያልፋል፣ ወይም በሕመሙ ይሰቃያሉ ሲሉ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አስረድተዋል፡፡

ኩላሊትን ጨምሮ ሌሎች የሰውነት ክፍሎችን ሰዎች በሕይወት ሳሉ ለግሰው  ሲሞቱ፣ ለሕመምተኞች በንቅለ ተከላ አማካይነት እንዲተላለፍ የሚፈቅደው የጤና አዋጅ ከሦስት ዓመታት በፊት ረቂቁ እንደተጀመረና በጉጉት ሲጠብቁት እንደነበር የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አክለው ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰዓረላ አብዱላሂ በበኩላቸው፣ የኩላሊት ሕመም ሕክምና በዓለም አቀፍ ደረጃም የግብዓት እጥረት አለበት ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ በቅርቡ ከተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ የተባባሰውን ችግር ለመቅረፍ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዝግጅት ላይ ያለው ረቂቅ የጤና አዋጅ ምንም እንኳ ዕሳቤው በጤናው ዘርፍ ያሉና ሕግ ያልወጣላቸውን አሠራሮች በሕግ ማዕቀፍ ሥር ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ሰፊ የሕግ ረቂቅ ቢሆንም፣ በተደጋጋሚ በተደረጉ ምክክሮች አገሪቱ ካለችበትና ዓለም ከደረሰበት የሕክምና ዘርፍ ጋር ተያይዞ ብዙ መጨመር ያለባቸው ጉዳዮች በመኖራቸው፣ በዘርፉ በቂ ልምድ ያላቸውን ምሁራን በማሳተፍ እንደገና እየታየና እየተከለሰ ስለሆነ በቅርቡ ለሕዝቡ ውይይት ይቀርባል ብለዋል፡፡ሕጉ በውይይት ዳብሮ ሲወጣ ለኩላሊት ታማሚዎችም ሆነ ለሌሎች የሕክምና ዘርፎች ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የተሳሳተ መረጃ ማስተካከያ!! የኢፌዲሪ ፈዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሀገር ክህደት ወንጀል የፈፀሙ በርካታ የህወሓት ቡድን አባላት የሆኑ ጀኔራል መኮንኖች ፣ ከፍተኛና የመስመር መኮንኖች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ማውጣቱንና እነዚህን ህገወጦች በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል መጀመሩን ለህዝብ ይፋ ማደረጉ ይታወቃል። ኮሚሽኑ የክትትል ስራውን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በኢትዮ FM የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል…
"38 የህወሃት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ" ስለሚለው ዜና:

የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ዛሬ ለኢትዮጵያ ቼክ እንዳሳወቁት ተያዙ ተብለው በሚዲያዎች የተጠቀሱት ግለሰቦች በትግራይ ክልል የሚገኙ "ዋናዎቹን የህወሃት ሰዎች" የተመለከተ አይደለም።

ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም እንደገለጹት በሚድያ የተጠቀሱት ተጠርጣሪዎች ከሳምንታት በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉ እና ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት በመከታተል ላይ የሚገኙ ናቸው። ከነዚህም መካከል ከሰሜን ዕዝ ጋር የሚደረገውን የሬዲዮ ግንኙነት እንዲቋረጥ ያደረጉ ይገኙበታል ብለው ለኢትዮጵያ ቼክ ተናግረዋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫም "በኢትዮ FM የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ገልፀዋል" በሚል ያስተላለፈው መረጃ ሐሰት መሆኑን ጠቁሟል።

ኢትዮ FM በበኩሉ "38 የህወሓት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ገልፀዋል በሚል በተሰራጨዉ ዘገባ ላይ ያለዉ የስም ስህተት ብቻ መሆኑን እየገለጽን ይህን የተናገሩት ም/ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ መሆናቸዉን እያሳወቅን ለተፈጠረዉ የስም ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ ከዚህ ዉጭ ግን ዜናዉ የተጓደለ መረጃ የሌለዉ መሆኑንም ማሳወቅ እንወዳለን" ብሏል።

Via @EthiopiaCheck
@YeneTube @FikerAssefa
በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን የሚከታተሉና በዘንድሮው አመት ለምረቃ የሚበቁ ተማሪዎችም ምንም አይነት ችግር ሳይገጥማቸው መቆየታቸውን ተናግረው ሆኖም ግን ለከፍተኛ ርሃብና የውሃ ጥም ተዳርገው መቆየታቸውንና በአሁኑ ሰዓት የመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሚገኝ ነግረውኛል ሲል ጋዜጠኛ አበበ ሰማኝ ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ተማሪዎቹ ምንም አይነት ምግብ የሚያዘጋጁ ሰራተኞች በቅጥር ግቢው ባለመኖራቸው ምክንያት እየተቸገሩ መሆናቸውን በመግለፅ መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት በጉዳዩ ላይ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጧቸውም በአፅንኦት ጠይቀዋል ።

በተያያዘ ዜና በመከላከያ ሃይል በቁጥጥር ስር የዋለችው መቀሌ ከተማ ምንም እንኳን ህዝቦቿ ወደቀደመ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ባይመለሱም በአስተማማኝ ሰላም ላይ ትገኛለች፣ ሲል አበበ ሰማኝ ነግሮናል።

@YeneTube @FikerAssefa
በመቐለ ከተማ መከላከያ የማያውቀው የመሳሪያ ማከማቻ ዲፖ ተገኘ!

የልዩ ዘመቻ 2ኛ ብርጌድ 3ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ሳድቅ አህመድ እንዳሉት መቐለ ከተማ ላይ መከላከያ የማያወቀው የመሳሪያ ማከማቻ ዲፖ ተገኝቷል።የጁንታው ቡድን ውጊያውን መቋቋም ሲሳነው ትጥቁን እያራገፈ ፈርጥጧል ያሉት አዛዡ ከዚህ ውስጥ ሰራዊቱ የማያውቀው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች የተከማቹበት ዲፖ ተገኝቷል ብለዋል።የሰሜን እዝ አመራሮችን ጠይቀን ስለዲፖው እንደማያውቁ ገልጸውልናል ያሉት ሌተናል ጀነራሉ፤ በቀጣይም ተመሳሳይ የመሳሪያ ማከማቻወችም ሊገኙ እንደሚችሉ ገልፀዋል።በመሆኑም እነዚህ ከቀላል እስከ ቡድን መሳሪያዎች ወንጀል እዳይፈጸምባቸው የፍተሻ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ፎቶ: አበበ ሰማኝ
@YeneTube @FikerAssefa