YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከታህሳስ 12 እስከ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለፋና ብሮድካስቲንግ እንደገለፁት ባለፈው ዓመት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የትምህርት ዘመኑ ሳይጠናቅ ትምህርት መዘጋቱን አስታውሰዋል፡፡በዘንድሮው ዓመት ደግሞ በሀገሪቱ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ህዳር ወር ሊሰጥ የነበረው ክልልና ሀገር አቀፍ ፈተና ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ከዚህ ባለፈም በተፈጠረው የፀጥታ ችግር በሰሜን ወሎ ዞን ዋግኸምራ፣ ሰሜን ጎንደር ፣ምዕራብ ጎንደርና ማዕከላዊ ጎንደር ውስን አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንደነበርም ገልፀዋል፡፡አሁን በክልሉ ሰላም በመፈጠሩ የተዘጉት ትምህርት ቤቶች ከትናንት ጀምሮ ተከፍተዋልም ነው ያሉት፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ወታደሮች በሱዳን ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረ ኢትዮጵያዊ የሚሊሻ መሪ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ፡፡

የሚሊሻ መሪ ነው የተባለው ግለሰብ በሱዳን ክልል ውስጥ ከህወሓት ወገን ሆኖ ሲዋጋ የነበረ መሆኑንም ሱዳን ትሪቢዩን ታማኝ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ማንነቱ ያልተጠቀሰው ግለሰብ ከቤተሰቦቹ እና በርካታ ቁጥር ካላቸው ወታደሮችና አጃቢዎች ጋር በገዳሪፍ ግዛት አልፋሻቃ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉም ነው የተገለጸው፡፡በወቅቱም አምስት ቢሊየን ፓውንድ (የሱዳን ይሁን የእንግሊዝ ያልተጠቀሰ)፣ መጠኑ ያልተገለጸ ወርቅ፣ የእንጨት ስራ ውጤቶች እና ሁለት ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ጋር መያዙም ተገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኬንያ ባለስልጣኖቿ የኮቪድ-19 ክትባትን ከቻይና እንዲፈለጉ አዘዘች!

የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የአገራቸው የጤና ባለስልጣናት ለኮሮናቫይረስ መከላከያ የሚሆን ክትባት ከቻይና እንዲያፈላልጉ አዘዙ።ኬንያ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በቅርቡ አገልግሎት ላይ ይውላሉ ከተባሉት ክትባቶች ምዕራባዊያን ባለጸጋ አገራት 3.8 ቢሊዮን የክትባት ምርት ለመግዛት ማዘዛቸው ይፋ ከተደረገ በኋላ ነው።በዚህም መሠረት ፕሬዝዳንት ኬንያታ የጤና ጥበቃ መስሪያ ቤታቸው ቻይና እያዘጋጀች ካለው ክትባት ውስጥ ለዜጎቻቸው የሚሆን እንዲገዛ አዘዋል።"ኬንያ ውስጥ ኮሮናቫይረስ በከፋ ሁኔታ ተመልሶ እየተከሰተ ይመስላል፤ በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ ያለው የበሽታው መስፋፋት እየጨመረ ነው" ያሉት የኬንያ ጤና ሚኒስትር ሙታሂ ካግዌ ናቸው።
በተለያዩ አገራት ውስጥ እየተዘጋጀ ያለው የኮቪድ-19 ክትባትን በተለይ ለታዳጊ አገራት ለማቅረብ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተደራሽነቱ ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ከጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን ያመለከቱት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ ትግራይ ውስጥ ውጊያው እንዲቆም ማሳሰባቸውን አስታወቁ።

ወደ ዴሞክራሲ ለሚደረገው ሂደት በመካሄድ ላይ ያለውን ግጭት መፍታት ወሳኝ መሆኑን ያመለከቱት ባለሥልጣኑ ውይይት እንዲጀመር፤ ነፃና ለደህንነት አስተማማኝ የሆነና የማይደናቀፍ የሰብዓዊ አቅርቦት እንዲኖርም መጠየቃቸውን ገልጸዋል። ምክትል ቃል አቀባያቸው ካሌ ብራውን ከዚህም ሌላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሀገራቸው የአፍሪቃ ሕብረትና ሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ለውይይትና እርቅ የሚያደርጉትን ጥረት ለመደገፍ ፈቃደኛ መሆኗን መግለጻቸውንም አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ትናንት ለምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ በሕግ «ተጠያቂ» ካሉት ቡድን ጋር ውይይት እንደማይታሰብ ገልጸዋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ከጠቅላይ ሚንስር ዐቢይ ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ሲቪሎች ለተጨማሪ ጉዳት እንዳይዳረጉና ውጊያውን ሸሽተው ወደ ሱዳን ለሚሸሹ ስደተኞች ከለላ ስለመስጠት አጽንኦት ሰጥተው መነጋገራቸውንም አመልክተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥት የትግሬንም ሆነ የሁሉንም ጎሳዎች ሰብዓዊ መብት መከበሩን እንዲያረጋግጥ መማጸናቸውንም ቃል አቀባዩ ጠቅሰዋል። አያይዘውም ዩናይትድ ስቴትስ ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ ጉድኝት እንዳላት ገልፀው፣ በውይይታቸው «ታሪካዊ» ያሉትን የኢትዮጵያን የለውጥ አጀንዳ መደገፍ እንደምትቀጥል፤ በአፍሪቃ ቀንድም ኢትዮጵያ ብልጽግናንና መረጋጋትን ለማስፈን ጠቃሚ ሚና እንደምትጫወት መነሳቱንም ጠቅሰዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የእናት ወግ የበጎ አድራጎት ማህበር  ከኃይለማርያም እና ሮማን ፋዉንዴሽን  ጋር ተዋሀደ።

በቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ተስፋዬ አነሳሽነት በ2006 ዓ.ም የተቋቋመዉ እና በአዲስ አበባ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የህጻናት የቁርስና ምሳ ምገባ ፕሮግራም ፈር ቀዳጅ በመሆን ከ21 ሺህ በላይ ደሀ ህጻናትን ሲመግብ የነበረዉ የእናት ወግ  የበጎ አድራጎት ማህበር ከኃይለማርያም እና ሮማን ፋዉንዴሽን ጋር መዋሀዱን ፋውንዴሽኑ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡የእናት ወግ የበጎ አድራጎት ማህበር ከበጎ አድራጊ ኢትዮጵያዊያን ግለሰቦች እዲሁም የተለያዩ ተቋሞች የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ ሲያካሄደዉ የቆየዉ የምገባ ፕሮግራም ህጻናት በምግብ እጦት ምክንያት ለጤና እና ለስነልቦና ጉዳቶች እንዳይዳረጉ አንዲሁም ከትምህርት ገበታቸዉ እንዳይስተጓጎሉ በማድረግ ለትምህርት ተደራሽነት እና የኢኮኖሚ ጥራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ድርጅት ነዉ፡፡

በተጨማሪም የእናት ወግ በምገባ ስራዉ ላይ ለተሰማሩ ከ1 ሺህ 500 በላይ ችግረኛ ሴቶች የስራ እድል በመፍጠር የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን  ለማጠናከር ሲሰራ ቆይቷል፡፡

የእናት ወግ የበጎ አድራጎት ማህበር መልካም ተሞክሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2012 ዓ.ም በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለጀመረዉ የምግባ ፕሮግራም እንደሞዴል ያገለገለና መሰረት የጣለ ዉጤታማ የበጎ አድራጎት ስራ ነዉ፡፡የእናት ወግ የበጎ አድራጎት ማህበር ወደ ኃይለማርያም እና ሮማን ፋዉንዴሽን የተዋሃደዉ በድርጅቱ ሲከናወኑ የቆዩ የስርአተ ምግብና  የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራዎችን በማጠናከር እና በዘላቂነት ለማስቀጠል እንዲቻል ነዉ፡፡የእናት ወግ የበጎ አድራጎት ማህበር  በዚህ ዘርፍ ያካበተዉ የበርካታ አመታት ተሞክሮ  ኃይለማርያም እና ሮማን ፋዉንዴሽን  በስርአተ ምግብና  የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ዙርያ ለሚያካሂዳቹ የአድቮኬሲ ስራዎችና ፕሮግራሞች ጠንካራ መሰረት የሚጥሉ ናቸዉ፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የ600 ሺ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ለማቅረብ ጨረታ ያሸነፉ ሁለት ድርጅቶች ውል ተፈራረሙ!

የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በቅርቡ ላወጣቻው ሁለት የስንዴ ግዥ ጨረታዎች የተሻለ ዋጋ ያቀረቡ የጀርመን እና ቱርክ ድርጅቶች ምርቱን ለማቅረብ ውል ተፈራረሙ፡፡ለብሄራዊ አደጋ ስጋት አስተዳደር ኮሚሽን የ200 ሺ ሜትሪክ ቶን እንዲሁም ለንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የገበያ ማረጋጊያ 400 ሺ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ ጨረታ ከሳምንታት በፊት ተከፍቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ለ200 ሺ ሜትሪክ ቶን ጨረታ የጀርመኑ Marthina Mertens Sampl Lebensmittel Handel (Food Trading) ዝቅተኛ ዋጋ አቅርቦ በጨረታው ማሸነፉ የተገለፀ ሲሆን፡፡የቱርኩ Rosentreter Global Food Trading ለ400 ሺ ሜትሪክ ቶኑ እጅግ የተሻለ ዋጋ በማቅረብ ጨረታውን ማሸነፍ ችሎ ነበር፡፡በመሆኑም ሁለቱ ድርጅቶች ምርቱን ለማቅረብ ውል ያሰሩ ሲሆን ምርቱን በጨረታ ሰነዱ በተጠቀሰው መሰረት ምርቱን እንደሚያቀርቡ የግዥ አገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ መልካሙ ደፋሊ ለካፒታል ተናግረዋል፡፡የሁለቱም ተጫራቾች ምርት ከሩስያው ኖቨርሲስክ ወደብ እንደሚጫን ይጠበቃል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
በማይካድራ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም እየመረመረ ያለው ቦርድ ገልጿል፡፡

መርማሪ ቦርዱ ሰሞኑን በማይካድራ ከተማ ባደረገው የመስክ ምልከታ በከተማዋ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ስለተፈጸመው አሰቃቂ የግድያ ወንጀል በቦታው ተገኝቶ መረጃ ሰብስቧል።የመርማሪ ቦርዱ አባላት ከ50 እስከ 60 አስከሬኖች በአንድ ላይ የተቀበሩባቸውን ቦታዎች ተዘዋውረው መመልከታቸውን ገልፀዋል፡፡

መርማሪ ቦርዱ ባገኘው መረጃ የሟቾቹ ቁጥር ቀደም ሲል የተለያዩ ሚዲያዎችና የሰብዓዊ መብት ተቋማት ከጠቀሱት ሊያሻቅብ እንደሚችል ተገልጿል፡፡የምርመራ ቡድኑ አባላት በአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች ጥቆማ ደርሷቸው በአካባቢው የሚገኘው ጊዜያዊ አስተዳደር ገና ያልደረሰባቸውና አፈር ያልለበሱ አስከሬኖችን መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡ጥቃቱ በአካባቢው የነበረው የሚሊሻና የፖሊስ ጸጥታ መዋቅር አከባቢውን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለቆ ሸሽቶ ከመውጣቱ በፊት "ሳምሪ" ከተባለ መደበኛ ያልሆነ የትግራይ ወጣቶች ቡድን ጋር በማበር የፈጸሙት ወንጀል ስለመሆኑ ቦርዱ ማረጋገጥ ችያለው ብሏል፡፡

በአንጻሩ አጥቂው ቡድን ሲያሳድዳቸው የነበሩ ሰዎችን በቤታቸው፣ በቤተክርስቲያንና በእርሻ ቦታዎች በመደበቅ የብዙ ሰዎች ህይወት እንዲተርፍ ያደረጉ የትግራይ ተወላጆችም መኖራቸውን መርማሪ ቦርዱ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡የመርማሪ ቦርዱ አባላት ተጎጂዎቹ በብዛት በሚኖሩበትና በተለምዶ "ግንብ ሰፈር" በተባለው አካባቢ ተገኝተው ከሟች ቤተሰቦችና ከግድያ ሙከራው ከተረፉ ሰዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ ከጉዳቱ ሰለባዎች ጋር በተወያዩበት ወቅት፤ መንግስት ወንጀለኞቹን አድኖ ለፍርድ እንዲያበቃ ለማገዝ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በቀን የ31 ሰዎች ህይወት በኤች አይ ቪ ምክንያት ያልፋል!

የኤች አይ ቪ/ ኤድስ ቫይረስ ወረሽኝ በአለማችን ከተከሰተ 40 አመታትን አስቆጥሯል። በእነዚህ አመታት ውስጥ 32.7 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሀገራችን ደግሞ በዓመት 14ሺህ ሰዎች ህይወታቸው እንደሚያልፍ የፌደራል የኤች.አይ.ቪ መካላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮ ለአዲስ ዘይቤ ገልፅዋል፡፡ በሃገራችን በአሁን ሰዓት 669 ሺ ሰዎች ከበሽታው ጋር አብረው የሚኖሩ ሲሆን በቀን 31 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ የቢሮው የኮሚውኒኬሽን ዳይሬክተር የሆነው አቶ ዳንኤል በትረ ገልጿል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት 2019 የሰራው ጥናት በአለማችን 38 ሚሊዮን ሰዎች ከቫይረሱ ጋር አብረው እንደሚኖሩ ያሳያል፡፡ ጥናቱ በወጣበት አመት ብቻ 1.7 ሚሊዮን አዲስ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሲሆኑ 690 ሺ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ዛሬ ለ33ኛ ጊዜ ህዳር 22፣ 2013 ዓም እየተከበረ የሚገኘው የአለም አቀፍ የፀረ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ቀን “ኤች አይ ቪ/ኤድስን ለመግታት ዓለም አቀፋዊ ትብብር የጋራ ኃላፊነት” በሚል መሪ ቃል ነው፡፡ የዘንድሮን ለየት የሚያደርገው ደግሞ የኮቪድ ወረርሽኝ በመከሰቱ ምክኒያት የጤና ዘርፎቻቸው ደካማ በሆኑ ሃገራት ላይ ለኤች.አይ.ቪ ቫይረስ አስፈላጊውን የህክምና እርዳታ ለመስጠት እንቅፋት መሆኑ ነው፡

Via @Addiszeybe
@YeneTube @FikerAssefa
ሽሬ ጊዜያዊ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ ተሾመላት!

በሽሬ ከተማ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ከንቲባ በመሆን የተመረጡት መምህር ሐጎስ በርሄ ህዝባዊ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።“ከአገር ሽማግሌዎች፣ ከወጣቶችና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን በከተማዋ ሰላም እንዲሰፍን፣ ማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲሳለጡና ልማት እንዲከናወን እሰራለሁ” ብለዋል።የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ሆነው የተመረጡት ኢንጂነር ጀሚል ሙሐመድ በበኩላቸው ሕዝብ የጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።

በከተማው ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋሙ ለሕዝቡ መረጋጋት እንደሚያመጣ ጠቁመው፤ ሰላም ለማረጋገጥ ሂደትም ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።በከተማው የአቅም ግንባታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው የተመረጡት መምህርት ንግሥቲ ፋንታሁንም ህዝቡን በቅንነትና ታማኝነት ለማገልገል መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።የከተማው ነዋሪዎች ከጎናቸው በመቆም ድጋፍና እገዛ እንዲያደርጉላቸውም አመራሮቹ ጠይቀው፤ ቀደም ሲል በህወሃት ዘመን የነበረው በመተዋወቅ፣ በዝምድናና በኔትወርክ መስራት እንደማይደገም አረጋግጠዋል ተብሏል።የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት ዶክተር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ህዝቡን በማወያየት ላይ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ለ2012 ዓም ተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ አደረገ!

ጅግጅጋ ዩንቨርስቲ #MoSHE ከህዳር 21/2013 ዓም ጀምሮ ለተመራቂ ተማሪዎች ዩንቨርስቲዎች ጥሪ እንዲያደርጉ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከህዳር 26 እስከ 28/2013 ዓም የመግቢያ ጊዜ መሆኑን አሳውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ክልል ቀጣዩና ጊዜ የማይሰጠው ትኩረቴ በሬሽን ለሚኖረው ሕዝብ መድረስ እና የወደሙ የክልሉን መሰረተ ልማቶች መጠገን ነው አለ።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባቦት ቃል አቀባዩ ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)ን የሰኞ ኅዳር 21 የእንደራሴዎች ምክር ቤት ማብራሪያ ተከትሎ ከሮይተርስ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገዋል።ለ41 ደቂቃ ባደረጉት ቃል ምልልስ ስለቀጣዩ የመንግሥት ትኩረት ተጠይቀዋል። ሲመልሱም ትግራይን በአካላዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊና ሰነ ልቡናዊ ጉዳዮች ፈጥኖ መገንባት ይፈልጋል ነው ያሉት።

ትግራይ ክልል ከሌሎቹ ክልሎችም በከፋ ሁኔታ በርካታ ሕዝብ ለምግብ ገንዘብ እየተደጎመ የሚኖርበት ነው ያሉት ቃል አቀባዩ ለዚህ ሕዝብ መድረስ እንደሚያስፈልግ ነው ያስረዱት።በውጊያው ሕወሓት የአክሱም አየር ማረፊያን ጨምሮ በርካታ መሰረተ ልማቶችን እያወደመ መሸሹን በመጥቀስም መንግሥት መልሶ ገንባት የሚጠበቅበት ድልድዮች ብዙ ናቸው ብለዋል።በትግራይ ክልል ጥቂትና በመቶዎች የሚቀጠሩ የመከለከያና የፖለቲካ ባለሥልጣናት እኛን ይጠሉናል ያሉት ሬድዋን፤ ሕዝቡን ሲጠቀሙበትና ሲበዘብዙት እንደነበር ያነሳሉ። በአንፃሩ ሕዝብ የፌደራሉን መንግሥት ይወዳል ሲሉም ተደምጠዋል።

[Reuters/ Ahadu TV]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የምርት ገበያ የግብይት ታሪክ በሁሉም የምርት አይነቶች በመጠንም በዋጋም ከፍተኛው ግብይት ዛሬ ተመዝግቧል። በዛሬው እለት የተመዘገበው የግብይት ዋጋ 427 ሚልዮን ብር መሆኑን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትሩ መላኩ አለበል የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::

[ፎቶ: ካፒታል]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ “Decade of Airline Excellence Award” ሽልማትን ተቀዳጀ። ሽልማቱ አየር መንገዳችን ለአቪዬሽን ኢንደስትሪው ፈታኝ አለም አቀፋዊ ቀውስ ባጋጠመበት ወቅት ላስመዘገበው የላቀ አፈፃፀም እና ስኬት እውቅና የሰጠ ነው።

Via Ethiopian Airlines
@YeneTube @FikerAssefa
ፍርድ ቤት ዛሬ የአዲስ ስታንዳርድ መጽሄት አዘጋጅ መድኀኔ ዕቁበ ሚካዔል በ10 ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈታ ማዘዙን መጽሄቱ ዘግቧል፡፡ የኢትዮጵያ ሔራልድ ጋዜጣ ጋዜጠኞች የሆኑት ሃፍቶም ገ/እግዚያብሄር እና ጸጋዬ ሐጎስ እንዲሁም የአል ዐለም ዐረብኛ ጋዜጣ ባልደረባ አብርሃ ሐጎስ በዋስትና እንዲፈቱ አዟል፡፡

[Wazema/AS]
@YeneTube @FikerAssefa
ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ

ከተፈላጊ የህወሓት ጁንታ አባላት አንዷ የሆኑት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ።

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም የህውሓት ከፍተኛ አመራርና በመንግስት ከፍተኛ ሃላፊነት የነበራቸው እንዲሁም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት አገልግለዋል።

Via:- Fana
@Yenetube @Fikerassefa
የፌደሬሽን ምክር ቤት የቀድሞዋ አፈ ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም እጃቸውን እንደሰጡ መንግሥት አስታወቀ።በወንጀል ተጠርጥረው በሕግ የሚፈለጉት የሕወሓት ሥራ አስፈፃሚዋ የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸው ይታወቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከነገ ጀምሮ በትግራይ ክልል ባሉ ባንኮች አካውንት የከፈቱና ከትግራይ ክልል ውጭ ያሉ ደንበኞች በያሉበት የአገሪቱ አካባቢዎች ሂሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ መፈቀዱ እና ለባንኮችም ይህ መመሪያ መተላለፉን ብሄራዊ ባንክ ዛሬ ኅዳር 22/2013 አስታውቋል።

ይህ በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በወንጀል ተጠርጥረው ሂሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ የተደረጉ ደንበኞችን የሚመለከት እንዳልሆነም ታውቋል።

የፀጥታ ሁኔታ ለባንኮች አመቺ በሆነባቸው የትግራይ ክልል ከተሞች ባንኮች ተከፍተው ስራ እንዲጀምሩ ብሄራዊ ባንክ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። የፀጥታ ሁኔታ አመቺ ባልሆነባቸው የክልሉ ከተሞች ባንኮች ተዘግተው እንደሚቆዩ ብሄራዊ ባንክ ለኢቲቪ ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሰሜንና ምዕራብ አማራ ክልል ተዘግተዉ የነበሩ ት/ቤቶች ተከፈቱ!

መንግስት ህግ የማስከበርና የህልውና ዘመቻ ባለው ውጊያ ምክንያት በአንዳንድ የሰሜንና ምዕራብ አማራ ዞኖች ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ተከፍተው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፣ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በቀጣዩ ወር ይሰጣልም ተብሏል፣ ለፈተናው ከ415 ሺህ በላይ ተማሪዎች ይቀመጣሉ፡፡

መንግስት ህግ የማስከበርና የህልውና ዘመቻ ባለው ውጊያ ምክንያት በአንዳንድ የሰሜንና ምዕራብ አማራ ዞኖች ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ተከፍተው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፣ በኮቪድ ምክንያት ሲገፋ የነበረው የ2012 ዓ ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በቀጣዩ ወር ይሰጣልም ተብሏል፣ ለፈተናው በ5ሺህ 162 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ከ415 ሺህ በላይ ተማሪዎች ይቀመጣሉ፡፡

 የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ዛሬ በጽ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ሰሞኑን በአገሪቱ ተከስቶ በነበረውና መንግስት በትግራይ ክልል “ህግ የማስከበርና የህልውና ዘመቻ” ባለው ውጊያ ምክንያት በሰሜን ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደርና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች 193 ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ቆይተዋል፡፡
ቢሮ ኃላፊው እንዳሉት አሁን በአካባቢዎች አንፃራዊ ሰለም የሰፈነ በመሆኑ ትምህርት ቤቶቹ ከትናንትና ጀምሮ ተከፍተው ተማሪዎች እየተማሩ እንደሆነ አብራረወተዋል፡፡  

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ባስከተለው ችግር ትምህርት ቤቶች ባለፈው መጋቢት 2012 ዓም መዘጋታቸውንና እንደገና ጥቅምት 2013 ዓም ቢከፈቱም ተፈጥሮ በነበረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በሰሜንና ምዕራባዊ የአማራ ክልል ዞኖች በርካታ ት/ቤቶች እንደገና ተዘግተው በመቆየታቸው አገር አቀፍና ክልል አቀፍ ፈተናዎች መራዘማቸውን አስታውሰዋል፡፡

 ጊዜው እየገፋና ሁኔታውም ጫና እየፈጠረ ሰኔ ላይ ይሰጥ የነበረው የ2012 ዓ ም የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በቀጣዩ ወር እንደሚሰጥ ዶ/ር ይልቃል ተናግረዋል፡፡

ፈተናውን መስጠትየሚያስችሉ ዝግጅቶች ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ መሆናቸውን ቢሮ ኃላፊው አመልክተው ለተግባራዊነቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
ተማሪዎችም ፈተናው ከሌላው ጊዜ የተለየ አለመሆኑን አውቀው ባለችው አጭር ጊዜ ተዘጋጅተውና በስነልቦናም ዝግጁ ሆነው ፈተናቸውን እንዲፈተኑ አሳስበዋል፡፡  የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ቢያዝን በበኩላቸው የ2013 የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች ሁሌም እንደሚደረገው በመደበኛ የመፈተኛ ጊዜያቸው ሰኔ ወር አጋማሽላይ እንደሚሰት ተናግረዋል፡፡

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
በህወሓት ቁጥጥር ሥር ነበሩ የተባሉ ከአንድ ሽህ አንድ መቶ በላይ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ አማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን መግባታቸውን የዞኑ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ አስታውቋል፡፡በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ዞኑ የሚገቡት የሠራዊት አባላት ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል መምሪያው ገልጿል።

Via:- VOA
@YeneTube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ 19 ምክንያት የደረሰው የህይወት ጉዳት 1706 መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የሚኒስቴሩ የኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል የዛሬን መረጃ ሳይጨምር ሦስት መቶ ሰዎች የፅኑ ህመም ህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

@Yenetube @Fikerassefa