YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
“ማንኛውም ሰው ከኦነግ ሸኔ ታጣቂ ኃይል ጋር ያለውን ግንኙነት በአስቸኳይ ማቋረጥ አለበት”፦ አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ

የጉጂ አባ ገዳ እና የኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት ሰብሳቢ አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ ማንኛውም ሰው ራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ ከሚጠራው ታጣቂ ኃይል ጋር ያለውን ግንኙነት በአስቸኳይ እንዲያቋርጥ አሳስበዋል።አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደቡብ ኦሮሚያ እያጋጠመ ያለውን አለመረጋጋት አስመልክቶ ቡሌ ሆራ ከተማ ውስጥ የተካሄደውን ስብሰባ ተከትሎ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል።በውሳኔዎቹም ከአሁን ወዲህ መንግሥት ካስታጠቀው ኃይል ውጭ የትኛውም አካል መሣሪያ ታጥቆ ሕዝብ ውስጥ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን ገልጸዋል።

የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ኃይል በተለይ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን እንግልት ከግንዛቤ በማስገባት ኦሮሞ የሆነ ሰው ሁሉ ከዚህ ታጣቂ ኃይል ጋር ያለውን ግንኙነት በአስቸኳይ እንዲያቋርጥ አባ ገዳው ውሳኔ አስተላልፈዋል።በኦሮሞ ላይ አፈ-ሙዝ አዙሮ የሚወጋ የትኛውም ወገን ኦሮሞነቱ መሰረዝ እንዳለበትም ገልጸዋል።የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ኃይል የኦሮሞን ባህል እና ወግ በመተላለፍ ከሁለት ዓመታት በፊት በገዳ የተላለፈውን አዋጅ በመጣስ የኦሮሞ ሕዝብ ለባህሉ ያለውን ክብር ያዋረደ በመሆኑ ሕዝቡ ከአሁን ወዲህ ሊነቃ ይገባል ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።ይህ ታጣቂ ኃይል በታላቁ የኦሮሞ ሕዝብ ባህል መሠረት ተመክሮ ከጥፋቱ ሊመለስ ባለመቻሉ “ጠላት” የሚል ስያሜ ሊሰጠው እንደሚገባም ነው አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ የገለጹት።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
#ሰበር ዜና

መከላከያ ሠራዊት መቀሌን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ!

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ መከላከያ ሠራዊት መቀሌን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አረጋገጡ።

የመከላከያ ሠራዊት ባካሄደው ዘመቻ ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ፣ ከተሞቻችንና ቅርሶቻችን ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ገፃቸው ገልፀዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ጠ/ሚ ዐቢይ በትግራይ ክልል ተካሄደው ህግን ማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን አስታወቁ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን አስታውቅዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፥ “በትግራይ ክልል ስናካሂድ የነበረው የህግ የማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን እና መቆሙን ላሳውቅ እወዳለሁ” ብለዋል።

“ቀጣይ ትኩረታችንም ክልሉን መልሶ መገንባት እና ሰብአዊ ድጋፎችን መድረስ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው።በዚሁ ጊዜም የፌደራል ፖሊስ በህግ የሚፈለጉ ወንጀለኛ የህወሃት አባላትን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እንደሚሰራም ገልፀዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ውድ የሃገራችን ህዝቦች!

እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን።

እነሆ ዛሬ! በሃገር መከላከያ ሰራዊታችን በሳል የውጊያ ጥበብ እና የትግል ወኔ የህውሃት ጁንታ ቡድን የከተመባትን የመቀሌ ከተማ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።

በክልሉ መንግሥት በጥንቃቄ እና በፍጥነት እየወሰደ የሚገኘው ህግ የማስከበር እርምጃ በስኬት ታጅቦ ወሳኝ የድል ምዕራፍ ተቀዳጅቷል።

ለዚህ ዘመን ተሻጋሪ ድል ላበቁን ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን፣ ለአማራ ክልል ልዩ ሃይል እና ሚሊሻዎች ታላቅ ምስጋና እና ክብር ይገባቸዋል።

በዚህ ህግ የማስከበር ዕርምጃ በኢትዮጵያዊነት ለአፍታ ለማይደራደረው የትግራይ ክልል ህዝብ ለመከላከያ ሰራዊታችን ብርቱ ደጀን በመሆን ለተጫወተው ታሪካዊ ሚና ልዩ ክብር እና ምስጋና ይገባዋል።

በመቀጠል የጁንታውን ቡድን አድኖ ለህግ የማቅረብ ተልዕኮ በተቀጣጠለው የድል ስሜት እስከመጨረሻዋ ሰዓት ተጠናክሮ ይቀጥላል።

መንግሥት በደረሰበት ወሳኝ የድል ምዕራፍ ዜጎችን ከጥቃት የመጠበቅ እና የመከላከል ተግባሩን በጥንቃቄ፣ በንቃት እና በሃላፊነት ስሜት የሚወጣ ይሆናል።

በቀጣይ በትግራይ ክልል እና በአከባቢው ፍፁም ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን አስፈላጊውን ሁሉ በመንግስት በኩል ተፈፃሚ ይደረጋል።

በአጭር ሂደት በትግራይ ክልል በጁንታው ቡድን ሴራ የፈራረሱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት እና የማቋቋም እንዲሁም በሂደት በክልሉ ዘላቂ ሰላም እና ልማት የማረጋገጥ ስራዎች በትኩረት ይከናወናሉ።

በጠንካራ የአመራር ጥበብ የተመራው ህግ የማስከበር እርምጃችን መሪ ዓላማ የጁንታውን ቡድን ካለበት ለቅሞ ለህግ ማቅረብ ተልዕኮ በመሆኑ፤ አሁንም እስከመጨረሻው ድረስ ለዓላማው የተሟላ ተፈፃሚነት የትግራይ ክልል ህዝብ ወንጀለኞችን ከተደበቁበት ፈልፍሎ የማጋለጥ ታሪካዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

አለ ገና ~ ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል!!

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ
ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን መልዕክት
@Yenetube @Fikerassefa
ደስታችን በጥንቃቄ ይታጀብ

የመቀሌን ነፃ መውጣት ተከትሎ ህዝቡ የተሰማውን ደስታ እየገለፀ ነው።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳለው በአሁኑ ሰአት በክልላችን ሁሉም አካባቢዎች ህብረተሰቡ ደስታውን እየገለፀ ሲሆን የደስታ አገላለፃችን ለሰርጎ ገቦች እንዳያጋልጠን አሁንም ወንጀለኞቹ በህግ ቁጥጥር ስር እስኪውሉ አካባቢያችንን በጥንቃቄ እንድንጠብቅ በማለት አሳስቧል።
@Yenetube @FikerAssefa
#ሰበር_ዜና

ዛሬም የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ እንዲሁም ማንደፍራ በሮኬት ተመተዋል - ኤርትሪያ ፕረስ

ከምሽቱ አራት ሰዓት አከባቢ ላይ አስመራ በሮኬት መመቷቷን ከኤርትሪያ ፕረስ የፌስቡክ ገፅ ተመልክተናል።
@Yenetube @Fikerassefa
#HappeningNow

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊት በትላንትናው ምሽት የተቀዳጀውን ድል በማስመልከት በኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በመገኘት የድጋፍ ሰልፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ።

በተያያዘም ነዋሪዎቹ 15ኛውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዘቦች በዓል በማክበር ላይ ናቸው ።

Via Addis Ababa City PS
@YeneTube @FikerAssefa
"የራያ ህዝብ እጣ ፋንታ ድህረ-ትህነግ" በሚል ምክረ ሃሳብ የምሁራን ውይይት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።

የትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ) ቡድን ድል በተደረገበት ማግስት የራያ ህዝብ እጣ ፋንታ ምን መሂን አለበት በሚል ሃሳብ የአካባቢው ተወላጆች እና ሙህራን በዛሬው እለት በአዲስ አበባ እየመከሩ ይገኛሉ፡፡በዚህ ውይይት ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የአገልግሎት ዘርፎች ክላስተር አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ የራያ ህዝብ ውብ ባህሉ እና ማንነቱ ተከብሮ ወደ ሚፈልገው እና ወደ ሚመስለው የወሎ ህዝብ እንዲጠቃለል የምሁራን ውይይት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ጊዜው ችግሮችን በውይይት የምንፈታበት እንደመሆኑ ህዝቡ ምን ይላል የሚለውን አዳምጦ በትህነግ ጭቆና ውስጥ የነበረውን ማህበረሰብ የነጻነት አየር የሚተነፍስበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ የመወያያ ሃሳብ ያቀረቡት ምህራን ትህነግ የአማርኛ ስም መጠሪያ ያላቸውን ስፍራዎች ወደ ትግርኛ ቀይሮ መቆየቱን እና ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዳይማሩ ተደርገው ስለመቆየታቸው አውስተዋል፡፡ማህበረሰቡ ላይ የተፈጸመውን በኢኮኖሚያ አሻጥር አስመልክቶም ተጽእኖ ለግዙፍ ፋብሪካ የተዘጋጁ ማሽነሪዎች ተነቅለው ወደ ትግራይ እንዲወሰዱ መደረጉ ምን ያህል የአካባቢ ነዋሪ ከምጣኔ ሃብት እድገት ተነጥሎ እንደኖረ ማሳያ ነውም ይላሉ ምሁራኑ፡፡ለገበሬው የተቆረፉ የውሃ ጉድጓዶች እንዲደፈኑ መደረግና በኢንቨስትመንት ስም ከፍተኛ የሆነ የመሬት ወረራ መፈጸም ሌላኛው የራያ አካባቢዎች ላይ በትህነግ የተፈጸመ ድርጊት ነው የሚሉት ምሁራኑ ለትህነግ ፋብሪካዎች ግብዓት እንዲሆን ከፍተኛ የሆነ የደን ጭፍጨፋ መፈጸሙንም አንስተዋል፡፡

በዚህም በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ በረሃማነት እንዲስፋፋ ሆኗል ብለዋል፡፡የአካባቢው ተወላጃም በትህነግ የተነጠቀውን ማንነቱን ለማስጠበቅ በግፍ ተገድሏል ተብሏል፡፡ አካባቢውንም ለቆ እንዲሰደድ ተደርጓል ብለዋል፡፡ዛሬም ድረስ የት እንዳሉ በማይታወቅበት ሁኔታ ታፍነው የተወሰዱ የአካባቢው ተወላጆች እንዳሉም ተነስቷል፡፡የራያ ህዝብ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች ያለፍላጎቱ ተከፋፍሎ እንዲኖር ያደረገው የትህነግ ሃይል መወገዱን ተከትሎ ዛሬም በፖለቲከኞች ጉተታ አሁን ያገኘውን እድል እንዳያጣ በጥንቃቄ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ነገ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ይሰጣሉ!

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ነገ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተገለጸ።የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚገኘው መሰብሰቢያ አደራሽ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ማካሄድ ይጀምራል፡፡

አጀንዳዎቹም
1. የም/ቤቱን 6ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፣
2. የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች የሚሰጡትን መልስ ማዳመጥ እንደሆነ ምክር ቤቱ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጁቡቲ ገቡ!

ፕሬዝዳንቷ ጁቡቲ ሲደርሱ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊዘሌ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።ፕሬዝዳንቷ በጅቡቲ በሚኖራቸው ቆይታ ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር በሁለትዮሽ በቀጠናዊ እና ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ በተመለከተ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ለነበሩ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ!

በ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ከነገ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ሚኒስቴሩ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ ከአንድ ሳምንት በኋላ ሌሎች ቀሪ ተማሪዎች እንዲገቡ እና በዚህ የትምህርት ዘመን የሚጠበቅባቸውን ሦስት የትምህርት ሴሚስቴር እንዲያጠናቅቁ በቂ ድጋፍ እና ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል ሲል ገልጿል።ተመራቂ ተማሪዎች በቀሪዎቹ አጭር ወራት ውስጥ ያልተጠናቀቁ የትምህርት እና ሥልጠና ተግባራትን በተቻለ ቅልጥፍና እና ዝግጁነት በማጠናቀቅ ተመርቀው ወደ ሥራ ዓለም እንዲትቀላቀሉ እና የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ላይ አሻራቸውን እንዲያኖሩ አሳስቧል።

ሌሎች በ2013 ትምህርት እና ሥልጠና ዘመን ሙሉ ዓመቱን በተቋማት ቆይታ የሚደርጉት ተማሪዎች በሙሉ፣ ትምህርታቸውን በአግባቡ እየተማሩ ለአገራችን እና ለሕዝባችን አንድነት እና ኅብረት እንዲሁም ብልጽግና ጉዞ ፋይዳ ያላቸው ሰብአዊ እና ማኅበራዊ በጎ አድራጎት ተግባራት እና አገልግሎቶች በንቃት በመሳተፍ ወገንተኝነታቸውን እንዲገልጹ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጥሪ አድርጓል።የከፍተኛ ትምህርት እና ሥልጠና ማኅበረሰብ በሙሉ የተለመደውን ቀና ድጋፍ እና ትብብር በማከል የ2013 ትምህርት እና ሥልጠና ዘመን የተሳካ እንዲሆን የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ከአደራ ጭምር አሳስቧል።

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa
ሦስተኛው ምዕራፍ የህግ ማስከበሩ ዘመቻ በድል መጠናቀቁን እና አሁን ላይ ወደ መልሶ ማደራጀት መገባቱን ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ገለጹ፡፡

“ብንማረክ እንኳን በእነርሱ አንማረክም፤ እኛን የሚማርከን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” ያሉት የራያ ግንባር የጦር አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ወቅታዊ የህግ ማስከበር ሥራን በተመለከተ በትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን ተራሮች ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸው ሦስተኛው ምእራፍ የህግ ማስከበሩ ዘመቻ በድል መጠናቀቁን እና አሁን ላይ ወደ መልሶ ማደራጀት መሸጋገራቸውን ተናግረዋል፡፡

የጁንታው ርዝራዦች የጦር መሪዎችን ማርከናል እያሉ የሚነዙት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ስለ ጦርነት አውድ ያላቸው እውቀት አናሳነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡አንድን የጦር አዛዥ ለመማረክ ሰራዊቱን ሰብሮ መግባት እንደሚጠይቅ በማብራራት፤ የትህነግ ጁንታ ቡድን ሀይል ሰራዊቱን ሰብሮ መግባት ቁመናም እንደሌለው አይተናል ብለዋል ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ፡፡ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ዘመቻውን አስመልክቶ እና በቀጣይ ሁኔታ ላይ ከጄኔራል አበባው ታደሰ ጋር በመቀሌ ከተማ መግለጫ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።

[አብመድ]
@YeneTube @FikerAssefa
በሀገር ክህደት ወንጀል ተጠርጥረዉ በእስር ላይ የሚገኙ የጦር መኮነኖች ቤት ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የሚችሉ የጦር መሳሪያዎች መያዛቸው ተገለፀ!

በሀገር ክህደት ተጠርጥረዉ በእስር ላይ የሚገኙ የጦር መኮነኖች ቤት በተደረገው ፍተሻ የጦር ሜዳ መነጽሮች፣ ጂፒኤስ፣ በሳተላይት የሚሰሩ ስልኮች፣ ቦምቦች ፣ ክላሽንኮቭ፣ ብሬን፣ለእኩይተግባር ማስፈፀሚያ የሚዉሉ የተቀየረው የሰራዉይቱ የደንብ ልብሶች እና ሌሎች በግለሰብ እጅ መያዝ የሌለባቸዉ መሳሪያዎች በፍተሻ መያዛቸወረን የፌዴራልፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የሕወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት ማድረስ ከጀመረበት እለት አንስቶ በተደረጉ ፍተሻዎችና ብርበራዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መያዛቸዉ ይታወቃል።

ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
አለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በመቀሌ ከተማ የሚገኙ ሆስፒታሎች ቁስለኞችን ለማከም የሕክምና ግብዓቶች እጥረት እንደገጠማቸው አስታወቀ። በከተማው የሚገኝ ሆስፒታል የአስከሬን ማስቀመጫ ከረጢት እንደሌለው የገለጸው ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የእጅ ጓንትን ጨምሮ መሰረታዊ አቅርቦቶች እያለቁ መሆኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ እንዳለው 500 ሺሕ ገደማ ነዋሪዎች ያሏት መቀሌ ዛሬ እሁድ እረጭ ብላ ውላለች።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ሁለት ሻንጣ ሙሉ ብር ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ።

ዋና ሳጅን ታከለ እሸቴ ይባላል የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ባልደረባ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በሁመራ ከተማ ሰላም እያስከበረ ይገኛል።

በቀን 19/03/2013 ዓ.ም ሰላም እያስከበረ በሚገኝበት ሁመራ ከተማ ላይ በአንድ በባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ(ባጃጅ) ላይ ሁለት ግለሰቦች ሁለት ሻንጣ ይዘው በመጓዝ ላይ ሳሉ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ ፍተሻ በሚያደርግበት ጊዜ ሁለቱም ሻንጣ ሙሉ ብር ሆኖ ተገኝቷል።

በወቅቱ ግለሰቦች አንዱን ሻንጣ ሙሉ ብር እንስጥህና ልቀቀን ቢሉትም ቃል የገባለትን ህዝብ እና ሙያውን በማስበለጥ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።

Via Amhara Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa