YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
#መልካም_ሰዎች_ለምን_ይሰቃያሉ?
#ሁለተኛው_ዕትም_በገበያ_ላይ

መልካም ሰዎች ላይ መጥፎ ነገር የሚደርሰው ለምንድን ነው? መከራን የሚቀበሉትስ ለምን ይሆን? ከዚህ ሁሉ ጥያቄ በኋላ እኛ ያላወቅነው ምስጢር ይኖር ይሆን?

ይህ መጽሐፍ ‹‹ፈጣሪ ለምንድነው ይሄን ሁሉ በእኔ ላይ ያመጣብኝ?›› ለምንለው ነገር ሁሉ ምላሽ አለው!!!

“በሃሳቦች የተሞላ፣ በተዋጣላቸው አመክንዮዎች የተተነተነ፣ የመንፈሳዊ ጥንካሬ መመሪያዎችን የያዘ ድንቅ መጽሐፍ!!”
#ዘ_ዋሽንግተን_ፖስት

“ይህ ላዘኑ መጽናናትን፣ ማባሪያ በሌለው ፍርሃት ለተተበተቡት ሰዎች ደግሞ ሰላምን የሚሰጥ የሃሳብ እድገት መጽሐፍ ነው!”
#ስፕሪችዋሊቲ_ኤንድ_ሄልዝ

“ይህ ለሰው ልጆች ሁሉ አስፈላጊ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ በመከራ የተሞሉ የህይወትን ውጣ ውረዶችን ለመረዳትና ፈጠራ በተሞላበት ጥብበ ለመወጣት ይጠቅማል!”
#ኖርማን_ቪንሰንት_ፒል

#ሁለተኛውን_ዕትም_በየመጽሐፍት_መደብሩና_በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል

👉 ይቀላቀሉን http://tttttt.me/teklutilahun
Forwarded from YeneTube
TOP book series 📚ቶፕ የተማሪዎች አጋዥ መፅሀፍት

📌ከ 1-12 ክፍል በ ተለያዩ ቋንቋ የተዘጋጀ
📌በ ኦሮምኛ
📌በ አማርኛ
📌በ እንግሊዘኛ በሁሉም አይነት ትምህርት የተዘጋጀ
- maths chemistry biology physics ...
📌ለ 8 እና 12ኛ ክፍል ፈተና የሚያዘጋጁ
📌ለ ልጆችም 20 አይነት ተረት መጽሀፍት ታትሞዋል

❗️❗️በሁሉም መፅሀፍት ቤት ይጠይቁ
 
ዋና አከፋፋይ : ኤደን መጽሀፍት ቤት  
* * መገናኛ ሀይሌ ህንፅ ፊት ለ ፊት
📞 0911238057
0912732493

@TOPBOOkSERIES
ከ43 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ድንበር አቋርጠው ወደ ሱዳን ገብተዋል።

በትግራይ እየተካሄደ ያለውን ወታደራዊ ግጭት በመሸሽ ወደ ሱዳን በመግባት ላይ ላለው እና ቁጥሩ እየጨመረ ለመጣው ስደተኛ የሚደረገውን ዕርዳታ ኦፕሬሽን ለመመልከት የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮምሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ካርቱም ናቸው።ቁጥሩ ከ43 ሺህ በላይ የሚሆን ተፈናቃይ በያዝነው ድንበር አቋርጦ ምስራቃዊ ሱዳን መግባቱም ተዘግቧል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን በሙያቸው ለማገዝ ሁለተኛ ዙር የአዲስ አበባ የህክምና ባለሙያዎች ልዑካን ወደ ስፍራው አቀኑ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ ሆስፒታሎች የተውጣጡ ከ60 በላይ የጤና ባለሙያዎችን እና ሁለት ድጋፍ ሰጪ አምቡላንሶች ለመከላከያ ሰራዊት ሙያዊ ድጋፍ ለመሰጠት በዛሬው እለት ወደ ስፍራው አቅንተዋል።የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ለህክምና ባለሙያዎች አሸኛኘት አድርገዋል።

የሀገር ጥሪን በመቀበል ሰራዊቱን በሙያቸው ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹት የጤና ባለሙያዎቹ በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡በመጀመሪያው ዙር የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላን ጨምሮ ስፔሻሊስት ሀኪሞች እና ነርሶች በጠቅላላው 48 የህክምና ባለሙያዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

[Addis Ababa City PS]
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስም የታተሙ ህገ ወጥ መታወቂያዎች ተገኝተዋል።

በራያ አላማጣ ከተማ ከአንድ የመንግስት ቢሮ ውስጥ በርካታ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስም የታተሙ ህገ ወጥ መታወቂያዎች ተገኝተዋል።በስፍራው አስተያየታቸውን የሰጡት ምክትል ኮማንደር ጥላሁን ታደሰ እንደገለፁት ይህን መታወቂያ የሚጠቀሙት ግለሰቦች በአማራ ህዝብ ስም ወንጀልና የሽብር ጥፋት ለማድረስ ነው ብለዋል።ይህ የትህነግ ድርጊት በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ህዝብ ስም ወንጀል በመፈፀም የአማራን ህዝብ ከሌሎች ብሄረሰቦች ጋር ለማጋጨት ያሴሩት ሴራ ነው ሲሉ ምክትል ኮማንደሩ ተናግረዋል።ሁሉም የሀገራችን ህዝብ እና የፀጥታ አካላት መታወቂያ በሚያዩበት ጊዜ በደንብ ማስተዋል ይገባል።አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ደግሞ ከሚመለከታቸው አካላት ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ምክትል ኮማንደር ጥላሁን ታደሰ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Via Amhara Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከኅዳር 30 እስከ ታኅሣሥ 2 እንደሚሰጥ ተገለጸ!

በክልል ደረጃ የሚሰጠው የ8ኛ ክፍል ፈተና በኦሮሚያ ከኅዳር 30 እስከ ታኅሣሥ 2 የሚሰጥ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።በክልሉ ከመዋዕለ ሕፃናት ውጪ ያለው የመማር ማስተማር ሂደት ከመጪው ማክሰኞ አንስቶ እንደሚጀምርም ተገልጿል።የመዋዕለ ሕፃናት ትምህርት መጀመሪያ ጊዜ ለሁለት ሳምንታት መራዘሙ ነው የተገለጸው።

@YeneTube @FikerAssefa
የህወሓት ቡድን ልዩ ሃይል አባላት በአዲ ምስኖ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዛት ያላቸው ጥይቶችን በማከማቸት የአካባቢውን ህብረተሰብ ያስቆጣ ተግባር ፈፅሟል ተባለ።

[አበበ ሰማኝ ( ከግዳጅ ቀጣና )]

አቶ በሀይሉ በርኸ "ቤተ ክርስቶያን ውስጥ የመድፍ ጥይት እና ቢ ኤም መሳሪያ አምጥተው አስቀመጡ፡፡ለምን ስንላቸው ቤተክርስትያኑ አይመታባችሁም ከተመታም የጥይት ሳጥን እንሰጣችሁና እሱን ሸጣችሁ ታስጠግኑታላችሁ አሉን" ብለዋል።

አቶ በሀይሉ፣ ቤተ ክርስትያኑ ፈርሷል ውስጡ ያለው ፅላትም ይኑር አይኑር የምናውቀው ነገር የለም ፥ ወያኔ ለሃይማኖት እኩልነት እቆማለሁ ሲል የነበረ ድርጅት ዛሬ ግን ስጋወደሙ የምንቀበልበትን የእምነት ቦታ አርክሶብናል ሲሉ በሃዘንና በቁጭት ስሜታቸውን አጋርተውናል።

በየትኛውም ፖለቲካዊ እይታ ህዝብን ያልያዘ ሃይል የድል ባለቤት ሊሆን አይችልም፡፡ከሞቱ መቃብር አፋፍ ላይ የሆነው ትህነግ፣ ግን በራሱ ልክ በተሰፋው የሴራ ፖለቲካ ተተብትቦ በሰው ህሊና ሊፈፀሙ አይደለም ሊታሰቡ የማይችሉ ተግባራትን ከመፈፀም አልቦዘነም።

ለሁሉም በመላው ህዝባችን ድጋፍ በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ጀግንነት ዘራፊውና ከሃዲው ቡድን ያለችው የተስፋ ጭላንጭል ተሟጣ የመኖር ጀንበሩ ልትጠልቅ አጭር እድሜ ብቻ ቀርተውታል።

[ፎቶግራፍ ብርሀኑ አባተ]
@YeneTube @FikerAssefa
አዋሽ ባንክ 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር አመታዊ ትርፍ ማግኘቱን ገለጸ ።

አዋሽ ባንክ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 25ኛ  ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።ባንኩ በ2019/ 2020 አጠቃላይ የትርፍ መጠን የስንምት በመቶ ዕድገት በማሳየት 3.6 ቢሊየን አመታዊ ትርፍ ማግኘቱ ባንኩ ገልጿል ።ባንኩ ባለፈው አንድ አመት 57 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ብድር ማበደሩንም አስታውቋል።ባንኩ እንዳስታወቀው በ2019/ 2020  በጀት ዓመት የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 74 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር መድረሱን ገልጿል።ይህም ከዚህ በፊት ከነበረው የ19 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተገልጿል።በበጀት አመቱ ማጠቃለያ የባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠን 19.7 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ 89.3 ቢሊየን ብር መድረሱንም ተነግሯል ።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢራን የኑክሌር ሳይንቲስቷን ግድያ እንደምትበቀል ዛተች!

የኢራኑ ፕሬዝደንት ሐሰን ሩሃኒ ለአገራቸው ዋነኛ የኑክሌር ሳይንቲስት ግድያ እስራኤልን ተጠያቂ በማድረግ፤ ግድያው የኢራንን የኑክሌር መረሃ ግብር ፍጥነት እንደማይቀንሰው ተናገሩ።ፕሬዝደንቱ ጨምረውም በሳይንቲስቱ ሞህሲን ፋክሪዛዴህ ግድያ የኢራን ጠላቶች ምን ያህል በጠለቀ "በተስፋ መቁረጥና በጥላቻ" ውስጥ እንዳሉ ያሳ ነው ብለዋል።እስራኤል ከኢራን በኩል Iየቀረበባትን ክስ በተመለከተ ምላሽ ባትሰጥም፤ ቀደም ሲል ሞህሲን ፋክሪዛዴህ ኢራን በድብቅ ከምታካሂደው የኑክሌር ጦር መሳሪያ ግንባታ ጀርባ አሉ ስትከስ ነበር።

ኢራን በዋነኛው የኑክሌር ሳይንቲስቷ ሞህሲን ፋክሪዛዴህ ላይ የተፈጸመውን ግድያ እንደምትበቀልም አሳውቃለች።ፋክሪዛዴህ ትናንት አርብ በዋና ከተማዋ ቴህራን አቅራቢያ ባልታወቁ ሰዎች በተፈጸመባቸው ጥቃት ሆስፒታል ተወስደው ነበር ህይወታቸው ያለፈው።የኢራን ሐይማኖታዊ የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ወታደራዊ አማካሪ ሆሴን ዲጋን እንዳሉት ግድያውን በፈጸሙት ላይ ኢራን "በመብረቃዊ ጥቃት" እንደምትበቀላቸው ተናግረዋል።

የምዕራባዊያን የስለላ ተቋማት እንደሚሉት ሳይንቲስቱ ፋክሪዛዴህ ኢራን በድብቅ እያካሄደች ነው ከሚሉት የኑክሌር ጦር መሳሪያ ግንባታ ፕሮግራም ጀርባ ያሉ ቁል ሰው ናቸው።ነገር ግን ኢራን እያካሄደች ያለው የኑክሌር መረሃ ግብር ለሰላማዊ ዓላማ አገልግሎት የሚውል እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጻለች።ግድያውን ተከትሎ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሐመድ ጃቫድ ዛሪፍ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ "መንግሥታዊ የሽብር ተግባር" ያሉትን እንዲያወግዝ ጠይቀዋል።"ሽብርተኞች ታዋቂውን ኢራናዊ ሳይንቲስት ዛሬ ገደሉት" ሲሉም ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የህዳሴ ግድቡ ውሃ በሚተኛበት አካባቢ ሁለተኛው ዙር የደን ምንጣሮ ለማካሄድ ካርታ እየተዘጋጀ ነው!

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ በሚተኛበት አካባቢ ሁለተኛው ዙር የደንና ቁጥቋጦ ምንጣሮ ለማካሄድ የካርታ ስራ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሥራ እድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡በመጀመሪያው ዙር አንድ ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የነበረ ደንና ቁጥቋጦ ምንጣሮ መካሄዱ ተመልክቷል።የኤጀንሲው ዳይሬክተር አቶ በሽር አብዱራሂም ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ሁለተኛው ዙር የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት በተያዘው ዓመት መጨረሻ እንደሚከናወን ይጠበቃል፡፡“ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ሲከናወን ውሃ የሚተኛበት አካባቢ የሚገኘውን ደን እና ቁጥቋጦ ለመመንጠር የሚያስችል በ”ጂ.ፒ.ኤስ.” ተክኖሎጂ የታገዘ ካርታ እየተዘጋጀ ይገኛል” ብለዋል፡፡

የካርታ ዝግጅት ሥራው ከአንድ ሳምንት በኋላ እንደሚጠናቀቅም አቶ በሽር ጠቁመዋል።የካርታ ስራው በተያዘለት ጊዜ ሲጠናቀቅ የሚመነጠረው ደን እና ቁጥቋጦ ቦታ ስፋት፣ ስራው የሚጠናቀቅበት ጊዜ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ዝርዝር ሥራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸዋል፡፡በሁለተኛው ዙር ምንጣሮ ከሶስት ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል ይፈጠራል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል፡፡በመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት ቀድሞ በተካሄደ የደን እና ቁጥቋጦ ምንጣሮ በማህበር ለተደራጁ ከ1 ሺህ 500 በላይ ዜጎች የሥራ እድል እንደተፈጠረ አቶ በሽር አስታውሰዋል፡፡ለመጀመሪያው ዙር ምንጣሮ ከ31 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉና በወቅቱም አንድ ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የነበረ ደን እና ቁጥቋጦ ተመንጥሯል።

(ኢዜአ)
@YeneTube @FikerAssefa
የመከላከያ ሰራዊት መቐለ መግባቱን ዲፕሎማቶችና ዶ/ር ደብረፂዮን አስታወቁ!

ዶክተር ደብረፂዮን ለሮይተርስ ባደረሱት የጽሁፍ መልዕክት መቐለ ከተማ ላይ ከባድ ፍንዳታ እንደሚሰማ ገልፀዋል።ከከተማው ነዋሪዎች ጋር ቀጥተኛ ግኑኝነት አላቸው የተባሉ ዲፕሎማቶችም ይህንን አረጋግጠልኛል ብሏል ሮይተርስ።ዲፕሎማቶቹ እንዳሉት በከተማዋ ሰሜናዊ ክፍል ሃምዳይ በሚባል አካባቢ ፍንዳታው ተሰምቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ታግተው የነበሩ ከ6 ሺህ በላይ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የልዩ ኃይል አባላት መለቀቃቸው ተገለጸ፡፡

በትህነግ ወታደራዊ ቡድን ታግተው የነበሩ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ አባላት፣ የፌዴራል ፖሊስ አባላትና በተለያዩ ጊዜያት የተወሰዱ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት መለቀቃቸውንና ሰሜን ጎንደር ዞን በየዳ ወረዳ መግባት መጀመራቸውን ወረዳው አስታውቋል፡፡ የበየዳ ወረዳ አስተዳዳሪ ታደገኝ ውባዬሁ በስልክ እንዳስታወቁት ከተለቀቁት ወታደሮች መካከል 606 የትግራይ ክልል ወሰንን አልፈው በየዳ ወረዳ ልዋሬ ቀበሌ ገብተዋል፡፡

ወታደሮቹ ብዛታቸው ከ6 ሺህ በላይ እንደሆነና መኮንኖቹን በሙሉ ለይተው እንዳስቀሯቸው መግለጻቸውን አቶ ታደገኝ ለአብመድ ተናግረዋል፡፡የሠራዊት አባላቱ በርሀብ ተጎድተውና ተጎሳቁለው እስከ ተከዜ ድረስ በመኪና በትህነግ መሸኘታቸውን አቶ ታደገኝ ገልጸው የተወሰኑ አባላትም በርሀብና ድካም ሕይወታቸው ማለፉን አመልክተዋል፡፡ ወረዳው የመሠረተ ልማት ችግር ያለበት በመሆኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላቱን ተቀብሎ ከልዋሬ ወደ ደባርቅ ለማጓጓዝ የተሽከርካሪ እጥረት መኖሩን የገለጹት አቶ ታደገኝ መንግሥት አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

ወረዳው በቻለው አቅም ለደረሱት የዕለት ምግብና የሕክምና ዕርዳታ እያደረገ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡ትህነግ ከሠራዊት አባላቱ ጋር አስርጎ የራሱን ሰዎች እንዳያስገባ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ እንደሆነ የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው ልዋሬ ቀበሌ የደረሱትን በወረዳው ተሽከርካሪዎች ወደ ዋና ከተማው ድል ይብዛ እያጓጓዙ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

[አብመድ]
@YeneTube @FikerAssefa
ዳንኤል ብርሃኔን ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም አገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ 7 ግለሰቦች እና በ27 ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዘዝ መውጣቱን ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ!

የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙና በተለያዩ እርከን በሚገኙ 27 ወታደራዊ ሹማምንት በፈፀሙት የዘረፋ ወንጀል ንብረታቸው የሚፈለግ የጁንታው ህወሃት ቡድን አባላት እና ዳንኤል ብርሃኔ፣ ዶክተር እዝቅኤል ገቢሳ፣ ዶክተር አወል አሎ ቃሲም እና ሌሎች አምስት ግለሰቦች በአገር ውስጥና ባህር ማዶ ሆነው የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም አገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የመያዣ ትዕዘዝ መውጣቱን ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በመግለጫው መሠረት ቀደም ሲል በፈፀሙት የአገር ክህደት ወንጀል የመያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸው 117 ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች በተጨማሪ ስማቸው ቀጥሎ የተገለፀው 7 በተለያየ እርከን ላይ የሚገኙ ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዛዝ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሠረት፡-
1/ሜጀር ጀነራል ዘውዱ ኪሮስ ገብረኪዳን
2/ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሣይ
3/ ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር ዓለምሰገድ
4/ኮሎኔል የማነ ገብረሚካኤል
5/ሻምበል ተወልደ ገብረመድህን
6/ኰሎኔል ጌትነት ግደያ
7/ኮሚሽነር ረታ ተስፋዬ

ሲሆኑ በተያያዘም ቀደም ሲል የነበራቸው ወታደራዊ ኃላፊነት እና ከጁንታው የህወሃት ቡድን ጋር ያላቸውን ጥብቅ ትስስር ተጠቅመው ከፍተኛ የዘረፋ ወንጀል በመንግሥት ላይ በመፈፀም ከፍተኛ ንብረት ማካበታቸው የተደረሰባቸው 2ዐ ግለሰቦችም ስማቸው ቀጥሎ ተገልጿል፡፡
1. ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ
2. ሜ/ጀ ገብረ አድሃና /ገብረዲላ/
3. ተክለብርሃን ወልደአረጋይ /ሳንቲም/
4. ሜ/ጀ ብርሃነ ነጋሽ /ወዲመዲህን/
5. ሜ/ጄ ማዕሾ በየነ
6. ሜ/ጄ ኢብራሂም አብዱልጀሊል
7. ሜ/ጄ ዮሃንስ ወልደጊዮርጊስ
8. ሜ/ጄ ነጋሲ ትኩዕ
9. ብ/ጄ አባዲ ፍላንሳ
10. ብ/ጄ ፀጋየ ተሰማ /ፓትሪስ/
11. ብ/ጄ ምግበ ኃይለ
12. ብ/ጄ ተክላይ አሸብር /ወዲ አሸብር/
13. ብ/ጄ ኃይለሥላሴ ግርማይ /ወዲ ዕበይተ/
14. ብ/ጄ ሙሉጌታ በርሔ
15. ኮ/ል ተወልደ ገብረተንሳይ
16. ኮ/ል ገብረእግዚአብሔር ዓለምሰገድ
17. ኮ/ል ደጀን ግርማይ
18. ኮ/ል የማነ ገብረሚካኤል
19. ኮ/ል ገብረሀንስ አባተ/ /ወዲአባተ/
20. ሻምበል ተወልደ ገብረመድህን /ወዲ አድዋ/

ከሕዝብ የዘረፉትን ንብረቶች ማስመለስ ይቻል ዘንድ ንብረቶቹ የሚገኙበትን ትክክለኛ አድራሻ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ቢሮ ስልክ ቁጥሮች፡- 011 1 55 12 00 ወይም የነፃ የጥሪ መስመር 861 ወይም በአካል ወንጀል ምርመራ ቢሮ በመገኘት እንድታሳውቁ ሲል ፖሊስ ጠይቋል፡፡

በመጨረሻም በአገር ውስጥና በውጪ አገር ተቀምጠው የተለያዩ የሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም አገር በማፍረስ ተግባር ላይ የተሰማሩ፡-

1/ዶክተር እዝቅኤል ገቢሳ
2/ዶክተር አወል አሎ ቃሲም
3/ዶክተር ኢታና ሀብቴ
4/ዶክተር ፀጋዬ አራርሳ
5/አቶ ዳንኤል ብርሃኔ
6/አቶ ፍፁም ብርሃኔ
7/አቶ አሉላ ሰለሞን
8/ ሠናይት መብርሃቱ

በፈፀሙት የአገር ማፍረስ ወንጀል በሕግ የሚፈለጉ መሆኑን እናስታውቃለን ሲል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
“ማንኛውም ሰው ከኦነግ ሸኔ ታጣቂ ኃይል ጋር ያለውን ግንኙነት በአስቸኳይ ማቋረጥ አለበት”፦ አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ

የጉጂ አባ ገዳ እና የኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት ሰብሳቢ አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ ማንኛውም ሰው ራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ ከሚጠራው ታጣቂ ኃይል ጋር ያለውን ግንኙነት በአስቸኳይ እንዲያቋርጥ አሳስበዋል።አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደቡብ ኦሮሚያ እያጋጠመ ያለውን አለመረጋጋት አስመልክቶ ቡሌ ሆራ ከተማ ውስጥ የተካሄደውን ስብሰባ ተከትሎ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል።በውሳኔዎቹም ከአሁን ወዲህ መንግሥት ካስታጠቀው ኃይል ውጭ የትኛውም አካል መሣሪያ ታጥቆ ሕዝብ ውስጥ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን ገልጸዋል።

የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ኃይል በተለይ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን እንግልት ከግንዛቤ በማስገባት ኦሮሞ የሆነ ሰው ሁሉ ከዚህ ታጣቂ ኃይል ጋር ያለውን ግንኙነት በአስቸኳይ እንዲያቋርጥ አባ ገዳው ውሳኔ አስተላልፈዋል።በኦሮሞ ላይ አፈ-ሙዝ አዙሮ የሚወጋ የትኛውም ወገን ኦሮሞነቱ መሰረዝ እንዳለበትም ገልጸዋል።የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ኃይል የኦሮሞን ባህል እና ወግ በመተላለፍ ከሁለት ዓመታት በፊት በገዳ የተላለፈውን አዋጅ በመጣስ የኦሮሞ ሕዝብ ለባህሉ ያለውን ክብር ያዋረደ በመሆኑ ሕዝቡ ከአሁን ወዲህ ሊነቃ ይገባል ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።ይህ ታጣቂ ኃይል በታላቁ የኦሮሞ ሕዝብ ባህል መሠረት ተመክሮ ከጥፋቱ ሊመለስ ባለመቻሉ “ጠላት” የሚል ስያሜ ሊሰጠው እንደሚገባም ነው አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ የገለጹት።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
#ሰበር ዜና

መከላከያ ሠራዊት መቀሌን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ!

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ መከላከያ ሠራዊት መቀሌን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አረጋገጡ።

የመከላከያ ሠራዊት ባካሄደው ዘመቻ ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ፣ ከተሞቻችንና ቅርሶቻችን ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ገፃቸው ገልፀዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ጠ/ሚ ዐቢይ በትግራይ ክልል ተካሄደው ህግን ማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን አስታወቁ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን አስታውቅዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፥ “በትግራይ ክልል ስናካሂድ የነበረው የህግ የማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን እና መቆሙን ላሳውቅ እወዳለሁ” ብለዋል።

“ቀጣይ ትኩረታችንም ክልሉን መልሶ መገንባት እና ሰብአዊ ድጋፎችን መድረስ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው።በዚሁ ጊዜም የፌደራል ፖሊስ በህግ የሚፈለጉ ወንጀለኛ የህወሃት አባላትን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እንደሚሰራም ገልፀዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ውድ የሃገራችን ህዝቦች!

እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን።

እነሆ ዛሬ! በሃገር መከላከያ ሰራዊታችን በሳል የውጊያ ጥበብ እና የትግል ወኔ የህውሃት ጁንታ ቡድን የከተመባትን የመቀሌ ከተማ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።

በክልሉ መንግሥት በጥንቃቄ እና በፍጥነት እየወሰደ የሚገኘው ህግ የማስከበር እርምጃ በስኬት ታጅቦ ወሳኝ የድል ምዕራፍ ተቀዳጅቷል።

ለዚህ ዘመን ተሻጋሪ ድል ላበቁን ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን፣ ለአማራ ክልል ልዩ ሃይል እና ሚሊሻዎች ታላቅ ምስጋና እና ክብር ይገባቸዋል።

በዚህ ህግ የማስከበር ዕርምጃ በኢትዮጵያዊነት ለአፍታ ለማይደራደረው የትግራይ ክልል ህዝብ ለመከላከያ ሰራዊታችን ብርቱ ደጀን በመሆን ለተጫወተው ታሪካዊ ሚና ልዩ ክብር እና ምስጋና ይገባዋል።

በመቀጠል የጁንታውን ቡድን አድኖ ለህግ የማቅረብ ተልዕኮ በተቀጣጠለው የድል ስሜት እስከመጨረሻዋ ሰዓት ተጠናክሮ ይቀጥላል።

መንግሥት በደረሰበት ወሳኝ የድል ምዕራፍ ዜጎችን ከጥቃት የመጠበቅ እና የመከላከል ተግባሩን በጥንቃቄ፣ በንቃት እና በሃላፊነት ስሜት የሚወጣ ይሆናል።

በቀጣይ በትግራይ ክልል እና በአከባቢው ፍፁም ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን አስፈላጊውን ሁሉ በመንግስት በኩል ተፈፃሚ ይደረጋል።

በአጭር ሂደት በትግራይ ክልል በጁንታው ቡድን ሴራ የፈራረሱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት እና የማቋቋም እንዲሁም በሂደት በክልሉ ዘላቂ ሰላም እና ልማት የማረጋገጥ ስራዎች በትኩረት ይከናወናሉ።

በጠንካራ የአመራር ጥበብ የተመራው ህግ የማስከበር እርምጃችን መሪ ዓላማ የጁንታውን ቡድን ካለበት ለቅሞ ለህግ ማቅረብ ተልዕኮ በመሆኑ፤ አሁንም እስከመጨረሻው ድረስ ለዓላማው የተሟላ ተፈፃሚነት የትግራይ ክልል ህዝብ ወንጀለኞችን ከተደበቁበት ፈልፍሎ የማጋለጥ ታሪካዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

አለ ገና ~ ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል!!

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ
ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን መልዕክት
@Yenetube @Fikerassefa