YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
እነ ጃዋር መሐመድ ለደህንነታቸው ሲባል የፍርድ ሂደታቸው የሚታይበት ቦታ እንዲቀየር ጥያቄ አቀረቡ!

በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ፤ ለደህንነታቸው ሲባል የፍርድ ሂደታቸው የሚታይበት ቦታ እንዲቀይር ጥያቄ አቀረቡ። ሁለቱ ተከሳሾች በደህንነት ስጋት ምክንያት ዛሬ አርብ፤ ህዳር 18 በነበረው የችሎት ውሎ ሳይገኙ ቀርተዋል።

በአቶ ጃዋር መሐመድ ስም በሚጠራው የክስ መዝገብ ስር የተካተቱ 24 ተከሳሾች ጉዳያቸው እየታየ የሚገኘው፤ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሕገ መንግስታዊና ጸረ ሽብር ችሎት ነው። በመዝገቡ በአንደኛነት እና ሁለተኛነት የሰፈሩት አቶ ጃዋር እና አቶ በቀለ፤ ሀገሪቱ አሁን ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ እና ቀደም ሲል በእነርሱ ላይ በመገናኛ ብዙሃን ይቀርብ ነበር ባሉት ፕሮፖጋንዳ የተነሳ፤ የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው በጠበቆች በኩል ለችሎቱ ባቀረቡት ደብዳቤ አመልክተዋል።

ከጠበቆቻቸው አንዱ የሆኑት አቶ ከዲር ቡሎ ለ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" እንደተናገሩት፤ ተከሳሾቹ በእነርሱ ላይ አንድ ችግር ቢደርስ ለሀገር ደህንነት ላይ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ጭምር በደብዳቤያቸው ላይ ጠቁመዋል። በዚህም ምክንያት የፍርድ ሂደታቸው በታሰሩበት አቅራቢያ ባለ ቦታ እንዲካሄድ ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።የተከሳሾችን ጉዳይ የሚመለከተው ችሎት በጉዳዩ ላይ ከበላይ አካላት ጋር ተነጋግሮ ውሳኔ ለመስጠት ለታህሳስ 8፤ 2013 ቀጠሮ ሰጥቷል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን 469 የኦነግ ሸኔ አባላት፣ የቡድኑ ተላላኪዎች እና ሽፍቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ፡፡

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ታሪኩ ድሪባ እንደገለጹት በዞኑ 415 የኦነግ ሸኔ ተላላኪዎች እና 47 ሽፍቶች በቁጥጥር ስር ሲውሉ 7 የኦነግ ሸኔ አባላት ደግሞ ተማርከዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኦነግ ሸኔ አባላትና ሽፍቶች በተጨማሪ፣ 12 የኦነግ ሸኔ አባላት እና 8 ሽፍቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል፡፡ወንጀል ሲፈፀምባቸው የነበሩ ከ100 በላይ የጦር መሳሪያ እና 27 ሺህ የተለያዩ የጥይት አይነቶች ተይዘዋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ እንደሻው ብርሃኑ ለኦቢኤን እንደተናገሩት በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎችን ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ ስለመሆኑም አስረድተዋል፡፡

[OBN/FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያና የሶማሌ ትምህርት ቢሮ አመራሮች አፋን ኦሮሞ እና አፍ- ሶማሊ በሁለቱም ክልሎች ለማስተማር እየተወያዩ ነው!

የኦሮሚያና የሶማሌ ትምህርት ቢሮ አመራሮች አፋን ኦሮሞ እና አፍ- ሶማሊን በሁለቱም ክልሎች ለማስተማር የሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ውይይት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡የኦሮሞና የሶማሌ ህዝቦች አንድነት ይበልጥ ለማጠናር በትውልድ ላይ መሰራት ይገባል ተብሏል፡፡የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ የኦሮሞና የሶማሌ ህዝብ አንድ ህዝብ መሆኑን ገልጸው፣ የሁለቱን ህዝቦች አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር ትውልድ የሁለቱን ህዝቦች ቋንቋ እንዲማር ማድረግ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ ፈታህ መሐመድ የሁለቱን ህዝቦች አንድነት ለማጠናከር በሁለቱም ክልሎች አፍ- ሶማሊ እና አፋን ኦሮሞ ትምህርት መሰጠት እንዳለበት መግለጻቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፍሪካ ህብረት ልዑክ ጋር መወያየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዑኩን በጽህፈት ቤታቸው ነው ተቀብለው ያነጋገሩት፡፡ከልዑካኑ መካከል የቀድሞ የላይቤሪያ ፕሬዚዳን ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ፣ የቀድሞው የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ጆኣኪም ቺሳኖ፣ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኪጋሌማ ሞትላንቴ ናቸው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና የአፍሪካ ህብረት ልዑካን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዑኩ በአፍሪካዊ ወንድማማች መንፈስ የኢትዮጵያ ሁኔታ አሳስቦት መምጣቱን አድንቀዋል፡፡በውይይቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡እንዲሁም ለሁለት ዓመታት ያህል ህወሓት ሃገሪቷን ለማተራመስ የሄደበትን ርቀትና መንግስት ያሳየውን ያላሰለሰ ሆደ ሰፊነት ለልዑካኑ አስረድተዋል፡፡

Via FBC/PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️
ትህነግ ለውሸት ድምሰሳ 21ኛ ክ/ጦርን ለምን መረጠ?

በአበበ ሰማኝ (ከአዲ-ቀይህ) ህዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም

ከምስረታው ጀምሮ ምንም አይነት ሰብዓዊነት ያልፈጠረበት ትህነግ ለበርካታ አመታ የውሸት ካህን ሆኖ በህዝቦች ዘንድ መጠራጠርን፥ ኢትዮጵያን መካድን ለትውልድ አውርሶ በመቃብሩ ጫፍ ላይ ዛሬም እንደትናንቱ በተሰፋበት የሃሳዊነት አኮፋዳ ቱሪናፋውን ይለቃል።

ሰሞኑን የትህነግ የውሸት ቱቦ ማፍሰሻ ጌታቸው ረዳ በበቀቀኑ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርቦ ትርጉም በሌለውና ውጤት አልባ ሆኖ በትህነግ የፖለቲካ ሴራ በተሸረበው ነገር ግን ውስጡን ያላውቁት ቆራጥ የህዝብ ልጆች ለድንበራቸው መከበር ዋጋ በከፈሉበት የሻዕቢያ ጦርነት ታላቅ ገድል የፈፀመችው 21ኛ ክ/ጦር ሙሉ በሙሉ ደምስሰናታል ብሏል ።

ለመሆኑ ትህነግ ኢትዮጵያችን ካሏት ጀግና ክ/ጦሮች ውስጥ 21ኛን መርጦ ሙሉ በሙሉ ለምን ደመሰስኩ አለ?

21ኛ ጉና ክ/ጦር ከሃገራዊ ለውጡና ከሃገር ከሃዲዎች የመቀሌ መመሸግ ማግስት በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረውን አለመረጋጋት ወደቀደመ ሰላሙ ለመመለስ ከጫካ ውጭ ሌላ የትግል አማራጭ የማያውቀውን የትህነግ ታናሽ ወንድም ኦነግ ሸኔን እግር በእግር ተከታትላ አፈር ድሜ ያበላችና ለአካባቢው ህዝብ እፎይታን የሰጠች ጀግና ክ/ጦር ናት ።

ዛሬም መንግስት ህግን ለማስከበርና የዘመናት የህዝቦችን ጥያቄ በዘለቄታዊነት ለመፍታት ተገዶ በገባበት ጦርነት ውስጥ ትውልድ የሚሻገር ገድል በራያ ግንባር ተሰልፋ በመስራት ላይ ትገኛለች፥ ከቆቦ እስከ አዲቀይህ ያለውን 160 ኪሎመትር የሚረዝም ፈታኝ የመሬት ገፅ በኢትዮጵያዊነት ፍቅር በተማረኩት ጅግና ልጆቿ ታጅባ የጠላትን መቃብር ያፋጠነች እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ጀግና ክ/ጦር ነች። 21ኛ ጉና ክፍለ ጦር

ትህነግ ከድሃ ኢትዮጵያዊ ጉሮሮ ነጥቆ ለአመታት የደከመባቸውና ምናልባትም ለረጅም ጊዜ መከላከልን መሰረት አድርጎ የገነባቸው ኮንክሪት ምሽጎችን ለጠላት እንኳን ግርምትን በሚፈጥር ቅፅበት አመድ ሆነዋል።
መሬት ላይ ተቀብረው ለተኩስ አገልግሎት ሲውሉ የነበሩ በርካታ ታንኮች ወድመዋል፥ አካባቢው በጠላት አስክሬን ተሸፍኗል፥ የሚተማመንበት ኮንክሪት ምሽግ እንኳን ፊቱን አዙሮበታል ።

እርግጥ ትህነግ ከምስረታው ጀምሮ በሰው አምኖ አያውቅም በዘራፊው ቡድን ትርጓሜ ሰው ማለት የራሱን ጉዳይ የሚያስፈፅም በድን አካል ነው ከፍላጎቱ ውጭ ያለ ማንኛውም ፍጡር ከማውደም ወደኋል የማይል ጭራቅ ቡድን ነው። እናም ባላወቁትና በስልጣን ጥም ፍላጎት እየተገፉ የጥይት እራት ከሆኑት በርካታ ወጣቶች በተጨማሪ በከፍተኛ ውጪ የተገነቡና ለትግራይ ህዝብ ግልጋሎት የሚሰጡ ከፍተኛ የሃይል ማስተላለፊያ ፖሎች በዘራፊው ቡድን ከባድ መሳሪያዎች ወድመዋል ።

ይሄ ሁሉ ሲሆን ትህነግና የሽርፍራፊ አነፍናፊ ቡችላዎቹ አሁንም የሃሰት ካባቸውን ማውለቅ ተስኗቸዋል፥ ከከበባቸው ኢትዮጵያዊ እውነት ይልቅ የውስጥ ፍላጎታቸውን ይዘባርቃሉ። እናም ለዚሁ ውሸታቸው ማልበሻ ይሆን ዘንድ በጀግንነቷ ወደር የማይገኝላትን ክፍለ ጦር ደመሰስን ከሚል ህልማቸው ጋር ተጣብቅዋል።

የሆነው ሆኖ ክፍለ ጦሯ አስቸጋሪ ምሽጎችን በመስበር፥ በርካታ የጠላት ጦርን በማውደም ፥ ጠላት ሲጠቀምባቸው የነበር በርካታ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያወችን በመማረክ ከመቀሌ በ 40 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከነሙሉ ዝግጅቷና ኢትዮጵያዊ ደም በተቀባ ማንነት ተሞሽራ በተጠንቀቅ ትገኛለች ።

ለስንብት እንዲሆነኝ የክ/ጦሩ አባላትን ይህንን ብለዋል
ኮሎኔል ተክሉ ውሪሳ (21ኛ ክ/ጦር 3ኛብርጌድ አዛዥ)
" ትህነግ ነጭ ውሸት ተፈጥሮው ነው፥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እንኳን እስከ ህይወቱ ፍፃሜ ድረስ መዋሸቱን አያቆምም፥ ክፍለ ጦራችን በርካታ ጀግኖች ያሏት ለኢትዮጵያ ህዝቦች ክብር ራሳችን አሳልፈን ለመስጠት የተዘጋጀን ነን የህዝብ ልጆች ነን፥ ደመሰስናቸው ካሉን ሃይሊች ጋር በቅርብ ቀን መቀሌ ላይ እንገናኛለን፥ የጀግኖችን የሃይል ምት መቋቋም ያቃተው የከሃዲው ቡድን ሃይል በዛሬው እለት ብቻ ከ300 በላይ ላውንቸርና ብዛት ያላቸው ድሽቃዎችን ጥሎ ነው የፈረጠጠው" ብለዋል

ሻምበል ሲሳይ ተሾመ (21ኛ ክ/ጦር 3ኛብርጌድ 3ኛ ሻልቃ አዛዥ)
" ለትህነግ ውሸት አዲስ ነገር አይደለም መላ ኢትዮጵያውያንን ለበርካታ አመታት ሲዋሽና ሲዘርፍ የነበረ ቡድን ዛሬ የሽንፈቱ ማሳያዎች የሆኑ በርካታ ቀልድ መሰል ውዥንብሮችን በየቀኑ ይቀባጥራል፣ ይህ ደግሞ ለእርሱ የሞቱን መፍጠን ለእኛ ደግሞ የድላችን መድመቅ ማሳያ መስታውታችን ነው"

ምክትል አስር አለቃ ዋሲሁን አበበ (ተመላሽ የሰራዊት አባል)
" ቤት እያለሁ ብዙ ውዥንብሮች ይወራሉ እዚህ ስመጣ መሬት ላይ ያለው እውነት በጣም የተለየ ነው ይሰበራሉ ተብለው የማይታሰቡ ኮንክሮት ምሽጎች በማይታመን ጀግንነት ተሰብረዋል፥ በዘረፋ የተከማቹ በርካታ መሳሪያዎች ወድመዋል፣ ሰራዊቱ በከፍተኛ እልህና ወኔ በሃገር ፍቅር ስሜት ወደፊት ይገሰግሳል፣ ይሄን መቋቋም ያቃተው ከሃዲው ቡድን ከመዋሸት ውጪ አማራጭ እንዳይኖረው አድርገን ቀብረነዋል"

ምክትል አስር አለቃ ሃዊ ረጋሳ (ሃኪም)
" የተሸነፈ ብዙ ያወራል እኔ የ21ኛ ክፍለ ጦር ሃኪም ነኝ ከቀላል ቁስለኛ ውጪ ይህ ነው የሚባል ከባድ ጉዳት አላየሁም፣ ከየት አምጥተውት ደመሰስናቸው እንዳሉ አላቅም፣ ሰራዊቱ በከፍተኛ ጀግንነት ከጠላት አፍንጫ ስር ነው ያለው ጠላትን በቁጥጥር ስር አውለን ለህዝባችን እስከምናስረክብ ድረስ ፈጣን ጉዟችን አይገታም "

ምንጭ:- አበበ ሰማኝ የመከላከያ ጋዜጠኛ
@Yenetube @Fikerassefa
የግብጹ ፕሬዚዳንት ነገ ደቡብ ሱዳን ይገባሉ!

የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ነገ ጁባ እንደሚገቡ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ፕሬዚዳንት ሳል ቫኪር ማያርዲት ነገ በጁባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለግብጹ አቻቸው አቀባበል እንደሚያደርጉ የገለጸው ጽ/ቤቱ ሕዝቡም በቦታው ተገኝቶ አቀባበል እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡ሁለቱ መሪዎች የምሳ ፕሮግራም እንደሚኖራቸው የተገለጸ ሲሆን በጁባና ካይሮ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡ከዚህ ባለፈም በቀጣው የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚደርጉም የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በሱሉልታ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በኦሮሚያ ክልል የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ሱሉልታ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ።የትራፊክ አደጋው በዛሬው እለት ከቀኑ 8 ሰዓት ገደማ ላይ መድረሱን ከሱሉልታ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከደብረ ማርቆስ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ከአዲስ አበባ ወደ አሊ ዶሮ ሲጓዝ ከነበረ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የደረሰው።በአደጋውም እስካሁን የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና ሌሎች ተሳፋሪዎች ላይ ደግሞ ከከባድ እስከ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱም ታውቋል።

[Fana]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የገጽ ለገጽ ትምህርት ህዳር 21 እንደሚጀመር ተገለጸ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገጽ ለገጽ ትምህርት ህዳር 21 እና 28 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር የመዲናዋ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።ቢሮው በግል ትምህርት ቤቶቸ ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ ህዳር 21 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር ከከተማ አስተዳደሩ ከትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።እንዲሁም በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ህዳር 28 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር ትምህርት ቢሮው ገልጿል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አዲሱ ሻንቆ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ህዳር 24 እና 25 እንደሚሰጥም አክለው ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
Today is the last day of Virtual Agrofood & Plastprintpack Africa 2020. It has indeed become a truly global event with a clear Africa focus. Considering that the event includes not only the core period from 23 - 26 November, but also a bonus period until 03 December, one can well imagine that the event will become a great success.

Only on the first day:
No fewer than 904 attendees have already become active users, out of the 2,001 meanwhile registered from 81 countries. The attendees networked with each other and of course with the

64 exhibitors from 17 countries participating
4,522 messages were exchanged
444 attendees attended the conference sessions
a total of 2,022 contacts were made
444 participants attended the panel sessions, presentations and product demos
The opening talk on how exhibitors, attendees & speakers can best benefit from the event was followed by 172 participants

You can still be part of this trade fair Today! Register now as an attendee here;, it's free of charge
በማይካድራ ተጨማሪ የጅምላ መቃብሮች ተገኙ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጥናት አድርጎ ከተመለሠ በኃላ ከማይካድራ ከተማ ወጣ ባሉ የገጠር አካባቢዎች በርካታ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ጋዜጠኞች በቦታው በመገኘት አረጋግጠዋል።በአንድ ቦታ 18 ሰው በጉድጓድ ውስጥ በጅምላ የተጣሉ ሲሆን በሌላ የገጠር አካባቢ ደግሞ 57 ሰዎች በጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ውስጥ በጅምላ ተገድለው እና ተጥለው ተገኝተዋል።በዛሬው ዕለትም በማይካድራ ሌላ የገጠር ቀበሌ ውስጥ 17 ሰዎች በጅምላ ተገድለው በጉድጓድ ውስጥ ተጥለው ተገኝተዋል።አሁንም ሴንትራል፣ ደሮ እርባታ፣ በረኸት በሚባሉ አካባቢዎች ላይ አሠሳ እየተደረገ እንደሚገኝ እና ቁጥሩ እንደሚጨምር የማይካድራ ነዋሪዎች ገልጸዋል።በዚህ የ'ዘር ማጥፋት' ወንጀል ተሳታፊ ናቸው የሚባሉት ተጠርጣሪዎች በብዛት ሱዳን ሐሻባ በሚባል የስደተኞች መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ ይነገራል።ከዚህ በተጨማሪ በማይካድራ የ'ዘር ማጥፋት' ወንጀል ላይ ተሳታፊ ናቸው በሚል ተጠርጥረው ከተያዙት 60 ግለሠቦች ውስጥ 17ቱ በቀጥታ የወንጀሉ ተሳታፊ መሆናቸውን የማይካድራ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ገልጿል።

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ወሳኝ የሚባሉ ቦታዎች በመከላከያ ሰራዊት ነፃ መውጣታቸውን የገለፁት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ሕግ የማስከበር ወታደራዊ ዘመቻው በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቅ ገለፁ፡፡

ከፍራንስ 24 ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉት ሚኒስትሩ ዘመቻው ከአንድ ሳምንት ባጠሩ ቀናት ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ተስፋ መደረጉን ነው የጠቀሱት፡፡ንፁሃን እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ እየተደረገ ነው ያሉት አህመድ ሽዴ አሁን ላይ ዘመቻው በመቐለ እና ዙሪያዋ ባለ ጠባብ ቦታ የሚከወን መሆኑን አስተድተዋል፡፡ በሌሎቹና ከሕወሓት ነፃ በሆኑ ቦታዎች የሰብኣዊ አገልግሎቶች እንዲደርሱ ክፍት መደረጉንም አንስተዋል፡፡

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
በራያ ግንባር የተሰለፈው ሰራዊት መቀሌን ለመቆጣጠር 2 ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

አበበ ሰማኝ (ከሄዋኔ) ህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም

በራያ ግንባር ተሰልፎ አስቸጋሪ የመሬት ገፆችን በማለፍ የድል ባለቤት የሆነው መከላከያ ሰራዊት ከ2 ቀናት በኋላ መቀሌ ከተማን እንደሚቆጣጠር የግንባሪ መሪ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደብሌ ተናገሩ።

በራያ ግንባር ተሰልፎ የጠላትን አከርካሪ በመስበር ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት በአንድ ብኩል ከጨርጨር እስከ መሆኒ በሌላ በኩል ደግሞ ከቆቦ አለማጣ ኩኩፍቱ እና መሆኒ በማድረግ ግዳጁን በሁለት አበይት አቅጣጫዎች ሲፈፅም ቆይቷል።

ምንም እንኳን የገጠምነው ሃይል የጎበዝ አለቃ ወታደር ቢሆንም አካባቢው ካለው ተራራማ የመሬት ገፅ አንፃር ያሉ ፈታኝ ሁኔታዎችን አልፈን የሚከፈለውን መስዋዕትነት በመክፈል በአሁኑ ሰዓት ከመቀሌ በ30 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ሄዋኔ ከተማን ተቆጣጥረናል ብለዋል።

በቀጣይ ግዳጅ ላይ የምንሰራቸው ማይ ነብሪ እና አዲ ጉዶም የተባሉ ከተማዎችን መቆጣጠር ነው ያሉት ጀነራል ባጫ እነዚህን ተልዕኮዎች በሚገባ በመፈፀም በቀጣይ 2 ቀናት ውስጥ መቀሌ ከተማን እንቆጣጠራልን ሲሉ ተናግረዋል።

ሜጀር ጀነራል አለምእሸት ደግፌ በበኩላቸው ጁንታው ቡድን ለረጅም ጊዜ እዋጋበታለሁ ብሎ የገነባቸው ኮንክሪት ምሽጎች ከ3 ቀናት መራራ ውጊያ በኋላ ሲደመሰሱ ካለአማራጭ ቦታውን ልቆ እንዲሸሽ ተደርጓል ብለዋል።

የመከላከያ ሃይሉ የከባድ መሳሪያ ምድብተኞች በተመረጡና ኢላማቸውን በጠበቁ ተኩሶች የጠላትን የማድረግ አቅም ማዳከም ተችሏል ያሉት ጀነራል አለምሸት በዚህም የጁንታው ቡድን ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ወደ አዲጉዶም ሸሽቷል ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአገር መከላከያ ሠራዊት ሀውዜን፣ አል ነጃሺ፣ አዲ ቀይህ፣ ማይመሳኖንና ውቅሮን ከጁንታው ታጣቂ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ

የአገር መከላከያ ሠራዊት ሠራዊቱ መቀሌን እና የወንጀለኛው ጁንታ ቡድን አባላትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስትራቴጂክ ቦታዎች መያዙን አስታወቀ።

ሠራዊቱ ሀውዜን፣ አል ነጃሺ፣ አዲ ቀይህ፣ ማይመሳኖንና ውቅሮን ከጁንታው ታጣቂ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።

የትግራይ ሕዝብ ከመጀመሪያው ዕለት አንሥቶ ለመከላከያ ሠራዊት ወገንተኝነቱን አሳይቷል።

የሕወሓት ጁንታ በሰላም እጁን እንዲሰጥ መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓታት ጊዜ ሊጠቀም ባለመቻሉ ከትናንት ጀምሮ የሕግ ማስከበር ስራው ቀጥሏል።

በመከላከያ ሠራዊት ኅብረት ሥልጠና ዋና መምሪያ ሓላፊ ሌተናል ጄኔራል ሐሰን ኢብራሂም በሰጡት መግለጫ፣ የሕግ ማስከበር ሂደት በውጤታማነት ቀጥሎ ተጨማሪ የትግራይ ክልል ከተሞችን ከጁንታው ታጣቂ ነፃ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በዚህም በአድዋ ግንባር የተንቀሳቀሰው ሠራዊት ሃውዜን፣ አብርሃ ወአጽብሃንና ውቅሮን የተቆጣጠረ ሲሆን፣ አጉላን ደግሞ በግማሽ ቀን መቆጣጠሩን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም በመቀሌ አቅራቢያ ወደሚገኘው መሰቦ ተራራ እየገሰገሰ ሲሆን፣ ይህም መቀሌን በጥቂት ቀናት ውስጥ ለመቆጣጠር እንደሚያስችል ጠቁመዋል።

በሁለተኛው ግንባርም በአዲግራት በኩል ሳንቀጣ እና አልነጃሺን በመቆጣጠር ውቅሮ ገብቷል።

በሦስተኛው የራያ ግንባር ደግሞ አዲቀይህን የተቆጣጠረ ሲሆን፣ ሄዋናን በመቆጣጠር ሁሉንም ምሽጎች ሰባብሮ ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል።

በመቀሌ ያለውን የወንጀለኛ ቡድን የመቆጣጠር ተግባር በማጠቃላይ ምዕራፍነት የተያዘ ሲሆን፣ ሠራዊቱ ግዳጁን በምን አኳኋን መፈጸም እንዳለበት በቂ ዝግጅት አድርጎ የወንጀለኛውን ቡድን በቁጥጥር ስር ለማዋል መዘጋጀቱን አመልክተዋል።

የትግራይ ሕዝብ ሠራዊቱ የጁንታውን አባላት ለመያዝ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ወገንተኝነት ከማሳየቱም በላይ፣ በሠራዊቱም ላይ ጥይት አለመተኮሱ የትግራይ ሕዝብ እና ጁንታው የተለያዩ መሆናቸውን አረጋግጧል።

የጁንታው ቡድንም በፕሮፓጋንዳ ጭምር እያፈገፈገ መሄዱ ሽንፈቱን እያረጋገጠ መሆኑን አመልክተዋል።

በማጠቃለያው ምእራፍ መቀሌን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስትራቴጂክ ቦታዎች መያዙን አስታወቀ።

በራያ በኩልም አድ ቀይህ፣ አዲመሳኖን እና ሄዋናን ከታጣቂ ኃይሉ መቆጣጠሩን ገልጸዋል።

በጉላን በኩል መንገድ ለመዝጋት ቢሞክርም፣ እንዳልተሳካለት እና ወደኋላ ማፈገፈጉን ተናግረዋል።

አሁን ላይ መቀሌ ብቻ መቅረቱን የገለጹት ሌተናል ጀነራል ሐሰን በጥቂት ቀናት ወስጥ ተጠናቆ ጁንታው ለሕግ እንደሚቀርብ አረጋግጠዋል።

የጁንታው ኃይል በራያ በኩል ያለ የሌለ ኃይሉን በመጠቀም የሠራዊቱን ጥቃት ለመቋቋም ቢሞክርም በመመታቱ ለመልቀቅ ተገዷል ነው ያሉት።

የሕወሓት ጁንታ ሽንፈቱን እያረጋገጠ በመምጣቱ በሐሰት ወሬ ላይ ተጠምዶ ሕዝብን በማደናገር ላይ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
በራያ ግንባር እየተወሰደ ያለው ሕግ የማስከበር እርምጃ ውጤታማ ነው - ሌተና ጄነራል ባጫ ደበሌ

የራያ ግንባር አዛዥ ሌተና ጄነራል ባጫ ደበሌ በራያ ግንባር እየተወሰደ ያለው ሕግ የማስከበር እርምጃ ውጤታማ መሆኑን ገለጹ።

ሌተና ጄነራል ባጫ በሰጡት መግለጫ በግንባሩ የሚገኘው መልክዓ ምድር ፈታኝ እንደነበር ተናግረዋል።

ጄነራሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሠራዊቱ መቀሌ እንደሚገባም አመልክተዋል።

የሠራዊቱ ወቅታዊ ዝግጁነት እና የግዳጅ አፈጻጸም የላቀ መሆኑንም ሌተና ጄነራል ባጫ ጠቅሰዋል።

የራያ ግንባር የከባድ መሣሪያዎች አስተባባሪ ሜጀር ጄነራል ዓለምእሸት ደግፌ በበኩላቸው፣ ሠራዊቱ ታጣቂ ቡድኑን ከሲቪል ነጥሎ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።

ሠራዊቱ ከባድ መሣሪያዎችን በማቀናጀት በአካባቢው በነበረው የትሕነግ ታጣቂ ቡድን ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱንም ጠቁመዋል።

Via:- EBC
ፎቶ:- በሻምበል ብርሃኑ ወርቁ
@YeneTube @Fikerassefa
አየር ኃይል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለተለያየ የስራ ጉዳዮች በትግራይ ክልል የሚገኙ ሰራተኞችን ወደ የአካባቢያቸው የማመላለስ ስራ መጀመሩን አሳወቀ።

@Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ ማምሻውን ከትግራይ የተወነጨፉ በርከት ያሉ ሮኬቶች አስመራን እንደመቱ ኤርትሪያን ፕሬስ በፌስቡክ ገፁ ፅፏል ።

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)
በርካታ ሮኬቶችን ወደ ተለያዩ የኤርትራ ከተሞች ማስወንጨፉ ተሰማ።

ለ2ኛ ጊዜ የተፈጸመውን ይህን የህወሓት ድርጊት ኤርትራ ፕሬስን ጨምሮ ሌሎች ሚዲያዎች ዘግበውታል።

ህወሓት ጦርነቱን ዓለማቀፋዊ ይዘት ለማላበስ የመጨረሻውን ሙከራ አድርጓል ያለው
ኤርትራ ፕሬስ ወደ አስመራ የተተኮሱት ሮኬቶች በተጨናነቁ የመኖሪያ አካባቢዎች አቅራቢያ ቢያርፉም ያደረሱት አንዳች ጉዳት እንደሌለ አረጋግጫለሁ ብሏል።

ህወሓት ከአሁን ቀደምም ወደ አስመራ ሮኬት ማስወንጨፉ የሚታወስ ነው።

ሆኖም ያደረሰው ጉዳት አልነበረም ብላል።
የኤርትራ መንግስትም ያለው ነገር አልነበረም በወቅቱ።

@Yenetube @FikerAssefa
Forwarded from ABENI★ Fab
videotogif_2020.11.17_05.08.23.gif
1.2 MB
📌አሜሪካ ሰራሹ ተአምረኛው ትሪትመንት አገራችን ገባ በ ቀናት ውስጥ ከ መላጣነት ወደ ማበጠሪያ ተጠቃሚነት ይዞራሉ👉🏼 አላድግም ብሎ ለቀረ
👉🏼 ራሰ በርሃ ለሆነ
👉🏼 ወደራሰ በርሃነት የተጠጋ  ለሳሳ ፀጉር
👉🏼 ወደውስተጥ ለገባ ፀጉር
👉🏼 ፐረም ወይም ጄል ለጨረሰው ፀጉር
👉🏼ላሽ ለበላው #ፂም #ፀጉር
100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ 🔽USA🇺🇸 አሁኑኑ ያናግሩን ☞@Brandlife1
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮችየቀረቡ የዉፍረት መቀነሻ ቀበቶዎች, [Human hair ] {Wireless Wifi router}+ለ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ገንቢ የሆኑ ፕሮቲኖች (protein shake), በተለያየ ምክንያት ለመጣ ጠባሳ ማጥፊያ የሚሆኑ ትሪትመንቶችን ከኛ ያገኛሉ፡፡➡️ ☎️+251991203033
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g
Forwarded from YeneTube
#የጥፋት_አርበኞች
#አዲስ_መጽሐፍ_በገበያ_ላይ

አንዳንድ ሀገሮች የመፈራረስ ዕጣ ፈንታ የገጠማቸው በጥፋት አርበኞች የጀብደኝነት ተግባር እንደሆነ ያውቃሉ? እኛስ እያጋጠመን ያለው ይሄው እጣፈንታ ይሆን?

የጥፋት አርበኞች የሚንቀሳቀሱት ከንቃተ ህሊናቸውን ጋር በተፋቱ ስሜቶቻቸውና በተሳሳቱ እምነቶች እንጂ በምክንያት አይደለም! መመሪያቸው አረመኔያዊነት፣ ተግባራቸውም እንሰሳዊነት ነው ይላል፡፡ #የጥፋት_አርበኞች_ልክ_የበሰበሰ_ሬሳ_ላይ_እንደሚራኮቱ_ምስጦች_የሚተባበበሩት_ለጥፋት_ነው፡፡

#ይሄ_መፅሐፍ_ደግሞ_ብዙ_ የጥፋት_ሚስጥራቸውን_ይገልጥልናል፡፡

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።

ይቀላቀሉን 👉http://tttttt.me/teklutilahun