YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኅዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ዓመት ሙሌት እና ዓመታዊ የውሃ አለቃቅ ላይ የተጀመረውን የሦስትዮሽ ድርድር ማስቀጠል አስፈላጊነት ላይ ስምምነት ቢደረስም፤ ሱዳን የድርድር ሂደቱ ካልተቀየረ አልሳተፍም ማለቷ ተሰማ፡፡

የሶስቱ አገራት የውሃና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ኅዳር 10 በበይነ መረብ ድርድር አድርገዋል፡፡የአፍሪካ ኅብረት አስፈፃሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ለመሪዎች ሊቀርብ የሚችል ውጤት ሊመዘገብ ይገባል ሲሉ አሳስበው ስብሰባውን ዘግተውታል፡፡

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንግሥት በዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም ላይ ቅሬታ እንዳለው ገለጸ!

የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተሩ ቴድሮስ አድሐኖምን በተመለከተ ቅሬታ እንዳለውና ደስተኛ አለመሆኑን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ዶክተር ቴድሮስ በአገሪቱ ውስጥ ምን እንደተከሰተ ከመንግሥት በኩል ለመረዳት አለመሞከራቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ዶ/ር ቴድሮስ "አንዳንድ በሮችን ማንኳኳታቸውን" መንግሥት እንደሚያውቅ አመልክተው ይህንንመ በተመለከተ መንግሥት በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለበት ይወስናል ሲሉ ተናግረዋል።በተያያዘም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክትር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግጭት ውስጥ የሚገኘው ህወሓትን የሚደግፍ የማግባባት ሥራ አከናውነዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ በትናንትናው እለት ተናግረው ነበር።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ የጦር አውሮፕላን ዛሬ በመቀሌ ከተማ የቦንብ ድብደባ እንደፈጸመ የትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል። ድብደባው የተፈጸመው በመቀሌ ዩኒቨርስቲ መለስ ካምፓስ አካባቢ ነው ብሏል ዜናው። በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ግን ዜናው ያለው ነገር የለም።

@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል መንግስት ህወሃት ላይ እየወሰደ ላለው የውጊያ አማራጭ ተጠያቂው እራሱ ህወሓት መሆኑን አቶ አባዱላ ገመዳ፡፡

ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በተለያዩ የሃገሪቱ ከፍተኛ የስልጣን እርከኖች ላይ ሲሰሩ የነበሩት አቶ አባዱላ ገመዳ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ በፌዴራሉ እና ትግራይ ክልልን በሚያስተዳድረው "ህወሓት" መካከል የነበሩ የሃሳብ ልዩነቶች ጦር ለመማዘዝም የማያበቁ እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡ 

ይሁንና ከብልጽግና ፓርቲ ምስረታ በኋላ "የሁለቱ ወገኖች ልዩነት የመጥበብ አዝማሚያን አላሳየም" ያሉት አባዱላ በተለይም ህወሓት "በፌዴራሉ መንግስትና በህገ መንግስቱም ጭምር እውቅና የተነፈገ" ካሉት የትግራዩ ምርጫ በኋላ ግን ነገሮች ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ማምራታቸውን እና የድርድር መስመርን ያጠበቡ ብለውታል፡፡ 

በህወሓት ባለስልጣንም ጭምር ተረጋግጧል ያሉት የሰሜን ዕዝ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የተወሰደው ያልታሰበ ያሉት ጥቃት ደግሞ "የፌዴራሉ መንግስት ተገዶ ወደ ጦርነት ለመግባቱ ማሳያ ነው" ያሉት አቶ አባዱላ አሁን ሊደርስ የሚችለውን ቀውስ የሚያሳንሰው የጦርነቱን ጊዜ ማሳጠር ብቻ ነው ሲሉም አክለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በትግራይ ክልል የባንክ አካውንታቸው የታገደባቸውን ኤጀንሲዎች አስመልክቶ መረጃ ሰጥቷል። በዚህም መሠረት ንብረታቸው እና የባንክ አካውንታቸው የታገደባቸው ኤጀንሲዎች የህወሓት የንግድ እና የወንጀል ግዛት አካል የሆኑት ብቻ መሆናቸውን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ ትግራይ መዲና መቀሌ እየደረሰ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥትን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘገበ።በትግራይ የሕወሓትን ቡድን ወደ ሕግ ለማቅረብ በሚል የጀመረዉ ጦርነት ሁለት ሳምንት እንደሞላዉ የዜና ወኪል ሮይተርስ ጨምሮ ዘግቦአል። በጠቅላይ ሚኒስትር የተቋቋመዉ የትግራይ ግጭትን የሚከታተለዉ ግብረ ኃይል የትግራዩን ጦርነት ሸሽተዉ ወደ ወደ ሱዳን የሸሹ ዜጎችን ለመመለስ እቅድ መያዙን ሮይተርስ ን ዘቅሶ ዘግቦአል። ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ የሰብዓዊ ቀዉስ መርጃ የሚሆን ቁሳቁሶችን ለመላክ የልዑካን ቡድን ወደ ስፍራዉ ማቅናቱ ተመልክቶአል።

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ከሚገኘው ጦርነት ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ስማቸው ሲነሳ የቆየው ዶ/ር #ቴድሮስ_አድሃኖም የሚከተለውን መልእክት አስተላለፉ።

@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ከሚገኘው ጦርነት ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ስማቸው ሲነሳ የቆየው ዶ/ር #ቴድሮስ_አድሃኖም የሚከተለውን መልእክት አስተላለፉ። @Yenetube @Fikerassefa
ወደ አማርኛ #ሲተረገም

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የቀረበባቸውን ውንጀላ አስተባበሉ።

የዓለም ጤና ድርጀት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በቲዊተር ገጻቸው ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት በሃገራቸው ኢትዮጵያ በተከተለው ሞት እና መፈናቀል ማዘናቸውን ገልጸው ፣ሁሉም ወገኖች ለሰላም እና ለሲቪሎች ደህንነት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

ከሕወሃት ጋር አብረዋል በሚል የቀረበባቸውን ውንጀላም አስተባብለዋል፣በአጋርነት የምቆመው ከአንድ ነገር ጋር ብቻ ነው እሱም ሰላም ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
'የህወሓት ቡድን' ዛሬ ሌሊት 7፡40 አካባቢ ወደ ባህር ዳር የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን አብመድ ገልጿል።በተፈፀመው ጥቃት የደረሰ ጉዳትም የለም ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ በህወሓት በኩል የሽምግልና ፍላጎት እንደሌለ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ!

በትግራይ ያለው ውጊያ በንግግር እንዲፈታ በቀጠና፣ አህጉር እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ መሪዎች የማሸማገል ጥያቄ ቢያቀርቡም፤ በኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ በህወሓት በኩል የሽምግልና ፍላጎት እንደሌለ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ተናገሩ። የህወሓት አመራሮች ውጊያውን ሲጀምሩ የተከተሉት ታክቲክ፤ “ካቀዱት ተቃራኒውን ውጤት አምጥቷል” ብለው እንደሚያምኑም ገልጸዋል።

በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት ቲቦር ናዥ ይህን የተናገሩት በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ትላንት ሐሙስ ምሽት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው የጥያቄ እና መልስ ቆይታ ነው። በስልክ ኮንፈረንስ አማካኝነት በተካሄደው እና “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በቀጥታ በተከታተለችው የጋዜጠኞች የገለጻ መርሃ ግብር ላይ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ማይክል ራይነርም ተሳትፈዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
ትናንት ሌሊት በባህርዳር ከተማ የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን የአየር ሀይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ አረጋግጠው፣ "ወደ ህዝብ ነበር የተተኮሰው ነገር ግን ጉዳት ሳይደርስ ጫካ ውስጥ ነው የወደቀው፣ እኛም አፀፋዊ ምላሽ የምንወስድ ይሆናል" ሲሉ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ይህን በተመለከተ የስጡት ሙሉ ማብራርያ ከላይ በድምፅ ተያይዟል።

@YeneTube @FikerAssefa
ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሚዲያዎች ጋር ውይይት እያደረገ ነው!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀም እና ድልድል ረቂቅ መመሪያ ላይ ከመገናኛ ብዙኃን እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ መገናኛ ብዙኃን ለሁሉም እኩል የመወዳደሪያ ሜዳ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
የህወሃት ንብረትነቱ የመከላከያ ሰራዊት ባልሆነ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ተፈጽሞብኛል የሚለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ የአየር ሀይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለፁ።

ሜጀር ጀኔራል ይልማ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ የጠላት ኢላማዎችን ያለምንም ርህራሄ እንዳልነበር ማድረግ ለሰራዊቱ ማነቆ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን በማፍረስ መንገዱን ቀና የማድረግ ተግባርም ይከውናልም ነው ያሉት፡፡

በመቐለ አቅራቢያ ኪያ እና አዲግራት ጭምር የነበሩ የነዳጅ ዴፖዎችም በ'ጁንታው' ቡድን ጥቅም ላይ ሳይውሉ መውደማቸውንም ተናግረዋል፡፡እስካሁን የተዋጣላት ሀገርንም ያኮራ ስራ እና እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፥ በዚህ ሁሉ ውስጥ ህገ ወጡ ቡድን የአየር ድብደባው ንጹሃንን እና የተለያዩ የእምነት ተቋማትን እንዲሁም የህዝብ መገልገያ ፕሮጀክቶችን ኢላማ ስለማድረጉ ክስ ያቀርባል።የአየር ሀይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፥ ውንጀላው ከእውነት የራቀ መሆኑን እና ይህ የቡድኑ የኖረ የውሸት እና የውንብድና ትርክቶች መሆናቸውን አውስተዋል።

የጦር አውሮፕላን መትተን ጥለናል የሚለው የህገ ወጡ ቡድን ወሬም ቢሆን የበሬ ወለደ እንጂ የአቅም እና የመሳሪያ ሁኔታው አልፈቀደለትም ይላሉ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ።የትግራይ ወንድም እና እህቶችን ህይወት እና ሀብት ባላስገበረ መልኩ የተለዩ ኢላማዎችን የማጥቃት እርምጃው እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።“ይህን ስናደርግ ደግሞ በራሳችን በገነባነው የቴክኖሎጂ ልክ እንጂ የማንንም እርዳታ እና ድጋፍ አንጠይቅም” ብለዋል ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሚዲያዎች ጋር ውይይት እያደረገ ነው! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀም እና ድልድል ረቂቅ መመሪያ ላይ ከመገናኛ ብዙኃን እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ መገናኛ ብዙኃን ለሁሉም እኩል የመወዳደሪያ ሜዳ እንዲሆኑ…
የፖለቲካ ፓርቲዎች ከጠቅላላ የአየር ሰዓት እና አምድ እኩል የሚከፋፈሉበት ቀመር

👉ለምርጫ የሚወዳደሩ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከተመደበው ጠቅላላ የመገናኛ ብዙኃን የአየር ጊዜ እንዲሁም የጋዜጣ አምድ ውስጥ 25 በመቶ የሚሆነውን እኩል ይከፋፈላሉ።

👉ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚወዳደሩበት የፌደራል ወይም ክልል ምክር ቤቶች በሚያቀርቡት እጩ ብዛት መሰረት ከጠቅላላው የአየር ጊዜ ወይም የጋዜጣ አምድ ውስጥ 40 በመቶ ይከፋፈላሉ።

👉ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤቶች ባቀረቧቻው የሴት እጩ ተወዳዳሪዎች ብዛት መሰረት ከጠቅላላው የአየር ጊዜ እና የጋዜጣ አምድ 20 በመቶ ይከፋፈላሉ።

👉የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚያቀርቧቸው የአካል ጉዳተኞች ብዛት መሰረት ከጠቅላላው የአየር ሰዓት ወይም የጋዜጣ አምድ ውስጥ 10 በመቶ ይከፋፈላሉ።

👉በስራ ላይ ባሉት የህዝብ ተወካዮች እና ክልል ምክር ቤት ባላቸው መቀመጫ ብዛት መሰረት ከጠቅላላው ምርጫ የአየር ጊዜ እንዲሁም የጋዜጣ አምድ 5 በመቶ እንደ መቀመጫ ብዛታቸው ይከፋፈላል።ሲል የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ጋር በጋራ ባወጣው ጠቅላላ ድንጋጌ ላይ አስታውቋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ከትግራይ ክልል ወደ ሱዳን በገቡ ኢትዮጵያውያን ዙሪያ የኢትዮጵያ መንግስት ከሱዳን መንግስት ጋር በሁሉም መስክ ተባብሮ እየሰራ ነው ሲሉ በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ተናገሩ።

በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ከስካይ ኒውስ የአረብኛ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቃለ ምልልስ ባደረጉበት ወቅት መንግስት በትግራይ ክልል የጀመረው ሕግ የማስከበር እርምጃ ጥቂት ወንጀለኞችን ለህግ ለማቀረብ የሚደረግ ዘመቻ ነው ብለዋል።ይህም ማንኛዉም መንግስት የሚያደርገዉ እንደሆነ የገለፁት አምባሳደሩ ማንም መንግስት ህግ እየተጣሰ ቁጭ ብሎ የሚያይበት ሁኔታ እንደሌለ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ በሚገኘው እርምጃ ምክንያት ችግሩ አካባቢያዊ ሊሆን የሚችልበት እድል የለምም ብለዋል።በህግ ማስከበር ሂደት ከቀያቸዉ ተፈናቀለው ወደ ሱዳን የገቡ ኢትዮጵያውያን በተለይም የምዕራቡ ትግራይ ክፍል ሙሉ በሙሉ ሰላም የተረጋገጠ በመሆኑ በቅርቡ ወደ ቀያቸው እንደሚመለሱ አረጋግጠዋል።ከዚህ ጋር በተያየዘ ከሱዳን መንግስት ጋር በሁሉም መስከ በትብብር እየሰሩ መሆኑንም አምባሳደሩ አስገንዝበዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር እንደተያያዘ በተገመተ ምክንያት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን አባረረች፡፡

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮቤል ናቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን አህመድ ኢሴ አዋድን ከሥልጣን ያነሱት፡፡ተባራሪው ሚኒስትር አገራቸው በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ጉዳይ አቋም አልያዘችም መግለጫም አላወጣችም ሲሉ በፃፉ ሰዓታት ልዩነት ከሥልጣናቸው ተነስተዋል፡፡የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለኢትዮጵያ አንድነት ድጋፍ እናደርጋለን ሲል መግለጫ ቢያወጣም፤ ሚኒስትሩ አገሪቱ ይፋዊ መግለጫ አላወጣችም ሲሉ በቲውተር ገፃቸው መፃፋቸው ለመባረራቸው ምክንያት መሆኑ ነው የተገመተው፡፡ሚኒስቴሩ ግን ሶማሊያ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አስተዳደር ለሕገ መንግሥታዊ ማዕቀፎች እና የአገሪቱ ሉኣላዊነት መከበር ከሚወስዳቸው እርምጃዎች ጎን መሆኗን ያረጋግጣል፡፡

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ ዐቃቤ ህግ ያቀረበው ሁለተኛው ክስ እንዲሻሻል ፍርድቤቱ አዘዘ፡፡

አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ሁለተኛው ህገመንግስቱን ለማፍረስ በማሰብ የሽግግር ሰነድ ማዘጋጀት ወንጀል የቀረበባቸው ክስ ነው እንዲሻሻል የታዘዘው።የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ወንጀል ችሎት በባለፈው ቀጠሮው ክሱ ላይ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠትና አቶ ልደቱ ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ተለዋጭ ሰጥቶ ነበር፡፡በዚህ ቀጠሮ መሰረት ፍርድ ቤቱ ዛሬ ዐቃቤ ህግ ያቀረበው ክስ አንቀጽና ዝርዝሩ አይጣጣምም ሲል ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ አዟል።አቶ ልደቱ የጠየቁት ዋስትና ጥያቄን ክሱ ተሻሻሎ ሲመጣ ለመመልከትና ብይን ለመስጠት ለህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል ሰጥቶት የነበረውን የዘገባ ፈቃድ ሰረዘ፡፡

ባለስልጣኑ በሃገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ “በተሳሳተ መንገድ ዓለም እንዲያውቀው እና በመንግስት ላይ ጫና እንዲበረታ በሚያደርጉ” ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡እርምጃውን በማስመልከት ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 መረጃን የሰጡት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዷለም መቀመጫቸውን አዲስ አበባ በማድረግ ፈቃድ የተሰጣቸው የውጭ ሃገር የሚዲያ ተቋማት ወቅታዊውን ሁኔታ በጥንቃቄ እና ሙያዊ ስነ ምግባርን በተከተለ መንገድ እንዲዘግቡ ማሳሰቢያ ሰጥተናል ብለዋል፡፡

ሆኖም ማሳሰቢያውን ችላ በማለት “በእምቢተኝነት በቀጠሉት ላይ እርምጃ ወስደናል” ብለዋል ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡ዶቼ ቬለ፣ ቢቢሲ እና ሮይተርስ ባለስልጣኑ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እስከ መጻፍ የደረሰባቸው የውጭ የሚዲያ ተቋማት ናቸው፡፡“ሮይተርስ ከትናንትና ወዲህ ባለው ሃገር ውስጥ ያለችው ዘጋቢ በምንም ዓይነት መልኩ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እንቅስቃሴ እንዳታደርግ እና ዘገባዎችን ዜናዎችንም እንዳትሰራ ሙሉ በሙሉ አግደናታል” ሲሉም አቶ ወንድወሰን የሮይተርስን መታገድ ተናግረዋል።“ወደ አንድ ወገን ያጋደሉ ስራዎችን በሚሰሩ ሌሎች ተቋማት ላይ ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ” እርምጃ መውሰዳችን ይቀጥላልም ነው ያሉት፡፡ባለስልጣኑ ለሃገር ውስጥም ሆነ ለውጭ የሚዲያ ተቋማት ወኪል ዘገባዎች ፈቃድ ሰጪ አካል መሆኑ ይታወቃል፡፡

[Sheger/Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የሀዋሳ ከተማ የራሷ መገለጫ የሆነ ምልክትን (Logo) አጸደቀች።

የሀዋሳ ከተማ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት አለም አቀፉን መስፈርት ታሳቢ በማድረግ ከተማዋ የራሷን ምልክት ይፋ አድርጋለች ብለዋል።

አዲሱ ምልክት የሀዋሳን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ተፈጥሯዊ እና የሰው ሰራሽ ሀብቶቿን ታሳቢ ያደረገ ነውም ብለዋል።

ምልክቱ በሚቀጥሉት ጊዜያት በሁሉም የአስተዳደሩ እርከኖች ማናቸውም ከተማዋን በሚመለከቱ ተግባራት ተፈጻሚ ይሆናል ስለመባሉ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቻለው ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢንተርናሽናል ክራይስ ግሩፕ ተንታኝ ዊሊያም ዴቪሰን የስራ ፍቃድ ታገደ!

የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የኢንተርናሽናል ክራይስ ግሩፕ ሲኒየር ተንታኝ የሆነውን ዊሊያም ዴቪሰን የስራ ፍቃድ ማገዱን አዲስ ዘይቤ አረጋግጫለው ብላለች፡፡ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዛሬ በፃፈው ደብዳቤ ግለሰቡ በኢትዮጵያ እንዲሰራ ከተፈቀደለት ስራ ውጭ በሌላ ስራ ላይ ስለመሰማራቱ መረጃ ደርሶኛል ብሏል፡፡

ይህም ለውጭ ሀገር ዜጎች በሀገር ውስጥ የስራ ፍቃድ ለመስጠት የተቀመጠውን መመርያ የሚጥስ መሆኑን ገልጿል፡፡በዚህም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ የስራ ፍቃዱ የታገደ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ክትትል በማድረግ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱም የደብዳቤውን ግልባጭ ለጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ ለኢንቨስትመንት ኮሚሽን ፣ ለፌደራል ፖሊስ ፎረንሲክ ምርመራ፣ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ልኳል፡፡

Via @AddisZeybe
@YeneTube @FikerAssefa