YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ 1,337 ንግድ ቤቶች ላይ እርምጃ ወሰደ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ወቅትን እና አጋጣሚን ምክንያት በማድረግ ያልተገባ ንግድ እንቅስቃሴ ላይ የተሰማሩ 1,337 ንግድ ቤቶች ላይ እርምጃ ወሰጃለሁ አለ።የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ እርምጃዉን ወሰድኩ ያልዉ ያለአግባብ ምርት የሚያከማቹ፣ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ፣ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈ ምርትን ለገበያ እያቀረቡ ባሉ ንግድ ቤቶች ላይ ነው:: የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድ ኢንስፔክሽን እና ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ጥላዬ ለአዲስ ዘይቤ እንደተናገሩት በሀገራችን በሰሜን አካባቢ ከሰላም መደፍረስ ጋር ተያይዞ ያለ አግባብ ጭማሪ እንዳይደረግ መደበኛ እና ድንገተኛ ፍተሻ እያደረጉ እንደሆነ ነግረውናል። አያይዘዉም በአዲስ አበባ በሚገኙ  32 የሚሆኑ ወፍጮ ቤቶች ላይ ርምጃ ተወስዷል ሲሉ ገልጸዋል።

የጤፍ እና ሌሎች የዋጋ ጭማሪን ያሳዩ ምርቶችን በሚመለከት ጤፍ ላይ የተወሰነ ጭማሬ እንዳለ መታዘባቸውን ገልፀው ህብረተሰቡ የሸማች ህብረት ስራ ማህበራትን አማራጭ እንዲያደግ ጠቁመዋዉ በህብረት ስራ ማህበራት ውስጥ ጤፍ ከ 4150-4200 ብር ድረስ እየተሸጠ መሆኑን አንስተዋል። በፓስታ እና መኮረኒ ላይ የተደረገው ጭማሪ ላይ ከአምራቾች ጋር በመነጋገር ወደ ቦታው መመለሱን አንስተውልናል።አያይዘዉም ከ63 ሺ በላይ የንግድ ተቋማት ፍተሻ እንዳደረጉ የገለፁ ሲሆን ወቅትን እና ሁኔታን ተገን እያደረጉ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ካሉ ህብረተሰቡ በ8588 የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በመደወል ጥቆማ እንዲያደርሠን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Via @addiszeybe
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት 8 ሰዎች በአንበሳ መበላታቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን እንዳስታወቀው ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 8 ሰዎች በአንበሳ ተበልተው ህይወታቸው አልፏል።በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባምባሲ ወረዳ 3 ሰዎች በጋምቤላ ብሄራዊ ፓርክ አቦቦ ወረዳ 5 ሰዎች በአንበሳ መበላታቸውን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ወረዳ 44 ፍየሎች በአንበሶች መበላታቸው ተገልጿል።በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ በሰውና ጅብ መካከልም በተደጋጋሚ ግጭት እንደሚፈጠር የተገለጸ ሲሆን ዋናው የሰዉና የዱር እንስሳቱ ግጭት መንስኤ ሰዎች በዱር እንስሳቱ መኖሪያ በመግብታቸው ነው ተብሏል።ለዚህም መፍትሄ ለመስጠት ሰዎችን ከእንስሳቱ መኖሪያ ፓርክ ርቀው እንዲኖሩ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ እንደሆነም አቶ ኩመራ ተናግረዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።

ከያዝነው ወር ህዳር 22 ጀምሮ ደግሞ በአሮጌው የብር ኖት ግብይት መፈጸም የማይቻል መሆኑን አስታውቋል።ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።የብር ኖት ቅያሬው በሶስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መወሰኑም ይታወሳል።በመሆኑም የአሮጌው የብር ኖት ቅያሬ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም የሚጠናቀቅ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።ከዚህ ቀን በኋላ በባንኮች አሮጌ የብር ኖት እንደማይኖርም ገልጿል።በዚሁ መሰረት የተፈቀደው የብር መቀየሪያ የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ 25 ቀናት ብቻ እንደቀሩት ይፋ አድርጓል።

[ENA]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ ወቅት 'የሕወሓት ጁንታ' ከዚህ የባሰ ጥፋት ከማድረሱ በፊት በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርብ፤ የከተማው ሕዝብ እንዳይጎዳ፣ ሕግ ለማስከበር በሚደረገው ዘመቻ በከተሞች አካባቢ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ፤ በጁንታው ግጭት ቀስቃሽነት ምክንያት የተፈናቀሉ ትግራዋይን ለመመለስና ለመርዳት በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በኩል የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በሚሉ ጉዳዮቾ ላይ ውይይት ተደርጎ ስምምነት ላይ ተደርሷል።ሕግ የማስከበር ዘመቻው ሲጠናቀቅ ትግራይን መልሶ ለማቋቋም የተዘጋጀው ዕቅድ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት እንተደረገበት ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የተከማቹ 19 ቦንብ እና ሌሎች በርካታ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ህዳር 9 ቀን 2013 ዓ/ም በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች በሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ውስጥ የተከማቹ 19 ቦንብ ፣55 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 21 ሽጉጦች ፣ 2 ኤስ ኬ ኤስ ጠመንጃ ፣3 ቺኮዝ፣ 1ብሬን ፣6 ቺቺ ጠመንጃ፣ እና ሌሎች ጠመንጃዎች በአጠቃላይ 113 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ተይዘዋል ፡፡ በተጨማሪም 309 የሽጉጥ እና 4829 ዓይነታቸው የተለያየ ጥይቶች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ትራኮን ሪልስቴት አካባቢ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ 64ሺህ 200 የአሜሪካ ዶላር መያዙን እና ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ከህዝብ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተከናወነ ተግባር ህዳር 9 ቀን 2013 ዓ/ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የተያዘውን ጨምሮ ከህዳር 3 ቀን ጀምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ በተሰሩ ስራዎች 37 የእጅ ቦንብ፣ 1ብሬን፣ 5የጦር ሜዳ መነፅር፣18 የሬዲዮ መገናኛ ቁሳቁሶች፣589 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣350 ሽጉጦች፣46 የተለያዩ ጠመንጃዎች በአጠቃላይ 1023 የተለያዩ አይነት የጦር መሳሪያዎች ከ10ሺህ 404 መሰል ጥይቶች ጋር በብርበራ እና በፍተሻ ተይዘዋል፡፡738 የተለያዩ የፀጥታ አካላት የደንብ አልባሳት በፍተሻው ወቅት መገኘታቸውንም የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጠቅሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኅዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ዓመት ሙሌት እና ዓመታዊ የውሃ አለቃቅ ላይ የተጀመረውን የሦስትዮሽ ድርድር ማስቀጠል አስፈላጊነት ላይ ስምምነት ቢደረስም፤ ሱዳን የድርድር ሂደቱ ካልተቀየረ አልሳተፍም ማለቷ ተሰማ፡፡

የሶስቱ አገራት የውሃና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ኅዳር 10 በበይነ መረብ ድርድር አድርገዋል፡፡የአፍሪካ ኅብረት አስፈፃሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ለመሪዎች ሊቀርብ የሚችል ውጤት ሊመዘገብ ይገባል ሲሉ አሳስበው ስብሰባውን ዘግተውታል፡፡

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንግሥት በዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም ላይ ቅሬታ እንዳለው ገለጸ!

የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተሩ ቴድሮስ አድሐኖምን በተመለከተ ቅሬታ እንዳለውና ደስተኛ አለመሆኑን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ዶክተር ቴድሮስ በአገሪቱ ውስጥ ምን እንደተከሰተ ከመንግሥት በኩል ለመረዳት አለመሞከራቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ዶ/ር ቴድሮስ "አንዳንድ በሮችን ማንኳኳታቸውን" መንግሥት እንደሚያውቅ አመልክተው ይህንንመ በተመለከተ መንግሥት በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለበት ይወስናል ሲሉ ተናግረዋል።በተያያዘም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክትር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግጭት ውስጥ የሚገኘው ህወሓትን የሚደግፍ የማግባባት ሥራ አከናውነዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ በትናንትናው እለት ተናግረው ነበር።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ የጦር አውሮፕላን ዛሬ በመቀሌ ከተማ የቦንብ ድብደባ እንደፈጸመ የትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል። ድብደባው የተፈጸመው በመቀሌ ዩኒቨርስቲ መለስ ካምፓስ አካባቢ ነው ብሏል ዜናው። በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ግን ዜናው ያለው ነገር የለም።

@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል መንግስት ህወሃት ላይ እየወሰደ ላለው የውጊያ አማራጭ ተጠያቂው እራሱ ህወሓት መሆኑን አቶ አባዱላ ገመዳ፡፡

ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በተለያዩ የሃገሪቱ ከፍተኛ የስልጣን እርከኖች ላይ ሲሰሩ የነበሩት አቶ አባዱላ ገመዳ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ በፌዴራሉ እና ትግራይ ክልልን በሚያስተዳድረው "ህወሓት" መካከል የነበሩ የሃሳብ ልዩነቶች ጦር ለመማዘዝም የማያበቁ እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡ 

ይሁንና ከብልጽግና ፓርቲ ምስረታ በኋላ "የሁለቱ ወገኖች ልዩነት የመጥበብ አዝማሚያን አላሳየም" ያሉት አባዱላ በተለይም ህወሓት "በፌዴራሉ መንግስትና በህገ መንግስቱም ጭምር እውቅና የተነፈገ" ካሉት የትግራዩ ምርጫ በኋላ ግን ነገሮች ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ማምራታቸውን እና የድርድር መስመርን ያጠበቡ ብለውታል፡፡ 

በህወሓት ባለስልጣንም ጭምር ተረጋግጧል ያሉት የሰሜን ዕዝ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የተወሰደው ያልታሰበ ያሉት ጥቃት ደግሞ "የፌዴራሉ መንግስት ተገዶ ወደ ጦርነት ለመግባቱ ማሳያ ነው" ያሉት አቶ አባዱላ አሁን ሊደርስ የሚችለውን ቀውስ የሚያሳንሰው የጦርነቱን ጊዜ ማሳጠር ብቻ ነው ሲሉም አክለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በትግራይ ክልል የባንክ አካውንታቸው የታገደባቸውን ኤጀንሲዎች አስመልክቶ መረጃ ሰጥቷል። በዚህም መሠረት ንብረታቸው እና የባንክ አካውንታቸው የታገደባቸው ኤጀንሲዎች የህወሓት የንግድ እና የወንጀል ግዛት አካል የሆኑት ብቻ መሆናቸውን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ ትግራይ መዲና መቀሌ እየደረሰ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥትን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘገበ።በትግራይ የሕወሓትን ቡድን ወደ ሕግ ለማቅረብ በሚል የጀመረዉ ጦርነት ሁለት ሳምንት እንደሞላዉ የዜና ወኪል ሮይተርስ ጨምሮ ዘግቦአል። በጠቅላይ ሚኒስትር የተቋቋመዉ የትግራይ ግጭትን የሚከታተለዉ ግብረ ኃይል የትግራዩን ጦርነት ሸሽተዉ ወደ ወደ ሱዳን የሸሹ ዜጎችን ለመመለስ እቅድ መያዙን ሮይተርስ ን ዘቅሶ ዘግቦአል። ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ የሰብዓዊ ቀዉስ መርጃ የሚሆን ቁሳቁሶችን ለመላክ የልዑካን ቡድን ወደ ስፍራዉ ማቅናቱ ተመልክቶአል።

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ከሚገኘው ጦርነት ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ስማቸው ሲነሳ የቆየው ዶ/ር #ቴድሮስ_አድሃኖም የሚከተለውን መልእክት አስተላለፉ።

@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ከሚገኘው ጦርነት ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ስማቸው ሲነሳ የቆየው ዶ/ር #ቴድሮስ_አድሃኖም የሚከተለውን መልእክት አስተላለፉ። @Yenetube @Fikerassefa
ወደ አማርኛ #ሲተረገም

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የቀረበባቸውን ውንጀላ አስተባበሉ።

የዓለም ጤና ድርጀት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በቲዊተር ገጻቸው ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት በሃገራቸው ኢትዮጵያ በተከተለው ሞት እና መፈናቀል ማዘናቸውን ገልጸው ፣ሁሉም ወገኖች ለሰላም እና ለሲቪሎች ደህንነት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

ከሕወሃት ጋር አብረዋል በሚል የቀረበባቸውን ውንጀላም አስተባብለዋል፣በአጋርነት የምቆመው ከአንድ ነገር ጋር ብቻ ነው እሱም ሰላም ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
'የህወሓት ቡድን' ዛሬ ሌሊት 7፡40 አካባቢ ወደ ባህር ዳር የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን አብመድ ገልጿል።በተፈፀመው ጥቃት የደረሰ ጉዳትም የለም ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ በህወሓት በኩል የሽምግልና ፍላጎት እንደሌለ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ!

በትግራይ ያለው ውጊያ በንግግር እንዲፈታ በቀጠና፣ አህጉር እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ መሪዎች የማሸማገል ጥያቄ ቢያቀርቡም፤ በኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ በህወሓት በኩል የሽምግልና ፍላጎት እንደሌለ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ተናገሩ። የህወሓት አመራሮች ውጊያውን ሲጀምሩ የተከተሉት ታክቲክ፤ “ካቀዱት ተቃራኒውን ውጤት አምጥቷል” ብለው እንደሚያምኑም ገልጸዋል።

በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት ቲቦር ናዥ ይህን የተናገሩት በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ትላንት ሐሙስ ምሽት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው የጥያቄ እና መልስ ቆይታ ነው። በስልክ ኮንፈረንስ አማካኝነት በተካሄደው እና “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በቀጥታ በተከታተለችው የጋዜጠኞች የገለጻ መርሃ ግብር ላይ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ማይክል ራይነርም ተሳትፈዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
ትናንት ሌሊት በባህርዳር ከተማ የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን የአየር ሀይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ አረጋግጠው፣ "ወደ ህዝብ ነበር የተተኮሰው ነገር ግን ጉዳት ሳይደርስ ጫካ ውስጥ ነው የወደቀው፣ እኛም አፀፋዊ ምላሽ የምንወስድ ይሆናል" ሲሉ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ይህን በተመለከተ የስጡት ሙሉ ማብራርያ ከላይ በድምፅ ተያይዟል።

@YeneTube @FikerAssefa
ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሚዲያዎች ጋር ውይይት እያደረገ ነው!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀም እና ድልድል ረቂቅ መመሪያ ላይ ከመገናኛ ብዙኃን እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ መገናኛ ብዙኃን ለሁሉም እኩል የመወዳደሪያ ሜዳ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
የህወሃት ንብረትነቱ የመከላከያ ሰራዊት ባልሆነ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ተፈጽሞብኛል የሚለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ የአየር ሀይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለፁ።

ሜጀር ጀኔራል ይልማ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ የጠላት ኢላማዎችን ያለምንም ርህራሄ እንዳልነበር ማድረግ ለሰራዊቱ ማነቆ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን በማፍረስ መንገዱን ቀና የማድረግ ተግባርም ይከውናልም ነው ያሉት፡፡

በመቐለ አቅራቢያ ኪያ እና አዲግራት ጭምር የነበሩ የነዳጅ ዴፖዎችም በ'ጁንታው' ቡድን ጥቅም ላይ ሳይውሉ መውደማቸውንም ተናግረዋል፡፡እስካሁን የተዋጣላት ሀገርንም ያኮራ ስራ እና እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፥ በዚህ ሁሉ ውስጥ ህገ ወጡ ቡድን የአየር ድብደባው ንጹሃንን እና የተለያዩ የእምነት ተቋማትን እንዲሁም የህዝብ መገልገያ ፕሮጀክቶችን ኢላማ ስለማድረጉ ክስ ያቀርባል።የአየር ሀይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፥ ውንጀላው ከእውነት የራቀ መሆኑን እና ይህ የቡድኑ የኖረ የውሸት እና የውንብድና ትርክቶች መሆናቸውን አውስተዋል።

የጦር አውሮፕላን መትተን ጥለናል የሚለው የህገ ወጡ ቡድን ወሬም ቢሆን የበሬ ወለደ እንጂ የአቅም እና የመሳሪያ ሁኔታው አልፈቀደለትም ይላሉ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ።የትግራይ ወንድም እና እህቶችን ህይወት እና ሀብት ባላስገበረ መልኩ የተለዩ ኢላማዎችን የማጥቃት እርምጃው እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።“ይህን ስናደርግ ደግሞ በራሳችን በገነባነው የቴክኖሎጂ ልክ እንጂ የማንንም እርዳታ እና ድጋፍ አንጠይቅም” ብለዋል ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሚዲያዎች ጋር ውይይት እያደረገ ነው! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀም እና ድልድል ረቂቅ መመሪያ ላይ ከመገናኛ ብዙኃን እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ መገናኛ ብዙኃን ለሁሉም እኩል የመወዳደሪያ ሜዳ እንዲሆኑ…
የፖለቲካ ፓርቲዎች ከጠቅላላ የአየር ሰዓት እና አምድ እኩል የሚከፋፈሉበት ቀመር

👉ለምርጫ የሚወዳደሩ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከተመደበው ጠቅላላ የመገናኛ ብዙኃን የአየር ጊዜ እንዲሁም የጋዜጣ አምድ ውስጥ 25 በመቶ የሚሆነውን እኩል ይከፋፈላሉ።

👉ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚወዳደሩበት የፌደራል ወይም ክልል ምክር ቤቶች በሚያቀርቡት እጩ ብዛት መሰረት ከጠቅላላው የአየር ጊዜ ወይም የጋዜጣ አምድ ውስጥ 40 በመቶ ይከፋፈላሉ።

👉ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤቶች ባቀረቧቻው የሴት እጩ ተወዳዳሪዎች ብዛት መሰረት ከጠቅላላው የአየር ጊዜ እና የጋዜጣ አምድ 20 በመቶ ይከፋፈላሉ።

👉የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚያቀርቧቸው የአካል ጉዳተኞች ብዛት መሰረት ከጠቅላላው የአየር ሰዓት ወይም የጋዜጣ አምድ ውስጥ 10 በመቶ ይከፋፈላሉ።

👉በስራ ላይ ባሉት የህዝብ ተወካዮች እና ክልል ምክር ቤት ባላቸው መቀመጫ ብዛት መሰረት ከጠቅላላው ምርጫ የአየር ጊዜ እንዲሁም የጋዜጣ አምድ 5 በመቶ እንደ መቀመጫ ብዛታቸው ይከፋፈላል።ሲል የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ጋር በጋራ ባወጣው ጠቅላላ ድንጋጌ ላይ አስታውቋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ከትግራይ ክልል ወደ ሱዳን በገቡ ኢትዮጵያውያን ዙሪያ የኢትዮጵያ መንግስት ከሱዳን መንግስት ጋር በሁሉም መስክ ተባብሮ እየሰራ ነው ሲሉ በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ተናገሩ።

በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ከስካይ ኒውስ የአረብኛ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቃለ ምልልስ ባደረጉበት ወቅት መንግስት በትግራይ ክልል የጀመረው ሕግ የማስከበር እርምጃ ጥቂት ወንጀለኞችን ለህግ ለማቀረብ የሚደረግ ዘመቻ ነው ብለዋል።ይህም ማንኛዉም መንግስት የሚያደርገዉ እንደሆነ የገለፁት አምባሳደሩ ማንም መንግስት ህግ እየተጣሰ ቁጭ ብሎ የሚያይበት ሁኔታ እንደሌለ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ በሚገኘው እርምጃ ምክንያት ችግሩ አካባቢያዊ ሊሆን የሚችልበት እድል የለምም ብለዋል።በህግ ማስከበር ሂደት ከቀያቸዉ ተፈናቀለው ወደ ሱዳን የገቡ ኢትዮጵያውያን በተለይም የምዕራቡ ትግራይ ክፍል ሙሉ በሙሉ ሰላም የተረጋገጠ በመሆኑ በቅርቡ ወደ ቀያቸው እንደሚመለሱ አረጋግጠዋል።ከዚህ ጋር በተያየዘ ከሱዳን መንግስት ጋር በሁሉም መስከ በትብብር እየሰሩ መሆኑንም አምባሳደሩ አስገንዝበዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa