YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከጣና ሐይቅ ላይ እምቦጭን ለማስወገድ ለአንድ ወር ሲካሄድ የነበረው ዘመቻ እስከ ሕዳር 30 እንዲቀጥል ተወሰነ።

እስካሁን በነበረው ዘመቻ ከፍተኛ ውጤት እንደተመዘገበ የዘመቻው አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡የዘመቻውን መራዘም አስመልክቶ የዘመቻው አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ ዛሬ ማምሻውን በውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ከጥቅምት 9 እስከ ሕዳር 9 ቀን 2013 ሲካሄድ በቆየው ዘመቻ በተለያዩ ምክንያቶች ሁሉንም ቀናት መጠቀም ባለመቻሉ የዘመቻውን ጊዜ እስከ ኅዳር 30 ማራዘም አስፈላጊ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

እስካሁን በነበረው የዘመቻ ጊዜ አረሙን በማስወገድ ረገድ ተጨባጭ ለውጥ መታየቱም ተገልጿል፡፡በመግለጫውም በእስካሁኑ ዘመቻ የእምቦጭ አረም ተከስቶባቸው ከነበሩት 30 ቀበሌዎችን ከሚያዋስነው የሐይቁ አካል በ17 ቀበሌዎች ውስጥ የተከሰተውን አረም ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡በዘመቻውም ከ200 ሺህ በላይ የሰው ኃይል መሳተፉ በመግለጫው ተመልክቷል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በሱማሊያ ከሠፈሩት የኢትዮጵያ ወታደሮች ውስጥ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወታደሮች ትጥቃቸውን እንዲፈቱ እንደተደረጉ ከዲፕሎማቲክ እና ደኅንነት ምንጮች ሰምቻለሁ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ትጥቅ እንዲፈቱ የተደረጉት አንድ ወታደራዊ ምክትል አዛዥን ጨምሮ፣ በአሚሶም ስር የሚገኙ እና በተናጥል የሠፈሩ ወታደሮች ናቸው፡፡ ትጥቅ የፈቱት ወታደሮች ከ200 እስከ 300 የሚገመቱ እንደሆኑ እና ከጦር ሠፈራቸው እንዳይወጡ መታዘዛቸውን ዘገባው ጠቅሷል፡፡ ርምጃው የተወሰደው በወታደሮቹ ታማኝነት ላይ ስጋት በመፈጠሩ ነው ተብሏል፡፡ መንግሥትም ሆነ አሚሶም እስካሁን ለዘገባው ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ አልሰጡም፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 533 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 300 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 4 ሺህ 871 የላቦራቶሪ ምርመራ 533 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 103 ሺህ 928 ደርሷል።በሌላ በኩል የዛሬውን ጨምሮ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 64 ሺህ 593 ሆኗል።ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ13 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 601 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 37 ሺህ 732 ሰዎች መካከል 305 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
“በሸኔ ታጣቂዎች ተከበናል መንግስት ይድረስልን”-የድባጤ ወረዳ ተፈናቃዮች

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ከድባጤ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ተፈናቅለው ጋሊሳ ከተባለ የወረዳው ቀበሌ ሰፍረው የሚገኙ “የአማራ ተወላጅ ነን”ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ጥሪ አቀረቡ፡፡“ትናንት እና ከትናንት ወዲያ በተፈጸመብን ጥቃት ቀያችን ለቀን ወጥተናል”ያሉት ነዋሪዎቹ “አሁንም ባረፍንበት ቀበሌ የኦነግ/ ሸኔ ታጣቂዎች እየተመላለሱ እያስፈራሩን ነው” ብለዋል፡፡አንድ ስማቸውን ለመግለጽ ያልፈለጉ እና ከተፈናቃዮቹ መካከል የሆኑ ግለሰብ “ጨለማን ተገን አድርገው የሚንቀሳቀሱ የሸኔ ተጣቂዎች አሉ ሌሊቱን በእነሱ ተከበን ነው ያደርነው” ሲሉ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡

ሙሉ ዘገባው👇👇👇
https://am.al-ain.com/article/idps-in-metekel-zone-dibate-woreda-urge-gov-t-to-reach-them-immediately

Via Al-ain
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል በሰጡት መግለጫ ራያ እና ሽረ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መያዛቸውን አረጋገጡ።

ደብረጽዮን "ትግሉ አሁንም ቀጣይ ነው።ገና ነው።ውጊያ ውስጥ ነን" ብለዋል።በትግራይ የተጀመረው ውጊያ አስራ ስድስት ቀናት ሆኖታል።ከትናንት በስቲያ የአውሮፕላን ጥቃት ያስተናገደችው መቐለ ትናንት እና ዛሬ መረጋጋት እንደታየባት የዶይቸ ቨለ ዘጋቢ ከመቐለ ዘግቧል።ሁሉም የግል እና የመንግሥት ባንኮች ተከፍተዋል።የነዳጅ እጥረት በመኖሩ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መቀነስ መጀመሩን የገለጸው ዘጋቢ የስልክ እና የኢንተርኔት ግልጋሎቶች እንደተቋረጡ መሆናቸውን ዘግቧል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው የህወሃት ቡድን አመራሮች በሰላም እጅ እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ!

የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው የህወሃት ቡድን አመራሮች ከድርጊታቸው ተቆጥበው በሰላም እጅ እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡የህወሃት ቡድን ታጣቂዎች እንደ ማይካድራ ባሉ ቦታዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸው በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ ቡድኑ ከዚህ ቀደም ባሉት ጊዜያት በተለያዩ ቦታዎች ተመሳሳይ ችግሮችን ሲፈጥር መቆየቱ ተገልጿል፡፡የፌዴራል መንግስት በእነዚህ የጥፋት ድርጊቶች ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለፍርድ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሜ አረጋግጧል፡፡በትግራይ የሕግ የባለይነትን የማስከበር ስራ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የሚገኝ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የህወሃት ቡድን ኃይሎች እንደ ማይካድራ ባሉ ቦታዎች ላይ የፈጸሙት ድርጊት በኢትዮጵያ ሕግም ሆነ በዓለም አቀፍ ሕግ በወንጀል ሊያስጠይቁ የሚችሉ ጥፋቶች መሆናቸው ሊገነዘብ ይገባል መባሉን ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የተለያዩ የአለም አቀፍ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውን ከመቀሌና ከትግራይ አካባቢዎች በማስወጣት ላይ ናቸው።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለካፒታል ጋዜጣ እንደተናገሩት የተባበሩት መንግስታት ደርጅትን ጨምሮ ሐገራት ዜጎቻቸውንና ሠራተኞቻቸውን ከትግራይ ክልል እያስወጡ ሲሆን በትላንትና እለት ብቻ ከ200 የሚበልጡ የUN ሰራተኞች በአፋር ክልል በኩል የወጡ እንደሆነ ተናግረዋል።ደርጅቶች ባላቸው የሳተላይት መገናኛ ከሠራተኞቻቸው ጋር በመገናኘት ከመቀሌ እስከ አፋር ክልል ድንበር ድረስ የክልሉ መንግስት ጥበቃ እያደረገላቸው የሚመጡ ሲሆን ከአፋር ክልል በዋላ የፌደራል መንግስትና ድርጅቶቻቸው የሚቀበሏቸው እደሆነ ገልጸዋል።ይህ ሲሆን ሁሉም ድርጅቶች የሚያስወጧቸውን ሠዎች ዝርዝር ለፌደራል መንግስት መስጠትና ለወንጀል የማይፈለጉ መሆናቸው መረጋገጥ ይኖርበታል።ይህ በእንዲህ እዳለ በትግራይ ክልል የሚፈጠረውን የኑሮ ጫና ለማገዝ መንግስት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ለመስጠት ምቹ ሁኔታዎችን እየፈለገ ቢሆንም ከተፈጠረው ችግር ባሻገር TPLF እያደረገ ያለው መንገድና ድልድዮች ላይ ጥፋት ሁኔታውን ይበልጥ አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት አራት ወራት ከወርቅ የተሻለ ገቢ መገኘቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገልጸዋል፡፡

“ባለፉት አራት ወራት የወርቅ ምርት ወደ ውጪ ልከን የተሻለ ገቢ ማስገባት ተችሏል፤ ለአራት ተከታይ ወራት ከፍተኛ ገቢ ካስገቡ ምርቶችም ቀዳሚው መሆን ችሏል፤ በቀጣይ ወራትም ግዙፍ ኩባንያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ወደ ማዕድን ምርት እየገቡ ስለሆነ ቀጣይ ጊዜያት የተሻለ ስራ ሰርተን የተሻለ ውጤት የምናስመዘግብበት ይሆናል” ብለዋል ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው።

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል በሚዋቀረው አዲስ አስተዳደር የክልሉ ምክር ቤትና ካቢኔ እንደገና ይዋቀራሉ ተባለ!

የመጀመሪያው ኃላፊነት የክልሉን አስተዳደር መልሶ ማዋቀር ነው ሲሉ በትግራይ የተቋቋመው ጊዚያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተናግረዋል።በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ የተቋቋመው የጊዚያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለፁት የክልሉ ምክር ቤትና ካቢኔ እንደገና ይዋቀራሉ።መንግሥት እያካሄደ ካለው ዘመቻ በኋላ ክልሉ የሚመራበት ቻርተር መዘጋጀቱንም አብራርተዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
የፖሊስ የደንብ ልብስ በመልበስ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ወርቅ የሰረቁ ተጠርጣሪዎች ከነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በወንጀሉ ተሳትፈዋል የተባሉ 5 ተጠርጣሪዎችን፣ ለወንጀል ተግባር ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የፖሊስ የደንብ አልባሳት፣ሽጉጥ፣ ካቴና እና ስለቶችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ፣ የፖሊስ የደንብ አልባሳቱንም ከየት አምጥተው እንደለበሱ የማጣራት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የጃንሜዳ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ለውጥአየሁ ከበደ ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክር ቤት በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አካሂዷል።

በምክክር መድረኩ ላይ በጊዜያዊ አስተዳደሩ መሪነት በክልሉ ሰላም ለማምጣት በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ምን መሆን አለበት የሚል ሐሳብ ተነሥቷል።በክልሉ ሊሠሩ የታሰቡ ዐበይት ሥራዎች የተገለጹ ሲሆን፣ ባለ ስድስት ነጥብ ረቂቅ ቻርተር ዝግጅት መደረጉ ታውቋል።

እነዚህም የአስተዳደር መዋቅር ማስተካከል፣ የክልሉ ሰላም እና ደኅንነት ማስጠበቅ እና ማረጋገጥ፣ ፍትሕ እና መልካም አስተዳደር ማስጠበቅ እና ማረጋገጥ፣ የተቋረጠውን ማኅበራዊ አገልግሎት ማስቀጠል፣ የክልሉን ኢኮኖሚ እንዲያገገም ማድረግ እንዲሁም በቀጣይ ከሚካሄደው 6ኛው አገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ በክልሉ ውስጥ መንቀሳቀስ ለሚፈልጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሐሳባቸውን በነፃነት አቅርበው እንዲወዳደሩ የፖለቲካ ምኅዳሩን ማመቻቸት ሥራዎች መሆናቸው ተዘርዝሯል።

ፓርቲዎቹ በአሁኑ ወቅት በክልሉ እየተካሄደ ላለው ሕግ የማስከበር ዘመቻ ግብ እስኪመታ ከመንግሥት እና ከመከላከያ ኃይል ጎን እንዲቆሙ ተጠይቋል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ 27 ሚሊየን ዜጎች ሜዳ ላይ እንደሚጸዳዱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የዓለም የመፀዳጃ ቤቶች ቀን በማስመልከት በአዲስ አበባ የተለያዩ የህብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች፣አመራሮች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት እየተወያዩ ነው።የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ በውይይቱ ላይ እንዳሉት 27 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን አሁንም ሜዳ ላይ ይጸዳዳሉ።በኢትዮጵያ ከሚከሰቱ ህመሞች 30 በመቶ የሚሆኑት ተላላፊ በሽታዎች መንስኤያቸው ከመጸዳጃ ቤትና ከአካባቢ ንጽህና ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል።ዜጎች ጥንቃቄ ከማድረግ ይልቅ ሲታመሙ ብዙ ወጪ ያወጣሉ ተብሏል መንግስትም ይሄን ለማከም በርካታ ወጪዎችን ያወጣሉ ብለዋል ዶክተር ደረጀ።

ይህ በመሆኑ ምክንያት ተላላፊ በሽታዎች በመጨመሩ በየዓመቱ ከ13 ቢሊዮን በላይ ብር ለመድሃኒት ግዥ እና ለሌሎች ህክምና ወጪዎች እንደሚወጣም ዶክተር ደረጀ ገልጸዋል።በሜዳ ላይ የሚጸዳዱ ዜጎችን ቁጥር ለመቀነስ ጤና ጥበቃ ሚኒስሬር በሚቀጥሉት 10 አመታት ኢትዮጵያን ከውጭ መጸዳዳት ነጻ ሀገር ለማድረግ መታቀዱን ገልጸዋል።አሁንም ሜዳ ላይ የመጸዳዳት ልማድ ያለው የህብረተሰብ ክፍል እንዳለ የተነገረ ሲሆን 27 ሚሊየን ዜጎችም ሜዳ ላይ ይጸዳዳሉ ተብሏል።ከ10 አመት በፊት መጸዳጃ ቤት የሚጠቀሙ ዜጎች ቁጥር 40 በመቶ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን 70 በመቶ መድረሱም ተገልጿል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ በቀጣዩ ቀናቶች በአንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል ኃይል ይቋረጣል!

አርብ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 5:00 ድረስ፣
• በኦሎፒያ፣ በፍላሚንጎ፣ በደንበል፣ በኦሮሚያ ቢሮ፣ በሰንሻይን ጀርባ፣ በለቡ፣ በጆሞ 1 በከፊል እና አካባቢዎቻቸው፣

በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 9:30 ድረስ፣
• በደራርቱ ት/ቤት፣ በአየር ኃይል ካምፕ፣ በወርቁ ሰፈር፣ በመንገድ ትራንስፖርት፣ በሳሚት ኮንደሚኒየም፣ በጊዮርጊስ ቤ/ክ፣ በፈረንሳይ ኤምባሲ፣ በጉራራ፣ በፊልም ማዕከል፣ በራስ ካሳ ክሊኒክ፣ በአቦ ቤ/ክ፣ በእንጦጦ ኪዳነምህረት ቤ/ክ እና አካባቢዎቻቸው፣

ዕሁድ ህዳር 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 9:00 ድረስ፣
• በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ በጉርድ ሾላ፣ በአየር መንገድ ቤቶች እና አካባቢዎቻቸው፣

እንዲሁም ሰኞ ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 5:00 ድረስ፣
• በቀጨኔ 8 ቁጥር ማዞርያ፣ በመቀጠያ፣ በታቦት ማደርያ እና አካባቢዎቻቸው፣

በተጨማሪም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ፣
• በደራርቱ ት/ቤት፣ በአየር ኃይል ካምፕ፣ በወርቁ ሰፈር፣ በመንገድ ትራንስፖርት፣ በሳሚት ኮንደሚኒየም፣ በጊዮርጊስ ቤ/ክ፣ በካኦ ጄጄ፣ በጊዮን በረኪና፣ በዊንጌት ት/ቤት ጀርባ፣ በታይዋን ገበያ፣ በኮልፌ ቁሳቁስ፣ በገርጂ ኮንደሚኒየም፣ በኢፔሪያል ሆቴል፣ በገርጂ ጤና ጣቢያ፣ በዳችያ ቀለም፣ በገርጂ አንበሳ ጋራዥ፣ በጎሮ፣ በሰሚት ለስላሳ፣ በሰሚት ኪዳነምህረት ቤ/ክ፣ በፍርድ ቤት እና አካባቢዎቻቸው፣ በመካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ ክቡራን ደንበኞች ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲይያደርጉ ተብሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ተመድ በረሃብ አደጋ ውስጥ ላሉ 7 ሀገራት 100ሚሊዮን ዶላር ለቀቀ!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ እርዳታ ቢሮ ለረሃብ አደጋ ተጋላጭ ናቸው ላላቸው ሰባት የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የ100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡የተመድ ዋና ጸኃፊ የኮሮና ቫይረስና ግጭት ባለበት ወቅት አለም ወደ ተለመደው ረሃብ መመለሷ አስቀያሚ ነው ማለታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ እንደ ቢሮው መግለጫ 80 ሚሊዮን ዶላሩ ለአፍጋኒስታን፣ ለቡርኪና ፋሶ፣ ለኮንጎ፣ ለናይጀሪያ፣ ለደቡብ ሱዳን እና የመን መሰራጨቱን የጠቀሰ ሲሆን ቀሪው 20 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ባለው ግጭት ምክንያት “ለሚጠበቀው ረሃብ” መመደቡን ገልጿል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
እናቱን የገደለዉ ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ!

በአማራ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን ወላጅ እናቱን የገደለዉ ተከሳሽ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ። ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወረኢሉ ተዛዋሪ ችሎት የ20 ዓመቱ ወጣት ተከሳሽ ኡስማን መሀዲ በ1996 ዓ.ም ተሻሽሎ የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 540 የተመለከተውን ተላልፏል በሚል ነው ዐቃቤ ህግ ክሱን ያቀረበው፡፡በክስ ዝርዝሩም መጋቢት 21 ቀን 2012 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 9፡00 ስዓት አካባቢ በጃማ ከተማ ጌንጌቶ ተብሎ በሚጠራው ልዩ ስፍራ የወንጀል ድርጊቱ መፈፀሙን ጠቅሷል፡፡

ተከሳሹ ወላጅ እናቱን በመጥረቢያ (በምሳር) በግራ በኩል ጆሮዋን በመምታት የገደላት በመሆኑ በተራ የሰው መግደል ወንጀል ነው ክሱ የቀረበበት፡፡አዲስ ዝይቤ ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባገኘቸው መረጃ መሰረት ችሎቱ የግራ ቀኙን የሰው ምስክሮችንና የሰነድ ማስረጃዎችን ከመረመረ በኋላ ተከሳሹ ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የወንጀል ሪከርድ አለማስመዝገቡን እንደ ቅጣት ማቅለያ ይዞለታል፡፡በዚህም መሰረት ህዳር 8 ቀን 2013 ተሰይሞ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የፍርድ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ባለቤት ያልተገኘላቸው ህንጻዎች 100 መድረሳቸውን የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተማ ከተውጣጡ የከተማዋ ወጣቶች ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂዷል።በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት፣ በከተማዋ የሚገኙ ህንጻዎች፣ ታጥረው የሚገኙ መሬቶች እና የቀበሌ ቤቶችን በተመለከተ እየተደረገ ባለው ዳሰሳ እስካሁን 100 ህንጻዎች ባለቤት አልተገኘላቸውም።
ከዚህም በተጨማሪ ታጥሮ የተቀመጠ ከ1 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ባለቤት ሳይገኝለት ቀርቷል።በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶች ላይም ማጣራት እየተደረገ መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የከተማዋ ወጣቶች በትግራይ ክልል እየተደረገ ያለውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ እንደሚደግፉ እና ከመከላከያ ሠራዊት ጎን መሆናቸውን ገልጸዋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ኤርትራ በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ ዝምታዋን ሰበረች!

በሰሜናዊ ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት በተመለከተ ምንም አይነት አስተያየት ሳትሰጥ የቆየችው ኤርትራ በማስታወቂያ ሚኒስትሯ በኩል ዝምታዋን ሰብራለች።በዚህም ኤርትራ በዋና ከተማዋ አሥመራ ላይ የሚሳኤል ጥቃት ከተፈጸመ ከቀናት በኋላ የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ግዛት የሆነችውን የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረውን ህወሓትን በ"ክፉ ዓላማና ድርጊት" ወቅሳለች።በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ወደ ሦስተኛ ሳምንቱ በተሸጋገረበት በአሁኑ ወቅት የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል ትናንት ህወሓት ላይ ወቀሳ ሰንዝረዋል።

ሚኒስተሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ ያሳፈሩት ጥቅምት 25/ 2013 ዓ.ም መንግሥት በህወሓት የሚመሩት የክልሉ ኃይሎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ በኋላ ስለግጭቱ ከኤርትራ በኩል የተሰማ ይፋዊ አስተያየት ነው።ሚኒስትር የማነ ጨምረውም ብዙም ግልጽ ባልሆነው ሁኔታ ባሰፈሩት መልዕክት ላይ፤ የህወሓትን "ተገማች የሆነ ገነር ግን ውጤት አልባ የመጨረሻ መፍጨርጨርን ማጉላት አስፈላጊ አይደለም" ብለዋል።የማስታወቂያ ሚኒስትሩ መልዕክታቸው ላይ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ከኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ወደ አሥመራ ከተማ ስለተተኮሱት ሚሳኤሎችም ሆነ የኢትዮጵያ ሠራዊት እያካሄደ ስላለው ወታደራዊ ዘመቻ ምንም ሳይሉ ቀርተዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ጤና ድርጅት ቢያንስ 20 በመቶውን የአፍሪካ ህዝብ ለመከተብ አስቧል!

የዓለም ጤና ድርጅት ቢያንስ ለ20 በመቶው የአፍሪካ ህዝብ የኮሮና ክትባት ለመከተብ ማሰቡን የድርጅቱ የአፍሪካ ዳይሬክተር አስታወቁ፡፡ዳይሬክተሩ ዶ/ር ማትሺዲሶ ሞኤቲ ሁሉም የአህጉሪቱ ሃገራት ራሳቸውን ለክትባቱ እንዲያዘጋጁ ትናንት በተካሄደ የኦን ላይን ውይይት አስታውቀዋል፡፡ክትባቶቹን በተቻለ አቅም በቶሎ የማድረስ ውጥን በድርጅቱ በኩል መያዙንም ነው ያስታወቁት፡፡እስከ ትናንት የተጠናቀሩ የአህጉሪቱ የበሽታዎች ቁጥጥር ማዕከል መረጃዎች የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከ2 ሚሊዬን ማሻቀቡን ማሳየታቸው የሚታወስ ነው፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የአየር ሰዓት ድልድል መመሪያ ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ቦርዱ በላከው መግለጫ የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የአየር ሰዓት ድልድል መመሪያ የተዘጋጀ ሲሆን በነገው ዕለት በዚህ መመሪያ ዙሪያ ከሚመለከታቸው ተቋማት እና ባለሙያዎች ጋር በአዲስ አበባ ይመክራል።ምርጫ ቦርዱ፣በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 የተሰጡትን ሃላፊነቶችና ግዴታዎች ለመወጣት እንዲያስችለዉ የተለያዩ መመሪያዎችን እያረቀቀ እንደሚገኝም ገልጧል፡፡ከነዚህ መመሪያዎች መካከልም የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀምና ድልድል መመሪያ ይገኝበታል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ-ቴሌኮም ለሀገር መከላከያ የገቢ ማሰባሰቢያ የአጭር የጽሁፍ መልዕክት ቁጥር ይፋ አደረገ።

ኢትዮ-ቴሌኮም በዛሬው እለት ይፋ ያደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ የአጭር የጽሁፍ መልዕክት ቁጥር 6800 መሆኑን አስታውቋል።በዚህ መሰረት ማንኛውም ሰው ወደ 6800 የፈለገውን የገንዘብ መጠን በማስገባት በመላክ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያለውን ክብር እና አጋርነት ማሳየት እንደሚችልም ኩባንያው አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa