ለመከላከያ ሰራዊቱ የህክምና ድጋፍ ለመስጠት ወደ ጦር ግንባር ለሚያመሩ የህክምና ባለሙያዎች አሸኛኘት ተደረገ!
ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የህክምና ድጋፍ ለመስጠት ወደ ጦር ግንባር ለሚያመሩ የህክምና ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሸኛኘት ተደርጓል።በአሸኛኘቱ ላይ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ፤ የከተማዋ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላን ጨምሮ በርካታ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ከዚህ የሽኝት መርሃግብር ቀጥሎ የጤና ባለሙያዎች በቀጥታ ወደ ስፍራው የሚያመሩ ይሆናል።
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላን በዚህ ወቅት ''የጤና ባለሙያች የመከላከያ ሰራዊቱን ለማገልገል እድል በማግኘታቹ እንኳን ደስ አላችሁ'' ብለዋል።የህክምና ድጋፍ ለመስጠት የሚሄዱት ባለሙያዎች 10 ስፔሳሊስት ዶክተሮች፤ 24 ነርሶች፤ አንድ ማደንዘዣ የሚሰጥ ስፔሻሊስት ዶክተርን ጨምሮ 48 የህክምና ባለሙያዎች በሁለት ቡድን ተከፍለው ይጓዛሉ ብለዋል።
Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa

የአፍሪካ ሚሊየነሩ ሰባኪ ‘ነብይ’ ቡሺሪ ከደቡብ አፍሪካ አመለጠ!
በአፍሪካ የናጠጠ ሀብታም ነው የሚባለው አወዛጋቢው ሰባኪ ነብይ ሸፐርድ ቡሺሪ ከደቡብ አፍሪካ አመለጠ። ቡሺሪ በደቡብ አፍሪካ በቁጥጥር ሥር ውሎ የፍርድ ሂደቱን እየተከታተለ ነበር።አወዛጋቢው ቡሺሪ በደቡብ አፍሪካ በቁጥጥር ሥር ውሎ የነበረው ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ላይ ነበር።የተመሰረተበት ክስ ደግሞ ከማጭበርበርና ከሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ጋር የተያያዘ ነበር። ይህን የፍርድ ሂደት በመከታተል ላይ ሳለ ነው በድንገት ከደቡብ አፍሪካ አምልጦ ወደ ትውልድ አገሩ ማላዊ የገባው።
ሚሊየነሩ ነብይ ቡሺሪ እንዴት ሊያመልጥ ቻለ የሚለው ደቡብ አፍሪካዊያንን እያነጋገረ ሲሆን ምናልባት የማላዊ ፕሬዝዳንት በሚጠቀሙበት ቻርተርድ ጄት አውሮፕላን እንደሸሸ ተገምቷል።አንዳንድ ዘገባዎች እንዲያውም የማላዊው ፕሬዝዳንት ላዛረስ ቸክዌራ ናቸው ሸሽገው በግል አውሮፕላናቸው ከደቡብ አፍሪካ ያስወጡት ይላሉ።የማላዊ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ግን ይህንን ክስ አስተባብሏል።የሚሊየነሩ ሰባኪ ሼፐርድ ቡሺሪ ጉዳይ በደቡብ አፍሪካና በማላዊ መካከል የዲፕሎማሲ ቅራኔ ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አለ።የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ማላዊ ተጠርጣሪውን ከነባለቤቱ አሳልፍ እንድትሰጣት እንደምትጠይቅ ተናግራለች። ደቡብ አፍሪካና ማላዊ ወንጀለኞችን አንዱ ለሌላው አሳልፎ የመስጠት ስምምነት አላቸው።
Via BBC

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በትግራይ ክልል በተለያዩ መስሪያ ቤቶቹ ተመድበው ይሰሩ የነበሩ የተወሰኑ ሰራተኞቹን ማስወጣቱን ምንጮች ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።
የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው እና ኢትዮጵያውያን የድርጅቱ ሰራተኞች፤ በተመድ ተሽከርካሪዎች ተጭነው ክልሉን የለቀቁት ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ መሆኑንም ገልጸዋል።አዳራቸውን ትላንት በአማራ ክልል ያደረጉት እኚሁ ሰራተኞች፤ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ እነዚሁ ምንጮች ጠቁመዋል።በአዲስ አበባ ከሚገኙ የተመድ መስሪያ ቤቶች በአንዱ የሚሰሩ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ምንጭ፤ ድርጅቱ ሰራተኞቹን የማስወጣት የአስቸኳይ ጊዜ እንቅስቃሴ የጀመረው ባለፈው ማክሰኞ መሆኑን አስረድተዋል።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

በአዲስ አበባ ፍልዉሃ አካባቢ ተነስቶ የነበረዉን እሳት አደጋ መቆጣጠሩን የእሳት እና አደጋ ስጋት ኮሚሽን አስታወቀ!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍልዉሃ አካባቢ ተነስቶ የነበረዉን እሳት አደጋ መቆጣጠሩን የእሳት እና አደጋ ስጋት ኮሚሽን አስታወቀ።የእሳት እና አደጋ ስጋት ኮሚሽን የእሳት እና ድንገተኛ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ወንደምአገኝ አልታየ እንደተናገሩት ከሆነ አደጋዉ የተከሰተዉ ከፍልዉሃ አደባባይ ወደ አምባሳደር የሚወስደዉ መንገድ ላይ የሚገኙ ሬስቶራንቶች እና ሌሎች ንግድ ቦታዎች ላይ ሲሆን በአጭር ሰዓት ሊቆጣጠሩት እንደቻሉ ገልፀዋል።ዳይሬክተሩ አያይዘዉም በተደረገው ፈጣን ምላሽ ብዙ ንብረት ማዳን እንደተቻለ ተናግረዋል። ምን ያህል መጠን ያለው ጉዳት ደረሰ የሚለው ገና በማጣራት መሆኑን የተናገሩ ሲሆን የፖሊስ ፎረንሲክስ አባላት የእሳቱን መንስኤ እያጣሩ ነዉ ብለዋል።
Via Addis Zeybe

በኢትዮጵያ የተጀመረው ሕግ የማስከበር ስራ የአገሪቷን አንድነት በጠበቀ መንገድ እንዲካሄድ ሩሲያ አሳሰበች።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫን ዋቢ አድርጎ ስፑትኑክ በድረገጹ ይዞት በወጣው ዘገባ የሩሲያ የረጅም ጊዜ ወዳጅ የሆነችው ጦርነቱ ኢትዮጵያ ግዛቷን እና አንድነቷን በማያናጋ መንገድ እንዲቋጭ ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች።ሚኒስቴሩ አክሎ እንዳለው ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄሮች እና ሀይማኖቶች አገር እንደመሆኗ የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ክልል የአገሪቱን አንድነት እና ዘላቂ ሰላም በጠበቀ መንገድ እንዲመክሩ በመግለጫው ጠቁሟል።
በኢትዮጵያ ከሳምንት በፊት የሰሜን ዕዝ ላይ በህዋሃት የደረሰበትን ጥቃት ተከትሎ የኢትየጵያ መንግስትም አጸፋውን በሃይል እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ጊዚያዊ የሽግግር መንግስት ማቋቋሙም ይታወሳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ባሳለፍነው አርብ የትግራይ ልዩ ሃይል ህገመንግስቱን በማስከበር ላይ ላለው የአገር መከላከያ ሰራዊት እጅ እንዲሰጡ የሰጡት የሶስት ቀናት ጥሪ ዛሬ ያበቃል።የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ በትናንትናው ዕለት የአላማጣ ከተማን እና ካባቢውን ሙሉ ለሙሉ ከትገራይ ልዩ ሃይል መቆጣጠራቸው ይታወሳል።
Via Ethio FM

“የፌዴራል መንግስቱ እና ህወሓት ለድርድር ሊቀመጡ ከሚችሉበት የህግ እና የሞራል እኩሌታ ላይ አይደሉም”-የፌዴሬሽን ምክር ቤት
ከህወሓት ጋር ለድርድር መቀመጥ የፌዴራል መንግስት በህገ መንግስቱ መሰረት የተሰጠውን ኃላፊነት ማቅለል ነው ሲል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አሳሰበ፡፡ምክር ቤቱ የፌዴራል መንግስቱን ጣልቃገብነት በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል፡፡
ህወሓት በሃገሪቱ መከላከያ ሰራዊት እና በአጎራባቹ የአማራ ክልል ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ህግና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን እንዲያስከብር ለፌዴራል መንግስቱ ጣልቃ የሚገባበትን ፍቃድ መስጠቱን ያስታወቀው ምክር ቤቱ አንዳንዶች ህግ የማስከበሩን ዘመቻ እንደ እርስበርስ ጦርነት በመቆጠር ለድርድር ጥሪ አቅርበዋል ብሏል፡፡
ሆኖም ከህወሓት ጋር ለድርድር መቀመጡ “የፌዴራል መንግስቱ ህገ መንግስቱንና የፌዴራል ስርዓቱን ለመጠበቅ የተሰጠውን ህገ መንግስታዊ ኃላፊነት ማቃለል” እንደሆነም ነው ያስታወቀው፡፡
በብረት የታገዘ አመጽ መቀሰቀስ፣ ከሌሎች ክልሎች ጋር ያሉ ችግሮችን ሰላማዊ ባልሆኑ መንገዶች ለመፍታት መሞከር እና የፌዴራሉን የሰላምና የጸጥታ ሁኔታ ማናጋት የፌዴራል መንግስቱ በክልሎች ጣልቃ እንዲገባ ሊጋበዝ የሚችልባቸው ህገ መንግስታዊ ምክንያች እንደሆኑም ምክር ቤቱ አብራርቷል፡፡
በትግራይ ክልል የነበረውን ሰራዊት ያጠቃውና የዘረፈው ህወሓትም እነዚህኑ የፌዴራል መንግስቱ ጣልቃ እንዲገባ የሚጋበዝባቸውን ምክንያቶች ያሟላ ህገ ወጥ ድርጊት መፈጸሙንም ነው የገለጸው፡፡
ህገ መንግስታ ስርዓቱን አደጋ ላይ ከጣሉት ከእነዚህ አካላት ጋር መደራደሩ የፌዴራል መንግስቱን ኃላፊነት ማቃለል ይሆናል ሲልም በአጽንኦት ገልጿል፡፡“ይህ እንዲሆን የሚፈቅደው ህገ መንግስት በራሱ በህወሓት ንቁ ተሳታፊነት ተዘጋጅቶ መጽደቁንም ማስታወሱ ይጠቀምማል”ም ነው ምክር ቤቱ ያለው፡፡በዚህ ምክንያት ህወሓት የፌዴራል መንግስቱን ጣልቃ ገብነት ሊሞግት አልያም እንደራደር ሊል የሚችልበት አግባብ እንደሌለም አስቀምጧል፡፡
በተጨማሪም የፌዴራል መንግስቱ ለድርድር ይቀመጥ ማለቱ ለህወሓት ህጋዊና ሞራላዊ የእኩልነት ደረጃን እንደመስጠት ተደርጎ እንደሚቆጠርም ነው ያስቀመጠው፡፡ሊደራደሩ የሚችሉበት “ህጋዊም ሞራላዊም አግባብ የለም”ም ብሏል፡፡የፌዴራል መንግስቱ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመታደግ እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡ይህ ሳይሆን ቀርቶ የፌዴራል መንግስቱ ህገ መንግስታዊ ስልጣኑን ተጠቅሞ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመታደግ ካልቻለ እና መደራደርን ከመረጠ ወደ ፊት እጅግ አደገኛ ሁኔታ እንደሚገጥመው አሳስቧል፡፡ይህ ማለት ሌሎች የፌዴሬሽኑ አካል የሆኑ የክልል መንግስታት የፌዴራሉን መንግስት ያለ ማንም ከልካይነት መገዳደር እንዲችሉ መፍቀድ ማለት እንደሆነም ነው ምክር ቤቱ “ሊታለፍ የሚችል” እንዳልሆነ በመጥቀስ ያሳሰበው፡፡
Via Al ain

በትግራይ ክልል ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ ክልሉ በጊዜያዊ አስተዳድሩ መመራቱ እንደሚቀጥል የፌደራል ዲሞክራሴ ግንባታ ማዕከል አስታወቀ።
በትግራይ ክልል እየተወሰደ ያለው ህግን የማስከበር ስራ እንደተጠናቀቀ ክልሉ በጊዜያዊ አስተዳድሩ ከተመራ እና ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ ከተፈጠረ በኋላ ምርጫ እንደሚካሄድም ማዕከሉ ገልጿል።በክልሉ ህግ የማስከበር ስራው ሲጠናቀቅ ክልሉ ምን ይሆናል? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው።
በጉዳዩ ላይ የፌደራል ዲሞክራሴ ግንባታ ማዕከል አስተባበሪ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የትግራይ ክልል ህዝብ ለነጻነት ፤ለሰላም እና ራስን በራስ ለማስተዳደር ለእኩልነት በጣም ከፍተኛ ዋጋ የከፈለ ኩሩ ህዝብ ነው ብለው፡፡ህዝቡን ከህወሃት አምባገነን ቡድን ነጻ የማውጣት እና ህግን የማስከበር ስራው እንደተጠናቀቀ ጊዜያዊ አስተዳድር ይቋቋማል በመቀጠልም በምርጫ የራሱን አስተዳድር እና ክልላዊ መንግስት ያቋቁማል ሲሉ ዶክተር ብቂላ ተናግረዋል።
በህገመንግስቱ መሰረት አንድ ክልልም ሆነ በፌደራል መንግስቱ ውስጥ ስልጣን የሚያያዘው በምርጫ እና በህዝብ ይሁንታ ብቻ እንደሆነም ያስረዳሉ፡፡በትግራይ ክልል አሁን ባለው ህገወጥ አካሄድ ምክንያት ከፍተኛ የሆኑ የህግ ጥሰት በማጋጠሙ ምክንያት በክልሉ ውስጥ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም የፌደሪሽን ምክር ቤት ቀድም ብሉ መወሰኑን አስታውሰዋል።
አሁን ግን ቅድሚያ የህግ ማስከበሩን ሂደት እያከናወንን ከስር ከስር ትግራይ ክልል ውስጥ ጊዜያዊ አስረዳደር ይዋቀራል ብለዋል ዶ/ር ቢቂላ፡፡ባለፈው ሳምንት የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳድርን በተመለከተ የክልሉ ህዝብ እንዲያውቅ የምንፈልገው ይህ አስተዳድር በስራ ላይ የሚቆየው ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ ብቻ መሆኑን ነውም ብለዋል ዶክተር ቢቂላ።
የጊዜያዊ አስተዳድሩ ሃላፊነቶች ህዝቡ መደበኛ አገልግሎቶችን እንዲያገኝ፣እንዲረጋጋ ፣እና ሌሎች መንግስታዊ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ መስጠት እንደሆነም ዶክተር ቢቂላ ገልጸዋል።የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴዕታ የነበሩት ዶክተር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።
[Ethio FM]

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያካሄደ ነው።
ህግ የማስከበሩ ዘመቻ የውስጥ ጉዳያችንን በራሳችን አቅም መልክ ለማስያዝ የሚካሄድ በመሆኑና "አክራሪው ሃይል" በህግ ስር ከመሆኑ በፊት ምንም አይነት የውጭ ሃይል እንቅስቃሴ ስርዓት አልበኝነትን በማንገስ የሀገራችንን ሰላም የማደፍረስ ውጤት የሚያስከትል መሆኑን መንግስት አቋሙን ግልፅ አድርጓል።
ይህንኑ አቋም በማስረዳት የቀጠናው አገራት መንግስት የጀመረውን ህግና ህገ መንግስት የማጽናት ጥረት እንዲደግፉ ለማስቻል የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልዕክት የያዘና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን ወደ ተለያዩ የቀጠናው አገራት ጉብኝት ጀምሯል።ጉብኝቱ ከስድስት በላይ አገራትን የሚሸፍን መሆኑ ታውቋል።
Via FBC

በአዲስ አበባ ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ ከባድ የእሳት አደጋ ደርሷል።
አደጋው የደረሰው ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ ቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ባለ አንድ የቻይና ኮንስትራክሽን ድርጅት መካዘን ላይ ነው።
አደጋው በፍጥነት በመቀጣጠል ላይ ሲሆን የእሳት አደጋ መቆጣጠር ሰራተኞች እስካሁን ቦታው ጋር አልደረሱም።
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
አደጋው የደረሰው ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ ቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ባለ አንድ የቻይና ኮንስትራክሽን ድርጅት መካዘን ላይ ነው።
አደጋው በፍጥነት በመቀጣጠል ላይ ሲሆን የእሳት አደጋ መቆጣጠር ሰራተኞች እስካሁን ቦታው ጋር አልደረሱም።
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በቃፍታ ሁመራ የሱር ኮንስትራክሽን ካምፕ ውስጥ በትህነግ ተከማችቶ የነበረ እና በጸጥታ ኃይሉ በቁጥጥር ስር የዋለ የጦር መሳሪያ
Photo: EBC
@YeneTube @FikerAssefa
Photo: EBC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በአዲስ አበባ ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ ከባድ የእሳት አደጋ ደርሷል። አደጋው የደረሰው ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ ቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ባለ አንድ የቻይና ኮንስትራክሽን ድርጅት መካዘን ላይ ነው። አደጋው በፍጥነት በመቀጣጠል ላይ ሲሆን የእሳት አደጋ መቆጣጠር ሰራተኞች እስካሁን ቦታው ጋር አልደረሱም። Via Ethio FM @YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት አካባቢ የደረሰው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል።
አደጋው የደረሰው ቦሌ ከኤድናሞል 22 ባለው መስመር ቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ባለ አንድ የቻይና ኮንስትራክሽን ድርጅት መጋዘን ላይ ነበር።የከተማዋ እሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ወደ ቦታው ደርሰው አደጋውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ችለዋል።የህንጻው ባለቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት አደጋው ሆን ተብሎ እንዲፈጠር ስለመደረጉ ስጋት እንዳላቸው የተናገሩ ቢሆንም ፖሊስ ትክክለኛውን መንስኤ ለማወቅ በማጣራት ላይ ይገኛል።

ዛሬ ረፋዱ ላይ በትግራይ ክልል ርዕሰ ከተማ መቀሌ ውስጥ የአየር ጥቃት መፈጸሙን የከተማዋ ነዋሪዎችና የቢቢሲ ዘጋቢ ከስፍራው ገለጸ።
ዘጋቢው እንደገለጸው የጦር አውሮፕላን ድምጽ በተሰማበት ጊዜ በነዋሪዎች ዘንድ መደናገጥ ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን፤ በሰዎች ላይ ጉዳት አለመድረሱንም ገልጿል።
የክልሉ ቴሌቪዥንም ሰኞ ኅዳር 07/2013 ዓ.ም ረፋድ 04፡45 ላይ ጥቃቱ መፈጸሙን ያረጋገጠ ሲሆን፤ የጥቃቱ ኢላማም በመቀለ ውስጥ በሚገኘው ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኘው እንዳ ጊዮርጊስ በተባለው አካባቢ መሆኑን ገልጿል።
ከሁለት ሳምንት በፊት ገደማ በተቀሰቀሰው የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊትና በትግራይ ልዩ ኃይል መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ውስጥ መንግሥት በተመረጡ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የአየር ጥቃት እንደሚፈጽም አሳውቆ ነበር።

ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ምኒስትር ደመቀ መኮንን የተገናኙት የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት በድርድር ሊቆም እንደሚገባ ጥሪ አቀረቡ።
ፕሬዝዳንቱ በዛሬው ዕለት ከምክትል ጠቅላይ ምኒስትር ደመቀ መኮንን ተገናኝተው መወያየታቸውን አስታውቀዋል።ሙሴቬኒ በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንዳሉት ውይይታቸው "በኢትዮጵያ ሰላም እና ጸጥታ" ላይ ያተኮረ ነበር። ፕሬዝዳንቱ "ጦርነት በኢትዮጵያ ለአጠቃላይ አኅጉሩ የከፋ ምስል ይሰጣል። ድርድር ተደርጎ ግጭቱ ሊቆም ይገባል። አለበለዚያ ወደ አላስፈላጊ የሰው ሕይወት መጥፋት ይመራል።
ኤኮኖሚውንም ያሰናክላል" ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ውጭ ጉዳይ ምኒስትርነትን የደረቡት ደመቀ ለምን ወደ ዩጋንዳ እንዳመሩ በይፋ የገለጸው ነገር የለም። የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በቅርቡ ባቋቋመው "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ" የተባለ ማኅበራዊ ድረ-ገጽ በኩል "የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በኡጋንዳ ከሕወሐት ጋር በሽምግልና ውይይቶች ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በተለያዩ የዜና አውታሮች የቀረበው መረጃ የተሳሳተ እና በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ግብረ ኃይል ያልተረጋገጠ ነው" ብሎ ነበር።
[DW]

በምዕራብ ወለጋ ዞን 36 የሸኔ ታጣቂዎች ሲደመሰሱ 169 ተማረኩ!
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ 36 የጁንታው ተላላኪ የሸኔ ታጣቂዎች መደምሰሳቸው ተገለፀ።በተወሰደው እርምጃ ከተደመሰሱት በተጨማሪ 169 ታጣቂዎች ተማርከዋል፡፡ከዚህ ባለፈም ለጁንታው ተላላኪዎች ድጋፍ በመስጠት የተጠረጠሩ 96 ሰዎችም ተይዘው ጉዳያቸው እየተመረመረ መሆኑን ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤትን ጠቅሶ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

በትግራይ ክልል መቀሌ ሀራ ገበያ ዓዲ ጉደም ምድር ባቡር ፕሮጀክት በሚጠብቁት ላይ ከተፈጸመ ጥቃት አምልጠው የተረፉ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
Via Federal Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
Via Federal Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
ውጊያ ሸሽተው ወደ ሱዳን የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ20 ሺሕ በላይ ደረሰ!
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት ጦርነት ሸሽተው ወደ ሱዳን የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ20,000 መሻገሩን አስታወቀ።በድርጅቱ መረጃ መሠረት 12,500 ሰዎች ወደ ሐምዳያት ሌሎች 7,500 ደግሞ ወደ አል-ሉቅዲ ተሰደዋል። ወደ ሐምዳያት የተሰደዱ በትግራይ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥቱ ኃይሎች እና የክልሉ መሪዎች ታማኞች ውጊያ መበርታቱን ትናንት እሁድ ለሬውተርስ ተናግረዋል።የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት ተወካይ የንስ ሔሰማን "በአሁኑ ወቅት ኹኔታው እጅግ የከፋ ነው። ባለፉት አምስት ቀናት የደረሱ 15,000 ስደተኞች አሉ። የተ.መ የስደተኞች መርጃ ድርጅት፣የዓለም የምግብ ድርጅት፣ የሱዳን ቀይ መስቀል፣ ሙስሊም ኤይድ እና የተለያዩ ለጋሾች ዕገዛ ማቅረብ ጀምረናል። የተወሰነ ዕርዳታ መስጠት መጀመሩን ማየት ይቻላል። ይሁንና ከዚህ በላይ መሠራት አለበት" ብለዋል።
Via DW

ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ምኒስትር ደመቀ መኮንን የተገናኙት የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት በድርድር ሊቆም እንደሚገባ ጥሪ አቀረቡ። ፕሬዝዳንቱ በዛሬው ዕለት ከምክትል ጠቅላይ ምኒስትር ደመቀ መኮንን ተገናኝተው መወያየታቸውን አስታውቀዋል።ሙሴቬኒ በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንዳሉት ውይይታቸው "በኢትዮጵያ ሰላም እና ጸጥታ" ላይ ያተኮረ ነበር። ፕሬዝዳንቱ…
የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኔ በሕወሓትና የፌደራሉ መንግሥት መካከል ድርድር ያስፈልጋል ሲሉ በቲውተር የለጠፉትን መልዕክት ሰረዙ።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
“ህወሓት ከነባራዊ ሁኔታ በተቃራኒ ሀሰተኛ መረጃዎችን እየነዛ በመሆኑ በተጨባጭ መሬት ላይ ያለውን ነገር መገንዘብ ያስፈልጋል” አምባሳደር ሬድዋን
በኢትዮጵያ ለሚገኙ ዓለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት ተወካዮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እየተሰጠ ነው፡፡ማብራሪያውን እየሰጡ የሚገኙት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሚዲያ ተቋማቱ በህወሓት ሀሰተኛ የፕሮፖጋንዳ መረጃ እንዳይወዛገቡ አሳስበዋል።ከነባራዊ ሁኔታ በተቃራኒ ሀሰተኛ መረጃዎችን ህወሓት እየነዛ መሆኑን በመግለፅ በተጨባጭ መሬት ላይ ያለውን ነገር መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።
ለሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ የሚሰጥ እና የሚያስተባብር የከፍተኛ ባለስልጣናት ኮሚቴ መዋቅሩንም አምባሳደር ሬድዋን ገልፀዋል።ኮሚቴው በአካባቢው ተሰማርቶ ምላሽ መስጠት የሚያስችል መረጃ እያሰባሰበ እንደሆነ መናገራቸውን ፋብኮ ዘግቧል፡፡