YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በታገዱ የጥበቃ አገልግሎት ተቋማት በኩል የተቀጠሩ የተለያዩ ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ድርጅት ሠላማዊ የጥበቃ ሠራተኞች ስራቸውን በአግባቡ መሥራት እንዳለባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በሰጡት መግለጫ ተገቢውን ቅደም ተከተል ሳይከተሉ የተቀጠሩ እና የጥፋት ተልእኮ የያዙ አካላት ከ2012 መጀመሪያ እስካሁን ድረስ በባንኮችና በሌሌች ተቋማት ላይ 169 ዘረፋዎች መካሄዳቸውን ገልጸዋል።

ባለፈው ሳምንት የታገዱ 14 የጥበቃ አገልግሎት ድርጅቶች አሁን በቀጠሯቸው ሠተኞች ዘንድ በመሄድ እንደተገለሉ በመቁጠር ጥበቃ እንዳይሠሩ የሚያሠራጩት መረጃ የተሳሳተ መሆኑም ተጠቁሟል።

እንደ ምክትል ኮሚሽነሩ ገለጻ በአሁኑ ወቅት ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የጥፋት ተልዕኮ ያላቸው አካላት ሽብር ለመፍጠር የሚሠሩትን ሥራ ለማክሸፍ እየተሠራ ሲሆን እስካሁንም በርካታ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች፣ ቦንብ እና ፈንጅዎች እና ሌሎች መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

በአሁኑ ወቅት በርካታ የጦር መሣሪዎችና ፈንጅዎች በየአካባቢውና በፕላስቲክ ተጥለው ጉዳት እያደረሱ ነው ያለው ኮሚሽኑ ህብረተሰቡ ጥቆማ ማድረግ አንዳለበት አሳስበዋል።በሀገሪቱ በዋና ዋና ኬላዎች እና በአዲስ አበባ ድንገተኛ ፍተሻዎች እንደሚካሄዱ የጠቆመው ኮሚሽኑ ህብረተሠቡም ተባባሪ መሆን እንዳለበት ጥሪ አቅርቧል።

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ህገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች እና መገናኛ ሬዲዮኖች ጨምሮ የተለያዩ እቃዎች ተገኝቶባቸዋል የተባሉ አምስት ተጠርጣሪዎች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር እታገኘሁ ዜና እንዳሉት በካፋ ዞን ጊምቢ እና ገዋታ ወረዳዎች ጊምቢ፣ ኤል ኤች እና ዶክተር አምባቸው የቡና ተክል ልማት ድርጅቶች እንዲሁም በደቡብ ኦሞ ዞን ኛንጋቶም ወረዳ ደግሞ በአቶ ተስፋዬ ሲሳይ የእርሻ ልማት ድርጅት ውስጥ የተከማቹ የተለያዩ የጦር መሳሪዎች ተገኝተዋል።

ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ባለፉት ሁለት ቀናት ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የተገኙት የጦር መሳሪዎች 12 ክላሽንኮቭ፣ አምስት ኤስ ኬ ኤስ ፣ አንድ መስኮቪች ጠብመንጃዎች እና አስር ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተጨማረም ስምንት የአጭር ርቀት መገናኛ ሬዲዮኖች እና 553 ተተኳሽ ጥይቶችም በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ ኢንስፔክተር እታገኘሁ ተናግረዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
የአቶ ልደቱ አያሌው እና የዶ/ር ሁሴን ከድር የዋስትና መብት በአስቸኳይ ሊፈቀድ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ።የክልሉ ሥራ አስፈጻሚና የፍትሕ አካላት የተጠርጣሪዎች የዋስትና መብት መከበሩን እንዲያረጋግጡም ጠይቋል።

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያካሄደ ነው። ህግ የማስከበሩ ዘመቻ የውስጥ ጉዳያችንን በራሳችን አቅም መልክ ለማስያዝ የሚካሄድ በመሆኑና "አክራሪው ሃይል" በህግ ስር ከመሆኑ በፊት ምንም አይነት የውጭ ሃይል እንቅስቃሴ ስርዓት አልበኝነትን በማንገስ የሀገራችንን ሰላም የማደፍረስ ውጤት የሚያስከትል መሆኑን…
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን ናይሮቢ ገባ።

ህግ የማስከበሩ ዘመቻ የውስጥ ጉዳያችንን በራሳችን አቅም መልክ ለማስያዝ የሚካሄድ በመሆኑና "አክራሪው ሃይል" በህግ ስር ከመሆኑ በፊት ምንም አይነት የውጭ ሃይል እንቅስቃሴ ስርዓት አልበኝነትን በማንገስ የሀገራችንን ሰላም የማደፍረስ ውጤት የሚያስከትል መሆኑን መንግስት አቋሙን ግልፅ አድርጓል።

ይህንኑ አቋም በማስረዳት የቀጠናው አገራት መንግስት የጀመረውን ህግና ህገ መንግስት የማጽናት ጥረት እንዲደግፉ ለማስቻል የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልዕክት የያዘና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን ከኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ: በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
በአራዳ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ደጎል አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ፖሊስ ፈንጂ አመከነ በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቀው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን ፖሊስ አሰታወቀ፡፡

በአራዳ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ደጎል አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ፖሊስ ፈንጂ አመከነ በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቀው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሰታወቀ፡፡ዛሬ ህዳር 07ቀን 2013 ዓ.ም በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፒያሳ ደጎል አደባባይ አካባቢ ከሰዓት በፊት በጎዳና ላይ ተዳዳሪ የሆነ አንድ ግለሰብ በማዕድን ውኃ መያዣ ላስቲክ ድራፍት በመግዛት ለመጠጣት ወደ አንድ ጥግ መሄዱ ያጠራጠራቸው በአካባቢው በጫማ መስዋብ ሥራ ላይ ተሰማሩ ወጣቶች ለፖሊስ ባደረሱት ጥቆማ የአካባቢው ፖሊስ እና የፌዴራል ፖሊስ ፈንጂ አምካኝ ባለሙያዎች ቦታው ላይ በመገኘት ተከሰተ የተባለውን ማረጋገጥ መቻላቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር አካባቢያቸውን በንቃት የሚጠብቁ ወጣቶች መበራከታቸው የሚደነቅ መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሠጡትን መረጃ በመንተራስ ፖሊስ ባረጋገጠው መሰረት በላስቲክ የተሞላ ድራፍት ቢራ እንጂ ፈንጂ አለመሆኑን ህብረተሰቡ እንዲገነዘብ ሲል አሳስቧል፡፡ህብረተሰቡ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሚለቀቁ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዳይደናገጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መልዕክት አስተላልፏል፡፡

Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
በማይካድራው ጥቃት 500 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን መንግስት ይፋ አደረገ!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በሰጡት መግለጫ በማይካድራው ጥቃት 500 ሰዎቸ ላይ ጉዳት መድረሱን ይፋ አድርገዋል፡፡የፌደራል መንግስት ሃይሎች በምእራብ በኩል ከህወሓት ሃይሎች ጋር በነበረው ውጊያ፣ የህወሓት ሃይሎች ሲሸሹ በማይካድራ በሚገኙ ሰዎች ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ማድረሳቸውን መንግስት ገልጾ ነበር፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ ጥቃቱ በህወሓት ሃይሎች መፈጽሙን ጠቅሷል፡፡

አምሳደር ሬድዋን በሰሜን እዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን የተናገሩ ሲሆን ምንያህል የሚለውን ግን አልገጹም፡፡ የተገደሉት ወታደሮች ቁጥር ወሳኝነት የለውም፤ ጉዳዩን የሀገር ክህደት ወንጅል ከመሆን አያስቀረውም ብለዋል አምባሳደር ሬድዋን፡፡አምባሳደር ሬድዋን ኡጋንዳ ልታደራድር ነው ለሚለው ዘገባ ምላሽ ሲሰጡ፣ ኢትዮጵያ ኡጋንዳን ለድርድር እንዳልጠየቀችና ህወጦች ወደ ህግ ሳይቀርቡ ድርድር እንደማይኖር ግልጽ አድርገዋል፡፡

Via Al ain
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለጂቡቲው ፕሬዚደንት ኢስማኤል ዑመር ጊሌ አደረሱ!

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለጂቡቲው ፕሬዚደንት ኢስማኤል ዑመር ጊሌ በዛሬው ዕለት (ህዳር 07 ቀን 2013ዓ.ም) አድርሰዋል፡፡

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተላከ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ መልዕክት ያደረሱ ሲሆን በንግግራቸውም 'በህውሓት ጁንታ' ላይ የሚካሄደው ዘመቻ የህግ የበላይነትን በማስከበር፣ ወንጀለኞችን ለፍርድ የማቅረብና ህገ መንግስታዊ ስርዓትን የማስጠበቅ አገራዊ ግብ ያነገበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጂቡቲው መሪ ፕሬዚደንት ኢስማኤል ዑመር ጊሌ ከአገራቸው ጋር በደም፣ በቋንቋና በባህል ብሎም በምጣኔ ሃብት ለተሳሰረችው ኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ያላቸውን ሙሉ ድጋፍ ገልጸዋል፡፡ ፕሬዚደንቱ አክለውም የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ መንግስት ቁልፍና በጎ ሚና የአገሪቱን ሰላም፣ አንድነትና እድገት የሚያስጠብቅ ነው ብለዋል።

ምንጭ: በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 336 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4,213 የላብራቶሪ ምርመራ 336 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ12 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,581 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 264 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 64,130 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 103,056 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ በትናንትናው የአየር ጥቃት ዙሪያ ያለው:

"በሁለት ዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃን አማካኝነት፣ በመቐለ የአየር ጥቃት መደረጉን የሚገልጹ አርዕስት እና አጭር ቪዲዮዎች ወጥቷል። እነዚህ መረጃዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ኃይሉ ሳያረጋግጡ በሕወሐት መረጃ ላይ ብቻ የተመሠረቱ ሐሰተኞች ናቸው፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ በሂደቱ ውስጥ ሰላማዊ ሰዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል የሚለው መረጃም እንዲሁ ሐሰት ነው፡፡

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ በወሳኝ የሕወሕት ዒላማዎች ላይ ከመቀሌ ከተማ ውጭ የታለመ የአየር ጥቃት አካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሕግ የበላይነትን የማስከበር እንቅስቃሴ ዒላማን በጥንቃቄ መምታትን መሠረት ያደረገ ነው።ሕወሐት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃቱን ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ፣ የመከላከያ ሠራዊቱ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስቀረት ሲል ከከተሞች የራቀ ጥቃት ላይ አተኩሯል::"

@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሽያ እጁን ለመከላከያ ሠራዊት በመስጠት ራሱንና ሕዝቡን እንዲያድን የተሰጠው የ3 ቀን የጊዜ ገደብ ስለተጠናቀቀ በቀጣይ ቀናት የመጨረሻው ሕግ የማሰከበር ወሳኝ ተግባር ይከናወናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ሰሌዳቸው፣ በዚህ ጥሪ የተጠቀሙ የትግራይ ልዩ ኃይልና የሚሊሽያ አባላት ለወሰዱት ኃላፊነት የተሞላው ሕዝባቸውን የማዳን ውሳኔ ይመሰገናሉ ብለዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት ቀናት በተደረጉ ፍተሻዎች ከአንድ ሺህ በላይ ሽጉጥን ጨምሮ ቦምብ፣ ፈንጂ፣ የጦር ሜዳ መነጽር እና የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች መያዛቸው ተገለጸ።

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ኮሚሽነሩ በመላ አገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ጸጥታ የማደፍረስ ሙከራዎች ሊደረጉ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ችግሩን ለመከላከልም ጠበቅ ያለ የፍተሻ ስራ እንደሚሰራ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሌላ በኩል በቅርቡ የታገዱ 14 የግል የጥበቃ ድርጅቶች ስር ተቀጥረው የሚሰሩ የጥበቃ ሰራተኞች ስራቸውን በጥንቃቄ እንዲያከናውኑ ኮሚሽኑ አሳስቧል።በታገዱት ድርጅቶች ስር ተቀጥረው የሚሰሩ የጥበቃ ሰራተኞች ውስጥ ሰላማዊ የሆኑትን ሰላማዊ ካልሆኑት የመለየት ስራ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመው፤ ውጤቱ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጥቆማ‼️

በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ዘመዶቻቹ የጠፉባችሁ(የት እንዳሉ የማታውቋቸውን) ሰዎች ደህንነት ለማወቅ ከላይ በተቀመጠው የቀይ መስቀል ስልክ ደውላችሁ መረጃ ማግኘት እንደምትችሉ አለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል።የስልክ መስመሮቹ ከሚደውለው ሰው ብዛት አንፃር ሊጨናነቁ ስለሚችሉ ደጋግመው ይሞክሩ።

ስልክ ቁጥሮቹ:

+251943122207
+251115527110 ናቸው።

Forward በማድረግ ለወዳጅዎ ያጋሩ!
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ከረፋዱ 5:30 ጀምሮ "ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ" በሚል የ2 ደቂቃ ፕሮግራም ይካሄዳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችን ጥሪ የተቀበሉ ኢትዮጵያውያን በያሉበት ሆነው ለ1 ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ አድርገው በመቆም ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ክብር ይገልጻሉ።

ይህ ሲጠናቀቅ በቀጣዩ አንድ ደቂቃ ባሉበት ሆነው ባለማቋረጥ ለ አንድ ደቂቃ ያጨበጭባሉ።

5:33 ደቂቃ ሲሆን መገናኛ ብዙኃን የጥላሁን ገሠሠን ኢትዮጲያ የሚለውን ሙዚቃ ያጫውታሉ።

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ስሙ ኢንፎኔት ኮሌጅ አካባቢ አንድ በርሜል ገንዘብ ወድቆ ተገኘ።

በዚህ ስፍራ በአንድ በርሜል ተጠቅጥቆ መገኘቱን የኢትዮ ኤፍ ኤም ሪፖርተር በአካል ተገኝቶ አረጋግጧል።የተገኘው ገንዘብ የኢትዮጵያ ብር እና ዶላር ሲሆን ገንዘቡን ማን እንደጣለው ያልተተረጋገጠ ሲሆን የአካባቢው ፖሊስ በመኪና ጭኖ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰደውም ሪፖርተሩ አረጋግጧል።በተያያዘ ዜና በዚሁ ወረዳ ጣልያን ሰፈር ልዩ ስሙ ጉሊት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ አዛውንት ቤት ቁጥሩ እስካሁን ያልተረጋገጠ ገንዘብ በማዳበሪያ እና በመዘፍዘፊያ አስቀምጠው ተይዘዋል።አዛውንቷ በልመና ስራ የሚተዳደሩ ናቸው የተባለ ሲሆን የገንዘቡን መጠን ለማወቅ ቆጠራ እየተካሄደ መሆኑን ተሰምቷል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ጅቡቲ ለኢትዮጵያ የግዛት አንድነት መጠበቅ የዐቢይ አህመድ አስተዳደርን “ብቸኛው ዋስትና” አድርጋ አቀረበች!

ህወሓት በትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከፈጸመበት ከዛሬ 15 ቀናት በፊት ጀምሮ የተቀሰቀሰውን ግጭት በአንክሮ እየተከታተልኩ ነው ያለችው ጅቡቲ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት መጠበቅ እንደምትደግፍ አስታወቀች፡፡የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ሁኔታውን የተመለከተ መግለጫን አውጥቷል፡፡

በመግለጫው የጅቡቲ መንግስት ለኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት መጠበቅ “ብቸኛው ዋስትና” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ናቸው የሚል የተረጋገጠ አቋም እንዳለው አስታውቋል፡፡በተጨማሪም ጅቡቲ ይህ ውስጣዊ ያለችው ችግር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አመራር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥሪ አቅርባለች፡፡ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሄ ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት በተፈለገችበት ጊዜ ለመደገፍ የሚያስችል ዝግጁነት እንዳላትም ሪፐብሊካዊቷ ጂቡቲ አስታውቃለች፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
34 የህወሃት የፋይናንስ ተቋማትን ማሳገዱን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል።

ሜጋ ማተሚያ፣ ሱር ኮንስትራክሽን ፣ ጉና የንግድ ስራዎች ፣ ኢፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ መስፍን ኢንደስትሪያል ኢንጂነሪንግ ፣ ሠላም የህዝብ ማመላለሻ ማህበር፣ ኢፈርት ኃ/የተ/የግ ማህበር እገዳው ከተላለፈባቸው መካከል ናቸው።

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ከረፋዱ 5:30 ላይ ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለው በሚል ፕሮግራም ተካሄዷ።

ከተላኩል ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች በጥቂቱ

ፎቶ 📸 ከወሎ ዩንቨርስቲ !
@Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ ከረፋዱ 5:30 ላይ ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለው በሚል ፕሮግራም ተካሄዷ።

📸አዲስ አበባ ሚሊኑክ አደባባይ
@Yenetube @Fikerassefa