YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ወደ ባህርዳር ፣ጎንደርና ላሊበላ የሚደረጉ በረራዎች ተቋረጡ!

ለደህንነት ሲባል ላልተወሰነ ጊዜ ወደ ባህርዳር ጎንደርና ላሊበላ የሚደረጉ በረራዎች ተቋረጠዋል ተብሏል።

Via:- Fidel Post
@Yenetube @Fikerassefa
የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል አስመራ ላይ የሮኬት ጥቃት መፈፀማቸውን ለሮይተርስ የተናገሩ ሲሆን ምፅዋ ላይ ግን ምንም ጥቃት አልፈፀምንም ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሁመራ ከተማ በርካታ የጦር መሳርያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በሁመራ ከተማ ትህነግ ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ቡድኖች ሲጠቀሙ የነበሩባቸውን የተለያዩና ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የጦር መሳሪያዎችን የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ክልል ልዩ ሀይል በቁጥጥር ስር አውሎ ለምእራብ ጎንደር ዞን ሚሊሻ ገቢ ማድረጉን የምእራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መቐለ ባንኮች መከፈታቸው ተሰምቷል።

ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች በባንኮች ላይ የመዘረፍ ምልክት መታየቱን ብሔራዊ ባንክ ካሳወቀ በኋላ መዘጋታቸው ይታወሳል።አሁን ላይ አንድ ሰው ከአካውንቱ ማውጣት የሚችለው የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ቢኖርም መቐለ ያሉ ባንኮች አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ሰምተናል።

Photo: Girmay Gebru
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የሽብር አደጋዎችን ለማድረስ እቅድ የነበረው የህወሀት ቡድን የጸጥታ ሀይሉ ቁጥጥር ሲጠነክርበት በየቦታው የጣላቸው ቦንቦች ሊኖሩ እንደሚችሉ የፌደራል ፖሊስ አሳሰበ።

በመሆኑም ህብረተሰቡ የወደቁ ነገሮችን ሲያይ ለጸጥታ አካላት እንዲጠቁም እና ህጻናትን እንዲጠብቅ ኮሚሽኑ ጥሪውን አቅርቧል።እስካሁን በአዲስ አበባ የህውሀት ቡድን በጣሉት ቦምብ አምስት ህጻናት ጉዳት እንደደረሰባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አረጋግጧል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው በተለምዶ 02 ወይም ካፒቴን ደምሴ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ህፃናት ወድቆ ያገኙት ቦንብ እጃቸው ላይ ፈንድቶ ጉዳት እንደደረሰባቸው አሳውቋል።በዚህም መሰረት አራቱ ህጻናት መጠነኛ ጉዳት አስተናግደው የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ህክምና አግኝተው ወደ ቤተሰቦቻቸው ተቀላቅለዋል ተብሏል፡፡

አንደኛው ህጻን ግን ጉዳቱ ከፍተኛ ስለሆነ በሚኒሊክ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት እንደሚገኝ ነው የተነገረው፡፡የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ እንደተናገሩት የህውሀት ቡድን በአዲስ አበባ ሽብር ለመፍጠር ቢንቀሳቀስም ቁጥጥሩ ሲጠነክርበት ቦምቦቹን በየቦታው እየጣሉ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

እስካሁን እነዚህ ቡድኖች በሁለት ቦታ በጣሉት ቦምብ ስድስት ሰው ላይ ጉዳት ደርሳልም ብለዋል አቶ ጄይላን፡፡የህውሀት የጥፋት ቡድኖች በየቦታው ያሰማሯቸው ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች የጣሉዋቸው ቦምቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ አሁንም ወላጆች ለልጆቻቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ የተጣሉ እና የተቋጠሩ ነገሮችን በሚያገኝበት እና እየጣሉ የሚገኙ ሰዎችን በሚመለከትበት ጊዜ ለፖሊስ ጥቆማ መስጠት አለበት ተብሏል፡፡ማንኛውም የከተማው ነዋሪ የተጣለ ነገር ከማንሳቱ በፊት በ991 እንዲሁም በነጻ የስልክ መስመር 011 111 01 11 ላይ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ደውሎ ማሳወቅ ይችላል፡፡እንደዚሁም በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በ987 ወይም በቀጥታ የስልክ መስመር 011 551 80 00 ላይ ጥቆማቸውን ማድረስ ትችላላችሁ ተብሏል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የሚካሄደው የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሥራ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
ፍትሕ ታሸንፋለች፣ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች የሐሰተኛው አጥፊ ቡድን መጨረሻ ተቃርቧልም ብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ የሕግ የበላይነትን በማስከበር፣ ደግሞም ሀገራችንን በመዝረፍ እና ሰላሟን በማወክ የተሰማሩትን ተጠያቂ በማድረግ፣ ለዘላቂ ሰላም እና ህብረት የሚሆን ጠንካራ መሠረት እንገነባለን ሲሉ ገልጸዋል።
በተለይም ባለፉት ቀናት የታዩት ሁኔታዎች በሕወሓት ውስጥ ያለውን አጥፊ ቡድን ትክክለኛ ማንነት የገለጡ መሆናቸውን አመልክተዋል።በሰብአዊነት እና በሰላም ላይ ወንጀል የፈጸሙ ሁሉ ተጠያቂዎች ይሆናሉ። ፍትሕ እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ባለን ውሳኔ በቆራጥነት እንገሠግሳለን ብለዋል።በሴቶች እና በወንዶች ልጆቿ ጽናት እና ቆራጥነት፣ ኢትዮጵያ ብቻዋን የሕግ የበላይነት የማስከበሩን ዘመቻ በብቃት ታጠናቅቃለች ሲሉም ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በድባጤ ወረዳ፣ ከወንበራ ወደ ቻግኒ ትላንት ህዳር 5 ለሊት በመጓዝ ላይ በነበረ የሕዝብ ማመላሻ አውቶብስ ላይ በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ 34 ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ።

@Yenetube @FikerAssefa
YeneTube
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በድባጤ ወረዳ፣ ከወንበራ ወደ ቻግኒ ትላንት ህዳር 5 ለሊት በመጓዝ ላይ በነበረ የሕዝብ ማመላሻ አውቶብስ ላይ በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ 34 ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። @Yenetube @FikerAssefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በትናንትናው ዕለት አገር አቋራጭ አውቶብስ አስቁመው ንጹሐን ሰዎችን የገደሉ 16 "የሕወሓት የጥፋት ተልእኮ አስፈጻሚ ሽፍታዎች" መደምሰሳቸውን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ።

የጥፋት ኃይሎች በትናንትናው ዕለት ከወምበራ ወደ ግልገል በለስ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ በቡለን እና ድባጤ ወረዳዎች መካከል ቂዶ በሚባል ቦታ አስቁመው ጥቃት መፈጸማቸውን የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገልጿል።በጥቃቱ የንጹሐን ሕይወት ሲያልፍ በዞኑ የዲባጤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ላይ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሐመድ፣ በአካባቢው የሚገኘው የሀገር መከላከያ፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ የክልሉ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ባደረጉት የተቀናጀ እንቅስቃሴ ለንጹሐን ሞት ምክንያት የሆኑ 16 የሕወሓት የጥፋት ተልእኮ አስፈጻሚዎች መደምሰሳቸውን ገልጸዋል።ሌሎች ሁለት ደግሞ በሕይወት መያዛቸውን የገለጹት ኮሚሽነሩ ቀሪዎችን ተከታትሎ የመደምሰስ ሥራ መቀጠሉን አስታውቀዋል።የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙት ደግሞ አካባቢውን የማረጋጋት ሥራ እያካሄዱ መሆኑን ኮሚሽነሩ ለኢዜአ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የመከላከያ ሠራዊት አላማጣንና አከባቢውን "ከጁንታው የህውሀት ቡድን" ነፃ አወጣ። የግራካሶ ተራራና አከባቢውን ለመቆጣጠርም እየገሠገሠ ይገኛል፡

በራያ ቆቦና አከባቢው ህግን ለማስከበር የተሠማራው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊታችን ከአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ጋር በመተባባር ዋጃ ፣ ጥሙጋ ፣ አላማጣና አከባቢውን ከጁንታው የህውሀት ቡድን ነፃ አውጥቶ ተቆጣጥሯል ።

በሰራዊቱ ዝግጁነትና በህዝቡ ደጀንነት የተደናገጠው ደም መጣጩ ቡድን ፣ አከባቢውን ጥሎ የፈረጠጠ ቢሆንም ፣ በአላማጣ ከተማ ታስረው የነበሩ 10 ሺህ ዜጎችን ይዞ ማፈግፈጉን የደቡብ ዕዝ የሰው ሀብትና ሚዲያ ስራዎች አስተባባሪ ኮ/ል ደጀኔ ፀጋዬ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ሠራዊቱ የግራካሶ ተራራና አከባቢውን ለመቆጣጠር እየገሠገሠ እንደሚገኝና በምስራቅ አላማጣ ፣ በጨርጨር አከባቢ የተሠማራው ሠራዊትም ድል እያስመዘገበ እንደሚገኝ ኮ/ል ደጀኔ ፀጋዬ ገልፀዋል።

እንዲሁም ፅንፈኛው ቡድንን በዜጎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ ለመቆጣጠር ሠራዊታችን በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተራመደ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
ነዋሪዎችም ፅንፈኛውና ዘራፊው ቡድን አካባቢውን ጥሎ በመሸሹ ደስታቸውን በተለያየ መንገድ በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

የአማራ ልዩ ሀይል አዛዥ ፣ ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን በበኩላቸው ፣ ህብረተሰቡ ሳይጎዳ አካባቢውን ለመቆጣጠር መቻሉን ተናግረዋል።

Via FDRE Defense Force
@Yenetube @Fikerassefa
ህወሓት “የወልቃይት ስኳር ፋብሪካና የተከዜ ግድብ ተደብድቧል በጦር ጀት ተደብድቧል” በማለት ያናፈሰው ወሬ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ መሆኑን የስኳር ኮርፖሬሽን የፕሮጀክት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና ፣የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አስታወቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 399 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5,002 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 399 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 102,720 ደርሷል።በሌላ በኩል 191 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 63,866 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የህወሓት ጦር ከአላማጣ ተሸንፎ ሲባረር በእስር ላይ የነበሩ 10,000 ያህል ሰዎችን ይዞ ሸሽቷል ተባለ።

የመከላከያ ሰራዊት የራያ የአላማጣ ከተማን ከሕወሓት ነፃ አውጥቷል ሲልም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል።የከተማዋ ነዋሪዎች ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በላይ የሆኑ በርካታ የአካባቢው ወጣቶች በአጥፊው ኃይል ለጦርነት እንዳይመለመሉ በመፍራት አካባቢውን ለቀው መሰደዳቸውን ተናግረዋል ተብሏል።መከላከያ ሠራዊት አላማጣን በቁጥጥር ስር ማዋሉ፣የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራው በሰላማዊ ዜጎች ላይ ተጽዕኖ እንዳያስከትል አስፈላጊው ጥንቃቄ ታክሎበት፣በውጤታማ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ያሳያል ሲል መግለጫው ተናግሯል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በኤርትራ ላይ የሰነዘረውን የሚሳኤል ጥቃት አሜሪካ አወገዘች።በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር የሆኑት አምባሳደር ቲቦር ናዥ ዛሬ በማህበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ ሕወሓት በኤርትራ ላይ የሰነዘረውን ምክንያታዊ ያልሆነ ጥቃት አሜሪካ በጽኑ ታወግዛለች “ ብለዋል። ሕወሃት በትግራይ ያለውን ውጊያ አለማቀፋዊ ለማድረግ የሚያደረገውም ጥረት ተቀባይነት የሌለው እና የሚወገዝ መሆኑን ሚስተር ቲቦር ናዥ አሳስበዋል።

የሲቪሎች ደህንነት እንዲጠበቅ፣ሰላም እንዲመለስም ጥሪ አቅርበዋል።

@Yenetube @FikerAssefa
በጎንደር ከተማ አዘዞ ኮንደሚኒየም ነዋሪዎች በአሁኑ ሰአት ከአካባቢዉ እየለቀቁ ነዉ!

በአማራ ክልላዊ መስተዳደር ጎንደር ከተማ በተለመዶ አዘዞ ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪዎች በአሁኑ ሰአት የሮኬት ጥቃት ይደርሳል  በሚል ፍራቻ ከአከባቢው እየለቀቁ ነዉ።አዲስ ዘይቤ አገኘሁት እንዳለው መረጃ ከሆነ በአሁኑ ሰአት አብዛኛው ነዋሪ በምሽት ከቦታዉ እየለቀቀ እንደሆነና ነዋሪዎቹም መንግስት መረጃ በአፋጣኝ መስጠት አለበት ብለዉ እየጠየቁ ነዉ።

የኮንደሚኒየሙ መገኛ ለመከላኪያ ሰራዊት ካምፕ አቅራብያ በመሆኑ ነዋሪዉ ቤተሰቡን እና ጓዙን ሸክፎ ወደ መሀል ከተማ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።አዲስ ዘይቤም በጉዳዩ ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ወደ ከተማዉ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ቻላቸዉ ዳኘዉ  ጥሪ አድርጋ ነበር።እርሳቸውም በአከባቢው የተፈጠረዉን ሁኔታ አምነው "አካባቢው እንዳይታወክ እና ዝርፊያ እንዳይፈጸም  የፀጥታ አካላትን አሰማርተናል" ብለዋል።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ እና የዜና አውታሮች የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በኡጋንዳ ከሕወሓት ጋር በሽምግልና ውይይቶች ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ የተነገረው ወሬ የተሳሳተ መሆኑን እወቁት ተብሏል።

የቀረበው መረጃ የተሳሳተ እና በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ግብረ ኃይል ያልተረጋገጠ ነው መባሉን ሰምተናል።

የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል የሕግ የበላይነትን ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሠራ ነው ተብሏል፡፡

መገናኛ ብዙሀን እንደ መሠረታዊ የጋዜጠኝነት አሠራር የኢትዮጵያን የሕግ የበላይነትን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ሁልጊዜ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ኃይል ፕሬስ ሴክሪታሪያት በኩል እንዲያረጋግጡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ተናግሯል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

አደጋዉ ከደቂቃዎች በፊት ሸራተን ሆቴል ጫፍ ላይ ከዘውዲቱ ሆስፒታል አጠገብ ባለ አንድ ካፌ ላይ የተነሳ ሲሆን አደጋው በመዛመት ላይ ይገኛል።

የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ወደ ቦታው አቅንተዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ጀዋር መሀመድ እና በቀለ ገርባ ታመው ህክምና በመከልከላቸው የረሃብ አድማ ላይ ናቸው ብሏል OMN!

አቶ ጀዋር መሀመድ ስለታመመ አስቀድሞ ፍ/ቤት ባዘዘው መሰረት የግል ሃክሞቹ እንዲመጡለት መልዕክት አስተላልፎ ነበር። ይሁንና ሁለት ሃኪሞቹ በትናንትናው ዕለት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቢመጡም ማረሚያ ቤቱ ከ 2 ሰዓት ተኩል በላይ ካቆያቸው በኋላ ከልክሎ መልሷቸዋል።

አቶ በቀለ በበኩላቸው ከአራት ቀን በፊት እግራቸው አብጦ እንደሚያማቸው ቢያሳውቁም እስከዛሬ ህክምና አላገኙም።ከዚህ የተነሳ ዛሬ ከቤተሰብ ምግብ አልተቀበሉም የረሃብ አድማ ላይ በመሆናቸው ከክፍላቸው ወጥተው ቤተሰብና ጠያቂዎችን አላናገሩም። በእስር ቤቱ ያለው የህክምና ሆኔታ አጠቃላይ የታሳሪዎቹ አያያዝ እያሽቆለቆለ ብሏል የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) በዘገባው።

@YeneTube @FikerAssefa