YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ትናንት ማታ በባህርዳር ስለነበረው ፍንዳታ!

ትናንት ምሽት ወደ ባህርዳርና ጎንደር ከተሞች ሮኬት ተተኩሶ እንደነበር ተነገረ። በዚህም የአየር ማረፊያ አካባቢዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።ለዚህም "የህወሓት ጁንታ" ያለውን የመጨረሻ መሳሪያዎች እየተጠቀመ ይገኛል ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ክፍል አስታውቋል። በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ ነውም ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የድሬዳዋ ነዋሪዎች አንድነት ፓርቲ መስራች ከእስር ተፈቱ!

እንደ አዲስ አበባው ባልደራስ የድሬዳዋ ነዋሪዎችን በከተማ ደረጃ ለማታገል የተቋቋመው ድሬዳዋ አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ መስራች ከ4 ወራት እስር በኋላ በዛሬው ዕለት መፈታታቸው ተገለጸ። የድሬዳዋ ነዋሪዎች አንድነት ፓርቲ የተሰኘው ፓርቲ መስራች አቶ ሲሳይ አየለ የታሰረው በፌስቡክ ገጻቸው ካወጡት መረጃ ጋር በተያያዘ ነው።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በማይካድራ የተፈጸመውን ሰብአዊ ቀውስ በአፋጣኝ ለማጣራት የምርመራ ቡድን ወደ ቦታው ማሰማራቱን ገለፀ።

ኮሚሽኑ በትናንትናው ዕለት በትግራይ ክልል እተካሄደ ስላለው ጦርነት እና የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ሁኔታ ላይ ባወጣው መግለጫው እንዳለው በግጭቱ በተሳተፉ ማንኛውም ወገኖች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በመመርመር እና ማስረጃ በማሰባሰብ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ገልጿል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
"ለአገር መከላከያ ሠራዊት ክብር እቆማለሁ" በሚል መሪ ቃል ለመከላከያ ሰራዊት ክብር የመግለጽ መርሓ-ግብር ሊከናወን ነው!

"ለአገር መከላከያ ሠራዊት ክብር እቆማለሁ" በሚል መሪ ቃል የፊታችን ማክሰኞ ኅዳር 8/2013 ሁሉም ኢትዮጵያዊ " የአንድ ደቂቃ በየቤቱ እና በየመስሪያ ቤቱ በር ላይ ቀኝ እጁን በደረት በማድረግና በግራ እጅ ባንድራ ይዞ በመቆም ለመከላከያ ሰራዊት ክብር የመግለጽ መርሓ-ግብር እንደሚከናወን ተገለፀ።

ዛሬ ጠዎት ኅዳር 5/2013 በብሄራዊ ቲያትር ቀደምትና እውቅ የአገራችን የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት በተሰጠ መግለጫ እንደተገለጸው የአገር መከላከያ ሰራዊትን በኪነ-ጥበብ ሥራዎች የኋላ ደጀን ሆኖ ለመደገፍ ያለመ "ጥበብ ለአገር ክብር" የተባለ ግብረ ሀይል መቋቋሙ የተገለፀ ሲሆን የፊታችኝ ማክሰኞ የሚደረገዉም መረሃ ግብር የዚሁ ግብረ ኃይል አንድ አካል እንደሆነ ታውቋል።

አገራዊ ክብር የመግለጽ መርሓ-ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) በተገኙበት በአንድነት ፓርክ ከቀኑ 5:30 ላይ እንደሚጀመርም ተገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ በሌሎች ቀናት ለአንድ ደቂቃ በክብር እጅ የመንሳት ቀን፣ የማጨብጨብ፣ የመዝሙር፣የሙዚቃ ኮንሰርት የገቢ ማሰባሰቢያና የመአድ ማጋራት መርሓ-ግብሮች እንደሚከናወኑም ታውቋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ህዳር 04/2013 ምሽት በጎንደር የተሰማው ከባድ ፍንዳታ ሁኔታ

በትላንትናው እለት ሌሊት በጎንደር ከተማ በተለምዶ አዘዞ በሚባለው አካባቢ ከባድ ፍንዳታ የተሰማ ሲሆን አካባቢው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት 33ኛ ክፍለ ጦር እንዲሁም የጎንደር አፄ ቴዎድሮስ የአየር ማረፍያ የሚገኙበት እንደሆነ ይታወቃል።

ፍንዳታው በአካባቢው ላይ የተሰማው አርብ ህዳር 4፣ 2013 ከምሽቱ አምስት ሰዓት ከሩብ ደቂቃ ጀምሮ የተከሰተ ሲሆን በፍንዳታው አካባቢ ከአምስት ኪ.ሜ ርቀት በሚገኙ ቤቶች ላይ በግልፅ የሚታይ የንዝረት እንቅስቃሴ እንደተከሰተ በስፍራው የተገኘው የአዲስ ዘይቤ ባልደረባ ለማረጋገጥ ችሏል። በዚህም ንዝረት የተነሳ በአየር ማረፍያው ህንፃ መስታውቶች መሰባበራቸውን የአይን እማኞች ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።

በፍንዳታው ወቅት በአካባቢው የነበሩ የአይን እማኞች ለአዲስ ዘይቤ ባልደረባ እንደገለፁት ከሆነ በራሪ ጀት ለመሳፈር በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ስድስት ኮማንዶ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በተለይም በአካባቢው በተለምዶ ቪአይፒ በተሰኘው ቦታ ላይ መጠነኛ ጉዳት እንዳተከሰተ ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።በአሁኑ ወቅት ወደ አየር መንገዱ ማንኛውም ግለሰብ እንዳይጠጋ በመንግስት አካላት የተከለከለ ሲሆን የተቋሙ ሰራተኞች ሁኔታዎች እስከሚጣሩና እስከሚስተካከሉበት ወቅት ደረስ ወደ ስራ ገበታቸው እንዳይመለሱ ውሳኔ እንደተላለፈ ለመረዳት ተችሏል።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግጭት ውስጥ የሚገኘው ህወሓት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ጥቃቱን መፈጸማቸውን ለትግራይ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው የፌደራል መንግሥት አየር ኃይል በተለያዩ የትግራይ ከተሞች ላካሄደው የአየር ጥቃት "አጸፋዊ ምላሽ" በባሕር ዳርና ጎንደር አየር ማረፊያዎች ላይ "የሚሳኤል ጥቃት" መፈጸሙን አረጋግጠዋል።

ከዚህ ቀደምም የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ኤኤፍፒ "ትግራይን ለማጥቃት የሚውል አየር ማረፊያ. . . የጥቃት ዒላማ እንደሚሆኑ" እንደተነገረ ዘግቦ ነበር።

ትናንት አርብ ማታ ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ በባሕር ዳር ከፍተኛ የተኩስና የፍንዳታ ድምጽ መሰማቱን በስፍራው የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ የገለጸ ሲሆን፤ የክልሉ መንግሥት ስለክስተቱ መግለጫ እስከሚያወጣ ድረስ በከተማው ነዋሪ ዘንድ ግራ መጋባት ተፈጥሮ እንደነበር ገልጿል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ሸዋ ዞን ለጥፋት ተልዕኮ የተዘጋጀ የተለያየ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ!

በምዕራብ ሸዋ ዞን አስር ወረዳዎች ለጥፋት ተልዕኮ የተዘጋጀ የተለያየ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደንብ ልብስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 35 ግለሰቦች መያዛቸውም ተገልጿል።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራና ፍትህ አሰጣጥ ሀላፊ ኮማንደር ኑረሳ አካና ÷የጦር መሳሪያዎቹ የተገኙት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ሰሞኑን በወረዳዎቹ የተለያዩ ቤቶች በተደረገ ፍተሻ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም በቁጥጥር ስር ከዋሉት የጦር መሳሪያዎች መካከል ዘጠኝ ሽጉጥ፣ አራት ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 16 ቦምብ፣ ሁለት ፈንጂዎች፣ ከአምስት ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶችና አስር ገጀራዎች እንዲሁም 22 የቀድሞ የኦሮሚያ ፖሊስ እና ሌሎች የደንብ ልብሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስረድተዋል።

ሃላፊው ህብረተሰቡ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለጸጥታ አካላት በመጠቆም፣የአካባቢውን ሰላም ነቅቶ በመጠበቅና ወንጀልን በጋራ ለመከላከል ላደረገው ትብብር ምስጋና አቅርበው አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ታጣቂዎች በንፁሃን ላይ ተኩስ መክፈታቸው ተሰማ፡፡

ከአርብ ምሽት ጀምሮ በታጣቂዎች የተከፈተውን ተኩስ የአካባቢው ነዋሪዎች ሲከላከሉ መቆየታቸውን አሐዱ ቴሌቪዥን ከስፍራው እማኞች አረጋግጫለው ብሏል፡፡ከምሽቱ ተኩስ በተጨማሪ ኅዳር 5 ጠዋት ከወንብራ ወደ ባሕር ዳር ተሳፋሪዎችን ይዞ በመጓዝ ላይ ያለ ተሽከርካሪ መታገቱንም ነዋሪዎቹን ገልፀዋል፡፡"በስፍራው ያለው የመከላከያ ኃይል ከታጣቂዎቹ ጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ አስቸኳይ እና የተጠናከረ እርምጃ ያስፈልጋል" እንዲኖር ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡

ከሐሙስ ጀምሮ የሕወሓት ተልዕኮ ያላቸው ቡድኖች በክልሉ ጥቃት ፈፅመዋል ያለው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ ዛሬ ኅዳር 5 ደግሞ የወረዳ አስተዳዳሪው ደበሊ ባልጋፎን ጨምሮ የፀጥታ አካላት በታጣቂዎች መቁሰላቸውን አስታውቋል፡፡ታጣቂዎቹ ባገቱት ተሽከርካሪ ውስጥ የተሳፈሩ ተሳፋሪዎች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውንም የክልሉ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መለሰ በየነ ለአሐዱ ቴሌቪዥን የገለፁ ሲሆን ቁጥሮች ተጣርተው ይፋ እንደሚደረጉም አክለዋል፡፡በአሁኑ ሰዓት መከላከያ ሰራዊቱ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡መተከል ዞንን ከፀጥታ ቀውስ ለማውጣት በሚል በአገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፀጥታ መዋቅሮች የሚመራ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ ወደ ሥራ ከገባ ወራት እየተቆጠሩ ነው።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
በልዩ ልዩ ምክንያት ርችት መተኮስ ተከለከለ!

በልዩ ልዩ ምክንያት ርችት መተኮስ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታወቀ፡፡ሕብረተሰቡ ለኮሚሽኑ ስራ ስኬታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቆ አንዳንድ ግለሰቦችና ተቋማት ልዩ ልዩ ፕሮግሞችን ምክንያት በማድረግ ርችት እየተኮሱ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ካለችበት የፀጥታ ሁኔታ በምንም አይነት ምክንያት ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን አሳስቦ ይህንን መልእክት በመተላለፍ ርችት ሲተኩስ የተገኘ ግለሰብ በህግ የሚጠየቅ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጥብቅ አሳስቧል፡፡ ሕብረተሰቡ ለህግ መከበር እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቦ ትብብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa
በድሬዳዋ የጥፋት ተልዕኮ እንዳላቸው የተጠረጠሩ 18 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።

ድሬዳዋን ከጎረቤት ሀገራት የሚያገናኙትን በሮች ከሽብርተኞች ለመከላከል ከክልሎች ጋር በመቀናጀት እየተሰራ እንደሚገኝም ተመልክቷል።የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነር አለሙ መግራ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፤ በህዝብ ጥቆማ መሰረት ሰሞኑን በተለያዩ ቀናት በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።በእነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይ ዘጠኝ ሽጉጦች እንዲሁም ጥይቶች፤ የተለያዩ ሀገራት ፓስፖርቶችና ሰነዶች እንደተገኘባቸው አስታውቀዋል።በተጨማሪም የጥፋት ቡድኑን ለመደገፍ በለገሀሬ እና ጀርባ በሚባሉ ሰፈሮች ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር የሞከሩ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

እንደ ኮሚሽነር አለሙ ገለጻ ÷ድሬዳዋን ከህወሃት ጁንታና ሌሎች ሽብርተኛ ቡድን ተላላኪዎች ለመጠበቅ ምክር ቤት ተዋቅሮ ከኢሚግሬሽን፣ ኤርፖርት፣ ጉምሩክ፣ ፌዴራልና ከተማ ዋና ዋና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ጋር የጠበቀ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል።ከፌደራል ፖሊስና መከላከያ ሠራዊት እንዲሁም ከሚሊሻ ጋር ተመሣሣይ ሥራ እየተሰራ ይገኛል ያሉት ኮሚሽነሩ÷ በተለይ ማህበረሰብ ዓቀፍ የፖሊስ ተቋማትና ወጣቶች ለአካባቢው ፀጥታ መጠበቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆናቸውን አስረድተዋል።ድሬዳዋን ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያገናኛት መሠረተ ልማቶች፣ የወጪና ገቢ ንግድ መስመሮችን ያገናዘበ የመከላከል ሥራ ከምስራቅ ተጎራባች የፀጥታ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑንም ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።ከሲቲ ዞን፣ ሐረሪ ክልልና፣ ከምስራቅና ከምዕራብ ሐረርጌ ኦሮሚያ ዞኖች ጋር የጋራ እቅድ በማውጣትና ተግባራቱን በመገምገም ውጤታማ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የመከላከያ ሰራዊትና እና የአማራ ልዩ ኃይል አየር ማረፊያ ሰፈር የተባለውን አካባቢ እና ዋጃ ጥሙጋን የተቆጣጠረ ሲሆን አሁን ላይ መሆኔ የተባለውን አካባቢ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ውጊያ ላይ ይገኛል እንደ አማራ ክልል ልዩ ሃይል ዘገባ።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ኃይል ራያ አላማጣን ከትህነግ ቡድን ለማስለቀቅ በነበረው ውጊያ ከተያዙ ቦታዎች ባሻገር ቁጥራቸው በርከት ያለ የትህነግ ልዩ ኃይልና ሚሊሻዎች የተመቱና ቁስለኛ ሲሆኑ በሌላ በኩል እድል የቀናው የትህነግ ሰራዊት እግሬ አውጭኝ ብሎ እየፈረጠጠ ነው ሲል ዘገባው አክሏል። ቁጥሩ ቀላል የማይባል የትህነግ ሰራዊት ደግሞ ለመከላከያ እና ለአማራ ልዩ ኃይል እጃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ እንደ ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የወደቀ ቦንብ እጃቸው ላይ የፈነዳባቸው ህፃናት ጉዳት ደረሰባቸው!

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው በተለምዶ 02 ወይም ካፒቴን ደምሴ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ህፃናት ወድቆ ያገኙት ቦንብ እጃቸው ላይ ፈንድቶ ጉዳት እንዳደረሰባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ህግን ለማስከበር እየተሰራው ባለው ስራ የተደናገጡ የህውሃት ጁንታ ብድን ተላላኪዎች ሆን ብለው በሰዎች ላይ ገዳት ለማድርስ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪዎችን በየቦታው እየጣሉ ስለሆነ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኮሚሽኑ መልእክቱን በድጋሚ አስተላልፏል፡፡

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 564 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6,343 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 564 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 102,321 ደርሷል።በሌላ በኩል 104 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 63,675 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት የነበራቸው 14 የአልሸባብ እና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።

አልሸባብ እና አይ ኤስ አባሎቻቸውን ወደ አዲስ አበባ እና የተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመላክ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት በመፈፀም በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳይ ለማድረስ እንዲሁም የሀገሪቷን በጎ ገፅታ ለማበላሸት በዝግጅት ላይ እንዳሉ ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን 14 የሽብር ቡድኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ አባላትን በመመለመል፣ የሽብር እቅድ በማውጣትና ኢላማዎችን በመለየት እንዲሁም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ጥቃቶችን ለመፈጸም ስምሪት ወስደው እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የነበሩ ተጠርጣሪ የሽብር ቡድኖቹ አባላት እንዲያዙ ተደርጓል።የመግለጫው ሙሉ ቃል ከታች ተያይዟል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ከባድ ፍንዳታ ተሰምቷል። ይህም 3 ቦታ ላይ የተሰማ ሲሆን አንደኛው በአውሮፕላን ጣቢያ አካባቢ ሳይሆን እንዳልቀረ የተለያዩ ምንጮች ዘግበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ከባድ ፍንዳታ ተሰምቷል። ይህም 3 ቦታ ላይ የተሰማ ሲሆን አንደኛው በአውሮፕላን ጣቢያ አካባቢ ሳይሆን እንዳልቀረ የተለያዩ ምንጮች ዘግበዋል። @YeneTube @FikerAssefa
#Update

የቢቢሲው ጋዜጠኛ ሞውሊድ ሃጂ አብዲ ኤርትራ አስመራ ከተማ ምሽቱን በ3 ሚሳኤል መመታቷን ገልጿል።

ጋዜጠኛው የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር እና አስመራ ኤርፖርቱ አቅራቢ ጥቃት ሳይደርስ እንዳልቀረ ፅፏል።

ኤርትራን አስመልክተው የሚዘግቡ ሚዲያዎችም "አስመራ" ውስጥ ከፍተኛ ፍንዳታ መሰማቱ ፤ በኃላም ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ እንደነበር ዘግበዋል።

#Eriterian press
@Yenetube @FikerAssefa
ለማስታወቂያ ጊዜ የተደረገ ታላቅ ቅናሽ | ይዘዙ ይጠቀሙ
ከማንኛውም ሬስቶራንት
-የሀበሻ ምግብ
-መጠጦች
-ባስ ትኬት
-ፒዛ
-በርገር
-እንዲሁም ጣፋጭ ኬኮች ሲያዙ ከዴሊቨሪ ላይ 30% ቅናሽ ማድረጋችን ለማሳወቅ እንወዳለን።
0952626262 // 0462126282

#DiscountPrice 0-3km - #20birr 3-6km #40km
#DeliveryHawasssa #DeliveryDiscount