በአዲስ አበባ “የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን” ያሰማራቸው የተባሉ 242 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ!
በአዲስ አበባ ከተማ ትርምስ ለመፍጠር “የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን” ያሰማራቸው 242 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንዳሉት ግለሰቦቹ ቦምብ፣ ፈንጂ፣ ላውንቸርና የተለያዩ ተተኳሽ ጥይቶች ተገኝተውባቸዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

በአሶሳ ከተማ ዛሬ ረፋድ ለሽብር ስራ ሊውል ይችላል በሚል ተጠርጥሮ በፖሊስ የተያዘው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ቆጠራው እስካሁን አልተጠናቀቀም።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱላዚዝ ሙሀመድ እንደተናገሩት የህወሀት ቡድን ተላላኪዎች በክልሉ ከፍተኛ የጥፋት ሴራ ደግሰው ቢንቀሳቀሱም አስቀድመን እርምጃ በመውሰዳችን የታሰበውን ሴራ አክሽፈናል ብለዋል፡፡በክልሉም የተለያዩ ከተሞች የሽብር ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ግለሰቦች ዛሬ ረፋድ በአሶሳ ከተማ በሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ መያዙ የተገለጸ ሲሆን ትክክለኛውን የገንዘብ መጠን ለማወቅ ቆጠራ ላይ መሆናቸውንም ኮሚሽነር አብዱልአዚዝ ተናግረዋል።
ይህ ገንዘብ ከመቀሌ መላኩን የተናገሩት ኮሚሽነሩ የህወሃት ቡድን በውጊያ ላይ ሆኖም ሽብር ከመፍጠር ወደ ኋላ እንደማይል ማሳያ ነውም ብለዋል።ተጠርጣሪዎቹ በህግ ጥላ ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ለሽብር ተልዕኳቸው ማስፈጸሚያ በሚል ወደ አሶሳ የተላከው እና በፖሊስ እጅ የሚገኘውን የገንዘብ መጠን ለማወቅ ከዛሬ ረፋድ ጀምሮ ቆጠራ ላይ ነን ቆጠራው ሰልችቶናል ብለዋል።እስካሁን ባለን ቆጠራ እና ግምት የተያዘው ገንዘብ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ሊሆን እንደሚችል እና ቆጠራው እንዳለቀ መረጃውን ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን ሲሉም ተናግረዋል።
Via Ethio FM

YeneTube
የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ በመጥለፍ የተጠረጠሩ 7 የጄኔራል መኮንኖች ፍርድ ቤት ቀረቡ! የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛን በመጥለፍ እና የመገናኛ ሥርዓት እንዲቋረጥ በማድረግ፣ ዕዙ በጁንታው የሕዋሓት የጥፋት ቡድን ጥቃት እንዲፈፀምበት ሲያመቻቹ ተገኝተዋል በሚል የጠረጠራቸውን 7 የጄኔራል መኮንኖች ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቧል። ጄኔራል መኮንኖቹ በሀገር ክህደት እና…
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በእነ ሜ/ጄ ገብረመድህን ፍቃዱ (ወዲ ነጮ) መዝገብ የሚጠሩ 7ቱን ተጠርጣሪዎች ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት አቅርቧል።
የወንጀል ምርመራ ቢሮው ተጠርጣሪዎቹ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም መቐለ ለሚገኘው የሕወሓት ቡድን አመራሮች መረጃ በመስጠት እና ተልዕኮ በመቀበል የሬዲዮ መገናኛውን በመጥለፍ ሠራዊቱ እርስ በእርሱ እንዳይገናኝ በማድረግ ሀገር የማፍረስ ወንጀል ሠርተዋል በሚል ጠርጥሯቸዋል።እንደ ምርመራ መዝገቡ ተጠርጣሪዎቹ ይህንን ድርጊት በመፈፀማቸው በርካታ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለኅልፈት እና ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል እንዲሁም ከባድ የንብረት ውድመት ደርሷል።በእነዚህ እና በሌሎች ተያያዥ ወንጀሎች ፖሊስ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቋል።ተጠርጣሪዎቹ የተጠቀሰውን ወንጀል አልፈፀምንም ሲሉ ተከራክረዋል።ግራ ቀኙን የመረመረው ፍርድ ቤቱ የወንጀሉን ውስብስብነት እና ክብደት እንዲሁም በሀገር ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን ከግምት በማስገባት ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል። የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቅም ለኅዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
Via ETV

#FakeNewsAlert
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ የሱዳን ቅርንጫፍ በትዊተር ገፁ "ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ከአማራ ክልል ወደ ሱዳን ተሻግረዋል፣ በጠ/ሚር አብይ መንግስትና በትግራይ ክልል መካከል እየተደረገ ያለውን የእርስ በርስ ጦርነት ፍራቻ አሁንም እየተመሙ ነው" የሚል መልዕክት ያለው ፅሁፍ በፎቶሾፕ የተቀነባበረ እንጂ በገፁ ላይ እንደማይገኝ ኤጀንሲው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።ይህ ፎቶ በዛሬው እለት በማህበራዊ ሚዲያው በስፋት ሲሰራጭ የነበረ ነው።

#FakeNewsAlert የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ የሱዳን ቅርንጫፍ በትዊተር ገፁ "ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ከአማራ ክልል ወደ ሱዳን ተሻግረዋል፣ በጠ/ሚር አብይ መንግስትና በትግራይ ክልል መካከል እየተደረገ ያለውን የእርስ በርስ ጦርነት ፍራቻ አሁንም እየተመሙ ነው" የሚል መልዕክት ያለው ፅሁፍ በፎቶሾፕ የተቀነባበረ እንጂ በገፁ ላይ እንደማይገኝ ኤጀንሲው ባወጣው መግለጫ…
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኤጀንሲው ትክክለኛውን መረጃ ያወጣ ሲሆን ከ11,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ከትግራይ ክልል ድንበር አቋርጠው ሱዳን መግባታቸውን ኤጀንሲው አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በአዲስ አበባ “የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን” ያሰማራቸው የተባሉ 242 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ! በአዲስ አበባ ከተማ ትርምስ ለመፍጠር “የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን” ያሰማራቸው 242 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንዳሉት ግለሰቦቹ ቦምብ፣ ፈንጂ፣ ላውንቸርና የተለያዩ ተተኳሽ ጥይቶች ተገኝተውባቸዋል፡፡…
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሱር ኮንስትራክሽን የመገናኛ ራዲዮ መያዙን ተናገረ።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ መግለጫ የሰጡት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በከተማው ከ90 በላይ የእጅ ራዲዮ መገኘቱን ተናግረዋል።ከሱር ኮንስትራክሽን የመገናኛ ራዲዮ የተገኘውም በብርበራ መሆኑን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።ዋና ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ እንዲሰፍን ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት እየሠራን ነው ብለዋል።የሀገርን እና የህዝብን ሰላም ለማረጋገጥ ከሕዝብ በሚደርሰን ጥቆማ እና በ'ኢንተሊጀንስ' ጠንካራ ሥራ እየሠራን ነው ብለዋል።ከተማው ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ፈንጅ እና ቦንብ ተይዘው በፈንጅ ባለሙያም መነሳታቸውን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡
በሕወሓትና በደጋፊዎቹ የሁከትና የጥፋት መረብ እንዳይፈጠር፣ በሌላም በኩል የንፁኃን ትግርኛ ተናጋሪዎች ደኅንነት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ፖሊስ ኮሚሽኑ ምን እየሠራ ነው ሲል ሸገር ጠይቋል።ኮሚሽነር ጌቱ የትግራይ ተወላጆች ሰላማዊ ናቸው፤ በመከላከያ ኃይሉ የሚካሄደው ሕግ የማስከበር ዘመቻም ዓላማው የሕወሓትን ቡድን መደምሰስ ስለሆነ፣ ለሰላማዊ የክልሉ ተወላጆችና በአጠቃላይ ለትግርኛ ተናጋሪዎች ጥበቃ ይደረጋል፡፡ሕዝቡም ይህን በደንብ ይረዳል ብለዋል።በከተማው የተያዙ ባለሀብቶችም እንዳሉ ሸገር ሰምቷል፤ ይህስ እውነት ነው ወይ ከሆነስ በምን መስፈርት ነው ሲል ሸገር ጠይቋል።ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው የሕወሓትን ቡድን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የደገፉ ባለሀብቶች በማስረጃ መያዛቸውን ነግረዋል፡፡
Via Sheger

የሚኒስትሮች ምክር ቤት “በትግራይ ብሔራዊ ክልል የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ” ተግባራዊ የሚሆን ደንብ አፀደቀ!
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 (9) እና የፌዴራል መንግሥት በክልል ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀፅ 14/2/ለ/ መሠረት የትግራይ ብሔራዊ ክልልን በጊዜያዊነት የሚያስተዳድር፤ ለፌዴራል መንግሥቱ ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም መወሰኑ ይታወቃል።በዚህ መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት “በትግራይ ብሔራዊ ክልል የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ” ተግባራዊ የሚሆን ደንብ ማፅደቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።

የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ጺዮን ገ/ሚካዔል በተዋጊ አውሮፕላን ጥቃት በክልሉ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ሰላማዊ ሰዎች በአየር ጥቃት ተገደሉት በአዲግራት እና መቀሌ ከተሞች መሆኑን የጠቀሱት ደብረ ጺዮን፣ መቼ እና ስንት ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉ ግን ማስረጃ አላቀረቡም፡፡ደብረ ጺዮን ራሳችን ከጥቃት ተከላከልን እንጅ፣ በመከላከያ ሠራዊቱ ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት አልፈጸምንም በማለት ማስተባበላቸውን ጠቅሷል ሮይተርስ፡፡ የክልሉ ታጣቂዎች ከክልሉ ውጭ ጥቃት እንደማይፈጽሙ የተናገሩት ደብረ ጺዮን፣ ዐለማቀፉ ኅብረተሰብ ጣልቃ ገብቶ ድርድር እንዲያስጀምር ተማጽነዋል፡፡
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
“የ4ኛ ሜካናይዝድ አዛዥ ኮሎኔል ገብረስላሴ በላይ ሰራዊቱን በማታለልና ደባ በመስራት ጥቃት እንዲፈጸምበት የመሪነቱን ሚና ተጫውተዋል” ሲሉ ጥቃቱን ተከላክለው የተረፉ የሰሜን እዝ አባላት ተናገሩ!
"ከፅንፈኛው ቡድን" ጥቃት ተከላክለው የተረፉ የሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዳሉት፤ የተፈጸመው ጥቃት በታሪክ ከፍተኛ ክህደት ነው።"የጁንታው ቡድን" ህይወቱን ለአገር አሳልፎ በሚሰጠው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በማድረስ ወደ ዝርፊያ መግባታቸውንም ተናግረዋል።
ጥቃቱ በተፈፀመበት እለት የሰሜን እዝ 4ኛ ብርጌድ አዛዥ ኮሎኔል ገብረስላሴ በላይ የመከላከያ ሰራዊቱን መኪና ታርጋ በመቀየርና ሌሎች ተንኮሎችንም በመፈፀም አስጠቅተውናል ሲሉም ተናግረዋል።"የጁንታው ቡድን" ምሽት ላይ ከበባ በማድረግ ያልታሰበ ጥቃት እንደሰነዘረባቸው የገለፁት አባላቱ፤ ህወሃት ያስታጠቃቸው የልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት "ከጁንታው" ጋር ተባብረው ጥቃቱን እንደፈፀሙባቸውም ተናግረዋል።“ጁንታው የህወሃት ቡድን የፈጸመው አገርን የማፈራረስ አላማ የባነዳነት ድርጊት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያወግዘው ይገባል” ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 521 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 478 የላቦራቶሪ ምርመራ 521 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 101 ሺህ 248 ደርሷል።በሌላ በኩል የዛሬውን ጨምሮ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 63 ሺህ 268 ሆኗል።ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 554 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 36 ሺህ 424 ሰዎች መካከል 313 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 545 ሺህ 131 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸውን የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች እንዲታገዱ መወሰኑን የኢፌዴሪ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ፌዴራል ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ አንዳንድ የግል የጥበቃ ኤጀንሲዎች የተቋቋሙበትን የመንግሥት እና የግል ተቋማትን የመጠበቅ ዓላማን ወደ ጎን በመተው ከቀጠሯቸው የጥበቃ አባላት መካከል ለሌላ እኩይ ተግባር የመረጧቸውን በመመልመል፣ ለተቋም ጥበቃ የተሰጣቸውን የጦር መሣሪያ በማስታጠቅ እና በማሰማራት በሕዝብ እና በመንግሥት ተቋማት እንዲሁም በተለያዩ አካላት ላይ ጥቃት ለመፈፀም እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተደርሶበታል። ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎቹ በቀጠሯቸው የጥበቃ አባላት እና ተባባሪዎቻቸው ባንኮችን እና የተለያዩ ድርጅቶችን ሲዘርፉ እና ሲያዘርፉ መቆየታቸውንም በአብነት ጠቅሷል። በዚህም ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ እና ንብረት መዝረፋቸውን እና እንዲዘረፍም ማድረጋቸውን ገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም ተቋማቱን እንዲጠብቁበት የታጠቁትን በርካታ የጦር መሣሪያ ይዘው እንደጠፉም ተረጋግጧል ብሏል።እነዚህ ከተልዕኮአቸው ውጭ እንደሚንቀሳቀሱ የተደረሰባቸው የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች ይህም አልበቃ ብሏቸው አሁን ባለው ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ "በጁንታው የሕወሓት ወንበዴ" የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈፀም የተለያዩ ግለሰቦችን ወደ ኤጀንሲዎቹ አስርገው በማስገባት እና የጦር መሣሪያ በማስታጠቅ በኅብረተሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እያሴሩ መሆኑ ነው ፌዴራል ፖሊስ የገለጸው።
በመሆኑም ከታች የተዘረዘሩት የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች፦
1. ንስር የሰው ሃይል እና የጥበቃ አገ/ሃ/የተ/የግ/ማ
2. አጋር የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
3. ስብኃቱና ልጆቹ የንብረት አስ/ጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
4. ሰላም ሴኩሪቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማ
5. ኃይሌ ተክላይ እና ጓደኞቻቸው የጥበቃ አገልግሎት ህ/ስ/ማ
6. ክፍሌ ጎሳዬ ሃጎስ እና ወ/ገብርኤል የጥበቃ አገልግሎት ሽርክና /ማ
7. ዮናስ፣ ሮዛ እና መብርሂት የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሽ/ማ
8. ሃየሎም እና ብርሃኔ የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሸ/ማ
9. ደመላሽ፣ ሃፍቱ እና ጓደኞቻቸው የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሸ/ማ
10.ህሉፍና ሃለፎም የጥበቃ አገ/ህ/ሽ/ማ
11. ዋልታ የጥበቃ የሰው ኃይልና ኮሚሽን ኃ/የተ/የግ/ማ
12. ሴፍ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
13. አትላስ ጠቅላላ አገ/ኃ/የተ/የግ/ማ
14. ጎህ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
ለሀገር እና ለዜጎች ሰላም እና ደህንነት ሲባል ሥራቸውን እንዲያቆሙ የተወሰነና እስከአሁን ባለው ሀገር የማተራመስ እና ሕገ-ወጥ ሥራቸው በህግ የሚጠየቁ መሆኑን ገልጿል።ስማቸው የተገለጸው የጥበቃ ተቋማት በአስቸኳይ ሥራቸውን አቁመው ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሪፖርት እንዲያደርጉም አሳውቋል።
በተጨማሪም ማንኛውም የግልም ሆነ የመንግሥት አካል ከነዚህ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች ምንም ዓይነት ቅጥር እንዳይፈፅም የተከለከለ መሆኑን አሳስቧል።
በመጨረሻም የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎቹ ስር ተቀጥረው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ያሉ ሠራተኞችን በተመለከተ ተገቢውን ልየታ በማድረግ ማስተካከያ እስኪወሰድ ድረስ በተመደቡበት ቦታ የጥበቃ ሥራቸውን አጠናክረው እንዲሠሩ እና የሚጠብቋቸው የግል እና የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎችም በተሰጠው መግለጫ መሠረት ተገቢውን ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርጉ ሆኖ የዕለት ተዕለት ሥራቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የጦር መሣሪያ ቁጥጥርና የግል ጥበቃ ተቋማት ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ሪፖርት በማድረግ ቀጣይ በሚሰጡ የሥራ መመሪያዎች ብቻ ሊሠሩ እንደሚገባ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማኅበር በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች መታሰር አሳሳቢ መሆኑን ገለፀ።
የአዉሎ ሚዲያ አዘጋጅ ፤ የአዲስ ስታንዳር መጽሔት አዘጋጅ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋዜጠኞች እና የኦሮምያ ሚዲያ ኔት ዎርክ ጋዜጠኛ መታሰራቸዉን ተከትሎ ነዉ።የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ፤ የታሰሩት ጋዜጠኞች ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ጉዳያቸዉ እንዲታይ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ጥሪ ማስተላለፈፋቸዉ ይታወቃል።በኢትዮጵያ በሚከሰቱ የተለያዩ የፀጥታ ችግሮችን ተከትሎ ጋዜጠኞች ወከባ እስር እና የተለያዩ ተጽኖዎች እንደሚደርስባቸዉ ጋዜጠኞች ራሳቸዉ ይናገራሉ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት ኤርምያስ በጋሻዉ ለዶቼ ቬሌ እንደተናገሩት የመገናኛ ብዙኃን ስራ አንጻራዊ ነጻነት ታይቶበታል። ታስረዉ የነበሩ ተፈተዋል፤ ፈቃድ ተከልክለዉ የነበሩ በፈቃድ ይሰራሉ። ይሁንና ፤ አንጻራዊ ነጻነቱ እየደበዘዘ ነዉ። ጋዜጠኞች ከተለያዩ አካላት ወከባ እየደረሰባቸዉ ነዉ።
Via DW

"የሕወሓት ቡድን"ን በበላይነት በመምራት በትግራይ ክልል በሚገኘው በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም የአገር ክህደት ወንጀል የፈጸሙት የጥፋት ቡድን አባላትን አድኖ ለህግ ለማቅረብ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወጥቷባቸዋል፡፡
የጥፋት ቡድኑ አባላት ከኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች ፀረ-ሰላም ሃይሎች ጋር በመቀናጀትም ከተለያዩ ክልሎች አገርን የማፍረስ ተልዕኮ ያለቸውን ኃይሎች በመመልመል ትግራይ ክልል ድረስ በመውሰድ ለእኩይ ተልዕኮቸው ስኬት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎችን በማድረግ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ብሄርን ከብሄር በማጋጨት እና በሃይማኖት ሽፋን ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በማድረግ በርካታ ንፅሁን ዜጎች እንዲገደሉ፣ በአካልና በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው አመልክቷል፡፡የሀገር ህልውናን አደጋ ላይ በመጣል እንዲሁም ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል በመናድ ወንጀል የሚፈለጉትና የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው፡-
1.ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል
2.ጌታቸው ረዳ
3. ፈትለወርቅ ገ/እግዝያብሄር
4. አስመላሽ ወ/ስላሴ
5.ዶ/ር አብርሃም ተከስተ
6.ኪሪያ ኢብራሂም
7.ረዳይ አለፎም
8.አማኑኤል አሰፋ
9.ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ
10.ኪሮስ ሀጎስ
11.ያለም ፀጋ
12.ሰብለ ካህሳያ
13.ጌታቸው አሰፋ
14.ዳንኤል አሰፋ
15.ኢሳያስ ታደሰ
16.ዶ/ር አክሊሉ ሀ/ሚካኤል
17.አለም ገ/ዋህድ
18.ተክላይ ገ/መድህን
19.ዶ/ር እያሱ በርሄ
20.ዶ/ር ረዳይ በርሄ
21.ዶ/ር ኪዳነማርያም በርሄ
22.ነጋ አሰፋ
23.ሺሻይ መረሳ
24. ዶ/ር ገ/ህይወት ገ/እግዝያብሄር
25. አፅብሃ አረጋዊ
26.ዶ/ር ኢ/ር ሰለሞን ኪዳኔ
27.ሀዱሽ ዘነበ
28.በርሄ ገ/እየሱስ
29.ይትባረክ አምሃ
30.ዶ/ር ገ/መስቀል ካህሳይ
31.ዶ/ር ፍስሃ ሀ/ፂዮን
32.ርስቀ አለማየው
33.ዶ/ር አዲስ አለም ቤሌማ
34.ዘነበች ፍስሃ
35.ፍሬወይኒ ገ/እግዝያብሄር
36.አቶ ስዩም መስፍን
37.አቶ አባይ ፀሐዬ
38.እያሱ ተስፋይ
39.ለምለም ሀድጎ
40.ፕሮፌሰር ክንድያ ገ/ህይወት
41.ሀብቱ ኪሮስ
42.በየነ ምክሩ
43.ካሳዬ ገ/ህይወት
44.ሩፈኤል ሽፈራ
45.ሊያ ካሳ
46.ተወለደ ገ/ፃዲቅ
47.ሙሉ ገ/እግዝያብሄር
48.ኪሮ ስጉዑሽ
49.ዶ/ር አማኑኤል ሀይሌ
50.ደሳለኝ ተፈራ
51.ኢንጅነር አርአያ ብርሀኔ
52.አልማዝ ገ/ፃድቅ
53.ሰለሞን መአሾ
54.ተኪኡ ማዕሾ
55.ገነት አረፈ
56.ብርክቲ ገ/መድህን
57.ዶ/ር ሀጎስ ገዳፋይ
58.ዘራይ አስጎዶም
59.አሰፋ በላይ
60.አቶ ሸዋንግዘው ገዛኸኝ
61.አፅብሃ ግደይ
62.አቶ ስብሀት ነጋ
63.አቶ ሴኮቱሬ ጌታቸው
64.በሪሁን ተ/ብርሃን የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛ የነበሩ ናቸው፡፡
ከላይ ስማቸው የተዘረዘረው የወንበዴው የጁንታው ሕወሓት የጥፋት ቡድን አባላት የአገር ክህደት ወንጀል ከመፈጸማቸውም በተጨማሪ በከፍተኛ የአገር ሃብት ምዝበራና ዘረፋ እንዲሁም በሰበአዊ መብት ጥሰት ወንጀልም ጭምር የሚፈለጉ መሆናቸውን ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው አሳውቋል፡፡
በተመሳሳይም ከህውህት ቡድን አባላት ጋር እየተገናኙ የሀገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙና አገር በማፍረስ ሴራ በተሳተፉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፖሊስ አመራሮች ላይም የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው አስታውቋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ መንግስት እና ሕዝብ የጣለባቸውን አገራዊ ኃላፊነትና ህገመንግስታዊ ግዴት ወደጎን በመተው መቀመጫዉን ትግራይ ክልል ካደረገዉ ከወንበዴው የህወሃት ቡድን አባላት ተልዕኮ በመቀበል በሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላት ውስጥ ሴሎችን በማደራጀት ከማዕከል የነበረው ግንኙነት እንዲቋረጥና ጥቅምት24 ቀን 2013 ዓ/ም ጥቃት እንዲፈጸም በማድረግ የሞት፣የአካል ጉዳት እና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ እንዲፈፀም ማድረጋቸውን የኮሚሽኑ መግለጫ ያመለክታል፡፡
ባለፉት 21 አመታት በምሽግ አብረው ሲኖሩ የነበሩ ጓዶቻቸውን የ"ጁንታው ቡድን" እኩይ አላማ ማስፈጸሚያ በማድረግ አገር በማፍረስ ተልዕኮው በመምራትና በመሳተፍ የሚፈለጉት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የፖሊስ አባላት፡-
1.ሌ/ጀኔራል ታደሰ ወረደ ተስፋዬ (ውድወርደ)
2.ሜ/ጄኔራል ዮሐንስ ወ/ጎርጊስ ተስፋይ (መዲድ)፣
3.ሜ/ጄኔራል ብርሃነ ነጋሽ በየነ (ውድመድህን)፣
4.ብ/ጄኔራል ሀ/ስላሴ ግርማይ ገ/ሚካኤል
5.ብ/ጄኔራል ምግበ ሃይለ ወ/አረጋይ (አባበርሃ፣)
6.ሜ/ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል መሀመድዙን
7.ብ/ጄኔራል ገ/ኪዳን ገ/ማርያም የእብዮ
8.ሜ/ጄኔራል ገብረ ገ/አድሃና ወ/ዘጉ (ገብረዲላ)
9.ሜ/ጄኔራል ገ/መስቀል ገ/ዮሀንስ /አስቴር/
10.ብ/ጄኔራል አብርሃ ተስፋይ በርሄ /ድንኩል/
11.ብ/ጄኔራል ፍስሃ በየነ (ወርቅአይኑ)
12.ሜ/ጄኔራል ህንፃ ወ/ጎርጊስ ዮሐንስ
13.ብ/ጄኔራል አለፎም አለሙ ወ/ማርያም /ቸንቶ/
14.ብ/ጄኔራል ገ/መስቀል ገ/እግዝያብሄር (ጠቀም)
15.ብ/ጄኔራል ተ/ብርሃን ወ/አረጋዊ
16.ሜ/ጄኔራል አታክልቲ በርሄ ገ/ማርያም
17.ኮሚሽነር መኮንን ካህሳይ ገ/መስቀል (ፅንቡላ) የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር
18.ም/ኮሚሽነር መንግስቴ አረጋዊ የትግራይ ክልል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር
19.ኮ/ር ጌታቸው ኪሮስ የትግራይ ፖሊስ አመራር የነበረ
20.ም/ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ማንጁስ/ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ የነበረ
21.ም/ኮሚሽነር ተክላይ ፀሃዬ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ም/ሃላፊ የነበረ
22.ኮ/ር ንጉስ ወ/ገብርኤል የትግራይ ልዩ ሃይል ፖሊስ ሃላፊ፣
23.ኮ/ር ገ/ስላሴ ታፈረ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አመራር የነበረ
24.ኮ/ር ፍስሃ ተ/ማርያም (ወዲአርባ) የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አመራር የነበረ
25.ኮ/ር ተስፋዬ ገ/ኪዳን (ተስፋዬ ባንዳ) የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አመራር የነበረ
26.ሜ/ጀነራል ገ/መድህን ፍቃዱ ሃይሉ (ውድነጮ) በቁጥጥር ስር የዋሉ
27.ሜ/ጀነራል ይርዳው ገ/መድህን ገ/ፃድቅ(አስቴር)በቁጥጥር ስር የዋሉ
28.ብ/ጀነራል ገ/ህይወት ሲስኖስ ገብሩ በቁጥጥር ስር የዋሉ
29.ብ/ጀነራል ኢንሶ እጃጆ እራሾ በቁጥጥር ስር የዋሉ
30.ብ/ጀነራል ፍስሃ ገ/ስላሴ እንሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ
31.ኮ/ል ደሳለኝ አበበ ተስፋዬ በቁጥጥር ስር የዋሉ
32.ኮ/ል እያሱ ነጋሽ ተሰማ በቁጥጥር ስር የዋሉ ናችው:
ህዝቡ ፣የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤የአገራችን የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት ተቋማት እነዚህን የሕወሓት የጥፋት ቡድን ተፈላጊዎች አድኖ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ጥረት በያለበት የድርሻውን እንዲያበረክት ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

👍1
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው ሪፖርት በማይካድራ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሶስት ቀን በፊት በጅምላ መገደላቸውን ገልፇል።
ግድያውንም የፈፀሙትን አካሎች መንግስት ለህግ እንዲያቀርብ ጠይቋል።ግድያው ወደ ሁመራ መውጫ ባለ ስፍራ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካባቢ በሚገኝ ስፍራ መፈፀሙን በፎቶና ከአይን እማኞች አረጋግጫለው ሲል ሪፖርቱ ፅፏል።ግድያው ምንም ፖለቲካዊ ቁርኝት በሌላቸው በቀን ሰራተኞች ላይ የተፈፀመ ሲሆን የግድያው እውነተኛ አጀንዳ ጊዜ ያወጣዋል ያለ ሲሆን መንግስት እያደረገ ላለው የሚሊታሪ ኦፕሬሽን ግልፀኝነት ሲባልና የሰብአዊ እርዳታ ስራዎች በቀላሉ ለመስራት እንዲያግዝ በትግራይ የተቋረጠው የስልክና የኢንተርኔት ግንኙነት አንዲመለስ አምነስቲ የጠየቀ ሲሆን አምነስቲ በስፍራው የሚደርሰውን ማንኛውንም ኢ ሰብአዊ የመብት ጥሰትና ወንጀል እየመዘገብኩ ለአለም ህዝብ አጋልጣለው ብሏል።
Via FidelPost

ዶ/ር ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ።
በፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት በትግራይ ብሔራዊ ክልል የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ማጽደቁ ይታወቃል።
በጸደቀው ደንብ መሠረት ዶ/ር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሰይመዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል ሆነው፣ የክልሉን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትን የሚመሩ ኃላፊዎችን ፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመመልመል እንደሚሾሙ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

በወጋገን ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ከሚያስፈልገው በላይ የጦር መሳሪያ መገኘቱ ተሰማ!
የፋይናንስ አገልግሎት ሰጭ በሆነው ወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ በዛ ያለ የጦር መሣሪያ ተከማችቶ መገኘቱ ተሰማ።በአዲስ አበባ በርካታ የጦር መሳሪያ የተገኘባቸው ሌሎች ድርጅቶችም አሉ ተብሏል።በወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የተገኙት የጦር መሣሪያዎች ለሌላ ዓላማ ሊውሉ የሚችሉ መሆናቸውን ኮሚሽነሩ ለሸገር ነግረዋል።
በወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ የጦር መሠሪያ ተከማችቶ መገኘቱን የተናገሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ ከተገኙት መሣሪያዎች አንዳንዱ በፀጥታ ኃይሉ እጅ የሌሉ ጭምር ናቸው ብለዋል፡፡ሱር ኮንስትራክሽንም የተለያየ ተልዕኮ ወስዶ ሲንቀሳቀስ የነበረ ሌላው የሕወሓት አካል ነው ተብሏል።በእነዚህ መሥሪያ ቤቶች በሕዝብ ጥቆማ እና ኮሚሽኑ ካለው መረጃ በመነሳት ብርበራ እና ፍተሻ መደረጉን ሸገር ሰምቻለው ብሏል።
የጦር መሣርያ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን መከላከያ በራሱ ካምፕ ነው የሚያስቀምጠው ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ በእነዚህ ተቋማት በብርበራ የተገኙትም ከፍተኛ የጦር መሣርያዎች ናቸው ብለዋል።በከተማው ውስጥ ካሉ ባለሀብቶች መካከል ለሕወሓት ድጋፍ የሚያደርጉ እንደነበሩም ኮሚሽነሩ ለሸገር ነግረዋል፡፡ ባለሀብቶች በተለያየ መንገድ ንብረት ሊያፈሩ ይችላሉ ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ፣ የፖሊስ ኮሚሽኑ ከወንጀል ጋር የተያያዘ ተጨባጭ መረጃ እና ሕገ መንግሥታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ጥፋት በመፈፀም ተቀናጅተው የሚሠሩ አካላት ላይ ያተኮረ ሥራ ነው የሚያከናውነው ብለዋል፡፡
Via Sheger FM

የአፍሪካ ህብረት የደህንነት ሀላፊ የሆኑት ገ/እግዚአብሔር መብራቱ ከስልጣናቸው ተነሱ!
የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳፋቂ መሃማት ገ/እግዚአብሔር መብራቱ መለሰን ከህብረቱ የደህንነት ሀላፊነት ማንሳታቸውን ተገልጿል።ሮይተርስ የስንብት ደብዳቤው ከትናንት በስቲያ እንደተሰጣቸው የዘገበ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግስት በግለሰቡ እምነት እንደሌለው ከአንድ ቀን በፊት ካስታወቀ በኋላ የመጣ ውሳኔ መሆኑ ዘገባው አክሏል።

ቻይና የኮቪድ ክትባትን ለአፍሪካ ሀገራት ለማድረስ እንደምትሰራ አስታወቀች!
የቻይና ውጩ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዪ ሀገራቸው የኮቪድ ክትባቶች በዓለም ገበያ ላይ እንደሚኖሩ ለማድረግ አሁንም ፍቃደኛ መሆኗን ገልፀዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ክትባቶቹ ለግልጋሎት ዝግጁ በሚሆኑበት ሰዓት ለአፍሪካ ሀገራት የማከፋፈልን ጉዳይ ቻይና እያሰበችበት ነው ሲሉም መናገራቸውንም ግዙፉ የቻይና ሚዲያ ተቋም CGTN ዘግቦታል፡፡

3 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ተመርቶ ለህብረተሰቡ በነፃ እንደሚሰራጭ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴሩ የአግሮ ፕሮሰሲንግና ፋርማሲዮቲካል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተካ ገብረእየሱስ እንደገለፁት ከጅ አይ ዜድ በተገኘ ድጋፍ በተመረጡ 36 የጨርቃጨርቅና አልባሳት ፋብሪካዎች ተቀጥረው ለሚሰሩ 12 ሺህ ሰራተኞች የሁለት ወር ደመወዝ ይከፈላል ብለዋል፡፡ሰራተኞቹ ተቀጥረው በሚሰሩበት ፋብሪካ በወር ውስጥ 150 የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማምረት እንደሚጠበቅባቸው ጠቅሰው 3 ነጥብ 5 ሚሊየን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ተመርቶ የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በነፃ እንደሚሰራጭ መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Via AMN

ቻይና ለተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ለጆ ባይደን "የእንኳን ደስ አልዎ" መልዕክት ዛሬ አስተላለፈች!
የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸው ከተነገረ ከስድስት ቀን በኋላ ቻይና ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤቷ በኩል የእንኳን ደስ አሎት መልእክት አስተላልፋለች።ቻይና ለእንኳን ደስ አሎዎ መልእክት መዘግየቷ ምርጫውን ውጤት አልተቀበለችም የሚል ጥርጣሬ በብዙ ሀገራት በኩል አሳድሮ ነበር።