በኢትዮጵያ ተጨማሪ 400 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 981 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5,183 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 400 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።በሌላ በኩል 981 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 62,497 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።ባለፋት 24 ሰዓታት የ8 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,545 አድርሶታል።በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 100,727 ደርሷል።
@YeneTube @FikerAssefa

በሲዳማ ክልል ተጠርጣሪዎች ተያዙ!
የሲዳማ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ «ተጠርጣሪዎች የተያዙት በሀዋሳ ከተማ በሆቴል ውስጥ ተሸሸገው የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ ወጣቶችን በመመልመል ተግባር ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው ነው »እንደ ዶይቼ ቨለ ዘገባ
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ የክልሉን ሰላም ለማወክ በርካታ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችና ከ36 ሺህ ብር በላይ ሐሰተኛ የብር ኖቶች መያዛቸውን አቶ አለማየሁ ተናግረዋል።ከዛሬ ጀምሮም በሞተር ብስክሌት እና በባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን ተናግረዋል።በትናንትናው ዕለት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች በብሔረሰቦች መካከል ግጭት በመፍጠርና የጦር መሳሪያዎችን በማዘዋወር ሁከት ለመቀስቀስ ሞክረዋል በሚል የተጠረጠሩ በርካታ ሰዎች መያዛቸውን የክልሉ የፀጥታ ሃላፊዎች ገልጸዋል።
Via DW

በሃገር መከላከያ ሰራዊትና በህወሓት መካከል የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ በትግራይ ክልል ዋጃ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ተፈናቅለው ወደ አማራ ክልል ሰሜን ወሎ እየገቡ መሆናቸውን ገለጹ፡፡
የሰሜን ወሎ ዞን ለተፈናቃዮቹ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደርግ አረጋግጧል፡፡ ወታደራዊ ፍጥጫው ሥጋት ላይ የጣላቸው በትግራይ ክልል የዋጃ አካባቢ ኗሪዎች ጦርነቱ ከተከሰተ ጀምሮ ህይወታቸውን ለማትረፍ አጎራባቻቸው ወደሆነው ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ እየመጡ መሆኑን ይናገራሉ፡፡
Via VoA

በሀገረ አሜሪካ የፍሎሪዳ ገዢ ሮን ደሰይንትስ ዜጎች ለተቃውሞ ወጥተው ንብረት ሲያወድሙ መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች እንዲተኩሱባቸው የሚፈቅድ ህግን እንዳረቀቁ ተሰምቷል። ይህ ህግ በተለይ የንብረቱ ባለቤቶችን በአውዳሚዎቹ ላይ የመተኮስ መብት የሚያጎናፅፍ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች በርካታ የግልና የመንግስት የንግድና ማህበራዊ ተቋማትን ጭምር ሲያወድሙ ይሰማል።ዜናውን ያገኘነው ከአር ቲ ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል!
አምስተኛው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት ያካሂዳል።ምክር ቤቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በመደበኛ ስብሰባውም የተለያዩ አጀንዳዎችን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
በዚህም 1ኛ የምክርቤቱን 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፤ 2ኛ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአንድ አባል ሹመትን መርምሮ ማጽደቅ፤ 3ኛ የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኤክሳይዝ ታክስ ለማሻሻል የቀረበ ረቀቅ አዋጅን በተመከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ አሳብ መርምሮ አዋጁን ማጽደቅ ናቸው።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን ተከትሎ የተጎዱ የጦር ሠራዊት አባላት የመጀመሪያ የሕክምና እርዳታ የሚሰጡ ሦስት አምቡላንሶቹ ላይ ጥቃት እንደተፈጸመበት ገለፀ።
የቀይ መስቀል አምቡላንሶች እና የቀይ መስቀል አርማ ከወታደራዊ ጥቃት እንዲጠበቁ ጥሪ አድርጓል።በማኅበሩ የሰሜን ጎንደር ቅርንጫፍ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለመርዳት ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከዐሥር በላይ አምቡላንሶች እና በጎ ፈቃደኞች ማሰማራቱን ጠቅሶ፣ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ላይ ዳንሻ አካባቢ የታጠቁ ኃይሎች ተኩስ በመክፈት ጉዳት እንዳደረሱበት አስታውቋል።
ድርጊቱ ዓለም አቀፍ መርህ እና የቀይ መስቀል አርማ አጠቃቀም ሕግን የጣሰ፣ ሰብአዊ እሴትን የሚጻረር እና በሰብአዊ ሥራ ላይ በገለልተኝነት እና ያለ አድልዎየተሰማሩ በጎ ፈቃደኞችንና የሕክምና አካላት ለአደጋ እንዲጋለጡ ያደረገ መሆኑን ገልጿል።
አያይዞም በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም ወገኖች የቀይ መስቀል አርማ የሚሰጠውን ከለላለ በጄኔቫ ስምምነት መሠረት እንዲያከብሩ ጠይቋል።የማኅበሩ በጎ ፈቃደኞች፣ ሠራተኞች እና ሌሎች የሕክምና አካላት በግጭት ወቅት የግጭት ተሳታፊ ያልሆኑትንና ተሳታፊ መሆናቸውን ለዘለቄታ ያቆሙ ሰዎችን ሕይወት መታደግ እንዲችሉ ሰብአዊ እንቅስቃሴያቸው እንዳይታወክ ጠይቋል።
Via Walta

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቦሌ አየር ማረፊያ ተጨማሪ መታወቂያ መጠየቁን በተመለከተ ማብራሪያ ጠየቀ!
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቦሌ አየር ማረፊያ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን መንገደኞች ከፓስፖርት በተጨማሪ የቀበሌ መታወቂያ ወረቀት እንዲያቀርቡ መገደዳቸውን በተመለከተ ማብራሪያ ጠየቀ። አዲሱ አሰራር “ዜጎችን በብሔራቸው በመለየት ለጥርጣሬ እና መድልዎ እንዲጋለጡ የሚያደርግ ነው” ብሏል።
መንግስታዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ጥያቄውን ያቀረበው ለኢትዮጵያ ሲቪል አሺዬሽን ባለስልጣን እና ለአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ደህንነት ቢሮ ትላንት ማክሰኞ ህዳር 1፤ 2013 በጻፈው ደብዳቤ ነው። የኮሚሽኑ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያረጋገጡት የኢትዮጵያ ሲቪል አሺዬሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር ጄነራል ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው፤ ጉዳዩ እርሳቸው የሚመሩትን መስሪያ ቤት የሚመለከት እንዳልሆነ ተናግረዋል።
Via Ethiopia Insider

በመላ አገሪቱ የሽብር ጥቃቶችን ለመፈፀም ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ 150 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን መንግሥት አስታወቀ።
በፌደራሉ መንግሥት የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እውነታ አጣሪ ‹‹የሕወሓት ወንጀለኞች በአዲስ አበባ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ፍርሃትን ለመንዛትና እና የሽብር ጥቃትን ለማድረስ አስፈፃሚ መረብ አቋቁመዋል›› ብሏል።ተጠርጣሪ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው ያለው እውነታ አጣሪው፤ ተጠርጣሪዎቹ ከተለያዩ የኑሮ ዘርፎች የተውጣጡ የተለያዩ ብሔር ተወላጆች ናቸውም ሲል አብራርቷል።ከተያዙት 150 ተጠርጣሪዎች ውስጥ ጥቂቶቹ የፀጥታ ስጋትን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዋስ ተለቀዋልም ብሏል።‹‹የሕግ አስከባሪያችን አሰራር ደንብን የተከተለ እንጂ እንደሚወራው በማንነት ላይ ተመስርቶ ግለሰቦችን የሚያጠቃ አይደለም›› ሲል ሀሰተኛ መረጃዎች ተሰራጭተዋል በሚል ኮንኗል።
[Ahadu Television]

ጠ/ሚ ዐቢይ የምዕራቡ የትግራይ ክልል ቀጠና ነጻ ወጥቷል አሉ!
በሽራሮ አካባቢ እጅና እግራቸውን የፊጥኝ ታስረው የተረሸኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አሁን ሰራዊቱ አካባቢውን ሲቆጣጠር እንዳገኘ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ተናገሩ።ይህ የተደረገበት ዓላማ ኢትዮጵያን መስበር ነበር፣ ግን አላወቁም ከአልማዝ የጠነከረች መሆኗን ብለዋል።"በተጨማሪም ሠራዊታችንንና ሕዝቡን አስቆጥቶ ለበቀል ርምጃ ማነሣሣት ነው፣ አላወቁም ልበ ሰፊ ሕዝብና ሠራዊት እንዳለን"፣ ካሉ በኋላ በየቦታው ስንደርስ ከዚህ የከፋ ጭካኔና ግፍ ሊገጥመን ይችላል፣ ይህ ግን ለዚህ "ጁንታ" የመጨረሻው ነው ብለዋል በትዊተር ገፃቸው። ከዚህ በኋላም 'ሙት ይዞን እንዳይሞት' መፍጠን አለብን፤ የተረፉትን ለመታደግና ግፍ የተፈጸመባቸውንም ለዓለም ማጋለጥ አለብንም ብለዋል።ቀጥለውም የምዕራቡ የትግራይ ክልል ቀጠና ነጻ ወጥቷል።በዚያ ቀጣና ሠራዊቱ ሰብአዊ ርዳታና አገልግሎት እየሰጠ ነው።ነጻ ባወጣቸው አካባቢዎች ሕዝቡን እየመገበ፣ እያከመና እየተከባከበ ነው ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ግለሰቦች ያልተረጋገጠ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ አሳሰበ!
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ግለሰቦች ያልተረጋገጠ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ አሳሰበ። ጽህፈት ቤቱ በፌስቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ “እውቅና ያላቸውን ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጨምሮ ሁሉም ግለሰብ በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ በመሬት ላይ ያለውን እውነታ የማያንፀባርቅና ያልተረጋገጠ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ እናሳስባለን” ብሏል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው በወንጀል የተጠረጠሩ የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አነሳ።
በዚህም መሠረት ደብረፅዮን ገብረሚካኤል(ዶ/ር)፣ ጌታቸው ረዳ፣ አስመላሽ ወልደሥላሴ፣አቶ አፅበሃ አረጋዊ፣አቶ ገብር እግዚአብሄር አርአያ
ዶክተር አምባሳደር አዲስ ዓለም ቤሌማ እና ዓባይ ፀሐዬን ጨምሮ የ32 ግለሰቦች ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ሆኗል፡፡
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ ፍቅሩ ገብረሕይወትን የምርጫ ቦርድ አባል አድርጎ ሾሟል።
ዘገባው የኢቲቪ ነው።

በታንዛኒያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዋነኛ ተፎካካሪ የነበሩት ቱንዱ ሊሱ ለደህንነቴ እሰጋለሁ በማለት ቤልጂየም ገብተዋል፡፡
በመንግሥት ተሰጥቷቸው የነበረው ጥበቃ የምርጫው ውጤት ይፋ መሆንን ተከትሎ እንደተነሳ የተናገሩት የተቃዋሚ መሪው፤ የግድያ ዛቻዎች እንደደረሷቸው ለቢቢሲ አስታውቀዋል፡፡ከአራት ዓመታት በፊት ከተደረገባቸው የግድያ ሙከራ የተረፉት ፖለቲከኛው፤ ዛቻዎቹን በጥንቃቄ በማየት ከአገር መሰደዳቸውን ነው የገለጹት፡፡በቤልጂየም የመኖር ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ተቃዋሚው፤ ዓለም ዐቀፍ ትግላቸውን ማድረግ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
[አሐዱ ቴሌቪዥን]

በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች በቀጣዩቹ ቀናቶች ኃይል ይቋረጣል!
ለማሻሻያ ሥራ ሲባል በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች በቀጣዩቹ ቀናቶች ኃይል እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለፀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ እንደሚያከናውን ነው ያስታወቀው።
በዚህም አርብ ህዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 9:00 ድረስ፣
• በመነን ት/ቤት፣ በሽሮ ሜዳ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በቀጨኔ መድሀኒያለም ቤ/ክ፣ በላዛሪስት፣ በሐምሌ 19 መናፈሻ፣ በቦሌ ሚካኤል፣ በቦሌ ካርጎ፣ በማዕድን ማህበር እና አካባቢዎቻቸው፣
በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 10:00 ድረስ፣
• በሃና ማርያም፣ በሀይሌ ጋርመንት፣ በኦሮሚያ ኮንደሚኒየም፣ በማንጎ ሰፈር፣ በምስራቀ ፀሃይ ገብርኤል ፊት ለፊት፣ በየተባበሩት ነዳጅ ማደያ፣ በሚካኤል ፊት ለፊት፣ በጆሞ 1 በከፊል በጆሞ 3 እና አካባቢዎቻቸው፣
ቅዳሜ ህዳር 5 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 5:00 ድረስ፣
• በመነን ት/ቤት፣ በሽሮ ሜዳ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በቀጨኔ መድሀኒያለም ቤ/ክ፣ በላዛሪስት፣ በሐምሌ 19 መናፈሻ እና አካባቢዎቻቸው፣
በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 7:30 ድረስ፣
• በፈረንሳይ ኤምባሲ፣ በጉራራ፣ በፊልም ማዕከል፣ በራስ ካሳ ክሊኒክ፣ በአቦ ቤ/ክ፣ በእንጦጦ ኪዳነምህረት ቤ/ክ፣ በጉርድ ሾላ፣ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ በአየር መንገድ ቤቶች እና አካባቢዎቻቸው፣
እንዲሁም እሁድ ህዳር 6 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 10:30 ድረስ፣
• በፍሊንት ሰቶን ሪል እስቴት፣ በአትሌቶች መንደር እና አካባቢዎቻቸው፣
በተጨማሪም ሰኞ ህዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 9:30 ድረስ፣
• በቦሌ ሚካኤል፣ በቦሌ ካርጎ፣ በማዕድን ማህበር፣ በሳሚት ኮንደሚኒየም፣ በጊዮርጊስ ቤ/ክ፣ በጃክሮስ፣ በሳሌተ ምህረት፣ በፊጋ ሆቴል እና አካባቢዎቻቸው አገልግሎቱ የሚቋረጥ ይሆናል።
በመሆኑም ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳውቋል፡፡

የናይል ተፋሰስ ሃገራት ኢኒሽዬቲቭ (NBI) የሚኒስትሮች ምክር ቤት (NBI-COM) ዛሬ 28ኛ መደበኛ ዓመታዊ ጉባዔውን በኦን ላይን የግንኙነት ዘዴ (ቨርቹዋል) ያካሂዳል፡፡
ጉባዔው ኢትዮጵያን ጨምሮ የተፋሰሱ አባል በሆኑ 10 ሃገራት የውሃ ሚኒስትሮች የሚካሄድ ሲሆን በበጀት እና ተያያዥ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ ይመክራል፡፡የኢትዮጵያ የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለም በስብሰባው እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል፡፡በኢንሽዬቲቩ የሚከናወኑ ተግባራት “ለናይል ውሃ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ወሳኝ ናቸው” ያሉት ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያ ለውይይት እና ለጋራ ርዕዮች ስኬት ቁርጠኛ መሆኗን” በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል፡፡
በጉባዔው ርዋንዳ የምክር ቤቱን የበላይ መሪነቷን ከኬንያ በይፋ ተረክባ ለቀጣዩ አንድ ዓመት የምትመራ ይሆናል፡፡ኢትዮጵያን ጨምሮ ቡሩንዲ፣ ዴ.ሪ ኮንጎ፣ ግብጽ፣ ኬንያ፣ ርዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ የኢንሽዬቲቩ አባል መሆናቸው የሚታወስ ነው፡፡ኤርትራ ደግሞ በታዛቢነት ትሳተፋለች፡፡
[Al ain]

በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
አደጋው በወረዳው ትናንት ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ30 ከሽመለጋራ ተነስቶ ወደ ኮኪት ቀበሌ ሰሊጥ ጭኖ በመጓዝ ላይ ያለ ማርቸዲስ የጭነት ተሽከርካሪ ከጭነቱ በላይ ሰባት ሰዎችን እንደጫነ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት በመገልበጡ የደረሰ ነው ተብሏል፡፡በዚህም ረዳቱን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን ከመተማ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በተለምዶ ኮዬ ፈጬ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ካሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በአንዱ ህንጻ ላይ የተሰማው የፍንዳታ ድምጽ ስጋት ላይ ጥሎናል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ።
ድምፁን ተከትሎ የመስኮት እና የበር መስታወቶች መውደቃቸውን ነዋሪዎቹ ለሸገር ተናግረዋል፤ ሁኔታውን በአካል ጭምር ሄደን አይተናል የሚሉት የወረዳው እና የክፍለ ከተማው የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው የተከሰተውን ነገር በትክክል ለማወቅ መሃንዲሶችን እስከ ዛሬ ከሰዓት ድረስ ወደ አካባቢው እንልካለን ብለዋል።
Via Sheger FM

YeneTube
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው በወንጀል የተጠረጠሩ የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አነሳ። በዚህም መሠረት ደብረፅዮን ገብረሚካኤል(ዶ/ር)፣ ጌታቸው ረዳ፣ አስመላሽ ወልደሥላሴ፣አቶ አፅበሃ አረጋዊ፣አቶ ገብር እግዚአብሄር አርአያ ዶክተር አምባሳደር አዲስ ዓለም ቤሌማ እና ዓባይ ፀሐዬን ጨምሮ የ32 ግለሰቦች ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ሆኗል፡፡ በሌላ በኩል ምክር…
ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ስም ዝርዝር:
1. ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል
2. አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ
3. አቶ አባይ ጸሀዬ
4. አምባሳደር ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ
5. አቶ ጌታቸው ረዳ
6. አቶ አጽብሃ አረጋዊ
7. አቶ ታደሰ ሀይሌ
8. ዶ/ር መብራቱ መለስ
9. ወ/ሮ ለምለም ሀድጉ
10. አቶ ገ/እግዚአብሄር አርኣያ
11. አቶ ሀለፎም ግደይ
12. አቶ ሀዱሽ አዛነው
13. ወ/ሮ መብራት ገ/ጊዮርጊስ
14. ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሄር
15. ወ/ሪት ልዕልቲ ጸጋዬ
16. ወ/ሮ ማሚት ተስፋይ
17. ወ/ሮ ማና አብርሃ
18. አቶ ካላዩ ገ/ህይወት
19. አቶ ጌዲዮን ሀ/ስላሴ
20. መ/ር በርሄ ዝግታ
21. አቶ ታደለ አሰፋ
22. አቶ ነጋ አሰፋ
23. ወ/ሮ ናፈቁሽ ደሴ
24. ወ/ሮ ሽሻይ ሀ/ሰላሴ
25. ወ/ሮ አልማዝ አርኣያ
26. ወ/ሮ አሰለፈች በቀለ
27. ወ/ሮ አስቴር አማረ
28. አቶ አለምሰገድ ወረታ
29. ዶ/ር አድሃና ሃይለ
30. አቶ ኪሮስ ወ/ሚካኤል
31. አቶ ሹምዬ ገብሬ
32. አቶ ካሳ ጉግሳ
33. ወ/ሮ አበራሽ አድማሱ
34. አቶ ዮሀንስ በቀለ
35. አቶ ዳኘው በለጠ
36. ወ/ሮ ፅዋሃብ ታደሰ
37. አቶ ዊንታ ተክሉ እና
38. አቶ ግርማይ ሻዲ ናቸው፡፡
ምንጭ፡- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
1. ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል
2. አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ
3. አቶ አባይ ጸሀዬ
4. አምባሳደር ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ
5. አቶ ጌታቸው ረዳ
6. አቶ አጽብሃ አረጋዊ
7. አቶ ታደሰ ሀይሌ
8. ዶ/ር መብራቱ መለስ
9. ወ/ሮ ለምለም ሀድጉ
10. አቶ ገ/እግዚአብሄር አርኣያ
11. አቶ ሀለፎም ግደይ
12. አቶ ሀዱሽ አዛነው
13. ወ/ሮ መብራት ገ/ጊዮርጊስ
14. ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሄር
15. ወ/ሪት ልዕልቲ ጸጋዬ
16. ወ/ሮ ማሚት ተስፋይ
17. ወ/ሮ ማና አብርሃ
18. አቶ ካላዩ ገ/ህይወት
19. አቶ ጌዲዮን ሀ/ስላሴ
20. መ/ር በርሄ ዝግታ
21. አቶ ታደለ አሰፋ
22. አቶ ነጋ አሰፋ
23. ወ/ሮ ናፈቁሽ ደሴ
24. ወ/ሮ ሽሻይ ሀ/ሰላሴ
25. ወ/ሮ አልማዝ አርኣያ
26. ወ/ሮ አሰለፈች በቀለ
27. ወ/ሮ አስቴር አማረ
28. አቶ አለምሰገድ ወረታ
29. ዶ/ር አድሃና ሃይለ
30. አቶ ኪሮስ ወ/ሚካኤል
31. አቶ ሹምዬ ገብሬ
32. አቶ ካሳ ጉግሳ
33. ወ/ሮ አበራሽ አድማሱ
34. አቶ ዮሀንስ በቀለ
35. አቶ ዳኘው በለጠ
36. ወ/ሮ ፅዋሃብ ታደሰ
37. አቶ ዊንታ ተክሉ እና
38. አቶ ግርማይ ሻዲ ናቸው፡፡
ምንጭ፡- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዙሪያ በስሙ የተሰራጨው ዜና እንደማይወክለው ብሄራዊ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ገለፀ!
ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያ እና አምባሳደር ኢብራሂም እንድሪስ ትናንት ለዋልታ ቴሌቪዥን "የጁንታው ህወሃት ቡድን የእንደራደር ጥሪ ፍጹም ተቀባይነት የለውም" በሚል የሰጡት አስተያየት እርቀሰላም ኮሚሽንን የሚወክል እንዳልሆነ የኮሚሽኑ ህዝብ ግኑኝነትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አርቲስት ደበበ እሸቱ ለአዲስ ዘይቤ ገለፁ።"የእኛ ስራ ችግር ከመፈጠሩ በፊት ሰላም ማውረድ ነው፡፡ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አሁን ባለበት ሁኔታ ጣልቃ ሊገባ አይችልም፡፡ ምክኒያቱም ኮሚሽኑ ችግር ከመፈጠሩ በፊት ነው እንጂ አንዴ ከተፈጠረ በኋላ እንዲህ እናድርግ አይልም ይህን ጉዳይ አሁን የሚመለከተው የሰላም ሚኒስትር ነው" ብለዋል አርቲስት ደበበ፡፡
ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያ የሰጡት አስተያየት በጠቅላላ በፍፁም የእርቀሰላም ኮሚሽኑን አይወክልም፤ በእርቀሰላም ኮሚሽን ስምም ይህን መግለጫ ሊሰጥ አይችልም ያሉት ህዝብ ግንኙነቱ በዜናው የተጠቀሱት አምባሳደር ኢብራሂም እንድሪስ የተባሉት ግለሰብ ደግሞ ጭራሽ የኮሚሽኑ አባል እንዳልሆኑ አርቲስት ደበበ ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል፡፡ይህ ግጭት ከመፈጠሩ በፊት እርቅ ለማውረድ የተሞከሩ ጥረቶች እንደነበሩ አርቲስት ደበበ ያስታወሱ ሲሆን "የሞከርናቸው ነገሮች ነበሩ የኛ አባላት እዛው ትግራይ ድረስ ሄደውም አነጋግረው ነበር ሁለቱም ወገኖች ለእርቅ ፈቃደኛ ነን ይላሉ ነገር ግን ተግባራዊ ማድረግ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነበር፤ ሁለቱም ገፍተው ሊመጡ አልቻሉም ጥረታችን ግን አላበቃም ነበር ድጋሜ ሄደን ልንሞክር እቅድ እያለን ነበር ይሄ ነገር የተፈጠረው" ብለዋል፡፡
Via Addis Zeybe

የናይል ተፋሰስ ሃገራት ኢኒሽዬቲቭ (NBI) የሚኒስትሮች ምክር ቤት (NBI-COM) ዛሬ 28ኛ መደበኛ ዓመታዊ ጉባዔውን በኦን ላይን የግንኙነት ዘዴ (ቨርቹዋል) ያካሂዳል፡፡ ጉባዔው ኢትዮጵያን ጨምሮ የተፋሰሱ አባል በሆኑ 10 ሃገራት የውሃ ሚኒስትሮች የሚካሄድ ሲሆን በበጀት እና ተያያዥ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ ይመክራል፡፡የኢትዮጵያ የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለም በስብሰባው እንደሚሳተፉ…
ስለሺ በቀለ የኢኳቶሪያል ሃይቆች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሆነው ተመረጡ!
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢ/ር) በናይል ተፋሰስ ሃገራት የኢኳቶሪያል ሃይቆች የሚኒስትሮች ምክር ቤት (NEL-CoM) ሰብሳቢ ሆነው ተመረጡ፡፡ሚኒስትሩ የተመረጡት ዛሬ በዌቢናር በተካሄደው የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ (NBI) 28ኛው የናይል ተሰፋሰስ ሃገራት የሚኒስትሮች ምክር ቤት (NILE-CoM) እንዲሁም 23ተኛው በናይል ተፋሰስ የኢኳቶሪያል ሃይቆች ሃገራት የሚኒስትሮች ምክር ቤት መደበኛ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ነው፡፡በመሆኑም ለሚቀጥለው አንድ አመት በናይል ተፋሰስ ሃገራት የኢኳቶሪያል ሃይቆች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሆነው እንደሚያገለግሉ ሚኒስቴሩ በማህበራዊ ገጹ አስታውቋል፡፡በተመሳሳይ ጉባኤው የርዋንዳ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስተሯን ጂያን ዲአርክ ሙጃዋማሪያን (ዶ/ር) የናይል ተሰፋሰስ ሃገራት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ አድርጎ ሰይሟል፡፡በጉባዔው ኢትዮጵያን ጨምሮ የቡሩንዲ፣ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ፣ ሱዳን፣ ግብጽ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እንዲሁም የኡጋንዳና ታንዛኒያ የውሃ ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል፡፡

የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ በመጥለፍ የተጠረጠሩ 7 የጄኔራል መኮንኖች ፍርድ ቤት ቀረቡ!
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛን በመጥለፍ እና የመገናኛ ሥርዓት እንዲቋረጥ በማድረግ፣ ዕዙ በጁንታው የሕዋሓት የጥፋት ቡድን ጥቃት እንዲፈፀምበት ሲያመቻቹ ተገኝተዋል በሚል የጠረጠራቸውን 7 የጄኔራል መኮንኖች ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቧል። ጄኔራል መኮንኖቹ በሀገር ክህደት እና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በመናድ ወንጀል የተጠረጠሩ መሆናቸው ተገልጿል።
Via ETV