በአዲስ አበባ አድዋ ድልድይ ስር ዛሬ ጠዋት ከፍተኛ የፍንዳታ ድምጽ መስማታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች ገለጹ።
ፍንዳታው እንዴት እንደደረሰ እንደማያውቁ የሚናገሩት የዓይን እማኞች ሆኖም በፍንዳታው የተጎዳ ሳይሆን አይቀርም የተባለ አንድ ሰው ከድልድይ ስር ወጥቶ ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ መመልከታቸውን አስረድተዋል። የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት፤ ፍንዳታው ተሰማበት የተባለበትን የድልድዩን ክፍል እግረኞች እንዳይተላለፉበት አጥረው ምርመራ ሲያደርጉ የ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘጋቢ ተመልክቷል።የፌደራል ፖሊስ የፎረንሲክ እና ፈንጂዎች ምርምራ ቡድን ተሽከርካሪዎች እስከ ረፋዱ አምስት ሰዓት ድረስ በአካባቢው ቆመው ነበር። የአድዋ ድልድይም ሆነ ሌሎች መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ባይደረጉም በርከት ያሉ ፖሊሶች በአካባቢው የጸጥታ ቁጥጥር በማድረግ ላይ ናቸው።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa

YeneTube
በአዲስ አበባ አድዋ ድልድይ ስር ዛሬ ጠዋት ከፍተኛ የፍንዳታ ድምጽ መስማታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች ገለጹ። ፍንዳታው እንዴት እንደደረሰ እንደማያውቁ የሚናገሩት የዓይን እማኞች ሆኖም በፍንዳታው የተጎዳ ሳይሆን አይቀርም የተባለ አንድ ሰው ከድልድይ ስር ወጥቶ ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ መመልከታቸውን አስረድተዋል። የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት፤ ፍንዳታው ተሰማበት የተባለበትን…
#Update
ዛሬ ኅዳር 2 ጧት በአድዋ ድልድይ ስር ቦንብ ያፈነዳው ግለሰብ ተይዟል።
በስፍራው በርከት ያሉ ፖሊሶች ተሰብስበው የነበረ ሲሆን፤ ቦንቡ ጉዳት ሳያደርስ መፈንዳቱንና ለማፈንዳት የሞከረው ግለሰብ ሳይጎዳ እንዳልቀረ ያገኛቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።የቦንብ ፍንዳታው ከተፈፀመበት ድልድይ አጠገብ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአድዋ ድልድይ አካባቢ ቢሮ እና ሲግናል ጋር የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት አባላት መኖሪያ መንደር ይገኛል።
[አሐዱ ቴሌቪዥን]

በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል የሚደረገውን ጦርነት ተከትሎ ከ6ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሱዳን መሸሻቸውን የሱዳን ባለስልጣናትን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
የሱዳን ባለስልጣናት በቀጣይ ቀናት እስከ 200 ሺህ ኢትዮጵያውን ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን ሊገቡ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የትግራይ ልዩ ኃይል በአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ሰንዝሯል ካሉ በኋላ የአገር መከላከያ ሠራዊት እርምጃ እንዲወስድ ማዘዛቸው ይታወሳል።
ሮይተርስ የዜና ወኪል በዘገባው ወደ ሱዳን ድንበር የተሻገሩት ስደተኞች ሲቪል ወይም ወታደራዊ ይሁኑ ያለው ነገር የለም።የስደተኞቹ ቁጥር ትናንት ማክሰኞ 6ሺህ መድረሱን የሱዳን የስደተኞች ኮሚሽን ገልጾ ቁጥሩ ከዚህም ሊለቅ እንደሚችል ስጋቱን አስቀምጧል።
[BBC/Reuters]

#Update ዛሬ ኅዳር 2 ጧት በአድዋ ድልድይ ስር ቦንብ ያፈነዳው ግለሰብ ተይዟል። በስፍራው በርከት ያሉ ፖሊሶች ተሰብስበው የነበረ ሲሆን፤ ቦንቡ ጉዳት ሳያደርስ መፈንዳቱንና ለማፈንዳት የሞከረው ግለሰብ ሳይጎዳ እንዳልቀረ ያገኛቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።የቦንብ ፍንዳታው ከተፈፀመበት ድልድይ አጠገብ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአድዋ ድልድይ አካባቢ ቢሮ እና ሲግናል ጋር የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት…
በአድዋ ድልድይ ስር የፈነዳው ፈንጂ፤ ፍተሻው በመጠንከሩ እጃቸው ላይ እንዳይገኝ የፈሩ የጣሉት እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ስሙ አድዋ ድልድይ በሚባለው ቦታ ከጠዋቱ 2 ሰአት አካባቢ አንድ የታክሲ የረዳት ልጅ ለመፀዳዳት ወደ ድልድዩ ስር ገብቶ በነበረበት ወቅት በማዳበርያ ተጠቅልሎ የታሰረ ነገር አይቶ ምን ይሆን ብሎ ሲነካው እንደፈነዳ ተገልጧል፡፡ልጁ ቀላል ጉዳት ደርሶበት ምኒሊክ ሆስፒታል እየታከመ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮማንደር ፋሲካ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ኮማንደር ፋሲካ የጸጥታ ሀይሉ ባጠቃላይ በጥምር ተደራጅቶ የቁጥጥር፣የፍተሻ እና ድንገተኛ የአሰሳ ስራ እየሰራ ነው ሲሉ የገለፁ ሲሆን የህዝቡ ጥቆማና የፀጥታ ሀይሉ ጠንካራ እንቅስቀሴ ያስጨነካቸውና ያስፈራቸው እጃቸው ላይ ጦር መሳርያ ያላቸው ሰዎች እየመጡ ከሚያስረክቡት ሌላ ፤ ውጪ እየጣሉ የሚገኙ አሉ ብለዋል፡፡
በተለይ በአቃቂ ቃሊቲ፣በቦሌ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣በኮልፌ ቀራኒዮ እና ወጣ ወጣ ባሉ አካባቢዎች ይሄ ተስተሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ህብረተሰቡ በተለያየ መንገድ እጁ ላይ ጦር መሳርያ ካለ እንዲያስረክብ ጥሪያቸውን ያቀረቡ ሲሆን አካባቢውን በጥንቃቄ መከታተሉን፣መጠቆሙን እና መሰል ቁሶችን በጥንቃቄ መመርመሩን እንዳይረሳ አሳስበዋል፡፡
Via Ethio FM

በሀገራችን ባለፉት 3 ወራት ብቻ የ927 ሰዎች ህይወት በትራፊክ አደጋ ምክኒያት አልፏል!
በፌደራል ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የመንገድ ደህንነት ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ ለማ ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፁት በያዝነው ዓመት የመጀመርያ ሩብ ዓመት(ሶስት ወራት) ብቻ በአጠቃላይ 3442 ያህል የትራፊክ አደጋ የደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 927 የሞት አደጋ ነበር፡፡የደረሰው የሞት አደጋ ይህ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ15.26 በመቶ ቀንሷል ተብሏል፡፡
ከባድ የአካል ጉዳት ደግሞ 1382 የተመዘገበ ሲሆን ቀላል ደግሞ 1133 አደጋ ነበር፡፡አቶ ዮሃንስ አክለውም በንብረት ላይ 176 ሚሊዮን 156 ሺህ 811 ብር ያህል ጉዳት እንደደረሰም ገልፀዋል፡፡በተመሳሳይ ደግሞ በአዲስ አበባ ባለፉት 3 ወራት ብቻ 103 የትራፊክ የሞት አደጋዎች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ትራፊክ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጅሬኛ ሂርጳ ( ኢንጅ) ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል።የአለም የጤና ድርጅት ባስቀመጠው ደረጃ መሰረት ኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ ምክኒያት በየአመቱ በሚደርስ ሞት ከአለም 24ኛ ላይ ተቀምጣለች፡፡
Via Addis Zeybe

በአማራ ክልል ሕዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ በነገው እለት ይካሄዳል!
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽኀፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ሰልፉን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም ‹‹መላው የክልላችን ህዝብ፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች ህገ ወጡ የትህነግ ቡድን ያደረሰውን ግፍ እና የአገር ክህደት ወንጀል ለመላው ዓለም በምንችለው ሁሉ ለማሳወቅ የሰልፉ ተሳታፊ አንድንሆን ጥሪ እናቀርባለን›› ብለዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለጹት ከሆነም ‹‹ ሰልፉ የሚካሄደውም በክልላችን ባህር ዳር፣ ፍኖተ ሰላም፣ እንጅባራ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ ደብረ ታቦር ከተሞች ብቻ ነው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡‹‹ከእነዚህ ከተሞች ውጭ ባሉ የክልሉ ከተሞች ሰልፉ የማይካሄደው ህገ ወጡን የትህነግ ቡድን በህግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል በሚደረገው ውጊያ ልዩ የጸጥታ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ነው›› ሲሉም አክለዋል፡፡ሰልፉ ነገ ኀዳር 03/2013 ጠዋት 2፡30 ተጀምሮ በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ሲሆን በተዋቀረው የሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ እና በጸጥታ ኃይላችን ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለት መሆኑንም ከአማራ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

በአማራ ክልል ሕዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ በነገው እለት ይካሄዳል! የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽኀፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ሰልፉን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም ‹‹መላው የክልላችን ህዝብ፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች ህገ ወጡ የትህነግ ቡድን ያደረሰውን ግፍ እና የአገር ክህደት ወንጀል…
በተመሳሳይ ሕወሃት በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሚያና በሶማሊ ክልልም ከነገ ህዳር 3 ቀን 2013 ጀምሮ ሊደረግ መሆኑን የየክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮዎች ገልጸዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የባህሬን ጠቅላይ ሚኒስትር ልዑል ከሊፋ ቢን ሰልማን ዓረፉ!
ሀገራቸውን ከነጻነቷ በፊት ጀምሮ ለ50 አመት ጠ/ሚ ሆነው ያገለገሉት ልዑሉ ለረዥም ጊዜ ካገለገሉ የዓለም መሪዎች አንዱ ናቸው፡፡የሀገሪቱ መንግስት ለ1 ሳምንት የሚቆይ የሀዘን ጊዜ አውጇል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ሀገራቸውን ከነጻነቷ በፊት ጀምሮ ለ50 አመት ጠ/ሚ ሆነው ያገለገሉት ልዑሉ ለረዥም ጊዜ ካገለገሉ የዓለም መሪዎች አንዱ ናቸው፡፡የሀገሪቱ መንግስት ለ1 ሳምንት የሚቆይ የሀዘን ጊዜ አውጇል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከትግራይ ልዩ ሃይል ጋር በማበር በአገር መከላከያ ሰራዊት ጥቃት የተሳተፉ አባላቱን እያጠራ መሆኑን አስታወቀ።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ከታጠቁ እና ጸረ -ሰላም ከሆኑ ሀይሎች ጋር ግንኙነት ያላቸውን አባላቱን በመለየት እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡የግንባሩ ቃላ ቀባይ አቶ ቀጀላ መርዳሳ እንዳሳወቁት ከሰሞኑ በተለያዩ የመንግስት መግለጫዎች ከህወሃት ቡድን ጋር የኦነግ ሸኔ አባላት በጦርነቱ መሳተፋቸው ተነግሯል፡፡ይሁን እንጂ ኦነግ የሚለው ስም ከዚህ ተቀጥሎ እንዳይጠራ እየተነጋገርን ነው ብለዋል፡፡ምክንያቱም እኛ ከሸኔ ጋር ግንኙነት የለንም ፤የታጠቀ ሰራዊትም የለንም ነው ያሉት፡፡
ኦነግ በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ ምህዳሩን ተቀላቅሏል፣ የምንሰብቀው ጦርም የለም በእኛ ስም የሚንቀሳቀስ የታጠቀ ሃይል ካለ መንግስት እርምጃ ይውሰድ ሲሉ ተናግረዋል፡፡እንዲህ አይነት ተግባራት ላይ የሚሳተፉ እንዲሁም በተዘዋዋሪ ደግሞ ድጋፍ የሚሰጡና የሚያሰባስቡ አባላቶቻችንን እየለየን ነው ብለዋል አቶ ቀጀላ፡፡መንግስት በሚሰጣቸው መግለጫዎች የኦነግ ሸኔ አባላት ሳይሆን የሸኔ ታጣዊዎች እንዲልም አሳስበዋል፡፡አቶ ቀጀላ እንዳሉት በቀደመው ዘመን ሸኔ ማለት የስራ አስፈጻሚ አባላት የሚጠሩበት እንደነበር አስታውሰው በኃላ ላይ ግን ይህንን ስም አሁን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቲ በሚል እየተጠራ ነው ብለዋል፡፡

እስር ቤት የነበሩ 273 ኢትዮጵዊያን በዛሬው ዕለት ከሳኡዲ አረቢያ ጄዳ ከተማ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን በጄዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት አስታወቀ።
ከዛሬ ተመላሾች ውስጥ 134 ታዳጊ ልጆች፣ 137 ሴቶች እና 2 ህጻናት ቆንስላ ጽ/ቤቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የሳዑዲና የአገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ባደረገው ጥረት ጄዳ ከተማ ከሚገኘው የሼሜሲ እስር ቤት ወተው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ጉዳዩ ከሚመከታቸው መ/ቤቶች የተወከሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ከጄዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሜ/ጄ ይልማ ፣ አየር ኃይሉ ጠላት ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን ምርጥ ኢላማዎች በመደብደብ ከጥቅም ውጭ ማድረጉን አስታወቁ።
"ለጁንታው" እስትንፋስ የነበሩ የነዳጅ ዴፖዎች፣ የመሳሪያ ማከማቻዎች እና ሌሎች ምርጥ ኢላማዎችን ጀቶቻችን ያለምንም ከልካይ እንዳሻቸው እየተመላለሱ አውድመዋቸዋል ብለዋል።ፓይለቶች የተመረጡ ዒላማዎችን ለመደምሰስ መሣሪያ ጭነው እየሄዱ ሲቪል የሚጎዳ ከመሰላቸው ሳይተኩሱ በመመለስ ነጥሎ የመምታት ስትራቴጂ እየተከተሉ እንደሚገኙም አስረድተዋል። "ጁንታው" እንመታለን የሚለው ፣ እድሜውን ሲዋሽ ስለኖረና እየዋሸ ስለሚቀበር ባህሪው ነው ያሉት ሜ/ጀ ይልማ ፣ ባሻን ሰዓት እየተመላለስን ለህግ እስኪቀርብ ማጥቃታችንን እንቀጥላለን ብለዋል።
Via FDRE Defense

ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ህወሃት በአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ በማዘጋጀት ላደራጃቸው ታጣቂዎች በማልበስ ኤርትራ እንደወረረች በመግለጽ ህዝብን እያደናገረ ነው ሲሉ ተናገሩ።
ሁመራና አካባቢው ሙሉ ለሙሉ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር መዋሉን የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ አስታወቁ።
ሰራዊቱ በአሁኑ ሰዓት ከሁመራ እስከ ሽራሮ ያለውን ቦታ በማጥቃት የተለያዩ ስፍራዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሚገኝም አመልክተዋል።
ሰራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ የእርዳታ ድርጅቶች ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ተነጋግረው ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
የ'ህወሃት ጁንታ' በአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ በማዘጋጀት ላደራጃቸው ታጣቂዎች በማልበስ ኤርትራ እንደወረረች በመግለጽ ህዝብን እያደናገረ እንደሆነም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።በዚህ የተቀናበረ ድራማ ህዝቡ ሳይታለል ለመከላከያ ሰራዊቱ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በታሸጉ ውሃ ላይ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ መሰረት በማድረግ የተደራጀው የንግድ ክትትልና ቁጥጥር ግብረ ሀይል ባደረገው ምልከታ ምክንያታዊ ያልሆነ ዋጋ ጭማሪ በአንዳንድ ነጋዴዎች ላይ መስተዋሉን መሠረት በማድረግ መንግስት ከሚመለከታቸው የታሸገ ውሃ አምራቾችና ማህበራት ጋር ውይይት ማድረጉነን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አከበረኝ ወጋገን እንደገለፁት የተስተዋለው ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ መከሰቱ የተረጋገጠ መሆኑን ተናግረው የኢትዮጵያ የታሸገ ውሃ፣ የለስላሳ መጠጥ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማኀበር እና ከኢትዮጵያ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ጋር በጋራ በመሆን በተደረገ ውይይት የዋጋ ጭማሪው ተገቢ አለመሆኑን በመተማመን ሁሉም የታሸጉ ውሃዎች የመሸጫ ዋጋ በነበረበት የሸያጭ ተመን እንዲሸጥ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡
ቢሮው ከዛሬ ጀምሮ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወስድ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ማንኛውም የንግድ ተቋምም ሆነ ቸርቻሪ ነጋዴ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የታሸገ ውሃ መሸጫ ዋጋ ላይ ያደረገውን ጭማሪ በማንሳት በፊት በነበረበት የመሸጫ ዋጋ እንዲያስተካክል ም/ቢሮ ኃላፊው ማሳሰባቸውን ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ስራቸውን በይፋ ጀመሩ፡፡
ሚኒስትሩ በዛሬው እለት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመስሪያ ቤቱ በመገኘት ትውውቅ አድርገዋል፡፡በዚህ ወቅትም የስራ ሃላፊዎቹ ዝርዝር የስራ ሂደታቸውን በተመለከተ ለሚኒስትሩ ገለጻ አድርውላቸዋል፡፡ተሰናባቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም ለአዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተሳካና መልካም የስራ ዘመን እንደተመኙላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአዳማ ከተማ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ!
በአዳማ ከተማ በሉጎ ክፍለ ከተማ ቢቃ ቀበሌ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።በቦታው የተገኘው አዲስ ዘይቤ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች፣ መገናኛ ሬድዮዎች፣ ፎቶ ካሜራዎች ፣ የጦር ሜዳ አጉሊ መነፅር እና ጥይቶችን በቁጥጥር ስር መዋሉን ተመልክቷል፡፡
የከተማው ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር መንግስቱ ኢጃራ በከተማዋ በተደረገ አሰሳ 3 የአባቶርቤ አባላት ከነጦር መሳሪያቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።የከተማዋ ነዋሪዎች ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን የአካባቢያቸውን ሰላም ለማስጠበቅ ከምንግዜውም በላይ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ያሳሰቡት ኮማንደሩ ዛሬ የተገኘው የጦር መሳሪያ በህብረተሰቡ ጥቆማ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ኤርትራ እና ሱዳን በኢትዮጵያ ጉዳይ መወያየታቸው ተገለጸ!
የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አማካሪ የማነ ገብረ አብ የተካተቱበት የኤርትራ ልዑክ ዛሬ ካርቱም አቅንቶ ከሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ም/ቤት ፕሬዝዳንት አል-ቡርሃን እና ከጠ/ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ጋር መወያየቱን የሱዳን ዜና ወኪል ዘግቧል፡፡የኤርትራ ልዑክ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ የተላከ መልዕክት ለሱዳን መሪዎች ያደረሰ ሲሆን በቆይታቸው ከሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ካደረጉት ውይይት በተጨማሪ የሁለቱም ጎረቤት በሆነችው ኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ችግር መምከራቸውንም የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል በትዊተራቸው ገልጸዋል፡፡ይሁን እንጂ ስለውይይታቸው የተባለ ዝርዝር ጉዳይ የለም፡፡
Via Al ain

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከሁመራ 60 ኪ.ሜ ወደ ምሥራቅ ኢድሪስ በሚባል ቦታ ላይ የሕወሓት የጥፋት ቡድንን በመደምሰስ ላይ ይገኛል- ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ
"በሕወሓት የጥፋት ቡድን" ከበባ ውስጥ ገብቶ ለአምስት ቀናት ምግብና ውሃ ተከልክሎ የነበረው የሰሜን ዕዝ ጦር ከከበባ በመውጣት ራሱን መልሶ በማደራጀት እያጠቃ በርካታ ቦታዎችን በመቆጣጠር ወደፊት በመገስገስ ላይ መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።ሠራዊቱ በአሁኑ ወቅት ከሁመራ 60 ኪ.ሜ ወደ ምሥራቅ ኢድሪስ በሚባል ቦታ ላይ የጥፋት ቡድኑን እየደመሰሰ እንደሚገኝም ተናግረዋል።“ሠራዊታችን በተፈጸመበት ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በመበሳጨቱ በከፍተኛ ወኔ፣ ጀግንነትና ተነሳሽነትም ሁሉንም ነገር ወደነበረበት ለመመለስ እና ከሃዲውን ቡድን በሕግ ፊት ቀርቦ እንዲቀጣ ለማድረግ እየሠራ ነው” ብለዋል-ጀኔራል ብርሃኑ።
ሙሉ የኢቲቪ ዘገባ👇👇
https://telegra.ph/-11-11-911

መንግሥት ትናንት ማታ 4 ጋዜጠኞችን ማሰሩ እንዳሳሰባቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዳንዔል በቀለ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። ኮሚሽነሩ ትናንት ታሰሩ ያሏቸው ጋዜጠኞች፣ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ የሚሰሩት ሃፍቱ ገ/እግዚአብሔር፣ ጸጋዬ ሃዱሽ እና አብርሃ ሐጎስ እንዲሁም ለኦሮሞ ሜዲያ ኔትወርክ የሚሰራው ኡዲ ሙሳ ናቸው። የጋዜጠኞቹ ጉዳይ በትክክለኛ የሕግ አግባብ እንዲታይም ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በአማራ ክልል ሕዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ በነገው እለት ይካሄዳል! የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽኀፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ሰልፉን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም ‹‹መላው የክልላችን ህዝብ፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች ህገ ወጡ የትህነግ ቡድን ያደረሰውን ግፍ እና የአገር ክህደት ወንጀል…
ነገ በአማራ ክልል ሊካሄድ የነበረው ሰልፍ ለሌላ ጊዜ ተራዘመ!
በነገው እለት በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ሊካሄድ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ወደሌላ ጊዜ የተላለፈመሆኑን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።ሰልፉ “ህገ ወጡ የትህነግ መንግሥት እየፈጸመው ያለውን ግፍ ለመላው ዓለም ለማሳወቅ” በማሰብ እንደሚካሄድ የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ከሰዓታት በፊት በሰጡት መረጃ አስታውቀው ነበር፡፡በባህር ዳር፣ ፍኖተ ሰላም፣ እንጅባራ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ ደብረ ታቦር ከተሞች ብቻ እንደሚካሄድም ነበር የተገለጸው፡፡ሆኖም አሁን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አብመድ በዘገበው መሰረት ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ተደርጓል፡፡በምን ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ ሊተላለፍ እንደቻለ ግን የተገለጸ ነገር የለም፡፡