በኦሮሚያ የባንክ ገንዘብ በእንቅስቃሴ ላይ በነበረበት ወቅት የኦነግ ሸኔ አባላት ለመዝረፍ ያደረጉትን ሙከራን በፀጥታ ሀይሎች ከሸፈ።
በምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ አካባቢ ትናንት ምሽት የባንክ ገንዘብ በእንቅስቃሴ ላይ በነበረበት ወቅት የኦነግ ሸኔ አባላት ለመዝረፍ ያደረጉትን ሙከራን በፀጥታ ሀይሎች መክሸፉ ተነገረ፡፡የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ታዬ ደንደአ ፣ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ የባንክ ገንዘብ በእንቅስቃሴ ላይ በነበረበት ወቅት የኦነግ ሸኔ አባላት ለመዝረፍ ያደረጉትን ሙከራን በክልሉ የፀጥታ ሀይሎች መክሸፉ ተናግረዋል፡፡
ዘረፋ ለመፈፀም ሙከራ ያካሄዱት የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ የቆሰለ እና በቁጥጥር ስር የዋሉ መኖራቸውም ተናግረዋል፡፡ከኦነግ ሸኔ የዘረፋ ቡድን አባላት ያመለጡም መኖራቸውን እና በጥብቅ ክትትል በፀጥታ ሐይሎች እየታደኑ እንደሚገኝም አቶ ታዬ ገልፀዋል፡፡በአሁኑ ወቅት ክልሉ በሁሉም አቅጣጫዎች በልዩ ጥበቃ ላይ መሆኑንም ሀላፊው ተናግረዋል፡፡ልዩ ጥበቃውም ከሚሊሻ ፣ ከህዝቡ ፣ ከፖሊስ እና ከልዩ ሐይሉ ጋር በመጣመር የጥፋት ሀይሎች ሴራን ለማክሸፍ እየሰራ ነው ተብሏል፡፡
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa

ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከሽራሮ እስከ ዛላንበሳ ድረስ ያሉትን የሰሜን እዝ የጦር ክፍሎች በአሁኑ ሰዓት በጥሩ የዝግጁነት አቋም ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡በመግለጫቸው ከሽራሮ እስከ ዛላንበሳ ድረስ ያሉትን የሰሜን እዝ የጦር ክፍሎች በአካል አግኝተው መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡በስፍራው የጦር ሀይሎች ም/ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌ/ጀኔራል አበባው ታደሰ ሠራዊቱን አብረውት እየመሩት እንደሚገኙ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡
[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
ግዳጅ ላይ እያሉ ጥቃት የተፈጸመባቸዉ 11 የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ደባርቅ ገቡ፡፡
ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል መቀሌ ላይ ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና በጠገዴ አርማጭሆ በኩል ደግሞ በአማራ ልዩ ሀይል አባላትና ገበሬዎች ላይ የወረራ ሙከራ እንዲሁም በተከዜ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ጥበቃ ላይ በነበሩ የፌደራል ፖሊሰ አባላት ጥቃት ተሰንዝሮ ነበር፡፡ከጥቃቱ የተረፉት 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ህዳር 01/2013 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን መቀመጫ ደባርቅ ከተማ መግባታቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ዘገባው የAMN ነው

YeneTube
የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስትና ትግራይ ክልል መንግስት መካከል እየተካሄደ በሚገኝ ጦርነት በቀጥታ መሳተፍ ጀመረ ሲሉ የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ዶ/ር ደብረፅዮን ተናገሩ።በዚህም ጦርነቱ "ወደ ተለየ ምዕራፍ ተሸጋግሯል" ብለዋል። Via Million HaileSelasie @YeneTube @FikerAssefa
“የኤርትራ ወታደር ጥቃት እያደረሰብን ነው በሚል በደብረፂዮን ገብረሚካኤል የተሰጠው መግለጫ ፍፁም ሐሰት ነው ሲሉ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ ተናገሩ።
ሜጀር ጄነራል መሐመድ ለኢዜአ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ጁንታው በተለያዩ አጋጣሚዎች ለማደናገር ጥረት እያደረገ ይገኛል።ጁንታው ቀደም ሲል "በቂ ተዋጊ አለኝ፣ ሰሜን አዝም አብሮን ተሰልፏል፣ የመከላከያ ኃይሉን የጦር ጀቶች በሚሳኤል እንመታለን" የሚል ፉከራ ውስጥ እንደነበረ በማስታወስ፣ 'የትግራይ ምድር ለሚዋጉን ሁሉ መቀበሪያ ትሆናለች’ የሚል ዛቻም ያሰማ እንደነበር ገልጸዋል።“አሁን ያ ሁሉ ፉከራ ነገር አልሳካ ብሎ በመከላከያ ኃይሉ አከርካሪው እየተሰበረ ሲመጣ ሌላ የማደናገሪያ ሐሳብ ይዞ ብቅ ብሏል” ሲሉ ተናግረዋል ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ።
በመሆኑም ‘አሁን ላይ የኤርትራ ወታደር ጥቃት እያደረሰብን ነው’ በሚል በደብረፂዮን ገብረሚካኤል የተጠው መግለጫ ፍፁም ሐሰት መሆኑን ገልጸዋል።ኅብረተሰቡ ፅንፈኛ ቡድኑ በሚያሰራጫቸው የሐሰት ወሬዎች እንደይደናገርም መክረዋል።በፅንፈኛ ኃይሉ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸው፣ “በቅርቡም በርካታ የድል ዜናዎችን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እናበስራለን” ብለዋል።
ዘገባው የኢቲቪ/ኢዜአ ነው(Uncensored)

የኢፌዴሪ መከላከያ ኃይል በምእራብ ትግራይ ግንባር እየወሰደ ባለው ህግን የማስከበር እርምጃ እስካሁን 550 የህውሓት ታጥቂ ቡድን አባላት መደምሰሳቸው ተገለፀ።
በተጨማሪም 29 የልዩ ሃይል እና ሚኒሻ አባላትም ተማርከዋል።ህውሓት ታጣቂ ቡድን በዚህ በግንባር ከፍተኛ ቁሳዊ ኪሳራ የደረሰበት መሆኑም ተነግሯል።እስካሁንም 115 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 11 መትረየስ፣ 2 ድሽቃ፣ 8 አር ፒጂ ከባድ መሳሪያ፣ 152 የእጅ ቦንብ፤ 2 ስናይፕር፣ 4 ኤም-14 ጦር መሳሪያ፣ 2 ኢንኮም ሬድዬ ተማርኳል።
በተጨማሪም 21 ሺህ 650 የክላሽ ጥይት፣ 14 ሸህ 730 የመትረየስ ጥይት፣ 1 የጦር ሜዳ መነፅር፣ 64 የጦር ሜዳ ቀበቶ፣ 6 የአር ፒ ጂ ቅንቡላ፣ 90 የክላሽ መጋዘን እና 10 የመትረየስ ዝናር ተማርኳል።
እንዲሁም ከሰሜን እዝ 5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ተዘርፈው የነበሩ 5 ታንኮች ሲመለሱ አንዱ ወድሞ፤ አንድ ታንክ በጠላት እጅ ይገኛል።
የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል በላይ ስዩም፥ ህግን የማስከበር ዘመቻው በስፋት እና በድል ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።የሰራዊቱ ተልእኮን የመፈፀም ብቃት ከየትኛውም ጊዜ በላይ አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የተናገሩት ዋና አዛዡ፥ ስራዊቱ ዳንሻ ትርካን ዲቪዥን ባእኸር ራውያንን እና የሁመራ ከተሞችን መቆጣጠሩንም ተናግረዋል።
ዘገባው የኤፍ ቢ ሲ ነው

አቶ ገዱ አንዳጋቸው በካርቱም ከሱዳን መሪዎች ጋር ተወያዩ!
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳጋቸው ዛሬ ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ/ም በካርቱም ከሱዳን መሪዎች ጋር ተወያዩ፡፡መሪዎቹ በውይይታቸው ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ያላቸውን ሙሉ ድጋፍ ያረጋገጡ ሲሆን፤ ችግሩ ባጠረ ጊዜ እልባት ሊያገኝ እንደሚችል እምነታቸው መሆኑንም ገልፀዋል::አቶ ገዱ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተላከ መልዕክትንም ለሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሌትናንት ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ለጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ አድርሰዋል::
[Al ain]

የፀገዴ ወረዳን የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች ከተቆጣጠሩት በኋላ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ወደመደበኛ ኑሯቸው እየተመለሱ መሆኑ ተናገሩ።
በአማራ ክልል የጠገዴ ወረዳ መስሪያ ቤቶችም ሥራ እየጀመሩ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡ በራያ ቆቦ በኩል ያለው ሁኔታ ዉጥረt ያንዣበበት ከመሆኑ ዉጭ የተለየ ነገር እንደሌለም ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የትግራይ ልዩ ኃይል ግጭት ከፈጠሩባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ የፀገዴና ጠገዴ አካባቢ ነው፡፡ የፀገዴን ወረዳ የመከላከያ ሰራዊትና የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች ከተቆጣጠሩት በኋላ ህብረተሰቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እየተመለሰ እንደሆነና የከተማዋ ሰላም እንዲጠበቅ ስምሪት መሰጠቱን “ከተማ ንጉስ” ከተባለቸው የወረዳዋ ማዕከል አንድ አስተያየት ሰጪ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ኅብረተሰቡም ለመከላከያ ሰራዊትና ለአማራ ልዩ ኃይል ድጋፍ እደረገ እንደሆነም አመልክተዋል።
ዛሬ የገበያ ቀን በመሆኑም ሆቴሎችም ተከፍተው ኅብረተሰቡ በነፃነት ሰላማዊ ኑሮውን መኖር ጀምሯል ብለዋል የአካባቢው ነዋሪዎች። እንደዚሁም በአማራ ክልል በኩል የጠገዴ ወረዳ ማዕከል ቅራቅር ከተማ ያሉ ቢሮዎች በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ሥራ አቁመው የነበሩ ቢሆንም አሁን ስራ መጀመራቸውን የከተማዋ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በትግራይ ክልል አላማጣና በአማራ ክልል ቆቦ በኩል ያለው ሁኔታ ከውጥረት በስተቀር የተለየ ነገር እንደሌለ አንድ የከተማው ነዋሪ አመልክተዋል፡፡ ባንኮች ለአገልግሎት ክፍት ባይሆኑም አንዳንድ መስሪያ ቤቶች ክፍት መሆናቸውንም ገልፀዋል። በአማራ ክልል ስር የምትገኘው የቆቦ ከተማና በትግራይ ክልል ስር የምትገኘው አላማጣ ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ የሚገኙ ከተሞች ናቸው።
Via DW

የሰሜን ዕዝ ከማዕከል ጋር የሚኖረው የመገናኛ ሥርዓት እንዲቋረጥ በማድረግ "በጁንታው የህዋሃት የጥፋት ቡድን" ጥቃት እንዲፈፀምበት ሲያመቻቹ ነበሩ የተባሉ ጀነራል መኮንኖች ከነ ግብረ አበሮቹ በቁጥጥር ሥር ዋሉ።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በዛሬው ዕለት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ በመንግስት፣ በህዝብና በሀገር መከላከያ ሠራዊት የተጣለባቸውን አደራና ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው "የጁንታው ህወሃት" ሴራ አካል በመሆን የአገር ክህደት ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠሩ ጀነራል መኮንኖች፣ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል ሆነው ከጁንታው ህወሃት ጋር በመጣመር ጥቅምት 24, 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ በትግራይ ክልል የሚገኘው የሰሜን ዕዝ ከማዕከል ጋር የሚኖረው ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጥና የዕዙ የመገናኛ ሥርዓት "ለጁንታው የህዋሃት ወንበዴው ቡድን" እንዲመቻች በማድረግ የተጠረጠረው ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፈቃዱ ወይም በቅጽል ስሙ ወዲ ነጮ የተባለው ተጠርጣሪ በአገር ክህደት ወንጀል ከነ ግብረ አበሮቹ በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ተደርጓል።
ሙሉ መግለጫው👇👇
https://telegra.ph/-11-10-885
Via FBC(Uncensored)

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራ ሳይጠናቀቅ ከህወሃት ጋር ምንም አይነት ድርድር እንደማይኖር በትዊተር ገፃቸው ከላይ የተቀመጠውን በማለት አረጋግጠዋል።ታጣቂው ቡድን በሰሜን ኮማንድ አባላት ላይ ያደረሰውን በደልም መቼም አንረሳውም ብለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
“ከግጭቱ ዋዜማ የትግራይ መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተደዋውለው ነበር”- አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ወቅታዊ ሃገራዊ ሁኔታዎችን በማስመልከት መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የውጭ መገናኛ ብዙሃን ገለጻ አደረጉ፡፡“ከግጭቱ ዋዜማ የትግራይ ክልል መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተደዋውለው ነበር” ያሉት ቃል አቀባዩ “ሁኔታውን በቀላሉ እንደሚይዙት እና በንግግር ሊፈቱት እንደሚችሉ ተነጋግረው ነበር” ብለዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩም ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ በአዲስ የተቀየረውን ብር ወደ ትግራይ ለመላክ እና ክልሉ የእለት ተዕለት የቢዝነስ እንቅስቃሴ ለመደገፍ ቃል ገብተዋል፡፡ሆኖም በዚያው ቀን ምሽት በክልሉ በሚገኘው የሃገሪቱ ጦር የተለያዩ ጣቢያዎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት መከፈቱን ነው የገለጹት፡፡
ጥቃቱ በተመረጡ የሰራዊቱ አካባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት የተፈጸመ ነው፡፡በዚህም ተዋጊ ኃይል የሌለው የሰራዊቱ የመቀሌ ካምፕ በቀላሉ በጥቃት ፈጻሚዎቹ እጅ ሲገባ ሌሎች የሰራዊቱ አካባቢዎች ግን የተከፈተባቸውን ድንገተኛ ጥቃት ለመከላከል እና ወደተለያዩ አካባቢዎች ለማፈግፈግ ሞክረዋል፡፡“ሌሎች አካላት መጥተው እስከሚታደጉት ድረስም ሰራዊቱ ለሶስት ቀናት በከበባ ውስጥ ሆኖ ሲከላከል ቆይቷል” እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ፡፡“ጥቃቱ በተፈጸመ ማግስት የክልሉ መሪዎች ሊያጠቃቸው የሚመጣን የትኛውንም አካል ለመከላከል ብቻም ሳይሆን በተሻለ ለማጥቃት የሚያስችል አቅም እንዳላቸው መግለጻቸው ከሰራዊቱ የዘረፏቸውን ሮኬቶች እና ሚሳዔሎች በመተማመን ነው” ያሉት ቃል አቀባዩ ጦር መሳሪያዎቹ ተመልሰው ለጥፋት በማይችሉበት ሁኔታ እንዲወድሙ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
Via Al ain

በማይካድራ በዓለም አቀፍ ወንጀል የሚያስጠይቅ ዘር ማጥፋት መፈጸሙን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ!
እየሞትንም ቢሆን እናሸንፋለን! በሚል መግለጫ መልዕክት ያስተላለፉት አዲሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በማይካድራ የዘር ማጥፋት መፈጸሙን አስታወቁ።"ዝርዝሩ በፌደራል መንግስት በስፋት እንደሚገለፅ ብንጠብቅም፤ በዛሬዉ እለት ከአረመኔው የትህነግ ቡድን ነፃ በወጣችው በሁመራ አቅራቢያ በምትገኘው ማይካድራ ከተማ ነዋሪ በሆኑ የአማራ ወገኖቻችን ላይ በተሸናፊው የትህነግ ጦር አማካኝነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል" ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ "ቁጥሩ በሂደት ተጣርቶ ይፋ የሚደረግ መሆኑን እያሳወቅን ድርጊቱ በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑን እናምናለን" ብለዋል።
"ተሸናፊው ትህነግ በወገኖቻችን ላይ ይሄን አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀመው በህዝቦች መካከል የእርስ በርስ ጦርነት (Civil War) እንዲቀሰቀስ አስቦ መሆኑን እንደምታስተውል እናውቃለን" ሲሉ ለአማራ ህዝብ መልዕክት ያስተላለፉም ሲሆን "በተለመደው አስተዋይ ባህሪህ እንደ ትላንቱ ሁሉ ዛሬም ከየትኛውም ጥቃት ጥላ ከለላ ሁነህ ይህን ጊዜ እንድታሳልፈው ይሁን" ሲሉ ገልጸዋል።ርዕሰ መስተዳድሩ "በባህል፣ በሃይማኖት፣ በማህበራዊ ትስስር፣ አልፎም በረዥሙ የአገር ግንባታ ጉዞ" ከአንተ ጋር የጋራ ታሪክ አለው ካሉት የትግራይ ሕዝብ ጋር "መከታና ጋሻ ሆነህ አስተዋይነትና አብሮነት የምንጊዜም ምርጫህ እንደሆነ ለመላ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በተግባር እንድታሳይ" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
"የትግራይ ሕዝብ እንደትላንቱ ሁሉ፣ ዛሬም ሆነ ነገ አብሮህ ይኖራል። ዝንታለም ጠላትህ ትህነግና ወገኖችህን የጨረሰው የትህነግ ሰራዊት ነው። ስለዚህ ትህነግ ካጠመደልህ ወጥመድ ሳትገባ፤ የወገኖችህን ደም የምትመልሰው ትህነግንና ገዳይ ሰራዊቱን እስከመጨረሻው በመፋለም መደምሰስ ሲቻል ነው"ም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ያሉት።አቶ አገኘሁ "ስለቀጣይ እርምጃችን ሁኔታዎችን እየገመገምን እናሳውቃለን ብለዋል።ያም ሆኖ "ትህነግ ካጠመደው ወጥመድ እንዳትገባለት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግህን ለአፍታም ቢሆን እንዳትዘነጋ" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ተገለፀ!
በምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች አንዳንድ ከተሞችና ወረዳዎች ውስጥ የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት እንደተቸገሩ የተናገሩ ግለሰቦች ገለፁ።
የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በተጠቀሱ ስፍራዎች አገልግሎቱ ስለመቋረጡ መረጃ እንደሌላቸው አስታውቀዋል።
መንግሥት "በቦታው የሚንቀሳቀሱ አጥፊ ሃይሎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው። አካባቢውን ሰላም ለማድረግ እርምጃው ይቀጥላል" ብለዋል አቶ ጌታቸው።
በዚህ ዙሪያ ከኢትዮ-ቴሌኮም የሥራ ሃላፊዎች መረጃ ለማግኘት አልተቻለም።
Via VoA

አዋሬ አካባቢ ለአደጋ ተጋላጭነቱ እየታወቀ ዕርምጃ ባለመወሰዱ በተደጋጋሚ ጉዳት እየደረሰበት መሆኑ ተነገረ!
የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ በየካ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ አካባቢዎች የአዋሬ አካባቢ ቁጥር አንድ የአደጋ ተጋላጭ መሆኑን አጥንቶ፣ ለሚመለከታቸው አካላት የመፍትሔ ዕርምጃ እንዲወስዱ ምክረ ሐሳብ ቢያቀርብም፣ ተግባራዊ ባለመደረጉ በተደጋጋሚ አደጋ እያጋጠመው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በአዋሬ አካባቢ የደረሰውን የእሳት አደጋ አስመልክቶ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የአካባቢው የአደጋ ተጋላጭነቱ በኮሚሽኑ በኩል ተጠንቶ ነበር ብለዋል፡፡ ከጥናት ባለፈም ከየካ ክፍለ ከተማ፣ ከወረዳውና ከኅብረተሰቡ ጋር ውይይት መደረጉንም አስረድተዋል፡፡
አካባቢው በጣም ለአደጋ የተጋለጠ ስለሆነ ነዋሪዎች ወደ ሌላ ሥፍራ የሚዘዋወሩበትን ምክረ ሐሳብ ኮሚሽኑ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም፣ ይህ በሚመለከታቸው አካላት ተግባራዊ አለመደረጉን ገልጸወዋል፡፡እሳቸው በወቅቱ የኮሚሽኑ ባልደረባ ባይሆኑም ያገኙትን መረጃ ጠቅሰው እንዳስታወሱት፣ በሥፍራው በ2004 ዓ.ም. ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር፡፡
አካባቢው ለአደጋ ተጋላጭ በመሆኑ በኮሚሽኑ በኩል ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን፣ ሆኖም ይህ ተግባራዊ ባለመሆኑ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አዋሬ ገበያ ማዕከል ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ከሌሊቱ 10፡54 ሰዓት ላይ መንስዔው ባልታወቀው የእሳት አደጋ፣ አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ገልጸዋል፡፡ ኮሚሽኑ ከኅብረተሰቡ፣ ከአዲስ አበባና ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር 130 ሺሕ ሊትር ውኃ ተጠቅሞ አደጋውን ከማለዳው በ1፡50 ሰዓት ላይ በመቆጣጠሩ አራት ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ማትረፉንም አክለዋል፡፡ በአደጋው የሞትም ሆነ የአካል ጉዳት አልደረሰም ብለዋል፡፡
Via Reporter

ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ የወጡ ሐሰተኛ ምሥሎች የትኞቹ ናቸው?
በትግራይ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ በርካታ ሐሰተኛ ምስሎች በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ እየተጋሩ ይገኛሉ።የቢቢሲ <ፋክትቼክ ቡድን> አንዳንዶቹን ምሥሎች ነቅሶ አውጥቷቸዋል።
ምሥሎቹ በጭራሽ ከዚህ ጦርነት ጋር ተያያዥ አይደሉም።አንዳንዶቹ እውነት እንዲመስሉ ሆን ተብለው በልዩ ጥበብ የተቀናበሩ መሆናቸውን ተገንዝቧል።ከእነዚህም መካከል በስፋት የተጋሩ የተጭበረበሩ 3 ፎቶዎች የሚከተሉት ናቸው።
1ኛ፦ የሚሳይል መቃወሚያ (ሚሳይል ዲፌንስ ሲስተም) ከዚህም ባሸገር የሩሲያ ሰራሽ እሳት (አረር) የሚተፋ መሣሪያ (flamethrower system)
2ኛ፦ ተመትቶ ወደቀ የተባለው ተዋጊ ጄት
3ኛ፦ የተጭበረበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ፎቶ
ስለፎቶዎቹ ዝርዝር መረጃ ማወቅ ከፈለጉ👇👇
https://bbc.in/38vX6hf

0a759d40-6ffe-4c36-bfe8-a13019dd9692_16k
<unknown>
የሶማሌ ክልል አስተማማኝ ሰላም እንዳሰፈነና የፌዴራል መንግሥትንም በሚጠበቅበት ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁ እንደሆነ አስታወቀ። የክልሉ ተጠባባቂ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “በትግራይ ክልል እየተወሰደ ነው” ያሉት ህግን የማስከበር ዘመቻ በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።
የትግራይ ክልል የድርድር ጥያቄ ከማቅረቡ በፊት ህገመንግሥቱን በመጣስ ያካሄደውን ምርጫ ውድቅ ማድረግ፣ በውስጡ የደበቃቸውን ወንጀለኞች አሳልፎ መስጠትና ለሰላም ዝግጁ መሆኑን ማረጋገጥ ነበረበት ያሉት አቶ ሙስጠፌ ይህ ህግን የማስከበር እርምጃ እንጂ ዓለም አቀፍ ድርድር አያስፈልገውም ብለዋል። ሁሉም ክልሎች የትግራይ ክልል ተወላጆችን መብት ያላግባብ እንዳይጥሱ አቅጣጫ እንደተቀመጠላቸውም አስታውቀዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ የፀጥታ ስጋት እየፈጠረ ከሚገኘው ቡድን ጥቃት ሸሽተው ጠፍተው የነበሩ የጤና ባለሙያዎች የፌዴራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት ባደረጉት ጥረት በሠላም ተገኙ!
የጤና ባለሙያዎቹ፣ ከቀናት በፊት ከጉብላክ ወደ ማንቡክ በመሄድ ላይ እያሉ የጥፋት ቡድኑ በሚያደርሰው ጥቃት ምክንያት ሸሽተው ወደ ጫካ ገብተው መጥፋታቸው ከተሠማ ወዲህ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የክልሉ የጸጥታ ኃይል በጋራ ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡
የጸጥታ አካላት ባከናወኑት የተቀናጀ ተግባርም፣ በአካባቢው በነበረው የጸጥታ ችግር በጫካ ውስጥ ጠፍተው የነበሩ 6 የጤና ባለሙያዎችና 1 ሹፌር በድምሩ 7 ሰዎች ዛሬ በሠላም ተገኝተዋል፡፡
የጤና ባለሙያዎቹ በሠላም እንዲገኙ በተለይም ያሉበትን አካባቢ በመጠቆምና ትክክለኛ መረጃዎችን ለጸጥታ ኃይሉ በመስጠት ረገድ የጉብላክ ጤና ጣቢያ ባልደረባ የሆነው ወጣት ጀግናማው መኮንን የማይተካ ሚና ሚና ተጫውቷል ተብሏል፡፡ከላይ ፎቶው የተቀመጠው ወጣት ጀግናማው መኮንን ላከናወነው ትልቅ የሰብዓዊነት ተግባርም የክልሉ መንግስት የላቀ አክብሮትና ምስጋናውን አቅርቧል።
[የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን]

የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ በከተማዋ የተለያዩ የሽብር ስራዎችን ለመስራት ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋለሁ ያላቸውን አራት ተጠርጣሪዎች መያዙን አስታወቀ።
ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት ሀይማኖተኛ በመምሰል፣የአዕመሮ ህመምተኛ በመምሰል፣የልመና ስራ የሚሰሩ እና ሌሎች ህብረተሰቡ በማይጠረጥራቸው መንገድ ሲንቀሳቀሱ መሆኑን የከተማዋ ጸጥታ ጽህፈት ቤት ገልጿል።የሀይማኖት አልባሳትን በመልበስ በከተማዋ አከባቢዎች ሲንቀሳቀስ የነበረ ግለሰብ ተይዞ ምርመራ እንደተጀመረበት ተገልጿል፡፡
የከተማዋ አስተዳደር እና የፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ስንታየሁ ጥላሁን እንዳሉት ከተማዋን ለዳግም ብጥብጥ ሊዳርጉ የሚችሉ እቅስቃሲዎችን በጥንቃቄ ክትትል እየተደረገባቸው እንዳለ ተናግረዋል፡፡አቶ ስንታየሁ እንደሚሉት ትላንት ማምሻውን እንኳን አራት ስልኮችን የያዘና በአንድ አልቤርጎ ውስጥ ለስድስት ቀናት በመቀመጥ በከተማዋ የተለያዩ ስፍራዎች ያለ ስራ ሲንቀሳቀስ የነበረ አንድ ግለሰብ በክትትል መያዙን ይናገራሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪም እብድ በመምሰል ስለላ ሲሰራ የነበርና የተለያዩ ቋንቋዎችን ጠንቅቆ የሚናገር ሌላ ግለሰብም ተይዟል፡፡የሀይማኖቱ ተከታይ ሳይሆንም የሀይማኖት ልብስ በመልበስ በተመሳሳይ ስለላ እንቅስቃሴ ላይ የነበር እንዲሁ በጸጥታ አካላት መያዙን ተናግረዋል፡፡ከተማዋ አሁን በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፉ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ሰላማዊ መሆኗን አንስተው ይህንን ለማስቀጠልም የፖሊስ አይንና ጆሮ የሆነው ህብረተሰብ ጥቆማዎችን የማደርሱን ሰራ እንዲያጠናክር አሳስበዋል፡፡
[Ethio FM]