#FakeNewsAlert
(Via FDRE Defense Force)
የኢትዮጵያ አየር ኃይል አውሮፕላን በሕውሐት ቡድን እንደተመታ ተደርጎ በዚህ ቡድን ደጋፊዎች በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው ምስል ፍፁም ሐሰት ነው።የሀሰቱ ምስል የተወሰደው የዛሬ ዓመት ከቢሾፍቱ አየር ኃይል ጊቢ ለልምምድ በረራ የተነሳና ሞተሩ ላይ ባጋጠመው ችግር በተነሳ በደቂቃዎች ውስጥ የወደቀውን አውሮፕላን ነው።
በሌሎች ሀገራት ያጋጠሙ የአውሮፕላን አደጋዎችም ለዚህ የሀሰት ወሬ ማጀቢያ ጥቅም ላይ ውለዋል።
እውነታውን እንዲታወቅ ምስሎቹን አያይዘናል።
ሐሰተኛ ምስሎችን እነዚህን የማረጋገጫ መንገዶች በመጠቀም ይለዩ!
የትና መቼ ጥቅም ላይ እንደዋሉ ይነግርዎታል።
• Yandex.com/
• TinyEye:- tineye.com/
• FotoForensics:- fotoforensics.com/
• Googel image
@YeneTube @FikerAssefa

ፔንሲልቬኒያ ውጤታቸውን ይፋ ካላደረጉ ግዛቶች ትልቁ ኤሌክቶራል ድምጽ ያላት ግዛት ናት።
20 ኤሌክቶራል ድምጽ!
ባይደን በዚህ ግዛት አሸነፉ ማለት ወደ ዋይት ሃውስ የሚያደርጉት ጉዞ የተረጋገጠ ይሆናል ማለት ነው።
ለመሆኑ በዚህ ግዛት የድምጽ ቆጠራው ከምን ደርሷል? ልዩነታቸውስ?
በፔንሲልቬኒያ እስካሁን 95 በመቶ ድምጽ ተቆጥሯል።
በዚህ መሠረት ትራምፕ 3,286,171 (49.5%) አግኝተዋል።
ባይደን ደግሞ 3,267,942 (49.2%) አግኝተዋል።
በሁለቱ እጩዎች መካከል ያለው ልዩነት 18ሺህ 229 ድምጽ ብቻ ነው።
ያልተቆጠረው ድምጽ ደግሞ 344ሺህ 953 ነው።
ይህ ውጤት የተመዘገበው ጥቅምት 27 ከረፋዱ 4፡30 ላይ ነው
Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa

በሌላኛዋ ቁልፍ ግዛት ጆርጂያ በሁለቱ እጩዎች መካከል ያለው ልዩነት 665 ብቻ ሆኗል።
16 ኤሌክቶራል ድምጽ ባላት ጆርጂያ ሁሉቱ እጩዎች እጅግ በጣም ተቀራራቢ ውጤት ላይ ይገኛሉ።
ባይደን በዚህ ግዛት የነበራቸውን ልዩነት በከፍተኛ ሁኔታ ማጥበብ ችለዋል።
ያልተቆጠረው ድምጽ 1% ብቻ ነው።
የዚህን ግዛት የመጨረሻ ውጤት በቅርቡ የምንሰማው ይሆናል።
ይህ ውጤት የተመዘገበው ከጠዋቱ 4 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ላይ ነው።
Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
16 ኤሌክቶራል ድምጽ ባላት ጆርጂያ ሁሉቱ እጩዎች እጅግ በጣም ተቀራራቢ ውጤት ላይ ይገኛሉ።
ባይደን በዚህ ግዛት የነበራቸውን ልዩነት በከፍተኛ ሁኔታ ማጥበብ ችለዋል።
ያልተቆጠረው ድምጽ 1% ብቻ ነው።
የዚህን ግዛት የመጨረሻ ውጤት በቅርቡ የምንሰማው ይሆናል።
ይህ ውጤት የተመዘገበው ከጠዋቱ 4 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ላይ ነው።
Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው ድርድር በግብጽ ምክንያት ስምምነት ላይ አለመደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ስራዎች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።አምባሳደር ዲና እንዳሉት ኢትዮጵያ ግብጽ እና ሱዳን ከትናንት በስቲያ በበይነ መረብ በመታገዝ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ተወያይተዋል።ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን አስመልክቶ በቀጣይ ፍሬያማ ውይይት እንዲካሄድ ከሁሉም የአፍሪካ አገራት ሁለት ሁለት ባለሙያዎችን ባካተተ መንገድ ውይይት ይደረግ የሚል ሃሳብ አቅርባለች።
ሱዳን በኢትዮጵያ ሀሳብ የተስማማች ቢሆንም ግብጽ ግን ሀሳቡን ውድቅ እንዳደረገች አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።እንደ አምባሳደር ዲና ገለጻ ኢትዮጵያ ይሄንን ሀሳብ ያቀረበችው ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ በሚል ነው።አምባሳደር ዲና በሌሎች ጉዳዮችም መግለጫ የሰጡ ሲሆን ከአረብ ኢሚሬት በኢንቨስትመንት በቴክኖሎጂ አብሮ ለመስራት ስምምነት መፈረሙን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከህንድ ደግሞ 5 ሚሊየን ዶላር የሚገመት የኮቪድ መከላከያ የሚውል ድጋፍ ማግኘቷን ተናግረዋል።በኢትዮጵያ 580 የህንድ ኩባንያዎች ያሉ ሲሆን በኬሚካል ምርት፣ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ፣ኮንስትራክሽን እና ሌሎች ዘርፎች ተሰማርተዋል ተብሏል።በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይም ጅቡቲ፣ ሱዳን እና ሌሎች የጎረቤት አገራት የኢትዮጵያ ሰላም የእነሱም ሰላም እንደሆነ ማረጋገጣቸውን አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።
Via Ethio FM

ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ይጀመር የነበረው የ2013 የትምህርት ዘመን የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ፡፡
የ2013 የትምህርት ዘመን ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ይጀመር የነበረው የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡በአዲስ አበባ ከተማ የ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ በማያጋልጥ ሁኔታ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት ለመጀመር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ከ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ውጪ በተቀሩን ክፍሎች ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በኮቪድ-19 የቀውስ ጊዜ የትምህርት አመራርና አስተዳደር ስትራቴጂ እቅድ ላይ የተቀመጡ ስታንዳርዶችን ሟሟላት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አስፈላጊ ዝግጅቶች በተሟላ ደረጃ እስኪጠናቀቁ ድረስ በከተማዋ ለመጀመር የታቀደው የገጽ ለገጽ ትምህርት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ቢሮው አስታውቋል፡፡ከባለፈው ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም በመሰጠት የጀመረው የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል የገጽ ለገጽ የክለሳ ትምህርት የመማር ማስተማር ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቢሮው መግለጹነ ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡

የኦጋዴን ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) በፌዴራልና በትግራይ ክልል መንግስት መካከል በተፈጠረው ጦርነት ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫውም ምንም እንኳን ህወሓት በሶማሌ ህዝብ ላይ "የዘር ማጥፋት ወንጀል" ቢፈፅምም አሁን ያለው ውጥረት በጦርነት ይፈታል ብለን አናምንም ብሏል። አሁንም ቢሆን ችግሩ የሚፍታው በድርድር እንደሆነ እንደሚያምን አስታውቋል ።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ህወሓት በከተሞች ጥቃት እንዲፈፅሙ አሰማርቷቸዋል የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው በሰጡት መግለጫ ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን አዲስ አበባን ጨምሮ በአገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ጥቃት ለማድረስ ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው።
ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ያሉት በህብረተሰቡ ትብብርና ጥቆማ እንዲሁም በፀጥታ ሃይሉ ጠንካራ ክትትል መሆኑንም ገልጸዋል።
[ኢዜአ]

በሰሜን ኢትዮጵያ በመከላከያ ሰራዊት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ግልጽ፡ የተወሰነ እና ሊደረስበት የሚችል አላማን ያነገበ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ማክሰኞ ህወሓት ትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ መከላከያ ሰራዊት እርምጃ መውሰድ መጀመሩን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል፡፡እየተካሄደ ያለው ዘመቻም በሃገሪቱ ህግና ስርአትን ለማስፈን እና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለማስከበር ያለመ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በየትኛውም የሃገሪቱ አካባቢ ተንቀሳቅሰው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡መንግስት ከህወሓት ጋር ያለውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ለወራት ታግሶ ድርድርና ሽምግልና ሲያካሂድ መቆየቱንም አስታውሰዋል፡፡ይሁን እንጅ መንግስት ያደረገው ጥረት በሙሉ በህወሃት እምቢተኝነት መክሸፉንም ገልጸዋል፡፡

የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ከሰሜን እዝ ጋር ሆነን በሰራነው ስራ ራሳችን ለመከላከል እንድንጠቀምበት የሚያስችል ሁኔታ ፈጥረናል አሉ። በአሁኑ ሰአት በትግራይ ያለ የጦር መሳርያ ለትግራይ ህዝብ ደህንነት እንዲውል፣ለራሱ እንዲከላከልበትና እንዲጠቀምበት መጠቀም ጀምረናልም ፣ ወደፊትም እንጠቀምበታለን ብለዋል።በጦር መሳርያ ደረጃ ሙሉ የጦር መሳርያ ኣለን ማለት ነው፣ ውግያ አለ፣ እኛም እነዚህ ወራሪዎች ለመመከት ተዘጋጅተናል፤ ጭራሽም እንቀብራቸዋለን። ከቀጠሉ እዚሁ ቅርብ ያሉትን ብቻ ሳይሆን እዛ እሩቅ ያሉትም እላያቸው ላይ "እንዘንብላቸዋለን" ሲሉ መዛታቸውን የህወሓት የፌስቡክ ገፅ አስነብቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ባይደን በጆርጂያ መሪነቱን ከትራምፕ ተቀበሉ!
ጆ ባይደን 16 ኤሌክቶራል ድምጽ ባላት ጆርጂያ መምራት ጀመሩ።ትራምፕ በጆርጂያ ሲመሩ ቢቆዩም፤ 99% በመቶ ድምጽ መቆጠሩን ተከትሎ መሪነቱን ለጆ ባይደን አሳልፈው ሰጥተዋል። ባይደን 253 የተረጋገጠ ኤሌክቶራል ድምጽ ያላቸው ሲሆን በጆርጂያ አሸናፊ መሆናቸው ከተረጋገጠ 269 ድምጽ ይኖራቸዋል ማለት ነው።
ፕሬዝደንት ሆኖ ለመመረጥ 270 ኤሌክቶራል ድምጽ ያስፈልጋል።
ይህ ውጤት የተመዘገበው 12፡57 ላይ ነው።
[BBC]

ትግራይን ከአፋር ክልል ጋር በሚያገናኙ አጠቃላይ የወረዳ መንገዶች መዘጋታቸውን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡
የአፋር ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሒም ኡመድ መሀመድ እንደተናገሩት ክልሉ ከዚህ ቀደም በህወሀት ሞግዚቶች ይመራ የነበረ በመሆኑ ጥቃቶች እንዳይከሰቱ ከኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ፤ ከብሔራዊ ደህንነት ፤ ፌደራል ፖሊስ እና የክልሉን የፀጥታ ሀይል ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል፡፡ህወሀት ጥቃት ሊያደርስ ይችላል ተብለው የሚታሰቡ የክልሉ አካባቢዎች ተለይተው የፀጥታ ሀይሉ ሙሉ ቁጥጥር እያደረገባቸው እንደሚገኝም ሀላፊው ተናግረዋል፡፡
ክልሉ ከዚህ ቀደም በህወሀት ሞግዚቶች ይመራ የነበረ በመሆኑ በዚህ ክልል ውስጥ ሊያደርሱ የሚችሉትን ጥቃት በመለየት አስፈላጊው ጥንቃቄ እየተደረገ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡
አቶ ኢብራሂም አክለውም ወደ ትግራይ ክልል የሚገቡ እና የሚወጡ አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች በአፋር ክልል የሚያልፉ መሆናቸውን ገልፀው አሁን የፀጥታ ሀይሎችን በመመደብ አዋሳኝ የወረዳ ትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲገደብ ተደርጓል፡፡ ጥብቅ ቁጥጥርም እየተከናወነ ነው በማለት ገልፀዋል፡፡በአፋር ክልል ውስጥ በሚገኙ የሀገር አቋራጭ መንገዶች ላይ ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል የሚል ጥርጣሬዎች በመኖራቸው በእያንዳንዱ ሀገር አቋራጭ መንገዶች መከላከያ ሰራዊቱን ጨምሮ የክልሉ ልዩ ሀይል ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ ነው መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

"የምፈልገው የአማራ ልዩ ሃይል መሪ ሆኜ፣ የህውሃትን ቅስም መስበር ነው" - ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ
የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ጥሩ መሪ ይፈልጋል። በተደራጀ መንገድ የህውሃት ቅስም መሰበር አለበት።ይሄ ካልሆነ ሀገራችን ሰላም አታገኝም። የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ነበርኩ።ይሄ ዕዝ የኢትዮጵያ ልጆች ስብስብ ነው። ሆኖም ህውሃት መሳሪያ ለመንጠቅ ሲል ልጆቹን ጨፈጨፋቸው።ነገ የተጨፈጨፉት ልጆች ስም ዝርዝር ሲገለፅ ብዙ ቁጣ ይቀሰቅሳል።ከአማራ ክልል አመራሮች ጋር ተነጋግሬያለሁ፣ የምፈልገው የልዩ ሃይል መሪ መሆን ነው። የጀመርኩትን ስራ ማጠናቀቅ እፈልጋለሁ። ሆኖም officially ጥሪ አልተደረገልኝም።
ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ - ለበለስ ሚዲያ የተናገሩት

የፌዴራል ፖሊስ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት በወቅታዊ የሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል እንዳሻው ጣሰው እንዳሉት በትግራይ ክልል ጽንፈኛው የህወሓት ታጣቂ ቡድን የተከፈተውን ጦርነት ለመመከት የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች እና ሚልሻዎች በቅንጅት በወሰዱት እርምጃ አብዛኛው በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡የተቀረውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ መንግስት እና ህዝቡ ፊቱን ወደ ሰላምና ልማት እንዲያዞሩ ለማስቻል እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡በቀሪው ጊዜያትም ሁሉም የጸጥታ እና ደህንነት መዋቅሩ በአንድነት ተደራጅተው በመስራት በዚህ እኩይ ተግባር ላይ የተሰማራውን ኃይል ከስረመሰረቱ መንቀል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡የመንግስትና የህዝብ ተቋማትን መጠበቅ የህዝቡ የዕለት ዕለት ኑሮ እንዳይስተጓጎል ማድረግ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈፃሚ እንዲሆን ይሰራልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡በቀጣይም ህብረተሰቡ በየአካባቢው በመደራጀት ፀጉረ ልውጦችን ለጸጥታ ኃይሉ በመጠቆም ትብብር እንዲያደርግና መንግስት ለሚያደርገው ጥሪ ዝግጁ እንዲሆን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው፣ ህብረተሰቡ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እና ኃላፊነት ከማይሰማቸው የመገናኛ ብዙኃን እየተላለፉ ያሉ የሀሰት መረጃዎችን ከማሰራጨትና ከመቀበል መቆጠብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
[Walta]

የሳዑዲ አረቢያ የመኖሪያ ፈቃድ ህግን ተላልፈዋል በሚል በፖሊስ ተይዘው የነበሩ 57 ኢትዮጵያዊያን ከእስር ተፈቱ።
በሳውዲ አረቢያ መዲና ሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንዳስታወቀው የአገሩን የመኖሪያና ሥራ ፈቃድ ህግን ተላልፈው በሚል በህግ አስከባሪ ተይዘው የነበሩ 57 ዜጎችን አስፈትቷል።ኢምባሲው እንዳለው ዜጎቹ የተፈቱት ሴቶችና ታዳጊ ወጣት ዜጎቻችን ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ሴቶቹ ህጻናት ልጆቻቸውን ጡት የሚያጠቡና ታዳጊ ወጣቶችም እድሜያቸው ለእስር የሚያበቃ አለመሆኑን በማስረዳት መሆኑን ገልጿል።
በህግ አስከባሪ ሃይሎች ተይዘው ከተፈቱት ዜጎቻችን መካከል አንዳንዶች ከወራት እስከ 3 አመት እድሜ ያላቸዉ ህፃናት የያዙ እናቶች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ በቤታቸዉም ከ1 ወር እስከ 3 ወራት የሚሆኑ ህፃናት አስቀምጠው መንገድ ላይ የተያዙ እናቶች፣ ከ5 እስከ 8ኛ ወራቸዉ የገባ ነፍሰ ጡር ሴቶች፣ እና እድሜያቸው ለእስር የማያበቃቸው ታዳጊ ወጣት ዜጎች ይገኙበታል ተብሏል። እነዚህ ዜጎች ሁሉም በሚቻል ደረጃ ህይወታቸውን ለመለወጥ በጅቡቲ ወደብ በኩል ቀይ ባሕርን አቋርጠው በየመን በኩል ሳኡዲ የገቡ መሆናቸው ተገልጿል።

በቅራቅር አካባቢ አንፃራዊ ሰላም ቢኖርም የመንግስት መሥሪያ ቤቶች አልተከፈቱም።
በአማራ ክልል ጠገዴ ወረዳና በትግራይ ክልል ፀገዴ ወረዳ አዋሳኝ ቦታዎች የነበረው ግጭትን የመከላከያ ሰራዊት ቢቆጣጠሩትም የመንግስት መሥሪያ ቤቶች ሥራ እንዳልጀመሩ ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡አንድ ጠገዴ ወረዳ ቅራቅር ከተማ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ በስልክ እንደተናገሩት አሁን በአካባቢው የተኩስ ድምፅ እንደማይሰማ ገልፀው በከተማዋ ሰዎች በሰላም እየተዘዋወሩ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ይሁን እንጂ በጠገዴ ወረዳ ቅራቅር ከተማ አሁንም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ግጭቱ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን ዝግ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡የወረዳውን አመራር አስተያየት ለማካተት ቢሞከርም መረጃ የሚሰጠው ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች በጋራ ነው በማለታቸው አልተሳካም፡፡
[DW]

YeneTube
መቐለ ከተማ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ መጀመሩን የBBC ትግርኛ ዘጋቢ ከሆነው ግርማይ ገብሩ ፌስቡክ ገፅ ተመልክተናል። @Yenetube @Fikerassefa
የትግራይ ክልልና የፌደራል መንግሥት ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ከገቡ ሶስተኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል። ግጭቱን ተከትሎ በመቀሌ ከተማና በክልሉ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክና #የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀምሯል።
የኤሌክትሪክ አገልግሎት ትናንት ጥቅምት 26/2013 ዓ.ም የተመለሰ ሲሆን የትራንስፖርት አገልግሎት ደግሞ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም መጀመሩን የመቀሌ የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል።
ምንም እንኳን ትራንስፖርት ቢጀመርም ከመቀሌ ከተማ ወደተለያዩ ክፍሎች የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች በሙሉ ከከተማው ፖሊስ ልዩ ፍቃድ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።
ግጭቱን ተከትሎ የተቋረጠው የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው።
ከቀናት በፊት ተኩስ የተሰማባት መቀሌ ከተማ በአንፃራዊ ሁኔታ የተረጋጋ ሁኔታ ላይ ብትገኝም ማህበረሰቡ ግን ጦርነቱ በፈጠረው ውጅንብር ስጋት ላይ መሆኑንም የቢቢሲ ዘጋቢ ይናገራል።
በትናንትናው እለት በመቀሌ ከተማ የጦር አውሮፕላን ሲያንዣብብ የነበረ መሆኑን የታዘበው የቢቢሲ ዘጋቢ በድምፁም በርካቶች #መደናገጥና ፍራቻ ውስጥ እንደገቡ አክሎ ገልጿል።

በአዲስ አበባ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከዛሬ 27/02/2013 ዓ.ም ጀምሮ ከጧቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በሁሉም የክልሎች የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከጧቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ሰዓት ብቻ እንዲሠሩ ተወሰነ።
Via:- Capital
@Yenetube @Fikerassefa
Via:- Capital
@Yenetube @Fikerassefa