YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጆ ባይደን በ ፔንስልቬንያ (Pennsylvania) ግዛት ዶናልድ ትራፕን መምራት ጀምረዋል ውጤቱ በዚህ የሚጠናቀቅ ከሆነ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን ባይደን ማሸነፋቸውን ያረጋግጣሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
የህወሓት ኃይል ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን በስኬት እንደተጠናቀቀ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።

የአየር ሀይሉ በወሰደው እርምጃም በተለያዩ ስፍራዎች ላይ የነበሩ ሮኬቶችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ለማውደም መቻሉንም ገልፀዋል።እነዚህ ሮኬቶች እስከ 300 ኪሎ ሜትሮች መወንጨፍ የሚችሉ በመሆናቸው እና በወንጀለኛው ቡድን ሮኬቶቹን የመጠቀም ፍላጎት በመኖሩ በመቀሌ እና አካባቢዋ በነበረው የከባድ መሳሪያ ማስቀመጫ ላይ የአየር ኃይሉ እርምጃ እንዲወስድ መደረጉ ተገልጿል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የኦጋዴን ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ምክትል ሊቀ መንበር ሀሰን ሞዋሊም ከፓርቲው አመራርነት ራሳቸውን አገለሉ።ለ22 አመት ያህል የግንባሩ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ሃሰን ለአዲስ ስታንዳርድ በላኩት መግለጫ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል።ለመውረዳቸውም እንደምክንያት የሚወሰደው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማእከላዊ ኮሚቴው የሚታየው ክፍፍል ሳይሆን እንዳልቀረ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ትላንት የአውሮፕላን ጥቃት ደረሰባት የተባለችው የመቀሌ ዙርያ ዛሬ ዉሎዋ ሰላማዊ ነዉ ሲል ነዉ የዶቼ ቬለ ወኪል ከስፍራዉ ገልጿል።

በመቀሌ ከተማ መደበኛ ግብይትና የሰዎች እንቅስቃሴ ቀጥሎ ዉሎአል፤ የመንግስትና የግል ባንኮች ግን ዛሬም ዝግ ሆነዉ ነዉ የዋሉት።በከተማዋ የ12ኛ እና 8 ክፍል ተማሪዎች በየትምህርት ቤቶቻቸዉ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ዉለዋል።በቅርቡ ተመራቂ ተማሪዎቹን የተቀበለው መቀሌ ዩኒቨርስቲም ለተማሪዎቹ አገልግሎት እየሰጠ መሆንን መስማቱን የዶይቸ ቨለ ወኪል ተናግሯል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 355 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4,725 የላብራቶሪ ምርመራ 355 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,512 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 989 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 58,103 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 98,746 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በፌዴራል መንግስት እና በህወሓት መካከል የተፈጠረውን ግጭት በማስመልከት ያወጣውን መግለጫ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እና ብልጽግና ተቃወሙ።

ፓርቲዎቹ ሳንመክርበት የወጣ ነው ያሉት መግለጫ እንደማይመለከታቸው እና እንደማያውቁት አስታውቀዋል።ከአሰራር ውጭ የተደረገም ነው ፓርቲዎቹ ያሉት።ምክር ቤቱ ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም እና ሁለቱ ወገኖች ወደ ውይይት እንዲመጡ ሲል መጠየቁ የሚታወስ ነው።

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ጥቃት አደረሱ

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኬራሞ ወረዳ ባጃን ቀበሌ ሰጊ በተባለ ስፍራ በርካታ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአማራ ተወላጆች ላይ ዛሬ ማምሻውን ተኩስ ከፍተው በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

አርሶ አደሩ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችን ለመመከት ጥረት እያደረገ ቢሆንም የመንግስት ታጣቂዎች በአስቸኳይ ካልደረሱ የከፋ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ለጣቢያው እየገለጹ ነው።

ነዋሪዎቹ አክለውም የመከላከያ ሰራዊት ትናንት ጥቅምት 26 / 2013 ዓ/ም አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ቀበሌው እንደገቡ ነው የተገለጸው።
እስካሁን ግን በጥቃቱ ምን ያህል የሰው ህይወት እንደጠፋ እና ምን ያህል እንደቆሰለ የታወቀ ነገር የለም ።

ኢሳት [ጎበዜ ሲሳይ]
@Yenetube @Fikerassefa
የሲኤን ኤን "Quest means business" አዘጋጅና አቅራቢ ሪቻርድ ኩዌስት ዛሬ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት ከፍል ጥሩ አቀባበል ተደረገለት!

ዛሬ ማምሻውን ከሲሼልስ አዲስ አበባ የመጣውና ከዛም ወደ ኢስታንቡል ቱርክ የተጓዘው የሲኤን ኤን ቢዝነስ ጋዜጠኛ ሪቻርድ ኩዌስት በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት በነበረው አጭር ቆይታ የአየር መንገዱ ስራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከማኔጅመንት ክፍላቸው ጋር በመሆን ደመቅ ባለ ሁኔታ ተቀብለውት የተወሰነ ደቂቃ እንዳወሩት ፊደል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

ሪቻርድ ኩዌስት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ አውሮፕላን ከሁለት አመት በፊት እዚው ኢትዮጵያ ሲከሰከስ አየር መንገዱ ጠንካራ ጎኑን በማውሳት ዘገባ መስራቱ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የኢሕአዴግ የረጅም ጊዜ ውጭ ግንኙነት ሃላፊ ሴኮቱሬ ጌታቸዉ እና የቀድሞ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት በሪሁን ተወልደ ብርሃን ከድምጸ ወያነ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ህወሐት እያካሄደ ያለው ውጊያ ዐላማ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይን መንግሥት ከሥልጣን ለማስወገድ እንደሆነ ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው መለሰ!

ከደቡብ የሀገራችን ክፍል በመነሳት በህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች በመታለል ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ ያለበቂ ሰነድ ድንበር በማቋረጥ በተለያዩ የኬንያ አካባቢዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 78 ዜጎችን ከኬንያ የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት እና የፖሊስ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል፡፡ኤምባሲው ዜጎች ለህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ገንዘብ በመክፈል ያለምንም የጉዞ ሰነድ ከሀገር በመውጣት ሕይወታቸውን አደጋ ላይ እንዳይጥሉ አሳስቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ የሚያሳዩ ተብለው በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋውሩ የሚታዩት እነዚህ ሁለት ፎቶዎች ትክክለኛ #እንዳልሆኑ የአጃንስ ፍራንስ ፕረስ አለም አቀፍ fact checking ቡድን አስታውቋል። ከፎቶዎቹ ተመቶ የወደቀ አውሮፕላን የተባለው ከረጅም ጊዜ በፊት ሱዳን ውስጥ የተፈጠረ ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ እዚው ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሆንም ከ20 አመት በፊት እአአ በ2000 ዓም የተነሳ መሆኑን ከፎቶግራፈሩ እንዳረጋገጡ ገልጸዋል።

Via AFP Fact check
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ጣልቃ እንዲገባ እና ጊዜያዊ መንግስት (አስተዳደር) እንዲቋቋም የውሳኔ ሃሳብ አቀረበ፡፡ምክር ቤቱ በዛሬው እለት አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ይኛል፡፡በስብሰባው ላይ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ እየተወያየ ይገኛል፡፡

(ኤፍ ቢ ሲ)
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ጣልቃ እንዲገባ እና ጊዜያዊ መንግስት (አስተዳደር) እንዲቋቋም የውሳኔ ሃሳብ አቀረበ፡፡ምክር ቤቱ በዛሬው እለት አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ይኛል፡፡በስብሰባው ላይ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ እየተወያየ ይገኛል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ) @YeneTube @FikerAssefa
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በሙሉ ድምጽ ወሰነ!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ያሳለፈው ውሳኔ ቀዳሚው ነው፡፡ምክር ቤቱ ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 62(9) ማንኛውም ክልል ሕገ መንግሥት በመጣስ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ የፌዴራሉ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ያዛል በሚለው ድንጋጌ መሰረት ነው፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል ያለው ሕገ ወጡ ምክር ቤት እና ስራ አስፈጻሚ እንዲፈርስ፣ ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ እንዲቋቋም፣ ይህ ጊዜያዊ አስተዳደር ደግሞ ስራ አስፈጻሚዎችን እንዲሾም ወስኗል፡፡ በዚህም ሕገ መንግስታዊ ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድና ከፌዴራሉ መንግስት የሚሰጡ ትእዝዛትን እንዲፈጽም ይጠበቅበታል ብሏል፡፡የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርም በየሶስት ወሩ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ክልሉ ያለበትን ሁኔታ እንዲያሳውቁ ወስኗል፡፡ሁሉም የአገሪቱ ህዝቦች ከመከላከያ ጎን እንዲቆሙ እና በዚህ የጥፋት ቡድን ላይ የሚወሰደውን እርምጃ እንዲደግፉ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥሪ አቅርቧል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ሕገ-ወጥ ያላቸውን የውጭ አገር ስደተኞች ማባረር ጀመረ፡፡

ሰሞኑን የተቃውሞ ሰልፍ ሲያካሂዱ ከነበሩት የውጭ አገራት ስደተኞች 20ዎቹ እንደተባረሩ ፅፏል፡፡የውጭ አገር ዜጎቹ ለ5 ወራት የዘለቀ ተቃውሞ የተደረገው የአገሩ ሰዎች ሲያደርሱባቸው የቆየው የጥላቻ ጥቃት እንዲቆም ለመጠየቅ እንደሆነ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ሰልፈኞቹ በኬፕታውን በቤተክርስቲያ ተጠልለው መቆየታቸው ታውቋል፡፡ከመካከላቸው 20ዎች ከአገሪቱ መባረራቸው ቢነገርም ወዴት እንደተባረሩ ግን አልታወቀም ተብሏል፡፡በደቡብ አፍሪካ ከቅርብ 10 ዓመታት ወዲህ በተለይም በአፍሪካውያን ስደተኞች ላይ ያጣጠረው የአገሬው ሰዎች የጥላቻ ጥቃት እንደሚደጋገም መረጃው አስታውሷል፡፡

[Sheger]
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል በተለያዩ ዞኖች ህገወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሰባት ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኢንስፔክተር እታገኘሁ ዜና ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ ባለፉት ሁለት ቀናት በደቡብ ኦሞ፣ ካፋ፣ ኮንሶና ሸካ ዞኖች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 25 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 4 ሽጉጦችና 11 ተተኳሽ ጥይቶች ተይዘዋል።እነዚህን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።ከተያዙት ተጠርጣሪዎች መካከል በደቡብ ኦሞ ጂንካ ከተማ ሁለት ግለሰቦች የአዕምሮ ህመምተኛ መስለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እንደሚገኙበት ገልጸዋል።ግለሰቦቹ በህብረተሰቡ ጥቆማ ተይዘው ምርመራ ሲደረግባቸው ስድስት ሞባይል ስልክና 11 የተለያየ የባንክ የሂሳብ ደብተሮች እንደተገኘባቸውም ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሪፐብሊካኖች በትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል ሀሳብ ላይ ተከፋፍለዋል!

ፕሬዘዳንት ትራምፕ እየተካሄደ ባለው የአሜሪካ ምርጫ ጥያቄ እያነሱ ሲሆን የራሳቸው የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ፕሬዘዳንቱ ጉዳዩን ማርገብ እንዳለባቸው ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ምርጫው ከተካሄደ ከሶስት ቀን በኋላ በትራምፕና በተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን መካከል በፔንሲልቫኒያ፣ በአሪዞና፣ በጆርጂያና ኖርዝ ካሮሊና በተቀራራቢ ውጤት እየተመራሩ ይገኛሉ፡፡የትራምፕ በመረጃ ያለተደገፈ ምርጫው ተጭበርብሯል ክስ በተመለከተ የሪፐብሊካን አባል የሆኑት ሴናተር ሮይ ብለንት ለሮይተርስ እንተናገሩት ኃይት ሀውስ እንዲህ አይነቱን ክስ በመረጃ አስደግፎ ወደ ፍርድ ቤት መውሰድ አለበት ብሏል፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር የሕዝቡን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚያስከብር እንደሚሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አደም ፋራህ ገለፁ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳልፏል።ውሳኔውን አስመልክቶም የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አደም ፋራህ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ “የሚቋቋመው አስተዳደር በሕገ መንግስቱ ድንጋጌዎች መሰረት የሚሰራና የትግራይን ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚያስከብር ይሆናል” ብለዋል።“ሕገወጡ የህወሓት ቡድን የትግራይ ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚከበረው በእሱ ብቻ እንደሆነ አድርጎ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል” ብለዋል።ይህም የሕገ መንግስቱን መርሆዎች የሚፃረር እንደሆነ ነው የገለጹት።

ሕገወጥ ቡድኑ የፌዴሬሽንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች ውሳኔዎችን በመጣስ ኢ-ሕገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ ሲንቀሳቀስ ቆይቶ በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት ማድረሱንም አስታውሰዋል።በመሆኑም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቡድኑ ወደ ሕጋዊ መንገድ እንዲመጣ የተለያዩ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ የቆየ ቢሆንም ሊመጣ ባለመቻሉ የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ፣ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋምና የፌዴራል የፀጥታ አካል በክልሉ እንዲሰማራ ውሳኔ ማሳለፉን ተናግረዋል።በትግራይ ክልል የሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር በአጭር ጊዜ የሚቋቋም ሲሆን ተጠሪነቱ ለፌዴራል መንግስት ይሆናል ተብሏል።የሚቋቋመው አስተዳደር የክልሉ ምክር ቤትና ካቢኔ ሲሰራቸው የነበሩ ተግባራትን እንደሚያከናውንም ተገልጿል።ኃላፊነቱን ለመወጣትም እስከታችኛው መዋቅር ድረስ አስፈፃሚዎችን ይመድባል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሁለት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የተለያዩ የጦር መሳሪዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ሃላፊ ኮማንደር አወል አህመድ እንዳስታወቁት በክፍለ ከተማው ወረዳ አንድ በተለምዶ 72 ካሬ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከህዝብ በደረሰ ጥቆማ እና ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ/ም ፖሊስ ባደረገው ብርበራ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብቀው የተቀመጡ ለጥፋት ዓላማ ሊውሉ የነበሩ ሁለት የእጅ ቦምቦች ተይዘዋል፡፡

በተመሳሳይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት ክልል መና ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ እና ፖሊስም ጉዳዩን በማጣራት ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣት ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ባደረገው ብርበራ ኡዚ ተብሎ የሚጠራ የጦር መሳሪያ ከሁለት ካርታ እና ከ56 ጥይቶች ጋር እንዲሁም አንድ ኮልት ሽጉጥ ከአራት ጥይቶችጋር፣ 80 የተለያዩ የሽጉጥ ጥይቶች፣ አንድ የጦር ሜዳ መነፅር እና የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር አወል አህመድ አስረድተዋል፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa