የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን በይፋ ውህደት ፈጸሙ!
ወካይ፣ ጠንካራና መሰረተ ሰፊ የአሰሪዎች ኮንፌዴሬሸን እንዲኖር ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩት ሁለት የአሰሪዎች ኮንፌዴሬሽኖች ጥቅምት 21 ቀን 2013 ዓ.ም በይፋ የኢትዮጵያ አሰሪ ፌዴሬሽኖች ኮንፌዴሬሽን በሚል ስያሜ ውህደት ፈጸሙ፡፡ ውህደቱን የፈጸሙት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን ሲሆኑ ውህደቱን ለማከናወን ላለፉት ሁለት ዓመታት የተለያዩ ጥረቶች መደረጋቸውንና ለዚሁ ስኬት መብቃታቸውን በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል።የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ጥቃቱ የተፈፀመው በኦነግ ሸኔ ነው ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።ጉዳቱ ምን ያህል እንደሆነ ግን መግለጫው ያለው ነገር የለም።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የአረጋውያን መብት ተከራካሪ የነበሩት አቶ ጥላሁን አበበ አረፉ፡፡
አቶ ጥላሁን አበበ በተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች በኃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን የኢትዮጵያ አረጋውያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማህበር መስራችና አመራር ሆነው ያገለገሉ የእድሜ ልክ የክብር አባል ነበሩ፡፡በሀሳብ ልዕልናና በትጉህነታቸው የሚታወቁት አቶ ጥላሁን አበበ “አረጋውያን ተግባራዊ ምላሽ ይሻሉ” በሚለው የኢትዮጵያ አረጋውያንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማስከበር ሲካሄድ የኖረው አገራዊያን ንቅናቄ መስራችና ግንባር ቀደም ተዋናይ ነበሩ፡፡
[የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር]

YeneTube
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል።የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ጥቃቱ የተፈፀመው በኦነግ ሸኔ ነው ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።ጉዳቱ ምን ያህል እንደሆነ ግን መግለጫው ያለው ነገር የለም። @YeneTube @FikerAssefa
👆👆
"በትላንትናው ምሽት በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ዘርን መሠረት ያደረገ የአማራን የቡድን ጥቃት ሰምተናል። የጥቃቱን መጠንና ዝርዝር ሁኔታዎች ከፌዴራሉና ከክልሉ መንግሥት ጋር በመተባበር እያጣራን ሲሆን፤ በዚህ ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት የአማራ ህዝብና ድርጅታችን የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ክፉኛ አዝኗል፤ ተቆጥቷል፡፡ በመሆኑም ይህ ድርጊት የሚወገዝ ከመሆኑም በላይ አጥፊዎቹ እንደየስራቸው በህግ አግባብ ሊዳኙ ይገባል ብለን እናምናለን፡፡"
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ትናንት ምሽት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በሚገኙ የአማራ ብሄር አባላት ላይ የተፈፀመውን የጅምላ ግድያ አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ከላይ ቀርቧል።

በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ የታጠቁ ዘራፊ ቡድኖችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተንቀሳቀሱ የጸጥታ ሀይሎች ጉዳት ደረሰባቸው፡፡
ባሳለፍነው ቅዳሜ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ገደማ የታጠቁ ሁለት የዘራፊዎች ቡድን በቁጥጥር ስር ለማዋል ተንቀሳቅሰው የነበሩ የጸጥታ አካላት የመኪና አደጋ ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡የደቡብ ክልል የሰላምና የጸጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ እና የግጭት መከላከል እና አፈታት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ እንዳሉት በእለቱ በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ የታጠቁ ዘራፊዎች ቡድን መኪና በማስቆም ዝርፊያ እየፈጸሙ መሆኑን ጥቆማ የደረሰው የአከባቢው መደበኛ የፖሊስ ሀይል በዘራፊዎቹ ጥቃት ተፈጽሞበታል፡፡በኃላም በአከባቢው የነበረ የፌደራል የፀጥታ ሀይል በስፍራው ደርሶ የተወሰኑት በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
በተመሳሳይ ሰአት በዚህችው ከተማ ሌላ ዝርፊያ ላይ የነበሩትን የዘራፊ ቡድን ለመያዝ ሲሞክር የዘራፊ ቡድኑ አንድ አባል ለማምለጥ ሲሞክር በመኪና ተገጭቶ ወዲያው ህይወቱ አልፏል፡፡ያመለጡትን ለመያዝ በነበረ ጥረት ወቅት ግን የጸጥታ አካላቱን እና የመጀመሪያ ተጠርጣሪዎችን ይዞ የነበረው መኪና ተገልብጦ በአንድ የጸጥታ ሀይል ላይ የሞት አደጋ ሲከሰት አምስቱ ላይ ጎዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ከተያዙት ተጠርጣሪዎች ውስጥ ሁለቱ በሆስፒታል ህክምና ላይ እንዳሉ ህይወታቸው ማለፉን አቶ አንድነት ጨምረው ይናገራሉ፡፡
አሁን በአከባቢው ምንም አይነት ችግር የለም ነው ያሉት አቶ አንድነት፡፡በክልሉ ቁጥሩ እየጨመረ የመጣውን የዝርፊያ ወንጀል ለመከላከል የአከባቢዎቹ ሚሊሻና የክልሉ ልዩ ሀይል በጋራ እየሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ባሳለፍነው ቅዳሜ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ገደማ የታጠቁ ሁለት የዘራፊዎች ቡድን በቁጥጥር ስር ለማዋል ተንቀሳቅሰው የነበሩ የጸጥታ አካላት የመኪና አደጋ ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡የደቡብ ክልል የሰላምና የጸጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ እና የግጭት መከላከል እና አፈታት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ እንዳሉት በእለቱ በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ የታጠቁ ዘራፊዎች ቡድን መኪና በማስቆም ዝርፊያ እየፈጸሙ መሆኑን ጥቆማ የደረሰው የአከባቢው መደበኛ የፖሊስ ሀይል በዘራፊዎቹ ጥቃት ተፈጽሞበታል፡፡በኃላም በአከባቢው የነበረ የፌደራል የፀጥታ ሀይል በስፍራው ደርሶ የተወሰኑት በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
በተመሳሳይ ሰአት በዚህችው ከተማ ሌላ ዝርፊያ ላይ የነበሩትን የዘራፊ ቡድን ለመያዝ ሲሞክር የዘራፊ ቡድኑ አንድ አባል ለማምለጥ ሲሞክር በመኪና ተገጭቶ ወዲያው ህይወቱ አልፏል፡፡ያመለጡትን ለመያዝ በነበረ ጥረት ወቅት ግን የጸጥታ አካላቱን እና የመጀመሪያ ተጠርጣሪዎችን ይዞ የነበረው መኪና ተገልብጦ በአንድ የጸጥታ ሀይል ላይ የሞት አደጋ ሲከሰት አምስቱ ላይ ጎዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ከተያዙት ተጠርጣሪዎች ውስጥ ሁለቱ በሆስፒታል ህክምና ላይ እንዳሉ ህይወታቸው ማለፉን አቶ አንድነት ጨምረው ይናገራሉ፡፡
አሁን በአከባቢው ምንም አይነት ችግር የለም ነው ያሉት አቶ አንድነት፡፡በክልሉ ቁጥሩ እየጨመረ የመጣውን የዝርፊያ ወንጀል ለመከላከል የአከባቢዎቹ ሚሊሻና የክልሉ ልዩ ሀይል በጋራ እየሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል።የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ጥቃቱ የተፈፀመው በኦነግ ሸኔ ነው ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።ጉዳቱ ምን ያህል እንደሆነ ግን መግለጫው ያለው ነገር የለም። @YeneTube @FikerAssefa
አስተያየታቸውን ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት የሰጡ የአካባቢው(ትናንት ምሽት ጥቃቱ የተፈፀመበት) ነዋሪዎች እንደተናገሩት የጅምላ ጥቃቱን የፈፀመባቸው ኦነግ ሸኔ የተባለ የታጠቀ ቡድን ነው፡፡
ጥቃቱ በአንድ አካባቢ በሚኖሩ አማራዎች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡የታጠቀው ቡድን ትናንት 11፡00 ላይ 200 አባዎራዎችንና ሌሎች ነዋሪዎችን ከሰበሰበ በኋላ ተኩስ በመክፈት የንጹሃንን ህይወት መቅጠፉን ነው ነዋሪዎቹ የተናገሩት፡፡ከጥቃቱ የተረፉትም ከአካባቢው ሸሽተው እንደሚገኙ አስታወቀዋል፡፡
በዚህም የተነሳ የሟቾችንና አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸውን ቁጥር በትክክል መግለፅ እንደማይችሉ የተናገሩት ነዋሪዎቹ ቡድኑ በአካባቢው የሚገኝ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ከ120 በላይ ቤቶችን ማቃጠሉንም ነው የተናገሩት፡፡አሁን ላይ የጸጥታ ኃይል ወደ አካባቢው ተሰማርቶ ሁኔታውን እያረጋጋ መሆኑንም ታውቋል፡፡
Via AMMA

የሱማሌ ክልል ፖሊስ 3 አመራሮቹን እንዳሰረበት የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር በትዊተር ገጹ አስታውቋል፡፡አመራሮቹ ትናንት ማታ እና ዛሬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት በቀብሪደሃር ከተማ ነው፡፡በቁጥጥር ስር የዋሉት የግባሩ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሞሐመድ ሙርሳል፣ በቆራሄ ዞን የግንባሩ ሃላፊ ሞሐመድ ጋማዲድ እና ምክትላቸው ተማም ሞሐሙድ እንደሆኑ ግንባሩ ጠቅሷል፡፡የሱማሌ ክልል መስተዳድር በግንባሩ ላይ የሚፈጽማቸውን…
የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ከ12 ቀናት በፊት በሶማሊ ክልል ፖሊስ በቀብሪደሃር ከተማ የታሰሩበት አመራሮቹ በዋስ እንደተፈቱ አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በጉራ ፈርዳ አሁንም ታጣቂዎች ጥቃት ሊፈጽሙ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳለ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡
በጉራፈርዳ ባለፈው ጥቃት አደረሱ የተባሉት ታጣቂዎች ሙሉ ለሙሉ ባለመደምሰሳቸው አሁንም ስጋት እንዳለ የደቡብ ክልል የሰላምና የጸጥታ ቢሮ ገልጿል። ከሁለት ሳምንት በፊት ለሊት ላይ ነዋሪዎች በመኖሪያ ቤታቸው ባሉበት በተፈጸመው ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት ማለፉ እና ከአምስት ሺ በላይ ዜጎች ደግሞ መፈናቀላቸው የሚታወስ ነው፡፡
ከዚህ ጥቃት በኃላ ምንም አይነት ችግር ባይኖርም ጥቃቱን አድርሰዋል የተባሉና የታጠቁ ሽፍቶች ሙሉ ለሙሉ ባለመደምሰሳቸው አሁንም ስጋት እንዳለ የደቡብ ክልል የሰላምና የጸጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ እና የግጭት መከላከል እና አፈታት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ተናግረዋል፡፡ጥቃቱ በተደራጀ ሁኔታ እንዲፈጸም ያደረጉ ተጠርጣሪዎችን የማደኑን ስራ የክልሉ ልዩ ሀይል ከመከላከያ ሰራዊት ጋር እየሰራ ነውም ብለዋል አቶ አንድነት፡፡
ይሁን እንጂ በአከባቢው ባለው ጥቅጥቅ ጫካ ውስጥ እኚህ ያመለጡ ሽፍቶች በመሰወራቸው እነርሱን የመደምሰሱ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው የሚያነሱት፡፡እኚህ ሽፍቶች እስካልተደመሰሱ ድረስ ስጋቱ አሁንም እንዳለ መሆኑን አልሸሸጉም፡፡ካለፈው ጥቃት ጋር በተያያዘ የአከባቢው ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ጨምሮ 84 ተጠርጣዎች መያዛቸውን አቶ አንድነት ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፣ በቴሌኮም ማጭበርበር የተጠረጠሩ በርካታ ግለሰቦች ከነመሳሪያዎቻቸው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ አስታወቀ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው የቴሌኮም መሳሪያዎችን ወደ ሀገር በማስገባትና ከውጭ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ የስልክ ጥሪዎች ኢትዮ ቴሌኮም በዘረጋው ኔትወርክ ሳይሆን ራሳቸው በዘረጉት መስመሮች ለደንበኞች ሲያቀርቡ መቆየታቸውን በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ሳሙኤል ሰለሞን ገልፀዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ለዚህ ህገ-ወጥ ተግባር ሲጠቀሙባቸው የነበሩ 6 ጌትወይ፣ ከ570 በላይ ሲም ካርዶች፣ ቲፕሊንኮችና ሌሎች ህገ-ወጥ የቴሌኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች መያዛቸውም ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስትና የኤርትራ መንግስት ትግራይ ላይ የሐይል እርምጃ ለመውሰድ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው ሲሉ የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ዶክተር ደብረፅዮን ተናገሩ።ፕሬዝደንቱ ለህዝባቸው 'ለሁሉም ነገር ዝግጁ ሁን' ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa
Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) በአማራ ሕዝብ ላይ በየቦታው እየተፈፀመ ላለው "የዘር ማጥፉት ወንጀል" ሙሉ ኃላፊነቱን መንግስት ይወስዳል አለ።
ንቅናቄው ትናንት ምሽት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ጋንቃ ቀበሌ በሚገኙ የአማራ ብሄር አባላት ላይ የተፈፀመውን የጅምላ ግድያ አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ ከላይ አቅርበናል።
@YeneTube @FikerAssefa
ንቅናቄው ትናንት ምሽት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ጋንቃ ቀበሌ በሚገኙ የአማራ ብሄር አባላት ላይ የተፈፀመውን የጅምላ ግድያ አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ ከላይ አቅርበናል።
@YeneTube @FikerAssefa
"በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ባለው ማንነትን መሠረት ባደረገው ጥቃት እጅግ ማዘኔን እገልጣለሁ።" -ጠ/ሚር አብይ አህመድ
የኢትዮጵያ ጠላቶች፤ "ወይ እኛ እንገዛለን፤ ወይ ሀገር አትኖርም" ብለው ተነሥተዋል።ለዚህም የጥፋት ዐቅማቸውን ሁሉ እየተጠቀሙ ነው።አንደኛው ዒላማቸውም የሕዝባችንን ቅስም መስበር ነው።ለዚህ እየተጠቀሙበት ያለው ስልት ግራ ቀኝ የሜያውቁ ሰዎችን እየሰበሰቡ በማሠልጠንና በማስታጠቅ በየአካባቢው ማንነትን መሠረት ያደረገ አረመኔያዊ ጥቃት ማድረስ ነው።ይህ ተግባር ሕዝቡ እንዲደናገጥ፣ እንዲፈራና በስሜት ያልተገባ ርምጃ እንዲወስድ የታለመ ነው።መንግሥት በተለያዩ ቦታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ ያላቸውን ጥፋቶች በቅድሚያ መረጃ ሰብስቦ ርምጃ በመውሰድ ሲያከሽፍ ቆይቷል። ነገር ግን ያለፈው ሥርዓት ያወረሰንን ቀዳዳዎች ሁሉ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ደፍኖ መጨረስ አልተቻለም።
የጥፋት ኃይሎች ከውጭ ላኪዎቻቸውና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በሚገኙ ባልጠሩ አድር ባዮች ትብብር በሕዝባችን ላይ አሳዛኝ ጥቃት እያደረሱ ነው።ሁኔታው እንደ መሪም እንደ ዜጋም ልብ ይሰብራል።
ይህ ግን ከመንገዳችን ወደኋላ፣ ከግባችን ወደ ሌላ አያደርገንም። ተስፋ ቆርጠን እንድናቆም፣ ተሸንፈን እንድናፈገፍግ አያደርገንም።ከምንጊዜውም በላይ ኃይላችንን አሰባስበን እንድንነሣ ያደርገናል እንጂ። መንግሥት ሁሉንም ዓይነት አማራጮች ተጠቅሞ የችግሩን ሰንኮፍ ይነቅለዋል።የጸጥታ አካላት ጥቃቱ ወደተፈጸመበት አካባቢ ተሠማርተዋል።ርምጃም እየወሰዱ ነው። በቀጣይም የሕዝባችንን ደኅንነት ለማስጠበቅ መንግሥት የመንግሥትነቱን ሥራ በቁርጥና በጽናት ይሠራል።ሕዝቡ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጸጥታ አካላት፣ምሁራንና ሌሎችም፧ መንግሥት ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ የሚወስደውን ርምጃ በመደገፍ የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርባለሁ።
@YeneTube

በአሶሳ ግጭት በማስነሳት የተከሰሱ 32 ግለሰቦች እስከ 21 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ተወሰነባቸው!
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሶሳ እና አካባቢዋ አንደኛ ተዘዋዋሪ ችሎት ሰኔ 2010 ዓ.ም. በአሶሳ ከተማ ግጭት በማስነሳት በተከሰሱ 32 ግለሰቦች ላይ ከሰባት እስከ 21 ዓመት የሚደርስ የጽኑ እስራት ቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እንዳስታወቀው ሰኔ 16፣ 17 እና 18 ቀን 2010 ዓ.ም. በአሶሳ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት የ17 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ የንብረት ውድመትም ደርሷል፡፡ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በ32 ሰዎች ላይ ክስ መስርቷል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሶሳ እና አካባቢዋ አንደኛ ተዘዋዋሪ ችሎት ቀደም ሲልም በእነዚሁ ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ፍርድ ቤቱ ዛሬ በአሶሳ ከተማ በዋለው ችሎት ደግሞ በተከሳሾቹ ላይ ከሰባት ዓመት እስከ 21 ዓመት የሚደርስ የጽኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተላለፈባቸው 32 ሰዎች መካከል 15ቱ በሌሉበት ውሳኔ የተሰጠባቸው ናቸው፡፡በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ የፍርድ ሂደቱን ከጨረሱ በኋላ ከየትኛውም ህዝባዊ መብት ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ማገዱንም በውሳኔው ተመልክቷል ሲል የዘገበው ኤፍ ቢ ሲ ነው፡፡

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በምዕራብ ወለጋ ግምቢ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አስመልክቶ የአካባቢው ነዋሪዎች በስልክ ለአብመድ የሰጡት አስተያየት፡፡
Via Amhara Mass Media Agency
@YeneTube @FikerAssefa
Via Amhara Mass Media Agency
@YeneTube @FikerAssefa