YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣይ በሚያከናውነው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሒደት እና በወቅቱ ሊኖር በሚገባው የኮቪድ 19 ጥንቃቄ ዙሪያ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየመከረ ነው፡፡የውይይት መድረኩን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በንግግር ከፍተዋል፡፡በመድረኩ የውጭ ሀገራት የምርጫ ተሞክሮ በፅሁፍ ቀርቧል፡፡

Via OBN
@YeneTube @FikerAssefa
በቅርቡ ግብፅን የጎበኙት የሱዳኑ አልቡርሃን ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሏል!

አልቡርሃን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢትዮጵያ ግድብ ላይ ከሰጡትና ኢትዮጵያውያንን ካስቆጣው አስተያየታቸው በኋላ ወደ አዲስ አበባ የመጡ የመጀመሪያ መሪ ያደርጋቸዋል፡፡

Via Al ain
@YeneTube @FikerAssefa
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለያየ ጊዜ በተደረገ የቤት ውሰጥ ብርበራ ህገ-ወጥ የሆኑ 5ሽጉጦች ፣ 102 የሽጉጥ ጥይቶች እና 8 የክላሽ ጥይቶች ከ7ተጠርጣሪዎች ጋር ይዞ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አሰታወቀ።በተለያየ ቦታ እና ጊዜ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ከፍርድቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ባደረገው ብርበራ ህገ-ወጥ ሽጉጦችን እና ጥይቶችን ሊይዝ መቻሉን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
እውቁ የጄምስ ቦንድ ተዋናይ ሰር ሾን ኮነሪ ከዚህ አለም በሞት ተለየ!

በብሪታኒያ የሚስጥራዊ ተልእኮ ጓዶች ዙሪያ በሚያጠነጥኑት የጄምስ ቦንድ ፊልሞች ዶክተር ኖ፣ ፍሮም ሩሲያ ዊዝ ላቭ፣ ጎልድፊንገር፣ ተንደርቦል፣ ዩ ኦንሊ ሊቭ ትዋይስና ዳይመንድስ አር ፎሬቨር ላይ መሪ ተዋናይ የነበረው ስኮትላንዳዊ ሾን ኮነሪ በተወለደ በ90 አመቱ ከዚህ አለም ዛሬ በሞት መለየቱን ቢቢሲ ዘግቧል።ተዋናዩ ከቦንድ ፊልሞች በተጨማሪ ዘ ሃንት ፎር ሬድ ኦክቶበር፣ ኢንዲያና ጆንስ(ዘ ላስት ክሩሴደር) እንዲሁም ዘ ሮክ አሻራውን ያሳረፈባቸው ናቸው። ሾን በተዋናይነት ዘመኑ 3 ጎልደን ግሎብ፣ 2 ባፍታና የኦስካር ሽልማትን ማግኘት ችሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኤርትራ መንግሥት ህወሓትን ወነጀለ!

"በአፍሪካ ቀንድ መታየት ከጀመረው ለውጥ ትግራይ ተቋዳሽ እንዳትሆን ህወሓት እንቅፋት ሆነ" ሲል የኤርትራ መንግሥት ከሰሰ።የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ሻባይት በተባለው ድረ-ገፅ ዛሬ ባወጣው መግለጫ "የወደቀ" ብሎ የገለፀው የትግራይ ገዢ ፓርቲ አስቀድሞ በቀጣናው ለነበሩ ችግሮች እንደ መነሻ፣ አሁን ላይ ተፈጠረ ላለው መልካም ዕድል ደግሞ እንደ እንቅፋት አድርጎ ወቅሶታል።የአፍሪቃ ቀንድ ከነበረበት አስቸጋሪ ሁኔታ አሁን "ወደ አዲስ እና ልዩ ምዕራፍ" መሸጋገሩን የሚገልፀው የኤርትራ መንግሥት ለዚህም እንደማሳያ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ጎረቤታማቾቹ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የደረሱት የሰላም ስምምነት እና የትብብር ማዕቀፍ በቀዳሚነት አንስቷል።

አዲሱ ምዕራፍ ከሁለቱ አገራት አልፎ በአጠቃላይ ለአፍሪካ ቀንድ ሕዝቦች ተስፋ ይዞ የመጣ ተብሎ በኤርትራ መንግስት ተወድሷል። ይሁንና "የሩቅ" ያላቸው አውሮፓ ሕብረት እና ሌሎች የአህጉሩ ሀገራት (ሆላንድና ስዊድን) እንዲሁም "ጎሰኛ ቡድን" ብሎ የጠራው ህወሓት እንቅፋት ፈጥረዋል ሲል ወንጅሏል።

"ወያነ በሞት ጣር ላይ ሆኖ የሚያደርገው እንቅስቃሴ" ወደፊት መንደርደር የጀመረው ቀጠናዊው ሁኔታ ወደኋላ ሊመልሰው እንደማይችል የኤርትራ መንግስት በመግለጫው መጨረሻ አንስቷል።የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሚመሩት የኤርትራ መንግሥት ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ሥጋት እንዳለው አስታውቆ ነበር።የክልሉ መንግሥት ባለፈው ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ "የኢሳያስ ስርዓት ከትግራይ ህዝብ ጠላቶች ጋር ተሻርኮ ዳግም ወደ ደም መቃባት ሊያስገባን ላይ ታች በማለት ላይ ይገኛል" ብሎ ነበር።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዳሴ ግድብ የሶስትዮች ድርድር ነገ ይቀጥላል!

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ነገ እንደሚቀጥል የሱዳን የመስኖ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ሚኒስቴሩ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በሦስቱ ሀገራት የውሃ ጉዳዮች ሚኒስትሮች ደረጃ ድርድር እንደገና እንደሚጀመር ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ መካከል ከሰሞኑ የተደረገው የሶስትዮሽ ድርድር ነገ ዳግም እንደሚጀመር ነው ካርቱም ያስታወቀችው፡፡

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ከቀናት በፊት በወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲርል ራማፎዛ አነሳሽነት ከሰባት ሳምንታት በኋላ መጀመሩ ይታወሳል፡፡በድርድሩ ሕብረቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ ለተደራዳሪዎች ያረጋገጡት ራማፎዛ ቴክኒካዊ እና ህጋዊ ጉዳዮችን ጨምሮ ስምምነት ባልተደረሰባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሀገራቱ እንደሚስማሙ ያላቸውን እምነት ገልጸው ነበር፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተመራቂ ተማሪዎች በቂ የፌዴራል ትራንስፖርት አገልግሎት መዘጋጀቱን ትራንስፖርት ባለሥልጣን ገለጸ።

ከጥቅምት 23 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ተመራቂ ተማሪዎችን እንዲቀበሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ አስተላልፏል።በዚሁ መሠረት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ የትራንስፖርት ችግር እንዳይገጥም የትራንስፖርት ባለሥልጣን በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።ተማሪዎቹ የጉዞ ችግር እንዳይገጥማቸው በቂ አውቶቡስ መዘጋጀታቸውን በባለሥልጣኑ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ በላቸው ለኢዜአ ገልጸዋል።

የትራንስፖርት አገልግሎቱ ተማሪዎች እንዳይጉላሉ ሲባል ከመናኸሪያ እስከሚማሩበት ዩኒቨርሲቲ ድረስ የማጓጓዝ አገልግሎት ትብብርን መሠረት ባደረገ መልኩ እንደሚሰጥ ነው ዳይሬክተሩ የጠቆሙት። ለተማሪዎቹን የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ከፀጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት ለመሥራት ዝግጅት መደረጉንም ገልጸዋል። በባለሥልጣኑ የአዲስ ከተማ አገር አቋራጭ መናኸሪያ የስምሪትና ቁጥጥር ባለሙያ አቶ አረጋ፣ “ተማሪዎች በጉዞ ወቅት እንዳይጉላሉ ከፖሊስ፣ ከትራንስፖርት ማኅበራት እንዲሁም ከጫኝ እና አውራጆች ጋር ለመሥራት የሚያስችል ዝግጅት አድርገናል” ብለዋል።የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሲባል በጉዞ ወቅት ተማሪዎች አስገዳጅ የጤና መመሪያዎችን ሊተገብሩ እንደሚገባም ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 380 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,866 የላብራቶሪ ምርመራ 380 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ5 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,469 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 804 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 52,517 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 96,169 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዴሊቨሪ ሀዋሳ በ20 ብቻ!

ዴሊቨሪ በ20 ብቻ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ፓኬጅ ከየትኛውም ሬስቶራንት ምግብ መጠጥ ሲያዙ እንዲሁም የባስ ትኬት በዴሊቨሪ ሀዋሳ በኩል ሲቆርጡ የዴሊቨሪ የምናስከፍለው 20 ብር ብቻ መሆኑን እንገልጻለን።

#DiscountPrice 0-3km - #20birr 3-6km #40birr
#DeliveryHawasssa #DeliveryDiscount
የአውሮፓ ኅብረት የፌዴራልና የትግራይ ክልል መንግሥታትን ለማግባባት ጥረት መጀመሩ ተሰማ፡፡ የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነትና ደኅንነት ፖሊሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፕ ቦሬሌ የተመራ ልዑካን ቡድን ከሁለት ሳምንት በፊት ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ክልል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች፣ እንዲሁም በሁለቱም መንግሥታት ገዥ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር መወያየታቸውን የሪፖርተር ምንጮቼ ገልጸውልኛል ብሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ጄነራሉ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና ትብብር ዙሪያ ይመክራሉ፡፡ከዚህ በተጨማሪም ከሌሎች የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚገናኙ እና የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎም ባለፈው ሰኔ ወር ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ጄነራሉ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና ትብብር ዙሪያ ይመክራሉ፡፡ከዚህ በተጨማሪም ከሌሎች የኢትዮጵያ መንግሥት…
የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ!

ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ የገቡት የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በመሆን የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተዋል።ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን በአዲስ አበባ በሚኖራቸው የሁለት ቀናት ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና ትብብር ዙሪያ ይመክራሉ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በጉራፈርዳ ወረዳ የተፈናቀሉ ሰዎችን በ15 ቀናት ውስጥ ወደቀያቸው ለመመለስ እየተሠራ ነው!

በጥቃቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች እስካሁን 6ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ መደረጉን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ተካልኝ ሽፈራው ተናግረዋል።ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ከመንግስት ተቋማት እና ከኃይማኖት ተቋማት የተሰበሰቡ የምግብ ፣ የአልባሳትና የማብሰያ ቁሳቁሶች ለተፈናቃዮች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።የአካባቢው ኗሪዎችና መንግስት እያደረጉት ባለው ድጋፍና ባሳዩት አጋርነት ደስተኛ መሆናቸውን ተፈናቃዮቹ ገልጸዋል።

በወረዳው በተከሰተው ግጭት ከ5 ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የገለጹት የወረዳው አስተዳዳሪ ÷ከሚደረገው ድጋፍ ባሻገር ተፈናቃዮችን በ15 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወደቀያቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።በግጭቱ ተሳታፊ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 12 አመራሮችን ጨምሮ 64 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤንች ሸኮ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ጊስካር ገልጸዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ  ባለቤታቸው የማይታወቁ ቦታዎች፣ ህንጻዎች እና ቤቶች መገኘታቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው ያሉ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመከላከልና  ወደ ህጋዊ መስመር ለማምጣት ባደረገው ማጣራት ባለቤታቸው የማይታወቁ ቦታዎች፣ ህንጻዎች እና ቤቶች መገኘታቸውን አስታወቀ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ዛሬ ማምሻውን ባወጣው የጥሪ ማስታወቂያ፤ የከተማ አስተዳደሩ በከተማው ያሉ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመከላከልና  ወደ ህጋዊ መስመር ለማምጣት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑ ገልጿል።

ከነዚህ ተግባራትም ውስጥ አንደኛው እና ዋነኛው ህገ-ወጥ የመሬት ወረራና ህገ-ወጥ  ግንባታ ሲሆን ይህንኑ በከተማው የሚታየውን ህገ-ወጥ ድርጊት ለማጣራት  እና መረጃ ለማሰባሰብ   በየደረጃው ግብረሃይል በማደራጀት እና ህዝቡን በማሳተፍ ከአንድ ወር በላይ  የማጣራት ስራ ሲሰራ መቆየቱ የሚጠቀስ ነው ብሏል፡፡

ግበረ ሀይሉ ባደረገው ማጣራትም የደረሰባቸው ዋና ዋና  ግኝቶቹን የገለጸ ሲሆን፤ በህገ-ወጥ መንገድ የታጠሩ እና ባለቤትነታቸውን ማረጋገጥ ያልተቻለ ቦታዎችን፣ በህገ-ወጥ መንገድ መገንባት የተጀመሩ ግንባታዎች መኖራቸውን እና ባለቤቶቻቸው ያልታወቁ ቤቶች እና ህንፃዎች መገኘታቸውን  አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ በግኝቶቹ ላይ ውሳኔ ወስኖ እርምጃ ከመውሠዱ በፊት የኔ ነው ባይ ካለ አንድ እድል ለመስጠት እንደሚፈልግ ጠቅሶ፤ ህጋዊ ማስረጃ አለኝ የሚል አካልም ሆነ ግለሰብ ከነገ (ጥቅምት 23/02/2013) ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት መረጃም ሆነ ማስረጃ በመያዝ ለዚሁ ጉዳይ በየክፍለ ከተማው በተዋቀረ ግብረሃይል ጋር በመቅረብ እንዲያስረዳ የከተማ አስተዳድሩ አሳስቧል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የአውሮፓ ኅብረት የፌዴራልና የትግራይ ክልል መንግሥታትን ለማግባባት ጥረት መጀመሩ ተሰማ፡፡ የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነትና ደኅንነት ፖሊሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፕ ቦሬሌ የተመራ ልዑካን ቡድን ከሁለት ሳምንት በፊት ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ክልል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች፣ እንዲሁም በሁለቱም መንግሥታት ገዥ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር መወያየታቸውን የሪፖርተር ምንጮቼ ገልጸውልኛል ብሏል፡፡ @YeneTube…
⬆️
#CrossCheck

Via @EthiopiaCheck

ሪፖርተር ጋዜጣ "የአውሮፓ ኅብረት የፌዴራልና የትግራይ ክልል መንግሥታትን ለማግባባት ጥረት መጀመሩ ተሰማ" በሚል በፊት ገፁ ዛሬ ያስነበበው ዜና 'ስህተት' መሆኑን የአውሮፓ ህብረት እንዲሁም በዜናው ላይ የተጠቀሱት የህወሀት ባለስልጣን አቶ ጌታቸው ረዳ ለኢትዮጵያ ቼክ ማምሻውን አሳውቀዋል።

ሪፖርተር በዘገባው የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነትና ደኅንነት ፖሊሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፕ ቦሬል የተመራ ልዑካን ቡድን ከሁለት ሳምንት በፊት ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ክልል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በሁለቱም መንግሥታት ገዥ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር መወያየታቸውን ገልጾ ፅፏል፡፡

አክሎም "የኅብረቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ጋር በወቅቱ ተገናኝተው መምከራቸውን ሪፖርተር ከምንጮች ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የኅብረቱ ከፍተኛ ልዑካን ወደ ትግራይ ክልልም በማምራት ከክልሉ መንግሥት አመራሮች እንዲሁም ከዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል ጋር መወያየታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይኼው ቡድን ከሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች ጋርም በአካል ተገናኝቶ የመከረ ሲሆን፣ ይህንንም የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑ አቶ ጌታቸው ረዳ ለሪፖርተር ገልጸዋል" ብሏል።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር የሆኑት ዮሀን ቦርግስታም ለኢትዮጵያ ቼክ በሰጡት ማብራርያ "በጆሴፕ ቦሬል የተመራው ልኡክ ከሁለት ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ እና ጅግጅጋ ቆይታ አድርጓል። በጅግጅጋ የሰብአዊ ድጋፍ አሰጣጥን የጎበኙ ሲሆን በአዲስ አበባ ደግሞ ከጠ/ሚር አብይ ጋር በቀጠናው እና ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ባለው ግንኙነት ዙርያ ውይይት አርገዋል። ዜና ላይ ዛሬ እንደወጣው ግን ወደ ትግራይ አልተጓዙም፣ ደጋግሜ ላረጋግጥልህ የምፈልገው ጆሴፕ ቦሬልም ሆኑ ሌላ የልኡኩ አባል እንደተፃፈው ወደዛ አልሄዱም። ፍፁም ስህተት ነው" ብለዋል።

በዜናው ላይ የተጠቀሱት አቶ ጌታቸው ረዳ ደግሞ "የምናነጋግራቸው ብዙ አካላት አሉ፣ በዚህ ግዜ በግልፅ የምንነግራቸው ድርድር የሚባል ነገር እንደማንቀበል እና ሀገራዊ ውይይት (national dialogue) እንደሚያስፈልግ ነው። ጋዜጠኛው መረጃ በጠየቀኝ ወቅት ያስረዳሁት ይህን ነው፣ የአውሮፓ ህብረት ቡድን ትግራይ ለውይይት መጥቶ ነበር ተብሎ የተፃፈው ከየት እንደመጣ አላውቅም" ብለዋል።

በዶ/ር ደብረፅዮን የተፈረመ እና ከስድስት ቀን በፊት በህወሓት የፌስቡክ ገፅ ላይ የተቀመጠ ደብዳቤ ክልሉ የአውሮፓ ህብረት እያደረገ ያለውን ጥረት እና እንቅስቃሴ እንደሚያደንቅ ይገልፃል፣ ይህን ወደ ትግራይ ክልል በአውሮፓ ልኡክ ተደረገ የተባለውን ጉዞ ግን አልጠቀሰም።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 414 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,901 የላብራቶሪ ምርመራ 414 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ9 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,478 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 935 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 53,452 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 96,583 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from SHOPIA ®
SMART WATCH
ሲም ካርድ እና ሚሞሪ ካርድ ይቀበላል
ስልክ መደወል እና ጥሪ መቀበል
ፎቶ ያነሳል(camera)📸📸
facebook,Twitter,WhatsApp ያለው
ከስልኮ ጋር በ ብሉቱዝ(BLUETOOTH ) በማገናኘት የስልኮን አገልግሎት በሰዓቱ መጠቀም ማስቻሉ

የእንቅልፍ ሰዓቶን መቁጠር መቻሉ ሌላም ብዙ አገልግሎት መስጠት መቻሉ ልዩና ተመራጭ ያደርገዋል🥇🥇🥇🥇
Price 💵 1200Birr(20%OFF)
👥Contact @ibrokhalifa/ @Billalnur 📞 call 0921354837/ 0913607603
Forwarded from HEY Online Market
Iphone 12 PRO (New)

Storage: 128 GB
Brand New
Color : Blue, Gold & Silver

Price : 75,000 birr

Contact us
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4
0910695100 @Roviii
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በኮቪድ 19 ከተያዘ ሰው ጋር መገናኛታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ለብቻ ማግለላቸው (ኩዋራንቲን) ማድረጋቸው ተገለፀ።

ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ በቅርበት ያገኙት ሰው የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት ስለተረጋገጥ ራሳቸውን ለብቻ አግልለዋል።

በአሁኑ ሰዓትም ጤናቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ አንደሚገኝ እና ምንም አይነት የቫይረሱ ምልክት እንደሌለባቸውም አስታውቀዋል።

ሆኖም ግን በዓለም ጤና ድርጅት ፕሮቶኮል መሰረት ለቀጣይ ቀናት ራሳቸውን አግልለው እንደሚቆዩ ያስታወቁት ዶክተር ቴድሮስ፥ ስራቸውንም ከቤታቸው ሆነው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአገራችን 16 የሚሆኑ የተንቀሳቃሽ ስልክ መገጣጠሚያ ኩባንያዎች የነበሩ ሲሆን ብዙዎቹ ዘግተው አምስት የሚሆኑት ብቻ በአሁኑ ሰአት በስራ ላይ እንደሚገኙ ታወቀ።

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የአይሲቲ ኢቲ ሀርድዌር ቡድን ባለድርሻ የሆኑት አብይ ምንውየለት እንዳሉት አምራች ኩባንያዎቹ ከገበያ የወጡበት ምክንያት የመጀመሪያው እና ዋነኛው ምክንያት ለተንቀሳቃሽ ስልኮች መገጣጠሚያ ግብአቶች በአገር ውስጥ አለመኖራቸው ሲሆን በዚህም ምክንያት ከውጪ አገር ማስገባት ስለሚያስፈልግ ይህንን ለማድረግ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ከፍተኛ ተግዳሮት መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa