YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለትግራይ ክልል ወረዳዎች የተመደበውን የሴፍቲ ኔት ዕርዳታ ገንዘብ ፌደራል መንግሥቱ እንዳልያዘ የገንዘብ ሚንስቴር ኮምንኬሽን ሃላፊ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ ገንዘብ ሚንስቴር ምንጊዜም የሴፍቲኔት ዕርዳታ ገንዘብን በቀጥታ ፈሰስ የሚያደረገው በመርሃ ግብሩ ለታቀፉ ወረዳዎች እንጅ ለክልሉ እንዳልሆነ ሃላፊው አስታውሰዋል፡፡የክልሉ ወረዳዎች ቅሬታ ያላቀረቡትም ገንዘቡ ስላልታገደባቸው ነው ብለዋል ሃላፊው፡፡

[Sheger/Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
አልጀሪያ አዲስ ህገመንግስት አጸደቀች!

የአልጀሪያ ህገመንግስት ሀገሪቱ ነጻነቷን ካገኘች ከፈረንጆቹ 1962 ወዲህ ለ8ኛ ጊዜ ተሻሽሏል፡፡ኃላፊው እንደገለጹት እንዲጸድቅ በአዎንታ ድምጽ የሰጡት 3.3 ሚሊዮን ወይም 66.8 በመቶ ናቸው ብለዋል፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 359 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,726 የላብራቶሪ ምርመራ 359 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,489 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 953 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 54,405 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 96,942 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ በትናንትናው እለት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን በጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ፣ ጊላ-ጎጎላና ሰቃ-ጀርቢ ቀበሌዎች በተፈፀመው ጥቃት በትንሹ 32 ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን አስታውቋል፣ ባለው መረጃ መሰረት የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል መግለጫው ያሳያል።ኮምሽኑ የደረሰው ጉዳትም በገለልተኛ አካል እንዲጣራ አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ወደ ውጊያ የሚገባ ከሆነ ሙሉ ሀላፊነቱ የሚወስዱት የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስትና የኤርትራ መንግስት ናቸው።"

የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ዶክተር ደብረፅዮን ዛሬ በሰጡት መግለጫ የተናገሩት።
@YeneTube @FikerAssefa
የአውሮፓ ሕብረት ትናንት ሰኞ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ እንዳሳሰበው አስታውቋል።

የሕብረቱ ምክትል ፕሬዝደንትና የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ተወካይ የሆኑት ጆሴፍ ቦሬል ባወጡት መግለጫ ነው የሕብረቱን አቋም ያንፀባረቁት።'ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው' የሚለው መግለጫው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎችና ጎረቤት አገራት ውጥረት ለመቀነስ መጣር እንዳለባቸው አሳስቧል።መግለጫው አክሎ ሁሉም ቡድኖች "ግጭት ቀስቃሽ ቃላት" መጠቀም ማቆም እንዳለባቸውና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን መግታት እንዳለባቸው አሳስቧል።"ይህ መሆን ካልቻለ ግን" ይላል መግለጫው፤ "ይህ መሆን ካልቻለ ግን ጉዳቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናውም ነው" ይላል።

መግለጫው ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር አገር አቀፍ ውይይቶች እንደሚያስፈልጉ አትቷል። በዚህ ውይይት ላይ ሁሉም የፖለቲካ ተዋናዮች ተሳታፊም እንዲሆኑም ጥሪ አቅርቧል።ለኢትዮጵያ ሕዝብ መፃዒ ተስፋና ብልፅግና ብሔራዊ መግባባት እንጂ ግጭት መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል የምክትል ፕሬዝደንቱ መግለጫ ያትታል።የአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያን ለውጥ ለመደገፍ ቁርጠኛ እንደሆኑም ጆሴፍ በመግለጫቸው ተናግረዋል።የሰብዓዊ መብትና የሕግ የበላይነት መከበር በ2021 [በአውሮፓውያኑ] የሚካሄደው ምርጫ ነፃ፣ ተዓማናኒና ፍትሃዊ እንዲሆን ያግዛል ይላል የሕብረቱ መግለጫ።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኮት ዲቯር በተደረገ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አላሳኔ ዋታራ በድጋሚ አሸንፈዋል። የወቅቱ ፕሬዚዳንት ምርጫውን ያሸነፉት አጠቃላይ ከተሰጠው ድምፅ 94.27 በመቶ በማሸነፍ መሆኑን የሀገሪቱን የምርጫ ኮሚሽን ጠቅሶ የዘገበው ፍራንስ 24 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ልደቱ ህክምና እንዲያገኙ ፍርድ ቤት ዛሬ ትዕዛዝ መስጠቱን ተከትሎ ዛሬ ህክምና እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ገለጹ።

“ህመም እየተሰማቸው ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ ህክምና እንዲያገኙ ትዕዛዝ እንዲሰጥልን” የሚል ማመልከቻ ማቅረባቸውን በዚሁ መሠረት ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በመስጠቱ ዛሬ ወደ ሐኪም ይሄዳሉ ሲሉ አቶ አዳነ ለቢቢሲ ተናግረዋል።አቶ ልደቱ ስላሉበት የጤና ሁኔታ ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄም “በእውነት ምንም ሳልደብቅ መናገር የምፈልገው ነገር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ የህመም ስሜት ይታይባቸዋል። ሰውነታቸው ትንሽም ቢሆን ቀነስ ብሏል። በእርሳቸው ህመም ሰው እንዲጨነቅ ስለማይፈልጉ በጣም ካልባሰባቸው በስተቀር ህመማቸውን እና ስቃያቸውን ለሰው መናገር አይፈልጉም።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኦስትሪያ ቬና በሽብር ጥቃት 3 ሰዎች ተገደሉ!

ትናንት ምሽት በኦስትሪያ ዋና ከተማ ቬና 6 የተለያዩ ስፍራዎች ላይ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት 3 ሰዎች መገደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡15 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል፡፡ጥቃቱ የተፈጸመው በእስላማዊው ጽንፈኛ ቡድን አይኤስ ደጋፊ እና በግብረአበሮቹ መሆኑን የኦስትሪያ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ካርል ኔሃመር ተናግረዋል፡፡ በቴሌቪዥን በተላለፈው መግለጫቸው ህዝቡ በቤቱ እንዲቆይ አሳስበዋል፡፡ጥቃቱን ከፈጸሙት ግለሰቦች አንዱ በፖሊስ የተገደለ ሲሆን ሌሎቹን ፖሊስ እያፈላለገ ነው፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ባንክ ለዛሬ ጠርቶት የነበረውን መግለጫ ሰረዘ።

በምስረታ ላያ የሚገኘው የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር በቀጣይ እንቅስቃሴው ዙሪያ ዛሬ በአዲስ አበባ መግለጫ ለመስጠት መገናኛ ብዙሃንን ጠርቶ ነበር፡፡በምስረታ ላይ ያለው አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንክ የሚጠይቀውን መስፈርት በሟሟላት አሁን በአክሲዮን ሽያጭ ላይ ነው የሚገኘው።ባንኩ በምሥረታ ሂደት ላይ ሲሆን ከነሐሴ 11 ቀን 2011ዓ.ም አንስቶ በጀመረው የአክስዮን ሽያጭ እስካሁን ድርስ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ የአክሲዮን ሽያጭ መፈጸሙን አስታውቋል።

በጠቅላላው ከሸጠው አክስዮን ውስጥም ከ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ መከፈሉንም ገልጿል፡፡ይህ ባንክ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ከሚያዝያ 8 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የአክሲዮን ሽያጩን ማራዘሙ ይታወሳል፡፡በባንኩ ቀጣይ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ለህዝብ መረጃ ለመስጠት ይዞት የነበረውን ፕሮግራም ከትናንት በስቲያ በኦሮሚያ ክልል በተፈጸመው ማንነት ላይ መሰረት ባደረገው ጥቃት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን ባንኩን ጠቅሶ ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከክፍያ ጋር በተያያዘ እገዳ የተላለፈበት አንድነት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እንዲከፈት ተወሰነ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ባለመተግበሩ እና ወላጆች በተደጋጋሚ ለትምህርት ሚኒስቴር ባቀረቡት ቅሬታ እገዳ የተላለፈበት ትምህርት ቤት በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እገዳው ተነስቶለታል፡፡ትምህርት ሚኒስቴር ባደረገው የሱፐርቪዝን ስራ ትምህርት ቤቱ አስፈላጊውን ማስተካካያ ማድረጉ እና ከወላጅ ኮሚቴዎች ጋር ስምምነት ላይ የተደረሰ መሆኑንን ቢያረጋግጥም ትምህርት ቤቱ ትምህርት ሚኒስቴር የጣለበትን እገዳ ሳያነሳ እና ሳያሳውቅ ትምህርት በመጀመሩ ትምህርት ቤቱ በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እንዲከፈት መወሰኑ ተገልጿል፡፡

በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እገዳው የተነሳለት አንድነት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ከዛሬ ጀምሮ በመመሪያው መሰረት መደበኛ ስራውን ማከናወን እንደሚችልም ተነግሯል፡፡ከዚህ በኋላ ትምህርት ቤቱ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣውን ማናቸውም መመሪያዎችን ተላልፎ ከተገኘ ትምህርት ቤቱን እስከ መዝጋት የሚያደርስ እርምጃ እንደሚወሰድም ትምህርት ሚኒሰቴር አስታውቋል፡፡ሌሎች ትምህርት ቤቶችም ትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣቸውን መመሪያዎች በመከተል የመማር ማስተማሩን ሄደት ማስቀጠል እንዳለባቸው ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

[MoE]
@YeneTube @FikerAssefa
ከጉራ ፈርዳ ግጭት ጋር በተያያዘ ሶስት የዞን እና አስራ አንድ የወረዳ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ከሁለት ሳምታት በፊት ተፈጥሮ ከነበረው ግጭት ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች ከቀዬዓቸው ሲፈናቀሉ 31 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።ከዚህ ግጭት ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ ተጠርሪዎች እንደተያዙ ተገልጿል።የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን እንደተናገሩት በግጭቱ ተሳትፎ የነበራቸው ሰዎች እየተያዙ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ስድስት የመንግስት ሰራተኞች እና ባለሙያዎች እንዲሁም አራት የፖሊስ አካላትም በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አቶ ፍቅሬ ተናግረዋል።

አንድ የቀበሌ አስተዳዳሪ እና ሶስት የቀበሌ ሰራተኞችም በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲሉ ተናግረዋል ዋና አስተዳዳሪው፡፡ከጉራ ፈርዳ ግጭት ጋር በተያያዘም እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ 87 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ተናግረዋል።የዞኑን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ የፖለቲካ እና የጸጥታ ስራዎች በተደራጀ መልኩ እየተሰራ እንደሆነ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።ግጭቱ በተከሰተባቸው ሁለቱ ቀበሌዎች በድጋሚ ሌላ ችግር እንዳይከሰት ከኮማንድ ፖስቱ ጋር በመቀናጀት የጸጥታ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል አቶ ፍቅሬ፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ብሔርን ለይቶ እየተፈፀመ ያለው ጥቃት በመግለጫ የሚሽሞነሞን ሳይሆን የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሕግ አማካሪ መርሃፅድቅ መኮንን ገለፁ፡፡

እየደረሰ ያለው ጥቃት ‘የንፁሀን ህልፈት’ እየተባለ የሚሽሞነሞን ሳይሆን በዓለም ዐቀፍ ሕግ ይቅርታ እና ምህረት እንኳን የማያሰጥ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ያሉት አማካሪው ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡አማካሪው በቆይታቸው “ይህንን በድፍረት ለመናገር በመንግሥት አካላት ላይም ድፍረቱም የለንም፤ ከፍተኛ የሆነ የወንጀል ጥቃት እየደረሰ ነው፤ የተደራጀ ወንጀል እየተፈጸመ ነው፤ ድርጊቱን በስሙ የመጥራት ድፍረት ሊኖረን ይገባል” ብለዋል።

ድርጊቱን ማንም ይፈፅም ማን ኃላፊነቱን የሚወስደው በዚያ አካባቢ የሚገኘው የመንግሥት አካል እንደሆነም አማካሪው አስምረውበታል፡፡በአካባቢው የሚገኝ የፀጥታ አካል፣ ደኅንነት፣ የመከላከያ ሰራዊት እና ወታደራዊ ኃይል እነዚህን ጥቃቶች መከላከል ካልቻለ የመንግሥትን እና የዜጎችን ኅልውና መታደግ እንደማይችልም ጠቅሰዋል።“የሕግ አስከባሪ አካላት ራሳቸው ምን ያህል ከችግር የፀዱ ናቸው የሚለው ጉዳይም አነጋጋሪ ነው” ብለዋል፡፡

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
በጉጂ ዞን ጉሚ የኦነግ ሸኔ አባላት በፈፀሙት ጥቃት 4 ሰዎች ሲሞቱ በ3ቱ ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የዞኑ አስተዳዳሪ አስታወቁ!

በጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም በጉጂ ዞን ጉሚ ኤልዳሎ ወረዳ መሸጋገሪያ ድልድይ እየሰሩ በነበሩ ሰዎች ላይ የኦነግ ሸኔ አባላት በፈፀሙት ጥቃት 4 ሰዎች ሲሞቱ፣ በ3ቱ ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የዞን አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ኡዶ አስታውቀዋል፡፡በልማት ስራ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት የሀገሪቱን ልማት ለማደናቀፍ እና ህዝቡን የመሰረተ ልማት ተጠቃሚ ላለማድረግ በሽፍቶች የተፈፀመ ወንጀል በመሆኑ ድርጊቱን እንደሚያወግዙት የጉጂ ዞን አባ ገዳዎች ተናግረዋል።መንግስት በእነዚህ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድም ጠይቀዋል።የፀጥታ ኃይሎች በህብረተሰቡ ትብብር ባደረጉት ክትትል በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የፈፀሙ 11 የኦነግ ሸኔ አባትን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የጉጂ ዞን የፀጥታ እና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወልዴ ዱጎ መናገራቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
"በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ በአማራዎች ላይ በተፈፀመው ጥቃት መንግሥት ተጠያቂ ነው" - የአማራ ክልል ምሁራን መማክርት

አብመድ እንደዘገበው የአማራ ምሁራን መማክርት በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ በአማራዎች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡የምሁራን መማክርቱ በመግለጫው እንዳለው ጥቃቱን ማንም ይፈፅመው ማን መንግስት የማስቆም ግዴታ አለበት።በአማራ ላይ የተቃጠውን ጥቃት መንግስት ማስቆም ካልቻለ ኢትዮጵያን ወደ ማትመለስበት ችግር ይከታታል፤ መንግስት የህዝቦችን ደህንነትን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት ቢያውቅም ችላ በማለቱ በተለይም በአማራ ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ቀጥለዋል፤ ይሄም የአማራን ህዝብ በከፍተኛ ደረጃ አስቆጥቷል፤ መንግስት ጉዳዩን በውል ሊረዳው ይገባል ብሏል።

መንግስት የአማራን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ተጨባጭ ሥራ ሰርቶ ማሳየት ይገባዋልም ነው ያለው በመግለጫው።አማራ ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት የአንበሳው ድርሻ እንደተጫዎተ ቢታወቅም አሁን ላይ አንገቱን ቀና እንዳይደረግ ከሁለተኛም ዜጋ ባነሰ ሁኔታ እንዲሆን እያደረገ ነው፤ይሄ ኢትዮጵያን ያፈርሳል፤መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ችግሩን ከማውገዝ ባለፈ ሊከላከል ይገባልም ብሏል፡፡ችግሩ ሰፍቶ ሁላችንም ወደማያባራ እልቂት ከመዳረጉ በፊት ሊታሰብበት እንደሚገባ አመላክቷል፡፡የፌደራል መንግስት ድርጊቱ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሆነ በማመን እርምጃ መውሰድ እንዳለበት የምሁራን መማክርቱ ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
በዜጎች ግድያ ላይ የመንግስት አስፈፃሚ ማብራሪያ እንዲሰጥ የፓርላማ አባላት ጠየቁ፡፡

የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለዛሬ የያዛቸውን አጀንዳዎች እንዲወያይባቸው በአፈ ጉባኤው በኩል የቀርበለትን ዜጎች ማንነታቸውን መሰረት ባደረገ ጥቃት እየተጨፈጨፉ ሌላ አጀንዳ ላይ አንወያይም ብለዋል፡፡በእምቢተኝነታቸው በፅናትም ለዕለቱ የተያዘላቸውን አጀንዳ ውይይት ከመጀመራቸው በፊት ከ2 ሰዓት በላይ ስለዚሁ ጉዳይ በእንባ እየተናነቃቸው ጭምር ሀሳባቸውን በስሜት ገልፀዋል፡፡በመግለጫ መፍትሄ አይመጣም፣ድርጊትና እርምጃ ያስፈልጋል፣ዛሬ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እየተጨፈጨፉ ዝም ካልን ነገ በሺዎች የሚቆጠሩ እንዲጨፈጨፉ መፍቀድ ነው፣ ሲሉም ሞግተዋል፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ ስብሰባውን በተለየ መንገድ ነው ነበር የጀመረው፡፡ አፈ ጉባኤው፣የዕለቱን አጀንዳዎች በዝርዝር ከማቅረባቸው በፊት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ከትናንት በስቲያ በዜጎች ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ በተመለከተ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ የሚያሳስብ መግለጫ በማንበብ ጀምረዋል።የ1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት ከተደረገ በኋላ ወደ ዕለቱ አጀንዳዎች ለመገንባት ማስተዋወቅ ሲጀምሩ፣የተለያዩ የምክር ቤቱ አባላት እዚህም እዛም እጅ እያወጡ ተራ ሳይጠብቁ መናገር ጀመሩ፡፡በዜጎች ላይ የብሔር ማንነትንና ሃይማኖትን መሰረት ባደረገ ጥቃት በየጊዜው እየተጨፈጨፉ በምን ሞራል ነው ሌላ አጀንዳ ላይ የምንነጋገረው? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ብሔራዊ የመረጃ ደህንነት ሰላም ሚኒስቴር ፣ የመከላከያ ሚኒስትር እና ሌሎችንም የሚመለከታቸው አካላት መጥተው ማብራሪያና ምላሽ እንዲሰጡን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡አልሸባብና አይ ኤስ ኤስን ለመመከት በሰው አገር ጭምር ሰላም የሚያስከብረው የመከላከያ ሰራዊታችን ፣ እውን ኦነግ ሸኔን ማሸነፍ አቅቶት ነው ወይ ሲሉ የጠየቁ የምክር አባላትም አሉ፡፡ከ2 ዓመት በፊት በለውጥ ስሜት ስራ ስንጀምር የነበረን ተስፋና ሞራል አሁን የለም ፤ ሲሉ በስሜትና በእንባ ታጅበው ሀሳባቸውን ሲገልፁ ተደምጠዋል፡፡

የምዕራብ ወለጋ አካባቢ የሰላም የማጣት ችግር እንዳለበት እየታወቀ የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ከሚችል ሌላ አካል ጋር ርክክብ ሳይደረግ መከላከያው ለምን ከዛ ስፍራ ለቆ ወጣ? የሚለው መጠናትና ሪፖርት መቅረብ ያስፈልገዋል፣ ከአስፈፃሚ የመንግስት አካላትም ማብራሪያ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ብለዋል የምክር ቤቱ አባላት፡፡

መንግስት ጥቃት በተፈፀመ ቁጥር፣ይህን ያደረገው እገሌ ነው እያለ በተደጋጋሚ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ጠላት ነው የተባለው ከታወቀ “ለምን የማያዳግም እርምጃ መውሰድ አልተቻለም”? ሲሉም ጠይቀዋል፡፡የምክር ቤቱ አባላት በሙሉ በአንድ ድምፅ እና በተመሳሳይ ስሜት ውስጥ ሆነው ስለ ጉዳዩ በምሬት ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ ሕዋሃት እና ኦነግ ሸኔ በምክር ቤቱ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የጠየቁ የምክር ቤት አባላትም አሉ፡፡ከአባላቱ መካከል በዛሬው ስብሰባ ላይ ሙሉ ጥቁር ልብስና ጥቁር ሻርብ የለበሱ 15 ያህል ሴቶችንም ተመልክተናል፡፡እንዲህ በጋለ ስሜት ከ2 ሰዓት በላይ ከተወያዩ በኋላ በአጠረ ጊዜ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት በምክር ቤቱ ተጠርተው ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡና አስፈላጊው ውሳኔ እንዲተላለፍ በመወሰን ወደ እለቱ አጀንዳቸው ተመልሰዋል፡፡

ዘገባው የሸገር ነው
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ የደህንነት ስጋት አለን በሚል ምክንያት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት የተከሳሾች የንብረት እግድ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነበር ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው።ይሁን እንጂ ከተከሳሾች መካከል አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ፍርድ ቤት አልተገኙም።ፍርድ ቤቱም አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ለምን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ በጠየቀበት ወቅት፤ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ተከሳሾቹ የደህንነት ስጋት አለብን በሚል ምክንያት አለመቅረታቸውን ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል።በእነ አቶ ጀዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ውስጥ የተከሰሱት አቶ ሐምዛ ቦረና፤ "አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለ 'አገሪቱ አሁን ያለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ስጋት ስላለን በዚህ ቀጠሮ መገኘት አንችልም' ብለዋል" ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

"አሁን ባለው ሁኔታ አይደለም ጉዳት ይቅርና ሙከራ [የግድያ] ቢደረግብን አገሪቱ ወደ ከፋ አደጋ ውስጥ ስለሚያስገባት ለአገሪቱ በማሰብ ወደ ፍርድ ቤት ከሚደረግ ጉዞ እራሳችንን ቆጥበናል" ስለማለታቸው አቶ ሐምዛ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።ከዚህ በተጨማሪም አሁን አገሪቱ ውጥረት ውስጥ እያለች በንብረት ጉዳይ ላይ ለመከራከር ፍርድ ቤት መመላለስ 'ለእኛ ሃፍረት' ነው በሚል ምክንያት ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን አቶ ሐምዛ፤ አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለን ወክለው ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።በእነ አቶ ጀዋር መዝገብ ስር ተከሰው ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ተከሳሾችም አገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ አሳስቦናል በማለት ለፍርድ ቤቱ መናገራቸውን ከእነ አቶ ጀዋር ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ከድር ቡሎ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ፍርድ ቤቱ በንብረት እግዱ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሕዳር 15 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር የንጹኀን ግድያ አወገዙ፤ ሁሉን አካታች የፖለቲካ ንግግር እንዲደረግም ጥሪ አቀረቡ!

የአፍረካ ኅብረት ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሐመት ዛሬ፣ ጥቅምት 24/2013 ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ግድያ በአጽንዖት አውግዘዋል።ለሰለባዎቹ ቤተሰቦች ጥልቅ የሆነ ሐዘናቸውን የገለጹት ሊቀ መንበሩ፥ ለቆሰሉት ፈጥኖ መሻልን ተመኝተዋል።ይህንን ጭካኔ የተሞላበት ወንጀል የፈጸሙትን መንግሥትን ተከታትሎ በመያዝ ተጠያቂ እንዲያደርጋቸው ጥሪ አቅርበዋል።ሊቀ መንበሩ ሁሉም ወገኖች ግጭቶችንን ከማባባስ እንዲቆጠቡና ውጥረቱን እንዲያረግቡ ጥሪ ከማቅረብ በተጨማሪ ሁሉን አካታች የሆነ ብሔራዊ ንግግር በፖለቲከኞች መካከል በመካሄድ ቀልፍ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ ስምምነት መድረስ ይገባል ብለዋል። ይህ የማይሆን ከሆነ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይወሰን ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ በቀጠናው ላይ ጭምር ያስከትላል ሲሉ አሳስበዋል።የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላምና ደኅንነት ለማስፈን እየወሰደ ያለውን ማሻሻያ እንደሚደግፍ በድጋሜ በማረጋገጥ ሊቀ-መንበሩ መግለጫቸውን ደምድመዋል።

መሉውን መግለጫ ማስፈንጠሪያውን በመንካት ማንበብ ይችላሉ
👇👇

https://au.int/en/pressreleases/20201103/statement-auc-chairperson-situation-ethiopia?fbclid=IwAR2DyyEp11fyjYP-513Yx2NUSl7uSFFBdlj5mR_Xl6BdQV4wJgKUrTE0oyM
መንግሥት ለዜጐች አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጠየቀች!

ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እንዳይፈጸም መንግሥት ለዜጐች አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ እና ወንጀለኞችንም ለፍርድ እንዲያቀርብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጠየቀች።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ በሰጡት መግለጫ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ፣ በደቡብ ክልል ቤንች ሼኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምንም ዓይነት የፖለቲካ አመለካከት የሌላቸው ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አውግዘዋል።

የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ በዓመታዊ ስብሰባ ላይ እያለ ድርጊቱን የሰማው መሆኑን በመጥቀስ፣ ድርጊቱ ሲኖዶሱንና ቤተ ክርስቲያኗን በእጅጉ ያሳዘነ ኢ-ሰብአዊ መሆኑን በመግለጽ አውግዞታል ብለዋል።ቤተ ክርስቲያኗም አላስፈላጊ በሆነ ምክንያት በግፍ ለተገደሉና ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ልባዊ ሐዘኗን ትገልጻለች ብለዋል።መላው ኢትዮጵያውያንም በወንድማማችነት፣ በፍቅርና በአንድነት በመተሳሰብ በፍቅር እንዲኖሩ እና ለጋራ ሰላምና አንድነት እንዲቆሙ ጥሪ ማቅረባቸውን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ በተፈፀመው ጥቃት የሟቾች ቁጥር 34 ደርሷል ተብሏል።

የክልሉ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለሸገር እንዳለው በጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ሲከታተሉ ከነበሩ አስር ሰዎች ውስጥ የሁለቱ ህይወት ማለፉን ዛሬ ጠዋት መረጃው ደርሶኛል ብሏል።በዚህም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 34 መድረሱን የቢሮው ሃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ተናግረዋል።እሁድ አመሻሸሽ በተፈፀመው ጥቃት የሠላሣ ሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ትናንትና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን መግለጹ ይታወሳል።የጥቃቱ ፈፃሚዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ በሶስት አቅጣጫ የፀጥታ ሃይሎች መሰማራታቸውን የተናገሩት የቢሮ ሃላፊው በቁጥር ባይገልፁትም በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች እንዳሉም ተናግረዋል።

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa