YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር አበረከተ!

የገንዘብ ድጋፉን የባንኩ አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አስረክበዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባንኩ የህዝብ እንደመሆኑ መጠን ለህዝብ የሚጠቅሙ ፕሮጀክቶች ላይ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልጸው፤ ለአስተዋጽኦው ምስጋና አቅርበዋል።ከተደረገው ድጋፍ 571 ሚሊዮን ብሩ ከባንኩ ሰራተኞች፤የቦርድ አባላትና ማኔጅመንት የተሰበሰበ ሲሆን ቀሪውን ባንኩ ወጭ ማድረጉ ተገልጿል። የዛሬውን ጨምሮ የፋይናንስ ዘርፉ እስካሁን በአጠቃላይ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ግንባታ የ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል።

[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa
ዩኬ በታሰረችው የዩኬና ኢራን ዜግነት ባለት ሰራተኛ ምክንያት የኢራንን አምባሳደር ጠራች!

የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት(ዩኬ) የዩናይትድ ኪንግደምና ኢራን ጥምር ዜግነት ባለው ናዛኒን ዛጋሪ ራትክሊፌ በተባለችው የእርዳታ ሰራተኛ እስር ምክንያት የኢራንን አምባሳደር መጥራቷን የውጭ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል፡፡የዩኬ ባለስልጣናት ለኢራኑ ዲፕሎማት ሃሚድ ቤይድነጃድ የናዛኒን ዛጋሪ ራትክሊፌ በደፈናው መታሰር እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል፡፡የውጭ ገዱይ ቢሮው የታሳሪዋ አያያዝ ምክያታዊ ያልሆነና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ዛጋሪ ራትክሊፌ በመጋቢት ወር የተለቀቀች ቢሆንም እንደገና በአዲስ ክስ በመስከረም ወር ታስራለች፡፡

Via All ain
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለሰባት የጤና ተቋማት ወደ ውጭ አገራት ለሚጓዙ መንገደኞች የኮሮና ቫይረስ ምርምራ እንዲያደርጉ ፈቀደ።

የግል የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ማዕከላት እንደ ልብ አለመገኘት በርከት ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ቅሬታ ሲያስነሳ ቆይቷል፡፡በተለይም የዉጭ ጉዞ ያለባቸዉ ሰዎች አብዝተዉ ሲያማርሩ ቆይተዋል፡፡የምርመራ ዉጤት ማፍጠኛ ገንዘብ መጠየቃቸውንም መንገደኞቹ ሲያነሱ ቆይተዋል፡፡

አሁን ላይ ታዲያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቀደም ሲል ምርመራ ሲያደርግ የነበረዉን ኢንተር ናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪስን ጨምሮ 7 የግል ሆስፒታሎች የኮቪድ 19 ምርመራ እንዲያደርጉ ፈቅጃለሁ ብሏል፡፡ይህንም የሚመለከታቸዉ አካላት ሁሉ እንዲያዉቁት ተደርጓል ብለዋል፤ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብሄራዊ የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ክፍል አስተባባሪ አቶ ይማም ጌታነህ፡፡

የኮቪድ ምርመራ እንዲያደርጉ የተፈቀደላቸዉ ሆስፒታሎችም፣አሜን ጠቅላላ ሆስፒታል፣አሜሪካ ሜድካል ሴንተር፣ቤተ-ዛታ ሆስፒታል፣ኢንተር ናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪስ፣ አዲስ አበባ ሲልክ ሮድ ሆስፒታል፣ኢንተርናሽናል ኦርጋናይዛሽን ፎር ማይግሬሽን እና ዉዳሴ ዲያግኖስቲክስ መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ይህ በብዛት ሼር እየተደረገ ያለ መረጃን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንደማያውቀው ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቋል።

ባልተረጋገጠ መረጃ እንዳይደናገሩ በሶሻል ሚድያ ከሚተላለፉ የሀሰተኛ መረጃዎች ራስዎን ይጠብቁ።

Via @EthiopiaCheck
@YeneTube @FikerAssefa
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ስልጠና ለማስጀመር የሚያስችል ዝግጅት ማከናወኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ አስታወቀ።

አሁን ላይም ወረርሽኙን እየተከላከሉ የትምህርትና ስልጠናውን ተግባር ለማስቀጠል የሚያስችል በቂ ዝግጅት የተከናወነ በመሆኑ ትምህርትና ስልጠናው ጥቅምት 23 እንደሚጀመር ተገልጿል።ወረርሽኙን ተከትሎ ትምህርትና ስልጠና ቢቋረጥም ከከተማው የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ጋር በመሆን ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ኤጀንሲው ተገልጿል።

በዚህም የኮቪድ ሕሙማን ማቆያ አልጋዎችን፣ ማስኮችን፣ ሳኒታይዘር፣ አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያዎችን እንዲሁም የሸገር ዳቦ ማከፋፈያ አሮጌ አውቶቡሶችን የማምረትና የማደስ ስራ እና መሰል ተግባራት ተከናውነዋል ተብሏል።ይህ በኮሌጆቹ የተከናወነው ማህበረሰባዊ ችግሮችን የመፍታት ጅምር እንቅስቃሴ የሚበረታታና በቀጣይ በሁሉም መስክ መቀጠል የሚገባው መሆኑ ነው የተገለፀው።ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመገኘት በኮሌጁ የተደረገውን ቅድመ ዝግጅት ተመልክተዋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬው ዕለት አቶ ልደቱ አያሌው አዳማ በሚገኘው ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር።

የዛሬው የአቶ ልደቱ ቀጠሮ "ሕገመንግስቱን በኃይል ለመናድ፤ የሽግግር መንግስት ሰነድ በማዘጋጀት፤ ከድጡ ወደ ማጡ የተሰኘ ለውጡን የሚቃወም መጽሃፍ በመጻፍ፤ ....ወዘተ" በሚል የኦሮሚያ ክልል መንግስት ዓቃቤ ሕግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ ጠበቆቻቸው ያቀረቡትን የመጀመሪያ የክስ መቃወሚያ ላይ ብይን መስጠት (ያስከስሳል ወይስ አያስከስስም በሚለው ላይ) እንዲሁም የቀረበውን የዋስትና መብት መርምሮ ለመፍቀድ ነበር።በዚህ መሰረት ዐቃቤ ህግ፣ አቶ ልደቱ እና የአቶ ልደቱ ጠበቆች 8.40 ላይ በተሰየመው ችሎት ቀርበዋል።

ችሎቱ "የመጀመሪያ መቃወሚያ የቃል ክርክሩ ወደ ፅሁፍ ተገልብጦ ስላልደረሰ በዛሬ ችሎት ጉዳዩን መርምረን ብይን ለመስጠት አልቻልንም። ስለዚህ ተለዋጭ ቀጠሮ ለመስጠት እንገደዳለን በዚህ ላይ አቃቢ ህግ እና ጠበቆች አስተያየት ካላችሁ " ሲል ገልጿል።አቃቢ ህግ ተቃውሞ እንደሌለው ሲያስታውቅ የአቶ ልደቱ ጠበቆች ግን የተፋጠነ ፍትህ እንደሚያስፈልግ፤ አቶ ልደቱ እያመማቸው እንደሆነ፤ በ48 ሰአት ውስጥ የዋስትና ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ህጉ ቢደነግግም ጥያቄ ካቀረቡ ሳምንት እንዳለፈ በማመልከት ችሎቱ የቃል ክርክሩን መሠረት አድርጎ በዋስትናው ላይ ብይን ሊሰጠን ይገባል በማለት አቤቱታ አቀረቡ።

ችሎቱም አቶ ልደቱ የተፋጠነ ፍትህ ማግኘት እንዳለባቸው እንደሚያምን። ነገር ግን የቃል ክርክሩ በፅሁፍ ተገልብጦ መመርመር ሳይችል ዋስትና መፍቀድ አንደማይችል ገለጿል።ከሚቀጥለው ቀጠሮ በፊት የቃል ተቃውሞው በጽሁፍ ተገልብጦ ከደረሰ ችሎቱ ሊያየው እንደሚችል በመግለጽ የዋስትና ጥያቄው ላይም ሆነ የመጀመርያ ደረጃ መቃወሚያው ላይ ብይን ለመስጠት ለህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4 ሰአት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን በስፍራው የተገኙት የኢዴፓ ፕሬዚደንት ገልጸውልናል።

Via Ethiopian Democratic Party(ኢዴፓ)
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ከ'ፀረ ሰላም ኃይሎች' ጋር ሲሳተፉ የነበሩ 15 ግለሰቦች እጃቸውን ሰጡ!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ስር በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የ'ፀረ ሰላም ኃይሎች'ን ተልእኮ በመፈጸም ሲሳተፉ እና ሲተባበሩ የነበሩ 15 ግለሰቦች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን መስጠታቸው ተገጸ።በዞኑ የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት በተለይም ከኅብረተሰቡ ጋር እየተካሄደ ባለው ውይይት እና በተደረሰው የጋራ መግባባት በወምበራ ወረዳ 14 እንዲሁም በማንዱራ ወረዳ ደግሞ አንድ በድምሩ 15 ከ'ፀረ ሰላም ኃይሎች' ጋር ሲሳተፉ እና ሲተባበሩ የነበሩ ግለሰቦች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጥተዋል ነው የተባለው።የክልሉ መንግሥት በመተከል ዞን የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፈታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሠራ ያለውን ሥራ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ምርመራ ውጤት ሳይዙ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ግብጻውያን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲቆዩ መደረጉን በአዲስ አበባ የግብፅ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡ግብጻውያኑ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ለ14 ቀናት ያህል ቆይተው ወደ ኩዌት ለመሄድ ነበር ብሏል ኢምባሲው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከሐሰተኛ የገንዘብ ኖት ዝውውር ጋር በተያያዘ 5 የክስ መዝገቦችን ከፍቶ እያጣራ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ከሚሽን አስታወቀ፡፡

በሐሰተኛ ነባሩ የብር ኖት አንድ የክስ መዝገብና በሐሰተኛ አዲሱ የብር ኖት ደግሞ አራት የክስ መዝገቦችን በመክፈት እያጣራ መሆኑን በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ የህገ-ወጥ ገንዘብ ዝውውር ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጥበቡ ገልጸዋል፡፡በዚህም መሰረት 174 ሺህ 350 ሐሰተኛ ነባሩ ባለ መቶና ባለ አምሳ የብር ኖት በሁለት ተጠርጣሪዎች እጅ የተያዘ ሲሆን በአንድ ግለሰብ ደግሞ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ሐሰተኛ አዲሱ ባለ መቶና ባለ ሁለት መቶ የብር ኖት በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ ተከትሎ በተደረገ ክትትል 14 ሺህ 800 ሐሰተኛ ባለ መቶና ባለ አምሳ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር መዋሉም ተጠቁሟል፡፡ሐሰተኛ የገንዘብ ኖት ከትክክለኛው ጋር በመቀላቀል ገበያ ላይ ከዋለ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ቢሮው የወንጀሉን ምንጭ ለማድረቅ ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየሰራ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡በአሁኑ ጊዜ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተሰራጨ ያለውን የሐሰተኛ ገንዘብ ዝውውርን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጠይቀዋል፡፡

[የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት]
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በኤጂያን ባህር የተነሳ የመሬት መንቀጥቀጥ ቱርክና ግሪክን አንቀጠቀጠ!

በኤጂያን ባህር የተከሰተ ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ ቱርክና ግሪክ ደርሶ ህንጻዎች እንዲደረመሱ ምክንያት ሆኗል፤በፈረንጆቹ 1999 በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በእዝመር ከ17ሺ በላይ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡

Video:Social Media
[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ማእከሉን መቐለ ላደረገው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ አዲስ የተመደቡ አንድ አዛዥ ዛሬ መቐለ ከደረሱ በኃላ በክልሉ የፀጥታ ሐይል እንዲመለሱ መደረጉ ተገለፀ።የትግራይ ክልል መንግሥት "የፌደራል መንግስት ሰራዊቱን ማዘዝ አይችልም" ይላል። Via Million HaileSelasie @YeneTube @FikerAssefa
ትናንት ከመቀሌው አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ወደመጡበት የተባረሩ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን የሉም ሲሉ የሕወሃት ሥራ አስፈጻሚ አባል ጌታቸው ረዳ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ ጌታቸው ወታደራዊ አዛዡን በስም ባይጠቅሱም፣ ከመስከረም 30 በኋላ የተሰጠ የእሳቸውም ሆነ የሌሎች ከፍተኛ መኮንኖች ሹመት በትግራይ ክልል መንግሥት ተቀባይነት እንደሌለው ግን ለተጠቀሱት መኮንን ተነግሯቸዋል ብለዋል፡፡ የክልሉ መንግሥት ሕጋዊ ካላቸው ነባሮቹ የሰሜን ዕዝ አዛዦች ጋር ተባብሮ መስራቱን እንደሚቀጥልም አውስተዋል፡፡ ፌደራል መንግሥቱ ስለ ጉዳዩ እስካሁን የሰጠው ማረጋገጫ አልሰጠም፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 488 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,866 የላብራቶሪ ምርመራ 488 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,464 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 960 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 51,713 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 95,789 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በኢትዮጵያ ፌዴራዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀጽ 87 በተደነገጉ ግልጽ መርሆዎች መከላከያ ሰራዊት አዋጅ ቁጥር 1100/2011 በተሰጡት ግዳጆች መሰረት ዝርዝር ተልዕኮዎችን ለማስፈጸም የሚያስችሉ ደንቦች እና መመሪያዎችን በማውጣት በሃገራችን ላይ የተቃጡ የውጭና የውስጥ ጥቃቶችን በመመከት የሃገራችንን ሉዓላዊነት አስከብሯል። የህዝብንም ሰላም በማስጠበቅ ላይ ይገኛል።

መከላከያ ሰራዊቱ የአፍሪካውያን ወንድሞቻችን ሰላም የእኛም ሰላም ነው በሚል መርህ በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ተሰማርቶ ዛሬም ግዳጁን በአስደናቂ ሁኔታ በመወጣት ላይ ይገኛል። ከሁሉም በላይ የዓለም ህዝቦችና የቀጠናችን ብሎም የሃገራችን ዋነኛ ጠላት የሆነውን አሸባሪነት ለመዋጋት በጎረቤት ሃገር ሶማሊያ የመሸገውን የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን በመመከት ቀጠናችን ሰላም የሰፈነበትና የተረጋጋ እንዲሆን መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ነው።

በሃገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ አለመረጋጋቶችን ከሌሎች የሃገራችን የፀጥታ ሃይሎች፣ ከክልል መስተዳድሮች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሃገር ሽማግሌዎችና በዋነኝነት ከህዝባችን ጋር በመተባባር ችግሩን ለመቅረፍ ዘለቄታዊ መፍትሄ እንዲመጣ ሰርቷል፤ አሁንም በመስራት ላይ ይገኛል። በዚህ ተግባሩ ሰራዊታችን በደረሰበት ቦታ ሁሉ ህዝብ ከፍተኛ የሰላም አየር የሚተነፍስ እና እፎይታ የሚሰማው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝቦች ህያው ምስክር ናቸው።

ከእነዚህ የሰራዊቱ አኩሪ ድሎች የምንረዳው ነገር ቢኖር ሰራዊታችን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በአንድ ጊዜ ግዳጆችን መወጣት የሚችል፣ ለፈተናዎች የማይበገር፣ ለሃገር ሉዓላዊነት እና ለህዝቦች ሰላም ሲል ማንኛውንም መስዋዕትነት ከመክፈል ወደ ኋላ የማይል ህዝባችን የሚመካበት ሰራዊት መሆኑን ነው።

የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች

የመከላከያ ሰራዊታችን የተጋድሎና የአሸናፊነት ገድሉ በወታደራዊ ስምሪት እና የግዳጅ አፈጻጸም ላይ ብቻ ሳይገደብ የህዝብ ችግር ችግሬ ነው የሚል የህዝቦች ደህንነትና ኋላ ቀርነት የሚያንገበግበውና የሚቆጨው ያለውን ሁሉ ለመስጠት ወደ ኋላ የማይል፣ የህዝባችን አለኝታ የሆነ የልማትና የሰላም ሰራዊት ነው። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የአንድነትና የጥንካሬ መለያ የሆነውን ታላቁ የህዳሴ ግድብ ገንብቶ ለማጠናቀቅ በሚደረገው ጥረት ሰራዊቱ ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ለግድቡ ግንባታ ከወር ደመወዙ በማዋጣት በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ አስተዋጽኦ ከማበርከት አልፎ በግድቡ ላይ ሊሰነዘር የሚችል ማንኛውንም አይነት ጥቃት ለመመከት ሌት ተቀን ዘብ ቆሞ በመጠበቅ ላይ ይገኛል። መከላከያ ሰራዊታችን ከራሱ በፊት ለህዝቡና ለሃገር የሚለውን እሴት መሰረት በማድረግ የሃገራችን ህዝቦች ለገጠማቸው ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ግንባር ቀደም ተዋናይ በመሆን አብነት የሚሆን ተግባር እየፈጸመ ይገኛል።

በጎርፍ አደጋ ዜጎች የሚደርስባቸውን አደጋ ለመቀነስ፣ በደም ልገሳ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ፣ በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ ተሰማርቶ በማገዝ፣ በተፈጥሮ ጥበቃ ላይ ጉልህ ተሳትፎ በማድረግ፣ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ የሆነውን ኮቪድ19 በሽታን ለመከላከል፣ ከደመወዙ ቀንሶ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ በማድረግ፣ ገበታ ለሃገር ፕሮጀከት እውን እንዲሆን የወር ደመወዙን በማዋጣት እና በሃገራችን በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰተውን የአንበጣ ወረርሽኝ ከህዝቡ ጋር በመሆን በመከላከል ከፍተኛ ጥረት ያደረገና በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ ህዝባዊነቱን ያስመሰከረ ተግባሩን ከመጀመሪያውኑ ሰራዊቱ የታነጸበት መሰረታዊ ባህሪው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ የሚያውቀው ሃቅ ነው።

መከላከያ ሰራዊታችን ሃገራዊ ግዳጆቹን ሲወጣና ህዝባዊ ተግባራቱን ሲያከናውን የሚገጥሙትን ችግሮች ሁሉ በመቋቋም ፈተናዎችን በጽናት ተጋፍጦ በማለፍና ውድ ህይወቱን መስዋዕት በማድረግም ጭምር መሆኑ በህዝባችን የሚታወቅ ሃቅ ነው። ይሁን እንጅ ሰራዊቱ የሃገሪቱን ሉዓላዊነትና የህዝቦችን ሰላም የማረጋገጥ ህገ መንግስታዊ ተልዕኮውን በጀግንነትና በቁርጠኝነት እየተወጣ ባለበት በዚህ ሰአት የሃገራችንን ሰላምና ደህንነት የማይፈልጉ ቡድናዊና ፖለቲካዊ ፍላጎት ያላቸው ሃይሎች የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የሰራዊቱን ስምና ዝና በማጠልሸት በመርህና በህግ ላይ ያልተመሰረተ የትችት ናዳ በማውረድ ላይ የሚገኙ ቢሆንም ሰራዊቱ ይህን የፀረ ሰላም ሃይሎች አጀንዳ በውል በመገንዘብ ትኩረቱን ግዳጁ ላይ ብቻ በማድረግ እየሰራ ይገኛል።

የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች

ሰሞኑን በተለያዩ የትግራይ መገናኛ ብዙሃን ወቅታዊ የአቋም መግለጫ በሚል ርዕስ ስር መግለጫ ያወጣው አካል ሰራዊቱን የሚመለከቱ ጉዳዮች የተካተቱበት ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቶ አሰራጭቷል። በዚህ መግለጫ 1ኛ ተራ ቁጥር ላይ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 87(5) ድንጋጌ መሰረት የመከላከያ ሰራዊቱ ተግባር ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ በሆነ አኳኋን እንደሚያከናውን የተደነገገውን መርህ በሚጥስ መልኩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሃይሎች ተወያይተው ከሚሰጡት መፍትሄ ውጭ መከላከያ የአደረጃጃት፣ የስምሪትና የቁጥጥር ተግባሩን መፈጸም አይችልም በማለት መከላከያ በተቋማዊ እቅዱ እንዲሁም ወቅታዊና ሃገራዊ የደህንነት ስጋቶችን መነሻ አድርጎ ግዳጁን እንዳይፈጽም በሚገድብ አኳኋን የተዛባ ይዘት ያለው መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ መግለጫ ተራ ቁጥር 5 ላይ ደግሞ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሃገር ሉዓላዊነትና የህዝብ ደህንነት አደጋ ላይ የወደቀ በዝምታ እንዳለፈና የህገ ወጥ የፖለቲካ ሃይሎች ጥቅም አስጠባቂ ሃይል መሆኑን የሚገልጽ መልዕክት በመግለጫ ላይ ተካቷል። እውነታው የመከላከያ ሰራዊታችን የዜጎችን ህይወት ለመታደግ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ተሰማርቶ አስፈላጊ ተገቢና ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ይህንን በተጻረረ መልኩ ሰራዊቱ ህዝብን እየጨፈጨፈ ነው በማለት የመከላከያ ሃይሉን የማይመጥን፤ ተቋሙ ለሃገርና ለህዝብ የከፈለውን እና እየከፈለ ያለውን ክብር መስዋዕትነት የሚያንኳስስ ሃገራዊ ተልዕኮውን እና አኩሪ ታሪኩን የሚያጠልሽ መልዕክት ይህ አካል ባወጣው መግለጫ ተስተጋብቷል። ይህንኑ መግለጫ ተከትሎ አንዳንድ ግለሰቦች እና ባለስልጣናት በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ይህ አካል መከላከያን በሚመለከት ያወጣውን መግለጫ በማስተጋባት ፍጹም የሰራዊቱን ህገ መንግስታዊ ተልዕኮ በማራከስ ተግባር ላይ ተጠምደው ይገኛሉ።

ይህ ተግባር መከላከያ ሰሰራዊቱ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እና በትግራይ ክልል የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ከክልሉ ህዝብ ጋር ከፍተኛ ጥረት በሚያደርግበት የክልሉ ህዝብ የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት ትርጉም ባለው ደረጃ ህዝባዊ ወገንተኝነቱን እያስመሰከረ ባለበት እና አጠቃላይ በክልሉ ያለውን ስምሪት የሃገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር አላማ አድርጎ ግዳጁን ለመወጣት ዝግጁነቱን ባረጋገጠበት ወቅት የሰራዊቱን ተልዕኮ የሚገድብ መግለጫ ማውጣቱ አግባብነት የጎደለው ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል።

ይህ መግለጫ የሰራዊቱን ተልዕኮ ያላገናዘበ፣ ግዳጁንም ተንቀሳቅሶ እንዳይፈጽም የሚያስተጓጉል ሃገራዊና ክልላዊ ተግባሮቹንም በአግባቡ እንዳይወጣ የሚያደናቅፍ ሃላፊነት የጎደለው መግለጫ ነው።

ከዚህ በፊትም እነዚህ አካላት ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶች በማስተላለፍ ላይ የነበሩ ቢሆንም (1/2)
ለህዝቦች ክብር እና ጥቅም ሲባል በከፍተኛ ሃላፊነት መንፈስ ለማለፍ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። መላው የሃገራችን ህዝቦች እንደሚገነዘቡት የመከላከያ ሰራዊታችን የማንም ፖለቲካ ሃይል¸ክልል ወይንም ቡድን ጉዳይ አስፈጻሚ ሳይሆን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሉዓላዊነታቸውን እንዲያስከብርላቸው¸ሰላምና ደህንነታቸውን እንዲያረጋግጥላቸው የገነቡት ጠንካራ፣ ብሄራዊና ሃገራዊ ተቋም ነው። ስለሆነም የሰራዊቱን አደረጃጀት¸ስምሪትና የግዳጅ አፈጻጸም የሚመለከቱ ጉዳዮችን ሰራዊቱ በህገ መንግስቱ የተቀመጠለትን መርህና በአዋጅ የተሰጠውና ግዳጅና ተልዕኮ መሰረት በማድረግ ተግባራቱን በራሱ የሚወስን እንጅ የሰራዊቱን አጠቃላይ ተልዕኮ እኔ ነኝ የምወስንልህ በሚል አግባብ ይህ አካል የሰጠው መግለጫ የሰራዊቱን ገለልተኝነት የሚጋፋ ግልጽ የሆነ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት መግለጫ ሆኖ አግኝተነዋል።

ይህ ወቅት የሃገራችን ህዝቦች እንደ ሃገር የገጠማቸውን ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች በመመከት ሰላማቸውን ለማረጋገጥና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ ደፋ ቀና በሚሉበት ወቅት የሃገራችንን እድገት የማይፈልጉ አካላት በተለይ ከህዳሴ ግድባችን ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በግልጽ በሚጻረር መልኩ በእጅ አዙር እና በቀጥታ ጥቃት የሚፈጽሙበትና አንዳንድ ፀረ ሰላም ሃይሎች ሃገራችንን ወደለየለት ትርምስ ለማስገባት አላማ አድርገው በሃገራችን የተለያዩ ክፍሎች በዜጎች ላይ አሰቃቂ ግድያ እና የማፈናቀል ወንጀል በመፈጸም ላይ የሚገኙ መሆኑ ይታወቃል።

መከላከያ ሰራዊት ከህዳሴ ግድብ ጋር የተያያዙ የደህንነት ስጋቶችን ለመመከት የሚያስችል ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ ባለበት እና በሃገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የተከሰቱ ግድያዎች እና መፈናቀሎችን ለማስቆም አስቸጋሪ የአየር ፀባይ እና መልክዓ ምድራዊ ቦታዎች ዘልቆ ሰፊ ስምሪት በማድረግ፤ ክቡር መስዋዕትነትን በመክፈል የህዝቡን ሰላም ለማረጋገጥ ጥረት በሚያደርግበት በዚህ ወቅት መግለጫውን ያወጣው አካል የሰራዊቱን ወርቃማ እድል በሚያጎድፍ መልኩ ሰራዊቱን በሚመለከት ያሰራጨው መልዕክት ፍጹም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

ጉዳዩ ከህገ መንግስቱ ጋር በቀጥታ የሚቃረን¸የሃገር መከላከያ ሰራዊት ስምሪት እና ተልዕኮ በምንም መልኩ በአንድ አካል ወይም ቡድን ስር የማይወድቅ ህጋዊና ህገ መንግስታዊ በሆነ አግባብ ብቻ የሚመራ መሆኑን እያስታወቅን መግለጫውን ያወጣው አካል ስህተቱን በይፋ እንዲያርም አጥብቀን እንጠይቃለን። ማንኛውም አካል የሰራዊቱን ተልዕኮ በሚያደናቅፍ አግባብ መግለጫ ከመስጠት እና አላስፈላጊ መልዕክት ከማስተላለፍ እንዲቆጠብም እናሳስባለን።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ሃገርና ህዝብ የሰጠንን ህገ መንግስታዊ ተልዕኮ በገባነው ቃልኪዳን መሰረት ከማንኛውም የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ በመሆን፣ ክቡር የሆነውን ህይወታችንን በመክፈል ጭምር የሃገራችንን ሉዓላዊነትና የህዝባችንን ሰላም ለማስጠበቅ ከመቸውም ጊዜ በላይ በአስተማማኝ ቁመና ላይ የምንገኝ መሆኑን ለመላው ህዝባችን እያረጋግጥን የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም እንደወትሮው ሁሉ ከጎናችን ሆኖ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን እንዲቀጥል ጥሪያችንን እናቀርባለን።

መላው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት

እኛ የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት በተጋድሎና በድል የደመቀ አንፀባራቂ ታሪክ ያለን ሰራዊት ነን። በከፍተኛ ህዝባዊ ወገንተኝነትና ፅናት ምድራዊ ፈተና ተቋቁመን እና ጥሰን በማለፍም ለሃገራችን እና ለህዝባችን ሰላም፣ ደህንነትና ልማት ስንል ሁሉንም አይነት መስዋዕትነት እየከፈልን አልፈናል። በቀጣይም ከዚህ ጉዟችን ሊያደናቅፉን የሚጥሩ፣ ከተልዕኳችን ሊገድቡን ከሚሞክሩና አንድነታችንን ሊሸረሽሩ በሚታክቱ ማንኛውም አይነት ሃይሎች ሴራ ሳንገታ ደማቅ ታሪክ መስራታችንን እንቀጥላለን።(2/2)

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በሰበታ አወዳይ እና ሻሸመኔ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች እና ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት መገደላቸው ተገለፀ።

የኦሮሚያ ፀጥታ አስተዳደር በበኩሉ የአወዳዩ ግድያ በሰህተት የተፈጠረ እና የሻሸመኔው ህግ ለማስከበር የተወሰደ እርምጃ ሲሆን፤ የሰበታው ደግሞ እርስ በርስ በተፈጠረ ሽኩቻ ነው ብሎታል። በግድያው የተጠረጠሩ ሰዎች ደግሞ በቁጥጥር ሰር ውለዋል ብሏል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ያጸደቀችው የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ በግለሰቦች እጅ የተያዙትን መሳሪያ ለመቀማት የወጣ ሳይሆን ህጋዊ ለማድረግ የሚረዳ መሆኑን የሰላም ሚኒስትር ሚኒስቴር አማካሪ አቶ ሚናስ ፍሰሃ ተናገሩ።

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አማካሪ ሚናስ ፍሰሃ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ህብረሰተቡ ቀድሞ የያዘውን የጦር መሳሪያ የሚቀማ ሳይሆን ቀድሞ የያዙትም ህጋዊ ለማድረግ የሚረዳ ነው። ማስመዝገቡም ጥቅሙ ከፍተኛ ነው።

አዋጁ ከጸደቀ 10 ወራት ያስቆጠሩን ያስታወሱት አቶ ሚናስ ፣ ቀደም ብለው የታጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎች የታጠቁት የጦር መሳሪያ በቀሪው ዓመት ከሁለት ወር የሽግግር ጊዜ በአካባቢያቸው በሚገኙ ተቆጣጣሪ ተቋም ተገኝቶ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ ህጋዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አመልክተዋል።

እንደ አቶ ሚናስ ገለጻ፤ በጊዜው የጦር መሳሪያውን የሚያስመዘግብ ሰው ከዚህ ቀደም መሳሪያው በህገወጥ መንገድ የተገኘ ቢሆንም እንኳ እንደየወንጀሉ ሁኔታ ምህረት ይደረግለታል።ሆኖም በጊዜ ገደቡ ውስጥ ፍቃድ ያልወጣበት የጦር መሳሪያ በተቆጣጣሪው የሚወረስ ሲሆን፤ የጦር መሳሪያ ፍቃዱ ለግለሰብ በሁለት ዓመት ለድርጅት ደግሞ በ5 ዓመት መታደስ እንዳለበት ስለተደነገገ ቀድሞ ፍቃድ ማውጣት ይገባል።

ለመሳሪያቸው ፍቃድ ለማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች የአደንዛዥ እጽ ወይም የመጠጥ ሱስ የሌለባቸው እና የአእምሮ ጤናቸው የተስተካከለ እንዲሁም በአካባቢያቸው የመልካም ስነ ምግባር መገለጫ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ያሉት አቶ ሚናስ፣ ለአብነት በመንደራቸው ከብዙ ሰዎች ጋር የሚጣሉ እና አምባጓሮ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚሳተፉ ከሆነ ለደህንነታቸው ሲባል የጦር መሳሪያ እንዲይዙ ህጉ እንደማይፈቅድ አስታውቀዋል።

[አዲስ ዘመን]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ቀደም ሲል እንደገመተው እንዳለሆነ የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) አስታወቀ!

በተተናቀቀው በጀት አመት የአገሪቱ ጠቅላላ የስራ ውጤት (GDP) እድገት 1.9 በመቶ እንደሆነ የገ፣ተ ሲሆን በሚያዝያ ወር ይህ ግምት 3.2 በመቶ እንደሚሆን ነበር፡፡ከሳምንት በፊት የወጣው የተቋሙ የሰሃራ በታች የኢኮኖሚ ምልከታ የአገራት ኢኮኖሚ እድገት የኮሮና ተህዋስ በፈጠረው ተፀእኖ ይበልጥ እንደተጎዳ ያብራራል፡፡ከዚህ ተፀእኖ ያልወጣቸው ኢትዮጵያም የኢኮኖሚ እድገቷ ቀደም ሲል(ከወረርሽኑ መከሰት በፊትም ጭምር) ሲገመቱ ከነበሩ የእድገት መቶኛዎች አንፃር እጅግ ዝቅ ያለ ነው፡፡ሆኖም ኢትዮጵያ አዎንታዊ እድገት ካላቸው ጥቂት የክፍለ አህጉሩ አገራት ተርታ ተመድባለች፡፡

ሆኖም አብዛኞቹ የሰሃራ በታች አገራት የኢኮኖሚ እድገት ከዜሮ በታች እና ኔጋቲቭ ውስጥ መሆኑ በኢኮኖሚ ምልከታው ታይቷል፡፡የኢትዮጵያ ጠቅላላ የስራ ውጤት በ2021 እኤአ በሚጠናቀቀው በጀት አመት ዜሮ እንደሚሆን ድርጅቱ የገመተ ሲሆን ይህም በ 2022 ወደ መልካም እድገት ይቀየራል ሲል ገምቷል፡፡ከፍተኛ ጠቅላላ የስራ ውጤት እድገት እንሚኖራቸው ተገለፁት ሌሎች አገሮች ደቡብ ሱዳን በ4.1 በመቶ፣ ቤኒን እና ሩዋንዳ በሁለት በመቶ፣ ታንዛኒያ እንደ ኢትዮጵያ በ1.9 በመቶ ሲሆን፡፡ እንዲሁም ኮትዲቯር በ1.8 በመቶ እድገት በ2020 እንደሚኖራት ተገምቷል፡፡ በተረፈ በርካታ አገራት ምንም በሚባል ደረጃ ኢኮኖሚያዊ እድገት መቀዛቀዝ ውስጥ ናቸው፡፡መንግስት የኢትዮጵያ ጠቅላላ የስራ ውጤት እድገት 6.1 በመቶ መሆኑን መናገሩ ይታወሳል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚደረጉ ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታወቀ!

የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚደረጉ ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታወቀ።የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ በአገሪቱ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎች ለቱሪስት ዝግ ሆነው መቆየታቸው ይታወሳል።በዚህም በአገሪቱ ዙሪያ የሚገኘው የቱሪስት መስህቦች ደረጃ በደረጃ ወደ ስራ እየተመለሱ ይገኛሉ።

ቱሪዝም ኢትዮጵያ በአማራ ክልል ላልይበላ ከተማ በቱሪዝም ዘርፍ ለተሰማሩ ባለድርሻ አካላት በጎብኚዎች ደህንነት አጠባበቅ፣ ለቱሪስት መረጃ አሰጣጥ እና በአገር አቀፍ የቱሪዝም መለያ /ብራንድ/ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።በጎንደር፣ በባህርዳር፣ በላልይበላ እና በደባርቅ አከባቢ ለተወጣጡ ከ600 በላይ ለሆኑ አስጎብኚዎች፣ የሆቴል ባለቤት ተወካዮች፣ ድጋፍ ሰጪዎች እና የደህንነት ጠባቂ ባለሙያዎች ነው ስልጠናው የተሰጠው።የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ግርማ እንዳሉት የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትም ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚደረግ ለኢዜአ ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የመገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት የእንባ ጠባቂና የግልግል ዳኝነት ፓናል አባላት የትውውቅ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል!

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት የእንባ ጠባቂና የግልግል ዳኝነት ፓናል አባላት የትውውቅ መድረክ በካፒታል ሆቴል በአሁኑ ሰዐት በመካሄድ ላይ ይገኛል።የፓናሉ አባላት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ከሕግ ባለሙያዎች፣ ከሲቪል ሶሳይቲ፣ ከምሁራን፣ ወዘተ ተወጣጥተው የተመረጡ መሆናቸውም በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳዋለች" የሚልና በህዳሴ ግድብ ዙሪያ አሉታዊ አስተያየቶችን መስጠታቸውን በመቃወም ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ልትጀምር ነው።

ስነ ስርአቱ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 21፣ 2013 ዓ.ም በግዮን ሆቴል 10 ሰዓት ላይ እንደሚጀመርም በዋነኝነት ይህንን ፊርማ የማሰባሰብ ስራ የሚመራው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት አስታውቋል።የፅህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኃይሉ አብርሃም ፊርማው በበይነ መረብ (ኦንላይን) የሚካሄድ ሲሆን ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳዋለች ለሚለው አፀፋዊ የተቃውሞ ምላሽ መሆኑንም ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ከዛሬ ጥቅምት 21፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ባሉትም አራት ቀናት ኢትዮጵያውያን የፕሬዚዳንቱን ንግግር ፊርማቸውን በማኖር እንዲቃወሙ ጥሪ የቀረበላቸው ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ለሚመለከታቸው አገራት ደግሞ ትኩረት እንዲሰጡትም ያለመ መሆኑንም አቶ ኃይሉ ያስረዳሉ።በነዚህ አራት ቀናትም ውስጥ እስከ 150 ሺህ ፊርማ የማሰባሰብ እቅድም ተይዟል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa