YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
YeneTube
የአውሮፓ ኅብረት የፌዴራልና የትግራይ ክልል መንግሥታትን ለማግባባት ጥረት መጀመሩ ተሰማ፡፡ የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነትና ደኅንነት ፖሊሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፕ ቦሬሌ የተመራ ልዑካን ቡድን ከሁለት ሳምንት በፊት ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ክልል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች፣ እንዲሁም በሁለቱም መንግሥታት ገዥ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር መወያየታቸውን የሪፖርተር ምንጮቼ ገልጸውልኛል ብሏል፡፡ @YeneTube…
⬆️
#CrossCheck

Via @EthiopiaCheck

ሪፖርተር ጋዜጣ "የአውሮፓ ኅብረት የፌዴራልና የትግራይ ክልል መንግሥታትን ለማግባባት ጥረት መጀመሩ ተሰማ" በሚል በፊት ገፁ ዛሬ ያስነበበው ዜና 'ስህተት' መሆኑን የአውሮፓ ህብረት እንዲሁም በዜናው ላይ የተጠቀሱት የህወሀት ባለስልጣን አቶ ጌታቸው ረዳ ለኢትዮጵያ ቼክ ማምሻውን አሳውቀዋል።

ሪፖርተር በዘገባው የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነትና ደኅንነት ፖሊሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፕ ቦሬል የተመራ ልዑካን ቡድን ከሁለት ሳምንት በፊት ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ክልል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በሁለቱም መንግሥታት ገዥ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር መወያየታቸውን ገልጾ ፅፏል፡፡

አክሎም "የኅብረቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ጋር በወቅቱ ተገናኝተው መምከራቸውን ሪፖርተር ከምንጮች ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የኅብረቱ ከፍተኛ ልዑካን ወደ ትግራይ ክልልም በማምራት ከክልሉ መንግሥት አመራሮች እንዲሁም ከዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል ጋር መወያየታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይኼው ቡድን ከሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች ጋርም በአካል ተገናኝቶ የመከረ ሲሆን፣ ይህንንም የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑ አቶ ጌታቸው ረዳ ለሪፖርተር ገልጸዋል" ብሏል።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር የሆኑት ዮሀን ቦርግስታም ለኢትዮጵያ ቼክ በሰጡት ማብራርያ "በጆሴፕ ቦሬል የተመራው ልኡክ ከሁለት ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ እና ጅግጅጋ ቆይታ አድርጓል። በጅግጅጋ የሰብአዊ ድጋፍ አሰጣጥን የጎበኙ ሲሆን በአዲስ አበባ ደግሞ ከጠ/ሚር አብይ ጋር በቀጠናው እና ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ባለው ግንኙነት ዙርያ ውይይት አርገዋል። ዜና ላይ ዛሬ እንደወጣው ግን ወደ ትግራይ አልተጓዙም፣ ደጋግሜ ላረጋግጥልህ የምፈልገው ጆሴፕ ቦሬልም ሆኑ ሌላ የልኡኩ አባል እንደተፃፈው ወደዛ አልሄዱም። ፍፁም ስህተት ነው" ብለዋል።

በዜናው ላይ የተጠቀሱት አቶ ጌታቸው ረዳ ደግሞ "የምናነጋግራቸው ብዙ አካላት አሉ፣ በዚህ ግዜ በግልፅ የምንነግራቸው ድርድር የሚባል ነገር እንደማንቀበል እና ሀገራዊ ውይይት (national dialogue) እንደሚያስፈልግ ነው። ጋዜጠኛው መረጃ በጠየቀኝ ወቅት ያስረዳሁት ይህን ነው፣ የአውሮፓ ህብረት ቡድን ትግራይ ለውይይት መጥቶ ነበር ተብሎ የተፃፈው ከየት እንደመጣ አላውቅም" ብለዋል።

በዶ/ር ደብረፅዮን የተፈረመ እና ከስድስት ቀን በፊት በህወሓት የፌስቡክ ገፅ ላይ የተቀመጠ ደብዳቤ ክልሉ የአውሮፓ ህብረት እያደረገ ያለውን ጥረት እና እንቅስቃሴ እንደሚያደንቅ ይገልፃል፣ ይህን ወደ ትግራይ ክልል በአውሮፓ ልኡክ ተደረገ የተባለውን ጉዞ ግን አልጠቀሰም።

@YeneTube @FikerAssefa