YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ባለፉት ሶስት የክረምት ወራት ብቻ ከ130 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በጎርፍ አደጋ ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው የመፈናቀል አደጋ እንደደረሰባቸው የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።ከሰኔ ወር መጀመሪያ እስከ ነሀሴ ወር አጋማሽ ባለው ወቅት በሁሉም የአገሪቷ አካባቢዎች ከ130 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በጎርፍ አደጋ ምክንያት መፈናቀላቸውን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አልማዝ ደምሴ ገልፀዋል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
ተማሪዎች ከሚደረስባቸው የስነ ልቦና ጉዳት እንዲላቀቁ ትምህርት ለመጀመር የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ምክረ ሃሳብ ቀረበ።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት ቤት በመዘጋቱ ቤታቸው የዋሉ ተማሪዎች ለተለያዩ ጉዳቶች እየተጋለጡ መሆናቸው ይታወቃል። ተማሪዎች ያለ እድሜ ጋብቻ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ጉልበት ብዝበዛና ይህንን ተከትሎ በሚመጣ የስነ ልቦና ችግር እየተጋለጡ መሆናቸውን ጥናቶች አሳይተዋል።እነዚህን ችግሮች ለማስወገድና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማድረግ የትምህርት ሚኒስቴር ኮሮናን በመከላከል ትምህርት መጀመር የሚቻልባቸውን ሁኔታዎች እያጠና ይገኛል።በተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶች ተማሪዎች የትምህርት መጀመርን በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን።

በሌላ በኩል ወላጆች የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት ልጆቻቸው ትምህርት ቤት ሲሄዱ ለኮሮና ቫይረስ ሊጋለጡ ይችላሉ የሚለው ከፍተኛ ስጋት እንዳለባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡እነዚህን ተቃራኒ ሃሳቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት ትምህርት ሚኒስቴር እንደ አካባቢዎቹ ወቅታዊ የኮሮና ስርጭት ሁኔታ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በደረጃ መክፈት የሚያስችሉ መንገዶችን እየገመገመ ይገኛል።ትምህርት ሚኒስቴር እያካሄደ ባለው ጥናት ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት በአንድ ክፍል ውስጥ ከ 20 እስከ 25 ተማሪዎችን ማስተማር፣ የንፅህና መጠበቂያ ለትምህርት ቤቶች ማቅረብ፣ ተጨማሪ ትምህርት ቤቶችን መገንባት የሚሉ አማራጮች ቀርበዋል።ጥናቱ ሲጠናቀቅ በሚቀርበው ተጨማሪ ምክረ ሃሳብ መሰረት አስፈላጊው ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ትምህርት ለመጀመር ጥረት ይደረጋል።

[MoE]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን የአንድ ዓመት ወጪ ለመሸፈን ቃል ገባ!

ለ2013 ዓ.ም የሚሆን ስጦታ በሚል በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን በሙሉ የአንድ ዓመት ወጪ እንደሚሸፍን የከተማ አስተዳደሩ ቃል ገብቷል፡፡ዛሬ እየተከበረ የሚገኘውን የምስጋና ቀን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዘውዲቱ ሆስፒታል የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን ጎብኝተዋል፡፡ምክትል ከንቲባዋ በጉብኝታቸው ወቅት ቃል እንደገቡት በከተማዋ በመንግስት ሆስፒታሎች የሚገኙ የኩላሊት እጥበት የሚያደርጉ ሁሉም ህሙማን የአንድ አመት የህክምና ወጪያቸው በከተማ አስተዳደሩ የሚሸፈን ይሆናል፡፡ ይህም በገንዘብ ሲሰላም ከ 12 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን የአንድ ዓመት ወጪ ለመሸፈን ቃል ገባ! ለ2013 ዓ.ም የሚሆን ስጦታ በሚል በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን በሙሉ የአንድ ዓመት ወጪ እንደሚሸፍን የከተማ አስተዳደሩ ቃል ገብቷል፡፡ዛሬ እየተከበረ የሚገኘውን የምስጋና ቀን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ…
በአገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን ወደ 312 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች በኮረና ቫይረስ መያዛቸውን እና አሁን ላይ የተወሰኑት አገግመው 56 የሚሆኑ ክትትል እያደረጉ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡ይህንንም ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በነበራቸው የምስጋና ቀን ጉብኝት ህይወታቸውን መስዋዕት አድርገው እያደረጉ ላለው ሁሉ ከልብ ምስጋና እናዳላቸው ገልጸዋል፡፡ ለበዓል መዋያ 2 በሬዎችን እና 5 በጎችንም በስጦታ አቅርበዋል፡፡በቀጣይ የጤና ባለሞያዎች የሚያነሷቸውን ችግሮች በከተማ አስተዳደሩ ውይይት ተደርጎበት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ምላሽ ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርገው ሾመዋል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ዶናልድ ትራምፕ ለኖቤል ሽልማት ታጩ!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና እስራኤል የሰላም ስምምነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ለኖቤል የሰላም ሽልማት ታጩ።ትራምፕ የታጩት ለስምምነቱ ስኬት ቁልፍ ሚናን ተጫውተዋል በሚል ባሞካሿቸው የኖርዌይ ምክር ቤት አባል ክሪስቲያን ታይብሪንግ ነው፡፡በሃገራቱ መካከል ሰላምን ለማውረድ ከየትኛውም እጩ በላይ ትራምፕ ሰርቷል ሲሉም ነው ታይብሪንግ ለፎክስ ኒውስ የተናገሩት፡፡በሽልማቱ ህግ መሰረት የምክር ቤት አባል የሆነ የትኛውም ሰው ለዓለም ሰላም መጠበቅ የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል ያለውን ሰው እጩ አድርጎ ለማቅረብ ይችላል፡፡“ታሪካዊ” በሚል የሚጠቀሰውን ስምምነት በማርሽ ቀያሪነት የጠቀሱት ታይብሪንግ ሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ሊከተሉት የሚችሉት እንደሆነም ለሽልማት ተቋሙ በጻፉት የእጩ መጠቆሚያ ደብዳቤ ገልጸዋል፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ለጃዋር መሐመድ የሳተላይት መሳሪያ በመግጠም የተከሰሱ ባለሙያ ዋስትና ተፈቀደላቸው!

በአቶ ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት ህገ ወጥ የሳተላይት መሳሪያ በመግጠም የተከሰሱት አቶ ሚሻ አደም ዋስትና ተፈቀደላቸው። ተከሳሹ የ20 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ዛሬ ውሳኔ የሰጠው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።የአቶ ሚሻን ክስ እየተመለከተ የሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት ለዛሬ ረቡዕ ጳጉሜ 4፤ 2012 ቀጠሮ የሰጠው የተከሳሹ ጠበቆች ባቀረቡት ዋስትና ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነበር።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ551 ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገላቸው!

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የ2013 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በፌዴራል፣ በክልልና በመከላከያ ወታደራዊ ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ 551 የፌዴራል ታራሚዎች በተለያዩ መስፈርቶች መነሻነት ይቅርታ ማድረጉን አሰታውቋል፡፡መጪውን የ2013 ዓ.ም አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከፌዴራል ማራሚያ ቤቶች ለ398፣ ከመከላከያ ወታደራዊ ማረሚያ ቤት ለ129፣ ከኦሮሚያ ክልል ለ18 እና ከአማራ ክልል ለ6 የፌዴራል ታራሚዎች የይቅርታ ቦርድ የቀረበውን ማስረጃ መርምሮ ይቅርታ እንዲደረግ ለኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ባቀረበው የውሳኔ ሀሳብ መሰረት የውሳኔው በመጽደቁ ታራሚዎቹ የይቅርታው ታጠቃሚ መሆናቸውን ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ባንኮች ከሚሰጡት አመታዊ ብድር 5% የሚሆነውን በተንቀሳቃሽ ንብረት ለሚሰጥ የብድር አይነት እንዲውል ብሄራዊ ባንክ በመመሪያ አዘዘ።

በከፍተኛ ለውጥ እያለፈ ያለው ብሄራዊ ባንክ ባለፈው ሁለት አመታት 47 መመሪያዎችን ማውጣቱን አስታወቀ።የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ከወጡት መመሪያዎች አብዛኞቹ አዳዲስ ናቸው።የተቀሩት ደግሞ የቀደሙትን ማሻሻያ ነው።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ወደ ዩንቨርስቲ መግቢያ ቀን እንደተቆረጠ የሚሰራጨው ዜና ሀሰት እንደሆነ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ!

በኮቪድ 19 ወረርሸኝ ምክንያት የገጽ ለገጽ ትምህርት መቋረጡና ለበለጠ ጥንቃቄ ሲባል ተማሪዎች በልዩ ዝግጅት ወደቤተሰቦቻቸው መሸኛታቸው ይታወሳል።ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል የሚያስችሉ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን ቀደም ተብሎ መገለፁ ይታወቃል።ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ዩኒቨርስቲዎች የሚከፈቱበት ቀን እንደተቆረጠ ሆኖ በተለያዩ አካላት የሚወጣው መረጃ የተሳሳተ እንደሆነና የተቋረጠው ትምህርት ሊቀጥል የሚችለው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ትምህርት ማስቀጠል የሚያስችል መረጃ ሲገኝ ብቻ እንደሆነ እና መረጃውም የሚሰጠው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል ብቻ መሆኑን እንድታውቁ ተብላቿል።

[MoSHE]
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ኒውስ ኔትዎርክ (ኦ.ኤን.ኤን.) ጋዜጠኞችና ሠራተኞች ዛሬ ለፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

እሁድ ከሰዓት የዓዲስ ዓመት የመዝናኛ ፕሮግራም በመሥራት ላይ ሳሉ በአከባቢው ከሚገኙ 26 ሰዎች ጋር ወደ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው እንደነበር ጣቢያው ዐሳውቋል፡፡በጋዜጠኛ ደሱ ዱላ መዝገብ ስር ዛሬ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡ 22 ሰዎች ከሸማቂው የኦነግ ሸኔ ኃይል ጋር ትሰራላችሁ በሚል ተጠርጥረው መከሰሳቸውንም ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለዶይቼ ቨሌ ተናግረዋል፡፡ዛሬ በዋለው ችሎት ላይ በአካል መቅረብ ያልቻለው አንደኛው ተጠርጣሪ ሙዚቀኛ ጋሮማ ሁንዴ በህመም ምክኒያት በ10 ሺህ ብር ዋስትና ሲለቀቅ፤ ቀሪዎቹ 21 ሰዎች ለነገ ጠዋት ሌላ ቀጠሮ መሰጠቱንም አቶ ቱሊ አክለው ተናግረዋል፡፡የኦ.ኤን.ኤን ዳይሬክተር አቶ ሶርሳ ደበላ ለዶይቼ ቨሌ እንደተናገሩት አስቀድመው ትናንት አራት ሰዎች መለቀቃቸውን ገልጸው የጋዜጠኞቹ ቡድን ለቀጣይ አዲስ ዓመት ክብረ በዓል የመዝናኛ ፕሮግራም በማሰናዳት ላይ ሳሉ ድንገት ወደ ፖሊስ ጣቢያው መወሰዳቸውን ከጋዜጠኛ ደሱ ዱላ መረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በገበታ ለአገር የእራት ፕሮግራም 3 የ VVIP መግቢያ ለመግዛት መወሰኑን አስታወቀ።በዚህም መሰረት በጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ ለሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ለእያንዳንዳቸው የ 10 ሚሊየን ብር ለመደገፍ መድን ሰጭው ወስኗል።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ወንበራና ቡለን ወረዳዎች የተከሰተውን የፀጥታ ችግር የማረጋጋት ስራ እየተሰራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር አምሳሉ ኢረና እንዳሉት ከሰሞኑም በመተከል ዞን ቡለንና ወንበራ ወረዳ በሚገኙ አንዳንድ ቀበሌዎች ላይ "የጥፋት ተልእኮ በተሰጣቸው ኃይሎች" የተከሰተው የፀጥታ ችግር የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች፣ የፌደራል ፖሊስና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በቦታው ተገኝቶ የህግ የበላይነትን የማስፈንና የማረጋጋት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡የፀጥታ ኃይሎች እየሰሩት ባለው ስራ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ምክትል ኮሚሽነሩ በወንበራ ወረዳ መልካን ቀበሌ በጥፋት ኃይሎች 26 ንጹሃን ዜጎች መታገታቸውን አስታውቀዋል፡፡

በተመሳሳይ በቡለን ወረዳ ኤፓር ቀበሌ ላይ የጥፋት ቡድኑ በንፁኃን ዜጎች ላይ ጥቃት ማድረሱን ያስታወቁት ምክትል ኮሚሽነሩ በፀጥታ ችግሩ የደረሰው የጉዳት መጠን ምን ያክል መሆኑን በአካባቢው የኔት ወርክ ችግር ያለ በመሆኑ ትክክለኛ አሁናዊ መረጃ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ እንደሌላቸው ጠቁመዋል፡፡የደረሰውን ጉዳት ትክክለኛ መረጃ በማጣራት ኮሚሽኑ በቀጣይ ለህብረተሰቡ የሚያሳውቅ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡የአካባቢውን ሰላምና የህዝቡን ደህንነት ለማስከበር የጸጥታ አካሉ ከሚያደርገው ጥረት ጎን ህብረተሰቡም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር አምሳሉ ኢረና ጥሪ አቅርበዋል፡፡

[የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት]
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ ራሷን የቻለች የፌደሬሽኑ ክልል እንድትሆን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ጥሪ አድርጓል። የክልልነት መብትን በሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እና የከተማው ነዋሪዎች በሚሳተፉበት ሕዝበ ውሳኔ ለማረጋገጥ እንዲቻል መንግሥት ላይ ግፊት ለማድረግ ጥሪ አድርጓል። የከተማዋ ነዋሪ ፓርቲው ትናንት በጀመረው የፊርማ ማሰባሰብ እንቅስቃሴ በነቂስ እንዲሳተፍም ፓርቲው አሳስቧል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
animation.gif
338 KB
የቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ ከተናገሩት👇👇

<<የቤቶች ግንባታ የተጀመረው ከ15 ዓመታት በፊት ሲሆን፣ እስካሁን ተገንብተው ከተላለፉት፣ እየተገነቡ ካሉትና ዕጣ ሊወጣባቸው ከታቀዱት ከ300 ሺሕ በላይ ቤቶች ውስጥ በከተማው ካቢኔ የተወሰነው ለ20 ሺሕ አርሶ አደሮች ነው።እንዲህ ዓይነት ውሳኔዎች አሁን የተጀመሩ አይደሉም።ከዚህ በፊትም (በቀድሞዎቹ አስተዳደሮች) ለመምህራንና ለጤና ባለሙያዎች፣ ለፓርላማ አባላት፣ እንዲሁም ለአገር መከላከያ ሠራዊት የጦር ጉዳተኞች በተመሳሳይ ውሳኔ ሲሰጥ ነበር።የአርሶ አደር ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲ አጀንዳ የሚሆንበት ምንም ምክንያት የለም።

አርሶ አደር በመሆናቸው በደሉን ተሽክመው ይኑሩ የሚል ጭፍን ፍርድ ከሌለ በስተቀር። አርሶ አደሩ እኮ ለብዙ ዓመታት ከራሱ መሬት፣ ከራሱ የእርሻ ማሳ ‹‹በልማት›› ምክንያት (በሪል ስቴት፣ በኢንዱስትሪ ፓርክ፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ) ምክንያት ከመሬቱ ተነቅሏል። እኛ ያደረግነው ምንድን ነው? በአጠቃላይ ከ6 ክፍላተ ከተሞች ከኑሮአቸው ስለተፈናቀሉ እንዲቋቋሙ ስለተፈለገ በካቢኔ አስወሰንን።ይህም ማለት ከአጠቃላይ የቤቶች ግንባታ ስድስት በመቶ ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች እንዲሰጥ ነው የወሰንነው።

 ከ20 ሺሕ ውስጥ አርሶ አደር ያልሆኑ ሰዎች አሉ፣ በጥናታችን ለይተናል ካሉ ደግሞ ይህ ሥራቸው ያስመሠግናቸዋል።ነገር ግን ይህንን ጥናት ያሉትን ነገር ይፋ ለማድረግ ለምን የአመራር ሽግሽግ ወቅት ጠበቁ? ለምን አሁን? እኔ ወደ ሌላ ኃላፊነት እየሄድኩ ባለበት ወቅትና የቀረበውን ትችት መልስ ለመስጠት በማልችልበት ወቅት ለምን ለማቅረብ መረጡ የሚለውን ጥያቄ አንስቼ መልሱን ለራሳቸው መተው እፈልጋለሁ።>>

ሙሉውን ለማንበብ👇👇👇
https://telegra.ph/-09-09-1117
ሸገር ፓርክ ነገ ይመረቃል።

በጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስተባባሪነት እየተገነባ ያለው የሸገር ፓርክ ነገ ይመረቃል ተብሏል።ፓርኩን ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት እንደሚመረቅ ከጠቅላይ ሚንስቴር ጽህፈት ቤት ሰምተናል።የፓርኩ ምረቅ ስነ ስርዓነገ ጠዋት ጀምሮ እስከ ምሽት የሚቆይ ፕሮግራም መዘጋጀቱንም ኢትዮ ኤፍ ኤም ከጽህፈት ቤቱ ያገኘው የዝግጅት ሰነድ ይጠቁማል።የሸገር ፓርክ ግንባታ ከአንድ ኣመት በፊት "ገበታ ለሸገር" በሚል በተሰናዳ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ በተሰበሰበ ገንዘብ መገንባቱ ይታወሳል።የፓርኩ ዋና ዋና ግንባታ በመገባደዱ ምክንያት ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በወልቃይት ጠገዴ በተለይም በአማራ እና ትግራይ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት እንደነበር የአካባቢው የፀጥታ አካላት ለቢቢሲ ተናገሩ።

ቢቢሲ የሁለቱንም ክልል የፀጥታ ኃላፊዎች ያነጋገረ ሲሆን አንዳቸው በሌላኛቸው ክልል ወገን ግጭት መቀስቀሱን ገልፀዋል።ቢቢሲ በአማራ ክልል ሥር የሚገኘው የጠገዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ሙሉጌታ ስለ ጉዳዩ ጠይቆ፣ እርሳቸው በሚያስተዳድሩት ወረዳ ምንም ግጭት አለመኖሩን ገልጸው በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የጸገዴ ወረዳ ግን ከምርጫው ጋር ተያይዙ ግጭት መኖሩን እንደሰሙ ለቢቢሲ ገልጸዋል።ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የትግራይ ክልል ፀጥታ ከፍተኛ ኃላፊም በምዕራብ ትግራይ ጸገዴ አካባቢ በትግራይ መሬት ገብቶ የተኮሰ አካል እንደሌለ በመግለጽ "በአማራ ክልል ውስጥ ግን ተኩስ እንደነበረ ሰምተናል" ሲሉ ተናግረዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በወልቃይት ጠገዴ በተለይም በአማራ እና ትግራይ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት እንደነበር የአካባቢው የፀጥታ አካላት ለቢቢሲ ተናገሩ። ቢቢሲ የሁለቱንም ክልል የፀጥታ ኃላፊዎች ያነጋገረ ሲሆን አንዳቸው በሌላኛቸው ክልል ወገን ግጭት መቀስቀሱን ገልፀዋል።ቢቢሲ በአማራ ክልል ሥር የሚገኘው የጠገዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ሙሉጌታ ስለ ጉዳዩ ጠይቆ፣ እርሳቸው በሚያስተዳድሩት ወረዳ…
የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይል ፣ የትግራይ ክልል በሚያስተዳድረው «ፀገዴ» ወረዳ ጨጓርጉዶና ማይወዲሳህላይ በተባሉ ቀበሌዎች ጥቃት ለማድረስ ተንቀሳቅሷል የሚለውን ስሞታ በአማራ ክልል የጠገዴ ወረዳ አስተባበለ።

በአማራ ክልል የ «ጠገዴ» ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ሙሉጌታ ለዶይቼ ቬለ በስልክ እንደተናገሩት «የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይል ትግራይ በሚያስተዳድረው «ፀገዴ» ወረዳ ጨጓርጉዶና ማይወዲሳህላይ በተባሉ ቀበሌዎች ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀስ በትግራይ የፀጥታ ኃይል ተመትቶ ተመለሰ» እየተባለ ከወደትግራይ የሚነዛው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው» ብለዋል።

ችግሩ አልመርጥም ምረጥ በሚል እሰጣ ገባ፣ እዛው የራሳቸው የፀጥታ ኃይል በነዋሪው ኅብረተሰብ ላይ የፈጠረው ችግር እንደሆነ ነው አቶ ጌታቸው ያስረዱት።«የወሰደው ምንም ዓይነት እርምጃ የለም፤ ምንም ዓይነት ጥቃት የለም ከእውነት የራቀ ነው ይሄ። የራሳቸው ኃይል የፈጠረው ችግር እንጂ ወደእነርሱ የሄደ ኃይል የለም። እዛው ላይ ምርጫውን መሠረት አድርጎ ምርጫ አንመርጥም የሚል አካል አለ፤ እዚያው እርስ በርሳቸው የተፈጠረ ችግር ነው። በፍጹም ስህተት ነው። ከእውነት የራቀ ነው።»ስለጉዳዩ ከትግራይ ክልል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 916 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ የ17 ሰዎች ህይወት አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 15,561 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 916 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

319 ሰዎች ሲያገግሙ 17 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

እስካሁን በአጠቃላይ 61,700 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 23,054 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ966 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሸገር ፓርክ የምረቃ ስነስርዓት

Photo: Daniel Getachew[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa