የሻምበል አበበ ቢቂላ የሮም ኦሎምፒክ ድል ዛሬ ስልሳ አመት ሞላው!
ሁሌም አዲስ አመትን ስናከብር ከምንጊዜውም ጀግናችን የአፍሪካ ኩራት ሻምበል አበበ ቢቂላ የሮም ኦሊምፒክ ድል ጋር ነው።ይሄ ታላቅ ድል ዘንድሮ 60 ዓመት ሞላው።
ወቅቱ በኢትዮጵያ ቀን አቆጣጠር የአዲስ አመት ዋዜማ ምሽት ጳጉሜ 5/1952 ዓ,ም በዛሬዋ ቀን ነበር አዲሱን ዓመት 1953ን በታላቅ ደስታ ኢትዮጵያዊያን መስከረምን የተቀበሉበት።ይህ ታላቅ ድል ለአፍሪካ ከተመዘገበ 60ዓመት ሞላው።
★ክብር ለጀግኖቻችን
★መልካም አዲስ አመት
Via EOC
@YeneTube @FikerAssefa

ለፀጥታ ሲባል በአዲስ አበባ ማንኛውም ግለሰብ ሪችት መተኮስ እንደማይችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት የሚዲያ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት መግለጫ÷ ሪችትን ምክንያት በማድረግ የሽብር ጥቃት ለማድረስ እየተዘጋጁ ያሉ ግለሰቦች መኖራቸውን ፖሊስ በጥናት ደርሶበታል ብለዋል።ስለሆነም ወንጀልን ለመከላከል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ማንኛውም ግለሰብ ሪችት መተኮስ አይችልም ብለዋል። ይህንን ተላልፎ ሪችት የሚተኩስ ማንኛውም ሰው በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚውል ተናግረዋል።
በተያያዘ ዜናም በአዲስ አበባ በአስሩም ክፍለ ከተማ በጥናት በተደረገ ፍተሻ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።በፍተሻው አንድ ቦምብ እና አራት ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው የተናገሩት።ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም የተጠረጠሩ 180 ግለሰቦች ተይዘው ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑንም አመላክተዋል።ዋና ኢንስፔክትር ማርቆስ አያይዘውም ህብረተሰቡ የራሱን ሰላም በመጠበቅ፣ ሰላምን ሊያውኩ የሚችሉ ወንጀለኞችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት እንዲተባበርም ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ እና ተመድ 7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር የዘላቂ ልማት ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራረሙ!
ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር የዘላቂ ልማት ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራረሙ።ማዕቀፉ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን ከአውሮፓውያን 2020 እስከ 2025 የሚተገበር መሆኑ ተነግሯል፡፡የስምምነት ሰነዱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴና በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ተጠሪ ዶክተር ካትሪን ሶዚ ተፈራርመዋል።አቶ አህመድ በስምምነቱ ወቅት ማዕቀፉ በአገሪቱ ለሚተገበረው የ10 ዓመት ዕቅድ በአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር ለተካተቱና አገሪቱ ቅድሚያ ለሰጠቻቸው የልማት ጉዳዮችን ይውላል ሲሉ ነው የገለጹት።
[FBC]

በትግራይ ምርጫ ለሊቱ ድምፅ ሲቆጠር አድሯል፡፡ በሁሉም የምርጫ ጣብያዎች ውጤት ይፋ እየተደረገ ነው፡፡ህወሓት ከፍተኛ ድምፅ ማግኘቱ በአንዳንድ ጣብያዎች የተለጠፈ ውጤት ያመለክታል፡፡
Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa
Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በሬድዮ በቀጥታ ለማስተላለፍ ለሚፈልጉ ድርጅቶች ሊሸጥ ነው!
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ በ2013 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በሬድዮ የቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ ለሚፈልጉ የሚዲያ ተቋማት ሊሸጥ መሆኑን አስታውቋል።የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ለመምራት የተቋቋመ ህጋዊ ተቋም ነው፡በመሆኑም ካምፓኒው በቀጣይ የሚካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በቀጥታ የሬድዮ ስርጭት ለማስተላለፍ የሚያስችለውን መብት፣ ህጋዊ ፍቃድ ላላቸው የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት ለመሸጥ በሚቀጥለው ሳምንት ጨረታ እንደሚያወጣ ተነግሯል፡፡ሊግ ካምፓኒው ቀደም ሲል የሊግ ውድድሩን የቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት እና የውድድር ስያሜ ሽያጭ ጨረታ አውጥቶ አሸናፊውን ለመለየት በሂደት ላይ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡የሚያገኘው ገቢ የካምፓኒውን እና የተወዳደዳሪ ክለቦችን ፋይናንሻል አቅም ያሳድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በ7 ተከሳሾች ላይ አቃቤ ህግ ክስ መሰረተ።
ክሱ በሁለት የተከፈለ ሲሆን፥ ከአቶ እስክንድር ነጋ እስከ 3ኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ በሽብር ወንጀል ነው ክስ የተመሰረተው።ቀሪዎቹ ማለትም ከ4ኛ እስከ 7ኛ ተከሳሾች ላይ ደግሞ የእርስ በእርስ ግጭት በመፍጠር ወንጀል ነው ክስ የተመሰረተው።ክሱ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው የተመሰረተው።ተከሳሾቹ በሰኔ 23 እና 24 2012 ዓ.ም የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ፣ ማደራጀትና ማስተባበር ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ ሲከናወንባቸው መቆየቱ የሚታወስ ነው።በአሁኑ ወቅት ችሎቱ ጉዳያቸውን እየተመለከተ እንደሆነ ፋና ዘግቧል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ 508 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሱን አስታወቀ።
የውሳኔ ሀሳቡ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደድር ቀርቦ ተቀባይነት ያገኙ በመሆኑ ከነገ መስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚለቀቁ በክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፤ የሕግ አገልግት ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ንጋቱ ዓለሙ ዛሬ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።አቶ ንጋቱ እንደተናገሩት ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በማረሚያ ቤት የስነ ምግባር ለውጥ ያሳዩ ናቸው።
የሚፈቱት በፈጸሙት ወንጀል የተጸጸቱ ይኸንንም ማረሚያ ቤቱ ያረጋገጠላቸው ታራሚዎች ሲሆኑ ከአንድ ዓመት ከአራት ወር እስከ አስራ ሰባት ዓመት በእስር ቤት የቆዩ ናቸው።በዚሁ መሰረት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ከሚገኙት ሶስት ዞኖች ከካማሺ ማረሚያ ቤት 69 ታራሚ፣ ከመተከል ዞን 312 እና ከአሶሳ ዞን ደግሞ 127 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን ነጋሳ ደሳለኝ ከአሶሳ ዘግቧል። ከሚፈቱት መካከል ሰባቱ ሴቶች ናቸው።
[DW]

በሊባኖስ የቤይሩት ወደብ አዲስ የእሳት ቃጠሎ ተነሳ።
ቃጠሎው ከአንድ ወር ገደማ በፊት በተከሰተው ከፍተኛ ፍንዳታ ከድንጋዜ እና ሐዘን ያልተላቀቁ የዋና ከተማዋ ነዋሪዎችን ሥጋት ላይ መጣሉን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።በከተማዋ ዳርቻ በሚገኘው ወደብ ወፍራም ጥቁር ጢስ ወደ ሰማይ ሲትጎለጎል የታየ ሲሆን የአገሪቱ ጦር ነዳጅ እና ጎማ የተከማቸባቸው መጋዘኖች ማውደሙን አስታውቋል። ቃጠሎው በምን ምክንያት እንደተነሳ እስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። የሊባኖስ ጦር በትዊተር ባሰፈረው አጭር መግለጫ "እሳቱን ለማጥፋት ጥረት ተጀምሯል።ወታደራዊ ሔሊኮፕተሮችም በዚህ ጥረት ውስጥ ይሳተፋሉ" ብሏል።ባለፈው ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. አሞኒየም ናይትሬት የተባለ የማዳበሪያ እና የፈንጂ ማምረቻ ግብዓት ምክንያት በተፈጠረው ፍንዳታ ከ190 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ቆስለው ነበር። ፍንዳታው ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች አሞኒየም ናይትሬት የተባለው ኬሚካል ክምችቶቻቸውን እንዲፈትሹ አስገድዷቸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የቁም እንስሳት ገበያዎች በበሬ መሸጫ ዋጋ ላይ ከአምስት ሺህ እስከ 10 ሺህ ብር የሚደርስ ጭማሪ መታየቱን ሸማቾች ገለጹ።
በመዲናይቱ ገበያዎች አንድ በሬ ከ20 ሺህ እስከ 55 ሺህ ብር እየተሸጠ ነው።የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ ተዘዋውሮ በተመለከታቸው አቃቂ፣ ካራ እና ፈረንሳይ ጨፌ በተሰኙ የቁም ከብት መሸጫ ስፍራዎች አነስተኛ በሬ ከ20 እስከ 25ሺህ ብር ሲሸጥ ውሏል። በእነዚህ ገበያዎች መካከለኛ በሬ ከ35 ሺህ እስከ 45ሺህ ብር ባለ ዋጋ የሚገኝ ሲሆን ከፍተኛ ለሚባለው ነጋዴዎች እስከ 55ሺህ ብር ዋጋ ሲጠሩ ተስተውሏል። በአንፃራዊነት የዋጋ ቅናሽ በሚታይበት ባለ በአቃቂ በሰቃ፤ ገበያ በሬ ከ22 ሺህ እስከ 35 ሺህ ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል።
[Ethiopia Insider]

የዓለም ጤና ድርጅት ለድሆች የኮሮና ክትባት የሚሆን 700 ሚሊዮን ዶላር አሰባሰብኩ አለ!
የአለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው በድሃ ሀገራት ለሚገኙ ዜጎች የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለማድረግ የሚውልና ከተፈለገው ከግማሽ በታች የሚሆን 700 ሚሊዮን ዶላር ከዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡
ዘኮቫክስ አድቫንስድ ማርኬት ኮሚትመንት የተባለው ድርጅት የ 2 ቢሊዮን ዶላር ክትባት ለመግዛት የመጀመሪያ እቅድ አስቀምጧል፡፡
እስካሁን መሰብሰብ የተቻለው 700 ሚሊዮን ዶላር ብቻ በመሆኑ የተፈለገውን እርዳታ ለማግኘት ገና ብዙ ስራ መስራት እንደሚጠበቅ የዓለም ጤና የድርጅቱ አፍሪካ ዳይሬክተር ማትስዲሾ ሞይቲ ገልጸዋል፡፡
ኮቫክስ በፈረንጆቹ 2021፣ 2 ቢሊዮን ውጤታማነቱ የተረጋገጠ ክትባቶችን የማቅረብ አላማ እንዳለው ገልጿል፡፡ ደቡብ አፍሪካን፤ ጋቦንን፣ ናሚቢያንና ኢኳቶሪያል ጊኒን ጨምሮ በትንሹ 8 የአፍሪካ ሀገራት በራሳቸው ወጭ መድሃኒቱን ለመግዛት ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
[Al ain]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 878 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 16,665 የላብራቶሪ ምርመራ 878 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡
ባለፋት 24 ሰዓታት የ8 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 974 አድርሶታል።
በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 586 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው የገገሙ ሰዎችን ቁጥር 23,640 አድርሶታል፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 62,578 ደርሷል፡፡

በትግራይ ምርጫ አጠቃላይ ውጤት ከደቂቃዎች በኋላ ይፋ ይደረጋል፡፡ እስካሁን የተረጋገጠ፡ ህወሓት 152 ወንበሮች አሸንፏል፡፡ በተመጣጣኝ የምርጫ ስርዓት በሚያዙት ቀሪ 38 ወንበሮች ምናልባት ተቃዋሚዎች የተወሰነ ዕድል አላቸው፡፡
Via Million HaileSelassie
@YeneTube @FikerAssefa
Via Million HaileSelassie
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ምርጫ ውጤት:
👉ህወሓት - 98.2 %
👉ባይቶና - 0.8%
👉ውናት - 0.71%
👉ሳወት - 0.27%
👉ዓሲምባ - 0.01%
ከአጠቃላይ ድምፁ አግኝተዋል፡፡
Via Million HaileSelassie
@YeneTube @FikerAssefa
👉ህወሓት - 98.2 %
👉ባይቶና - 0.8%
👉ውናት - 0.71%
👉ሳወት - 0.27%
👉ዓሲምባ - 0.01%
ከአጠቃላይ ድምፁ አግኝተዋል፡፡
Via Million HaileSelassie
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 789 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ የ 12 ሰዎች ህይወት አለፈ!
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 12,164 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 789 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
384 ሰዎች ሲያገግሙ 12 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
እስካሁን በአጠቃላይ 63 ሺ 367 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 24 ሺ 024 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ986 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

የዛሬ 19 አመት ነበር 9/11 በመባል የሚታወቀው ጥቃት የደረሰው።
አሜሪካም ሆነ አለም እስከዛሬ ካስተናገደቻቸው የሽብር ጥቃቶች የከፋው እንደሆነ የሚጠቀስለት በኒውዮርክ የ'World Trade Center' መንታ ህንፃዎች በአልቄይዳ በተጠለፉ የመንገደኞች አውሮፕላኖች ነበር የወደሙት። በዚህም በአውሮፕላኑ የነበሩ ሰዎች ሁሉም ሲሞቱ በአጠቃላይ ወደ 3000 የሚጠጉ ንጹኃን ዜጎች ሞተዋል፣ የዚህን እጥፍ የሚያክሉት ደግሞ ተጎድተው ነበር። የዚህ ጥቃት ሰለባዎች በየአመቱ ኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ በዓሏን በምታከብርበት ቀን ታስበው ይውላሉ።በዛሬው እለትም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከባለቤታቸው ሜላኒያ ጋር ለጥቃቱ ሰለባዎች በተገነባው መታሰቢያ ተገኝተው ስነ ስርዓቱን ታድመዋል።
ከላይ የምታዩት ይህ የአለምን ታሪክ በብዙ መልኩ እንደቀየረ የሚነገርለት ጥቃት እንደተፈፀመ የተወሰዱና ታሪካዊ የሚባሉ ፎቶዎችን ነው፣ በመጀመሪያው ፎቶ ኖርዘርን ታወር የሚባለው በመጀመሪያ ላይ የተመታው ህንፃን ያሳያል፣ ሁለተኛው ፎቶ ደግሞ በወቅቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጆርጅ ቡሽ ስለጥቃቱ ሲረዱ፣ ቀጥሎ የሚታየው የህንፃዎቹ ፍርስራሽ(from ground zero) ሲሆን ፣የመጨረሻው ደግሞ ከጥቃቱ የተረፈች ሴት በደቀቁ የኮንክሪት ብናኞች ሰውነቷ ተሸፍኖ ያሳያል።
የፎቶዎቹ ባለመብት አጃንስ ፍራንስ ፕረስ ነው

የናይጄሪያ ግዛት በህፃናት ደፋሪዎች ላይ የማኮላሸት ህግን ልታፀድቅ ነው!
የናይጄሪያዋ ካዱና ግዛት ከአስራ አራት አመት በታች ያሉ ህፃናትን የሚደፍሩ ግለሰቦች በህክምና እንዲኮላሹ የሚያዝ ረቂቅ ህግን አሳልፋለች።ረቂቁ ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ የግዛቲቷ አስተዳዳሪ ናስር አህመድ ኤል ሩፋይ መፈረም ይኖርባቸዋል።አስተዳዳሪው ከዚህ ቀደም ደፋሪዎች ተግባራቸውን እንደገና እንዳይፈፅሙ ብልታቸው ሊኮላሽ ይገባል ሲሉም ነበር።የናይጀሪያ ፌደራል መንግሥት ደፋሪዎችን ከአስራ አራት አመት እስከ እድሜ ልክ እስራት ቢቀጣም ግዛቶች ግን የራሳቸውን ህግ ማውጣት ይችላሉ።የተደፈሩ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በማህበረሰቡ ካለው ተጠቂዎችን ጥፋተኛ ከማድረግ እሳቤ አንፃር ብዙዎች ደፍረው ወደ ህግ ቦታ አይሄዱም።ደፍረው ሪፖርት ያደረጉትም ቢሆን ክስ ተመሰርቶ የሚፈረድባቸውም ጥቂቶች ናቸው።
በሰኔ ወር ላይ በርካታ የናይጄሪያ ግዛት አስተዳዳሪዎች እየጨመረ የመጣውን የሴቶች መደፈርና ጥቃት አስመልክቶ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተላልፈው ነበር።በናይጄሪያ ከጎርጎሳውያኑ 2015 ጀምሮ የተፈረደባቸው 40 ደፋሪዎች ብቻ እንደሆኑ የተገኘው መረጃ ያሳያል።አገሪቷም ህጓን አሻሽላለች።የመድፈር ክስን አስቸጋሪ የሚያደርገው አቃቤ ህግ ማስረጃ ማምጣት ስለሚኖርበት አድካሚና ቴክኒካል ጉዳዪ የተወሳሰበ እንደሚያደርገው ይነገራል።የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የተጣለው የእንቅስቃሴ መገደብም የሚደፈሩ ሴቶችን ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጎታል።በሃምሌ ወር የ22 አመት እድሜ ያላት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ተደፍራ መገደሏ ከፍተኛ ቁጣን ፈጥሯል።
ይህንንም ተከትሎ ናይጄሪያውያን ንዴታቸውን ለመግለፅ ጎዳና ላይ ወጥተዋል፤ 'ዊ አር ታየርድ' (ደክሞናል) በሚልም በትዊተር ላይ ዘመቻ ተጀምሮም ነበር።በርካቶችም የሞት ቅጣትን ጨምሮ ጠበቅ ያለ ህግ እንዲወጣም ጠይቀዋል።"ደፋሪዎችን የመኮላሸት ቅጣት ህግ በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ያለውን መደፈርን ይቀንሰዋል ብለን እናምናለን" በማለት የካዱና ምክርቤት አባል ሼሁ ዩኑሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።"የካዱና አስተዳዳሪ ከፈረሙና ህጉም ከፀደቀ በኋላ ቀጣዩ ደፋሪ የሚሰለብ ይሆናል" ብለዋል።የስርዓተ-ፆታ መብት ተሟጋችና የመደፈር ጥቃት የደረሰባቸው ዶሮቲ ንጄዝማንዜም ህጉ እንዳስደሰታቸው ገልፀው በሌሎች ግዛቶችም ተግባራዊ ሊሆን ይገባል ብለዋል።"በዚያን ወቅት የደፈሩኝ ቢኮላሹ ኖሮ ሌሎች ደፋሪዎች አይፈጠሩም ነበር፤ ብዙዎችም ከዚህ ጥቃት ይተርፉ ነበር" ብለዋል።በህክምና የመስለብ ቅጣት በአንዳንድ አገራት ተግባራዊ ቢሆንም አወዛጋቢ ነው።
[BBC]