YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለብሉምበርግ፣ ኒውዮርክ ታይምስ እና ቪኦኤ እንግሊዘኛ የሚፅፈው ፍሪላንስ ጋዜጠኛ ሳይመን ማርክስ እና ሌሎች አስር ገደማ ሰዎች ወደ መቐለ ለመሄድ ቦሌ አየር ማረፊያ ቢገኙም በፀጥታ አካላት እንዳይጓዙ እንደታገዱ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።ሳይመን ወደ መቐለ ሊጓዝ የነበረው ምርጫውን ለመዘገብ እንደነበር መረጃው ያመለክታል።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በአማራ ክልል ለሰላም መስፈን አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጠ! በአማራ ክልል ለሰላም መስፈን አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና የመስጠት ስነስርአት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።በስነስርአቱ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተገኝተዋል።መድረኩ…
የአማራ ክልልን ሰላም በማስከበር የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የፖሊስ አካላት የማዕረግ ሽልማት ከተለያዩ የፌዴራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች በተገኙ ተከናውኗል።

ማዕረግ የተሰጣቸው!

አምስት የምክትል ኮሚሽነርነት
አስራ ሶስት የረዳት ኮሚሽነርነት
ሁለት የኮማንደርነት
ሶስት የምክትል ኮማንደርነት
አንድ የዋና ኢንስፔክተርነት
ሁለት የረዳት ኢንስፔክተርነት ማዕረግ ሽልማት ተሰጥቷል።

[አማራ ፓሊስ ኮሚሽን]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የቤት መኪኖች በወንበር ልክ መጫን እንደሚችሉ አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ በወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍና የመጫን አቅም መመሪያ ላይ በተደረገው ማሻሻያ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሚኒባስ፣ የአንበሳ አውቶብስ፣ ሸገር እና ሀይገር ባሶች በወንበራቸው ልክ እንዲጭኑ መወሰኑ ይታወቃል፡፡የቤት መኪኖችን እንዲሁም የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ተሸርካሪዎችን በሚመለከት ግን በማሻሻያው ላይ የተጠቀሰ ነገር ባመኖሩ ኢትዮ ኤፍ ኤም በዚሁ ጉዳይ ላይ ቢሮውን ጠይቋል፡፡

የቢሮው የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ እንዳሉት የቤት መኪኖች እንዲሁም የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪዎችም በወንበር ልክ እንዲጭኑ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ በሚል የቤት መኪኖች ከሹፌሩ ውጪ መጫን ከሚችሉት የሰው ቁጥር በግማሽ ቀንሰው ይጭኑ እንደነበር ይታወሳል፡፡እንዲሁም ባለ ሶስት እና ባለ አራት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች እስከ ሹፌሩ 3 ሰው መጫን እንደሚችሉም ተነግሯል።ቀላል ባቡር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መመሪያ በ25 በመቶ የመጫን አቅም ብቻ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው አሁን ላይ ወደ 75 በመቶ ከፍ እንዲል መደረጉንም አስታውቋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ለብሉምበርግ፣ ኒውዮርክ ታይምስ እና ቪኦኤ እንግሊዘኛ የሚፅፈው ፍሪላንስ ጋዜጠኛ ሳይመን ማርክስ እና ሌሎች አስር ገደማ ሰዎች ወደ መቐለ ለመሄድ ቦሌ አየር ማረፊያ ቢገኙም በፀጥታ አካላት እንዳይጓዙ እንደታገዱ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።ሳይመን ወደ መቐለ ሊጓዝ የነበረው ምርጫውን ለመዘገብ እንደነበር መረጃው ያመለክታል። Via Elias Meseret @YeneTube @FikerAssefa
#Update

ከምርጫው ጋር ለተያያዘ ሥራ በአውሮፕላን ሊጓዙ የነበሩት ጋዜጠኞች ቁጥራቸው ከ10 በላይ እንደሆነም የተነገረ ሲሆን፤ በበረራ መርሃ ግብራቸው መሰረት ወደ አውሮፕላን ከገቡ በኋላ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ መደረጉ ተገልጿል።

ከጋዜጠኞቹ መካከል አንዱ የሆነው ለብሉምበርግና ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የሚሰራው ሳይመን ማርክስ "የተወሰንን ሰዎችን መታወቂያ ካርድ ከተመለከቱ በኋላ ተሳፍረንበት ከነበረው አውሮፕላን ተገደን እንድንወርድ ተደርገናል" በማለት ለቢቢሲ ተናግሯል።

ዛሬ ረፋድ ላይ ወደ መቀለ ሊጓዝ በነበረው አውሮፕላን ውስጥ ሰላሳ የሚደርሱ መንገደኞች የነበሩ ሲሆን የአውሮፕላን ማረፊያው የደኅንነት ሠራተኞች የተሳፋሪዎቹን መታወቂያ ከተመለከቱ በኋላ ተጓዦቹ እንዲወርዱ ማደረጋቸውን አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ተሳፋሪ ገልጸዋል።ቢቢሲ ያናገራቸው አንድ ተጓዥ እንዳሉት ደግሞ የጸጥታ ሠራተኞቹ የመንገደኞቹ ሞባይል እና ላፕቶፕ ሲቀበሉ መመልከታቸውን ተናግረው በረራውም ሳይሰረዝ እንዳልቀረ ገልጸዋል።ወደ መቀለ እንዳይጓዙ ከተደረጉ ተሳፋሪዎች መካከል የዓለም አቀፉ የቀውስ ጉዳዮች አጥኚ ተቋም የኢትዮጵያ ተመራማሪ የሆነው ዊሊያም ዳቪሰንም እንዳለበት ቢቢሲ አረጋግጧል።

ሮይተርስ ወደ መቀሌ ለማምራት በዝግጅት ላይ የነበረው አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ መንገደኞች ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው ከሆነ አራት ጋዜጠኞችን ጨምሮ 12 የሚሆኑ ሰዎች ወደ መቀሌ በረራ ለማድረግ ከተዘጋጀው አውሮፕላን ውስጥ እንዲወርዱ ተደርገዋል።የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ተከትሎ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃንና ጋዜጠኞች በትግራይ የሚካሄደውን ምርጫ እንዳንዘግብ ጫና እየደረሰብን ነው ያሉ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዳይሬክተር ጌታቸው ደንቁ (ዶ/ር) ለድምጸ ወያኔ እንዲህ አይነት ነገር እንደሌለ ባለፈው ቅዳሜ ተናግረው ነበር።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ወንጀል የሚዘክር ቋሚ መታሰቢያ እንዲያቆም አብን ጠየቀ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።ንቅናቄው በመግለጫው እንዳስታወቀው የአገሪቱ የዲሞክራሲ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ መምጣቱንም አስታውቋል።በአጠቃላይ አብን በጥናቴ አረጋግጫቸዋለሁ መንግስትም በቀጣይ የማስተካከያ እርምጃዎችን ሊወስድባቸው ይገባል ያላቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አስቀምጧል።

በኦሮሚያ ክልል የተደረገው "የዘር ማጥፋት" ተገቢውን ትኩረት ያለማግኘቱና ችግሩን በአጭር ጊዜም ይሁን በዘለቄታ ለመፍታት የሚታየው ዳተኝነት ፓርቲውን ክፉኛ እንደሚያሳስበውም ገልጿል። በመሆኑም

ሀ) የተፈፀመው ወንጀል "የዘር ማጥፋት" መሆኑ ታምኖበት በስሙ እንዲጠራና ለተፈፀመው ወንጀልም ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠየቅ፤

ለ) መንግሥት የተፈፀመውን "የዘር ፍጅት" የሚያጣራና የሚመረምር ልዩ የምርመራ ኮሚሽንና አቃቤ ሕግ ጽ/ቤት እንዲያቋቁምና ወንጀለኞች የሚዳኙበት ልዩ ችሎት እንዲሰይም፤

ሐ) መንግሥት በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ወንጀል የሚዘክር ቋሚ መታሰቢያ እንዲያቆም፤

መ) ችግሩን በዘለቄታ ለመፍታት በክልሉ በሚኖሩ የተለያዩ ማህበረሰቦችና ህዝቦች መካከል የእርቅና የመግባባት ስራዎች እንዲጀመሩ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልልም በክልሉ ለሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ማህበረሰቦችና ህዝቦች ሰብአዊና ህገ መንግሥታዊ መብቶቻቸው የሚከበሩበት ዋስትና እንዲሰጥ ንቅናቄው ጠይቋል።

Via Ethio FM

ሙሉ መግለጫው 👇👇👇

https://telegra.ph/-09-07-523
ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋርን ጨምሮ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ እስከ መስከረም 8 2013 ዓ.ም ክስ እንዲመሰርት ብይን ሰጠ!

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቶ ጃዋር መሃመድና በቀለ ገርባን ጨምሮ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ እስከ መስከረም 8 2013 ዓ.ም ክስ እንዲመሰርት ብይን ሰጠ።ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ ከጳጉሜ 2 እስከ ጳጉሜ 5 2012 ዓ.ም የተሰሙ የምስክር ቃል ተገልብጦ ወስዶ እስከ መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም ክስ አንዲመሰርት ነው ብይን የሰጠው።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ሌሎች ከ11ኛ እስከ 14ኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ደግሞ በ5 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሰርትባቸውም ትእዛዝ ሰጥቷል።ፍርድ ቤቱ በዛሬ ውሎው ተጠርጣሪዎቹ ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ትእዛዝ ሳይሰጥ፤ ተጠርጣሪዎቹ በማረፊያ ቤት አንዲቆዩ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 93 መሰረት ትእዛዝ ሰጥቷል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ማስክ ሳያደርግ ታክሲ ውስጥ የተገኘ ሰው 500 ብር እንደሚቀጣ ተገለፀ!

ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ በወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት መመሪያ ላይ ተሳፋሪዎች ማስክ ሳያደርጉ ትራንሰፖርት መጠቀም እንደማይችሉ ቢከለክልም ባላደረጉት ላይ ያስቀመጠው የቅጣት መጠን አለመኖሩ ይታወሳል፡፡በመመሪያው ላይ ዛሬ በተደረገው ማሻሻያም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ወይም ማስክ በማያደርጉ ተሳፋሪዎች ላይ የ500 ብር ቅጣት መጣሉን የቢሮው የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪዎችን የጫነ አሽከርካሪና ረዳት ላይም እያንዳንዳቸው 1 ሺ ብር እንዲቀጡ መወሰኑን አቶ አረጋዊ ተናግረዋል፡፡ከዚህ ቀደም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የተጣለው የምሽት 2 ሰዓት ገደብ ከተነሳ የቆየ ቢሆንም አሁንም ተሳፋሪዎች እንዲሁም አሽርካሪዎች ላይ ብዥታ ተፈጥሯል፡፡ይህንንም ተከትሎ ትራንስፖርት ሰጪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው የሰዓት ገደብ ከተነሳ መቆየቱን እና ይህ ብዥታ ሊኖር እንደማይገባ አክለው ተናግረዋል፣ ዘገባው የኢትዮ ኤፍ ኤም ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል ምርጫ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ህገ-ወጥ እና የክልሉ ህዝብም ሆነ መንግስት የማይቀበለው መሆኑን የትግራይ ክልል አስታወቀ፡፡

የትግራይ ክልል የመንግስት ኮምኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊያ ካሳ ለአሀዱ እንዳስታወቁት የክልሉ መንግስት እያካሄደ ያለው ምርጫ የህዝብ ውሳኔ የታከለበት እና ህገ-መንግስታዊ ስርዓትን የተከተለ ነው ብለዋል፡፡የምርጫው ባለቤት የትግራይ ህዝብ ነው ያሉት ወይዘሮ ሊያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ያስተላለፈው ውሳኔ የትግራይን ህዝብ ያስቆጣ እና ኢ-ህገ-መንግስታዊ ነው ብለውታል፡፡የፌዴሬሽን ምክር ቤት አገሪቱን የሚበታትን እንጅ ለህዝብ የሚጠቅም ውሳኔ ወስኗል ብለው እንደማያምኑም ነው ወይዘሮ ሊያ ያስታወቁት፡፡

[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
የማስጠንቀቂያ መልክቶች ሰሚ ባለማግኘታቸው የሰው ህይወት እየጠፋና ንብረት እየወደመ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች ሊከሰቱባቸው የሚችሉ ቦታዎችን በመለየት ግጭቶች ተከስተው በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ቀድመን በተደጋጋሚ ብናሳውቅም በመንግስት በኩል ትኩረት እየተሰጠው አይደለም ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ገልጿል፡፡

ኮሚሽኑ ከመንግስትም ሆነ ከህብረተሰቡ ሳይወግን የሚሰራ እንደመሆኑ መረጃዎችን አጥንቶ በሚያሳውቅበት ወቅት በመንግስት በኩል ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ በለጠ ይልማ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ከሶስት ሳምንታት በፊት በወላይታ ሶዶና በዞኑ ባሉ አንዳንድ ከተሞች ተከስተው የነበሩ ግጭቶችን ለመገምገም ኮሚሽኑ በቦታው በመገኘት ከመንግስት አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ሙሉ መረጃዎችን አሰባስቦ ጨርሷል፡፡ሙሉ ሪፖርቱን በሚቀጥሉት 3 ቀናት ውስጥ እንደሚያሳውቁ አቶ በለጠ አስታውቀዋል፡፡

[አሐዱ ሬዲዮ 94.3]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የጋዜጠኞች የጉዞ ክልከላን በተመለከተ “መረጃ አልነበረኝም” አለ

ከነገ በስቲያ በትግራይ የሚካሄደውን ምርጫን ለመዘገብ፤ ዛሬ ወደ መቀሌ ሊጓዙ የነበሩ ጋዜጠኞች ከአውሮፕላን ጣቢያ እንዲመለሱ መደረጉን በተመለከተ ቅድሚያ መረጃ እንዳልነበረው እና ጉዳዩን እንደሚያጣራ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጸ። የጉዞ እገዳ የተደረገባቸው ጋዜጠኞች መታወቂያቸው፣ የተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው፣ ላፕቶፖቻቸው፣ ካሜራዎች እና ሌሎች የስራ ዕቃዎቻቸው መወሰዳቸውን በጸጥታ ኃይሎች እንደተወሰዱባቸው ተናግረዋል።

ጋዜጠኞቹ እና ሌሎች መንገደኞች ወደ መቀሌ ሊጓዙ የነበረው ዛሬ ከቀኑ አምስት ሰዓት ላይ ነበር። ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ መንገደኛ እንደተናገሩት የአየር ማረፊያ የጸጥታ ሰዎች ከወትሮው በተለየ ለውጭ ሀገር ዜጎች ጥያቄ ሲያቀርቡ ነበር። በኢትዮጵያ የኒው ዮርክ ታይምስ ዘጋቢ የሆነው ሳይመን ማርክስ በተለይ በርካታ ጥያቄዎች ሲቀርቡለት እንደነበር ማየታቸውን ተናግረዋል።

Via Ethiopia insider
@YeneTube @FikerAssefa
በድርድርና ሽምግልና የሚለቀቅ ተጠርጣሪ አይኖርም- ጠ/ዐቃቤ ህግ

በድርድርና ሽምግልና የሚለቀቅ ተጠርጣሪ አይኖርም ሲል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ፍቃዱ ጸጋ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ በመግለጫቸው ወንጀልን በሽምግልና የምንፈታበት ህግም ስልጣንም የለንም ነው ያሉት።በአደባባይ ሰው የገደሉና ውድመት እንዲፈጠር ያደረጉ ተጠርጣሪዎች ሳንመረምር አናስርም የሚል የለም ማስረጃውን መዝኖ ለህግ የማቅረብ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።

በመግለጫቸው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን በመፈጸምና ግድያውን ተከትሎ በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ተብሎ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ክስ እንደሚመሰረት አስታውቀዋል።

በሰጡት መግለጫ ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ቀጥታ ተሳትፎ የነበራቸውንና አብራው በነበረችው ግለሰብ ፣ በእነ አቶ ጃዋር መሀመድ መዝገብና በእነ አቶ እስክንድር ነጋ መዝገብ ላይ እስከ ፊታችን ሀሙስ ድረስ ክስ እንደሚመሰረት ገልፀዋል።በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ያሉት በአብዛኞቹ ላይ ምርመራው ተጠናቋል ተብሏል።አቶ ፍቃዱ ጸጋ በመግለጫው ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያለውን አቅም ተጠቅሞ ጥፋተኞችን ለፍትህ የማቅረብ ሂደት በሻለ ሁኔታ ተፈጻሚ እየሆነ ነው ብለዋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮ ቴሌኮም 5 በመቶ ድርሻ ለበርካታ ዜጎች በአክሲዮን እንደሚሸጥ ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ ለግል ኩባንያዎች የአገልግሎት ፍቃድ የመስጠቱ ሂደት፣ ከመስከረም እስከ የካቲት ይከናወናል፡፡ ለግል ኩባንያዎች 40 በመቶ ድርሻ የሚሸጥላቸው ሲሆን፣ መንግሥት እና ሕዝቡ 60 በመቶ ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡ ይህ የተገለጸው የኩባንያው ከፊል ሽያጭ ሂደት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ባሉበት ዛሬ በተገመገመበት ስብሰባ ላይ ነው፡፡

[Reporter & Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 976 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 19,449 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 976 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

309 ሰዎች ሲያገግሙ 15 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

እስካሁን በአጠቃላይ 59,648 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 21,789 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ933 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ትምህርት ሚኒስቴር የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የሚያስችሉ ሁኔታዎችን እያጤንኩ ነው አለ፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቲዎስ የ2013 አ.ም.የትምህርት ሂደትን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ከትምህርት ቤቶች አከፋፈት ጋር ተያይዞ ባሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱን ተከትሎ ከ42 ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይማሩ የነበሩ ከ26 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል፡፡የ2013 ዓመት ትምህርትን ለመጀመር የሚስችሉ ሁኔታዎችን ለመቃኘት የጥናት ቡደን ተቋቁሞ ጥናት እያደረገ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡በጥናቱ መሰረት ትምህርት ቤቶች በአንድ ክፍል ውስጥ ከ20 እስከ 25 ተማሪዎችን ለማስተማር የሚያስችል አቅም ስለመኖርና አለመኖራቸው ልየታ እየተካሄድ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የተማሪዎችን ርቀት ለማስጠበቅ በአንድ ወንበር አንድ ተማሪ እንዲቀመጥ የሚደረግ ሲሆን በፈረቃ ትምህርት መስጠት፣ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች መገንባት፣ የማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ለማስተማሪያነት መጠቀም እንደ አማራጭ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ተገልጧል፡፡ይህንን ታሳቢ በማድረግ አንዳንድ ክልሎች አስቀድመው ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን የገነቡ ቢሆንም ሁሉም ክልሎች በየትምህርት ቤቱ ተጨማሪ ክፍሎችን እንዲገነቡ እየተደረገ ነው።በትምህርት ቤቶች ውስጥ ውሃ እንዲኖር ማድረግ፣ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘርና ማስክ የማቅረብ ስራዎችም እንደሚሰሩ ተነስቷል፡፡የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ያለበት ሁኔታ እየተገመገመ ደረጃ በደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት የሚያስችሉ ሁኔታዎች እየተጤኑ ነው ያሉት ሚስትር ዴኤታው ሚሊዮን ማቲዎስ ለስኬቱ ወላጆችና ባለድርሻ አካላት ከመንግስት ጎን እንዲቆሙ ጠይቀዋል፡፡

[MoE]
@YeneTube @FikerAssefa
#ትንቢተ_ፍጻሜ
#3ኛ_ዕትም_በገበያ_ላይ

እያንዳንዷን ቀን በጥንቃቄ እና በብልሀት መኖርን መዘንጋት የለብንም፡፡ እኛ የመጨረሻዎቹ የሰው ልጅ ፍጥረቶች መሆናችንን ተገንዝበን ይህችን ዓለም ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንደምንሰናበታት ባወቅን ጊዜ በእያንዳንዷ ቀናችን ጠንቃቃና ዝግጁ መሆን እንዳለብን መካሪ አያሻንም፡፡ ለሞት ከሚያበቁ በሽታዎች በርን ዘግቶ ማምለጥ፣ ከድንገተኛ መቅሰፍት እና ከወቅታዊ ወረርሽኝ ራስን በመሰወር የመጨረሻዋን ምድራዊ ሕይወት ኑሮ ጨርሶ ወደ ዘላለማዊ ቤታችን ጠቅልሎ ለመሄድ መጠንቀቅ የብልሆች ስራ ነው፡፡ ይህን እያሰባችሁ መኖር እንዳለባችሁ ለማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡
#ሲልቪያ_ብራውን
#END_of_DAYS መጽሐፍ
#ትንቢተ_ፍጻሜ በሚል በአማርኛ ተተርጉሞ በገበያ ላይ ውሏል፡፡

*
በክርስትና፣ በእስልምና፣ በጆሆቫ፣ በራስ ተፈሪያኖች… በሁሉም ኃይማኖቶች ስለዓለም ፍጻሜ የተነበየ መጽሐፍ፡፡
#ኢትዮጵያ_እና_የንጉሶች_ንጉስ_የሆኑት_አጼ_ኃይለስላሴም_በዚህ_መጽሐፍ_ውስጥ_ተጠቅሰዋል፡፡ ከትንቢተ ፍጻሜው ጋር ምን ያገናኛቸው ይሆን?

#እውን እንደሚባለው ዓለም ፍጻሜዋ አሁን ይሆን? #ወይስ_ስንት_ዘመን_ትቆይ_ይሆን?

ተርጓሚ ራሴላስ ጋሻነህ
የመጽሐፈ ሔኖክ ኢትዮጵያዊና የስኬት ፍልስፍና መጽሐፍት ተርጓሚ
👉 ይቀላቀሉን http://tttttt.me/teklutilahun
#መከረኞች
#እምዩ
ዘመን የማይሽራቸው መጽሐፍት በገበያ ላይ!!

#መከረኞች በአንድ ፊቱ የህብረተሰብ ታሪክ፣ በሌላ ፊቱ ፍልስፍና፣ በሶስተኛ መልኩ የጥበብ ስራ፣ ከዚህም ውጪ በብዙ አንጻር ሊተረጎም የሚችል ‹‹ዘላለማዊ›› ተብለው ከሚጠሩ ስነ-ፅሁፎች የሚመደብ፡፡

#እምዩ #የእናት_ፍቅርና_መስዋዕትነት ከባድ ፈተና ውስጥ የሚገባበት… እጅግ መሳጭ ታሪክ የያዘ ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር መጽሐፍ!!!

#የመጽሐፍ_ቅርስ_ካስፈለገዎት
#መከረኞችና_እምዩ_መጽሐፍት_አሉልዎት፡፡

በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኟቸዋል፡፡

ይቀላቀሉን 👉 http://tttttt.me/teklutilahun
Forwarded from YeneTube
N A T C O M P U T E R S ®
ናት ኮ ም ፒ ው ተ ር ስ ®

HP Envy X-360 (convertable touch screen)
Intel®core i7 8TH GENERATION
🟢Storage : 1Tb
🟨ram : 16GB DDR4
🟥 status: New
battery: 5hrs
🔘Inch : 15.6" FULL HD Slim CONVERTABLE TOUCH SCREEN
💵 price: 37500 ብር

አድራሻ : - ቦሌ መድሐኒያለም Morningstar Mall 1ኛ ፎቅ ከAngla Burger ፊት ለ ፊት
🖥 🖥 🖥 🖥 🖥 🖥 🖥 🖥 🖥
N AT C O M P U T E R S ®
ናት ኮ ም ፒ ው ተ ር ስ ®

ይደውሉ
☎️+251911522626 /+251953120011


📌join @natcomputers1
📩 @natyendex ለአጭር መልክት
YeneTube
ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋርን ጨምሮ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ እስከ መስከረም 8 2013 ዓ.ም ክስ እንዲመሰርት ብይን ሰጠ! የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቶ ጃዋር መሃመድና በቀለ ገርባን ጨምሮ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ እስከ መስከረም 8 2013 ዓ.ም ክስ እንዲመሰርት ብይን ሰጠ።ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሃመድና…
በትናንትናው ችሎት ላይ አቶ ጃዋር ምስጋና ማቅረብ እንደሚፈልጉና ለመንግሥትም መልዕክት እንዳላቸው የተናገሩ ሲሆን፣ ለዳኞችና ለፖሊስ ምስጋና አቅርበዋል።

የመናገር መብታቸው እንደተጠበቀላቸውና ፖሊሶችም ጥሩ እንክብካቤ እያደረጉላቸው እንደሆነ ጨምረው ተናግረዋል።"ይኹን እንጂ ይህ እንክብካቤ ለታዋቂ ሰዎች ብቻ ሳይሆን፤ ለሁሉም ሰዎች መሆን እንዳለበት በማንሳት በሌሎች ስፍራዎች ደንብ ልብስ የለበሱት ፖሊሶች "ሰዎችን እየገደሉ ነው" በማለት ተናግረዋል።አክለውም " እኛ የፖለቲካ ታሳሪዎች ነን፤ ገድለን፣ ሰርቀን ወይንም ዘርፈን አይደለም እዚህ የተገኘነው፤ የታሰርነው ለኦሮሞ ሕዝብ ስለታገልን ነው" ያሉት አቶ ጃዋር፣ የፍትህ አካላትም፣ ፍትህ ከፖለቲካ ሥልጣንና ከፖለቲካ ድርጅት በላይ እንዲሆን እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል አቶ በቀለ ገርባ "በእስካሁኑ ቆይታ ለፍርድ ቤቱ፣ ለአቃቢያነ ሕግ እና ለፖሊሶች ክብር አለን" ብለዋል።"የፖለቲካ ሰዎች ተመርጠው የዋስ መብት የማያሰጥ አንቀጽ እየተፈለገባቸው እየተከሰሱ ነው" ያሉት አቶ በቀለ መንግሥት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር መወያየት እንዳለበት ተናግረዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በክፍል ውስጥ የተማሪዎችን ቁጥር በመመጠንና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ትምህርት ለማስጀመር ጥናት ተደርጓል - አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ የትምህርት ሚኒስተር ዴኤታ

ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሊያጋልጥ በማይችልና ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የመማር ማስተማር ሂደቱን በአዲሱ ዓመት ለማስጀመር ጥናት መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ እንዳለው በአንድ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎችን ቁጥር በመመጠንና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ትምህርት ማስጀመር በሚቻልበት መንገድ ላይ ጥናት ተደርጓል።የትምህርት ሚኒስተር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን አመልክተዋል።

ኮሮናቫይረስ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ በሳደረው ጫና ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጭ እንዲሆኑ መደረጉንም አስታውሰዋል።
አቶ ሚሊዮን እንዳሉት ትምህርት መቋረጡ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት አስተዋፅኦ ቢኖረውም በተማሪዎች በተለይም ከህጻናት እድገት አንጻር ከፍተኛ ጫና አሳድሯል።በተለይ ህጻናት ትምህርት ዝግ ሆኖ ቤት በመዋላቸው ለአስገድዶ መደፈርና ያለዕድሜ ጋብቻ መዳረጋቸውን ሚኒስቴር ዴኤታው ገልጸዋል።በኢትዮጵያ ባሉ ከ42 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ከ700 ሺህ በላይ መምህራንና ከ26 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ይገኛሉ።

“ወቅቱ ኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ያለበት በመሆኑ ትምህርት ቤቶች መከፈታቸው ህብረተሰቡን እያነጋገረ ነው” ያሉት አቶ ሚሊዮን፣ ወረርሽኙ የሚቆምበት ጊዜ ባለመታወቁ ትምህርት እንደሚጀመርና ይህም የጤና ጥበቃ የሚያስቀምጠውን መስፈርት ተግባራዊ በማድረግ እንደሚከናወን ገልጸዋል።ባለፈው የመማር ማስተማር ሂደት በአማካይ ከ60 እስከ 80 ተማሪዎች በአንድ ክፍል ውስጥ ይማሩ የነበረበት ሁኔታ እንደነበር አቶ ሚሊዮን አስታውሰዋል።

በቀጣይ ትምህርት ሲከፈት በቅድመ መደበኛ 14 በመቶ የሚሆኑትን ትምህርት ቤቶች ከ20 እስከ 25 ተማሪዎችን ብቻ በአንድ ክፍል እንዲያስተምሩና አንድ ተማሪ በአንድ ዴስክ ብቻ እንዲቀመጥ ለማድረግ መታቀዱን አስረድተዋል።አቶ ሚሊዮን እንዳሉት ቀሪዎቹ 80 በመቶ ተማሪዎች በፈረቃ እንዲማሩና 6 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤት በመገንባትና አማራጭ ማህበራዊ ተቋማትን በመጠቀም ለማስተማር ታቅዷል።

በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 24 በመቶ ወይም ከ20 እስከ 25 ተማሪዎች በአንድ ከፍል ውስጥ እንዲማሩ፣ 56 በመቶ በፈረቃ እንዲሁም 20 በመቶ ተጨማሪ ክፍል በመገንባት እንዲማሩ ተወስኗል።በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 19 በመቶ ተማሪዎች ወይም ከ20 እስከ 25 የሚሆኑት በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲማሩ እንዲሁም 50 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በፈረቃ የሚማሩ ይሆናል።

ሌሎች 31 በመቶ ተጨማሪ ክፍሎችን በመገንባትና አማራጭ ማህበራዊ ተቋማትን በመጠቀም ለማስተማር መታቀዱንም አመልክተዋል።በሽታን በመከላከል የትምህርት ተቋማትን ስራ ለማስጀመር ተቋማቱን ማስፋት እንደሚገባም አቶ ሚሊዮን ተናግረዋል።
ኦሮሚያ ክልል ሃብት በማሰባሰብ 30 ሺህ አዳዲስ ክፍሎችን መገንባቱን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፣ “አማራ ክልልም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያለውን የክፍል እጥረት ችግር ለመቅረፍ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው” ብለዋል።

ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲማሩ የቀደመው የመማር ማስተማር ስልት በአዲስ መልክ እንደሚሆን ጠቁመው፣ ይህም የቡድን ስራን ጨምሮ የተማሪዎችን አካላዊ ንክኪን ሊያስቀር በሚችል መልኩ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።አቶ ሚሊዮን እንዳሉት የትምህርት ቤቶች አከፋፈት ጥናቱን መሰረት ያደረገ ይሆናል።ትምህርት ቤቶች በተመሳሳይ ወቀት አንድ ላይ ሊከፈቱ እንደማይችሉና ደረጃ በደረጃ የመክፈት ሂደት እንደሚኖር ገልጸው፣ አጀማመሩ ከክልል ክልልና ከዞን ዞን ሊለያይ እንደሚችል አመልክተዋል።

ይህንን ተከትሎ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ጭማሪ እየጠየቁ መሆኑን ገልጸው፣ ይህን በሚያደርጉ ተቋማት ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶችን እስከመዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ አመልክተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በጠገዴ ወረዳ ሰው አግቶ ገንዘብ በተቀበለ ግለሠብ ላይ የሦሮቃ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ።

ግንቦት 19/2012 ዓ/ም ተጠርጣሪ ሙቀት አለማየሁ የማይ አጋም ቀበሌ ነዋሪ የሆነውን በየነ ጥላሁን በሥራ ላይ እያለ 6 ሽህ ብር መክፈል አለብህ በማለት ለአራት ቀናት አግቶት ቆይቷል። የታገተው ግለሠብ ቤተሠቦችን ግንቦት 22/2012 ዓ/ም 6ሽህ ብር ከፍለው ከታገተበት አስለቅቀውታል። ተጠርጣሪው ገንዘቡን እንደተቀበለ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 አካባቢ ነዋሪነቱን አድርጓል። ፖሊስ ግለሠቡን በመከታተሉና ከማህበረሰቡ በደረሰ ጥቆማ በጎንደር ከተማ ነሀሴ 12/2012 ዓ/ም ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውላል።

የሶ/ን/ወረዳ ፖሊስ ተጠርጣሪውን ነሀሴ 25/2012 ዓ/ም ወንጀሉን ወደ ፈፀመበት ሶሮቃ ንዑስ ወረዳ በመውሰድ ምርመራውን ጀምሯል።ተከሳሹም ክዶ ተከራክሯል የሶ/ን/ወረዳ ዓ/ ህግ የተላለፈውን የኢፌድሪ ወንጀል ህግ አንቀፅ 586/1/ እና 590 ንዑስ ቁጥር "ሐ 2" በመጥቀስ በመተላለፍ የህግ ማስረጃወችን አሠምቷል።

ክሱን የተመለከተው የሶ/ን/ወረዳ/ፍ/ቤት ተከሳሹን ጥፋተኛ በማለት እሡንም ሆነ ሌሎችን ያስተምራል በማለት ናሀሴ 27/2012 ዓ/ ም በወለው የወንጀል ችሎት በ8 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ዓ/ህግ ተከሳሹ በጦር መሳሪያ ይዞ ወንጀሉን የፈፀመ በመሆኑ ቅጣቱን አንሷል ሲል ይግባኝ ጠይቋል ። መረጃውን ያደረሰን የሶሮቃ ንዑሥ ወረዳ ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤትን ጠቅሶ የጠገዴ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa