የአፍሪካ ህብረት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ስለሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድርና ፣ትናንትና ስለተደረገው ውይይት መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫውም ድርድሩ በ2 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ የተደረሰበት ሪፖርት እንደሚደረግ ይገልፃል። ከዚህ በተጨማሪ የፀጥታው ምክር ቤት ጉዳዩ ወደ አፍሪካ ኅብረት መመለሱን እንዲያውቀው በመግለጫው ተካቷል።
ሙሉ የእንግሊዝኛ መግለጫውን ከላይ አያይዘነዋል!
@YeneTube @FikerAssefa

ለጉምሩክ ኮሚሽን ሠራተኞች ብር 200,000 ጉቦ በመስጠት ንግድ ለማጭበርበር የሞከረ ባለሀብት በሠራተኞቹ አጋላጭነት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተነገረ።
በአስመጪ ያዴሳ ደሬሳ ትሬዲንግ ጀኔራል ስም በዲክላራሲዮን ቁጥር 8-147/20 በቀን 11/01/20 የተመዘገበ አገር አቋራጭ ትራንዚት ዕቃ ለዕቃው ዋስትና ብር 4,370,000 በማሲያዝ በመተሀር ቡርቤ አድርጎ ወደ ደቡብ ሱዳን እንዲጓጓዝ በ31/01/2020 የትራንዚት ፈቃድ ቢሰጠውም ከአገር ይወጣሉ ተብለው በትራዚት ላይ የነበሩ በ2 ተሽከርካሪዎች የተጫነ ዕቃ ሳይወጣ ቀርቷል ተብሏል፡፡አስመጪው በህገወጥ መንገድ ዕቃው ሳይወጣ እንደወጣ በማስመሰል ማረጋገጫ እንዲፃፍለት ሙከራ አድርጓል ።
መረጃው ለኮሚሽኑ አመራር የደረሰ በመሆኑ ክትትል ሲደረግ ቆይቶ ትናንት በቀን 20/10/2012 ዓ.ም የዕቃው ባለቤት ያሲያዘዉ ዋስትና ብር 4 ሚሊዮን 370 ሺህ ብር እንዲመለስለት እና ዕቃው ከአገር ሳይወጣ እንደወጣ በማድረግ ማረጋገጫ ለማግኘት ሙከራ ሲያርግ ብርቱ ክትትል ሲያደረጉ በነበሩ የኮሚሽኑ ኢንተሊጀንስ ባለሙያዎች ግለሰቡ ጉቦ ለመስጠት ከያዘው ብር 200 ሺ ጋር የጉምሩክ ኮሚሽን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሙስና ወንጀል ምርመራ ዲቪዢን ጋር በመተባበር ግለሰቡንና ግብራአባር የሆነውን አቶ አብዱልቃዲር ዘይኑ ሃሽም ቦሌ አለም ሲኒማ አካባቢ በቁጥጥር ስር አውሎ ጉዳዩ በምርመራ ሂደት ላይ ይገኛል።የኢንተሊጀንስ ሙያ የሚጠይቀውን ስነ ምግባር ተላብሰው ሙስናን በመጠየፍ ህገወጥነትን ለታገሉ የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ና ዋናው መ/ቤት የኢንተለጀንስ ባለሙያዎች፣ አመራሮች እና ለተባባሪ አካላት የጉምሩክ ኮሚሽን ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
ምንጭ፡-ገቢዎች ሚኒስቴር

የተማሪዎች ቀጣይ ሂደት የሚወሰነው ትምህርት ሚኒስቴር በሚያስተላልፈው መመሪያ መሰረት መሆኑ ተገለጸ!
በኮቪድ 19 ምከንያት በተቋረጠው ትምህርት ዙሪያ የተማሪዎች ቀጣይ እጣ ፋንታ አገር አቀፉ ኮማንድ ፖስት በሚያስተላልፈውና ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት የሚወሰን መሆኑ ተገለጸ።የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሯ ወይዘሮ ሀረጓ ማሞ እንደተናገሩት፤ በቤት ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት በሁሉም የአገሪቱ ክፍል በሚፈለገው ደረጃ ተደራሽ ነው ተብሎ ባይታመንም ብዙዎችን ከጭንቀት ለማላቀቅና ከትምህርት እርቀናል የሚል ስሜት እንዳይሰማቸው ለማድረግ አግዟል።
ትምህርቱና የቀጣይ ክፍል ዝውውር የሚወሰነው በኮሮና ወረርሽኝ መቆምና በመንግስት ውሳኔዎች መሰረት መሆኑን ተናግረዋል።የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን የትምህርት ስርጭት በተለይ ክልሎች ላይ ሰፊ መሰናክል እንደሚያጋጥም የጠቆሙት ወይዘሮ ሀረጓ፤ በመብራትና በስርጭት ጥራት የተፈለገውን ያህል ትምህርቱን ማዳረስ አለመቻሉን ገልጸዋል።አሁን እየተሰጠ ያለው ትምህርት በምንም መልኩ ከመደበኛ ትምህርቱ ጋር የሚገናኝ አይደለም ያሉት ወይዘሮ ሀረጓ መደበኛውን ትምህርትም አይተካም ብለዋል።
እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ፤ ትምህርቱ ሁሉንም ተማሪ የሚያቅፍበትና በእኩል ደረጃ ግንዛቤው የሚያዝበት ሁኔታ አለ የሚያስብል ስላልሆነ ከውጤት ጋር አያይዞ ለማስኬድ ከባድ ነው። የጥራት ጉዳይንም አደጋ ውስጥ ሊከተው ይችላል ብለዋል።ቴሌቪዥንና ሬዲዮ የማያገኙ ተማሪዎችም ቀደም ሲል የተማሩትን ትምህርት ከደብተራቸው እና እጃቸው ላይ ያለውን መጽሐፍ በፕሮግራም እንዲያነቡ በማድረግ ቤተሰብ ሰፊውን ድርሻ ይዞ እየሰራ መሆኑ አስረድተዋል።
ምንጭ፡ ኢፕድ

የOBN ሆርን ኦፍ አፍሪካ ቻናል ተመርቆ የተከፈተ ሲሆን የህፃናት ቻናልም በቅርቡ እንደሚጀምር ታውቋል።
ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አህመድ የOBN Horn of Africa ቻናል እና የኦቢቫን ዘመናዊ HD ተንቀሳቃሽ ማሰራጫን መርቀው ከፈቱ፡፡OBN በአሁኑ ወቅት በ8 የአገር ውስጥ ቋንቋዎች ስርጭት እያካሄደ ሲሆን፣ በቀጣይ በተጨማሪ ቋንቋዎች አገልግሎት ለመስጠት እቅድ እንዳለው ተገልጿል፡፡የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) የሕፃናት ቻናልን ለመክፈት ዝግጅት መጠናቀቁን ደግሞ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጸዋል።"ጋሜ" የሚል ስም የተሰጠው ኦቢኤን የሕፃናት ቻናል ዛሬ በይፋ ከተከፈተው የኦቢኤን ሆርን ኦፍ አፍሪካ ቻናል በመቀጠል 3ኛው የኦቢኤን ቻናል እንደሚሆን ተነግሯል።በተያያዘ ዜና የወሊሶ፣ አምቦ፣ እና ባሌ ሮቤ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ዛሬ ተመርቀዋል፡፡
ምንጭ: ETV

ቋሚ ኮሚቴው ገንዘብ ሚኒስቴር የምርጫ ቦርድን በጀት አስተካክሎ እንዲያቀርብ አዘዘ።
በረቂቅ በጀቱ ላይ ገንዘብ ሚኒስቴር ፓርላማው ከላከለት የምርጫ ቦርድ የበጀት ረቂቅ የቀነሰ የገንዘብ መጠን ማቅረቡ በገቢ በጀት እና ፋይናንስ አባላት አስተችቶታል።እንደሚታወቀው የዲሞክራታይዜሽን ተቋማት ማለትም ምርጫ ቦርድ፣ እንባ ጠባቂ፣ ፍርድ ቤቶች፣ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና ዋና ኦዲተር በጀታቸው በፓርላማው ታይቶ በቀጥታ በበጀት ዝግጅት እንዲካተት ለገንዘብ ሚኒስተር የሚቀርብ ነው።ሆኖም ገንዘብ ሚኒስቴር የምርጫ ቦርድን በጀት ቀንሶ በረቂቁ ማቅረቡ ታውቋል። የህም በቋሚ ከሚቴው ያስተቸው ሲሆን አስተካክሎ እንዲያቀርብም ታዟል።
Via Capital

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 119 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፣ የአራት ሰዎች ህይወትም አልፏል።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3895 የላብራቶሪ ምርመራ 119 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5689 ደርሷል።ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 87 (52 ከጤና ተቋም እና 35 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን 4 ናሙናዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 98 ደርሷል፡፡
ህይወታቸው ያለፈ 4 ሰዎች ሁኔታ:
1.በጤና ተቋም የነበሩ የ65 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ (ወንድ)
2.በጤና ተቋም የነበረ የ20 አመት የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ
3.በጤና ተቋም የነበረ የ21 አመት የሀረሪ ክልል ነዋሪ
4.በአስከሬን ምርመራ የተገኘባቸው የ80 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ(ሴት)

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 119 ሰዎች ሲሆኑ ከሶስቱ በስተቀር ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(73) ሴት(46) ናቸው!
➡️ዕድሜያቸው ከ1-80 አመት የሆኑ
➡️ተጨማሪ 117 ሰዎች (78 ከአዲስ አበባ፣ 35 ከትግራይ ክልል፣ 4 ከድሬዳዋ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2132 ነው።
➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(99)፣ ከትግራይ ክልል(5)፣ ከኦሮሚያ ክልል(3)፣ከሶማሊ ክልል(4)፣ ከሀረሪ ክልል(7)፣ ከአማራ ክልል(1) በድምር 119 ሰዎች ናቸው።
➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5689 ደርሷል።
➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 33 ነው።
➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 4 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 98 ነው።

የሕዳሴው ግድብ ቀጣይ የድርድር አጀንዳዎችን በተመለከተ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ባለስልጣናት ለዋዜማ ያሉት👇👇
የአፍሪቃ ሕብረቱ ድርድር ግብፅ በሙሉ ልብ የምትገባበት ባለመሆኑና በአጭር ቀናት ከስምምነት እንዲደረሰ ታስቦ የሚካሄድ ስለሆነ ውጤታማ ይሆናል የሚል ግምት እንደሌላቸው ከኢትዮጵያ ወገን የሆኑ ዲፕሎማት አስረድተዋል። ድርድሩ ወደ አፍሪቃ ህብረት መመለሱ ለሀገራችን ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት መሆኑንና ከዚሀ ቀደም ወደ ሌሎች የድርድር መድረኮች በመሄድ የተከሰቱ ስህተቶ የታረሙበት እርምጃ ነው።ይሁንና ግብፅ የአፍሪቃ ህብረት ድርድር እንዳይሳካ በማድረግ ጉዳዩ በድጋሚ ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዲመለስ ፍላጎት ሊኖራት እንደሚችል ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በኩል ያሉ ተደራዳሪዎች እንዳሉት ደግሞ በሚቀጥሉት ቀናት የሚጀመረው ድርድር ከዚህ ቀደም መግባባት ባልተደረሰባቸውና የህግ ብያኔ ባልተሰጠባቸው ቅንፎች ላይ ያተኮረ እንደሚሆንና ለዚህም የተደራዳሪ ቡድኑ ዝግጅትና ምክክር ማድረጉን አስታውቀዋል።የግድቡ ውሀ አሞላልና አለቃቀቅ በተለይ የድርቅ ወቅት የውሀ ስሌት ፣ የግድቡ አስተዳደርና ቁጥጥር እንዲሁም የግድቡ የደህንነት ጉዳዩች በቴክኒክና በህግ ባለሙያዎች በሚቀርቡ አማራጮች ላይ አተኩሮ ይካሄዳል የሚል እምነት አላቸው።የግድቡ የውሀ አሞላል የጊዜ ሰሌዳን በተመለከተ ከታችኛው የተፋሰሱ ሀገሮች በኩል እንዲዘገይ ብርቱ ፍላጎት ቢኖርም በኢትዮጵያ ወገን ሌላ አሳማኝ ምክንያት ካልተከሰተ በቀር ሙሌቱን የማዘግየትም ሆነ በጊዜ ሰሌዳው ላይ የመደራደር ዕቅድ የለም።
Via Wazema

👍1
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና አካባቢው በዘራፊዎች የተቋረጠው መስመር ተጠገነ!
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና አካባቢው ከሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ላለፉት አምስት ቀናት ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠግኖ አካባቢው ኃይል ማግኘት ጀምሯል፡፡በአካባቢው በተፈፀመ የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ስርቆት ኃይል ተቋርጦ የቆየ ሲሆን ችግሩ በተከሰተበት አካባቢ 20 ምሰሶዎችን በማቆም መስመሩን ለማገናኘት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡
የተቋሙ የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን የጥገና ባለሙያዎች ችግሩን ለመቅረፍ ለቀናት ሲያደርጉት የነበረው ጥረት እየጣለ ባለው ዝናብ ምክንያት አስቸጋሪ የነበረ ቢሆንም ዛሬ አካባቢው ኃይል እንዲያገኝ ማድረግ አስችሏል፡፡በኢንደስትሪ መንደሩና ከዚህ ጋር በተገናኘ ኃይል በተቋረጠባቸው አካባቢዎች ያላችሁ ነዋሪዎች የችግሩን ግዝፈት በመረዳት ኃይል ተመልሶ እስከሚገናኝ በትዕግስት ስለጠበቃችሁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ምስጋናውን አቅርቦላቿል፡፡
ምንጭ:የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንጾኪያ ገምዛ ወረዳ "አደገኛ" የተባለ የበረሐ አንበጣ መንጋ ተከስቷል። ወረዳው ግሾጌ በተባለ ቀበሌ ብቻ 1000 ሔክታር መሬት በአንበጣ መወረሩን ገልጿል። ለማባረር ቢሞከርም የሔደው እየተመለሰ አስቸገረ ተብሏል።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን
#ትንቢተ_ፍጻሜ
#3ኛ_ዕትም_በገበያ_ላይ
እያንዳንዷን ቀን በጥንቃቄ እና በብልሀት መኖርን መዘንጋት የለብንም፡፡ እኛ የመጨረሻዎቹ የሰው ልጅ ፍጥረቶች መሆናችንን ተገንዝበን ይህችን ዓለም ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንደምንሰናበታት ባወቅን ጊዜ በእያንዳንዷ ቀናችን ጠንቃቃና ዝግጁ መሆን እንዳለብን መካሪ አያሻንም፡፡ ለሞት ከሚያበቁ በሽታዎች በርን ዘግቶ ማምለጥ፣ ከድንገተኛ መቅሰፍት እና ከወቅታዊ ወረርሽኝ ራስን በመሰወር የመጨረሻዋን ምድራዊ ሕይወት ኑሮ ጨርሶ ወደ ዘላለማዊ ቤታችን ጠቅልሎ ለመሄድ መጠንቀቅ የብልሆች ስራ ነው፡፡ ይህን እያሰባችሁ መኖር እንዳለባችሁ ለማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡
#ሲልቪያ_ብራውን
#END_of_DAYS መጽሐፍ
#ትንቢተ_ፍጻሜ በሚል በአማርኛ ተተርጉሞ በገበያ ላይ ውሏል፡፡
*
በክርስትና፣ በእስልምና፣ በጆሆቫ፣ በራስ ተፈሪያኖች… በሁሉም ኃይማኖቶች ስለዓለም ፍጻሜ የተነበየ መጽሐፍ፡፡
#ኢትዮጵያ_እና_የንጉሶች_ንጉስ_የሆኑት_አጼ_ኃይለስላሴም_በዚህ_መጽሐፍ_ውስጥ_ተጠቅሰዋል፡፡ ከትንቢተ ፍጻሜው ጋር ምን ያገናኛቸው ይሆን?
#እውን እንደሚባለው ዓለም ፍጻሜዋ አሁን ይሆን? #ወይስ_ስንት_ዘመን_ትቆይ_ይሆን?
ተርጓሚ ራሴላስ ጋሻነህ
የመጽሐፈ ሔኖክ ኢትዮጵያዊና የስኬት ፍልስፍና መጽሐፍት ተርጓሚ
👉 ይቀላቀሉን http://tttttt.me/teklutilahun

#መልካም_ሰዎች_ለምን_ይሰቃያሉ?
#አዲስ_መጽሐፍ_በገበያ_ላይ
መልካም ሰዎች ላይ መጥፎ ነገር የሚደርሰው ለምንድን ነው? መከራን የሚቀበሉትስ ለምን ይሆን? ከዚህ ሁሉ ጥያቄ በኋላ እኛ ያላወቅነው ምስጢር ይኖር ይሆን?
ይህ መጽሐፍ ‹‹ፈጣሪ ለምንድነው ይሄን ሁሉ በእኔ ላይ ያመጣብኝ?›› ለምንለው ነገር ሁሉ ምላሽ አለው!!!
“በሃሳቦች የተሞላ፣ በተዋጣላቸው አመክንዮዎች የተተነተነ፣ የመንፈሳዊ ጥንካሬ መመሪያዎችን የያዘ ድንቅ መጽሐፍ!!”
#ዘ_ዋሽንግተን_ፖስት
“ይህ ላዘኑ መጽናናትን፣ ማባሪያ በሌለው ፍርሃት ለተተበተቡት ሰዎች ደግሞ ሰላምን የሚሰጥ የሃሳብ እድገት መጽሐፍ ነው!”
#ስፕሪችዋሊቲ_ኤንድ_ሄልዝ
“ይህ ለሰው ልጆች ሁሉ አስፈላጊ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ በመከራ የተሞሉ የህይወትን ውጣ ውረዶችን ለመረዳትና ፈጠራ በተሞላበት ጥብበ ለመወጣት ይጠቅማል!”
#ኖርማን_ቪንሰንት_ፒል
#በየመጽሐፍት_መደብሩና_በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።

Forwarded from Nat Computers®️ (Natnael Endrias)
🔵💻HP_Core_i3 (8th Generation)
Model :Notebook (2019 Model)
Condition: Brand New
🖥 Screen :15.6”
📼 Hard disk : 1tera (1000gb)
⏳Ram : 4gb
✅2.2 Ghz Speed
⭕️Color : Silver
🔋:>5hrs - 6hrs
💵Price 17,800br 👈
☎ +251911522626
+251953120011
📩 : @natyendex
🔶 ለበለጠ መረጃ
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAELbSrbiTDHFnicnnA
አድራሻ ቦሌ መድሀኒያለም ሞርኒንግ እስታር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ in front of angla burger

በኒው ዮርክ ከመጋቢት ወዲህ ዝቅተኛ የተባለው የሞት ቁጥር ተመዘገበ!
በአሜሪካ ክፉኛ በቫይረሱ በተጠቃችው ኒው ዮርክ ግዛት ከ30 ሺህ በላይ ሰዎች በወረርሽኙ ሕይወታቸው ማለፉን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያሳያል፡፡ይህም በሌሎች ግዛቶች ከተመዘገበው የሞት ቁጥር ከሁለት እጥፍ በላይ ነው፡፡ይሁን እንጅ ለወራቶች በአሳዛኝ ዜናዎች ተውጣ በነበረችው ኒው ዮርክ አሁን ላይ የቫይረሱ ሥርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መጥቷል፡፡እሁድ ዕለት የግዛቷ አስተዳዳሪ አንድሪው ኮሞ፤ 5 ሰዎች ብቻ በቫይረሱ መሞታቸውን ጠቅሰው፤ ከመጋቢት ወር ወዲህ የተመዘገበ ዝቅተኛ የሞት ቁጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
#BBC

ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ለመግባት የሸንገን ቪዛ ፍቃድ ካገኙ 11 የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ ሆናለች፡፡
በህብረቱ ሸንገን ቪዛ ፍቃድ ከተሰጣቸው 54 የዓለም ሀገራት መካከል ከአፍሪካ አልጄሪያ፣ አንጎላ፣ ግብፅ፣ ሞሪሺያስ፣ ሞሮኮ፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ፣ ሩዋንዳ፣ ቱኒዚያና ዛምቢያ ተካተዋል፡፡በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ድንበሮቻቸውን ዘግተው የቆዩት የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት እ.ኤ.አ ከሀምሌ1/2020 ጀምሮ ድንበሮቻቸውን ሲከፍቱ እንዲገቡ ፍቃድ ከተሰጣቸው አገራት መካከል እንደ አሜሪካ እና ብራዚል ያሉ ወረርሽኙ ያገረሸባቸው አገራት አልተካተቱም። አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን፣ ጀማይካ እና ኩባ ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ፍቃድ ካገኙ 54 አገራት መካከል ናቸው። ሸንገን ቪዛ አብዛኛውን የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ውስጥ ተጓዦች ያለገደብ አንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል የቪዛ አይነት ነው፡፡
ምንጭ፡- ገልፍ ኒውስ/ETV

በጋምቤላ ለሰፋፊ የእርሻ ልማት የዋለው መሬት ክልሉን ጎድቷል ተባለ!
በጋምቤላ ለሰፋፊ የእርሻ ልማት የዋለው መሬት በጥናት ላይ የተመሠረተ ባለመሆኑ በክልሉ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዑሞድ ኡጁሉ ተናገሩ።ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት ከ2000 ጀምሮ በክልሉ በሰፋፊ እርሻ ልማት ላይ እንዲሰማሩ የኢንቨስትመንት ፈቃድ የወሰዱ ባለሀብቶች በዘርፉ ያላቸው አቅምና ብቃት አልተፈተሸም። በክልሉ ለሰፋፊ እርሻ የሚውል 683 ሺህ ሔክታር መሬት ለ623 የአገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ተላልፏል። ለባለሀብቶቹ ከተላለፈው መሬት ውስጥ ልማት ላይ የዋለው 18 በመቶ ብቻ እንደሆነ በ2009 በተካሄደ ጥናት ተረጋግጧል።በመሆኑም ባለሀብቶች የወሰዱትን መሬት በማልማት ለወጣቶችም የሥራ ዕድል ባለመፍጠራቸው ክልሉ ማግኘት የሚገባውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ሳያገኝ መቆየቱን ዑሞድ ገልጸዋል።
ከ10 ዓመት በፊት በጋምቤላ ክልል ለባለሀብቶች በሚሰጠው መሬት ላይ በፌዴራል መንግሥትና በክልሉ ባለሥልጣናት መካከል ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት ተፈጥሮ እንደነበርም አስታውሰዋል።የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ገብነት በስፋት ነበር ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ “በስልክ ትዕዛዝ ብቻ የእርሻ መሬት እንዲሰጥ ይደረግ ነበር” ብለዋል። በወቅቱ ክልሉ እስከ 500 ሔክታር መሬት ድረስ ለባለሀብቶች እንደሚያስተላልፍ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በፌዴራል መንግሥት በኩል ግን ከተባለው ሔክታር በላይ ነበር ብለዋል። በወቅቱ የነበረው አሰራር በተፅዕኖ ሥር የወደቀ ስለነበረ በክልሉና በፌዴራል መንግሥት በኩል ለባለሀብቶቹ የሚሰጠው የመሬት ካርታ መደራረብ የታየበትና ለሙስና የተጋለጠ ነበርም ነው ያሉት።
በመሆኑም በካርታ አሰጣጥ ላይ የሙስና ወንጀል ሲፈጽሙ የነበሩ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሕግ ፊት ቀርበው እንዲቀጡ ተደርጓል ብለዋል። በክልሉ 284 ሺህ 796 ሔክታር መሬት ተመንጥሮ ሳይለማ እንደተቀመጠ የገለጹት ዑሞድ የክልሉ መንግሥት ባሳለፈው ውሳኔ ወደ መሬት ባንክ ገቢ ተደርጓል ብለዋል። ከአገራዊ ለውጡ በኋላ በክልሉ የሚከናወኑ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግባራት ከፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ገብነት የፀዳ መሆኑንም ተናግረዋል።በጋምቤላ ክልል በሰፋፊ የእርሻ ልማት ለመሰማራት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከወሰዱት 623 ባለሀብቶች መካከል የ360 ባለሀብቶች ፈቃድ ተሰርዟል፤ የወሰዱትም መሬት እንዲመለስ ተደርጓል።
Via Addis Maleda