YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 164 ሰዎች ሲሆኑ በዜግነት 163ቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ አንዱ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(47) ሴት(117) ናቸው!

➡️ዕድሜያቸው ከ1-92 አመት የሆኑ

➡️ተጨማሪ 33 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 434 ነው።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(104)፣ ከኦሮሚያ ክልል(2)፣ከአማራ ክልል(22)፣ ከሀረሪ ክልል(1)፣ ከደቡብ ክልል(4)፣ ከሶማሌ ክልል(26) ፣ ከትግራይ ክልል(4) እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ (1) በኮሮና የተያዙ በድምር 164 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2670 ደርሷል።

➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 32 ነው።

➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 5 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 40 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ጋር ሲነፃፀር በ10 እጥፍ መጨመሩ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ታማሚ ከተገኘ ዛሬ ሶስተኛ ወሩን ማስቆጠሩን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል። በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ብዛት 250 የነበረ ሲሆን ባለፈው አንድ ወር ብቻ 2420 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተገልጿል። ይህም ማለት ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ጋር ሲነፃፀር በ10 እጥፍ ጨምሯል።

በመሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኙ መስፋፋት ግምት ወስጥ በማስገባት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል፡፡“መከላከል ከመታከም ይበልጣል፣ ቤት መቆየት ሆስፒታል ከመተኛት ይሻላል፣ የአፍና የአፍንጫን መሸፈኛ አድርጎ መተንፈስ በማሽን ከመተንፈስ ይልቃል። ስለሆነም እነዚህን አንዲሁም ሌሎችን የመከላከያ መንገዶች ሳንዘናጋ በመተግበር እራሳችንን እና የምንወዳቸውን ከኮሮና ቫይረስ በሽታ እንጠብቅ።” በማለት ኢንስቲትዩቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
አብን እና ኦፌኮ ከምርጫ በፊት የህዝብና ቤት ቆጠራ እንዲካሄድ ጠየቁ።

ምርጫው መተላለፉ ካልቀረ የህዝብና ቤት ቆጠራ በመሀከሉ ማካሄድ አስፋላጊ ነው ይላሉ የኦፌኮው አባል አቶ ጃዋር መሀመድ፡፡ይህንን ማድረግ ደግሞ የምርጫውን ቅቡልነት ፤የምርጫውን እና የመንግስትን ተአማኒነት ከፍ ያደርገዋል፡፡መንግስትም ይህንን እንደሚያደርግም አምናለሁ ይላሉ አቶ ጃዋር፡፡የህዝብና ቤት ቆጠራ ማድረግ አስፈላጊነት የጎላ መሆኑን ያነሱት አቶ ጃዋር ቀደም ባለው ጊዜ እንደ ሱማሊ ክልል እና የአማራ ክልል ሲያነሱት የነበረው ጥያቄ በአግባቡ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አሳማኝ በሆነ መንገድ መሬት ለማስያዝ ማካሄዱ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ቆጠራውን ከማካሄዳችን በፊትም ደግሞ የህዝብና ቤቶች ቁጠራው የሚካሄድበት ሂደት ቴክኖሎጂው አሳማኝ በሆነ መልኩ የፖለቲካው ድርጅቶች ፤የሀገሪቱ ልሂቃን መሪዎች ባሉበት ውይይት እና መተማመን መፍጠር ያስፈልጋል ባይ ናቸው፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ምክትል ሊቀመንበር እና የስትራቲጂ ጥናት ሀላፊ አቶ ዮሱፍ ኢብራሂም በበኩላቸው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ሳይታወቅ የምርጫ ጣቢያዎችን መደልደል የሚቻል እንዳልሆነ አንስተው በዚያ ላይ በርካታ ያለፉ ችግሮች አሉ ብለዋል፡፡በዚህ ሀገር ላይ ፍትህ አልሰፈነም፤ በሰብአዊ ጥሰት ሲከሰስ የነበረው መንግስት አሁን ሰብአዊ መብት ሲጣስ ዝም ብሉ ተመልካች ሆኗል፡፡ይህ መጀመሪያ ሊታረም ይገባል ይላሉ አቶ ዮሱፍ፡፡በዚያ ላይ በበርካታ ሀገራዊ ጉዳዩች ላይ መግባባት አልተደረሰም የሚሉት ምክትል ሊቀመንበሩ በዘረኛው አገዛዝ የተወሰኑ ህዝቦች ተገለው ፤ተገፍተው የሀገር አካል እንዳይሆኑ ተደርጓል፡፡ስለሆነም የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ቀድሞ መደረግ አለበት ከዚያ ምርጫው ማካሂድ ይቻላል ብለዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
250 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ዛሬ ሰኔ 4 ቀን 2012 ዓም ከኩዌት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።ዜጎቻችን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከውጭ ጉዳይ እና ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Via Spokesperson of MoFA
@YeneTube @FikerAssefa
ፈረንሳይ ለግብጽ ጦር መሳሪያ መሸጥ መቀጠሏ አስደንጋጭ ነው ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች ባወጣው መግለጫ አውግዟል፡፡ ግብጽ ባለፈው የፈረንጆች ዐመት በ1 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያዎችን ከፈረንሳይ ገዝታለች፡፡ የግብጽ መንግሥት በሰሜናዊ ሲናይ በረሃ በአይኤስ አሸባሪዎች ላይ በሚያደርገው ወታደራዊ ዘመቻ፣ የጦር ወንጀሎችን ስለመፈጸሙ ሂውማን ራይትስ ዎች መረጃ አለው፡፡

Via ዋዜማ ራዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
ሩሲያ፣ በኮሮና ተሕዋሲ የተለከፉ ሰዎችን ለማከም ይረዳል ያለችዉን የፀረ-ተሕዋሲ መድሐኒት ዛሬ ለሐኪም ቤቶች ማደል ጀመረች።

ሮይተር ዜና አገልግሎት RDIF የተሰኘዉን የመድሐኒቱን ማምረቻ ወጪን የቻለዉን ኩባንያ ጠቅሶ እንደዘገበዉ ከ80ዎቹ የሩሲያ ግዛቶች ሰባቱ ዛሬ መድሐኒቱ ደርሷቸዋል።በተቀሩት ግዛቶች ለሚገኙ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎችም መድሐኒቱን ማሰራጨቱ እንደሚቀጥል ባለስልጣናቱ አስታዉቀዋል።የሩሲያ ጤና ጥበቃ ሚንስቴር Avifavir የተሰኘዉ መድሐኒት ለኮቪድ 19 ሕሙማን እንዲሰጥ ልዩ ፈቃድ ሰጥቷል።መድሐኒቱ ላጭር ጊዜ በሰዎች ላይ ቢሞከረም እንደሌሎች መድሐኒቶች በተከታታይና ለረጅም ጊዜ አልተሞከረም።ይሁንና የRDIF የበላይ ኪሪል ድሚትሪቭ እንዳሉት 10 ሐገራት መድሐኒቱ እንዲሸጥላቸዉ ጠይቀዋል።ሩሲያ ከዩናይትድ ስቴትስና ከብራዚል ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ሕዝብ በኮሮና ተሕዋሲ የተለከፈባት ሐገር ናት።502 ሺሕ 436።ይሁንና የርዕሠ ከተማ ሞስኮ ከንቲባ ሰርጌይ ሶብያኒን ትናንት እንዳሉት የተሕዋሲዉን ስርጭት ለመከላከል በከተማይቱ ላይ የተጣለዉ ገደብ ቀስበቀስ ይነሳል።«ከምናየዉ መረጃ በመነሳት ቀስበቀስ እና ደረጃ በደረጃ ወደ ተለመደዉ ሕይወት ለመመለስ መወሰን ይቻላል።ወደ ወትሮዉ ሕይወት የመመለሱ ሒደት ግን ሁለት ወር ግድም ይወስዳል።»

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️
ጾታዊ ጥቃትን በተመለከተ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ያስተላለፉት መልዕክት፣

@YeneTube @FikerAssefa
⚜️SHEBA - ሺባ⚜️

📞 በ 0941158969 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን

ጥራት ያለው ጌጣጌጥ 💎በተመጣጣኝ ዋጋ ከኩባንያችን (ሺባ) ይግዙ ይህንን::

⚠️(ሺባ) የተመሰረተበትን አንደኛ አመት እያከበርን ስለሆነ ‼️ነፃ ‼️ሰዐት ለማግኘት ከዌብ ሳይታችን ላይ ማንኛዉንም እቃ ይግዙ፡

👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼

Website - www.shebasluxury.com

Telegram - https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFfS1CHMcuedhCLPBQ

Contact Admin @ki_d_us

📞 በ 0941158969 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን🏍
#ዘ_አልኬሚስት
#4ተኛው_እትም_በገበያ_ላይ_ዋለ

ከ150 ሚሊዮን ኮፒዎች በላይ በመሸጥ ጊነስ ቡክ ላይ ለመስፈር የበቃ፣ ከ80 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የተተረጎመ፣ 115 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን የተቀዳጀ የምንጊዜም ምርጥ መጽሐፍ የሆነው ዘ-አልኬሚስት #አማርኛው_እነሆ_ለ4ተኛ ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ዋለ!!!

#ስለዚህ_ድንቅ_መጽሐፍ_ከተሰጡ አስተያየቶች

“ስለ አስማት፣ ህልም እና በሌሎች ቦታዎች ተግተን ስልምንፈልገው፣ ነገር ግን ከበራችን ደጃፍ ስላለው ሃብት የሚያወራ ውብ መጽሐፍ”
#ማዶና (ዘፋኝ)

“ከምርጥ መጽሐፎቼ አንዱ”
#ዊል_ስሚዝ (ተዋናይ)

Join T.me/teklutilahun
EmpowerMed የተሰኘ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የጤና ዘርፍ በእጅጉ የመደገፍ ብሎም የመዋቅር ለውጥ ለማምጣት የሚሰራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ሀገር በቀል ያልሆነ ግብረሠናይ ድርጅት ነው። መቀመጫውን በሀገረ አሜሪካ ያደረገው ይህ ግብረሠናይ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፉን በመክፈት እየሰራ ይገኛል። በቅርቡ በተቀሰቀሰው COVID-19 ወረርሽኝን ምክንያት ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎችን ለመርዳት ፕሮግራም በመቅረፅ ማገዝ ይፈልጋል። በየትኛውም የሀገሪቷ ክፍል ያላችሁ የህክምና ተማሪዎች ማለትም Medical, Nursing, Midwifery ወዘተ እና የማህበረሰብ ጤና ሰራተኞች በሙሉ ከድርጅታችን ጋር ህብረት መፍጠር የምትፈልጉ በሙሉ በተገለፀው ዌብሣይት እና የ ፌስቡክ ገፃችን ላይ በመግባት መመዝገብ እና ህብረት መፍጠር ትችላላችሁ ።
የድርጅቱ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ facebook.com/empowermed.ngo ነው።


የድርጅቱ ዌ ብ ሳ ይ ት
http://EmpowerMed.ngo

ነው።
#የጭን_ቁስል
#27ኛ_ዕትም_በገበያ_ላይ

ሕጻናት ዐምባ ውስጥ ያደገችው እንስት ማን እንደሆነችና ከየት እንደተገኘች አታውቅም፡፡ ዐምባው ወደ ሌላ ተቋም ሲቀየር ህይወቷ አደጋ ላይ ወደቀ…

እናም በገጠማት እጅግ መራርና አንገሽጋሽ የሕይወት ትግል እግዚአብሔርን የምታስፈራራ፣ ሞት ታግሎ ታግሎ ሊጥላት ያልቻለች ነፍስ ሆና የሁላችንንም ጓዳ እያስፈተሸች ማንም ትንፍሽ ሊል የማይደፍረውን ገመና ገላልጣ ታሳየናለች…

***
#ለደራሲው_ሥራ_ከተሰጡ_አስተያየቶች

ታሪኩ አጓጊ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ምእራፍ ወይም ክፍል የሚተረኩት ታሪኮች ስሜት ይዘው የሚነጉዱ ናቸው፡፡ ልብ ያንጠለጥላሉ፡፡ ቀጥሎስ? ከዚያ በኋላስ? መጨረሻውስ እያልን ነው የምናነበው፡፡ #አዲስ_አድማስ_ጋዜጣ

መጽሐፉ በሚመስጥ መልኩ ተጀምሮ፣ በሚመስጥ መልኩ የሚያልቅ ነው፡፡ #ኤፍ_ኤም_97.1

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።
join T.me/teklutilahun
በኮሮና የሟች ቤተሰቦች የጣሊያኑን ጠ/ሚኒስትር ሊከሱ እየተዘጋጁ ነው።

በሰሜን ጣሊያን አቃቢ ሕግ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፔ ኮንቴን ዛሬ አርብ ለምርመራ ቀጥሯቸዋል።
ምክንያቱ ደግሞ ዘመድ ወዳጆቻቸው በኮሮና የሞቱባቸው ቤተሰቦች "መንግሥት ቶሎ እርምጃ አልወሰደም፤ ተዘናግቶ ነበር፣ ቤተሰቦቻችንን በሞት ያጣነው በመንግሥት እንዝላልነት ነው" የሚል ክስ በማቅረባቸው ነው።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
የስፔኑ ከፍተኛ ሊግ ላሊጋ ከሶስት ወራት በኋላ ሲቪያ እና ርያል ቤቲስን ባገናኘው ጨዋታ ተጀምሯል።

ጨዋታው በሲቪያ አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን ከሜዳ ውጪ ግን ብዙ ችግሮች መስተዋላቸው ተገልጿል።

አንዳንድ የቡድኖቹ ደጋፊዎች የተቀመጠውን ጥብቅ መመሪያ በመጣስ ከጨዋታው በፊት በስታዲየሙ ዙሪያ ተሰባስበው ታይተዋል።

በጨዋታው ኦካምፖስና ሬጌስ ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ሲቪያ ማሸነፍ ችሏል።

Via:- BBC
@YeneTube @Fikerassefa
በሜደትራኒያን ባህር በርካታ አፍሪካውያን ስደተኞች ሰጥመው ሞቱ።

ስደተኞችን ጭና የነበረች ጀልባ ከሰጠመች በኋላ የ46 ስደተኞች አስክሬን መገኘቱን የቱኒዚያ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
በባሌ ዞን ዲንሾ ወረዳ የጭነት አሽከርካሪ ግድያ ተጠርጣሪዎች ታሰሩ

በባሌ ዞን ዲንሾ ወረዳ የጭነት መኪና አሽከርካሪ ሳዲቅ ሃጂ ኢብሮን በመግደል ወንጀል የተጠረጠሩ 12 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።ከተጠርጣሪዎች ውስጥ ሁለቱ የመደበኛ ፖሊስ አባላት ሲሆኑ አስሩ የዲንሾ ፓርክ ጥበቃ ሰራተኞች መሆኑ ተገለፀ።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል በታላቁ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት ሒደት ላይ የሚካሔደው ውይይት ነገ ይቀጥላል!

የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በታላቁ የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል የሚካሔደው ድርድር መቀጠሉን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።ድርድሩ እስከ ሰኔ 04 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለሦስተኛ ቀን የግድቡን የመጀመሪያ ሙሌት የሚመለከቱ መመሪያዎች እና ሕጎች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ታዛቢዎች በተገኙበት በቪዲዮ ውይይት አማካኝነት መካሔዱን ገልጿል።ሐሙስ ዕለት በኢትዮጵያ ሊቀመንበርነት በተካሔደው ውይይት አገራቱ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት እና አተገባበር ላይ ያላቸውን ስጋት አንሥተዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከታችኞቹ የተፋሰሱ አገራት ጋር ውኃውን ስለምትጠቀምበት ሁኔታ ሱዳን ባቀረበችው ምክረ ሐሳብ ላይ መምከራቸው ታውቋል።ኢትዮጵያ በሦስቱ አገራት መካከል የሚካሔደው የውይይት ሒደት በመልካም አቀራረብ እና ሁሉንም በሚያስማማ መልኩ እንዲከናወን ያላትን ጽኑ አቋም ማስታወቋም ተገልጿል።

ከዚህ ባሻገር ውጤቱ ምንጊዜም የሦስቱ አገራትን ሕዝቦች ተጠቃሚ ለሚያደርግ ስምምነት እንደምትሠራ አመልክታለች። ሐሙስ ዕለት የተካሔደው ውይይት የታዛቢዎች ሚና ምን መሆን እንዳለበት ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑም ተመልክቷል።በዕለቱ በአገራቱ መካከል የተዘጋጁ ዶክመንቶች ልውውጥ እና በአገራቱ መካከል ያሉ መሠረታዊ ልዩነቶች በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ በቀጣይ ቀናት ውይይት እንዲደረግባቸው ስምምነት ላይ መደረሱን ጠቅሷል።በስምምነቱ መሠረት ዓርብ እና እሑድ እረፍት በመሆኑ በሦስቱ አገራት መካከል የተጀመረው ውይይት ሰኔ 06 ቀን 2012 ዓ.ም በሱዳን ሊቀመንበርበት እንደሚቀጥል መግለጫው ጠቁሟል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa