YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from HEY Online Market
Playstation 4PRO (Slim)
With 2 controllers
1000 GB storage
With FIFA 2019 CD

Price 23,999 Birr

Contact us :
0953964175
0925927457 @eBRO4
0910695100
@heyonlinemarket
Forwarded from Kídus
⚜️SHEBA - ሺባ⚜️

📞 በ 0941158969 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን

ጥራት ያለው ጌጣጌጥ 💎በተመጣጣኝ ዋጋ ከኩባንያችን (ሺባ) ይግዙ ይህንን::

⚠️(ሺባ) የተመሰረተበትን አንደኛ አመት እያከበርን ስለሆነ ‼️ነፃ ‼️ሰዐት ለማግኘት ከዌብ ሳይታችን ላይ ማንኛዉንም እቃ ይግዙ፡

👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼

Website - www.shebasluxury.com

Telegram - https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFfS1CHMcuedhCLPBQ

Contact Admin @ki_d_us

📞 በ 0941158969 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን🏍
Forwarded from YeneTube
EmpowerMed የተሰኘ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የጤና ዘርፍ በእጅጉ የመደገፍ ብሎም የመዋቅር ለውጥ ለማምጣት የሚሰራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ሀገር በቀል ያልሆነ ግብረሠናይ ድርጅት ነው። መቀመጫውን በሀገረ አሜሪካ ያደረገው ይህ ግብረሠናይ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፉን በመክፈት እየሰራ ይገኛል። በቅርቡ በተቀሰቀሰው COVID-19 ወረርሽኝን ምክንያት ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎችን ለመርዳት ፕሮግራም በመቅረፅ ማገዝ ይፈልጋል። በየትኛውም የሀገሪቷ ክፍል ያላችሁ የህክምና ተማሪዎች ማለትም Medical, Nursing, Midwifery ወዘተ እና የማህበረሰብ ጤና ሰራተኞች በሙሉ ከድርጅታችን ጋር ህብረት መፍጠር የምትፈልጉ በሙሉ በተገለፀው ዌብሣይት እና የ ፌስቡክ ገፃችን ላይ በመግባት መመዝገብ እና ህብረት መፍጠር ትችላላችሁ ።
የድርጅቱ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ facebook.com/empowermed.ngo ነው።


የድርጅቱ ዌ ብ ሳ ይ ት
http://EmpowerMed.ngo

ነው።
Forwarded from Fiker Assefa
#ዘ_አልኬሚስት
#4ተኛው_እትም_በገበያ_ላይ_ዋለ

ከ150 ሚሊዮን ኮፒዎች በላይ በመሸጥ ጊነስ ቡክ ላይ ለመስፈር የበቃ፣ ከ80 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የተተረጎመ፣ 115 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን የተቀዳጀ የምንጊዜም ምርጥ መጽሐፍ የሆነው ዘ-አልኬሚስት #አማርኛው_እነሆ_ለ4ተኛ ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ዋለ!!!

#ስለዚህ_ድንቅ_መጽሐፍ_ከተሰጡ አስተያየቶች

“ስለ አስማት፣ ህልም እና በሌሎች ቦታዎች ተግተን ስልምንፈልገው፣ ነገር ግን ከበራችን ደጃፍ ስላለው ሃብት የሚያወራ ውብ መጽሐፍ”
#ማዶና (ዘፋኝ)

“ከምርጥ መጽሐፎቼ አንዱ”
#ዊል_ስሚዝ (ተዋናይ)

Join T.me/teklutilahun
#የጭን_ቁስል
#27ኛ_ዕትም_በገበያ_ላይ

ሕጻናት ዐምባ ውስጥ ያደገችው እንስት ማን እንደሆነችና ከየት እንደተገኘች አታውቅም፡፡ ዐምባው ወደ ሌላ ተቋም ሲቀየር ህይወቷ አደጋ ላይ ወደቀ…

እናም በገጠማት እጅግ መራርና አንገሽጋሽ የሕይወት ትግል እግዚአብሔርን የምታስፈራራ፣ ሞት ታግሎ ታግሎ ሊጥላት ያልቻለች ነፍስ ሆና የሁላችንንም ጓዳ እያስፈተሸች ማንም ትንፍሽ ሊል የማይደፍረውን ገመና ገላልጣ ታሳየናለች…

***
#ለደራሲው_ሥራ_ከተሰጡ_አስተያየቶች

ታሪኩ አጓጊ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ምእራፍ ወይም ክፍል የሚተረኩት ታሪኮች ስሜት ይዘው የሚነጉዱ ናቸው፡፡ ልብ ያንጠለጥላሉ፡፡ ቀጥሎስ? ከዚያ በኋላስ? መጨረሻውስ እያልን ነው የምናነበው፡፡ #አዲስ_አድማስ_ጋዜጣ

መጽሐፉ በሚመስጥ መልኩ ተጀምሮ፣ በሚመስጥ መልኩ የሚያልቅ ነው፡፡ #ኤፍ_ኤም_97.1

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።
join T.me/teklutilahun
በፔሩ ወረርሽኙን ተከትሎ የዝንጅብል የውጭ ገበያዋ 150 በመቶ ጭማሪ አሳየ

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በበርካቶች ዘንድ ለመከላከያነት ሲመከር የነበረው ዝንጅብል በዓለም ተፈላጊነቱ ጨምሯል።

ወረርሽኙንም ተከትሎ ፔሩ ወደ ውጭ የምትልከው የዝንጅብል መጠን በሦስት እጥፍ አድጓል።

ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ ያለው አሃዝ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲወዳደር በ150 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

የዝንጅብል ምርቱን ከፔሩ በገፍ እያስገቡት ያሉት ስፔን፣ ሆላንድና አሜሪካ ናቸው።
የሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም ያሳድጋል የሚባልለት ዝንጅብል ከኮሮናቫይረስ ከመያዝ ሊታደገን ይችላልም በሚል ብዙዎች እየወሰዱት ይገኛል።

ዝንጅብል ለጤና ጠቃሚ ከሚባሉ ስራስሮች አንዱ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ቢሆንም በቫይረሱ ከመጠቃት እንደማይከላከል ግን ልብ ሊባል እንደሚገባ ባለሙያዎች ይመክራሉ።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሚሊዮን አለፈ

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአሜሪካ ውስጥ መገኘቱ ከተረጋገጠ በኋላ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን ማለፉን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ አመለከተ።

በአሜሪካ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት ከ2 ሚሊዮን በላይ ሆኗል። ይህም አሃዝ በዓለም ቀዳሚዋ ሲደርጋት በሁለተኝነት ከምትከተላት ከብራዚል በሦስት እጥፍ የበለጠ ነው።

በብራዚል በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ772,400 በላይ ነው።

አሜሪካ ከየትኛውም አገር በላይ በርካታ ቁጥር ያለውን ምርመራ የምታደርግ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ በየቀኑም እስከ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ናሙናዎችን ትመረምራለች። ይህም በበሽታው የተያዙ በርካታ ሰዎች እንዲገኙ ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ ይነገራል።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassera
ከ20 አመት በላይ ተቋርጦ የቆየው የደብረታቦር አየር ማረፊያ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። አየር ማረፊያውን ለበረራ አገልግሎት ምቹ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ ነው፡፡ከሳምንት በፊት የደብረማርቆስ አየር ማረፊ ከረጅም ዓመታት በኅላ እንደገና አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወሳል።

Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
የገቢዎች ሚኒስቴር በግንቦት ወር 18 ነጥብ 35 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰብስቧል።

ሚኒስቴሩ በግንቦት ወር 23 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 18 ነጥብ 35 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 77 ነጥብ 8 በመቶ ማሳካቱ ተገልጿል።ይህም የእቅድ አፈፃፀም ከሀገር ውስጥ ታክስ 10 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር የተሰበሰበ ሲሆን ከውጪ ቀረጥና ታክስ ደግሞ 7 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል።አፈፃፀሙም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ3 ነጥብ 08 ቢሊየን ብር ወይም የ20 ነጥብ 15 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተመላክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ለ2013 በጀት ዓመት 476 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ለምክር ቤቱ ቀረበ!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የፌዴራል መንግስት የ2013 ረቂቅ በጀት በተመለከተ በሚያቀርቡት የበጀት መግለጫ በማድመጥ ላይ ይገኛል፡፡ረቂቅ በጀቱም ብር 476 ቢሊዮን ሆኖ ለምክር ቤቱ ውይይት ቀርቧል፡፡የ2013 በጀት ግብዓትን ከውጤት ጋር የሚያዛምድ እንዲሁም ኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀቱን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡በበጀት ዓመቱ ኢኮኖሚው በ8 ነጥብ 5 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብም የገንዘብ ሚነስትሩ መናገራቸውን ከETV ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የታላቁን የህዳሴ ግድብ የውሀ ሙሌት እና አመታዊ የውሀ አለቃቀቅ በተመለከተ የሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ ያላትን አቋም ግልፅ አደረገች!

የኢትዮጵያ ፣ የግብፅ እና የሱዳን የውሀ ሚኒስትሮች የታላቁን የህዳሴ ግድብ የውሀ ሙሌት እና አመታዊ የውሀ አለቃቀቅን በተመለከተ የሚያደርጉት የሶስትዮሽ ድርድር በትናንትናው እለትም ቀጥሎ ተካሂዷል፡፡በዚህም የሁለተኛው ቀን ውይይት ላይ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የሶስትዮሽ ትብብር ውይይቱን በተመለከተ ያላትን አቋም ለሁለቱ የተፋሰስ ሀገራት ግልፅ አድርጋለች፡፡የኢፌድሪ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ላይ ያወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ:

በዚህም መሰረት
1. ኢትዮጵያ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ የውሀ ሙሌት እና ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ህግ እና መመሪያዎች ላይ ቀና ትብብር እና ድርድር ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ በመግለፅ፤ በሶስቱ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች ደረጃ ውይይቱን እንደገና በመጀመሩ ደስተኛነቷን ገልፃለች፡፡

2. ኢትዮጵያ በሶስቱ ሀገራት መካከል የተደረጉ ስምምነቶች ሙሉ በሙሉ መከበር እንደሚገባቸውም አስገንዝባለች፡፡

3. የሦስቱ ሀገራት ስምምነት ላይ ደርሰው ልምድ እና ተሞክሮዎችን እንዲያካፍሏቸው ካልጠየቁ በስተቀር የታዛቢዎች ሚና ድርድር ከመመልከት እና ከመታዘብ የዘለለ መሆን እንደሌለበትም ኢትዮጵያ አሳስባለች፡፡

4. ከየካቲት 5-6 ቀን 2012 በተካሄደው ስብሰባ የሦስቱ አገሮች የሕግና የቴክኒክ ቡድኖች ያቀረቡት የሥራ ሰነድ የድርድሩ መሠረት መሆን እንደሚገባው አስታውቃ፤ በዚህም አውድ ፣. ኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ውሀ ሙሌት እና ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም መመሪያዎች እና ህጎችን በተመለከተ የራሷን አማራጭ ሃሳብ አካፍላለች፤ ሱዳንም እንዲሁ አቋሟን የሚያሳይ ሰነድ አስገብታለች፡፡

5. በሶስትዮሽ ውይይቱ የመጀመሪያ ቀን ማለትም ሰኔ 2/2012 እንደተስማሙት የህዳሴው ግድብ ድርድር እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከማክሰኞ ፣ አርብ እና እሑድ በስተቀር ባሉት ሁሉም ቀናት በኢንተርኔት የሚደረገው የቪድዮ ውይይት የሚቀጥል መሆኑም ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ በሶስትዮሽ ውይይቱ ጊዜ በተወያይ ወገኖች መካከል ጠንካራ እምነት መገንባት እጅግ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ያሳሰበች ሲሆን፣ ሆኖም ግን የግብፅ ቀጣይነት ባለው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ ለመሳተፍ ፈቅዳ በተመሳሳይ ሰአት የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም / ቤት የውጭ ዲፕሎማሲ ጫና እንዲያሳድር የምታደርገው ጥረት በድርድሩ ላይ ግልፅነት እና መተማመን እንዲኖር የሚያደርግ አይደለም ስትል ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡

ስለሆነም ኢትዮጵያ በድርድሩ ላይ የሚሳተፉ አካላት እውነተኛ የሆነ የውይይት እና የድርድር አቋምን ይዘው እንዲሳተፉ ጥሪን በማቅረብ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰቡም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በድርድሩ እንዲሳተፉ እንዲያበረታታ በጥብቅ ያሳስባል የሚል ጠንካራ እምነት እንዳላትም አስታውቃለች፡፡በመጨረሻም ኢትዮጵያ የሶስትዮሽ ድርድሩ በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን የበኩሏን ድርሻ ለመወጣት ሙሉ በሙሉ ትሰራለች፡፡

-የኢፌድሪ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር
ትርጉም በ @addismaleda
@YeneTube @FikerAssefa
በሰዓት 80,000 ፣ በቀን ደግሞ 1.6 ሚሊዮን ዳቦዎችን እንደሚያመርት የተነገረለት ሸገር የዳቦ ማምረቻ በዚህ ሳምንት ስራ ይጀምራል ተብሏል። ለግንባታው 900 ሚሊዮን ብር የወጣበትና 10 ወር የፈጀው፣ በሚድሮክ ሆራይዝን ኃ/የተ/የግ/ኩ ግንባታው የተከናወነው ይህ የዳቦ ማምረቻ 100 ግራም ዳቦ በ75 ሳንቲም ያቀርባል ብለዋል የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ፌቨን ተሾመ። ነገር ግን የፕሮጀክቱ ማናጀር ሲሳይ ደበበ በዚህ ዋጋ ለማቅረብ እስካሁን ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ስምምነት ላይ አለመደረሱን መናገራቸውን ፎርቹን ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን 25.8 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ የ15 የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ ስምምነት ተፈረመ።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
የኬንያ ፖሊስ አንዲትን ሴት ከሞተር ሳይክል ጀርባ አስሮ መንገድ ላይ መጎተቱ ቁጣን ቀሰቀሰ!

ኬንያዊው ፖሊስ አንዲትን ሴት ከሞተር ሳይክል ጀርባ አስሮ በመንገድ ላይ ሲጎትትና ሲገርፋት የሚያሳይ ቪዲዮ መውጣቱን ተከትሎ ቁጣን ቀስቅሷል፤ ፖሊሱም በምርመራ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።ግለሰቧ ሜሪ ቼሮኖ የምትባል ስትሆን ናኩሩ በምትባለው የኬንያ ከተማም ነዋሪ ናት።ፖሊሱ በከተማው በተፈጠረ ዝርፊያ ጠርጥሬያታለሁ በሚልም ነው መንገድ ለመንገድ የጎተታት ግለሰቧ በእጇና እግሯ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱም ሆስፒታል ህክምና ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል።ሜሪ ቼርኖ ፖሊሱን እንደምታውቀው ለሲትዝን ቴሌቪዥን ተናግራለች። ፖሊሶችን በተመለከተ ማጣራት የሚያደርገው ነፃ ድርጅትም ግለሰቡ ላይ የሚያስፈልገው እርምጃ እንደሚወሰድበት ገልጿል።በባለፈው ይኸው ድርጅት ባወጣው መግለጫ የኮሮናቫይረስን መዛመት ለመግታት የወጡ ህጎችን አስከብራለሁ በሚል የአስራ አምስት ኬንያውያን ህይወት መጥፋቱን እንዲሁም 31 መቁሰላቸውን አጋልጧል።የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ቢሮ ከሰሞኑ ባወጣው ሪፖርትፖሊስ ጭካኔ የተሞላበት ጥሰት ማድረሱን ያሳወቀ ሲሆን፤ ድርጅቱም መደፈር፣ ድብደባና ንብረቶችን በማውደም ፖሊስን ወንጅሎታል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሲዳማ ክልል በጀት ዛሬ በነበረው የ2013 በጀት መግለጫ የፓርላማ አባላት ለብቻ እንዲቀርብ ጠየቁ!

በበጀት መግለጫቸው የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የፌደራል እና ክልል በጀት ረቂቅን ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ አንዳንድ የፓርላማ አባላት የሲዳማ ክልል በጀት ለምን ለብቻ አልቀረበም ሲሉ ጠይቀዋል፡፡በመልሳቸው ሚኒስትሩ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የበጀት ቀመር መምጣት እንዳለበት አስታውሰው ያ ከመጣ የሂሳብ ስሌት ስለሆነ በቀላሉ የአዲሱን ክልል በጀት ማውጣት ይቻላል ብለዋል፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️
ዛሬ ስምምነት የተፈረመባቸው 15 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች።

Via ERA
@YeneTube @FikerAssefa
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በ2 ተቃውሞ፣ በ2 ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 164 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።

በ24 ሰዓታት ውስጥ 164 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ።ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 630 የላብራቶሪ ምርመራ 164 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 670 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ \ታደሰ አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ የ5 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፣ ባጠቃላይ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 40 ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ 5 ሰዎች ሁኔታ

➡️በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው የ92 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ(ወንድ)

➡️በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው የ58 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ(ወንድ)

➡️ በህክምና ላይ የነበሩ የ70 አመት፣ ከሶማሌ ክልል(ወንድ)

➡️በህክምና ላይ የነበሩ የ80 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ( ሴት)

➡️ በህክምና ላይ የነበረ የ36 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 40 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍1