የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮ ሱዳን የባቡር ፕሮጀክት ጥናት 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ!
የአፍሪካ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ለሚገነባው የባቡር ፕሮጀክት የአዋጭነት ጥናት ለኢትዮጵያ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማስረጉን አስታወቀ።ባንኩ ያፀደው ድጋፍ ለአዋጭነት ጥናቱ ከሚያስፈልገው 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር 35 በመቶውን የሚሸፍን ነው ተብሏል።የባቡሩ ፕሮጀክት ከካርቱም አልፎም በቀይ ባህር ላይ ከሚገኘው ፓርት ሱዳን ጋር የሚገናኝ ነው ተብሏል።አዲስ አበባን ከካርቱም የሚያገኛኘው የባቡር ፕሮጀክት 1 ሺህ 522 ኪሎ ሜትር ርዝመት እንዳለው ከኒውስ ዊክ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa

የከተማ አስተዳደሩ ባመቻቸው እድል እናት ባንክ የመጀመሪያው ተጠቃሚ ሆነ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከባንኮች ማህበር ጋር በገባው ስምምነት በከተማው እምብርት ብሄራዊ ባንክ አካባቢ ለባንኮች ግዙፍ ህንፃዎች ግንባታ እንዲሆን በማሰብ መሬት በማቅረብ ሂደቱ እናት ባንክ የመጀመሪያው ተጠቃሚ ሆነ፡፡ከተመሰረት አጭር እድሜ ያለው እናት ባንክ ከከተማ አስተዳደሩ ተገቢውን የሊዝ እና ሌሎች ክፍያዎች በመፈፀም 4,800 ካሬ ሜትር ቦታ ተረክቢያለው ብሏል፡፡ ባንኩ የተረከበው ቦታ አሁን ዘመን ባንክ ከሚገነባው ህንፃ ጀርባ ዮቤክ ህንፃ ፊት ለፊት መሆኑን የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ ወንድወሰን ተሸመ ለካፒታል ገልፀዋል፡፡ባንኩ በሁለት ቢሊየን ብር ወጪ የ 35 ፎቅ ህንፃ ግንባታ ለማከናወን እቅድ እንዳለው ፕሬዝዳንቱ ገልፀው ከዛ በፊት ግን ዝርዝር ሂደቶች እና የዲዛይን መረጣ መኖሩን አስታውሰዋል፡፡
Via Capital

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር በከተማ መሃል የሚገኘውን 'አመዶ ገብያ' ሙሉ ለሙሉ አፈረሰ። ከገብያው የተነሱ ዜጎች ተለዋጭ የመገበያያ ቦታ እንደተሰጣቸው የከተማው ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶክተር መሐሪ ታደሰ ገልጸዋል።
Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ የ3 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፣ ባጠቃላይ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 35 ደርሷል፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ 3 ሰዎች ሁኔታ
➡️በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው የ115 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ(ወንድ)
➡️በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው የ84 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ(ወንድ)
➡️ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው የ35 አመት፣ ከኦሮሚያ ክልል(ወንድ)
በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 35 ደርሷል፡፡

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 170 ሰዎች ሲሆኑ በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(93) ሴት(77) ናቸው!
➡️ዕድሜያቸው ከ2-115 አመት የሆኑ
➡️ተጨማሪ 22 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 401 ነው።
➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(81)፣ ከኦሮሚያ ክልል(7)፣ከአማራ ክልል(13)፣ ከሀረሪ ክልል(3)፣ ከደቡብ ክልል(2)፣ ከሶማሌ ክልል(57) ፣ ከትግራይ ክልል(7)፣በኮሮና የተያዙ በድምር 170 ሰዎች ናቸው።
➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2506 ደርሷል።
➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 33 ነው።
➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 3 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 35 ነው።

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ይካሄዳል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዳራሽ በሚደረገው 16ኛ መደበኛ ስብሰባ የም/ቤቱን 5ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ እና 5ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤዎችን መርምሮ በማጽደቅ የዕለቱ መደበኛ ስብሰባ የሚጀምር ይሆናል፡፡ምክር ቤቱ በነገው ውሎ የፌዴራል መንግስት የ2013 ረቂቅ በጀት ላይ በመወያየት ረቂቅ የበጀት አዋጁን ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ የሚመራ ሲሆን አራተኛውን የህዝብና ቤት ቆጠራ ለሶስተኛ ጊዜ ለማራዘም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ለማቅረብ የተዘጋጀውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም የገቢ፣በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ስለማዛወር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን እንዲሁም የህግ፣ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን እና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የሚቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን እንደሚያጸድቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#AMN

ኮቪድ-19ን መከላከል እንዲቻል በቀን 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል /ማስክ/ ለማምረት እየተሰራ መሆኑን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።የማስክ እጥረት እንዳይከሰትና ለኅብረተሰቡም ተደራሽ እንዲሆን የጨርቃጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪዎች የጨርቅ ማስኮችን እንዲያመርቱ እየተደረ መሆኑን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገልጿል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የባህልና ዘመናዊ ሕክምናዎችን አቀናጅቶ መሥራት ላይ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አሳሰቡ!
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ከወሎ ዩኒቨርስቲ፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንዲሁም የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር “በኮቪድ-19 እና በሌሎች ወረርሽኞች ዙሪያ አገር-በቀል የባህላዊ ህክምና እውቀቶች ሊያመጡ የሚችሉት መፍትሄዎች” በሚል ርዕስ ሳምንታዊ የምሁራን ምክክር ዌቢናር በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡በዌቢናር ምክክሩም ዶክተር ሊያ ታደሰ ‘‘በዓለም ላይ የተገኙ ግኝቶች ከተፈጥሮ መሠረት ያደረጉ ናቸው’’ በማለት የባህል ሕክምናውን ከዘመናዊው ሕክምና ጋር ማቀናጀት ካልተቻለ ወደፊት መሄድ እንደሚያስችገር አሳስበዋል፡፡
ይህ የምክክር መድረክ ‘‘አገር በቀል ዕውቀቶችን እንዴት አድርገን ወደ ሳይንሳዊ መንገድ እናምጣ? የሚለውን ጉዳይ አትኩሮት እንድንሰጥበት ይረዳናል ያሉት ሚኒስትሯ የባህልና ዘመናዊ ሕክምናዎችን አቀናጅቶ መሥራት በኢትዮጵያ እንብዛም ያልተሞከረ በመሆኑ ይህንን የኮሮና ወረርሽኝ ጊዜ እንደ አጋጣሚ በመጠቀም የባህል ሐኪሞች ጋር በመሆን ለአገርም ሆነ ለዓለም የሚጠቅም ሥራ መስራት የሚቻልበት ተስፋ እንዳለም ጠቁመዋል፡፡ በምክክሩ ላይም የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሒሩት ወልደማርያም (ፕሮፌሰር)፣ የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶክተር)፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሒሩት ካሳው (ዶክተር) እና ሌሎችም የዘርፉ ምሁራን እየተሳተፉበት እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል፡፡
Via Addis Maleda

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ አንድ (81) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ 22 ሰዎች ከኮሮና በሽታ አገግመዋል፡፡
በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ አንድ (81) ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ (1859) ደርሷል፡፡
በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፦
አዲስ ከተማ 27፤
ልደታ 2፤
ጉለሌ 15፤
ኮልፌ ቀራንዮ 7፤
ቦሌ 12፤
አራዳ 4፤
የካ 4፤
ንፋስ ስልክ ላፍቶ 8፤
አቃቂ ቃሊቲ 0፤
ቂርቆስ 2 መሆኑን የከተማው ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት ሃያ ሁለት (22) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ ማገገማቸውን የከተማዋ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

"ከሴቶችና ህፃናት ጥቃት ጋር በተያያዘ 94 መዝገቦች በፖሊስ ምርመራ ላይ ናቸው" ጠቅላይ አቃቤ ህግ
በባለፉት ወራት ከመቶ በላይ ህፃናት መደፈራቸው ጋር በተያያዘ 94 መዝገቦች በፖሊስ ምርመራ ላይ መሆናቸውን እና 23 ክሶች መመስረታቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል። ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአራት መዝገቦች ላይ የፍርድ ውሳኔ መሰጠቱንም ጠቁመዋል።የኮሮናቫይረስ ስርጭት መዛመትን ለመግታት ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ተከትሎ የተደፈሩ ህፃናት ቁጥር ማሻቀቡንና ከመቶ በላይ ህፃናት ሴቶችና ወንዶች መደፈራቸውን የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ከሰሞኑ መግለፁ የሚታወስ ነው።

YeneTube
"ከሴቶችና ህፃናት ጥቃት ጋር በተያያዘ 94 መዝገቦች በፖሊስ ምርመራ ላይ ናቸው" ጠቅላይ አቃቤ ህግ በባለፉት ወራት ከመቶ በላይ ህፃናት መደፈራቸው ጋር በተያያዘ 94 መዝገቦች በፖሊስ ምርመራ ላይ መሆናቸውን እና 23 ክሶች መመስረታቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል። ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአራት መዝገቦች ላይ የፍርድ ውሳኔ መሰጠቱንም ጠቁመዋል።የኮሮናቫይረስ ስርጭት…
ከዚህ ጋር በተያያዘ የቤት ውስጥ ጥቃት፤ የህጻናትና የቤተሰብ ጉዳዮችን የተመለከቱ አቤቱታዎች በመደበኛ ችሎቶች የሚስተናገዱ መሆናቸው ይቀጥላል ተብሏል፡፡
ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሆኑባቸው ባለፈው ሶስት ወራት የተፈጸሙ የህጻናትና ሴቶች የቤት ውስጥ ጥቃትን የያዘ መዝገብ አስቸኳነት ያላቸውን ጉዳዮችን ለማየት በተቋቋሙ ተረኛ ችሎቶች ለዳኝነት አለመቅረቡን ቀጥታ ክስ የሚያስተናግዱ የፌዴራል መጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ገልጸዋል፡፡የአዲስ አበባ ህጻናት፤ ሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ መስሪያቤት ከህክምና ማእከላት ያገኘውን መረጃ መነሻ በማድረግ ባላፉት ሁለት ወራት ብቻ 101 የህጻናትና ሴቶች ጥቃቶች መፈጸማቸውን የገለጸ ሲሆን ከእነዚህ ጥቃቶች መካከል በፖሊስና በአቃቤ ህግ ተደራጅቶ ለፍርድ ቤቶች የቀረበ አንድም ገዳይ እንደሌለ ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ጊዜ ተናግረዋል፡፡
በእንዲህ ያለው ሁኔታ የፍርድ ቤት ሚና ለቀረበለት ጉዳይ ህጋዊና ፍትሃዊ ዳኝነት መስጠት ነው ያሉት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ የቤት ውስጥ ጥቃቶቹ መፈጸማቸውን የህክምና ማዕከላቱ ካረጋገጡ ፖሊስና አቃቤ ህግ እንዲሁም የተጠቂ ቤተሰቦችና ማህበረሰብ ጥቃቱ እንዳይባባስ አጥፊዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበው አስተማሪ ቅጣት እንዲጠልባቸው የማድረግ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባ ነበር፡፡ ይህ ባለመሆኑ በተለይም በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ዘርፍ በማህበረሰቡና በፖሊስ፤ በፖሊስና በዐቃቤ ህግ እንዲሁም በዐቃቤ ህግና በፍርድ ቤትና መካከል ያለው የቅብበሎሽ ስራ ክፍተት ያለው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ከሚያዙት ሰማንያ በመቶ የሚሆኑት ምንም አይነት የበሽታውን ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ!
#MoHE
በዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት መሰረት ሰማንያ በመቶ የሚሆኑት የኮሮና ቫይረስ ቢኖርባቸውም እንኳን የበሽታውን ምልክቶች ላያሳዩ ይችላሉ። ይህ ማለት ግን ቫይረሱን አያስተላልፉም ማለት አይደለም፡፡ ምልክቶቹን ባለማሳየታቸው በረካታ ሰዎችን የማግኘትና ወረርሽኙን የማስፋፋት እድላቸው ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሽታው ቀሪውን ሃያ በመቶ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ አምስት በመቶ የሚሆኑት የጽኑ ህሙማን ክትትል ያስፈልጋቸዋል፡፡የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወደ ሃገራችን ከገባበት ከመጋቢት 04 /2012 ዓ.ም ጀምሮ ዕለት-በዕለት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ከሁለት ሺህ አምስት መቶ (2500) በላይ ደርሰናል፡፡ በምናደርጋቸው መዘናጋቶች ቀላል የማይባል ክቡር የሰው ልጅ ህይወትም እያለፈ እንደሚገኝም ልብ ልንል ይገባል፡፡
በድንገት ህይወታቸው የሚያልፉ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ሲደረግላቸው በውስጣቸው ቫይረሱ እንዳለባቸው ይገለፃል ፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የበርካታ ሰዎች ጥያቄ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡በዚህም ዙሪያ በኮቪድ-19 አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የክሊኒካል ኬዝ-ቲም ዩኒት አስተባባሪ ዶክተር ሚኪያስ ተፈሪ ይህ ሊሆንበት የሚችልባቸውን ምክንያቶች ሲዘረዝሩ፤ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ በውስጣቸው እያለባቸው የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነታቸው ዝቅተኛ ሆኖ ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል፤ ሌሎቹ የኮሮና ቫይረስ በውስጣቸው ኖሮባቸው ምልክቶችን ሳያሳዩ በድንገት በሌሎች የጤና ችግሮች ምክንያት ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል ፣ በምርመራ ወቅት የሚወሰደው ናሙና እስኪደርስ ድረስ ቫይረሱ እንዳለባቸው ሳይታወቅ ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል ከዚህ በተጨማሪ በአጭር ጊዜ ውስጥ ድንገተኛ በሆነ ህመም መባባስ ምክንያት በበሽታው ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል ብለዋል፡፡
For full read👇👇👇👇
https://telegra.ph/80-of-Covid-19-Patients-doesnt-show-any-symptoms-says-WHO-06-10

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የህዝብና ቤት ቆጠራን አራዘመ፤ አዲስ አፈጉባኤና ምክትል አፈጉባኤም መረጠ!
ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን የጀመረው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛውን የህዝብና ቤት ቆጠራ አራዘመ።ምክር ቤቱ በስብሰባው ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ የተራዘመው የህዝብና ቤት ቆጠራ አሁንም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለህዝብ ጤናና ደህንነት ሲባል እንዲራዘም ወስኗል።የሚመለከታቸው አካላት የቫይረሱን ስርጭትና ጉዳት ገምግመው መቀነሱን ወይንም ጉዳት ማድረሱ ማቆሙን ማረጋገጥ ሲችሉ ቆጠራው በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲካሄድ ወስኗል።
Via FBC

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አዲስ አፈጉባኤና ምክትል አፈጉባኤ መረጠ!
ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን የጀመረው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቅርቡ በፈቃዳቸው ስልጣን በለቀቁት የምክር ቤቱ አፈጉባኤ በነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ምትክ አቶ አደም ፋራን አፈጉባኤ አድርጎ መርጧል።ቀደም ሲል የምክር ቤቱ ምክትል አፈጉባኤ የነበሩት አቶ መሐመድ ረሽድ ዛሬ በአፈጉባኤነት ከተመረጡት ጋር ከአንድ ክልል የተወከልን በመሆኑ ለሌሎች እድል መስጠት ይግባል በሚል በፈቃዳቸው ሀላፊነታቸውን ለቀዋል። ያንንም ተከትሎ በምትካቸው ወይዘሮ እፀገነት መንግስቱ በምክትል አፈጉባኤነት ተመርጠዋል።
Via Ethio FM

በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የዞን ምክር ቤቶች የቀረቡ የክልልነት ጥያቄዎችን ምላሽ ለማሰጠት የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበው የመነሻ ምክረ ሃሳብ በሌሎች ሃሳቦች ዳብሮ የመጨረሻ ውሳኔ በራሱ በኮሚቴው እንዲሰጥበት ሲል የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አሳልፏል።
የከፋ፣ የወላይታ፣ የዳውሮ፣ የከምባታ ጠምባሮ፣ የሃዲያ፣ የጋሞ፣ የጉራጌ፣ የጌዴኦ፣ የጎፋና ደቡብ ኦሞ ዞኖች የክልልነት ጥያቄ ማቅረባቸውን ኮሚቴው ገልጿል።በመሆኑም የክልልነት ጥያቄዎችን በተገቢው መንገድ ለማስተናገድ የጋራ መድረኮችን የማመቻቸት፣ የምክር ቤቱን አስፈጻሚ ከክልሎች አስፈጻሚዎች ጋር የማገናኘትና የማወያየት፣ ከዚህ ቀደም የተጠኑ ጥናቶችንና የሰላም አምባሳደሮችን ስራ እንዲሁም ህዝብን በማወያየት የመጨረሻ ውሳኔ ማሳለፍ የሚያስችል የውሳኔ ሃሳብ ቋሚ ኮሚቴው ይዞ እንዲቀርብ በምክር ቤቱ አብላጫ ድምጽ ተወስኗል።

58 የባህል ሕክምና ናሙናዎች በቅደም ተከተላቸው እየተሠሩ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
“በኮሮና ቫይረስ እና በሌሎች ወረርሽኞች ዙሪያ አገር-በቀል የባህል ሕክምና ዕውቀቶች ሊያመጡ የሚችሉት መፍትሔዎች” በሚል ርእስ የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትሮችና የዘርፉ ምሁራን ውይይት አድርገዋል፡፡በውይይቱ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው እንደገለፁት ከዚህ በፊት ወደ ምርምር ሂደት እንደገቡ የተገለጹት 58 የባህል ሕክምና ናሙናዎች በቅደም ተከተላቸው እየተሠሩ ነው፡፡ የቀረቡት የባህል ሕክምና ናሙናዎቹ የኮሮና ቫይረስን ቅድመ መከላከልና ከተያዙ በኋላ ለማከም የሚያስችሉ ተብለው በባለሙያዎች ተለይተዋል፡፡ መድኃኒቶቹ በማጨስ፣ በማጠን፣ በመቀባትና በመዋጥ በሚል እንደተከፈሉም ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡ የአገር በቀል ዕውቀትን መጠቀም ግዴታ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ወደፊትም አገሪቷ በባህል ሕክምና መታወቅ መቻል እንዳለባት አመልክተዋል፡፡
Via AMMA

በዛሬው እለት በሶማሌ ክልል ኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 57 ሰዎች ውስጥ 55ቱ ከደዋሌ ለይቶ ማቆያ የተገኙ ሲሆኑ ሁሉም የጅቡቲ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።አንድ ሰው ከጅግጅጋ ዩንቨርስቲ ለይቶ ማቆያ ሲሆን ሌላ አንድ ሰው ደግሞ ከጅግጅጋ ከተማ ነው የተገኘው።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ኢትዮጵያና በአብዛኛው ደቡብ ሱዳን በቀጣዮቹ 10 ቀናት ከባድ ዝናብ ይጥላል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን /ኢጋድ/ አስታወቀ።ከመደበኛ ያለፈ ዝናብ በተወሰኑ የምስራቅ አፍሪካ አካባቢዎች ታይቶ የማይታወቅ ጎርፍ ሊያስከትል ይችላልም ብሏል።ኢጋድ ከሰኔ 4 እስከ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ባሉት 10 ቀናት በምስራቅ አፍሪካ ስለሚኖረው የአየር ሁኔታ ትንበያ አውጥቷል።
Via ICPAC/ETV
@YeneTube @FikerAssefa
Via ICPAC/ETV
@YeneTube @FikerAssefa