YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 86 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።የ7 ሰዎች ህይወትም አልፏል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6092 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ ስድስት (86) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2020 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ የ7 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፣ ባጠቃላይህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 27 ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ካለፈ 7 ሰዎች ትናንት ምሽት የሁለቱን ሞት መዘገባችን ታወሳል።እነሱን ጨምሮ የሰባቱ ሟቾች ሁኔታ

➡️በህክምና ላይ የነበረች የ34 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

➡️በህክምና ላይ የነበረ የ56 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

➡️በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት የ55 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

➡️በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት የ65 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

➡️በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት የ33 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

➡️በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት የ26 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

➡️በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት የ36 አመት ወንድ ፣ ከኦሮሚያ ክልል

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 27 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 86 ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው፣ በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(51) ሴት(35) ናቸው!

➡️ዕድሜያቸው ከ7-82 አመት የሆኑ

➡️ተጨማሪ 46 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 1 ሰው ከአማራ ክልል፣ 3 ከኦሮሚያ ክልል 13 ደግሞ ከሶማሌ ክልል ከህመማቸው ሲያገግሙ በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 344 ደርሷል።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(66)፣ ከኦሮሚያ ክልል(7)፣ከትግራይ ክልል(7)፣ አማራ ክልል(1)፣ ከደቡብ ክልል(4)፣ ድሬዳዋ(1) ፣በኮሮና የተያዙ በድምር 86 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2020 ደርሷል።

➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ ወደ 32 ከፍ ብሏል።

➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 7 ሞት የተመዘገበ ሲሆን ጠቅላላ የሟቾች ቁጥር 27 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ደቡብ ክልል አራት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን አራቱም በሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ላይ ይገኛሉ። እድሚያቸው ከ18 -41 መሆኑም በመግለጫው ላይ ተመልክተናል።
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1ሺህ500 በልጧል፡፡

በዛሬው እለት የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 86 ሰዎች ውስጥ 66 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ በአጠቃላይም በመዲናዋ 1ሺህ 510 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፦

አዲስ ከተማ 18፤
ልደታ 5፤
ጉለሌ 6፤
ኮልፌ ቀራንዮ 5፤
ቦሌ 9 ፤
አራዳ 4፤
የካ 1፤
ንፋስ ስልክ ላፍቶ 3፤
አቃቂ ቃሊቲ 3 ፤
ቂርቆስ 6 እና የ6 ሰዎች ክፍለ ከተማ በመጣራት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የደቡብ ክልልን በአዲስ መልክ ለማዋቀር በተዘጋጀ ምክረ ሀሳብ ላይ ከክልሉ አመራሮች ጋር በነገው ዕለት ሊወያዩ ነው።በውይይቱ ላይ የክልሉ የዞን እና ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪዎች ይሳተፋሉ ተብሏል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ5000 በልጧል። እስካሁን፣

➡️ሁሉም የእፍሪካ ህብረት አባላገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።

➡️184,333 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

➡️5071 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።

➡️81,780 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

ምንጭ:CDC Africa
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 119 መድረሱን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ።

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 239 የላቦራቶሪ ምርመራ አንድ ሰው የኮሮናቫይረስ ተገኝቶበታል።ቫይረሱ የተገኘበት የ28 ዓመት ወጣት በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ ማዕከል ክትትል ሲደረግለት የነበረ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል።ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በክልሉ ለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከላት የሚገኙት ሁሉም ሰዎች በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸውን፣ ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል የገባ ታማሚም አለመኖሩን ቢሮው በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል።በአማራ ክልል እስከ ዛሬ ግንቦት 30/2012 ዓ.ም ድረስ ለ3 ሺህ 31 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎ በ119 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ታውቋል። ከእነዚህ መካከል 23 ሰዎች አገግመዋል፤ እስካሁን በክልሉ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወቱ ያለፈ ሰው አለመኖሩንም የጤና ቢሮው መረጃ ያመላክታል።

እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ከምዕራብ ጎንደር ዞን (97) (ይህ አካባቢ ከሱዳን የሚገቡ ኢትዮጵያውያን በለይቶ ማቆያ የሚቆዩበት ነው)፣ ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን (አንድ)፣ ከጎንደር ከተማ (ሦስት)፣ ከደሴ (ሁለት)፣ ከባሕር ዳር (አራት)፣ ከአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር (ሦስት)፣ ከሰሜን ሸዋ ዞን (ሁለት)፣ ከሰሜን ወሎ ዞን (አራት)፣ ከደቡብ ጎንደር ዞን (አንድ)፣ ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር (አንድ) እና ከምሥራቅ ጎጃም ዞን (አንድ ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ) መሆኑ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ደግሞ እስከዛሬ ለ142 ሺህ 960 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸዋል፤ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርም 2 ሺህ 20 ደርሷል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 1 ሺህ 647 በሕክምና ላይ ይገኛሉ፤ 27 ሕይወታቸው አልፏል፤ 344 ደግሞ አገግመዋል፡፡ 32 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ክፍል ውስጥ እንደሚገኙም ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
#Scamalert

ከ50 እስከ 100 ዶላር ታገኛላችሁ በማለት በቴሌግራም እየተሰራጨ የሚገኘው ሊንክ ፍጹም ውሸት ነው። እንዲሁም ዌብሳይቱ ላይ ገብታችሁ ስልክ ቁጥራችሁን ስታስገብ ቴሌግራም የላከላችሁን ቁጥር አስገብ ይላሉ በምታስገቡበት ወቅት አካውንታችሁን የውስድባችኃል።

እውነተኛነታቸው የተረጋገጡ በይነ መረብን በመጠቀም ስራ መስራት የሚያስችሉ ገፆች ➡️ www.freelancer.com | www.upwork.com ታዋቂዎቹ እነዚህ ናቸው እኚህን በመጠቀም መስራት ይችላሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from HEY Online Market
Playstation 4PRO (Slim)
With 2 controllers
1000 GB storage
With FIFA 2019 CD

Price 23,999 Birr

Contact us :
0953964175
0925927457 @eBRO4
0910695100
@heyonlinemarket
Forwarded from Kídus
⚜️SHEBA - ሺባ⚜️

📞 በ 0941158969 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን

ጥራት ያለው ጌጣጌጥ 💎በተመጣጣኝ ዋጋ ከኩባንያችን (ሺባ) ይግዙ ይህንን::

⚠️(ሺባ) የተመሰረተበትን አንደኛ አመት እያከበርን ስለሆነ ‼️ነፃ ‼️ሰዐት ለማግኘት ከዌብ ሳይታችን ላይ ማንኛዉንም እቃ ይግዙ፡

👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼

Website - www.shebasluxury.com

Telegram - https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFfS1CHMcuedhCLPBQ

Contact Admin @ki_d_us

📞 በ 0941158969 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን🏍
በወምበራ ወረዳ ከ155 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰርተው የተጠናቀቁ 2 የመንገድ ፕሮጀክቶች በክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በተገኙበት ተመርቀው ለትራፊክ ክፍት ሆኑ፡፡

በወምበራ ወረዳ ከደብረዘይት- ሳንቂ- መልካን እና ከገሰንገሳ - ወግዲ የሚያገናኙ 2 የመንገድ ፕሮጀክቶች የበየኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል፡፡ለትራፊክ ክፍት ከተደረጉት መንገዶች ከገሰንገሳ - ወግዲ ቀበሌ የሚያገናኘው መንገድ የ11 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፣ ደብረዘይት - ሳንቂ - መልካን ቀበሌዎችን የሚያገናኘው የመንገድ ፕሮጀክት ደግሞ 33 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን መሆኑም በምርቃቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

Via BGMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ኒው ዚላንድ የእንቅስቃሴ ገደቡን ሙሉ በሙሉ አነሳች!

ኒው ዚላንድ የመጨረሻውን የእንቅስቃሴ ገደብ እኩለ ሌሊት ላይ ማንሳቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን አስታውቀዋል።ይህ ማለት በአገሪቱ የነበሩ ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴን የሚገድቡ መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ ይነሳሉ ማለት ነው። ነገር ግን ድንበሮች ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ተፅእኖ ለመቋቋም በ54 ማእከላት ለ17 ሺህ 500 ለሚሆኑ ህሙማን ማከሚያ ስፍራ ተዘጋጅቷል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ፣ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ባነሷቸው ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማብራሪያ እየሰጡ ነው።ኮሮናን አስመልክቶ የጤና ተቋማት ዝግጅት ላይ የተሰሩ ስራዎችን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲያብራሩ:

➡️እስካሁን ያለው በቫይረሱ የተያዘ ሰዎች ቁጥር 2020 ቢሆንም 17 ሺህ 500 ለሚሆኑ በቫይረሱ የተጠቁ ዜጎችን ለማከም የሚችል 54 የማከሚያ ተቋማት ተዘጋጅተዋል

➡️በአገሪቱ የበሽታው ምልክት ለታየባቸው 30 ሺህ ገደማ የሚሆኑ ሰዎች እስኪ መረመሩ ድረስ ለይቶ ማቆያ ስፍራ ተዘጋጅቷል

➡️ከውጭ ለሚመጡ ዜጎች በኳራንቲን ለይቶ ማቆያ 45 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች የሚሆን ስፍራ ተዘጋጅቷል

➡️በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የላብራቶሪ አቅም መገንባት ተችሏል፣ ለሁሉም ክልሎችም ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ ተመድቧል፣

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በግንቦት ወር 135 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ።

በተጨማሪም 348 የቱርክ ስሪት ሽጉጥ እና 300 ጥይት መያዙን አስታውቀዋል። የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በሁሉም የሀገሪቱ የጉምሩክ ጣቢያዎች በተደረገው ጥብቅ ክትትልና ፍተሻ መያዛቸውን ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
<<የማክሮኢኮኖሚ ኮሚቴው አባላት የውጪ ግብይት እንዲጨምር ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡ ባለፈው ዓመት የውጪ ግብይት በ13 በመቶ አድጓል፡፡ ባለፉት አስር ወራት፣ የ667 ሚሊየን ዶላር የቡና ሽያጭ በመካሄዱ ብቻ 16 በመቶ ዕድገት ተመዝግቧል፡፡የሥጋ ምርት የውጪ ገበያም በ41 ሚሊየን ዶላር ሽያጭ አማካኝነት በ21 በመቶ አድጓል፡፡ ቀጣዩ ሥራ ይህንን ዕድገት ማስጠበቅ ነው፡፡ >>

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከሰጡት ማብራሪያ

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ባለፉት 3 ቀናት ማለትም ከ28/09/2012-30/09/2012 ዓ.ም በደረሰ የትራፊክ አደጋ፦

➡️ ደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ አንድ ግለሰብ በጭነት መኪና (ሲኖ) ተገጭቶ ህይወቱ አልፏል።
➡️ ምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ ISUZU (መለስተኛ) የህዝብ ማመላለሻ መኪና አንድ ሰው ገጭቶ ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል።
➡️ ምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ አንድ ሰው በFSR (መለስተኛ) የህዝብ ማመላለሻ መኪና ተገጭቶ ህይወቱ አልፏል።
➡️ በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ የጭነት (ሲኖ) መኪና አንድ ሰው ገጭቶ ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል።
➡️ ደቡብ ጎንደር ዞን ንፋስ መውጫ ከተማ በመኪና ግጭት የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

በአጠቃላይ በሶስት ቀን ውስጥ አምስት የትራፊክ አደጋ ደርሶ የአምስት ሰው ህይወት አልፏል።

ምንጭ: የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
@YeneTube @FikerAssefa
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በይፋ ተጀመረ።

መርሀግብሩ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አርሶአደሮች መንደር ላይ ነው የተጀመረው።ኢ/ር ታከለ ኡማ ከግብርና ሚንስትሩ ዑመር ሁሴን ጋር በጋራ በመሆን መርሀግብሩን አስጀምረዋል።

Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
ምርጫው እንዲራዘም ከማይፈልጎት ፖርዎች ውስጥ ብልጽግና ቀዳሚ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አሕመድ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ሰተዋል፡፡ዶ/ር አብይ አህመድ እንዳሉት ብልጽግና ፖርቲ ለምርጫው ከፍተኛ ዝግጅት ሲያርግ እንደነበረ አስታውሰዋል።የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ምርጫ ቦርድ ከስራው አስቸጋሪ ስለሚሆን ምርጫውን ማድረግ እንደማይችል ሲናገር እንደማይቀበሉት በወቅቱ ለምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ጋር ሀይል በተቀላቀለበት ቃላት መመላለሳቸውን ተናግረዋል፡፡ምርጫው በምንም መልኩ እንደማይቀየር ሳስረዳቸው እንዲያ ከሆነ እና መንግስት በስራዬ ጣልቃ ለመግባት ከሞከረ ስራዬን በፍቃዴ እለቃለሁ ማለታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብ ተናግረዋል፡፡

ኃላ ላይም ከምክር ቤቱ አፈጉባኤ ጋር በመነጋገር ነገሩን መቀበላቸውን አስታውሰዋል፡፡በተቃዋሚ ፖርቲዎች እየቀረበ ያለው ወቀሳ ተቀባይነት እንደሌለው የሚናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምስት ቢሊየን ችግኝ መትከል ከተቻለ ምርጫው መቅረቱ አግባብ እንደሌለው ለማስረዳት መሞከሩን ተናግረው ይህ ግን የተለየ መሆኑን ያስረዳሉ።
ችግኙን በተለያዩ ጊዜያትና የሰው መጠን ማስኬድ ይቻላል ምርጫ ግን እንደዚያ አይደለም ብለዋል፡፡
ይልቅ አሁንም እኚህ ፖርቲዎች ወገባቸውን ጠበቅ ቢያደርጉ ይሻላል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa