የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሰራተኞቹን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ አዲስ አደረጃጀት እያዘጋጀ ነው። በስራቸው ያለመቀጠል ስጋት ያደረባቸው ሰራተኞቹ ለተቃውሞ እየተዘጋጁ ነው።
የመከላከያ ምርቶችን ከሚያመርቱ ፋብሪካዎች ተለይቶ ዘጠኝ ፈብሪካዎችን በስሩ ይዞ የተደራጀው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በስሩ ዘጠኝ ሺህ የሚሆኑ ሰራተኞችን አቅፎ ይዟል። ሆኖም ኮርፖሬሽኑ አዲስ ያወጣው የሰራተኛ ፍላጎት መዋቅር ብዙዎችን ከስራ ገበታ የሚያፈናቅል ነው የሚል ቅሬታ ቀርቦበታል።ዋዜማ ራዲዮ ያገኘችው በኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ለኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር የገባ የቅሬታ ደብዳቤ አዲሱ የኮርፖሬሽኑ የሰራተኛ ፍላጎት መዋቅር ፣ የሰራተኛውን ጥቅምና መብትን የማያስከብር ፣ ነባራዊ ሁኔታን ያላገናዘበ ፣ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁን ያልተከተለ እንዲሁም መነሻውና ግቡ ግልጽ ያልሆነ ነው በሚል ትችት ያቀርባል።
የሰራተኞቹ ደብዳቤ በተጨማሪም የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ቀድሞ በነበሩ አመራሮች ስግብግብነት የተበዘበዘ እንዲሁም መጣ በተባለው ለውጥ ተስፋ ያደረገ ቢሆንም አሁን የተዘጋጀው መዋቅር እንዳሳዘናቸው ይገልጻል። ይህም ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ችግር ውስጥ ወድቃ ነባር ሰራተኞችን እንደገና ፈትኖ ለመቅጠር ያቀደው እቅድ ተገቢ እንዳይደለም ያብራራል። የኮርፖሬሽኑ ችግርና ለኪሳራ ሲዳርገው የቆየው አሁን ያለው የሰራተኛ ብዛት ሳይሆን የአመራር ድክመት በመሆኑ አካሄዱ እንዲስተካከልም ሰራተኞች በደብዳቤያቸው ጠይቀዋል።
ኮርፖሬሽኑ በአዲሱ መዋቅር ከስራ ውጭ የሚሆኑ ሰራተኞች እንዲደራጁ አደርጋለሁ ሲል ለሰራተኞቹ ገልጿል።ነገር ግን በምን የስራ ዘርፍ ለማሰማራት እንደሚያደራጃቸውና ምን አይነት ዝግጅትስ እንዳደረገ አልገለጸም።አሁን ላይ ኮርፖሬሽኑ ያዘጋጀው ከግማሽ በላይ የሆኑ ሰራተኞቹን ከስራ ገበታቸው የሚያፈናቅላቸው መዋቅር ከአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ጋር የሚቃረን ከመሆኑም በላይ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ወደ ችግር ውስጥ እየገባ በርካታ ቁጥር ያለውን ሰራተኛ ለመቀነስ ማሰቡም ትችት እየቀረበበት ነው።
Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 129 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,500 የላብራቶሪ ምርመራ 129 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1934 ደርሷል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,500 የላብራቶሪ ምርመራ 129 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1934 ደርሷል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 20 ደርሷል፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የአንድ የ80 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ ህይወት አልፏል። ሟች ወደ ሆስፒታል ለሌላ ህክምና በመጡ በአንድ ሰአት ውስጥ ነው ህይወታቸው ያለፈው። ከዛ በኋላ በተደረገ የአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 20 ደርሷል፡፡

ዛሬ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 129 ሰዎች አምስቱ የውጭ ዜጎች ሲሆኑ፣ 124ቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው፣ በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(75) ሴት(54) ናቸው!
➡️ዕድሜያቸው ከ1-90 አመት የሆኑ
➡️ተጨማሪ 10 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 6 ከአፋር ክልል 1 ደግሞ ከሶማሌ ክልል ከህመማቸው ሲያገግሙ በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 281 ደርሷል።
➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(101)፣ ከኦሮሚያ ክልል(5)፣ከትግራይ ክልል(5)፣ አማራ ክልል(10)፣ ከሶማሌ ክልል(6)፣ ከሀረሪ ክልል(1) እና በጋምቤላ ክልል የመጀመርያው ተጠቂ(1) ተገኝቷል። በኮሮና የተያዙ በድምር 129 ሰዎች ናቸው።
➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,934 ደርሷል።
➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ ወደ 27 ከፍ ብሏል።
➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 1 ሞት የተመዘገበ ሲሆን ጠቅላላ የሟቾች ቁጥር 20 ደርሷል።

የትግራይ ክልል የኮሮና ቫይረስ መከላከል ኮማንድ ፖስት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ። በውሳኔውም:-
ከከተማ ወደ ከተማ ከዞን ወደ ዞን መንቀሳቀስ ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ከሰኔ 01 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተነስቷል።የሃይማኖት ተቋማት እንደረሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ የተጣሉ ገደቦችን በማላላት አገልግሎት እንዲሰጡ ተፈቅዷል።
Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
ከከተማ ወደ ከተማ ከዞን ወደ ዞን መንቀሳቀስ ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ከሰኔ 01 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተነስቷል።የሃይማኖት ተቋማት እንደረሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ የተጣሉ ገደቦችን በማላላት አገልግሎት እንዲሰጡ ተፈቅዷል።
Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
የ2021 DV ሎተሪ ለሞላችሁ ዛሬ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ በ https://dvlottery.state.gov/ በመግባት ውጤት ማየት እንደሚቻል በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኢምባሲ በፌስ ቡክ ገፁ አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2013 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት 476 ቢሊየን ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ!
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2013 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት 476 ቢሊየን ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ። ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ባካሄደው 84ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በ2013 በጀት ዓመት በፌዴራል መንግሥት ረቂቅ በጀት ላይ ነው፡፡

135 ዜጎቻችን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ!
ዛሬ ግንቦት 29 ቀን 2012 ዓም 135 ኢትዮጵየዊያን ዜጎቻችን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።ዜጎቻችን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፈያ ሲደርሱ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎች በቦታው ተገኘተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የዛሬዎቹን ጨምሮ በሳምንቱ ውስጥ ከሳኡዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የተመለሱ ዜጎቻችን ቁጥር 389 ደርሷል።
Via Spokesperson of MoFA

በአዲስ አበባ ከተማ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 101 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው!
በአዲስ አበባ ከተማ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አንድ (101) ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።በአጠቃላይ በከተማዋ የኮሮናቫይረስ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አንድ ሺህ አራት መቶ አርባ አራት (1444) መድረሱን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ መረጃ አመልክቷል።
ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፦
አዲስ ከተማ 17፤
ልደታ 3፤
ጉለሌ 19፤
ኮልፌ ቀራንዮ 8፤
ቦሌ 8 ፤
አራዳ 5፤
የካ 11፤
ንፋስ ስልክ ላፍቶ 14፤
አቃቂ ቃሊቲ 7 ፤
ቂርቆስ 4 እና የ5 ሰዎች ክፍለ ከተማ በመጣራት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡፡፡

👍1
በአማራ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረው ችግር ለመፍታት ከወር በፊት የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት 10,526 ቀስቶችና ድምጽ አልባ መሣሪያዎችን፣ 80 የጦር መሣሪያዎችን፣ 859 ጥይት በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።
Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የጉና-ጣና የተቀናጀ የመስክ ምርምር ማዕከል 2,095 ሰራተኞችን በማስተባበር ከግንቦት 24/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት በጣና ላይ የተንሰራፋው የእምቦጭ አረም የማስወገድ ስራ መከወኑን ገለጸ።
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የጉና-ጣና የተቀናጀ የመስክ ምርምር ማዕከል 2,095 ሰራተኞችን በማስተባበር ከግንቦት 24/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት በጣና ላይ የተንሰራፋው የእምቦጭ አረም የማስወገድ ስራ መከወኑን ገለጸ። Via Ethiopia Live Updates @YeneTube @FikerAssefa
ከእንቦጭ ጋር በተያያዘ ሌላ ዜና ፣ በውጭ ሀገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተገዝቶ የመጣ ማሽን እምቦጭ አረምን ለማስወገድ ስለማይረዳ ላለፉት 2 አመታት በጎርጎራ ወደብ ያለስራ መቀመጡን የጣና ሀይቅ እና የሌሎች ውሃ አካላት ልማትና ጥበቃ ኤጀንሲ ዳሬክተር ዶ/ር አያሌው ወንዴ ተናግረዋል።ከእስራኤል ሀገር የተገዛው ማሽን የፕላስቲክ ኮዳዎችንና ቅጠላቅጠሎችን ለመሰብሰብ የተሰራ መሆኑን የገለጹት ዳሬክተሩ፣ ማሽኑን አለመረከባቸውንም ገልጸዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
አሳዛኝ ዜና!!!
በኮቪድ 19 ተይዛ ልጇን የተገላገለችው እናት አርፋለች!
በሃገራችን ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 22 የደረሰ ሲሆን በበሽታው ተጠቅተው በየካ አጠቃላይ ሆስፒታል ነብሰ ጡር ሆና የገባችው በዚሁ ሆስፒታል የተገላገለችው እናት ከሰአታት በፊት ህይወቷ ማለፉን ጋዜጠኛ ታሪኩ ዘውዱ በገፁ አጋርቷል። ወላዷ እናት ልጆን አቅፋ ለመሳምና ጡቷን ለማጥባት ሳትታደል ህይወቷ ሊያልፍ የቻለ ሲሆን በተጨማሪም ሌላ ሞት በዚሁ ሆስፒታል መከሰቱን ጠቁሞ ሁለተኛው ሟች ወንድ እንደሆነና የሁለቱም ህልፈተ ህይወትም ከሰአታት በፊት ከምሽቱ 2 ሰዓት በየካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ነው ብሏል።ምሽቱን ህይወቷ እንዳለፈ ለተሰማው ወላድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በሆስፒታሉ ተገኝተው ስጦታ አበርክተውላት እንደነበር የሚታወስ ነው።
Via Sheger Times Magazine

#ዴሊቨሪ_ሀዋሳ_እሁድን_በቤቶ_ይቆዩ
ከታች ከተዘረዘሩት ሆቴል ፣ ካፌ እና ሬስቶራንት እንዲሁም ሱፐር ማርኬቶች የሚፈልጉትን ምግብ እና መጠጥ እንዲሁም የሱፐር ማኬት እቃዎችን ቢያዙን በሀያ ደቂቃ ውስጥ ያሉበት ቦታ እናደርሳለ።
✅ኬር አውድ ኢ.ተ ሆቴል ✅ ሌዊ ሆቴል
✅ሮም 1960 ✅ #ሴፍ_ዌይ ሱፐር ማርኬት
✅ሌዊ ሆቴል ፒያሳ ✅አሜሪካን በርገር
✅ታይም ካፌ ✅ ለንደን ካፌ
✅ሲዝን ሱፐር ማርኬት ✅ሌዊ ሆቴል መንኃሪያ
✅ሴፍላንድ ካፌ ✅ዶልቼ ቪታ
✅ሀበሻ ሆቴል ✅ ቡካ ባር እና ሬስቶራንት
ለማዘዝ ይደውሉ +251927797918
+251927797918
Join - t.me/deliveryhawassa

በኮሮና ቫይረስ የተያዙ የጤና ተቋም ስራተኛች ቁጥር 97 ደርሷል።
በኢትዮጲያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ የጤና ተቋም ስራተኛች ቁጥር 97 የደረሰ ሲሆን በአብዛኛዎቹ በሁለት ሳምንት ውስጥ የተያዙ ናቸው፡፡በኢትዮጲያ የኮረና ቫይረስ ከገባበት መጋቢት ወር በኃላ ስርጭቱ ባለፉት ሁለት ሳምታት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑንና በቫይረሱ የሚያዙ የጤና ተቋም ሰራተኛች ቁጥርም እያሻቀበ እንደሆነ የጤን ሚንስትሯ ሊያ ታደሰ ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ተናግረዋል።
ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ 81 የሚሆኑ የጤና ተቋም ባለሙያዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ይፋ ከተደረገው መረጃ ለመረዳት ችለናል፡፡ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል 91 የሚሆኑት በአዲስ አበባ የሚገኙ ናቸው፡፡ በቫይረሱ ከተያዙት የጤና ተቋም ሰራኞች መካከል 55 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡አብዛኞቹ ሰራተኛች ምንም አይነት የበሽታው ምልክት ያልታየባቸው ሲሆኑ ነገር ግን ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በምርመራ ተረጋግጧል፡፡
እስካሁን ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ንክኪ ነበራቸው ተብለው የተለዩ እና እራሳቸውን አግልለው የነበሩ የጤና ባለሙያውች ቁጥር 2340 ደርሷል ከነዚህ መካከል 1721 የሚሆኑት ተጋላጭ የነበሩት መጋቢት ወር ላይ ነው፡፡የጤና ባለሙያዎቹ በዘውዲቱ ሆስፒታል ክትትል ሲያደርጉ የቆዩ በሆንም አሁን ቁጥራቸው እየጨመረ ስለመጣ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተዘዋወሩ ነው፡፡ለህክምና ተቋማት የሚያስፈልጉ ራስን የመከላከያ ቁሳቁሶች እጥረት እንዳለ ሆኖ የአጠቃቀም እና የጥንቃቄ ጉድለቶች መስተዋላቸውንም ከተደረገው ሙያዊ ውይይት ለመገንዘብ ችለናል፡፡
ግንቦት 21 ቀን 2012 ከኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የወጣ ደብዳቤ ምን ያህል የጤና ለሙያዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ እንደሆኑ፤ በቫይረሱ እንደተጠቁ ወደ ለይቶ ማቆያ እንደገቡ አህዛዊ መረጃ ከመንግስት እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር፡፡ይህ ጥያቄው የተነሳው በበሽታው የሚያዙ የጤና ባለሙያውች ቁጥር እየጨመረ ስለመጣ ክፍተቱ የቱ ጋር በግልፅ እንዳለ ለመረዳት እና የስራ ላይ አደጋን ለመቀነስ የሚቻልበትን መንገድ ለማፈላለግ ያለመ መሆኑን የኢትዮጲያ ሕክምና ማህበር ያብራራል።
ምንጭ: ዋዜማ ራዲዮ

የጤና ተቋማት ሠራተኞቻቸውን ከኮሮናቫይረስ ተጋላጭነት የሚከላከል አሠራር እንዲዘረጉ ጤና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ወረርሽኙን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የኅብረተሰቡን ጤና ለመታደግ መተኪያ የሌለውን ሕይወታቸውን አጋልጠው በግንባር ቀደምነት እየሰጡ ላለው ሙያዊ አገልግሎት ጤና ሚኒስቴር ምሥጋና አቅርቧል፡፡የጤና ተቋማትም ሠራተኞቻቸው ለወረርሽኙ እንዳይጋለጡ የሚያደርግ ጠንካራ የብክለት መከላከልና መቆጣጠር ሥርዓት መተግበር የግድ እንደሚሆንባቸው ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡ለዚህም ከመግቢያ በር ጀምሮ የልየታ ሥራውን ማጠናከር፣ የተገልጋዮችና የሠራተኞች እንቅስቃሴ ደግሞ ብክለትና “ኢንፌክሽን” መከላከልን መሠረት ባደረገ እና ርቀትን በጠበቀ መልኩ እንዲሆን የሚያስችል የውስጥ “ዲዛይን” ማስተካከያ ሊያደርጉ እንደሚገባ ነው ጤና ሚኒስቴር ያሳሰበው፡፡
ከዚህ ባለፈም አስፈላጊውን የግል የመከላከያ ቁሳቁስ ለሠራተኞቻቸው በማቅረብ፣ የዕውቀትና ክህሎት ክፍተቶችን በመለየትና በመሙላት ሠራተኞቻቸው ለኮሮናቫይረስ እንዳይጋለጡ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም አስረድቷል፡፡ በየደረጃው ያሉ የጤና ባለሙያዎና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችም አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜ ከሕሙማን፣ ከሥራ ባልደረቦቻቸው እና ከሌሎች ሰዎች ጋር በሚኖራቸው ቅርርብ ሳይዘናጉ በሁሉም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ ሁሉ እንዲጠነቀቁ ጤና ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡
Via AMMA

በመዲናዋ 2 ዘመናዊ ሆስፒታሎች ሊገነቡ ነው!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሆስፒታሎችን ቁጥር ለመጨመር 2 ዘመናዊ ሆስፒታሎች ሊገነቡ ነው።አሁን ላይ በከተማዋ የታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣትና ያሉት ሆስፒታሎች የማስተናገድ አቅማቸው ባለመመጣጠኑ የሆስፒታሎችን ቁጥር መጨመር አስፈልጓል።በከተማዋ 6 የመንግስት ሆስፒታሎች የሚገኙ ሲሆን የማስተናገድ አቅማቸውም 1557 ታካሚዎችን ብቻ ነው።ይህንን ቁጥር ከፍ ለማድረግ እና አገልግሎቱን ለማስፋትም በንፍስልክ ላፋቶ እና በኮልፌ ቀራንዮ ክፋለ ከተሞች 2 ሆስፒታሎች ይገነባሉ ተብሏል።ሁለቱ ሆስፒታሎች ሲጠናቀቁም 940 ታካሚዎችን የማስተናገድ አቅም ይኖራቸዋል ሲል አዲስ ቲቪ ዘግቧል። በሆስፒታሎቹ ዲዛይን ላይም የጤና ሚንስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ ኣካላት እየተወያዩበት ነው።
Via AMN

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ነገ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ይሰጣሉ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዝብ ግንኙነት ክፍል እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ነገ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጉዳዮች ማብራሪያ ይሰጣሉ።ምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባውን በነገው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዳራሽ እንደሚያካሂድ የገለጸ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች፣ በመንግስት ስራ አፈጻጸም እና በሌሎች ከምክር ቤቱ አባላት በሚነሱላቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ምላሽ ይሰጣሉ ተብሏል።
Via Ethio FM

መንግሥት ሲሚንቶ እንዲያከፋፍሉ በመረጣቸው ድርጅቶች ላይ ቅሬታ ቀረበ!
የናይጄሪያው ባለሀብት ንብረት የሆነው ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካና የሳዑዲ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼክ መሐመድ አል አሙዲ ንብረት የሆነው ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ በተመሳሳይ ወቅት ለዕድሳት በሚል ምርት ማምረት ማቆማቸውን ምክንያት በማድረግ፣ ሲሚንቶ እንዲያከፋፍሉ የተመረጡ ድርጅቶችን መንግሥት መምረጡ ቅሬት አስነሳ፡፡የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከአንድ ሳምንት በፊት ባስተላለፊው ውሳኔ ነጋዴዎች ቅሬታ በማቅረባቸው፣ ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም. አምራቾችና ድርጅቶች ማለትም የአምባሰል የንግድ ሥራዎች ድርጅት፣ የወንዶ ኢንቨስትመንት ኩባንያ፣ ቢፍቱ አዱኛ ቢዝነስ ሼር ኩባንያ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንና የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ተወካዮች በንግድና ኢንዱስትሪ በሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ሰብሳቢነት ሲከራከሩ መዋላቸውን የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ሚኒስቴሩ በዋናነት አከፋፋዮቹ የተመረጡት ድርጅቶች እንዲሆኑ ውሳኔ ላይ ያደረሰው፣ ዳንጎቴና ደርባ ለዕድሳት ብለው ምርት በማቆማቸው በተፈጠረ የሲሚንቶ እጥረትና የዋጋ ንረት ምክንያት መሆኑም ታውቋል፡፡አብዛኛውን የሲሚንቶ ምርት የሚሸፍኑት ዳንጎቴና ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርት ማምረት በማቆማቸው፣ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች ያላቸውን ምርት በመያዝና እጥረት እንዲፈጠር በማድረግ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ማድረጋቸው መንግሥት የራሱን ውሳኔ እንዲወስን እንዳነሳሳው ታውቋል፡፡ሌሎቹ የሲሚንቶ ፋብሪካ ባለቤቶች ለሚኒስትሩ ባቀረቡት አቤቱታ እንደገለጹት፣ እነሱ ለሚያመርቱት ሲሚንቶ በኩንታል የተወሰነላቸውን ትርፍ ከማግኘትና ለአከፋፋዮች ከመስጠት ባለፈ ምንም ያደረጉት ነገር የለም፡፡የቫት ተመዝጋቢ በመሆናቸው ሁሉም አሠራራቸው የሚታወቅና በኦዲተር የሚረጋገጥ መሆኑን በማስረዳት፣ ለምን ግዳጅ ውስጥ እንዲገቡ እንደተፈለገ ማብራሪያ ጠይቀዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ነጋዴዎቹንና እንዲያከፋፍሉ የተመረጡትን ድርጅቶች ተወካዮች ካወያየ በኋላ፣ 12 አከፋፋዮችን በመጨመር ከአምስቱ ድርጅቶች ጋር እኩል ድርሻ ኖሯቸው እንዲያከፋፍሉ ውሳኔ ላይ መደረሱም ታውቋል።ድርጅቶቹ በየዕለቱ 340,280 ኩንታል ሲሚንቶ ከፋብሪካዎቹ በመረከብ እንዲያከፋፍሉም ተነግሯቸዋል፡፡ ድርጅቶቹ ምርቱን እንደሚያከፋፍሉ ተገልጿል፡፡ መንግሥት በሚወስነው ዋጋ ብቻ እንዲያከፋፍሉ፣ ቸርቻሪዎች ደግሞ ከአከፋፋዮች በተረከቡት ዋጋ ላይ በኩንታል 20 ብር ብቻ ትርፍ በማግኘት እንዲያከፋፍሉ፣ መንግሥት ከወሰነው በላይ ሲሸጡ ከተገኙ ግን ዕርምጃ እንደሚወሰድባቸው ማስጠንቀቁ ታውቋል፡፡
Via Reporter