YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from SHEBA - ሺባ
Get this watches for ‼️free‼️you just have to buy something using our website. Special deal for our anniversary don’t miss out

www.shebasluxury.com

ሺባ የተመሰረተበትን አንደኛ አመት እያከበርን ስለሆነ ‼️ነፃ ‼️ሰዐት ለማግኘት ከዌብ ሳይታችን ላይ ማንኛዉንም እቃ ይግዙ፡፡

www.shebasluxury.com

For more information call 0941158969
Forwarded from HEY Online Market
Playstation 4PRO (Slim)
With 2 controllers
1000 GB storage
With FIFA 2019 CD

Price 23,999 Birr

Contact us :
0953964175
0925927457 @eBRO4
0910695100
@heyonlinemarket
የምዕራብ ጎንደር ዞን ሦስት ወረዳዎች 17 ቀበሌዎችና አንድ ከተማ አስተዳደር ከሱዳን ጋር የሚዋሰኑ ሲሆን በየዕለቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ድንበሩን በማቋረጥ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ። በዚህ ምክንያትም አካባቢው ከኮሮናቫይረስ መስፋፋት ጋር በተያያዘ የስጋት ቀጠና ሆኗል። በሱዳን አዋሳኝ ቦታዎች ላይ 19 ዋና ዋና በሮች እንዳሉ ለቢቢሲ የገለጹት የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ አደባባይ ሙሉጌታ፣ በዞኑ 7 የሚደርሱ የለይቶ ማቆያ ማዕከሎች መኖራቸውን ይናገራሉ። ከሚገባው የሰው ቁጥር አንጻር ያሉት የለይቶ ማቆያ ማዕከሎች አነስተኛ ናቸው። በአንድ ለይቶ ማቆያም ከመያዝ አቅሙ አምስት እጥፍ የሚበልጥ ሰው እንደሚያስተናገድ ጨምረው አስረድተዋል።

BBC
@Yenetube @Fikerassefa
#ትግራይ_ክልል

በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ቆራሪት በተባለች ከተማ ነዋሪዎች ተቃውሞ ሰልፍ በማካሄዳቸው ሰዎች እያተሰሩ ነው ተባለ። በዚህ ሁለት ቀን ከ150 በላይ ሰዎች መታሰራቸው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የከተማው አስተዳደር በበኩሉ ታስረዋል ተብሎ የተገለፀው ቁጥር የተጋነነ ነው፤ የህዝብ ሰላም ለማወክ የሚሰሩ ሰዎች በመለየት ህጋዊ የእርምት እርምጃ እየወሰድን ነው በማለት አሳውቋል።

Via:- VOA
@Yenetube @Fikerassefa
በአሜሪካ የሚገኘው የመሀተመ የጋንዲ ሀውልት ባልታወቁ ሰዎች ቀለም ተረጭቶበታል።

የጆርጅ ፍሎይድ በፓሊስ እጅ መሞትን ተከትሎ በአሜሪካ በበረታው የተቃውሞ ሰልፍ በዋሽንግተን ከሚገኘው የህንድ ኢምባሲ ውጪ በቆመው የመሀተመ ጋንዲ ሀውልት ላይ ብርቱካናማ ቀለም የተረጨበት ሲሆን ጉዳዮን ፖሊስ እያጣራ መሆኑን ተነግሯል።
ቀለም የተረጨበት ሀውልት ፎቶ ከትናንት እሮብ ግንቦት 26,2012 ጀምሮ በበርካታ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲሽከረከር ታይቷል።

የህንድ ታላቅ መሪ ተብለው የሚወደሱት መሀተመ ጋንዲ በ117 አመት በፊት ጥቁር አፍሪካዊያን በተመለከተ " ቆሻሾች ፣አንደ አንሰሳ ነው የሚኖሩት " ብለው መናገራቸው በታሪክ የተመዘገበ ሲሆን ምን አልባት ከዚህ ጋር በተያያዘ ይሆናል ሰሞኑን " Black Lves Matter " በሚል ተቃውሞ የወጡ ሰዎች ሀውልቱ ላይ ቀለም የረጩት የሚል መላ ምትም እንዳለ አር ቲ ሚደያ ዘግቧል።

Via:- fidelpost
@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from EthioNova🇪🇹
Access 100+ both free and Paid online courses from leading institutions worldwide. Gain new skills and earn a certificate of completion. Join today.

Contact +251939560060 or @yenecademy

yenecademy.com/
አሜሪካ ከቻይና የሚደረጉ የመንገደኞች አውሮፕላን በረራዎች ላይ እገዳ መጣሏ ተሰምቷል።

ከቻይና ወደ አሜሪካ የሚደረጉ የመንገደኞች አውሮፕላን በረራዎች ላይ የተጣለው እገዳም ከሰኔ 9 ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ የሚደረግ መሆኑም ነው የታወቀው።የአሜሪካ የትራንስፖርት ቢሮ እንዳስታወቀው፥ እገዳው የተላለፈው ቤጂንግ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ከተቆጣጠረች በኋላ የአሜሪካ አውሮፕላኖች ወደ ሀገሪቱ እንዳይበሩ ፍቃደኛ ላለመሆኗ ቅጣት ነው።እንደ ትራንስፖርት ቢሮው ትእዛዝ እገዳው ኤር ቻይና፣ ቻይና ኢስተርን ኤር ላይን፣ ቻይና ሳውዘርን ኤር ላይን እና ሀይናን ኤር ላይን በተባሉ አራት የቻይና አውሮፕላኖች ላይ ተፈፃሚ የሚደረግ ነው።

ሆኖም ግን የመንገደኞች አውሮፕላን እግዳው ተፈፃሚ ለመሆን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ይሁንታ ካገኘ ብቻ ነው እየተባለ ነው።ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይናን በተደጋጋሚ ፍትሃዊ ባልሆነ የንግድ ስርዓት እንዲሁም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አያያዝ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ሲወቅሱ እንደነበረም አይዘነጋም።በአሜሪካዋ ዋሽንግተን የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ የበረራ እገዳው ላይ አስካሁን አስተያየት ከመስጠት መቆጠቡም ነው የተነገረው።

ምንጭ፦BBC/FBC
@YeneTube @FikerAssefa
“ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያዊያን የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም በመረባረብ ማጠናቀቅ ይገባዋል”

- ዶ/ር ፋሪስ ደለለ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት

@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ለታላቁ የኢትዩጵያ የህዳሴ ግድብ የ 200,000 ሺህ ብር ቦንድ ግዥ የፈጸመ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ለተቋቋመዉ ሶሻል ትረስት ፈንድ ከየክፍለ ከተማዉ መምህራን ማህበሮች እንዲሁም ከማዕከሉ የማህበሩ ጽ/ቤት የተሰበሰበዉን 335,000 ብር ድጋፍ ለከተማዉ አስተዳደር አሰረክባል ፡፡

በተያያዘ ዜናም ማህበሩን እራሱን ለማስቻል በሚደረገዉ እንቅስቃሴ ውስጥ የራሱ የሆነ ሁለገብ ማዕከል እና የመምህራን እጠቃላይ ሆስፒታል ለማስራት የኮንትራክተር ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማክስኞ ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ/ም ተጫራቾችን ጋብዛል፡፡

ምንጭ: የከተማ አስተዳደሩ ት/ት ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa
በአዳማ ከተማ 77 ሺህ 575 ብር ሐሰተኛ የብር ኖት ከአሳታሚዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ ።

የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኝነት ባለሙያ ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት አንዱ ግለሰብ ሐሰተኛ ኖት ይዞ ወደ ገበያ በወጣበት ወቅት ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ነው።ግንቦት 26 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በአዳማ ከተማ ሉጎ ክፍለ ከተማ ቢቃ ቀበሌ ሁለተኛውና ዋነኛው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል።ፖሊስ ዋናው ተጠርጣሪ ተከራይቶ ከሚኖርበት አዱላላ ቀበሌ ሃጤ ሀሮሬቲ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ውስጥ ሐሰተኛ የብር ኖቶች ፣ ማተሚያ ማሽን ከነሙሉ እቃው ጋር በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ተናግረዋል። በዚህም ባለ 100 ብር 75 ሺህ፣ ባለ 50 ብር 2 ሺህ 550 ብር፣ ባለ 10 ብር ሁለት፣ ባለ 5 ብር አንድ እንዲሁም የውጭ ሀገር ገንዘብ በቤቱ ውስጥ መገኘቱን ገልፀዋል።የሁለቱ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በምርመራ ላይ ሲሆን ምርመራው ሲጠናቀቅ ለፍርድ ይቀርባሉ ተብሏል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
አትላንታ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ኮቪድ-19ን ለመከላከል የ10 ሺህ ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለፀ!

አትላንታ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ኮቪድ-19ን ለመከላከል የ10 ሺህ ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ገለፁ።አምባሳደሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት እንዳሉት "ለወገን ደራሽ ወገን ነው!" በሚል መሪ ቃል ከኮሚኒቲው አባላት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን እና በዚሁ ወቅት 10 ሺህ ዶላር መሰብሰብ መቻሉን አስታውቀው ድጋፉን ላደረጉ የኮሚኒቲው አባላትም ምስጋቸውን አቅርበዋል፡፡በቀጣይም ይህንን የመሰሉ ውይይቶች እና ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም አምባሳደሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ተገለፀ!

የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ የሌሎች የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል ከግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም መወሰኑን የኢትዮጵያ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊያደርግ የሚችል መሆኑንም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስታውቋል፡፡

Via MoTI
@YeneTube @FikerAssefa
በጉራጌ ዞን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ከሆነች ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበራቸው 47 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸው ተገለጸ፡፡

በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ እናትየ ቀበሌ ነዋሪ የሆነች የ28 አመት እድሜ ያላት ሴት አዲስ አበባ ለቅሶ ደርሳ የተመለሰች እንስት በኮሮና ቫይረስ መያዟ በመረጋገጡ ወደ ለይቶ ማከሚያ መግባቷ ተገልጿል።ቫይረሱ ያለበት ይህች እንስት አሁን ላይ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደምትገኝም የጉራጌ ዞን ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል እና ቲቺንግ ሆስፒታል ሃላፊ ዶ/ር አብዱርሰመድ ወርቁ ከግለሰቧ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው 13 ሰዎች ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውንም ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ ቸሃ ወረዳ ላይ አዲስ አበባ ለቅሶ ደርሰው የተመለሱና ከእነኝህ ጋር ንክኪ የነበራቸው የተባሉ 34 ሰዎች ወደ ማቆያ መግባታቸውንም የዞኑ ጤና ቢሮ ጨምሮ ገልጿል፡፡ከዚህ በፊት በተጓዳኝ በሽታ ቡታጅራ አጠቃይ ሆስፒታል ለሌላ በሽታ ህክምና እያደረገ የነበረ ወንድ ቫይረሱ ተገኝቶበት ሙሉ ለሙሉ አገግሟል፡፡እስካሁን ድረስ በጉራጌ ዞን ሁለት የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች እንዳሉም ነው ዞኑ ያስታወቀው፡፡በዞኑ ውስጥ በ68 ቦታዎች ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ 1ሺህ 280 ንክኪ ያላቸውን ሰዎች መያዝ የሚችሉ የለይቶ ማቆያዎች ማዘጋጀቱን የዞኑ ጤና ቢሮ ገልጿል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ጆርጅ ፍሎይድ ኮሮናቫይረስ ነበረበት ተባለ!

በፖሊስ መገደሉ በመላው አሜሪካ ተቃውሞ የቀሰቀሰው ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ከመሞቱ ከሳምንታት በፊት ኮሮናቫይረስ ተገኝቶበት ነበር ተባለ።20 ገፅ የሚሆነውና ስለ አሟሟቱ የሚገልጸው ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ ጆርጅ ሚያዝያ 3 ኮሮናቫይረስ ይዞት እንደነበር ያሳያል።ነገር ግን የቫይረሱ ዘረ መል በአንድ ሰው ሰውነት ውስጥ ለሳምንታት ሊቆይ ስለሚችል፤ ጆርጅም የበሽታው ምልክት ሳይታይበት ሊቀር እንደቻለ ተገልጿል። ሪፖርቱ ጆርጅ “ቀደም ሲል ይዞት የነበረ በሽታ ያሳደረው ጉዳት” ይታያል ይላል።የጆርጅ ፍሎይድን አስክሬን በግል ከመረመሩት ሁለት ሀኪሞች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ማይክል ባደን፤ ለኒው ዮርክ ታይምስ እንደተናገሩት፤ ጆርጅ በኮቪድ-19 መያዙ አልተነገራቸውም ነበር ።“የአስክሬን ምርመራ ሲደረግ ሟቹ ኮሮናቫይረስ እንደነበረበት ከታወቀ፤ አስክሬኑን ለሚነኩ ሰዎች ባጠቃላይ ማሳወቅ ይገባል። [ቢታወቅ] ጥንቃቄ ይደረግ ነበር” ብለዋል ዶ/ር ማይክል።

Via BBC/Arts TV
@YeneTube @FikerAssefa
በሊባኖስ በአሰሪዎቻቸው ተባርረው መጠልያ እንዳይገቡ በቆንስላ ተከልክለው ሳምንታትን ጎዳና ላይ ያሳለፉ ወደ 40 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ከደቂቃዎች በፊት የሊባኖስ የስራ ሚኒስቴር ሆቴል እንደተመደበላቸው በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

Via Zekarias Zelalem/Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa
በጣና ሐይቅ ዙሪያ የሚታየውን የእምቦጭ አረም እስከ ሰኔ 30 ማስወገድ ካልተቻለ በሚቀጥለው ዓመት በእጥፍ ይጨምራል ሲል የጣና ሐይቅና ሌሎች ውኃማ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የውጪ ሀገር ዜግነት ያለው ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በመግባት ከ90 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ብር የአሜሪካ ዶላር እና የህንድ ገንዘብ ሰርቀው ለማምለጥ የሞከሩ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ::

Via Addis Ababa Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን ካነሳባቸው ሰዎች መካከል አምስቱ ነገ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ የክሉ ጠቅላይ አቃቢ ሕግ አስታወቀ።

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ከሁለት ሳምንት በፊት በተለያዩ ህገወጥ ተግባራት በህግ መጠየቅ አለባቸው የተባሉ 12 የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታቸው መነሳቱ ይታወሳል።ከነዚህ 12ቱ የምክር ቤት አባላት መካከል 5ቱ በወቅቱ ከተፈጠረው ሁከት ጋር በተያያዘ የክልሉን ዜጎች ለግጭት ሲቀሰቅሱ ነበር በሚል ተጠርጥረው መታሰራቸውም አይዘነጋም፡፡የሱማሌ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ አብዲዋሊ ጀማል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በ5ቱ ተጠርጣሪዎች ከፍርድ ቤት ቀጠሮ የተሰጠው መሆኑን ገልፀው ነገ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡና ክስ እንደሚመሰረትባቸው ነግረውናል፡፡ግለሰቦቹ በቅርቡ በተከናወነው የክልሉ ምክር ቤት ባለመግባባት ከአዳራሽ ከወጡ በኋላ በጅግጀጋ ከተማ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ ሲቀሰቅሱ ነበር ተብሏል።በወቅቱ ከተፈጠረው ግጭት ጋር በተያያዘ ከ5ቱ የምክር ቤት አባላት ውጭ የታሰሩ አለመኖራቸው ተገልጿል። በታሰሩት ግለሰቦች ላይ ምርመራው ተጠናቆ በነገው ዕለት የክስ ቻርጅ እንደሚደርሳቸው ጠቅላይ አቃቢ ሕጉ ተናግረዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ሃይንከን ኢትዮጵያ ለተለያዩ አካባቢዎች ግምቱ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ድጋፍ አደረገ!

ሃይንከን ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ግምቱ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ድጋፍ ለተለያዩ አካባቢዎች ማድረጉን ገለጸ።ድርጅቱ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በአዲስ አበባ ከተማ ለልደታና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች፣ ከአዲስ አበባ ውጪ ለጅማ፣ ጋምቤላ፣ ጅንካ፣ አርባ ምንጭ እና ኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎች የምግብና ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል።ሃይንከን ኢትዮጵያ ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ መግባቱ ከተገለጸበት ጊዜ አንስቶ ''በክፉም ሆነ በደግ ቀን ከኢትዮጵያ ጋር እንቆማለን'' በሚል መሪ ሃሳብ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa