ዓርብ ግንቦት 28፣ 2012 ዓመታዊውን የ#አረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ በይፋ ይጀመራል-ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
ዓርብ ግንቦት 28፣ 2012 ዓመታዊውን የ#አረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ በይፋ እንጀምራለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል።
አብይ አህመድ እንዳሉት ባለፈው ዓመት እያንዳንዳችን ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለን፣ ያቀድነውን አሳክተናል። ከ#ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር እየተፋለምን ቢሆን፣ 5 ቢሊየን ችግኞችን የመትከል ዕቅዳችንን እናሳካዋለን። እያንዳንዱ ቤተሰብ አካላዊ ርቀትን እንደጠበቀ ዐሻራውን ማሳረፍ የሚችልበትን መንገድ እናመቻች በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
@YeneTube @Fikerassefa

የደቡብ ሱዳን በግዛቷ ውስጥ ግብጽ ጦር ሰፈር እንድታቋቁም ፈቃድ ሰጥታለች እየተባለ የሚነገር ሐሰት መሆኑን ዛሬ ጠዋት የአገሪቱ ጦር ሠራዊት አስታወቀ።
ከትናንት ጀምሮ የተለያዩ ምንጮች ግብጽ በደቡብ ሱዳን ውስጥ ጦር ሰፈር እንዲኖራት ጥያቄ አቅርባ ተቀባይነት እንዳገኘች ሲናፈስ ነበር።መረጃው የደቡብ ሱዳን መንግሥት በጥያቄው ተስማምቶ በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስነው ፓጋክ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ጦር ሰፈሯን እንድታቋቁም ፈቅዷል የሚል ነበር።
"የተባለው ነገር ሐሰተኛ ዜና ነው።በሁለቱ አገራት ውስጥ ስምምነት ተደርጎ ቢሆን ኖሮ የደቡብ ሱዳን ጦር ሠራዊት ቀድሞ ያውቅ ነበር። ምንም አይነት ስምምነት አልተደረገም" ሲሉ አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ከፍተኛ የጦር ባለስልጣን መናገራቸው ተዘግቧል።
የጦር ባለስልጣኑ ጨምረው እንደተናገሩት "ከኢትዮጵያ ጋር የመከላከያ ስምምነት ስላለን ያንን በመጣስ ምንም አናደርግም። ኢትዮጵያ የዛሬዋ ደቡብ ሱዳን እንድትመሰረት አስተዋጽኦ አድርጋለች" ሲሉ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ጥብቅ ቁርኝት ገልጸዋል። ቢቢሲ አዲስ አበባ ከሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ ስለጉዳዩ መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረገ ቢሆንም እስካሁን አልተሳካለትም።ይህ ደቡብ ሱዳን፣ ግብጽ ፓጋክ በተባለው ግዛቷ ውስጥ የጦር ሰፈር እንድታቋቁም ፈቅዳለች የሚለው ዜና ጁባ ቲቪ እና ሳውዝ ሱዳን ኒውስ ናው በተባሉ መገናና ብዙኀን ላይ ከተሰራጨ በኋላ ነው ከፍተኛ ትኩረትን ያገኘው።
የጦር ሰፈሩ ይቋቋምበታል ተብሎ የተጠቀሰው ስፍራ ፓጋክ ደቡብ ሱዳንን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስነው ድንበር አቅራቢ ያለ ቦታ ሲሆን፤ ቦታው የአገሪቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሬክ ማቻር የሚመሩት ተቃዋሚው የሱዳን ሕዝብ ነጻነት ንቅናቄ ጠንካራ ይዞታ ነው። ወሬውን ትኩረት እንዲስብ ያደረገው ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው ግዙፍ ግድብን በተመለከተ ከሱዳንና ከግብጽ ጋር እያደረገችው የነበረው ድርድር መቋጫ ሳያገኝ በእንጥልጥል ባለበት ጊዜ መሆኑና ኢትዮጵያ ግድቡን በቀጣይ ወር በውሃ መሙላት ለመጀመር በምትዘጋጅበት ጊዜ መሆኑ ነው።
Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa

በኡጋንዳ በኮቪድ-19 የተያዙ 11 ኤርትራውያን ተገኙ!
ኡጋንዳ በመጋቢት 12፣ 2012ዓ.ም ለመጀመርያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው ስታገኝ አብዛኛዎቹ ሹፌሮች መሆናቸው ገልጻ ነበር።የጤና ሚኒስትሯ ጄን አሰንግ ባለፈው እሁድ በሰጡት መግለጫም፤ ከደቡብ ሱዳን ወደ ኡጋንዳ የገቡ 50 የሚሆኑ የትልልቅ መኪና አሽከርካሪዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ጠቁመዋል።ከእነዚህ ግንቦት ወር ላይ የተመረመሩ ሹፌሮች፤ 10 የሚጠጉት ኤርትራውያን መሆናቸው የሚኒስትሩ መግለጫ ያመለክታል።በዚህ መሰረት፣ በሚያዝያ 28፣ አንድ ከኬንያ በማላባ ድንበር ወደ ኡጋንዳ ሲገባ የተመረመረ ኤርትራዊ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።በግንቦት 6 ደግሞ፣ በተመሳሳይ ከታንዛንያ የመጣ፣ በግንቦት 8 ከደቡብ ሱዳን በኢለጉ ድንበር ሲገቡ የነበሩ አራት ኤርትራውያን በቫይረሱ መያዛቸው እንደተረጋገጠ የጤና ሚኒስቴሩ መግለጫ ያሳያል።ሌሎች 3 ኤርትራውያን ግንቦት 12 ላይ፣ ግንቦት 19 ደግሞ ሌላ አንድ ኤርትራዊ ሹፌር በቫይረሱ ተይዘው ሲገኙ፤ በትናንትናው እለትም አንድ ሰው መገኘቱ ተገልጿል።

‹‹ለሌላ ሕክምና የመጡ ስድስት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል››
-ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባልደረባ ረዳት ፕሮፌሰር ወንድወሰን አሞኘ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንዳሉት ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ እውነተኛው ወረርሽኝ እየታየ መሆኑንና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልም ለሌላ ሕክምና መጥተው የነበሩ ስድስት ሕሙማን የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ገልጸው፣ ሆስፒታሉ ብዙ ነገሮች ላይ እየሠራና እየተዘጋጀም መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 142 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4,120 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አርባ ሁለት (142) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,486 ደርሷል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4,120 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አርባ ሁለት (142) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,486 ደርሷል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 17 ደርሷል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት የ3 ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን አንደኛዋ የ71 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ ፣ ሁለተኛው የ46 አመት ወንድ ከኦሮሚያ ክልል ሶስተኛው የ40 አመት ወንድ ከደቡብ ክልል፣ የመጀመሪያዋ በሆስፒታል ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ሲሆን ሁለቱ ህይወታቸው ካለፈ በኋላ በተደረገ የአስከሬን ምርመራ ነው ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው፣ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ሰባት (17) ደርሷል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 142 ሰዎች ሲሆኑ ከአንድ ፓርቹጋላዊና ሌላ ጅቡቲያዊ ውጭ 140ዎቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው፣ በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(84) ሴት(57) ናቸው!
➡️ዕድሜያቸው ከ7-78 አመት የሆኑ
➡️ተጨማሪ 9 ሰዎች ከሶማሌ ክልል እና 6 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከህመማቸው ሲያገግሙ በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 246 ደርሷል።
➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(126)፣ ከኦሮሚያ ክልል(7)፣ ከአፋር ክልል(2) አማራ ክልል(6) እና ከሶማሌ ክልል(1) በኮሮና የተያዙ በድምር 142 ሰዎች ናቸው።
➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,486 ደርሷል።
➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 6 ነው።
➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 3 ሞት የተመዘገበ ሲሆን ጠቅላላ የሟቾች ቁጥር 17 ደርሷል።

አይቦፕሮፊን ለኮሮናቫይረስ ህክምና እንዲውል ሙከራ እየተደረገ ነው!
ሳይንቲስቶች አይቦፕሮፊን የተሰኘውን የህመም ማስታገሻ በሆስፒታል ውስጥ ለሚገኙ የኮሮናቫይረስ ህሙማንን ህክምና መዋል ይችላል የሚለው ላይ ምርመራ እያደረጉ ነው።ለንደን መቀመጫቸውን ያደረጉት ሴይንት ቶማስና ኪንግስ ኮሌጅ የተውጣጣ ቡድን ለህመም ማስታገሻነት የሚውለው አይቦፕሮፊን መተንፈስ ለሚያዳግታቸውም እፎይታን ይሰጣል እያሉ ነው።መድኃኒቱ ዋጋው ተመጣጣኝ ከመሆኑ አንፃርም በውድ ዋጋ ከሚሸጠው ቬንትሌተር ፈንታ ህሙማንን ሊታደግ ይችላል እያሉ ነው።ሊበሬት የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚህ ሙከራ ህሙማን ከሚደረግላቸው እንክብካቤ በተጨማሪ ግማሾቹ አይቦፕሮፊን ሰውነታቸው ላይ የሚያመጣው ለውጥ የሚገመገም ይሆናል።በሙከራው ገበያው ላይ ያለው አይቦፕሮፊን አይነት ሳይሆን በተለየ የአቀማመር ሁኔታ የተቀመሙ አይቦፕሮፊን ተግባራዊ ይደረጋሉ። እነዚህን ለየት ያሉ የአይቦፕሮፊን አይነቶች በመገጣጠሚያ ህመሞች የሚሰቃዩ ሰዎች ይወስዷቸዋል።

በጤና ተቋማት የሚሰሩ 65 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ሚኒስትሯ አስታወቁ!
በኢትዮጵያ እስካሁን ባለው ሂደት 49 የጤና ባለሙያዎችና 16 ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።እስካሁን ባለው ሂደትም 49 የሕክምና ባለሙያዎችና 16 ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ቫይረሱ ተገኝቶባቸው ክትትል እያደረጉ ነው ብለዋል።ባለሙያዎቹ በአብዛኛው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የጤና ተቋማት እየሰሩ መሆናቸውን በመግለጽ።የጤና ባለሙያዎችና የጤና ተቋማት ሠራተኞች የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እያደረጉት ላለው ተጋድሎም ምስጋና አቅርበዋል።መንግሥት የጤና ተቋማት ሠራተኞችን ተጋላጭነት ለመቀነስ ከሚያደርገው ሥራ በተጨማሪ ኅብረተሰቡ ራሱን በመጠበቅ የባለሙያዎቹን ጫና እንዲቀንስም ጠይቀዋል።ከዚህ ጋር ተያይዞ በተለይ ማህበረሰቡ የቫይረሱን ስርጭት የሚመጥን ጥንቃቄ አለመደረጉ እንደሚያሳስባቸው ሚኒስትሯ ተናግረዋል።"ጥንቃቄ የምናደርገው የጸጥታ አካላት ወይም የጤና ባለሙያዎችን ትዕዛዝ ለማክበር ሳይሆን፤ ለራሳችንና ለምንወዳቸው ወገኖቻችን ብለን መሆን አለበት" ሲሉም ምክራቸውን አስተላልፈዋል።
Via ENA

የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሽ በቀለ እና ልዑካቸው በዛሬው ዕለት ከሱዳን አቻቸው ፕሮፌሰር ያሲር አባስ ሞሐመድ እና ልዑካቸው ጋር የቪዲዮ ኮንፈረንስ በማድረግ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የሶስትዮሽ ድርድር ማስቀጠል በተመለከተ ተወያይተዋል።
የስብሰባውም አጀንዳ የሶስትዮሽ ድርድሩ እንደገና የሚጀምርበት፤ ስለሚከናወንበት የስነ ስርዓት ጉዳዮች እና ግድቡን በተመለከተ የሀገራቱ ዋና ዋና ጉዳዮች እና ሃሳቦችን የተመለከተ ነበር። ሁለቱ ወገኖች የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ የሶስትዮሽ ስብሰባው በቶሎ እንዲጀመር ስለማመቻቸት ተስማምተዋል። በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች ከድርድሩ ጋር የተያያዙ ይልተፈቱ ዋናዋና ጉዳዮችን በተመለከተም ሃሳብ ተለዋውጠዋል።
Via MoWIE

በአዲስ አበባ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃያ ስድስት (126) ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማው ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አንድ ሺህ ሰማንያ ሁለት (1082) መድረሱን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
ቫይረሱ ዛሬ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ ደረጃ:
አዲስ ከተማ 47
ኮልፌ 14
ቦሌ 11
ጉለሌና ቂርቆስ 10
ልደታ 8
አቃቂ ቃሊቲ 7
አራዳና የካ 6
ንፋስ ስልክ ላፍቶ 4
አድራሻቸው በመጣራት ያሉ 3 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
እስካሁን በየክፍለ ከተማዎቹ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ስንመለከት
አዲስ ከተማ 305
ልደታ 176
ጉለሌ 141
ኮልፌ ቀራንዮ 110
ቦሌ 99
አራዳ 48
የካ 46
ንፋስ ስልክ ላፍቶ 41
ቂርቆስ 41
አቃቂ ቃሊቲ 29
አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያሉ ደግሞ 46 ናቸው።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ያወጣሁት ሪፖርት ትክክለኛ ነው ሲል ለቢቢሲ አማርኛ ተናግሯል፡፡ ታጣቂዎች የሚፈጽሟቸው ወንጀሎች ሪፖርቱ ያላካተተው፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚፈጸሙት በመንግሥት በመሆኑ ነው፡፡ በታጣቂዎች የሚፈጸሙ ግድያዎችን የመከላከል ሃላፊነት የመንግሥት ነው፡፡
via:- wazema
@YeneTube @Fikerassefa
via:- wazema
@YeneTube @Fikerassefa
ደቡብ ሱዳን ለግብፅ የጦር መንደር መገንቢያ መሬት ልትሰጥ ነው መባሉን የሚያስተባብል ደብዳቤ ዛሬ ማምሻውን አውጥታለች። ይህ አሁን ከጁባ የደረሰኝ ደብዳቤ እንደሚያስረዳው በአንዳንድ ሚድያዎች ሲሰራጭ የነበረው መረጃ ፍፁም ውሸት ነው።በጉዳዩ ላይ በኢትዮጵያ ያሉት የደቡብ ሱዳን አምባሳደርም ነገ መግለጫ እንደሚሰጡ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።ደብዳቤው ተያይዟል።
Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የመቄዶንያ አረጋውያንና አእምሮ ሕሙማንና የጌርጌሶኖን የአእምሮ ሕሙማን ማዕከላት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የኬሚካል ርጭት ዛሬ ተካሄደ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ ርጭቱን በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን፣ ማዕከላቱንም ጎብኝተዋል።ለርጭቱ ኬሚካል አቅርቦት ድጋፍ ያደረጉት የኤም ቲ ኤስ ትሬዲንግና ኢትዮ ኤየርስ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያዎች ናቸው።
Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ ርጭቱን በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን፣ ማዕከላቱንም ጎብኝተዋል።ለርጭቱ ኬሚካል አቅርቦት ድጋፍ ያደረጉት የኤም ቲ ኤስ ትሬዲንግና ኢትዮ ኤየርስ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያዎች ናቸው።
Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል በምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ ቆራሪት በተባለ ቦታ የተሰባሰቡ ገበሬዎች የመንደራቸው አስተዳደራዊ መዋቅር በከንቲባ የሚመራ ከተማ እንድትሆን መወሰኑ ተቃውሞ ገጥሞታል።
በገጠር አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲቆይ የሚሹ ነዋሪዎች ወደ ሽረ እና ሌሎች አካባቢዎች የሚወስደው መንገድ እስከ መዝጋት ደርሶ ነበር።የአካባቢው ገበሬዎች ቅሬታ የፈጠረባቸው ግን የቆራሪት መንደር ወደ ከተማ አስተዳደር መቀየሯ ብቻ አይደለም። በወልቃይት ይገነባል የተባለ የስኳር ፋብሪካ መዘግየት ቅሬታ አሳድሮባቸዋል። የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ በአመት 4 ሚሊዮን 840 ሺ ኩንታል ስኳር እና 41 ሚሊዮን 654 ሊትር ኢታኖል ያመርታል ተብሎ ታቅዶ እንደነበር የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃ ይጠቁማል።
Via DW

በኤርትራ ከሚያዝያ 10 በኋላ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሁለት ሰዎች ተገኙ!
ከአንድ ወር ለሚበልጥ ጊዜ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው ሳትመዘግብ የቆየችው ጎረቤት አገር ኤርትራ፤ ዛሬ በቫይረሱ የተያዙ ሁለት ሰዎች መገኘታቸውን የኮቪድ -19 ከፍተኛ ግብረ ኃይል አስታወቋል፡፡በምርመራው 4659 ቤቶችን ማዳረስ የተቻለ ሲሆን ከአንድ ቤት አንድ ሰው እንዲመረመር ተደርጓል፡፡ በዚህም 4658 ሰዎች ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን አንዲት ሴት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተነግሯል፡፡ይህንን ተከትሎም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከግለሰቧ ጋር ንክኪ ያላቸው 13 ግለሰቦች ተለይተው ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ ከእነዚህ ግለሰቦች መካከል አንዱ የሴትዮዋ ባለቤት ሲሆኑ በኋላ ላይ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል፡፡

Forwarded from Nat Computers®️ (Natnael Endrias)
💻ከNat mobile & Computers
ማንኛውንም አይነት Laptop በተመጣጣኝ ዋጋ እንገዛለን
በተጨማሪም
🔴 ✿ #ጥራት ያላቸውንና ምርጫዎን የጠበቁ ሞባይሎች፣ ላፕቶፖች እና ታብሌቶች ሳይለፉ ሳይደክሙ ከኛ ይሸምቱ ከሙሉ ዋስትና ጋር
✅ Dell i5 7th 17500br
✅ HP i5 14500br
ስልክ
+251911522626
+251953120011
Inbox @Natyendex
🔶 ለበለጠ መረጃ
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAELykvO6oFdCT0mwAA
አድራሻ ቦሌ መድሀኒያለም ሞርኒንግ እስታር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ in front of angla burger