YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
መኪና የሰረቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ!!

የተሰረቀችው መኪና ባለቤት አቶ ቢረሳው አበጀ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 16 ነዋሪ ናቸው።ተሽከርካሪያቸውን ሰረቀ ተብሎ ከተጠረጠረው ግለሰብ ጋር ጓደኝነት አላቸው።ተቸገርኩ ባላቸው ጊዜም ገንዘብ ሲሰጡት ቆይተዋል።ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መኪናቸውን ለመሸጥ ይፈልጉና ጓደኛቸውን እንዲሸጥላቸው ያማክሩታል። ከቀናት በኋላ ግን ይች መኪና ከመኖሪያ ቤታቸው በር ላይ ትጠፋለች።አቶ ቢረሳውም ወደ 6ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ያመለክታሉ።ፖሊስም ጥቆማውን ተቀብሎ ምርመራ በሚያጣራበት ጊዜ መኪናው የተወሰደው መስታወቱ ሳይሰበር ስለሆነ የመኪናውን ቁልፍ ለሌላ ሰው ሰጥተው ያውቁ እንደሆነ ሲጠየቁ ለቅርብ ወዳጃቸው ለሆነው ግለሰብ ሰጥተውት እንደሚያውቁ ለፖሊስ ይገልፃሉ።ፖሊስም ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን ይጀመራል።በመጨረሻም የጠፋችው መኪና በዘጠነኛ ቀኗ ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ከተሽከርካሪ ማሳደሪያ (ፓርኪንግ) ውስጥ ተደብቆ መገኘቱን ፖሊስ ገልጿል።ልክ እንደ አቶ ቢረሳው ሁሉ ሌላው ህብረተሰብም በደምብ የማያውቁትን ሰው በማመን ንብረትን አሳልፎ መስጠት እንደሌለበት ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።አሁን ላይ ፖሊስ አስፈላጊውን ማስረጃ በማጠናከር የምርመራ መዝገቡን ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላኩን የ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ባለሙያ ዋና ሳጅን ቢራራ ሞላ ገልፀዋል።

Via Amhara Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
በአርባምንጭ ከተማ በኮቪድ 19 ተሐዋሲ በመጠርጠሯ ሕይወቷን አጠፋች።

ይሁንና ይህች እንስት ከአስከሬኗ ላይ ናሙና ተወስዶ ስትመረመር ግን ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆኗ በምርመራ መረጋገጡን የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ ዐስታውቋል።የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ዳንኤል አረጋ አንደገለጹት ወርቅነሽ ዲባባ የተባለችው የ25 ዓመት ወጣት ባለፈው ዓርብ እራሷን አጥፍታ የተገኘችው በአርባምንጭ ከተማ የሙቀት ልኬት ከተደረገላትና በለይቶ ማቆያ እንድታርፍ ከተደረገች በኋላ ነው።ኮማንደር ዳንኤል በማያያዝም «በእለቱ በአርባምንጭ ከተማ መግቢያ ላይ በአውቶብሱ ውስጥ በነበሩ 36 መንገደኞች ላይ የሙቀት ልኬት ፍተሻ ይካሄዳል። የሟች ወርቅነሽ የሙቀት መጠን ከፍ ብሎ በመገኘቱ ከሌሎች ተጓዦች ተለይታ አንድትቀር ይደረጋል።

በምርመራ እንዳረጋገጥነው ወጣቷ ምናልባት የገጠር ነዋሪ ከመሆኗ ጋር በተያያዘ ሊሆን ይችላል በሁኔታው የመደናገጥ፣ የመረበሽና የመገለል ስሜት ይስተዋልባት ነበር። የደም ናሙና ምርመራ አንደሚደረግላትና ከተሐዋሲው ነፃ ከሆነች ጉዞዋን እንደምትቀጥል ተሐዋሲው ካለባት ደግሞ እዚሁ የህክምና ድጋፍ እንደሚደረግላት ተነግሯት በለይቶ ማቆያ እንድታርፍ ተደርጋ ነበር። ይሁን እንጂ በማግስቱ ጠዋት ባደረችበት የማቆያ ክፍል ውስጥ በለበሰችው የአንገት ልብስ (ሻርፕ) እራሷን ሰቅላ መገኘቷን ለማረጋገጥ ተችሏል» ብለዋል ።የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የለይቶ ማቆያ ማዕከላት አስተባባሪ አቶ በርገና ኦላሞ በበኩላቸው በእርግጥ ሟች ወርቅነሽ ከሌሎች መንገደኖች ተለይታ በመቅረቷ ደስተኛ አልነበረችም ፣ የመረበሽ ስሜትም ይታይባት ነበር ይላሉ።

የምርመራ ውጤቷ እስከ ነገ እንደሚታወቅና እዚህ የምትቆየውም ለአንድ ሌሊት ብቻ እንደሆነ በማግባባት በማቆያው እንድታርፍ መደረጉን ይናገራሉ።አስተባባሪው አክለውም «ወርቅነሽ በእለቱ ያረፈችው በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው የለይቶ ማቆያ ውስጥ ነው። በተሰጣት የማረፊያ ክፍል ውስጥ ቀኑን በሰላም ማሳለፏን እርግጠኞች ነን።በነጋታው ግን የህክምና ባለሞያዎች መደበኛ ቅኝት ሲያደርጉ አንድ ሰው መጉደሉን በማረጋገጥ ሪፖርት አደርጉ። በሪፖርቱ መነሻነት በተደረገው ክትትል ወርቅነሽ ባረፈችበት ክፍል ሞታ መገኘቷንና ፖሊስም ሕይወቷን በራሷ እጅ እንዳጠፋች ማረጋገጡን ገልጾልናል። አሳዛኙ ነገር ግን የወርቅነሽ የደም ምርመራ ውጤት ሲመጣ ከኮረና ተሐዋሲ ነፃ (negative) እንደነበረች የሚያረጋግጥ ሆኖ መገኘቱ ነው» ማለታቸውን የጀርመን ድምጽ ሬድዮ ዘግቧል።

አሁን ባለው ሁኔታ ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ሲጠየቁ የፍረሃት፣ የጭነቀትና የመገለል ስሜት እንደሚስተዋልባቸው የሚናገሩት የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የለይቶ ማቆያ ማዕከላት አስተባባሪው አቶ በርገና ለይቶ ማቆያ በመግባታቸው ብቻ ራሳቸውን በተሐዋሲው አንደተያዙ አድርገው የሚቆጥሩ ብዙዎች ናቸው ይላሉ። በቀጣይ በኮረና ወረርሽኙ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፈጠር ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን በለይቶ ማቆያ ማዕከላት የስነ ልቦና ምክር አገልግሎት (counselling service) በስፋት ሊቀርብ ይገባል ሲሉም ምክረ ሀሳባቸውን ለግሰዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በፓሪስ ፈረንሳይ ምግብ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶችና ቡና ቤቶች ዛሬ ተከፍተዋል።

በርካታ ሀገሮች የጉብኝት ሥራን መቼ እንደሚጀመሩ ለመወሰን በሚያሰላስሉበት በአሁኑ ወቅት፣ የተባበሩት መንግሥታት ዓለምቀፍ የሲቭል አቪዬሽን ድርጅት፣ በአውሮፕላን መጓዝን አስመልክቶ፣ አንዳንድ የጥንቃቄ ምክረ-ሃሳቦችን እያቀረበ ነው። መንገደኞች አውሮፕላን ማረፍያ ላይ ሲደርሱ፣ የሰውነታቸውን ሙቀት መለካት ይኖርባቸዋል። የሚይዙት ዕቃ ማነስ አለበት። አውሮፕላኑ ውስጥም የአፈና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ ያስፈልጋል። የአካል መራርቅ ለመተግበር በማይቻልባቸው ተርሚናሎችም፤ የአውሮፕላኖቹ ኩባንያውች ለበረራ ሰራተኞች፣ የህክምና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችንና የእጅ ጓንቶችን የመሳሰሉ መከላከያዎችን እንዲያቀርቡ ድርጅቱ መክሯል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
ከተለያዩ የነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ ሲቀዱ የቆዩ በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ ተሸከርካሪዎች ከሰኔ 1 ጀምሮ ከከተማዋ መንገዶች ባለስልጣን፣ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን፣አንበሳ አውቶብስ ድርጅትና ሸገር አውቶብስ ድርጅት ስር በሚገኙ ዴፖዎች ብቻ ነዳጅ እንዲቀዱ ተወሰነ፡፡ውሳኔው በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ ተሽከርካሪዎች የሚታየውን የነዳጅ ብክነት ለመከላከልና ለነዳጅ የሚወጣውን አላስፈላጊ ወጪ ለመቆጣጠር ነው፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
ኢዜማ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚመረምር ልዩ ቡድን በአስቸኳይ እንዲቋቋም ጠየቀ። ቡድኑ የምርመራውን ውጤት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለክልል ምክር ቤቶች እና ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግም ፓርቲው አሳስቧል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
በቴሌግራም @Orangebusinessnetwork ን በመጎብኘት ለእርሶ እና ለድርጅቶ እድገት የሚረዱ መረጃዎች ፤ሀብቶችን እና ማበረታቻዎችን ያገኙ!

የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ
T.me/Orangebusinessnetwork
በአዲስ አበባ ከተማ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 67 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፦

አዲስ ከተማ 7፤
ልደታ 10፤
ጉለሌ 9
ኮልፌ ቀራንዮ16፤
ቦሌ 11፤
አራዳ 1፤
የካ 3፤
ንፋስ ስልክ ላፍቶ 1፤
ቂርቆስ 5፤
አቃቂ ቃሊቲ 2 እና
የ2 ሰዎች ክፍለ ከተማ በመጣራት ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
በቦሌ ክፍለ ከተማ 52 የኮንዶሚኒየም ሱቆች በማህበር ለተደራጁ ወጣቶች ተሰጡ!

የቦሌ ክፍለ ከተማ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተረከባቸውን 52 የኮንዶሚኒየም ሱቆች በማህበር ለተደራጁ 255 ወጣቶች በእጣ አስተላለፈ።የርክክብ ስነ-ስርዓቱ ዛሬ በተከናወነበት ወቅት የክፍለ ከተማው የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መዝገበ ልኡል እንደጠቆሙት፤ በቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም ሳይት እድሉን ያገኙት ወጣቶች ከክፍለ ከተማው ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡና በማህበር የተደራጁ ናቸው፡፡መንግስት በማህበር ለተደራጁ ወጣቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተላለፋቸው እነዚህ የኮንዶሚኒየም ሱቆች ወጣቱን ይበልጥ ተጠቃሚ ሊያደርጉ በሚችሉ የስራ መስኮች እንዲሰማራ እድል የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል፡፡ከዚህ ቀደም በሚሊዮኖች በሚቆጠር ገቢ ለባለሀብቶች በጨረታ ይተላለፉ የነበሩትን እነዚህን ሱቆች መንግስት ሲያስተላልፍ የወጣቱን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በማለም እንደሆነ ገልጸዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ የበጀት ብክነት አሳሳቢ እየሆነ እንደመጣ የፌደራል ዋና ኦዲተር ገመቹ ዲቢሶ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡ ዋና ኦዲተር በ2010 ዓ.ም የመንግሥት ተቋማት ተመላሽ እንዲያደርጉ ከጠየቀው 798 ሚሊዮን ብር የኦዲት ጉድለት ውስጥ ተመላሽ ያደረጉት 124 ሚሊዮኑ ብቻ ነው፡፡

Via Wazema/ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ታዋቂው የዓለም ቦክስ ሻምፒዮን ፍሎይድ ሜይዌዘር በቅርቡ በነጭ ፖሊስ የተገደለውን የጆርጅ ፍሎይድን የሐዘን ሥነ ሥርዓት ወጪውን ሙሉ በሙሉ እንደሚሸፍን አስታውቋል።

በርካታ የአሜሪካ ሚዲያዎችም እንደዘገቡት የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰቦችም የቦክሰኛውን ችሮታም በፀጋ ተቀብለዋል ተብሏል።በሁኔታው ልቡ እንደተሰበረ የተገለፀው የ43 አመቱ ቦክሰኛ በጆርጅ ትውልድ ቦታ ሂውስተን እንዲሁም ሚኒሶታና ቻርሎት ለሚደረጉ የኃዘን ስርአቶች ወጪውን ይሸፍናል ተብሏል።የጆርጅ ቤተሰቦች አራተኛ የኃዘን ስነ ስርአት ለማድረግ መፈለጋቸውን መግለፃቸውን ተከትሎም ከሶስቱ በተጨማሪ አራተኛውንም እሸፍናለሁ ማለቱን ሆሊውድ አንሎክድ ዘግቧል። "ይህንን በመናገሬ ሜይዌዘር ብዙ ደስተኛ ላይሆን ይችላል ነገር ግን ለሚደረጉት የሐዘን ስርአቶች በሙሉ ወጪያቸውን ይሸፍናል" ማለቱን ኢኤስፒኤን የፍሎይድ ሜይዌዘር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።አክሎም "ፍሎይድ ለባለፉት ሃያ አመታት እንዲህ አይነት ተግባራትን ሲፈፅም ነበር" ብሏል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ክልል መንግስት ሕዝቡ 'በአንዳንድ ሃይሎች' እየተጠራ ያለው የተቃውሞ ሰልፍ ለኮሮናቫይረስ እንደሚያጋልጠው አውቆ ቅድሚያ ለጤንነቱ ሊሰጥና ጥያቄውን በትክክለኛ መንገድ ሊያቀርብ እንደሚገባ አሳስቧል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
የምትሰሩትን ያክል Member ብዙ አላገኛችሁም ብላችሁ ለጠየቃችሁን እንዲሁም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ይህ ቻናል ያለ እናንተ ድጋፍ የትም እንደማይደርስ የሚታወቅ ነው።

ምን በማድረግ የቻናሉን ተከታዮች ቁጥር ማብዛት ይቻላል?

1 - ቻናላችን አሁን #ከጎናችሁ ላለ ሰው #ይጠቁሙ !!

2 - አሁን ለአስር ሰው Forward ያድርጉ

3 - ወደ ግሩፓች ሼር የምታደርጉ ከሆነ በቀላሉ እንበዛለን።

( መላካችሁን የሚያሳይ Screenshot @Fikerassefa መላክ ትችላላችሁ )


#አብረን_እንብዛ

#መብዛታችን ድምፃችሁ / ድምፃችን የምፈልገው አካል በቀላሉ እንዲሰማ ይረዳናል ።


Click And Join It ⬇️

https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEHerPG0OpTJJM-WxA

#Yenetube
እናመሰግናለን!!
የዶክተር ሊያ የኮሮናቫይረስ ሪፖርት ምን ይጎለዋል ?

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በየ24 ሰአቱ መግለጫ በማውጣት ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ሞት ፣ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ፣ያገገሙ ፣ ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር የነበራቸው ንኪኪ እና የጉዞ ታሪካቸው ፣የእድሜ ክልላቸው እና የሚኖሩበትን ከተማ ወይም ክልል ያካተተው የሪፖርታቸው ቁጥር 84 ደርሷል።

ሪፖርቱ የሚጎለው ነገር ?

ሪፖርቱ ከሚጎላቸው ነገሮች ኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች መሀል የትኞቹ ምልክቱ የሌለባቸው ግን ሆስፒታል ያሉ አንዲሁም ቀለል ወይም መሀከለኛ ህመም የሚሰማቸው እንዳለ የሚገልፀው ነገር የለም።
ሪፖርቱ ያገገሙ ሰዎችን ይናገር አንጂ ምን ያክል ሰዎች መሉ ለሙሉ ተሽሏቸው ከሆስፒታሉ አንደወጡ አይናገረም ።
በብዙ ሀገራት የመመርመር አቅምን በአንድ ሚልየን ሰው አየተሰላ ከአንድ ሚልየን ሰው ይህን ያክል የመመርመር አቅም እንዳለ ይናገራል የጤና ሚኒስትሯ ሪፖርት ይሄ ይጎለዋል።

የዶክተራ ሪፖርት በ24 ሰአት ውስጥ በምርመራ ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸውን ሰዎች በመኖርያ ክልላቸው ወይም በከተማቸው ሲያስቀምጥ የተወሰዱት ናሙናዎች በጥቅል እንጂ ከየት የት ክልልና ከተማ አንደተወሰዱ አይናገረም ።
ኢትዮጵያ ለህክምና ተቋማት ብቻ 131 ሚሊዮን ጭምብሎች እንደሚያስፈልጋት ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አገሪቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽንን ለመዋጋት በሚቀጥሉት አራት ወራት 131 ሚሊየን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) እንደሚያስፈልጋት መናገራቸውን ፋና ዘግቧል።

ሚኒስትሯ እንዳሉት እነዚህ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (ማስኮች) የሚያስፈልጉት በአገሪቷ ላሉ የጤና ተቋማት ብቻ ነው፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የመከላከል ስራን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ በተለይም በጤና ተቋማት ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የሚሆኑ የህክምና ጭምብሎች (ሜዲካል ማስኮች) በዓለም አቀፍ ደረጃ እጥረት መኖሩን በመጥቀስ፤ እንደ አገርም በርካታ ክፍተቶች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡
ወረርሽኙ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በአገሪቷ አራት ሚሊዮን ጭምብሎች (ማስኮች) ብቻ እንደነበሩ ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጅ ከዚያ በኋላ በተሰሩ ሥራዎች ከሰባት ሚሊየን በላይ ጭምብሎችን ለጤና ተቋማት ማሰራጨት ተችሏል ብለዋል፡፡

ምንጭ:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
በሚኖሶታ ሚድዌስት የኢትዮጵያ ቆንስላ እንዳለው የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ በቀሰቀሰው ተቃውሞ
1.ቦሌ ኢትዮጵያን ሬስቶራንት፣
2.ቺካጎ ፈርኒቸር፣
3.ገመቺስ አውቶሞቲቭ
4.ሴዋርድ ፋርማሲ
5.አድማስ ትራቭል ኤጄንሲ
በቃጠሎ ወድመዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን የህዳሴው ግድብ ስምምነት ላይ ሳይደረስ እንዳይሞላ የጸጥታው ምክር ቤትን ጠየቀች!

ሱዳን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ባስገባችው ደብዳቤ በህዳሴው ግድብ ላይ አጠቃላይ ስምምነት ሳይደረስ በፊት የግድቡ ሙሌት እንዳይጀመር ጠየቀች። ሁሉም ወገኖች በቅን ልቦና ወደ ድርድር እና ስምምነት እንደሚለሱ ሱዳን እያደረገች ያለውን ጥረት የጸጥታው ምክር ቤት እንዲያግዝም ጥሪ አቅርባለች።ሀገሪቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አስማ መሃመድ አብደላ የተፈረመውን ደብዳቤ ለጸጥታው ምክር ቤት ያስገባችው ትላንት ማክሰኞ ግንቦት 25፤ 2012 ነው። ግብጽ ሚያዚያ 23፤ 2012 እና ኢትዮጵያ ደግሞ ግንቦት 6፤ 2012 ለጸጥታው ምክር በቱ ያስገቧቸውን ደብዳቤዎች ተከትሎ ሱዳንም በጉዳዩ ላይ ካላት ጥቅም ተነስታ አስተያየት ለመሰጠት መወሰኗን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው ባለ 15 ገፅ ደብዳቤ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ አጠቃላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ ብዙ ርቀት መጓዛቸውን አስታውሷል። ሚኒስትሯ “የፖለቲካ ቁርጠኝነቱ ካለ በቀሩት ጥቂት ጉዳዮች ላይ መስማማት ይቻላል” ሲሉም ያላቸውን ተስፋ በደብዳቤያቸው ጠቁመዋል። 

የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አጠቃቀምን አስመልክቶ በተባበሩት መንግስታት አማካኝነት በ1989 ዓ. ም. የወጣውን ስምምነት በደብዳቤዋ የጠቀሰችው ሱዳን የስምምነቱ መርህ “በህዳሴው ግድብ ላይም ሊተገበር ይገባል” ብላለች። ምክንያታዊ እና ተመጣጠኝ የውሃ አጠቃቀም፣ የከፋ ጉዳት ያለማድረስ ኃላፊነት፣ መረጃ የመለዋወጥ እና የማሳወቅ ኃላፊነት እንዲሁም ግጭቶችን በሰላም መፍታት የሚሉት የኮንቬንሽኑን መርሆዎችንም በደብዳቤዋ ላይ አካትታለች።

ሙሉ ዘገባውን ከዌብሳይቱ ለማንበብ ፦ https://t.co/CVYCE0iLQg

Via Ethiopia Insider
@YeneTube
የግብፅ መንግሥት የአፍሪካ ኅብረት እንዲያደራድር የቀረበውን ሐሳብ እንደማይቀበል መግለጹን ሪፖርተር ምንጮቼ ነግረውኛል ብሏል፡፡

ግብፅ የአፍሪካ ኅብረትን አደራዳሪነት ላለመቀበል ስትል ከምታነሳቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ፣ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ በአዲስ አበባ መሆኑና ኅብረቱም የኢትዮጵያ ተፅዕኖ አለበት የሚል እንደሆነ ታውቋል፡፡በሌላ በኩል በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት የሚመጣ ውጤት የግብፅን ጥቅም የሚጎዳ ቢሆንና ግብፅ ውጤቱን ላለመቀበል ብትወስን የኅብረቱ አባል ከሆኑ የአፍሪካ አገሮች በሙሉ እንደሚያቃርናት፣ ይህም አጠቃላይ የዲፕሎማሲ ኪሳራ እንደሚያደርስባት በመሥጋት የኅብረቱን የአደራዳሪነት ሚና ላለመቀበል አቋም መያዟን ምንጩ ያስረዳሉ።የኅብረቱ ሊቀመንበርና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛና የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በተናጠል የአፍሪካ ኅብረት በአደራዳሪነት እንዲገባ ለግብፅ ጥያቄ አቅርበው የነበረ ቢሆንም፣ የግብፅ መንግሥት ሳይቀበለው መቅረቱን ጠቁመዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ👇👇https://telegra.ph/Continued-GERD-controversy-06-03
የቱሪስት መዳረሻ በሆነው ጢስ ዓባይ ፏፏቴ የሚወስደው የባሕር ዳር-ጢስ እሳት 22 ነጥብ 3 ኪ.ሜ መንገድ በአስፓልት ደረጃ ሊገነባ መሆኑ ተገልጿል።

በፕሮጀክቱ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ላይ የመስክ ሥራ ቅኝት መካሔዱም ታውቋል።መንገዱ ከዚህ ቀደም በጠጠር ደረጃ የነበረ በመሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ለብዙ ዓመታት ሲቸገሩ ቆይተዋል።በአሁኑ ወቅት የዲዛይን ቅየሳ፣ የአፈር ጠረጋ እና ድልደላ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተመልክቷል።ፕሮጀክቱ ወደ ዓባይ ፏፏቴ የሚወስድ የ1 ነጥብ 8 ኪ.ሜ ለእግረኞች መጠቀሚያ ብቻ የሚሆን ደረጃውን የጠበቀ መንገድ ግንባታ ሥራንም ያካተተ መሆኑም ተገልጿል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 637 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት እንደሚያስፈልገው ገለጸ!

የበጀት ፍላጎቱን ለሟሟላት የተለያዩ አማራጮች እየተወሰዱ ነው ተብሏል፡፡ድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አሊዪ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ባለንበት በጀት ዓመት አስተዳደሩ 2.8 ቢሊየን ብር ዓመታዊ በጀት መመደቡን አውስተዋል፡፡ ከዚህ በጀት ውስጥ 1.5 ቢሊየኑ በአስተዳደሩ የሚሸፈን ሲሆን 1.3 ቢሊየኑ ደግሞ በፌደራል መንግስት ድጎማ የሚሸፈን ነው፡፡በአስተዳደሩ የሚሸፈነው በጀት በዋነኝነት ከውስጥ ገቢ የሚሰበሰብ ነበር፡፡ በዘንድሮው ዓመት በተለያዩ ምክንያቶች ለመሰብሰብ ከታሰበው እጅጉን ያነሰ ገቢ ተሰብስቧል፡፡ በቀጣይ ወራት 1.08 ሚሊየን ብር ብቻ ገቢ እንደሚደረግ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህም ከእቅዱ አንጻር ሲታይ 419 ሚሊየን ብር የበጀት ጉድለት እንዳለበት አቶ ሱልጣን አሊዪ አስታውቀዋል፡፡በተጨማሪም ወቅታዊ የሆነው ኮቪድ 19 በሽታን ስርጭት ለመከላከል የሚያስችል 218 ሚሊየን ብር ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ውስጥ የተወሰኑ ፕሮጀክቶችን በማጠፍ ለድንገተኛ ወጪ ብቻ ዝግጁ እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል፡።በድምሩ በአስተዳደሩ 637 ሚሊየን ብር የበጀት ፍላጎት እንዳለ ተለይቷል፡፡

አቶ ሱልጣን አክለውም የተጠቀሱትን የበጀት ፍላጎቶች ለሟሟላት ከፌደራል መንግስት ጋር በመነጋገር 300 ሚሊየን ብር በብድር መገኘቱን ገልጸዋል፡፡ በተለይም ደግሞ ከፌደራል መንግስት የተገኘውን የገንዘብ ድጋፍ አጠቃቀም ሲገልጹ በዋነኝነት ሁሉም ሴክተሮች በጀቱን ለሚፈለገውና ውጤት በሚያመጡ ስራዎች ላይ እንዲያውሉት እና አስገዳጅ ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት ተጨማሪ ወጪ እንዳይወጣ በካቢኔ ውሳኔ ተላልፏል ብለዋል፡፡መንግስት ለሰራተኞች ያደረገው የነጥብ ሥራ ምዘና የፌደራል መንግስት ከሚያዝያ አስከ ሰኔ ያለው የተጣራ ተከፋይ የሚሆን ከ 13 ሚሊየን ብር በላይ ለአስተዳደሩ መላኩን አቶ ሱልጣን ገልፀዋል።ይህንን ለመክፈል የታክስ: የጡረታና የበረሐ አበል ክፍያ ተጨማሪ 22 ሚሊየን ብር በአስተዳደሩ ምክርቤት ፀድቆ ተፈፃሚ እንደሚሆን ጠቁመዋል።በአጠቃላይ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ለአስተዳደሩ ምክር ቤት ጥያቄ መቅረቡን አስረድተዋል፡፡

ምንጭ: የአስተዳደሩ መ/ኮ
@YeneTube @FikerAssefa
ፔፕሲኮ የበጎ አድራጎት ፋውንዴሽን ኮሮና ቫይረስ ባስከተለው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ለተጎዱ እና ጫና ለደረሰባቸው ዜጎች 8 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ለገሰ።

ፋውዴሽኑ ይህንን ድጋፍ የሚሰጠው ከሜቄዶንያ አረጋዊያን መርጃ ማህበር ጋር በመቀናጀት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ባስከተለው ኢኮኖሚያዊ ጫና በስፋት ተጋላጭ ለሆኑ የማኅበረሰብ አካላትን ለመደገፍ መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል።የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሥጋት እና የንግድ እንቅስቃሴ ገደብ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የምግብ ዋስትና አደጋ ላይ ጥሎታል፡፡ለዚህ ዓለም አቀፋዊ የማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠትም ፔፕሲኮ ከታወቁ ግብረሰናይ ተቋማት ጋር በመጣመር በይበልጥ ጫናው ክንዱን ላሳረፈባቸው አካላት ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል። ይህ ድጋፍ ምግብ ይለግሱ ተስፋን ይቀጥሉ ፕሮግራም አቅመ ደካሞችን፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን በመደገፍ ከሚታወቀው ሀገራዊ የበጎ አድራጎት ተቋም መቄዶንያ ጋር በጥምረት የሚከናወን ነው ተብሏል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa