YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጆርጅ ፍሎይድ የሞተው በትንፋሽ እጥረት (Asphyxia) እንደሆነ የአስከሬን ምርመራው አረጋጧል ብሏል ቢቢሲ በዘገባው። ምንም እንኳን በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ ራሱን ስቶ ይታይ የነበረ ቢሆንም ህይወቱ ያለፈው ወደ ሆስፒታል እንደተወሰደ መሆኑ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from Kídus
⚜️SHEBA - ሺባ⚜️

📞 በ 0941158969 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን

CURREN⌚️ሰዓቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ከኩባንያችን (ሺባ) ይግዙ ይህንን::

⚠️(ሺባ) የተመሰረተበትን አንደኛ አመት እያከበርን ስለሆነ ‼️ነፃ ‼️ሰዐት ለማግኘት ከዌብ ሳይታችን ላይ ማንኛዉንም እቃ ይግዙ፡

👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼

Website - www.shebasluxury.com

⭕️የ 1 ወር ዋስትና እንሰጣለን⭕️

Telegram - https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFfS1CHMcuedhCLPBQ

Contact Admin @ki_d_us

📞 በ 0941158969 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን🏍
Forwarded from YeneTube
🏡 Nat mobile & Computers
💻DELL Vostro 15
Core i5 7th Generation
✒️ 2.7ghz Amazing speed
🖥 Screen :15. 6 inch
📼 Storage : 1Tb
Ram : 4gb
🔋 Battery >3hrs

💵Price : 17,500birr

. 0911522626
0953120011

TxT :- @natyendex
🔶 ለበለጠ መረጃ
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAELbSrbiTDHFnicnnA

አድራሻ ቦሌ መድሀኒያለም ሞርኒንግ እስታር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ከAngla burger ፊትለፊት
የኢፌድሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዳነች አበቤ በቅርቡ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል በቀረበው የአንድ አመት ሪፖርት ተፈፀሙ የተባሉ የመብት ጥሰቶችን ማጣራት መጀመራቸውን ጠቅሰው በይፋዊ ማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ያሰፈሩት:

"ሰበዓዊ መብት የምናከብረው እና የምናስከብረው ለማንም ብለን ሳይሆን ለህዝባችን መከበር እና ለፍትህ ስንል ነው። በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የወጣውን መግለጫ ተመልክተነዋል። የማጣራት ስራም ጀምረናል። የማጣራት ስራችንን አጠናቀን ምላሽ ለመስጠት በሂደት እያለን መግለጫው በተለያዩ ሚዲያ ተሰራጭቷል።አሁን ዘገባዉን ከይዘቱ፣ ከከአካሄዱ፣ እንዲሁም እውነተኛነት እና ገለልተኛነት የማጣራት ስራችንን በቶሎ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው። በማጣራት ስራችን በሚገኘዉም ዉጤት፣ ሪፖርቱ እውነት በሆነበት መወሰድ ያለበቸውን እርምጃዎች እንወስዳለን::ሀሰት በሆነበት ወይም በተጋነነበት አኳያ ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል ጋራ በመወያየት ሪፖርቱ እንዲስተካከል እንጥራለን። ይህ ባይቻል እንኳን ህዝባችንና አለም እውነቱን እንዲያውቀዉ በመረጃ አስደግፈን እናሳያለን።"

@YeneTube @FikerAssefa
ልጆቻቸው የጠፉባቸው ወላጆች"እነአቶ ንጉሡ ጥላሁን አናግረውናል። ሥራ እየሠራን ነው ብለውናል።

ከእናነተ ጋር ነን እያሉን ነው። መንግሥትን ነው የምንጠበቀው። የመንግሥትን ምላሽ ነው የምንጠብቀው። ሌላ ምን የምናደርገው ነገር አለን። ከቤታችን ቁጭ ብለን እያለቀስን እያነባን ነው። ሥራ አንሰራም ልጆቻቸን ተበትነው ነው ያሉት።"
"ባለቤቴ ምንም ዋጋ የላትም በህክምና ላይ ነው ያለችው። ህክምና ላይ ነው ያለችው። በጸበል ላይ ነው ያለሁት። ምንም አዕምሮ የላትም። ከወለል ላይ ወደቀች። እግዚኦ እያለች እየተንፏቀቀች እህል አትበላ፤ ምን አትል ይኼው መከራችንን ነው የምናየው" ሲሉ የልጃቸው መጥፋት ቤተሰባቸውን እንደጎዳው ይናገራሉ።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ከተሞችና የግዛት አስተዳዳሪዎች እየተቀጣጠለ ያለውን ተቃውሞ ማብረድ የማይችሉ ከሆነ እኔ ራሴ ወታደር አዝምቼ አበርደዋለሁ ሲሉ ዛቱ።

@Yenetube @FikerAssefa
የሊቨርፑል ተጫዋቾች በአፍሪካ አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ላይ በፖሊስ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም በልምምድ ሜዳቸው ማሃል ላይ ክብ ሰርተው በጉልበታቸው ተንበርክከው አጋርነታቸውን አሳዩ።

@Yenetube @Fikerassefa
ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች የተካተቱበት ልዑካን ወደ ሱዳን ድንበር አቀና!

በዋዜማ ራዲዮ

በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር ላይ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የኢትዮጵያና ወታደራዊና ሲቪል ልዑካን ቡድን በድንበር አካባቢ ተገኝቶ የሀገሪቱን ራስን የመከላከል ዝግጁነት የገመገመ ቅኝት ማድረጉን ዋዜማ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።መንግስት የድንበር አካባቢ የፀጥታ ችግሩ የጋራ ወታደራዊ አጣሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ አንዲጣራና በዲፕሎማሲ እንዲፈታ በይፋ የሱዳን መንግስትን ጠይቋል።ከአምስት ቀናት በፊት ሱዳን በኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች የተደገፉ ታጣቂዎች ድንበሬን ጥሰው በመግባት ጥቃት አድርሰውብኛል ስትል ከሳለች።

በጥቃቱ የሞትና የመቁሰል ጉዳት መድረሱንም ሱዳን ትናገራለች።ይህንንም ተከትሎ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በተፈጠረው ግጭት በኢትዮጵያም ሆነ በሱዳን በኩል ጉዳት ለደረሰባቸው ሀዘኑን የገለጸ ሲሆን እንዲህ አይነት አጋጣሚዎች በሁለቱ አገራት ሕዝቦች መካከል ያለውን ጥብቅ ወዳጅነት እንደማይወክል ገልጿል። ይሁንና ከሱዳን በኩል የብቀላ ጥቃት ሊኖር ይችላል በሚል ስጋት መንግስት ወታደራዊ ዕዞቹን በተጠንቀቅ እንዲጠብቁ ማዘዙን ሰምተናል። በዛሬው ዕለትም (ሰኞ) የአማራ ክልል የፀጥታ ሀላፊዎች እና በሰሜን እዝ አዛዥ ጀኔራል ድሪባ መኮነን የተመራ የልኡካን ቡድን ቅኝቶችን አድርጓል፡፡

ወታደራዊ አዛዦች የተካተቱበት የልዑካን ቡድን ጉብኝት በምእራብ ጎንደር የሚገኙ ባለኃብቶች በተረጋጋ መልኩ ስራቸውን ማከናወን እንዲችሉ አለኝታ መስጠትና የፀጥታ ዘርፉን ማዘመን እና በበቂ ሁኔታ በማሰማራት ከተለያዩ ትንኮሳዎች የመጠበቅ ዓላማ እንዳለውም ተረድተናል፡፡ምእራብ ጎንደር ከሱዳን ጋር የ400 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ድንበር የሚጋራ ሲሆን በድንበሩ አካባቢ ካለፉት አስራ አምስት አመታት ወዲህ ተደጋጋሚ ግጭት እየተፈጠረ መቆየቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። አካባቢው ሰፊ የጥጥ፣ ሰሊጥ፣ እጣን፣ እና ሌሎች የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የሚደረግበት ነው።

በአካባቢው ባለኃብቶች ብቻ ሳይሆን ገበሬዎችም ጭምር መሬታቸው በሱዳን ወታደሮች እንደተወሰደባቸው እና የሱዳን የጦር ሰራዊት በቋራ እና ታች አርማጭሆ ባሉ አካባቢዎች የኢትዮጵያ ድንበር ጥሶ እንደገባ አቤቱታ ሲቀርብ መቆየቱ ይታወሳል። ዋዜማ የኢትዮጵያ ድንበር ስለመጣሱ በራሷ አላረጋገጠችም። ከምንጮቻችን ባገኘነው መረጃ መሰረት የዛሬው የልዑካን ቡድኑ ቅኝት ሱዳን ሰሞኑን ወታደሮቼ ተገደሉብኝ በማለቷ የአጸፋ እርምጃ እንዳትወስድ የድንበሩን አካባቢ ለማጥበቅ እና አካባቢውን ለማልማት በሚደረገው ጥረት እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ዘላቂ መፍተሄ ለማምጣት ነው ተብሏል፡፡በሱዳን በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትርና በወታደራዊ ምክር ቤቱ መካከል ባለው ሽኩቻ ማዕከላዊነት ያለው የፀጥታ አመራር የለም።

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ከ400 ሺሕ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ተጠቅተዋል!

የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት በክልሉ የሚገኙ 400 ሺሕ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን አስታወቀ።ኢንስቲትዩቱ ለአዲስ ማለዳ በሰጠው መረጃ እንደገለጸው፣ በዚህ ዓመት ቁጥራቸው እጅግ የበዛ ሰዎች በወባ ለመጠቃታቸው እና በክልሉ ለተከሰተው የወባ በሽታ ስርጭት መስፋፋት ምክንያቶች ውስጥ በኅብረተሰቡ ዘንድ እንዲሁም በመንግሥት ተቋማት የተፈጠረ ትኩረት ማጣት ነው ሲል አስታውቋል። የኢንስቲትዩቱ የወባ በሽታ የቡድን መሪ ማስተዋል ወርቁ ለአዲስ ማለዳ ሲያስረዱ፣ የተጠቂዎች ቁጥር ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 73 በመቶ መጨመሩን አስታውቀዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ኦሮሚያ ነጆ አራት የመንግሥት ሠራተኞች በታጣቂዎች ተገደሉ!

በምዕራብ ኦሮሚያ በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ ባለፈው ዓርብ አራት የመንግሥት ሠራተኞች በታጣቂዎች መገደላቸው ተነገረ።ከጥቃቱ የተረፉት የነጆ ወረዳ አስዳዳሪ እና ከሟች ቤተሰቦች ቢቢሲ እንደተረዳው ዓርብ ዕለት የሸኔ አባላት ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች በ10 የመንግሥት ሠራተኞች ላይ በተፈጸመ ጥቃት አራቱ ሲገደሉ ሦስቱ የመቁሰል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ሦስት ሰዎች ደግሞ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከጥቃቱ ተርፈዋል።

ግንቦት 21/2012 ዓ.ም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር ለማከፋፈል ከተለያዩ ቢሮዎች የተወጣጣ ኮሚቴ አሞማ ዴገሮ ወደ ሚባል ቀበሌ ተጉዞ እንደነበነር የነጆ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ ተፈራ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የመንግሥት ሠራተኞቹ ከሄዱበት ስፍራ በሰላም ሥራቸውን ጨርሰው እየተመለሱ ዋጋሪ ቡና ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሲደርሱ ጸረ ሰላም በሆኑት የሸኔ ታጣቂዎች ተኩስ ተከፍቶበናቸዋል" ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።

ለመስክ ሥራ ተሰማርተው የነበሩት ሰዎች በአጠቃላይ 10 እንደነበሩ የሚያስታውሱት አቶ ተሊላ በጥቃቱ ከመካከላቸው አራቱ ተገድለዋል።
"አንደኛው ሟች አብዲ አበራ የሚባል ሹፌር ሲሆን ሁለተኛው የእንስሳት ሐኪም የነበረው ዳዊት ተርፋሳ ሲሆን፤ ባሕሩ አየለ እና እስራኤል መርዳሳ የሚባሉት ሟቾች ደግሞ የወረዳው ሚሊሻ አባላት ናቸው" ብለዋል። በታጣቂዎቹ በተሰነዘረባቸው ጥቃት ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪ ሦስቱ በጥቃቱ የቆሰሉት ሲሆን፤ ከጥቃቱ ጉዳት ሳይደርስባቸው ያመለጡት ደግሞ ሦስት ናቸው።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ ብቻ 3 ሺህ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው መግባታቸው ተገለጸ፡፡

የጋምቤላ ክልል መንግስት እንዳስታወቀው ባለፈው ሳምንት ብቻ ወደ ክልሉ 3 ሺ የሚሆኑ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በህገ ወጥ መንገድ ወደ ክልሉ መግባታቸውን አስታውቋል፡፡ምንም እንኳን በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የድንበር መውጫ መግቢያ በሮች ዝግ የተደረጉ ቢሆኑም ተጋክ በሚባለው ድንበር ላይ በ ህገወጥ መንገድ የገቡ ከ 3 ሺ በላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መኖራቸውን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ም/ሃላፊ ኦቶ ኦቶው ኦኮት ተናግረዋል፡፡

ስደተኞቹን እዛው ድንበር አቅራቢያ ላይ በሚገኝ መጠለያ እንዲቆዩ መደረጉንም ክልሉ አስታውቋል፡፡ስደተኞቹ ባሉበት መጠለያ ሆነው የኮሮና ቫይረስ ህክምና ምርመራ እየተደረገላቸው መሆኑን የነገሩን አቶ ኦቶው እስካሁን ከ 100 በላይ ለሚሆኑ ስደተኞች ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡የስደተኞቹን የቀጣይ ሁኔታና መደረግ ስላለባቸው የቁጥጥር ተግባራት ከ ስደተኞችና ስደት ተመላሾች ኤጀንሲ ጋር እየተነጋገሩ መሆኑንም ተናግረዋል።አሁንም ቢሆን ወደ ክልሉ በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው የሚገቡ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ለመቆጣጠር በየድንበር ላይ ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ማዕከላት ቁጥር 46 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ መግባቱ ሲረጋገጥ ምንም ዓይነት የመመርመሪያ ማዕከል ያልነበራት ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት 46 ማዕከላት እንዳሏት የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ሚኒስቴሩ እስከ ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለ112,377 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ መከናወኑን በመግለጽ ይህም በአገር አቀፍ ደረጃ በአጭር ጊዜ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) በሽታ የላብራቶሪ ምርመራ አቅም እየጨመረ እንደሚገኝ ያሳያል ብሏል፡፡በቀጣይም የምርመራ ማዕከላትን የማስፋፋት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
በቦሌ ክፍለ ከተማ የውሃ መስመር ለአርሶ አደር ልጆች ብቻ መዘርጋቱ ቅሬታ አስነሳ!

በቦሌ ከፍለ ከተማ ስር ባሉ ኹለት ወረዳዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ለአርሶ አደር ልጆች ብቻ የውሃ መስመር ዝርጋታ እየተከናወነ ነው፣ ክፍለ ከተማው በተገቢው መንገድ እያስተናገደን አይደለም ሲሉ ቅሬታቸውን አቀረቡ።በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 እና ወረዳ 01 ነዋሪ የሆኑት ቅሬታ አቅራቢዎች ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣ ክፍለ ከተማው ጉዳያቸውን ተመልክቶ እልባት እንዲሰጣቸው ተብሎ ከወረዳቸው የድጋፍ ደብዳቤ ለ75 በላይ አባ ወራዎች ቢያስገቡም አለመስተናገዳቸውን ተናግረዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ለሚቀጥሉት 4 ወራት ለጤና ተቋማት ብቻ 130 ሚሊየን የአፍ እና አፍንጫ ሜዲካል ጭንብሎች እንደሚያስፈልጉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናገሩ።

 የጤና ሚኒሰትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የመከላከል ስራን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፥ የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ የሚያስችሉ ግብአቶችን የሟሟላት ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።በተለይም በጤና ተቋማት ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የሚሆኑ የሜዲካል ማስኮች አለማቀፋዊ እጥረት መኖሩን በመግለፅ፤ እንደ ሀገርም በዙ ክፈተቶች መኖራቸውን አንስተዋል።ወረርሽኙ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ እንደ ሀገር 4 ሚሊየን ማስክ ብቻ እንደነበር የተናገሩት ዶክተር ሊያ፥ ከዛ በኋላ በተሰሩ ስራዎች ከ7 ሚሊየን በላይ ማስኮችን ለጤና ተቋማት ማሰራጨት ተችሏል ብለዋል።እንደ ሀገርም የቫይርሱን ስርጭት ለመከላከል በሚሰራው ስራ በሚቀጥሉት 4 ወራት ለጤና ተቋማት ብቻ 130 ሚሊየን ሜዲካል ማስክ እንደሚያስፈልግ መለየቱን ነው ሚኒሰትሯ የተናገሩት።

የማስክ እጥረትን ለመፍታት ሲባል ከውጭ ሀገር ከማስመጣተ እንዲሁም በእርዳታ ከማግኘት በተጨማሪም በሀገር ውስጥ ጥራቱን የጠበቀ እና መስፈርቱን ያሟላ መስክ እንዲመረት ለማደርግም ከሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሯ ተናገርዋል።በተጨማሪም የመተንፈሻ አካል አጋዥ መሳሪያ ወይም ቬንትሌተር በአለም አቀፍ ደረጃ እጥረት ያለበት መሆኑን የሚናገሩት ዶክተር ሊያ፥ ከዚህ በፊት ለዚሁ ስራ የሚውል እንደ ሀገር 22 ቬንትሌተሮች ብቻ እንደነበሩም አንስተዋል።

በጥገና የተስተካከሉ እና በእርዳታ የተገኙትን ጨምሮ አዲስ ግዥ ተደርጎም አሁን ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ 221 ቬትሌተሮች ዝግጁ መደረጋቸውንም ተናግረዋል።የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የኦክስጅን ምርትን በሀገር ውስጥ በስፋተ እንዲመረት ማደረግ ላይም በትኩረት እየተሰራ መሆኑን እና ምርቱ የሚቀርብባቸው 3 ሺህ 600 የኦክስጅን ሲሊንደሮችም በሀገር አቀፍ ደረጃ መሰራጨታቸውን ተናግረዋል።እንደ ሀገር አሁን ያለው የቫይርሱ ስርጭት መስፋትን ተከትሎ ግብእቶችን ከማሟላት በተጨማሪ የምርመራ አቅምን ማሳደግ ላይም ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ዶክተር ሊያ በመግለጫቸው አንስተዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 87 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል!

@YeneTube @FikerAssefa
ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 14 ደርሷል፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት የሁለት ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን አንደኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን የ30 አመት ወንድና፣ ሁለተኛዋ የ56 አመት ሴት በአዲስ አበባ በተጓዳኝ ህመም ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ፣ ሁለቱም ከሞቱ በኋላ ቫይረሱ እንዳለባቸው ለአስከሬን ምርመራ በመጡበት በተወሰደ ናሙና ነው የታወቀው ።በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ሁለት (14) ደርሷል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 87 ሰዎች ሲሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው፣ በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(59) ሴት(28) ናቸው!

➡️ዕድሜያቸው ከ10-70 አመት የሆኑ

➡️28 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው

➡️18 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው

➡️41 የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው።

➡️ተጨማሪ 6 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 8 ከሶማሌ ክልል ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 231 ደርሷል።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(67)፣ ከኦሮሚያ ክልል(6)፣ ከትግራይ ክልል(2) አማራ ክልል(7)፣ ከሀረሪ ክልል(1) እና ከሶማሌ ክልል(4) በኮሮና የተያዙ በድምር 87 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,344 ደርሷል።

➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 8 ደርሷል።

➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 2 ሞት የተመዘገበ ሲሆን ጠቅላላ የሟቾች ቁጥር 14 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከ3.2 ቢሊዮን ብር በላይ የግብር ዕዳ ተሰረዘለት።ዕዳው የተሰረዘው ድርጅቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያሳድረውን ጫና ተቋቋሞ በግብር ከፋይነት እንዲቀጥል ለማድረግ ታስቦ ነው።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
እስከ 1 ሺህ 200 ሕሙማንን የማስተናገድ አቅም ያለው የአዲስ አበባ ሚሊኒየም የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ሕሙማንን መቀበል ጀመረ።

ባለፉት ሁለት ወራት ማዕከሉን የማደራጀት ሥራ ሲሰራ መቆየቱን የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እስማኤል ሸምሰዲን ለኢዜአ ገልጸዋል። ማዕከሉ 40 የጽኑ ሕሙማን መኝታዎችና 1 ሺህ ጽኑ ያልሆኑ ሕሙማን ታካሚዎች አገልግሎት መስጠት ይችላል።ጎን ለጎንም የላቦራቶሪ፣ የመድሃኒት ቤት፣ የጤና ባለሙያዎች ልብስ መቀየሪያ፣ መታጠቢያዎችና ሌሎች ክፍሎችም ተዘጋጅተዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa