YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በድሬዳዋ ከነገ ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የህዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች በሰሌዳ ቁጥራቸው የመጨረሻ ቁጥር መሰረት ሙሉና ጎዶሎ በሚል አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል:: በዚህም መሰረት በነገው ዕለት ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም ጎዶሎ ቁጥሮች አገልግሎት የሚጀምሩ ይሆናል::ከዚሁ ጋር ተያይዞ የአፍ መሸፈኛ ጭንብል /ማስክ/ ከማድረግ ጋር ተያይዞ በሀገር ደረጃ የተሰጠው መመሪያ በአስተዳደሩ ተግባራዊ እንዲሆንና ጥብቅ ቁጥጥርም እንደ ሚደረግ ግብረ-ሀይሉ አሳስቧል::
ግንቦት 20 ቀን 2012 ዓ.ም

ምንጭ: የከ/አስ/ፖሊስ ኮሚሽን
@YeneTube @FikerAssefa
በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው መመለስ ተጀመረ።

በሊባኖስ በተፈጠረ የፖለቲካ ቀወስ ምክንያት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን በአስቸጋሪ ሁኔታ በመምራት ላይ ነበሩ።እነዚህ ዜጎችም በተደጋጋሚ ወደ አገራችን መልሱን የሚል ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተው የኢትዮጵያ መንግስትም ከሊባኖስ አቻው ጋር ባደረገው ውይይት ዜጎቹ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ስራ ሲሰራ ቆይቷል።በዛሬው ዕለትም በመጀመሪያው ዙር ዛሬ ጧት በዲፖርቴሽን ማዕከልና በእስር ቤቶች የነበሩ ዜጎች፣ በኮሙኒቲ እና በካሪታስ መጠለያዎች የነበሩ እንዲሁም ሌሎች ወደ አገራቸው ለመጓዝ ሲጠባበቁ የነበሩ በአጠቃላይ 337 ዜጎች ወደ አዲስ አበባ መጥተዋል።

የንዚህ ዜጎች ሙሉ የትራንስፖርት ወጪያቸውን በኢትዮጵያ መንግስት በመሸፈን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል፡፡በምዝገባ ወደ አገር ቤት ለመጓዘ ለቀራማ እና ለትራንስፖርት ወጭዎች የሚሆን 550 ዶላር ከፍለው የነበሩ ዜጎቻችንም ሙሉ ገንዘባቸው 550 ዶላር ተመልሶላቸው ወደ አገር ቤት እንዲጓዙ መደረጉንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

እነዚህ ዜጎችም የኮቪድ19 ፕሮቶኮልን በጠበቀ መልኩ ዜጎቹ ተዘጋጅተው እንዲሄዱ በቤይሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ማመቻቸቱን አስታውቋል።ከሊባኖስ የተመለሱ ዜጎችም ወደየቤተሰቦቻቸው ከመቀላቀላቸው በፊት በቀጥታ ወደ ተዘጋጀላቸው ለይቶ ማቆያዎች ይሄዳሉ በቀጣይም ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ሲረጋገጥ ወደ ቤተሰቦቻቸው ይገባሉ ተብሏል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ውስጥ ተጨማሪ 100 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4950 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ (100) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ስምንት መቶ ሰላሳ አንድ (831) ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ 7ኛው ሞት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተመዝግቧል!

በተጓዳኝ ህመም ህክምና ላይ የነበሩ የ70 አመት ሴት የምርመራ ናሙና ተወስዶ ውጤቱ ሳይታወቅ ህይወታቸው ካለፈ በኋላ ቫይረሱ እንደነበረባቸው ተረጋግጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 100 ሰዎች 98ቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንድ የብሩንዲ ዜጋ መሆኑ ተገልጿል(በሪፖርቱ እንዱ የየት ሀገር ዜጋ እንደሆነ አልተገለፀም)፣ በፆታ ወንድ(53) ሴት(47) ናቸው

➡️ዕድሜያቸው ከ3-70 የሆኑ

➡️3 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው

➡️35 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው

➡️62ቱ የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው።

➡️ተጨማሪ 10 ሰዎች ከአዲስ አበባ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 191 ደርሷል።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(94)፣ ከትግራይ ክልል ሁሉም የጉዞ ታሪክ ያላቸው (1)፣ ከሶማሌ ክልል የጉዞ ታሪክ ያላቸው (2)፣ ከኦሮሚያ ክልል(3)፣ በኮሮና የተያዙ በድምር 100 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 831 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ወገኖች ለቫይረሱ የመጋለጥ ስጋት እንዳሳደረባቸው ገለፁ!

ለጤንነታችንና ለደህንነታችን ሲባል ለይቶ ማቆያ እንድንገባ ቢደረግም የማቆያ ማእከላቱ አመቺ ባለመሆናቸው ለቫይረሱ እንዳንጋለጥ ስጋት አድሮብናል ሲሉ በምዕራብ ጎንደር ዞን በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የሚገኙ ዜጎች ገለጹ፡፡የዞኑ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ግብረ-ኃይል በበኩሉ የተነሳው ችግር ትክክል መሆኑን አምኖ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
አሳዛኝ ዜና!

በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ የጣለው ዝናብ ያስከተለው ናዳና ጎርፍ የሞተ ሰው ቁጥር እስካሁን 10 መድረሱን የጋሞ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ ገለጸ።

የጋሞ ዞን እርሻና ተፈጥሮ መምሪያ ኃላፊ አቶ አንደኛ ሸናሌ አሁን በሰጡት መረጃ 10 ሰው የሞተ ሲሆን በናዳው ተቀብረው ከነበሩት 2ሴት 4ወንድ በድምሩ የ6 ሰው አስከሬን ወጥቷል። የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊጨምር እንደሚችል ተገልጿል።ዝናቡ በመቀጠሉ የናዳው ሁኔታም አልቆመም።የአስከሬን ፍለጋውንም አዳጋች አድርጎታል ብልዋል። በተመሳሳይ በገረሴ ወረዳ ጋርባንሳ ጋሎ ቀበሌ 3 ቤት ሰጥሟል።

ምንጭ: የዞኑ መ/ኮምኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa
333 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ዛሬ ከሊባኖስ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ!

ሲደረግ የነበረው አስፈላጊው ዝግጅት በመጠናቀቁ ዛሬ ግንቦት 20 ቀን 2012 ዓም 333 ኢትዮጵያዊያን ከሊባኖስ እንዲመለሱ ተደርጓል። በቀጣዩ ቅዳሜም 320 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከሊባኖስ ወደ አገራቸው የሚገቡ ይሆናል።

Via Spokesperson of MoFA
@YeneTube @FikerAssefa
በአሶሳ ኮሮናን ለመከላከል ተጨማሪ መናኸሪያና የግብይት ቦታዎች ተዘጋጁ!

የከተማአስተዳዳሩ ከንቲባ አቶ ዑመር መሐመድ ለኢዜአ እንዳሉት ከፍተኛ ሕዝብ ሲያስተናግድ ከነበረው ብቸኛው የከተማ አውቶቡስ መናኸሪያ በተጨማሪ የመለስተኛ አገር አቋራጭ ጊዜያዊ መናኸሪያ ማዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡የኅብረተሰቡን አሰፋፈር፣ የትራንስፖርትና ሌሎችንም መሠረታዊ አገልግሎቶችን ባማከሉ ቦታዎች ሦስት ጊዜያዊ የግብይት ሥፍራዎች ተዘጋጅተው የፊታችን ቅዳሜ ሥራ ይጀምራሉ ተብሏል።ሁኔታዎች በዚህ መልኩ ከተመቻቹ ቀጣዩ ሥራ የአስተዳደሩ አዋጁን በሚገባ ማስተግበር ነው ያሉት አቶ ዑመር ከዚህ በኋላ በተለይም አካላዊ ርቀትን በማይጠብቁ ሰዎች ላይ ተገቢው እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከ20 ቀናት በኋላ እንዲጀመር ክለቦች ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰማ። ይህንንም ተከትሎ June 17 ሼፈልድ ዩናይትድ ከአስቶንቪላ እንዲሁም ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል በሚያደርጉት ጨዋታ እንደሚጀመር ከዘ ኢዲፔንደንት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኬንያ በተከታታይ ለሁለተኛ ቀን ኮሮና ቫይረስ ከተከሰት ቀን ወዲህ ሪከርድ የተባለ የአዲስ ኬዝ ቁጥር ተመዝግቦባታል። ባለፉት 24 ሰዓታት ከወሰደችው 2831 ናሙናዎች 147 አዲስ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን አግኝታለች። 3 ተጨማሪ ሰዎችም ሞተዋል። እስካሁን በሀገሪቱ 1,618 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 58ቱ ሲሞቱ 421 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
⬆️ኮቪድ 19ን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ የወጣ ሪፖርት ፣

ቫይረሱ የተገኘባቸው ክ/ከተማዎችና የተያዙ ሰዎች ቁጥር :

1.አዲስ ከተማ 138
2.ልደታ 133
3.ቦሌ 62
4.ጉለሌ 44
5.ኮልፌ ቀራኒዮ 47
6.ንፋስ ስልክ ላፍቶ 29
7.የካ 26
8.አራዳ 23
9.አቃቂ ቃሊቲ 10
10.ቂርቆስ 19
11.አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያሉ 21 ሲሆኑ በድምር በከተማዋ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 552 ነው።

Via Addis Ababa City P.S
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
በቴሌግራም @Orangebusinessnetwork ን በመጎብኘት ለእርሶ እና ለድርጅቶ እድገት የሚረዱ መረጃዎች ፤ሀብቶችን እና ማበረታቻዎችን ያገኙ!

የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ
T.me/Orangebusinessnetwork
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ናሙና መመርመር የሚያስችል ማሽን ለመዳ-ወለቡ ዩኒቨርሲቲ ለገሰ። የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በፊት 2 የኮሮና ቫይረስ ናሙና መመርመሪያ ማሽኖችን ለነቀምቴ ምዕራብ ላቦራቶሪና ለአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መለገሱ ይታወሳል።

በተያያዘ ዜና በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በይፋ ተጀመረ። የምርመራ ማዕከሉ በሙሉ አቅሙ ከሰራ በአንድ ቀን 400 ሰዎችን የመመርመር አቅም አለው ሲል ዩኒቨርስቲው ገልጿል።

Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
#NewsAlert
የቅድመ ምረቃ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ሳይማሩ እንደማይመረቁ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

ለሳይንስና ከፍትኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑና በስራ ላይ ያሉ 44 ዩኒቨርሲቲዎች ከመጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደታቸውን ማቋረጣቸው ይታወሳል።የሳይንስና ከፈተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፥ በቅድመ-ምረቃ መርሃ ግብር በቴክክኖሎጂ ትምህርት ማስቀጠል ባለመቻሉ ተማሪዎች ሳይማሩ አይመረቁም ብለዋል።“በቴክኖሎጂ የቅድመ-ምረቃ ትምህርት ማስቀጠል ከሞላ ጎደል አልተቻለም፤ እያንዳንዱ ተማሪ በየቀኑ፣ በየሳምንቱ የሚማረውን እያነበበ፤ ምዕራፍ በምዕራፍ፣ ሞጁል በሞጁል ተምሮ ምዘና እየተደረገለት አልቆየም።

በዚህ ረገድ ያልመጣን፣ የትምህርቱን ይዘት ያላጠናቀቀን ተማሪ ተምሯል ብሎ ወስዶ፤ ይህንን ኮርስ ጨርሰሃል፣ በዚህ መልኩ ተገምግመሃል እና ይህንን ውጤት አግኝተሃል ብሎ ውጤት ሰጥቶ ማስመረቅ በትምህርትም በአሰራርም ወንጀል ነው፤ መሰል አካሄድ አይፈቀድም፤ እንደዚህም አይሆንም!” ብለዋል።የድህረ ምረቃ የሁለተኛ እና የሶስተኛ ዲግሪ መርሃ-ግብር በቴክኖሎጂ ማድረስ በመቻሉ ይመረቃሉ ከሚል ድምዳሜ ተደርሷል።ሆኖም የቅድመ-ምረቃ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ምረቃ በኮቪድ 19 የስርጭት መጠን የሚወሰን እንደሆነ ነው ዶክተር ሳሙኤል የተናገሩት፤ ይህም የምረቃ ዓመታቸውን ተገማች የማያደርገው ነው።

ተጨማሪ ለማንበብ👇👇👇
https://telegra.ph/MoSHEs-statement-on-students-graduation-05-28
ግብፅ ኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ ከተከሰት ቀን ወዲህ ሪከርድ የተባለ የአዲስ ኬዝ ቁጥር ተመዝግቦባታል። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 1127 አዲስ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን አግኝታለች። 29 ተጨማሪ ሰዎችም ሞተዋል። እስካሁን በሀገሪቱ 20793 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 845ቱ ሲሞቱ 5359 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሃይማኖት በዳዳን ገዳይ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ!

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጤና ኮሌጅ የሁለተኛ ድግሪ ተማሪ የነበረችው እና ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ/ም በኮሌጁ አስተዳደር ህንፃ ላይ በሚገኘው የላቦራቶሪ ቤተ ሙከራ ክፍል ለምርምር በገባችበት ሁኔታ ህይወቷ ያለፈው ሀይማኖት በዳዳ ገዳይ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ፖሊስ ኮሚሽኑ እንዳለው የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ የሆነውና በ20ዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ደግነት ወርቁ የተባለ ወጣት ነው የ27 ዓመቷን ሃይማኖት በዳዳ ሕይወት ያጠፋው፡፡ትናንት ምሽት 1 ሰዓት ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጋር በመሆን ቀን ከሌሊት ባካሄደው ክትትል ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ሊያውለው መቻሉን አስታውቋል፡፡

ግለሰቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪ እንደነበርና የኤች አይ ቪ ኤድስ መድኃኒት ለማግኘት ምርምር ላይ ስለሆንኩ የጥቁር አንበሳ ሐኪሞች ይርዱኝ በማለት ወደ ግቢው በተለያዩ ጊዜያት ይመላለስ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ከሟች ጋር ምንም ዓይነት ትውውቅ እንዳልነበራቸው ትናንት እስከ እኩለ ሌሊት በተደረገ ምርመራ የወንጀሉን ዝርዝር ለፖሊስ ማስረዳቱም ታውቋል፡፡በግንቦት 17 ቀን 2012 እንደልማዱ ለዚሁ ጉዳይ እንደመጣ ገንዘብ እንደተቸገረና ቢላዋ ይዞ በግቢው ውስጥ ከሚገኙ ቢሮዎች በአንዱ ላፕቶፕ ወይም ሞባይል ካገኘ ሰርቆ ሽጦ ለመጠቀም ሲዟዟር የሟች ክፍል ክፍት ሆኖ በማግኘቱ መግባቱን አስረድቷል፡፡

ሟች ሞባይሏን እንድትሰጠው ጠይቋት እምቢ ስትለው መታገላቸውንና ከዚያም በያዘው ስለት ወግቷት ንብረቱን ይዞ መውጣቱን ተናግሯል፡፡ፖሊስ ከሟች ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው 12 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ተጨማሪ ምርመራ ማድረጉን የግድያ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ለኢቲቪ ገልጿል፡፡ለፖሊስ ምርመራ ትልቅ አቅም የሆነው የሟች ወላጅ አባት ከሳምንት በፊት ለልጃቸው የሰጧት የ5 ሺ ብር ቼክ ነው፡፡ገዳዩ በወቅቱ የሟችን ላፕቶፕና ሞባይል ፓስፖርት መታወቂያና ይህንን ቼክ ወስዶ ስለነበር ቼኩን የካ አካባቢ በአንድ ባጃጅ ተሳፍሮ አሽከርካሪውን መታወቂያ ስላልያዝኩ በአንተ መታወቂያ ይህንን ብር አውጣልኝ ብሎት የባጃጅ ሹፌርም መልኩን አስተውሎ ስለነበር ምርመራው ከዚህ እንደጀመረ ፖሊስ ገልጿል፡
ኮሚሽኑ በወቅቱ የሆስፒታሉ ሴኩሪቲ ካሜራ አፕዴት ሳይደረግ ከአገልግሎት ውጪ መሆኑንና የጥበቃ ሰራተኞችም ቢላዋ ተይዞ እስከሚገባ ፍተሻቸው አጋላጭ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የሸዋል በዓልን ለማክበር በሚል ወደ ስልጤ ዞን የሚመጡ የብሔረሰቡ ተወላጆችን ለ14 ቀናት ማቆያ እንዲገቡ የዞኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተግባሪ ግብረ-ሀይል ውሳኔ አሳለፈ።

በዘርፉ የተደራጀው ግብረ ሀይል ትናንት ማምሻውን በጋራ በመምከር የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሰለፉን ለዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ገልጿል።ለተከታታይ አምስት ቀናትም የባጃጅ ትራንስፖርት እንደሚቆምም ግብረ-ሀይሉ በመግለጫው ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል።ግብረ ሀይሉ በዓሉን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በዓሉን በዞኑና ከዞኑ ውጪ በሚኖሩ የብሔረሰቡ ተወላጆችና የማህበረሰብ ክፍሎች በዓመት አንዴ ተገናኝተው በድምቀት የሚያከብሩት እንደሆነ ዝርዝር ሃሳቦችን አንስቶ በጥልቀት ተወያይቷል።ይሁንና ዘንድሮ በአለም፣ በአህጉርና በሀገራችን በፍጥነት እየተስፋፋ በመጣው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ማህበረሰቡ በዓሉን በያለበት እንዲያከብር በመግለጫው መልዕክት ተላልፏል።ይህን ተላልፈው ለበዓሉ በሚል ወደ ዞኑ የሚመጡ የማህበረሰቡ የአብራክ ክፋዮችና የበዓሉ አክባሪዎች እሚኖሩ ከሆነ ግን ለህዝቡ ደህንነት ሲል ለ14 ቀናት ወደ ተዘጋጁ ማቆያዎች እንዲገቡ ለማድረግ እሚገደድ ስለመሆኑ ውሳኔ አሳልፏል።

ምንጭ: የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዳሴው ግድብ ውኃ የሚያርፍበት የደን ምንጣሮ ሊጀመር ነው!

የሕዳሴው ግድብ ፕሮጀክት በመጪው ሐምሌ ውሃ ሙሊት የሚጀምር በመሆኑ ውኃ የሚተኛበት አንድ ሺ ሄክታር የደን ምንጣሮ ሥራ በመጪው ሰኞ ግንቦት 24 እንደሚጀመር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት አጀንሲ አስታወቀ።ለምንጣሮውም በአንድ ሄክታር 29 ሺ ብር ወጪ ይደረጋል፡፡የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በሽር አብዱራሂም በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳሉት፣ ከዚህ በፊት በተከናወኑት የታላቁ የሕዳሴው ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የደን ምንጣሮ ሥራዎች የክልሉ ሥራ አጥ ወጣቶች እምብዛም ተጠቃሚ እንዳልነበሩ ገልጸው በዚህ ዓመት የሚከናወነውን የደን ምንጣሮ ሥራ በክልሉ ሥራ አጥ ወጣቶች እንዲከናውኑ መደረጉ የሚያስመሰግን ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ኃላፊነትን የሚጠይቅ እንደሆነ ተናግረዋል።በዚህ ዓመት መያዝ የሚጀመረው ውኃ የሚተኛበት አንድ ሺ ሄክታር ቦታ ለምንጣሮ መዘጋጀቱን የተናገሩት አቶ በሽር ለዚህ ሥራም በ70 ማህበራት የተደራጁ አንድ ሺ ሁለት መቶ ወጣቶችና በሥራቸው ከ800 በላይ ወጣቶች (በድምሩ ከሁለት ሺ በላይ የሚሆኑ የክልሉ ሥራ አጥ ወጣቶች) በ45 ቀናት ሥራውን ለማጠናቀቅ ከሚመለከተው አካል ጋር ውል ማሰራቸውን ተናግረዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa