YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኮድ ሁለት የቤት ተሸከርካሪዎች ተጥሎ የነበረዉ ክልከላ ተነስቶ አጠቃላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን ለመገደብ የሚያስችል አማራጭ ክልከላ እንድተገበር በሚኒስትሮች ኮሚቴ መወሰኑን ዛሬ በጠ/አቃቤ ህግ ተገልጿል።

በሌላ በኩል የትራንስፖርት መጨናነቅን ለመቀነስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የስራ መግቢያ ስአት 1፡30 እንዲሆን የተቀመጠ ሲሆን መዉጫ ስአቱም 9፡30 እንዲሆን ተደርጎ ተሸጋሽጓል ብሏል የጠ/አቃቤ ህግ መግለጫ።

@YeneTube @FikerAssefa
እንቅስቃሴ ለመቀነስ ተብሎ ከተወሰዱ እርምጃዎች አንደኛው በሀገር አቋራጭ ተሸከሪካሪዎች የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ነው፡፡

የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ሰዎች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ለመገደብ አስተዋጽኦ እንደሚያደረግ በትራንስፖርት ሚኒስቴር የተደረገው ጥናት ያመላክታል፡፡በዚሁ መሰረት አገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች መደበኛ የወንበር አቅማቸዉ ከ45(አርባ አምስት) ሰዉ በላይ የሆነ ተሸከርካሪዎች የሚያስከፍሉት የታሪፍ ጭማሪ ከመደበኛ ዋጋዉ 75% እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን መደበኛ የወንበር ቁጥራቸዉ እስከ (45) አርባ አምስት ሰዉ የሆኑ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች የሚያስከፍሉት የታሪፍ ጭማሪ ደግሞ 100% መሆኑ ተወስኗል፡፡

-ጠ/አቃቤ ህግ
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
በቴሌግራም @Orangebusinessnetwork ን በመጎብኘት ለእርሶ እና ለድርጅቶ እድገት የሚረዱ መረጃዎች ፤ሀብቶችን እና ማበረታቻዎችን ያገኙ!

የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ
T.me/Orangebusinessnetwork
በአዲስ አበባ ለበርካታ የኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሕክምና መስጫ የሚውል 'አዲስ አበባ ኮቪድ-19 ፊልድ ሆስፒታል ተገነባ።

በቅርቡ ሥራ የሚጀምረውን ሆስፒታል የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰና የዓለም የምግብ መርኃ ግብር ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ መርቀው ከፍተውታል።በቦሌ ቡልቡላ አካባቢ የሚገኘው ይህ የፊልድ ሆስፒታል 25 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፥ በዓለም የምግብ መርኃ ግብር ድጋፍ የተሰራ ነው ተብሏል።በሦስት ሣምንታት ውስጥ የተገነባው ሆስፒታሉ ቀሪ የማጠናቀቂያ ሥራዎች ተከናውነውለት ከ10 ቀናት በኋላ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል።ሆስፒታሉ በተለያየ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሕክምና መስጫነት የሚውል ሲሆን በዓለም ጤና ድርጅት የጥራት ደረጃ መሰረት መገንባቱ ተጠቁሟል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐርብ እንደሚሰበሰብ በፌስቡክ ገጹ ገልጧል፡፡

መወያያ አጀንዳዎቹም

1. የም/ቤቱን 5ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፣
2. የፌዴራል መንግስት የ2012 በጀት ዓመት የተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ማጽደቅ፣
3. የሰው ሀብትና ቴከኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽንን ለመደንገግ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ማጽደቅ፣
4. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፣
5. የልዩ የመንግስት ዕዳ ሰነድ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፣
6. የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፣
7. የጂኦተርማል ሀብት ልማት አዋጅን ለማሻሸል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፣ ይሆናል

@YeneTube @FikerAssefa
ከ219,000 በላይ ዜጎችን ከጎዳና ሕይወት ለማውጣት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡

ስምምነቱ የተፈረመው በሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴርና በኤልሻዳይ ሪሊፍና ዲቨሎፕመንት አሶሼሽን መካከል መሆኑ ተሰምቷል፡፡በመጪዎቹ 3 እና 4 ዓመታት ውስጥ ከ219,000 በላይ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶችን ከጎዳና ላይ ለማንሳት መታቀዱን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰምተናል፡፡በቅርቡ የመጀመሪያው ዙር ተግባራዊ ሲደረግ 20,000 ዜጎች ከጎዳና ላይ እንደሚነሱ ተነግሯል፡፡አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ጎዳናዎች ላይ የሚኖሩ ዜጎች እንዲነሱ ተደርጎ በኤልሻዳይ ሪሊፍ እና ዴቨሎፕመንት ማዕከላት ለ9 ወራት እንዲቆዩ ይደረጋል ተብሏል፡፡ለ3 ወራት የሥነ - ልቦና ስልጠና ለ6 ወራት ደግሞ የክህሎት ስልጠና ተሰጥቷቸው ራሳቸውን የሚችሉበት መንገድ እንደሚመቻችላቸውም ሰምተናል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አንዲት የህክምና ተማሪ በላብራቶሪ ከፍል ውስጥ ሞታ ተገኘች የአዳማ/ ናዝሬት ተወላጅ የሆነችው የ27 አመቷ የድህረ ምረቃ ተማሪ ምርምር በምታደርግበት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ትምህርት ላብራቶሪ ክፍል ውስጥ ሞታ እንደተገኘች ፊደል ፖስት ከሆስፒታሉ የየስራ ሀላፊዎች አረጋግጧል። ሐይማኖት በለው የተባለችው ይህች ወጣት የድህረ ምረቃ ትምህርቷን ለማጠናቀቅ ባቀረበቸው ጥናት…
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከተፈፀመው የግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ አራት ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ውለዋል፡፡

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጤና ኮሌጅ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ የሆነቸው ሀይማኖት በዳዳ ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ/ም በኮሌጁ አስተዳደር ህንፃ ላይ በሚገኘው የላቦራቶሪ ቤተ ሙከራ ክፍል ለምርምር በገባችበት መገደሏን ኮሚሽኑ ገልፆ የተለያዬ የሰውነት ክፍሏ በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተወግታ ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ/ም ከቀኑ 11 ሰዓት አስከሬኗ በክፍሉ ውስጥ ተገኝቷል፡፡ የሟች ሞባይል እና ሌሎች ዕቃዎች መወሰዳቸው የታወቀ ሲሆን በወንጀሉ የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦችን ይዞ ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጅቡቲ በአንድ ቀን ብቻ 229 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘውባታል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ጅቡቲ 989 ሰዎችን መርምራ 229 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን አግኝታለች፣4 ሰዎችም ሞተውባታል። እስካሁን በሀገሪቱ 2697 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆኑ 18ቱ ሞተዋል፣ 1185 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የጭነት መኪና ተገልብጦ አሽከርካሪውን ጨምሮ የ10 ጫኝና አውራጆችን ህይወት ቀጠፈ፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ ከጃቢ ገነት ወደ ደብረ ኤልያስ ከተማ እህል ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3-44850 ኢት የጭነት ማመላለሻ ተሸከርካሪ ዛሬ ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ በመገልበጡ አሽከርካሪውን ጨምሮ 10 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ አስታዉቋል።የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳዉ እንደገለጽት አደጋው የደረሰባቸው ጫኝና አውራጆች ሲሆኑ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

Via infoeastgojjam
@YeneTube @FikerAssefa
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በእገታ ወንጀል የመያዥያ ትእዛዝ ወጦባቸው የቆየ 3 "ፀረ-ሰላም ኃይሎች" ዛሬ ከተደረገ የተኩስ ልውውጥ በኋላ መመታታቸው የወረዳው የሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት አስታወቀ።"ፀረ-ሰላም ኃይሎቹ" በተደጋጋሚ አርሶ አደሮችን፣ ሞተረኞችን እንዲሁም መንገደኞችን በመቀማትና ሰዎችን በማገት ገንዘብ ይቀጡ ነበር ተብሏል።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም ዙሪያ ከአስፈፃሚ ኮሚቴው ጋር ተፍጥሮ የነበረውን የሀሳብ ልዩነት ለመፍታት እየተወያየ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁና የማስፈፀሚያ ደንቡ የተወሠኑ አንቀፆች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅትም ቢሆንም መከበር የሚገባቸውን ሰብዓዊ መብቶች የሚጥሱ በመሆናቸው ሊሻሻሉ ይገባል በማለት ሚያዚያ 26 ቀን 2012 ዓ.ም ለመንግስት የማሻሻያ ምክረ ሀሳቦችን አቅርቧል፡፡ኮሚሽኑ በሕጎቹ ላይ ካቀረባቸው የማሻሻያ ምክረ ሀሳቦች መካከል አንዱ የህጋዊነት መርህን የተመለከተ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ‹‹ማንኛውም አገር በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔ ውስጥም ቢሆን የመንግስት የህግ የበላይነት እና በህግ የመተዳደር ግዴታ ቀሪ አይሆንም›› ሲልም አሳስቦ ነበር፡፡
ይሁንና ይህና ሌሎች ምክረ ሀሳቦች በመንግስት በኩል ቅሬታን ፈጥረዋል፤ የሀሳብ ልዩነቶች ተንፀባርቀዋል፤ አለፍ ሲልም አለመግባባቶች አይለዋል የሚሉ አስተያየቶች ሲነገሩ ይሰማል፡፡ አሐዱም ይህ ልዩነት ከምን ደረሠ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ጠይቋል፡፡

ኮሚሽነሩ ዶክተር ዳኒኤል በቀለ ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከሉት ጭምብል ሳያደርጉ መንቀሳቀስ፣ ርቀትን ሳይጠብቁ መጓዝና አካላዊ ርቀትን አለመጠበቅ ዜጎች ሆን ብለው ሳይሆን በተለያዩ ምክንያቶች ሳይተገብሯቸው ሊቀሩ ይችላሉ፡፡ታዲያ በዚህ ጊዜ እነዚህ ሰዎች ደንቦቹን በማይተገበሩት ወቅት ግንዛቤ ማስጨበጥ እንጂ በወንጀል ህግ ማስተዳደር ተገቢ አይደለም ይላሉ፡፡እነዚህና ሌሎች ሊሻሻሉ ይገባል የተባሉት አፈፃፀሞች ዙሪያ በተያዘው ሳምንትም ውይይት ተካሂዶ እልባት ለማግኘት እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ስለመሆኑ ታውቋል፡፡

ምንጭ:አሐዱ ሬዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from Kídus
🔥 15 % 🔥በመቶ ቅናሽ
📞 በ 0941158969 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን

የተለያዩ የአውሮፓ ብራንድ ⌚️ሰዓቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ከኩባንያችን (ሺባ) ይግዙ ይህንን ቅናሽ እንዳያመልጥዎት::

⭕️የ 1 ወር ዋስትና እንሰጣለን⭕️

📲Multiple Items
- https://tttttt.me/Shebasluxury
📲Watches
- https://tttttt.me/Shebaswatches
📲Jewlery
- https://tttttt.me/Shebasjewlery

Contact Admin @ki_d_us

📞 በ 0941158969
📞 በ 0923320000 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን🏍
Forwarded from HEY Online Market
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች በዋስትና

🔸SAMSUNG #GALAXY A SERIES 
•A10S 2019 /32 GB/ 7,500ብር
•A20S 2019 /32 GB/ 8,500ብር
•A30S 2019 /64 GB/ 11,300 ብር
•A30S 2019 /128 GB/ 11,900 ብር
•A50S 2019 /128 GB/ 4GB 14,500
•A50S 2019 /128 GB/ 6GB 15,000
•A31 2020 /128 GB/ 4GB 14,200
•A51 2020 /128 GB/ 6GB 16,400
•A70 2019 /128 GB/ 6GB 16,200 ብር

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4
0910695100 @Roviii

@HEYOnlinemarket
Forwarded from YeneTube
🏡 Nat mobile & Computers
💻DELL Vostro 15
Core i5 7th Generation
✒️ 2.7ghz Amazing speed
🖥 Screen :15. 6 inch
📼 Storage : 1Tb
Ram : 4gb
🔋 Battery >3hrs

💵Price : 17,500birr

. 0911522626
0953120011

TxT :- @natyendex
🔶 ለበለጠ መረጃ
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAELbSrbiTDHFnicnnA

አድራሻ ቦሌ መድሀኒያለም ሞርኒንግ እስታር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ከAngla burger ፊትለፊት
👍1
የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የኮሮና ወረርሽኝ ስጋት ገና አላበቃም ሲሉ አስጠነቀቁ።

ሜርክል ዛሬ ወረርሽኙን ለመከላከል የተወሰዱ እርምጃዎችን ማላላት ከጀመሩ የምሥራቅ ጀርመን ግዛቶች መሪዎች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በሰጡት መግለጫ የኮሮና ተህዋሲ እልጠፋም ጀርመንም የተሻለ መቆጣጠሪያ ቢኖራትም ተህዋሲው ግን አሁንም አለ ሲሉ ተናግረዋል።

አሁንም የወረርሽኙ መነሻ ላይ ነን ያሉት ሜርክል በሽታው እንዴት በፍጥነት እንደሚሰራጭ ስለምናይ በጣም መጠንቀቅ አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

በጀርመን በኮሮና ተህዋሲ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሲቀንስ መንግሥት ጥብቅ የመከላከያ እርምጃዎች በመጠኑ አላልቷል።

አሁን የተደነገጉት ደንቦች እስከ መቼ እንደሚቀጥሉ የሃገሪቱ የተለያዩ ግዛቶች ፖለቲከኞች መስማማት አልቻሉም።ሜርክል አሁን ሃላፊነቱ በይበልጥ በግዛቶቹ ጫንቃ ላይ ይሆናል ብለዋል።

Via:- Dw
@Yenetube @fikerassefa
"የጎንደር ኅብረት ለኢትዮጵያ አንድነት" በአሜሪካን ከሚኖሩ በጎ ፍቃደኞች በተሰበሰበ ገንዘብ የተገዛ እህል ዛሬ በምዕራብ ጎንደር ዞን ለሚገኙ የአስገድዶ ለይቶ ማቆያዎች ለገሰ።
@Yenetube @Fikerassefa
አንዳንድ የትምህርት ተቋማት ከሁለተኛ ዲግሪ በላይ ያሉትን ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ መጀመራቸው ተገለፀ

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሁለተኛና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ መጀመራቸው ተጠቆመ፡፡ የመጨረሻ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ደግሞ ከየትምህርት ተቋሞቻቸው የሚላኩላቸውን የትምህርት ሰነዶች እያነበቡ እንደሚቆዩ ተገልጿል፡፡

በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ኤባ ሚጀና በኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ ምክንያት በዚህ ወቅት ይካሄድ ስለነበረው የከፍተኛ ተማሪዎች የምረቃ መርሃ ግብር ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት፣ በኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ ምክንያት የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርቱን እንዲከታተሉና ከአማካሪዎቻቸው ጋርም የሚገናኙበት ምቹ ሁኔታ በመኖሩ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ባይኖርም አንዳንድ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ እንደ ጀመሩ አመልክተው፣ በዚህም ጅማና ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ይጠቀሳሉ ብለዋል፡፡ ትምህርታቸውን ያልጨረሱ ተማሪዎችም እንደሚኖሩ ጠቁመዋል፡፡

ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ለመጨረስ የቻሉት በተመቻቸው የቴክኖሎጂ የማስተማሪያ ዘዴ በአግባቡ መጠቀም በመቻላቸው፣ እንዲሁም በተማሪውና በአማካሪዎቻቸው ጥንካሬ እንደሆነ የጠቆሙት ዶክተር ኤባ፣ የትምህርት ተቋማቱም በየጊዜው አስፈላጊውን ክትትልና ግምገማ በማድረግ ውጤታማ መሆኑ መቻላቸውን አመልክተዋል፡፡

የመጨረሻ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን በተመለከተም ዶክተር ኤባ እንዳብራሩት፣ በወረርሽኙ ምክንያት ባለመማራቸው፣ አንዳንዶችም የመጀመሪያ መንፈቅ (ሴሚስተር) ፈተና ለመውሰድ ዝግጅት ላይ እያሉ ወረርሽኙ በመከሰቱ ምክንያት ባለመፈተናቸው በዚህ ክረምት ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች አይኖሩም፡፡

እነርሱን በተመለከተ መደረግ ስላበት ነገር በየሳምንቱ ከየትምህርት ተቋማቱ የትምህርት አመራሮች ጋር ግምገማ እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተው፣ ወረርሽኙ ቢገታ ወይም ቢቆም መደረግ ስላለበት ሁኔታ ከወዲሁ ዝርዝር ዕቅድ ያዘጋጁ የትምህርት ተቋማት መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡

ዝርዝር ዕቅዱ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ምን ላይ እንዳቆሙ እና ካቆሙበት በመቀጠል ደግሞ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ በመሸፈን ትምህርታቸውን ማጠናቀቅ እንደሚችሉ የሚያሳይ እንደሆነም አስረድተዋል።

Via:- EPA
@Yenetube @Fikerassefa
የ2012 የውድድር ዓመት የአማራ ሊግ መቋረጡን የክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
@Yenetube @Fikerassefa