አምስት የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባላት ታስረዋል ተባለ!
የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን ካነሳባቸው የምክር ቤቱ አባላት ውስጥ አምስቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቤተሰቦቻቸው እና ባልደረቦቻቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። አምስቱ የምክር ቤት አባላት ላለፉት አራት ቀናት ጅግጅጋ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በእስር ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa

በመላው ዓለም በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ5 ነጥብ 5 ሚሊዬን አሻቅቧል
በዛሬው ዕለት ብቻ 50 ሺ 237 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል
@Yenetube @Fikerassefa
በዛሬው ዕለት ብቻ 50 ሺ 237 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል
@Yenetube @Fikerassefa
ትምህርት ቤቶች ባልተዘጉባት ስዊድን በኮሮና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ4 ሺ አለፈ
በስዊድን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 4 ሺ 29 መድረሱን የሃገሪቱ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቃል አቀባይ ለሲኤንኤን ተናግረዋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
በስዊድን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 4 ሺ 29 መድረሱን የሃገሪቱ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቃል አቀባይ ለሲኤንኤን ተናግረዋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
ከኮሮና ታማሚዎች 35 በመቶ ያህሉ ምልክቶችን አያሳዩም
የአሜሪካ በሽታዎች መከላከልና ቁጥጥር ማዕከል አዲስ መመሪያን አዘጋጅቷል፡፡
በመመሪያውም ከኮሮና ወረርሽኝ ሲሶ (አንድ ሶስተኛ) ያህሉ ምልክቶችን የማያሳይ እንደሆነ ግምቱን አስቀምጧል፡፡
Via:- Al alin
@Yenetube @Fikerassefa
የአሜሪካ በሽታዎች መከላከልና ቁጥጥር ማዕከል አዲስ መመሪያን አዘጋጅቷል፡፡
በመመሪያውም ከኮሮና ወረርሽኝ ሲሶ (አንድ ሶስተኛ) ያህሉ ምልክቶችን የማያሳይ እንደሆነ ግምቱን አስቀምጧል፡፡
Via:- Al alin
@Yenetube @Fikerassefa
በደቡብ ክልል 7 ሺ አሽከርካሪዎች ተቀጡ
ከኮሮናጋር ተያይዞ የወጡ ክልከላዎችን የተላለፉ 7 ሺ አሽከርካሪዎች መቀጣታቸውን የደቡብ ክልል ም/ር/መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው አስታወቁ፡፡ አሽከርካሪዎች በድምሩ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ተቀጥተዋል።
Via:- ኢዜአ/ Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
ከኮሮናጋር ተያይዞ የወጡ ክልከላዎችን የተላለፉ 7 ሺ አሽከርካሪዎች መቀጣታቸውን የደቡብ ክልል ም/ር/መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው አስታወቁ፡፡ አሽከርካሪዎች በድምሩ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ተቀጥተዋል።
Via:- ኢዜአ/ Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
ትግራይ ክልል
በፌደራል ደረጃ በወጣው መግለጫ ከትግራይ ክልል ሁለት (2) የኮቪድ-19 ታማሚዎች ማገገማቸው መገለፁ ይታወሳል።
ያገገሙት ሁለቱ (2) የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች በመቐለ ዩኒቨርስቲ ኹሓ ካምፓስ ለይቶ ማቆያ ህክምና ማእከል ህክምና ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው።
የተቀሩቱም የኮቪድ-19 ታማሚዎች አስፈላጊውን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኘ ተገልጿል። ወረርሽኙን ከፊት ለፊት እየተጋፈጡ ላሉት የጤና ባለሞያዎች ምስጋና ቀርቧል።
Via:- Professor Kindeya Gebrehiwot

በኒው ዚላንድ ሆስፒታል ያለው አንድ ታማሚ ብቻ ነው!
በኒው ዚላንድ ሆስፒታል የሚገኘው አንድ ታማሚ ብቻ እንደሆነና በበሽታው ተይዘው ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኘው 22 ሰዎች ብቻ መሆናቸው ተገለጸ።አምስት ሚሊዮን ነዋሪዎች ባሏት ኒው ዚላንድ በወረርሽኙ የተያዙት 1,500 ሰዎች ናቸው። 21 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።ባለፈው ወር በበሽታው የተያዘ ሰው አለመገኘቱ፤ የአገሪቱ አመራሮች የወረርሽኙን ሥርጭት መቆጣጠራቸውን እርግጠኛ እንዲሆኑ አስችሏል።ኒው ዚላንድ የእንቅስቃሴ ገደብ እያነሳች ነው። ምናልባትም ዳግመኛ ድንበሯችን ስትከፍት ፈተና ይጠብቃት ይሆናል።
Via BBC

ሳዑዲ የጣለችውን ሰዓት እላፊ ሰኔ 14 ልታነሳ ነው።
ሳዑዲ ዓረቢያ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ጥላ የነበረውን የሰዓት እላፊ ገደብ ሰኔ 14 ከመካ ውጪ በሁሉም የአገሪቱ ክፍል እንደምታነሳ አስታወቀች።
@Yenetube @Fikerassefa
ሳዑዲ ዓረቢያ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ጥላ የነበረውን የሰዓት እላፊ ገደብ ሰኔ 14 ከመካ ውጪ በሁሉም የአገሪቱ ክፍል እንደምታነሳ አስታወቀች።
@Yenetube @Fikerassefa
ለመጀመሪያ ጊዜ በሰዎች ላይ የሚደረገው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ዛሬ በአውስትራሊያ ሜልቦርን ከተማ ተጀምሯል፡፡
NVX-CoV2373 የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ክትባት የተመረተው በአሜሪካ ኩባንያ ኖቫቫክስ ነው ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሙከራ የሚደረግባቸው 130 ጤናማ ጎልማሶች ላይ ሲሆን ውጤቱ ሀምሌ ላይ እንደሚታወቅ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡በመላው ዓለም የሚገኙ ተመራማሪዎች ከ100 በላይ ኮሮና ቫይረስን መከላከል የሚያስችሉ ክትባቶች ለማግኘት ጥረት ላይ ናቸው። ከወር በፊት በእንግሊዝ በሰዎች ላይ የሚደረገው የክትባት ሙከራ መጀመሩ አይዘነጋም፡፡በአውሮፓ የመጀመሪያ የሆነውን ሙከራ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ያስጀመሩት ሲሆን የክትባቱ ውጤታማነት የሚታወቀው ከወራት በኋላ ነው ተብሎ ነበር።
Via Ethio FM

በኢትዮጵያ የፀረ ኤች አይ ቪ (ኤድስ) መድኃኒት የሚወስዱ ሰዎች ቁጥር በግማሽ መቀነሱን የፌዴራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
የጽሕፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ጽጌረዳ ክፍሌ (ዶክተር) የፀረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት ተጠቃሚዎችን በተመለከተ የመጣላቸው መረጃ በጣም አስደንጋጭ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እንደ ዋና ዳይሬክተሯ ገለጻ መድኃኒቱን ከሚወስዱት ውስጥ ከ50 በመቶ በታች ናቸው እየወሰዱ ያሉት፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የመድኃኒት ተጠቃሚዎች ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በመፍራት ከጤና ተቋማት በመራቃቸው እንደሆነ ነው ዋና ዳይሬክተሯ ያስረዱት፡፡
ምንጭ:አብመድ

ሶማሌላንድ በዛሬ ሪፖርቷ 2 ሞትና 14 በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ማግኘቷን አሳውቃለች። በሀገሪቱ እስካሁን 217 ሰዎች የተያዙ ሲሆን 17 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ለሕዝብ ቆጠራ የተገዙ ታብሌቶች ለፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ሊከፋፈሉ ነው!
በአገር ዐቀፍ ደረጃ ለሦስተኛ ጊዜ ለማካሄድ ታቅዶ የነበረውን የቤትና ሕዝብ ቆጠራ በቴክኖሎጂ ለማገዝ በሚል በመንግሥት ተገዝተው የነበሩ 180 ሺሕ ታብሌቶች ያለሥራ ከመቀመጣቸው ጋር ተያይዞ ወደ ፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ሊከፋፈሉ መሆኑ ተገለፀ።የሚኒስትሮች ምክር ቤት በወሰነው ውሳኔ መሠረት በከፍተኛ ወጪ ተገዝተው በማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ውስጥ የሚገኙት ታብሌቶች ሕዝብ ቆጠራው ከመራዘሙ ጋር እንዲሁም ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ወደ ፌደራል መሥሪያ ቤቶች እንዲከፋፈሉ ከገንዘብ ሚንስትር ዲኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ደብዳቤ መጻፉን ምንጮች ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።
Via Addis Maleda

በአዲስ አበባ ቦሌ አትላስ አካባቢ በአንድ መኖሪያ ቤት በጦር መሳሪያ እና በኤሌክትሪክ ሾክ የታገዘ ዝርፊያ መፈሙን ነዋሪዎች ተናገሩ።
በአዲስ አበባ ከኡራኤል ቦሌ አትላስ መስመር አካባቢ በተለምዶ ይልማ ስጋ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ማለትም ሰኞ ለማክሰኞ ሌሊት ላይ የተደራጁ ዘራፊዎች በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ዝርፊያ መፈጸማቸው ተገልጿል።
ዝርፊያው የተፈጸመበት ግለሰብ አቶ ረብራ ተሸመ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳለው ዘራፊዎቹ በጦር መሳሪያ እና የኤሌክትሪክ ሾክ በመጠቀም 2 ላፕ ቶፕ 2 አይፎን ስልኮች 10 ሺህ 800 ብር በጥሬ ገንዘብ እና የተለያዩ የቤት ንብረቶች ዘርፈው ተሰውረዋል።አቶ ረብራ እንዳሉን በኤሌክትሪክ ሾኩ በተፈመበት ጥቃትም ለሰዓታት ያህል እራሱን ስቶ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ከኤልክትሪክ ሾክ በተጨማሪም በገጀራ አንገቱ አካባቢ ጉዳት እንዳደረሱበትም ተናግሯል፡፡
ዘራፊዎቹ የዘረፉትን ንብረት በያዙት መኪና በመጫን ከአካባው እንደተሰወሩ የተናገሩት አቶ ረብራ የአካባቢው ሰው ሲከተላቸው ተኩስ መክፈታቸውንም ተናግሯል፡፡አቶ ረብራ ዝርፊያውን አስመልክቶ በአካባቢው ለሚገኘው ካራማራ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ማመልከቱንም ተናግሯል። ጉዳዩን ለማጣራትም ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተደጋጋሚ ሙከራ ባደደርግም አልተሳካልኝም ብሏል ኢትዮ ኤፍ ኤም በዘገባው።

በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ወረዳ ተፈናቅለው የነበሩ 650 አባወራዎች በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ የምግብና ሌሎች አስፈላጊ እርዳታ ተደርጎላቸው ወደነበሩበት መመለሳቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በአፍሪካ በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 መቶ ሺህ አለፈ!
በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከ1 መቶ 12 ሺሕ በላይ መድረሱን ሲዲሲ አፍሪካ አስታውቋል።የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ተቋም ዛሬ እንዳስታወቀው ባለፉት አራት ቀናት ብቻ 19 ሺሕ 942 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን፤ 8 ሺሕ 803 የሚሆኑት ደግሞ አገግመዋል።447 የሚሆኑት ደግሞ በአራት ቀናት ውስጥ በቫይረሱ ሕይወታቸውን አጥተዋል።በአጠቃላይ በአፍሪካ 112 ሺሕ 290 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ 44 ሺሕ 920 ሰዎች አገግመው 3 ሺሕ 359 ህይወታቸውን አጥተዋል።ተቋሙ እንዳመለከተው፤ 14 ሀገራት በሚገኙበት ምሰራቅ አፍሪካ ባለፉት 4 ቀናት 2 ሺሕ 594 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 58 ሰዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል ሌሎች 325ቱ ደግሞ አገግመዋል።በቫይረሱ ከተጠቁ 14 ሀገራት በሚገኙበት በዚሁ የአህጉሪቱ ክፍል በአጠቀላይ 12 ሺሕ 291 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፣ 332 ሞተዋል፤ 3 ሺሕ 295 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።
Via ENA

ኢትዮጵያ ከኳታር 9 ቶን የሕክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አገኘች!
ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ የሚያስችል 9 ቶን የሕክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ ከኳታር መንግሥት አግኝታለች።የኳታር መንግሥት ድጋፉን ያደረገው በአገሪቱ የልማት ፈንድ በኩል መሆኑን ከኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ የሚያስችል 9 ቶን የሕክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ ከኳታር መንግሥት አግኝታለች።የኳታር መንግሥት ድጋፉን ያደረገው በአገሪቱ የልማት ፈንድ በኩል መሆኑን ከኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
የትምህርት ሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ትምህርት ቤቶች በተዘጉበት ባለፉት ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ በአንድ ክልል ብቻ 585 አስገድዶ/ያለዕድሜ ጋብቻና እንደተፈፀመና 1070 ሊደረጉ የነበሩ ጋብቻዎች መታገዳቸውን ጠቅሰው ትምህርት ቤቶች መልሰው በሚከፈቱበት ጊዜ በርካታ ሴቶች ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ላይመለሱ እንደሚችሉ ያላቸውን ስጋት ገልፀው ይህ እንዳይፈጠር የሁሉንም አካል ትብብር ጠይቀዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ትናንት የኮሮና ቫይረስ አለባቸው ተብለው ሪፖርት ከተደረጉ ሰዎች መካከል ከአንደኛው ጋር ንክኪ አለን ያሉ 40 ያህል ሰዎች በጳውሎስ ሆስፒታል ደጃፍ ተሰልፈው መርምሩን እያሉ ነው።
ሰዎቹ የኢድ አልፈጥር ምሽት ከልጁ ጋር አብሮ ያመሹ ባለፉት ቀናትም የቅርብ ንኪክ ያላቸው መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የጳውሎስ ሆስፒታል በበኩሉ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ የሚታከሙትንና አስታማሚዎቸን በኮሮና ቫይረስ ስጠረጥራቸው ምርመራ አደርጋለው ከዛ ባሻገር ግን ራሱን ራሱን የጠረጠረን ሁሉ ለመርመር ሀላፊነት አልተሰጠኝም ብሏል፡፡
Via Sheger FM

የሚኒስትሪ ፈተና አሰጣጥን በሚመለከት ውሳኔ ላይ አልተደረሰም!
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዳኜ ገብሩ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት፣ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን የስምንተኛ ክፍልን ክልላዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች 12 ሺሕ ቢሆኑም ፈተና አሰጣጡ እንዴት እና መቼ ይሰጥ የሚለው ጉዳይ ላይ ግን ውሳኔ ላይ መድረስ አልተቻለም። እንደ ዳኜ ገለጻ ከሆነ፣ የ12ኛ ክፍልም ይሁን የስምንተኛ ክፍል ፈተና እንዴት እና በምን መንገድ ይሁን የሚለውን ከፌዴራል ባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረግ ንግግር የሚወሰን ይሆናል። እስከ አሁን ግን ምንም የተገለጸ ነገር የለም ሲሉ ምክትል ቢሮ ኃላፊው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።