YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ የኮሮና ስርጭት የገነነበት አንድ መንደር ሙሉ በሙሉ ከቤት መውጣት ተከለከለ!

በአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ተጨናንቆ ከሚኖርባቸው አካባቢዎች በአንዱ ፣ አብነት አካካቢ፣ የኮሮና ስርጭትን ለመግታት ሲባል ሙሉ በሙሉ አንድ መንደር ውሽባ እንዲገባ ተደርጎ ነዋሪዎች ከቤት እንዳይወጡ መከልከሉን ዋዜማ ራዲዮ ተመልክቻለው ብላለች።በልደታ ክፍለከተማ አብነት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወረዳ 3 ነዋሪ የሆኑ አንድ ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበራቸው 32 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ግለሰቡ በተጎዳኝ ህመሞች ለረጅም ጊዜ የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ቆይተው ህይወታቸው አልፎል፡፡ ቀድሞ የተወሰደው ናሙና ሟቹ ግለሰብ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በማሳየቱ ከሳቸው ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ላይ ምርመራና ክትትል ተደርጎ 32 ስዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከባለሙያዎች ስምተናል።

ይህንን ተከትሎም በወረዳው (አብነት አካካቢ) 500 አባወራ የሚገኝበት መንደር ከእንቅስቃሴ ታግዶ ተዘግቶል፡፡ ወደ መንደሩ በሚያስገባው ቅያስ ላይ ፖሊሶች እና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ቆመው ከነዋሪው ሌላ ሰው እንዳያልፍ ሲከለክሉ ተመልክተናል፡፡ለነዋሪው የአስቤዛ ፤የፅህና መጠበቂያ ሳሙና ፤ሳኒታይዘር እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡ አቅርቦቱ ከዚህ በፊት ለወረርሽኙ ተብለው ከተለያዩ አካላት ከተሰበሰበው እየተሸፈነ እንደሚገኝ ታውቋል ። በተለይም የአሊባባ ድጋፍ በእጅጉ እንዳገዘ የወረዳው አመራሮች ገልፀዋል፡፡

የስራቸው ሁኔታ ግድ ከቤት የሚያስወጣ ለሆነባቸው ነዋሪውች ለሚሰሩበት ተቋም የትብብር ደብዳቤ እየተፃፈ ነው፡፡በዚህ መንደር የሚኖሩት ነዋሪዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ እዛው ባሉበት ተወሽበው በመቆየት የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ የታለመ ነው፡፡ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል ግንዛቤ ለማስጨበጥ በተቋቋመው አደረጃጀት ውስጥ ያሉ በጎ ፍቃደኞችም የችግሩ ሰለባ ናቸው።በዚያው ክፍለከተማ አምስተኛ ተብሎ በሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ በእስረኞች እና ጉዳይ በሚያስፈፅሙ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ንክኪ በአንድ የቫይረሱ ታማሚ ምክንያት 66 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እና ልደታ ክፍለከተማ ጤና ሚኒስቴር ፣ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ለዚህ ሲባል የተቋቋመው ግብረሃይል ከዚህ የበለጠ እንዳይሰራጭ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ በርካታ ሰዎች በሚኖሩበት በልደታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሁሉም ህንፃዎች ላይ ምርመራ ተደርጎል፡፡ ምርመራውን ሲሸሹ የነበሩ ሰዎችንም ተመልክተናል፡፡እስከቅዳሜ ግንቦት 15 ድረስ ባለው መረጃ በልደታ ክፍለ ከተማ 104 ሰው በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ደግሞ 28 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ይህም ከሌሎቹ ክፍለ ከተሞች ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ነው፡፡ በጉለሌ ክፍለ ከተማ 11 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

ምንጭ:ዋዜማ ራዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
ለኢቢሲ ሠራተኞች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደረገ!

በዛሬው ዕለት 50 ለሚሆኑ ለቫይረሱ ተጋላጭ ናቸው ተብለው ለተለዩ የኢቢሲ ጋዜጠኞች፣ የካሜራ ባለሞያዎች፣ የጥበቃ ሠራተኞች እና ሹፌሮች የኮሮና ምርመራ ለማድረግ ናሙና ተወስዷል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በኮቪድ-19 የተያዘች አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት ልጇን በሰላም ተገላገለች! በኮቪድ-19 ተይዛ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሕክምና ላይ የምትገኝ አንዲት ኢትዮጵያዊት ነብሰ ጡር እናት በሰላም መገላገሏን ሆስፒታሉ አስታወቀ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም በሆስፒታሉ ዛሬ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለእመጫቷ ስጦታ አበርክተዋል። የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው እንደገለጹት በሆስፒታሉ ሕክምና…
በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከኮቪድ-19 ታማሚ እናት የተወለደው ሕፃን ከኮሮናቫይረስ ነፃ ሆኗል።

በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የለይቶ ሕክምና ማእከል ውስጥ ክትትል እየተደረገላት ከምትገኝ የ34 ዓመት እናት ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም የተወለደው ሕፃን 3.1 ኪ.ግ. ክብደት ያለው ወንድ ልጅ መሆኑም ታውቋል።ከሕፃኑ በተወሰደው ናሙና ላይ በተካሔደው የላብራቶሪ ምርመራ የኮሮናቫይረስ እንደሌለበት ማረጋገጥ ተችሏል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው ግጭት ተፈናቅለው የነበሩ 4,541 ዜግች ዛሬ ወደ ነበሩበት የመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ተመልሰዋል።

Via ELU
@YeneTube @FikkerAssefa
ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ እና የአሜሪካ አገራት አምባሳደሮች በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ገለፃ ተደረገ!

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ እና አሜሪካ አገራት አምባሳደሮች ስለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዛሬ ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓም በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ገለጻ አድርጓል።

Via Spokesperson of MoFA
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 73 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው!


ባለፉት 24 ሰዓታት ለ2 ሺህ 844 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 73 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ወደ 655 አሻቅቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 73 ሰዎች 67 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የተቀሩት የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ናቸው ወንድ(49) ሴት(24) ናቸው

➡️ዕድሜያቸው ከ6-75 የሆኑ

➡️27ቱ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው

➡️15ቱ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው

➡️31ዱ የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው

➡️ተጨማሪ 7 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 159 ደርሷል

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(56)፣ ከትግራይ ክልል ሁሉም የጉዞ ታሪክ ያላቸው (4)፣ ከሶማሌ ክልል የውጭ ጉዞ ታሪክ ያላቸው(8)፣ ከአማራ ክልል (2)፣ ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች (3) በኮሮና የተያዙ በድምር 73 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 655 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በአንድ ሳምንት ውስጥ 303 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን ባለፉት ሶስት ቀናት ደግሞ 222 ሰዎች ተይዘዋል። ከነዚህ ውስጥ 177 ሰዎች የተገኙት ከአዲስ አበባ ነው። በሀገሪቱ ጠቅላላ 159 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን 1 ሰው የፅኑ ህክምና ክፍል መግባቱ ታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከዛሬ ጀምሮ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በሁሉም ካምፓሶች ግቢ የፊት ጭንብል (ማስክ) ሳያደርግ ማንኛውም ሰው ወደ ግቢ መግባት እንደማይችል ዩንቨርስቲው አሳውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል መንግስት በተለያዩ ሚድያዎች የሀሰት ዜና እየተነገረብኝ ነው በሚል መግለጫ አውጥቷል!

በተለይም ትናንት ግንቦት 16/2012 ዓ/ም፣ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል፣ በብልፅግና ፓርቲ ፌስቡክ ፔጅ፣ በኣዲስ ኣበባ ብልፅግና ፓርቲ ፌስቡክ ፔጅ፣ በኣማራ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ከግል ሚዲያዎች፣ ማለትም በኢሳት፣ በኣባይ ሚዲያ፣ በዘሀበሻ ወዘተ የሚባሉ እንዲሁም መረጃ ዶት ኮም እና ኣዲስ ፋክት በተባሉ ማህበራዊ የሚዲያ ኣውታሮች በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተቃውሞ ሰልፎች ተደርገዋል፣ የፀጥታ መደፍረስ ተከስቷል በሚል ያሰራጩት ዘገባ ሀሰት ነው ብሏል፡፡

-የትግራይ ክልል መ/ኮ/ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ከ23 ሚሊየን ቶን በላይ የግራናይት ክምችት ተገኘ

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ሦስት ወረዳዎች ከ23 ሚሊየን ቶን በላይ የግራናይት ክምችት መገኘቱን የአማራ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ አስታወቀ። የግራናይት ክምችቱ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሚገኙት ባሶ ሊበን፣ ጎዛምን እና ደብረ ኤልያስ ወረዳዎች እንዳለ ተረጋግጧል ነው የተባለው።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በህገ-ወጥ መንገድ በአንድ ግለሰብ ተይዞ የነበረ 460 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ለአርሶ አደሮች ተላለፈ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ በአንድ ግለሰብ ተይዞ የነበረ 460 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ለአርሶ አደሮች ተላለፈ።ከ160 በላይ ለሚሆኑ ነባር አርሶ አደሮች የተላለፈው መሬት የከተማ ግብርና ልማት እንዲያካሂዱበት እንደሆነ ተገልጿል።በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት፤ መሬቱ በህገ-ወጥ መንገድ ተይዞ ነበር።

Via ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ May 25/ግንቦት 17 የአፍሪካ ቀን እየተከበረ ይገኛል። የአፍሪካ ህብረት በይፋ የተመሰረተው ከ57 አመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
በደሴ ከተማ አስተዳደር በኮሮናቫይረስ የተያዘ ግለሰብ መገኘቱን ተከትሎ ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ 30 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸው ታውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ ለአብመድ እንዳሳወቀው የጅቡቲ የጉዞ ታሪክ ያለው ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ የናሙና ምርመራ ተደርጎለት ግንቦት 15/2012 ዓ.ም የኮሮናቫይረስ እንዳለበት ተረጋግጧል፡፡አሽከርካሪው ወደ አማራ ክልል ከገባ በኋላ መጋቢት 10/2012 ዓ.ም ጋሼና ከተማ ጭነት አራግፎ፣ ወልድያ አድሮ በማግስቱ ወደ ደሴ ከተማ ከተማ አስተዳደር መሄዱ ታውቋል፡፡ወደ ከተማ አስተዳደሩ በገባ በማግስቱ የጤና ባለሙያዎች ጥቆማ ደርሷቸው ወደ ቤቱ ቢሄዱም ስላላገኙት ለሁለት ቀናት ሲንቀሳቀስ መቆየቱን የመምሪያው ኃላፊ አብዱል ሀሚድ ተናግረዋል፡፡ ግንቦት 11/9/2012 ዓ.ም ወደ ከተማው የገባው ግለሰቡ በ13/2012 ማለዳ በግል ሆስፒታል ለህክምና በሄደበት ተገኝቶ ነበር ወደ ለይቶ ማቆያ የገባው፡፡

በዕለቱም አሽከርካሪውን ጨምሮ ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ አምስት የሆስፒታሉ ሰራተኞች ወደ ለይቶ ማቆያ ገብተዋል።ከግለሰቡ ጋር ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ 30 ሰዎችም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በለይቶ ማቆያ መግባታቸውን መምሪያ ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡ ግለሰቡም ከመምሪያው ቁጥጥር ውጪ ባሳለፋቸው ሁለት ቀናት በመኖሪያ ቤቱ አቅራቢያ፣ በሱቅ አካባቢ እና በጎረቤት የነበረውን ንክኪ ጠቁሟል፤ በታክሲ መንቀሳቀሱንም ተናግሯል ነው ያሉት፡፡እንደ ኃላፊው ማብራሪያ ግለሰቡ ከሰጠው መረጃ በተጨማሪም በቅርብ የሚያውቁት ሰዎችም ጥቆማ ሰጥተዋል፤ እራሳቸውን ያጋለጡም አሉ፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በናይሮቢ የኢትዮየጵያ ኤምባሲ በሞያሌ በኩል ድንበር በማቋረጥ ያለበቂ የጉዞ ሰነድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ ኬንያ ከገቡ በኋላ በተለያዩ የኬንያ አካባቢዎች በሀገሪቱ የፀጥታ አካላት አማካኝነት በህግ ጥላ ስር የነበሩ ዜጎችን ከኬንያ ኢሚግሬሽን እና የፖሊስ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም 48 ዜጎችን ለሀገራቸው አብቅቻለው ብሏል። እነዚህ ዜጎች ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በኢትዮጵያ በሞያሌ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ከቆዩ በኋላ ወደየአካባቢያቸው የሚሸኙ ይሆናል።

Via FDRE Embassy, Kenya
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮና ቫይረስ መከሰት ተቋርጦ የቆየውን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ገለፀ።

ኤጀንሲው በቴክኖሎጂ የታገዘ የቤት ውስጥ ስልጠና ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል።በየትምህርት ክፍሉ የመማሪያ ጽሁፎች መዘጋጀታቸውንና በአገሪቷ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛዎች ተደራሽ በማድረግ ለማሰልጠን እየተሰራ መሆኑን የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አበራ አባተ ተናግረዋል።ተቋማቱ የሰልጣኞችን ዝርዝር በመያዝ ጽሁፎቹ እንዲደርሷቸው የማድረጉን ስራ እየሰሩ እንደሆነም ገልጸዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የመንግሥት ጸጥታ ሃይሎች 5 ሰዎችን እንደገደሉ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ ካለፈው ሳምንት ወዲህ እየተወሰደ ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ሰዎቹ የተገደሉት በላሎ አሳቢ ወረዳ ጃርሶ ዳሞታ፣ ዋንጆ እና ኬላይ በተባሉ ቦታዎች ነው፡፡ የዞኑ አስተዳደር ግን ሕግ እና ጸጥታን በማስከበሩ ርምጃ ሰላማዊ ሰዎች አልተጎዱም ሲል አስተባብሏል፡፡

Via Addis Standard/Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፈው የተገኙ 641 ሰዎ ች በገንዘብና በእስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ፡፡ ኮሚሽኑ በአንድ ቀን ምሽት ባደረገው ቁጥጥር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉ1887 ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ መጀመሩን እና ቁጥጥሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፆል ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ደብረ ብርሀን ከተማ ሲኖ ትራክ የተባለው ቻይና ሰራሽ መኪና በጫነው እንጨት ላይ ተደርበው ሲጓዙ የነበሩ ሶስት ሰዎች ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ ሲነኩ ኤሌክትሪክ ይዟቸው የአንዱ ሕይወት ወዲያው ያለፈ ሲሆን ከተረፉት መሃል አንዱ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa